ch
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

前往频道在 Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览

频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 361 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 755,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 537

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 361 名订阅者。

根据 18 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 91,过去 24 小时变化为 11,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 41.16%。内容发布后 24 小时内通常能获得 15.44% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 491 次浏览,首日通常累积 2 060 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 11

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

凭借高频更新(最新数据采集于 20 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。

13 351
订阅者
+1124 小时
+477
+9130
帖子存档
የኦሞ-ሳይ እና ሌፍት ካናል ብሪጅ (ሎት-1) መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል ጅንካ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኢመአ)፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በማጂ ወረዳ እየተገነባ ያለው የኦሞ-ሳይ እና ሌፍት ካናል ብሪጅ (ሎት-1) በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ መንገዱ 68 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው ወጪ ብር 1,882,967,504.80 ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው፡፡ ግንባታውን ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ የሥራ ተቋራጭ በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን የማማከሩን ሥራ ደግሞ ቤስት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እያከናወነ ይገኛል፡፡ ግንባታው የተጀመረው ታህሳስ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ሲሆን የፕሮጀክቱ አሁናዊ ገጽታ በኪ.ሜ. 14.54 እና በመቶኛ፡ 21.39 ነው፡፡ ከፕሮጀክቱ ጅማሮ እስካሁን የዲዛይን፣ የለውጥ መንገድ የጠረጋ፣ የአፈር ቆረጣ እና የአፈር ሙሌት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ መስመሩ ከዚህ በፊት ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ አውታር ያልተዘረጋበት ሲሆን መንገዱ ለአካባቢው ሕብረተሰብ ሆነ ለሀገራችን ያለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአስፓልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ይገኛል፡፡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በዋናነት ደቡብ ምዕራብ ኦሞ ዞን እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል (ማጂን ጨምሮ ሌሎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎችን) እንዲሁም ዋና መንገዶችን በማገናኘት ለአካባቢው ማህበረሰብ ብሎም ለሀገሪችን ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታን ያለው ነው፡፡ የፕሮጀክቱ መነሻ የኦሞ-ወንዝ የሚያቋርጥበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በስፋት የግብርና ምርቶች በተለይም በአካባቢው ለተገነቡ የስኳር ፋብሪካ ግብዓቶችን እንዲሁም የስኳር ምርቶችን በቤንች ማጂ በኩል ወደ ተለያዪ የአገራችን ከተሞች በተሻለ የጊዜ ፍጥነት ለማድረስ ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም የአሞ ብሔራዊ ፓርክ የቱሪዝም መዳረሻ የሚገኝበት አካካቢ ከመሆኑ አንፃር ለአካባቢው ብሎም ለሀገሪቷ ቱሪዝም ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

ከአምቦ እስከ ጉደር ከተማ የሚዘልቀው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል። የአምቦ-ጉደር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 19 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በመንግሥት በተመደበ 1,038,722,506.06 (አንድ ቢሊዮን ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስድስት ብር ከዜሮ ስድስት ሳንቲም) በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ነው። የአምቦ-ጉደር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመካሄድ ላይ የሚገኘው በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ነው። የመንገድ ግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር ረገድ ደግሞ ፕሮሚነንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ በአማካሪነት በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ መንገዱ 14 ሜትር ስፋት አንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፣ በሁለቱም አቅጣጫ 2.5 ሜትር የዕግረኛ መንገድ እና 2.5 ሜትር አካፋይ እንዲኖረው ተደርጎ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡ መንገዱ ከዚህ ቀደም በአስፋልት ደረጃ ተገንብቶ የነበረ ቢሆንም ፣ ነባሩ መንገድ እጅግ የተጎዳ በመሆኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከግምት ውስጥ ገብቶ በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የአፈር ቆረጣ ፣ የስትራክቸር ፣ የአስፋልት ንጣፍ ፣ የአራት ድልድዮች ግንባታ ፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ስራዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግንባታዎችን (የመንገድ ምልክቶችን መትከል ፣ መንገድ ቀለም መቀባት) ባካተተ መልኩ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡ ከፕሮጀክቱ ጅማሮ አንስቶ አስካሁን የድልድይ እና የፍሳሽ ውሃ ማስወገጃ ፣ አፈር ቆረጣ ፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ እንዲሁም አስፋልት የማንጠፍ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህም መሰረት የፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም 46 በመቶ ወይም 9 ኪሎ ሜትር ስራው ተጠናቋል፡፡ ግንባታው በመጪው 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይታመናል፡፡ የስራ ተቋራጩ በአሁኑ ወቅት ቀሪ የቁፋሮ ስራ ፣ የአስፋልት ንጣፍ ፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ንጣፍ ፣ የስትራክቸር ፣ የትራፊክ ምልክቶችን የመትከል እንዲሁም መንገዱን ቀለም የመቀባት ስራ ለማከናወን አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ አምቦ እና ጉደር ከተሞችን ከማገናኘት ባሻገር ሀገር አቋራጭ መንገድ በመሆኑ ለሀገሪቱ ትልቅ ፋይዳ ያስገኛል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው የተፈጥሮ ፍል ውሃ እና በፕሮጀክቱ አቅራቢያ የሚገኝ የወንጪ ሃይቅ የሚገኝ በመሆኑ ፤ የመንገዱ መገንባት ለቱሪስት መዳረሻነትም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

የአፍሪካ ልማት ባንክ ልኡካን ቡድን የአዳማ-አዋሽ የፍጥነት መንገድን ጎበኙ :: አዳማ ፣ ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓም (ኢመአ) ፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ልኡካን ቡድን እና የኢመአ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የአዳማ ኪሎ ሜትር 60 ( የአዳማ አዋሽ ) የፍጥነት መንገድን ጎበኙ ። የኢትዮ- ጅቡቲ ትራንስፖርት ኮሪደር አካል የሆነው የአዳማ አዋሽ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በሀገራችን ከሚገኙ ወሳኝና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው ጉልህ ከሆኑ መንገዶች አንዱ ነው ። መንገዱ ሦስት ክልሎችን ማለትም የኦሮሚያ ፣ የአፋርና የአማራ ክልሎችን ያስተሳስራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመንገዱ ጅማሮ ከአዲስ አበባ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ ከአዲስ አበባ - አዳማ ድረስ ያለውን የፍጥነት መንገድ የሚያያይዝና የሚያስቀጥል ነው ። 60 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የፍጥነት መንገድ ግንባታ የሚያከናውነው JMC Projects / India / Ltd. ከLongjiaw Road and Bridge co. Ltd. ጋር በጋራ በመሆን ነው ። የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ LASA ( Lea Associates South Asia PVT ከ UNICONW ( United Consulting Engineers PLC ) ጋር በጋራ በመሆን በማካሄድ ላይ ይገኛል ። በአሁኑ ወቅት 30.5 ኪሎ ሜትር የአፈር ጠረጋ ስራው ያለቀ ሲሆን ፣ 3.4 ኪሎ ሜትር የአፈር ሙሌትም ተጠናቋል ። እንዲሁም የካፒንግ ሌየር ፤ ሰብ ቤዝ ፣ ቤዝ ኮርስ ስራዎች ፣ የውሃ መፋሰሻ ቱቦዎች እንዲሁም ለተሽከርካሪ መተላለፊያ የሚውሉ ተገጣጣሚዎችን ( Precast Elements ) የማምረት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ። በእስካሁንም ከአጠቃላይ ስራው 9.73 በመቶ ተከናውኗል ። ለፍጥነት መንገዱ የሚውለው መዋለ ንዋይ በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን ፣ ስራውን በበላይነት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነው። የመንገዱ ግንባታ ወጪም ስድስት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሰማንያ ስምንት ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ አምስት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም (6,688,456,565.74 ) ነው :: የአፍሪካ ልማት ባንክ ልኡካን ቡድንና የኢመአ አመራር አካላት የአዳማ አዋሽን የፍጥነት መንገድ ከጎበኙ በኋላም በአዳማ ከተማ የግማሽ ቀን ውይይት አድርገዋል ። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚገናኘው የአሰብ ኮሪደር (ሜሎዶኒ መገንጠያ -ማንዳ-ቡሬ) የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ 71 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በመንግሥት በተመደበ 2,085,985,162.61 (ሁለት ቢሊዮን ሰማንያ አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከስልሳ አንድ ሳንቲም) በአስፋልት ኮንክሪት እና በሲሚንቶ ኮንክሪት ንጣፍ ደረጃ እየተገነባ ነው። ይህ መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በሀገራዊ እና ቀጠናዊ ትስስሩ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ የሚካሄድበት መልክኣ ምድራዊ አቀማመጥ ሜዳማ ፣ ዳገታማ እና ተራራማ ሲሆን ፤ ከአዲስ አበባ 787 ኪሜ ርቀት ላይ ከኤሊ ዳር ከተማ 16 ኪሜ በኃላ ጀምሮ ኢትዮ ኤርትራ ድንበር ላይ ያበቃል፡፡ የአሰብ ኮሪደር (ሜሎዶኒ መገንጠያ ማንዳ ቡሬ) የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመካሄድ ላይ የሚገኘው ሻንዶንግ ሉሽያዎ ግሩፕ ካምፓኒ ሊሚትድ በተባለ የውጭ ሀገር የሥራ ተቋራጭ ድርጅት ነው። የመንገድ ግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር ረገድ ደግሞ ስሜክ ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ሊሚትድ እና ቫልዩ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በንኡስ አማካሪነት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ መንገዱ ትከሻን ጨምሮ በገጠር፡- 10 ሜትር እና በቀበሌ ከተሞች ደግሞ 21.5 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በከፊል በጠጠር ደረጃ ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ይኸው መንገድ ፤ በአሁኑ ወቅት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከግምት ውስጥ ገብቶ በአስፋልት ኮንክሪት እና በሲሚንቶ ኮንክሪት ንጣፍ ደረጃ እየተገነባ ነው። ፕሮጀክቱ የአፈር ጠረጋ ፤ ቆረጣ እና ሙሌት ፤ ሰብቤዝ ፤ ቤዝ ኮርስ ፤ የአስፋልት ንጣፍ ፤ የሲሚንቶ ኮንክሪት ንጣፍ ፤ የአራት ድልድዮች ግንባታ ፤ እንደ ፓይፕ ፣ ስላብና ቦክስ ከልቨርቶች ያሉ የውሃ ማስተንፈሻ ስራዎችን እንዲሁም የመንገድ ምልክቶችን መትከል እና የመንገድ ቀለም መቀባት የመሳሰሉ ሌሎች ልዩ ልዩ ተግባራትን ባካተተ መልኩ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡ ከፕሮጀክቱ ጅማሮ አንስቶ አስካሁን 35 ኪሎ ሜትር (50%) የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ፤ 18 ኪሎ ሜትር (26%) የሳብቤዝ ስራውም አልቋል። ከዚህም ባሻገር 5 ኪ.ሜ (7%) የቤዝ ኮርስ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ፤ የአስፋልት እና የሲሚንቶ ኮንክሪት ንጣፍ ስራ ለመጀመር የሚያስችል የዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡ በተጨማሪም የአራት ድልድዮች የዲዛይን ስራ የተጠናቀቀ ከመሆኑም ባሻር ፤ 27% እንደ ፓይፕ ፣ ስላብና ቦክስ ከልቨርቶች የመሳሰሉ የውሃ ማስተንፈሻ ስራዎች ተከናውነዋል። በዚህም መሰረት ግንባታው በመጪው ሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይታመናል፡፡ ባለፉት ጊዜያት እንደሀገር የተከሰተው ከፍተኛ የሲሚንቶ እጥረት፤ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት የግንባታ ግብአቶችን ወደ ሳይት ማስገባት አለመቻል እና በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ተቀብረው ያልመከኑ ፈንጂዎች መኖር በግንባታ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድሩም ፤ እነዚህን ችግሮች በመቋቋም ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝቦችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር በማጠናከሩ ረገድ አማራጭ መንገድ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በተጨማሪም የአካባቢው ነዋሪዎች የትምህርት ፣ የጤና እንዲሁም መሰል ግልጋሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ቢሾፍቱ፣ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም (ኢመአ)፡ ለትግራይ ክልል መንገዶች ባለስልጣን እና የበኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለየአዲግራት ዲስትሪክት ሠራተኞች እና የ
+3
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ቢሾፍቱ፣ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም (ኢመአ)፡ ለትግራይ ክልል መንገዶች ባለስልጣን እና የበኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለየአዲግራት ዲስትሪክት ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በዋናነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የነበረውን አለመረጋጋት ታሳቢ ያደረገ የሥነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡ የሥራ ኃላፊዎቹና ሰራተኞቹ በሰሜኑ የሀገራችን አካባቢ በተከሰተው ግጭት የተጎዱና ከአገልግሎት ውጪ የነበሩ መንገዶችና ድልድዮች ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው ለመመለስ በሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ የሚገባቸው መሆኑንም በመድረኩ ተገልጿል፡፡ ቀጣይነት እንደሚኖረው በተገለጸው በዚህ የመጀመሪያ የስልጠና መድረክ ላይ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ኢ / ር ወንድሙ ሴታ ፣ የትግራይ ክልል የገጠር መንገድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር አርአያ ግርማይና የኢመአ አመራር አካላት ተገኝተዋል ። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ጋር በአቋራጭ የሚያስተሳስረው የአሳይታ-አፋምቦ-ጅቡቲ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመፋጠን ላይ ነው። የአሳይታ - አፋምቦ - ጅቡቲ ድንበር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 49 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በመንግሥት በተመደበ 1,676,348,103.83 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሶስት ብር ከሰማንያ ሶስት ሳንቲም ) በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ይገኛል። ይህ መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በሀገራዊ እና ቀጠናዊ ትስስሩ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ የሚካሄድበት መልክኣ ምድራዊ አቀማመጥ ሜዳማ ፣ ሸንተራራማ እና ተራራማ ሲሆን ፤ ከአዲስ አበባ በ663 ኪሎ ሜትር ርቀት አሳይታ ከተማ ላይ ጀምሮ ኢትዮ ጅቡቲ ድንበር ላይ ያበቃል፡፡ የአሳይታ-አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመካሄድ ላይ የሚገኘው አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ነው። የመንገድ ግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር ረገድ ደግሞ ይዲዲያ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማካሪነት በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ መንገዱ ትከሻን ጨምሮ በገጠር፡- 10 ሜትር ፣ በዞን፡- 21.5 ሜትር ፣ በወረዳ ደግሞ 19 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ይገኛል ፡፡ መንገዱ ከዚህ ቀደም በከፊል በጠጠር ደረጃ ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከግምት ውስጥ ገብቶ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ የአፈር ጠረጋን ፣ ቆረጣ እና ሙሌት ፣ የሰብቤዝ ፣የቤዝ ኮርስ ፣የአስፋልት፣የሶስት ድልድዮች ፣ የውሃ ማስተንፈሻ (ፓይፕ ፣ ስላብና ቦክስ ከልቨርቶች) ስራዎችን እንዲሁም የጎርፍ መከላከያ እና ልዩ ልዩ ግንባታዎችን (የመንገድ ምልክቶችን መትከል፣መንገድ ቀለም መቀባት) ባካተተ መልኩ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡ ከፕሮጀክቱ ጅማሮ አንስቶ አስካሁን 48 ኪሎ ሜትር (98%) የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ፣ 47 ኪሎሜትር (97%) የሳብቤዝ ስራውም አልቋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የፕሮጀክቱ 20 ኪሎሜትር (41%) የቤዝ ኮርስ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ፣ 95% የሶስት ድልድዮች ስራ እና 73% የውሃ ማስተንፈሻ (ፓይፕ ፣ ስላብና ቦክስ ከልቨርቶች) ስራዎች ከመጠናቀቃቸው ባሻገር የአስፋልት ግንባታ ስራም ተጀምሯል ። በዚህም መሰረት የፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም 40 ኪሎሜትር ወይም 82% በመቶ ተከናውኗል፡፡ ግንባታው በመጪው መስከረም ወር 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይታመናል፡፡ የስራ ተቋራጩ በቀሪ ጊዜያት ውስጥ 27% የውሃ ማፋሰሻ ስራዎችን ፣ ሙሉውን የአስፋልት ስራ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ስራዎችን (የትራፊክ ምልክቶች መትከል እና መንገዱን ቀለም የመቀባት ስራ) ለማከናወን አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ጊዜያት እንደሀገር የተከሰተው ከፍተኛ የሲሚንቶ እጥረት ፤ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት የግንባታ ግብአቶችን ወደ ሳይት ማስገባት አለመቻል ፤ ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ ችግሮች መኖራቸው እና አንዳንድ የአካባቢው ግለሰቦች ከመንገድ ስራው ጋር ባልተያያዘ ምክንያት ተደጋጋሚ የስራ ማስቆም አዝማሚያዎች የነበሩ ቢሆንም እነዚህን ችግሮች በመቋቋም ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በአካባቢው የአዋሽ ተፋሰስን ተከትሎ የአሳይታ እና አፋምቦ ወረዳዎች ለመስኖ ግብርና እጅግ አመቺ በመሆናቸው የሚመረቱትን የግብርና ውጤቶች በቀላሉ በጅቡቲ በኩል ወደ ውጪ ለመላክ የመንገዱ መገንባት አይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው ማምረት ከሚቻለው ምርት በከፊል እንደ ስኳር ፣ ስንዴ ፣ ሰሊጥ ፣ ጥጥ ፣ ቴምር እና መሰል የግብርና ምርት ለማከናወን አመቺ ሲሆን ፣ የመንገድ ፕሮጀክቱ ከሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር ይህንኑ ታሳቢ ተደርጎ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ በጅቡቲ በኩል የሚገነባው ቀጣይ የመንገድ ክፍል ሲጠናቀቅ ከዴቼቶ-ጋላፊ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ጋር በየብስ የሚያገናኝ አማራጭ መንገድ ሆኖ ያገለግላል። በአካባቢው የአዋሽ ተፋሰስን ተከትሎ የአፋምቦ ሀይቅ የሚገኝ ሲሆን ፤ ለቱሪስት መዳረሻነትም ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

የመካነ-እየሱስ/እስቴ-ስማዳ 50 ነጥብ 5 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በፍፃሜ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። አዲስ አበባ፣ ግንቦት 04፣ 2015(ኢመአ):- በደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ-እየሱስ/እስቴ-ስማዳ 50 ነጥብ 5 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በፍፃሜ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። አሁን ላይ ከአጠቃላይ የግንባታ ሥራው 86 በመቶው ተከናውኗል። ቀሪ ሥራዎቹን በሚቀጥሉት አምስት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው። ከጠቅላላው የመንገዱ ክፍል 47 ኪሎ ሜትሩን አስፋልት ማልበስ ተችሏል። በተጨማሪም የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ፣ የሾልደር፣ የውኃ መፋሰሻ፣ የድልድይ እንዲሁም የማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ ግንባታውን ዓለም አቀፉ 'ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ' እያከናወነ ይገኛል። ለግንባታው የሚውለው 1,925,451, 264.41 (አንድ ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ) ብር በፌደራል መንግስት ነው የሚሸፈነው። 'ፕሮሚናንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ' ግንባታውን የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ እየሠራ ይገኛል። አካባቢው ካለው በርካታ አገራዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡  በፕሮጀክቱ የከተማ ክልል ላይ ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ችግር በግንባታ ሥራው ላይ እክል ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም፥ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከወረዳ የመስተዳድር አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሩን መፍታት ተችሏል፡፡  ከዚህም ባለፈ የአካባቢው አስቸጋሪ የመልካ-ምድራዊ አቀማመጥ እንዲሁም የግንባታ ዕቃዎች የግብዓት ዕጥረት እና የዋጋ መናር በግንባታው ወቅት የገጠሙ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ የእስቴ-ስማዳ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ 657 ኪ.ሜ ርቀት እስቴ ከተማ ላይ ጀምሮ ወገዳ ከተማ ድረስ ይዘልቃል፡፡ ፕሮጀክቱ ዕውን ሲሆን በሥፍራው የሚገኙትን ትንንሽ መንደሮች ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በማገናኘት ወደ ከተማ የሚያድጉበትን ምቹ ዕድል ይፈጥራል፡፡የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን በማሳለጥም የተለያዩ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን ያጠናክራል፡፡ በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ሽንብራ፣ ኑግ፣ ባቄላ፣ ጓያ፣ ድንች እና መሰል የግብርና ምርቶች ገበያ በፍጥነት እና በጥራት ማድረስ ያስችላል፡፡

ሞባይል ሚዛን ጣቢያ ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው ተንቀሳቃሽ የቁጥጥር መተግበሪያ መሳሪያ ሲሆን አስካሁን ባለው ሁኔታ ያሉን ተንቀሳቃሽ ሚዛኖች ስድስት ብቻ በመሆናቸው በ ዋናው መ/ቤት በመዕከል ደረጃ በቻ የሚገኙ ሲሆን ለድጋፍ እና ቁጥጥር ስራ በቂየሆነ ተሸከርካሪ አንዲሁም የሰው ሀይል ባለመኖሩ በተገቢው ደረጃ ቁጥጥር ማድረግ አስቸጋሪ ቢሆንም ቋሚ ሚዛኖቸ የሌለባቸውን መንገዶቸ አየመረጥን ድንገተኛ ቁጥጥር ስራን እንዲሁም ከዲዛይን ዳይሬክቶሬት ለሚጠየቁ ለዲዛይን ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን በመሰብሰብ የድጋፍ ስራ አያከናወን የምንገኝ ሲሆን በጣም ለረጅም አመታት ሲያገለግሉ የቆዩ ነገር ግን ከከዚብዛት ተደጋጋሚ ብልሽት እየገጠማቸውን ተንቀሳቃስ ሚዛኖች ለመተካት የተጨማሪ (20) ሚዛኖቸ ግዚ ጥያቄ ለማቅረገብ ቅድም ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ 8. የተሸከርካሪ ክብደት ቁጥጥርን ከማዘመን አንፃር እስካሁን የተሰሩ ስራዎች እና በቀጣይ ሊተገበሩ የታሰቡ ተግባራት ላለፉት ከ30 አመታት በላይ ስንጠቀምባቸው የነበሩ የመመዘኛ ማሽኖች ሙሉ በሙሉ በማንዋል ወይም በቀጥታ የእጅ ንክኪ ይተገበሩ የነበሩ ናቸው፡፡ ከአምስት አመታት በፊት ተቋማችን ይህን አሠራራ ለመቀየር በነበረው ፍላጎት እና ይህንንም የጃፓን መንግስት (Jica ) ተገንዝቦ ድጋፍ ለማድረግ የጋራ መግባባት ላይ በተደረሰው ስመምምነት መሠረት አዲስ ዲጅታላይዝድ ማሽን ገጥመውልን በነባሩ አዋጅ መሠረት በኮምፒውተር የታገዘና ከእጅ ንኪኪ ነፃ የሆነ ስራ መተግበር ተችሏል፡፡ ነገር ግን ከአዲሱ ደንብ ጋር በተያያዘ በእርዳታ የተገኙት መመዘኛዎች ወጥ የሆኑ እና የጥንድ እና ባለሶስት አክስል ለየብቻ መለካት የማይችሉ ሲሆን ፣ ይህም በአዲሱ ደንብ መሰረት ወደ ስራ ለመግባት አስቸጋሪ ቢሆንም ፤ ይህን ችግር ከ(jica ) ጋር በመነጋገር መመዘኛ መሳሪያዎች ላይ እንዲደረጉ ማሻሻያዎችን ጠይቀናል፡፡ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በመመዘኛ ጣያቢያዎች ላይ በሚታየው የኤሌትሪክ ሀይል መቆራረጥ እና ከፍተኛ ሀይል መጨመር ምክንያት የሚደርሰውን የሀይል እጥረት እና የማሽኖችን ብልሽት ለመቅረፍ የባለ ብዙ ሀይል አማራጭ ሲሰተም ለመዘርጋት የፓወር ሀውስ ግንባታ እና የጀነሬተር ሶላር ፓኔል የባትሪ እና ኢንቨርተር ግዥ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ የሚዛን ጣያዎችን የአሰራር ስርአት የተቀናጀ አሰራር እና የቁጥጥር ስርአቱን ለማዘመን የፕሮጀክት ቀረጻ ስራ እያካሄድን እንገኛለን፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et

የመንገድ ግንባታ ለዘላቂ ልማት የኢኮኖሚ ልማትና የማህበራዊ ኑሮ እድገት ለማምጣት በሚደረግ ሀገራዊ ጥረት የመንገድ ዘርፍ የሚገኝበት ደረጃ እና የተሰጠው ትኩረት ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡ ለዚህም ነው መንግስት በየበጀት ዓመቱ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በመመደብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኘው፡፡ ይኸው ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስበት የመንገድ ሃብት የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ ተገቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል፡፡ በዚህም ረገድ የተሸከርካሪዎች የክብደት መጠን ቁጥጥር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ 1. የሚዛን ጣቢያዎች የቋቋሙበት ዓላማ፡- የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአዋጅ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በመንግስት እና በህዝብ የተጣለበትን ሀላፊነት ለመወጣት በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች ለህዝብ እና ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማህበራዊ ጠቀሜታ የሚሰጡ መንገዶችን የመገንባት የማስተዳደር እና ዲዛይን ለተደረጉበት የአገልግሎት ጊዜ ሳይበላሹ አንዲያገለግሉ የተለያዩ የቁጥጥር ስራዎቸን እያከናወነ ይገኛል:: ከነዚህ የቁጥጥር መንገዶቸ አንዱ በህግ ከተፈቀደላቸው የመጫን አቅም በላይ ከፍተኛ ጭነት በሚጭኑ የጭነት ተሸከርካሪዎች ምክንያት በመንገዶች እና በድልድዮች ላይ የሚደርስውን ከፍትኛ ጉዳት ለመቆጣጠር እና ለመንገድ ጥገና የሚወጡ ከፍተኛ ወጪዎችን ለመቀነስ ሲባል በአጠቃላይ በሀገሪቱ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የክብደት እና መጠን መቆጣጠሪያ ሚዛን ጣቢያዎቸን በመትከል የቁጥጥር ስራዎቸን እያከናወነ ይገኛል:: የተሽከርካሪዎችን ክብደት የመቆጣጠር ዋና አላማ በመንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸዉ የአክስል ክብደት መጠን በላይ ጭነት ጭነዉ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመንገድ አዉታሮች ላይ ጉዳት እንዳያደረስ የመከላከል እንዲሁም መንገዶች እና ድልድዮች ሳይበላሹ ለረዥም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ ነዉ፡፡ 2. በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የሚዛን ጣቢያዎች እና መገኛ ቦታቸው፡- እስካሁንም 14 ሚዛን ጣቢያዎቸን በተለያዩ ቦታዎቸ ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፣ መገኛ አካባቢያቸውም፡- ሞጆ ፣ ሆሎታ ፣ ሱሉልታ ፣ ሠንዳፋ ፣ ዲማ (ሰበታ) ፣ ጂማ ፣ ሻሸመኔ አዋሽ ፣ ሠመራ ፣ደንገጎ ፣ ኮምቦልቻ ፣ ጢቅ(ደጅን )፣ ወረታ ፣ ዮሓ (መቀሌ ) ናቸው ። 3. የተሸከርካሪዎችን የክብደት መጠን ለመወሰንና ለመቆጣጠር በወጣን የሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 491/2022 ውስጥ ዋና ዋና የድንጋጌ ነጥቦችን የተፈጻሚነት ወሰን - በማንኛዉም የኢትዮጵያ መንገዶች የሚጠቀሙ ጠቅላላ ክብደታቸዉ ከ3,500 ኪሎ ግራም በላይ በሆኑ ተሸከርካሪዎች ፣ የተጣመሩ ተሸከርካሪዎች እና ተሳቢዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች ፣ የተፈጥሮ አደጋ መከላከል ስራ ላይ በተሰማሩ ተሸከርካሪዎች ፣ በድንገተኛ አደጋ የወደሙ መሰረተ-ልማቶችን በመገንባት ሥራ ላይ በተሰማሩ ተሸከርካሪዎች ፣ ኢትዮጵያ በተፈራረመቻቸዉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መነሻነት የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች ፣ የግንባታ ስራ በሚከናወንበት አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የግንባታ ተሸከርካሪዎች እና በልዩ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ላይ የዚህ መመሪያ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ በደንቡ የተወሰነው ከፍተኛዉ የተሸከርካሪ ክብደት 56ቶን (560 ኩንታል) ሲሆን ፣ ይህም ድልድዮችን ከጉዳት ለመጠበቅ ሲባል የተቀመተጠ ከፍተኛ ገደብ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የትርፍ ጭነት የሚደርሰውን የመንገድ ሀብት ጉዳት መጠን ተመጣጣኝ የቅጣት ተመን በዝርዝር በደንቡ ላይ መቀመጡ ፣ እንዲሁም በትርፍ ጭነት ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ለመጠገን የሚያስፈልገውን ወጪ ከቅጣቱ የተገኘውን ገንዘብ መልሶ ለጥገና ለማዋል እንዲመች የቅጣት ገንዘቡ በሮድ ፈንድ አማካኝነት ወደ ኢመአ እንዲገባ በማድረግ መልሶ ለመንገድ ጥገና አገልግሎት እንዲውል ማድረግ ማስቻሉ፡፡ የትርፍ ጭነት ቅጣት ለሶስት የተከፈለ ሲሆን ፣ በዚሁም መሰረት አሽከርካሪው የጭነት ባለቤቱ እና የተሸከርካሪው ባለንበረት እንደ ቅጣቱ አይነት እና መጠን እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡ 4. ለእያንዳንዱ አክስል የሚፈቀድ የክብደት መጠን I. የነጠላ አክስል (Axle) ሁለት ወይም ሶስት ጎማዎች የተገጠሙለት ተሽከርካሪ የፊት እና የኋላ የአክስል (Axle) ክፍሎች ጠቅላላ የክብደት መጠን የሚከተለዉ ነዉ፡- ሀ) የፊት አክስል (የመሪ አክስል) Steering Axle የማይፈቀድ የክብደት መጠን ከ7.7 ቶን (77 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ፤ ወይም (9 ለ1) ለ) ከመሪዉ አክስል (Steering Axle) ዉጪ ሆኖ ነጠላ ጎማ የተገጠመለት ተሸከርካሪ ከሆነ ጠቅላላ ክብደቱ ከ8 ቶን (80 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ነዉ፡፡ (9 ለ2) ሐ) የ ኃላዉ የአክስል ክፍል አራት ጎማዎች የተገጠሙለት ከሆነ የአክስል ክብደቱ ከ10 ቶን (100 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ነዉ፡፡ (9 ሐ) II. የተሸከርካሪዉ የአክስል ክፍል ባለ ሁለት (Tandem Axle Unit) ወይም ባለሶስት (Tri-dem axle) ሲሆን ፣ ለተሸከርካሪዉ የማይፈቀድ የአክስል (Axle) የክብደት መጠን እንደሚከተለዉ ነዉ፡- ሀ) የጥንድ አክስል (Steering Tandem Axle) ክብደት ሳይጨምር ጠቅላላ የኋላ የአክስል ክብደቱ በአንድ ላይ ተደምሮ ከ18 ቶን (180 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ነዉ፡፡ ለ) ሶስት አክስሎች (Tri-dem axle) ከሆነ የሚፈቀደዉ ከፍተኛ ክብደት መጠን ከ24 ቶን (240 ኩንታል) የበለጠ እንደሆነ ነዉ፡፡ 5. የተደነገገውን ህግ ተላልፎ በሚገኝ ተሽከርካሪ ላይ የሚደረግ የቅጣት ሁኔታ በአዲሱ ደንብ መሰረት የቅጣት መጠን የመንገዶችን የጉዳት ልክ የሚመጥን እና ለመንገዶች ጥገና የሚውለውን ወጪ ያማከለ ሲሆን ፣ ለነጠላ ጥንድ ወይም ለባለሶስት አክስል እርስ በእርስ ሳደማመሩ በዝርዝር የተቀመጠው አነስተኛው ቅጣት መጠን 603 ብር ሲሆን ፣ ከፍኛው ደግሞ 70520 ብር ነው፡፡ 6. አንድ ተሽከርካሪ ከወደብ ወይም ከጫነበት ቦታ ሲነሳ የጫነው የክብደት መጠን ተመዝኖ እንዲንቀሳቀስ ለማስቻል እየተከናወነ ያለ ቅድመ ሁኔታን በተመለከተ እስካሁን ባለው ሁኔታ ጭነቶች ከመነሻቸው መቆጣጠር አስፈላጊ ቢሆንም ሚዛን ጣቢያን ለመትከል ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስፈልግ በመሆኑ በየአያንዳንዱ የሀገሪቱ መግቢያ እና መውጫዎቸ እንዲሁም የጭነት መነሻ ስፍራዎች ላይ የጭነት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መትከል አቅም ስለማይፈቅድ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአሁኑ ሰአት ያሉት ሚዛኖች በዋና አገናኝ መንገዶች እና ከፍተኛ ገቢና ወጪ ያለባቸውን መንገዶች ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተተከሉ ሲሆን ፣ ለወደፊቱ ለማቋቋም የቦታ መረጣና ተገቢው የቅድመ ሁኔታ ጥናት እንዲሁም የፕሮጀክት ድጋፍ ለመፈለግ አስፈላጊው ሰነድ በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡ 7. ተንቀሳቃሽ (ሞባይል) የሚዛን ጣቢያዎችን በተመለከተ

የቡልቡላ - አላጌ - ባራ - ሚቶ መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ነው ። 39 ኪሎ ሜትር ርዝመትን የሚሸፍነው የቡልቡላ - አላጌ - ባራ - ሚቶ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ  77 በመቶ ስራው ተጠናቋል። ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ኪቢሽ የተባለ ሀገር  በቀል የስራ ተቋራጭ ሲሆን ፣ United Consulting Engineers plc ( UNICON ) ደግሞ የማማከር እና የቁጥጥር ስራውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ለፕሮጀክቱ የተመደበው 878,514,732.42 (ስምንት መቶ ሰባ ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር ከአርባ ሁለት ሳንቲም) በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው። ከቡልቡላ ዋና ከተማ 2 . 5 ኪ . ሜ ርቀት ላይ መነሻውን ያደረገው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት የኦሮምያን ክልል ከደቡብ ክልል ጋር ያስተሳስራል።  አካባቢው እንደ በቆሎ ፣ ስንዴ ፣ ቦሎቄና በርበሬ  ያሉ የተለያዩ የግብርና ምርቶች የሚመረቱበት መሆኑ የመንገዱን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጉልህ ያደርገዋል። በአሁኑ ወቅት የመንገዱ 31 ኪ . ሜ ወይም 81 በመቶ የሰብ ቤዝ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ፣ 33 ኪ . ሜ ወይም 85 በመቶ የሰብ ግሬድ ስራውም ተከናውኗል። ከዚህም ባሻገር የስላብና ፓይፕ ካልቨርት ስራዎችም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ ። በቅርቡም የአስፋልት ንጣፍ ስራም እንደሚጀመር ታውቋል ። አጠቃላይ የመንገዱ አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፣  በተገቢው ጥራትና ጊዜ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስፈላጊውን ቁጥጥር እና ድጋፍ ያደርጋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et