ch
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

前往频道在 Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览

频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 331 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 756,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 541

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 331 名订阅者。

根据 16 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 90,过去 24 小时变化为 8,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 40.85%。内容发布后 24 小时内通常能获得 15.40% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 439 次浏览,首日通常累积 2 050 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 17

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

凭借高频更新(最新数据采集于 17 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。

13 323
订阅者
+824 小时
+217
+9030
帖子存档
የጋምቤላ - አቦቦ - ጎግ - ዲማ፣ ኮንትራት 2፡ ፑኝውዶ - ጎግ - ጊሎ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመልካም የግንባታ አፈጻጸም ላይ ይገኛል አዲስ አበባ ፣ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢ መ አ) በጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአኝዋሃ ዞን እየተገነባ የሚገኘዉ የጋምቤላ - አቦቦ - ጎግ - ዲማ ፣ ኮንትራት 2 ፑኝውዶ - ጎግ - ጊሎ ወንዝ ኪሎ ሜትር 72 የመንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት በመልካም የግንባታ አፈጻጸም ላይ ይገኛል፡፡ የመንገድ ግንባታዉ ከተጀመረ አራት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን አሁናዊ የግንባታ አፈጻጸሙ 90.1 በመቶ ላይ ደርሷል። በዚህም የግንባታዉ ዋና ዋና ስራዎች እየተገባደዱ ይገኛሉ፡፡ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ 876 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘዉ ፒኝውዶ ከተማ መነሻዉን በማድረግ ጊሎ ወንዝን ተሻግሮ ፍጻሚዉን ያገኛል፡፡ መንገዱን እየገነባ የሚገኘዉ የሥራ ተቋራጭ ቻይና ሬይል ዌይ ሰቨንዝ ግሩፕ ሲሆን የማማከር እና ቁጥጥር ስራው ደግሞ ኢንጅነር ዘውዴ እስክንድር ኮንሰልቲንግ እና እንስራድ ሲቪል ሲስተምስ ኢንጂነሪንግ በጣምራ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ መንገዱ የሚገነባበት መልከዓ-ምድራዊ አቀማመጥ 12.5 % ሜዳማ ሲሆን 87.5% ደግሞ ጠመዝማዛ ነው፡፡ የመንገዱ የጎን ስፋት የመንገድ ትከሻን ጨምሮ በገጠር 10 ሜትር ፤ በቀበሌ 12 ሚትር ፤ በወረዳ ከተማ ደግሞ 21.5 ሜትር ተጨማሪ ስፋት እንዲኖረዉ ተደርጎ ነዉ እየተገነባ የሚገኘዉ፡፡ የዚህ መንገድ ግንባታ 60 ሜትር ርዝማኔ ያለዉ የጊሎ ወንዝ ድልድልይ ስራ የሚያካትት ሲሆን ተጨማሪ 110 በላይ ጥቃቅን የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች ግንባታም የፕሮጀክቱ አካል ናቸዉ፡፡ የመንገዱ የቀድሞ ይዞታ ግማሹ ነባር የጠጠር መንገድ ሲሆን የተቀረዉ ምንም መንገድ ያልነበረበት አዲስ መስመር ነዉ፡፡ ባለፋት አመታት የአካባቢዉ ህብረተሰብ በመንገድ እጦት ምክንያት በርካታ እንግልት ሲያስተናግድ ቆይቷል። ይህ መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ አኝዋሃ ዞን ዉስጥ የሚገኙ ጎግ ወረዳን ጨምሮ በርካታ ከተሞችን እና ቀበሌዎችን በቅርብ ርቀት በማስተሳሰር በአካባቢው ይስተዋል የነበረውን የትራንስፖርት ችግር እንደሚቀርፍም ይታመናል። ከዚህም ባሻገር በመቶ ኪሎ ሜትሮች ተራርቀዉ ይገኙ የነበሩትን የዲማ ወረዳና የዞኑን ዋና ከተማ የሆነችው አቦቦ ከተማን ከክልሉ ዋና ከተማ ጋምቤላ ጋር እንዲሁም ከአጎራባች የጎግ ወረዳ ጋር በቅርበት ያገናኛል፡፡ በተጨማሪም አካባቢው ሰፊ የኢንቨስትመንት እና የማዕድን ሃብትን መገኛ በመሆኑ የመንገዱ መገንባት የሀገራችን የኢንቨስትመንትና ማዕድን ልማት ከማጠናከር አኳያ ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ አስፈላጊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የመሀልሜዳ - ግሼራቤል -መኮይ-ሚላሚሌ (ሎት 1፡ መሀልሜዳ - ጦርመሳያ) የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 61 ነጥብ 5 በመቶ ደረሰ አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢ መ አ) በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙትን የወረዳና የቀበሌ ከተሞችን የሚያስተሳስረው የመሀል ሜዳ - ግሼራቤል - መኮይ- ሚላሚሌ (ሎት 1፡ መሀልሜዳ - ጦርመሳያ) የመንገድ ፕሮጀክት 61.5 በመቶ ደርሷል፡፡ በፕሮጀክቱ የስራ እንቅስቃሴ ላይ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የውሀ ማፋሰሻ ቱቦና ፉካ ቀበራ ፣ የአራት ድልድይ ግንባታ እንዲሁም 18 ኪሎ ሜትር የሚሆን የአስፋልት ንጣፍ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ 65.5 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚሸፍነው ይኸው መንገድ በወረዳ 21 ሜትር ፣ በቀበሌ 12 ሜትር ፣ በገጠር 10 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ነው፡፡ በመንገዱ የግንባታ ሂደት ያጋጠሙ የወሰን ማስከበር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት ኢመአ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ይህም ፕሮጀክቱን በሚፈለገው ፍጥነት እንዲሄድ የሚያስችለው ይሆናል፡፡ ግንባታውን እያካሄደ ያለው ዦንግሚ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሊሚትድ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ ኢንፍራስትራክቸር ዴቨሎፕመንት ኮንሰልታንትስ (አይ.ዲ.ሲ.ኦ.ኤን) እያከናወነው ይገኛል፡፡ ለፕሮጀክቱ የሚውለው (1,781,238,954.95) አንድ ቢሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሠላሳ ስምንት ሺ ዘጠኝ መቶ አምሳ አራት ብር ከዘጠና አምስት ሣንቲም በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡ ከዚህ ቀደም መንገዱ በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ጠቀሜታ አንፃር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲገነባ ተደርጓል፡፡ የዚህ መንገድ መገንባት በመንገድ ኮሪደሩ ስር የሚገኙትን የወጀድ፣ ግራኝ፣ ዳርገኝ፣ ጦር መሳያ ከተሞችን ከመሀል ሜዳ ከተማ ጋር በቅርበት ከማገናኘት ጎን ለጎን የጓሳ ኮሚዩኒቲ ጥብቅ ፓርክን ተደራሽ ለማድረግ ብሎም በአካባቢው የሚመረቱ የተለያዩ የግብርና ምርቶች ለማውጣት የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

Are you following US on YouTube? https://www.youtube.com/@ethioroads?sub_confirmation=1
Anonymous voting

Are You Follow Us in YouTube ? https://www.youtube.com/@ethioroads?sub_confirmation=1
Anonymous voting

በአቦምሳ - አሰኮ - ዲቡ ወንዝ የመንገድ ፕሮጀክት አስፋልት ማንጠፍ ተጀመረ አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢመአ) 60 .91 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የኮንትራት አንድ አቦምሳ - አሰኮ - ዲቡ ወንዝ የመንገድ ፕሮጀክት ላይ የአስፋልት ንጣፍ ተጀምሯል፡፡ መነሻውን አቦምሳ ከተማ አድርጎ ዲቡ ወንዝ ላይ በሚያበቃው በዚህ የመንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ስራ ጎን ለጎን የአፈር ድልዳሎ፣ የምርጥ ጠጠር፣ የድልድይ ግንባታ ስራዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የግንባታ እንቅስቃሴ 36.43 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህንንም በማጠናከር በተቀመጠው እቅድ መሰረት ለማስኬድ በትኩረት እየተሰራ ነው። ፕሮጀክቱ በሚፈለገው ፍጥነት ለማስኬድ ብሎም በግንባታ ሂደቱ ላይ ያጋጠሙ የፀጥታና አለመረጋጋት እንዲሁም የካሳ ክፍያ ችግሮችን ለመፍታት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በኩል የቅርብ ድጋፍና ክትትል እየተደረገበት ይገኛል፡፡ የመንገድ ግንባታውን ሐቨሪም ኮንስትራክሽን ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ ከአለማየሁ ከተማ ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ ጋር በጣምራ እያከናወኑት ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱን የማማከር እና የቁጥጥር ስራ መታፈሪያ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ከኤልዳ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነር ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩት ነው፡፡ መንገዱ በወረዳ 19 በቀበሌ 16 ፣ በገጠር 10 ሜትር የመንገድ ትከሻን ጨምሮ አጠቃላይ የጎን ስፋት ያለው ነው ። ግንባታውን ለማከናወን የሚያስችለውን ሁለት ቢሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ አርባ ሶስት (2,260,899,043) ብር በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኗል። የአቦምሳ-አሰኮ-ዲቡ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በዋናነት በአርሲ ዞን ስር የሚገኙ በርካታ የወረዳ እና የቀበሌ ከተሞችን በቅርበት በማስተሳሰር የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመፍጠር የሚያስችል ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው በስፋትየሚገኙትን የጤፍ ፣ የስንዴ ፣ የገብስ ፣ የማሽላ ፣ የበቆሎ ፣ የሽንኩርት እና የጫት ምርቶች ወደ ገበያ አውጥቶ በመሸጥ ነዋሪዎች ከምርታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር ጠቀሜታው የላቀ ነው። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ ዘርፉ የሚገኝበትን ነባራዊ ሁኔታ፣ የዘርፉ ቁልፍ ፈተናዎች እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ከባለድርሻ አካላት ጋር በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ምርምር ማዕከል ምክክር ተካሂዷል። የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ዴኤታ አቶ የትምጌታ አሥራት፥ መንግስት ለዘርፉ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን አንስተው፥ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ፣ የጥራት ደረጃ እና የዋጋ መጠን አለመጠናቀቅ፣ የጸጥታ ስጋቶች፣ የአንዳድን የሥራ ተቋራጮች የአቅም ማነስ እና ጤናማ ያልኾነ ፉክክር፣ የቴክኖሎጂ እና የብቃት ክፍተት እንዲሁም የፍይናንስ እጥረቶች የዘርፉ ማነቆ መኾናቸውን ገልጸዋል። በመኾኑም የኢንዱስትሪውን ውስብስብ እና አንገብጋቢ ችግሮች ለመፍታት እና ውጤታማ ለማድረግ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የዘርፉ ተዋንያን የነቃ ተሳትፎ አስፈላጊ መኾኑን አጽንዖት ሰጥተውበታል። ከዚህ አንጻር የዛሬው መድረክ በቀጣይ ለሚኖሩ ዕርምጃዎች መደላድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሠራሮች እና የስነ ምግባር ጉድለቶችን በጋራ መታገል ይገባልም ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የግንባታ ጥሬ እቃ ዋጋ መናር፣ የአቅም ማነስ፣ ፍትሃዊ የኾነ የውድድር ከባቢ ማነስ፣ የጸጥታ ችግር እንዲሁም የገንዘብ እጥረት ፈተና እንደኾነባቸው አንስተዋል። ዘርፋን ከተደቀኑበት ችግሮች አላቅቆ ውጤታማ እንዲኾን በዋናነት አስቻይ የሥራ ከባቢዎችን መፍጠር፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ የፖሊስ ማሻሻያዎችን በየጊዜው መተግበር እና ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ እና ብቁ የሰው ኃይል አቅርቦት ሊኖር ይገባል ብለዋል። በቀጣይም የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት ከመንግስት እና ከሁሉም የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እና በትብብር እንደሚሠሩም ተሳታፊዎቹ አረጋግጠዋል። ሚንስቴር መ/ቤቱ ባሰናዳው በዚሁ መድረክ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪ መሀንዲሶች፣ የሙያ ማኅበራት እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ተሳትፈዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2017 (ኢ መ አ):- የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ምርምር ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል። የኮንስትራክሽን እመርታ ለሀገር ግንባታ በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው መድረኩ፥ የኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ (ደረጃ)፣ የዘርፉ ቁልፍ ፈተናዎች እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ትኩረቱን አድርጓል። የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ባሰናዳው በዚሁ መድረክ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪ መሀንዲሶች እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ይሳተፉበታል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads