ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

前往频道在 Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览

频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 977 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 694,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 550 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 977 名订阅者。

根据 26 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 151,过去 24 小时变化为 6,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 35.97%。内容发布后 24 小时内通常能获得 17.69% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 027 次浏览,首日通常累积 2 472 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 25。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 27 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。

13 977
订阅者
+624 小时
+307 天
+15130 天
帖子存档
ከዬት ወዴት? 75 ዓመታት የመንገድ ልማት፤ ትናንት እና ዛሬ:- የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር 75ኛ ዓመትን ስናከብር፣ የተገነቡ መንገዶችን ብቻ ሳይኾን በእነዚህ መንገዶች የተፈጠረውን የሀገር ለውጥ እናስታውሳለን። ከ75 ዓመታት በፊት ከአንድ አካባቢ ወደ ዋና የአስፋልት መንገድ ለመድረስ ሰዓታት አልፎ ተርፎም ቀናት ይወስድ ነበር። ዛሬ ላይ ግን በመንገድ አውታሩ መስፋፋት ምክንያት ዜጎች በአማካኝ 1 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ወደ ዋና መንገዶች መድረስ ችለዋል። ይህ የጊዜ ለውጥ ብቻ አይደለም፤ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የማኅበራዊ ትስስር እና የአገልግሎት ተደራሽነት መሠረት ነው። መንገዶች የገበያ በሮችን ከፍተዋል፤ የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ እንዲደርሱ፣ ኢንዱስትሪዎች ከጥሬ ዕቃና ከወደብ ጋር እንዲገናኙ፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው፣ ሕሙማን ወደ ጤና ተቋማት እንዲደርሱ አስችለዋል። በጥራትም እንዲሁ ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል። ትናንት የመንገድ ግንባታ በውስን ቴክኖሎጂና አቅም ይከናወን ነበር፤ ዛሬ ግን የዘመናዊ ምህንድስና መርሆዎች፣ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓቶች፣ የላብራቶሪ ምርመራዎችና የብቁ የሀገር ውስጥ ባለሙያዎች አቅም የዘላቂነትና የጥራት አዲስ ምዕራፍ ፈጥረዋል። ወደፊትም ግባችን የበለጠ ጥራት ያላቸው፣ ዘላቂ፣ አካባቢን የሚጠብቁ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፉ እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚመጥኑ መንገዶችን መገንባት ነው። በመንገድ ዘርፉ የተገኘው ሌላው ታላቅ ለውጥ የሰው ኃይል አቅም ነው። በአንድ ዘመን በውጭ ባለሙያዎች ይመራ የነበረው ዘርፍ፣ ዛሬ በኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች፣ ዲዛይነሮች፣ ተቆጣጣሪዎች እና ባለሙያዎች እየተመራ ነው። ይህ የ75 ዓመታት ጉዞ ስኬቶች መካከል አንዱ ነው።   የ75 ዓመታት ቁጥራዊ ዕውነታዎች:-   👉ጠቅላላ የመንገድ አውታር       1943 ዓ.ም - 6 ሺህ 400 ኪ.ሜ (ጠጠር እና አፈር)       2018 ዓ.ም - 180 ሺህ 232 ኪ.ሜ 👉 የአስፋልት መንገድ ርዝመት        1943 ዓ.ም - ውስን       2018 ዓ.ም - 16 ሺህ 760 ኪ.ሜ 👉 ወደ ዋና የአስፋልት መንገድ ለመድረስ የሚፈጀው ጊዜ       1943 ዓ.ም - የቀናት ጉዞ (ክረምት ከበጋ የሚያስኬድ)       2018 ዓ.ም - 1 ሰዓት ከ25 ደቂቃ 👉 የመንገድ ጥግግት      1943 ዓ.ም - 0.46 ኪ.ሜ      2018 ዓ.ም - 1.46 ኪሜ 👉 በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መንገድ      1943 ዓ.ም - 22 በመቶ      2018 ዓ.ም - 62 ነጥብ 7 በመቶ 👉 ኢትዮጵያዊያን መሀንዲሶች      1943 ዓ.ም - ደጃዝማች ዒሳ ሸሪፍ      2018 ዓ.ም - በሺዎች የሚቆጠሩ   ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት መንገዳችን፣ ኃላፊነታችን! በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

75 ዓመታት፤ ከውስን የመንገድ አውታር ወደ ሀገርን የሚያስተሳስር ዘመናዊ መሠረተ ልማት! ሀገራችን ከዝቅተኛ የመንገድ መሠረተ-ልማት ወደ ሰፊ፣ ዘመናዊና የኢኮኖሚ ኮሪደሮችን የሚያገናኝ መንገድ ጉዞ አድርጋለች። በተለያዩ ምዕራፎች የተተገበሩ የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራሞች ይህን ጉዞ በተቀናጀ አቅጣጫ የመሩ ሲኾን፤ የመንገድ ግንባታ ከቁጥር ባለፈ፣ ዘላቂነትና ተደራሽነትን ያረጋገጠ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያስመዘግብ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም በ1989 ዓ.ም የተጀመረው የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም በኢትዮጵያ የመንገድ ልማት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ የመንገድ አውታሩን ማስፋት፣ ጥራትን ማሻሻል፣ የጥገና ሥርዓትን ማጠናከርና ተቋማዊ አቅምን መገንባት ነበር። የመጀመሪያው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (1989–1994 ዓ.ም)፡- ዋና ትኩረቱ አዲስ አበባን ከክልል ዋና ከተሞች፣ ከንግድ ማዕከላትና ከወደብ መስመሮች ጋር የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎችን ማሻሻል ነበር። በዚህ ወቅት 8 ሺህ 709 ኪ.ሜ መንገድ ተገንብቶና ታድሶ ለአገልግሎት በቅቷል። ሁለተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (1995–1999 ዓ.ም)፡- የመንገድ አውታርን ማስፋት፣ የገጠር ተደራሽነትን ማሻሻልና አዳዲስ መንገዶችን መገንባት ተቀዳሚ ትኩረቶች ነበሩ። በዚህ ወቅት 11 ሺህ 589 ኪ.ሜ መንገድ ተገንብቷል። ሦስተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (2000–2002 ዓ.ም)፡- ነባር የጠጠር መንገዶችን ወደ አስፋልት ማሳደግ፣ አዳዲስ አገናኝና ዋና መዳረሻ መንገዶችን መዘርጋት ላይ ተተኮረ። በዚህ ወቅት 12 ሺህ 395 ኪ.ሜ መንገድ ተገንብቷል። አራተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም (2003–2007 ዓ.ም)፡- የገጠር አካባቢዎችን ከመንገድ አውታር ጋር ማገናኘትና ተደራሽነትን ማስፋት ትኩረት አግኝቷል። በዚህ ወቅት 85 ሺህ 860 ኪ.ሜ የሚሸፍኑ የተለያዩ መንገዶች ተገንብተዋል። አምስተኛው የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም (2008–2012 ዓ.ም)፡- ይህ ዘመን የመንገድ ልማትን ከጥራት፣ ከዘላቂነትና ከቴክኖሎጂ ጋር ያስተሳሰረ ምዕራፍ ነበር። በፕሮግራሙ የመጀመሪያ ሦስት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ 27 ሺህ 210 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ መንገዶች ግንባታ ተካሄዷል፡፡ ስድስተኛው የመንገድ ዘርፍ የልማት ፕሮግራም (2012–2017 ዓ.ም)፡- በዚህ ዘመን 28 ሺህ 949 ኪ.ሜ የፌዴራል እንዲሁም የክልልና የወረዳ መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል። በዚህም የሀገሪቱ አጠቃላይ የመንገድ አውታር በ1989 ዓ.ም ከነበረበት 26 ሺህ 550 ኪ.ሜ ወደ 180 ሺህ 232 ኪ.ሜ አድጓል። ባለፉት 28 ዓመታት በተተገበሩ ስድስቱ ፕሮግራሞች በአጠቃላይ 805 ነጥብ 76 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ መዋለ-ንዋይ ፈሰስ ተደርጓል። በአጠቃላይ እነዚህ ፕሮግራሞች የመንገድ አውታርን በማስፋት ብቻ ሳይወሰኑ፤ የጥራት ደረጃን ከፍ ማድረግ፣ የገጠርና የከተማ ትስስርን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ኮሪደሮችን ማሳደግና የሀገር አቀፍ ልማትን ማፋጠን የቻሉ የለውጥ ምዕራፎች በመኾን ወደ ተሻለ የዕድገት ጎዳና የምትጓዝ ኢትዮጵያን ገንብተዋል። ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት  መንገዳችን፣ ኃላፊነታችን! በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

መንገድ የልማት መሠረት ነው፤ የ75 ዓመታት ጉዟችን የክብር ታሪካችን ነው! መንገድ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ለሕዝቦች ማኅበራዊ ትስስር መጎልበት ዋነኛውና ቀዳሚው መሠረት ነው። ተቋማችን ላለፉት 75 ዓመታት የሀገሪቱን የመንገድ አውታር ለመዘርጋትና ለማዘመን ያደረገው ጉዞ በብዙ ፈተናዎች እና ስኬቶች ውስጥ ያለፈ የክብር ታሪክ ነው። በአውራ ጎዳና ፕሮግራሞች (በመንገዶች ግንባታ፣ ማሻሻያ እና ጥገና) የተገነባው 18,781 ኪሎሜትር የመንገድ መሠረተ-ልማት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል። ተቋሙ ቀደም ሲል ሲያከናውናቸው የነበሩትን የመንገድ ልማት ፕሮግራሞች በመቀየር የመንገድ ሴክተር ልማት ፕሮግራሞችን በሥራ ላይ አውሏል፦ የመጀመሪያው የመንገድ ሴክተር ፕሮግራም (1971 - 1974 ዓ.ም)፦ የሀገሪቱን የግብርና ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ይበልጥ ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ የመጋቢና የገጠር መንገዶች ግንባታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሰርቷል። ሁለተኛው የመንገድ ሴክተር ፕሮግራም (1974 - 1979 ዓ.ም)፦ የዋና እና የገጠር መንገዶችን ግንባታ ከመፈጸም ባለፈ፣ የነባር መንገዶችን ደረጃ ማሳደግና የአየር ማረፊያዎች ግንባታን በስፋት ማካተት ችሏል። በእነዚህ ሁለት ስልታዊ ፕሮግራሞች በአጠቃላይ 8,899 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል። የሀገራችን ኢኮኖሚ በግብርና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ዕድገት ለማሳካት እና የመንገድ ተደራሽነት ፍላጎትን በዘላቂነት ማሟላት የመንግሥት ቀዳሚው የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል። ለዚህም ሲባል የመንገድ መሠረተ-ልማቱን በከፍተኛ ደረጃ ማዘመን የሚያስችለው መጠነ-ሰፊ የመንገድ ዘርፍ ልማት ዕቅድ ተነደፈ። በወቅቱ ከመንግሥት የሚመደበው በጀት ለሰፊው የመሠረተ-ልማት ፍላጎት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ፣ አበዳሪና ለጋሽ ሀገራት የተሳተፉበት ታሪካዊ የፋይናንስ ኮንፈረንስ በ1988 ዓ.ም ተካሂዷል። በዚህ ስኬታማ ኮንፈረንስ ከ1.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በብድርና በእርዳታ ማግኘት የተቻለ ሲሆን፤ ይህም በ1989 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ታሪክ ውስጥ ትልቁና መጠነ-ሰፊ የመንገድ ዘርፍ ልማት ዕቅድ (RSDP) ወደ ተግባር እንዲሸጋገር በር ከፍቷል። በቀጣይ ክፍሎች፣ የመንገድ ልማት ዘርፉ የእስከአሁን ያሳየው አፈጻጸም ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ያበረከተውን ጉልህ አስተዋጽዖ በስፋት የምንዳስስ ይሆናል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

መንገድ  የልማት  መሠረት ነው፤ የ75 ዓመታት ጉዞአችን የክብር ታሪካችን ነው!   መንገድ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ለሕዝቦች ማኅበራዊ ትስስር መጎልበት ዋነኛውና ቀዳሚው መሠረት ነው። ተቋማችን ላለፉት 75 ዓመታት የሀገሪቱን የመንገድ አውታር ለመዘርጋትና ለማዘመን ያደረገው ጉዞ በብዙ ፈተናዎች እና ስኬቶች ውስጥ ያለፈ ነበር፡፡   በአውራ ጎዳና ፕሮግራሞች (በመንገዶች ግንባታ ፣ ማሻሻያ እና ጥገና 18 ,781 ኪሎሜትር) የተመዘገበው  ውጤት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል። የባለስልጣን መ/ቤቱ ቀደም ሲል ሲያከናውናቸው የነበሩ መንገድ ልማት ፕሮግራሞች በመቀየር  የመንገድ ሴክተር ልማት ፕሮግራሞችን በሥራ ላይ አውሏል። አንደኛው የመንገድ ሴክተር ፕሮግራም (1971 - 1974 ዓ.ም)  የሀገሪቱን የግብርና ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ይበልጥ ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ መጋቢና የገጠር መንገዶች ግንባታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሰርቷል። ሁለተኛው የመንገድ ሴክተር ፕሮግራም(1974 -1979 ዓ.ም) የዋና እና የገጠር መንገዶችን ግንባታ ከመፈጸም ባለፈ የነባር መንገዶችን ደረጃ ማሳደግና የአየር ማረፊያዎች ግንባታን በስፋት ማካተት ችሏል። በመንገድ ሴክተር ፕሮግራሞቹ በአጠቃላይ 8,899 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል። ቀጣይነት ያለውና የተሻሻለ የመንገድ ይዞታን ለመፍጠር እንዲሁም የመንገድ ተደራሽነት ፍላጎትን በዘላቂነት መመለስ የመንግሥት ቀዳሚው የትኩረት አቅጣጫ ሆነ።   በተለይም የሀገራችን ኢኮኖሚ በግብርና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ዕድገት ለማሳካት የመንገድ መሠረተ ልማቱን በከፍተኛ ደረጃ ማዘመን የሚያስችለው መጠነ ሰፊ የመንገድ ዘርፍ ልማት ዕቅድ ተነደፈ። ከመንግሥት የሚመደበው በጀት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ  አበዳሪና ለጋሽ ሀገራት የተሳተፉበት ታሪካዊ የፋይናንስ ኮንፈረንስ በ1988 ዓ.ም ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ  ከ1.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በብድርና በእርዳታ ማግኘት ተቻለ፡፡ ይህም በ1989 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ታሪክ ውስጥ ትልቁና መጠነ  ሰፊው የመንገድ  ዘርፍ ልማት  ዕቅድ (RSDP) ወደ ተግባር ተሸጋግሯል ።   በቀጣይ  የመንገድ  ልማት  ዘርፍ  የእስከአሁን  አፈፃፀም  ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ያበረከተውን ጉልህ አስተዋጽዖ የምንዳስስ ይሆናል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

ያለፈው ስኬታችን ዛሬን ያጠናክራል፤ የዛሬው ጥንካሬችንም ነገን ይገነባል! የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሀገሪቱን ከተሞችና ገጠራማ አካባቢዎች እርስ በርስ ለማስተሳሰርና መሠረታዊ የመንገድ ልማት ጥያቄዎችን በየደረጃው ለመመለስ መሥራት ከጀመረ  75 ዓመታት ተቆጥረዋል። ይህ ታሪካዊ ተቋም በጥር 17 ቀን 1943 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 115 ሲመሠረት የአሁኑ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በወቅቱ  "የአውራ ጎዳና ባለሥልጣን" የሚል ስያሜ ነበረው፡፡ ተቋሙ የተመሠረተበት ዋና ዓላማም የፈራረሱትን መንገዶች መጠገን፣ አዳዲሶችን መገንባትና ለዘርፉ ዘላቂ ኃላፊነት የሚወስድ ጠንካራ   አካል መፍጠር የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ሀገሪቱ የነበራት ጠቅላላ የመንገድ ርዝማኔ 6,400 ኪሎ ሜትር ብቻ የነበረ ሲሆን  ከዚህ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኘውና አገልግሎት የሚሰጠው  875 ኪሎ ሜትር  ብቻ ነበር። ይህንን  የመንገድ  ውስንነት ለመቀየር እና ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት  በብቃት  ለመወጣት  ከ1943 - 1973 ዓ.ም  ባሉት ዓመታት  ውስጥ ስድስት ተከታታይ የአውራ ጎዳና  ፕሮግራሞችን አከናውኗል፡፡ የመጀመሪያው  የአውራ ጎዳና ፕሮግራም (1943 - 1949 ዓ.ም ) ከዓለም ባንክ በተገኘ  ብድር በ 20 ዓመታ ውስጥ  የሚከፈል  12,500,000 ብር  ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት 23,000,000 ብር ጨምሮበት ለመጀመሪያው የአውራ ጎዳና ፕሮግራም  የሦስት ዓመት  ማከናወኛ እንዲውል ተደረገ። ይህ ፕሮግራም ዋነኛ ትኩረቱ  በኢጣሊያ ወረራ ወቅት ተገንብተው በእንክብካቤ ጉድለት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ነባር መንገዶች ማሻሻልና መጠገን ላይ አደረገ። ሁለተኛው  የአውራ ጎዳና ፕሮግራም (1949 - 1958 ዓ.ም) ነባር መንገዶችን ከመጠገንና ከማሻሻል ባለፈ አዳዲስ መንገዶችን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ እመርታ አሳይቷል። ሶስተኛው  የአውራ ጎዳና ፕሮግራም (1958 - 1961 ዓ.ም ) የተቋሙ  አቅም ይበልጥ እያደገ በመምጣቱ፤ የአዳዲስ መንገድ ግንባታ፣ የአስፋልት ሥራ፣ የድልድይ ግንባታ እንዲሁም የቅየሳና የዲዛይን ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል። አራተኛው የአውራ ጎዳና ፕሮግራም (1961 - 1966 ዓ.ም.) የሀገሪቱን ዋና ዋና ከተሞችና የኢኮኖሚ ማዕከላትን ይበልጥ ለማስተሳሰር የሚያስችሉ አዳዲስ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ መንገዶች ተገንብተዋል። አምስተኛው የአውራ ጎዳና ፕሮግራም (1966 - 1969 ዓ.ም ) በዚህ ምዕራፍ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ለእርሻ ልማትና ለኢንዱስትሪ ዕድገት ቀጥተኛ እገዛ ለሚያደርጉ መጋቢ መንገዶች ግንባታ ነበር። ስድስተኛው የአውራ ጎዳና ፕሮግራም (1969 - 1973 ዓ.ም.) የመንገድ ልማት ተደራሽነትን ይበልጥ በማስፋት፣ የኢትዮጵያን የልማት ትስስር ወደ ገጠሩ ማኅበረሰብ ያደረሰ ምዕራፍ ነበር፡፡ በእነዚህ  ስድስት የአውራ ጎዳና ፕሮግራሞች የተመዘገቡት ስኬቶች የመንገድ ልማቱን ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጋር በስፋት በማስተሳስር ረገድ የተመዘገቡትን ውጤቶችን እንዲሁም ቀጣይ የልማት ፕሮግራሞችን የምናይ ይሆናል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

75 ዓመታት ፤ ኢትዮጵያን በመንገድ ያስተሳሰረ ጉዞ! የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር የ75 ዓመታት የልማት ጉዞ ስንዘክር፣ ይህ የታሪክ ምዕራፍ ለተቋማችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን በመገንዘብ ነው። ባለፉት ሰባት አሥርት ዓመታት ተኩል፤ ተቋማችን በመላው የኢትዮጵያ ምድር ላይ የዘረጋቸው የመንገድ አውታሮች ተራራን በመውጣት፣ ሸለቆን በመሻገርና ርቀትን በማጥበብ የሕዝባችንን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር አጠናክረዋል። ይህ የ75 ዓመታት ጉዞ በኢትዮጵያውያን መሃንዲሶችና ሌሎች ባለሙያዎች ከፍተኛ ጥረት የታነጸ የፅናት ታሪክ ነው። ሀገራችን ከነበረባት የቴክኖሎጂ ውስንነት እና መልካ-ምድራዊ ፈተናዎች ተነስታ ዛሬ ላይ የደረሰችበት የመንገድ ግንባታ አቅም፣ የሀገር ውስጥ የሰው ኃይል ብቃትና የቴክኖሎጂ ዕድገት ኢትዮጵያ የራሷን የልማት አቅጣጫ በራሷ አቅም መቅረጽ የምትችል መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው። የመንገድ መሠረተ ልማት የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ መሰረት እንደመሆኑ በየዘመናቱ የነበሩ መሐንዲሶቻችንና ሌሎችም ባለሙያዎች እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦችንና የተፈጥሮ ተግዳሮቶችን በመቋቋም የግብርና ምርቶች ወደ ገበያ እንዲደርሱ፣ ኢንዱስትሪዎቻችን ከወደብ ጋር እንዲገናኙና ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የላቀ ሚና ተጫውተዋል። ዛሬ ላይ ቆመን ወደ ኋላ ስንመለከት ተቋማችን የዘመናዊ መንገድ ግንባታን ሥልጣኔ ወደ ሀገራችን ከማስገባት ባለፈ በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ትልቅ የዕውቀት መቅሰሚያ ሆኗል። ይህ የሰው ኃይል አቅም ለቀጣዩ የልማት ውጥናችን ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው። ወደፊት በምናደርገው ጉዞ የ75 ዓመታት ልምዳችንን ከዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ከዘመናዊ የኢንጂነሪንግ አሠራሮችና ሪፎርሞች ጋር በማጣጣም የበለጠ ጥራት እና ዘላቂነት ያላቸው መንገዶችን በመገንባት ለቀጣዩ ትውልድ የሚመጥን የመሠረተ-ልማት ለማስረከብ በቁርጠኝነት የምንተጋበት ነው። በግንባታ ሂደት ውስጥ የአካባቢ እና ማኅበራዊ ጥበቃን እንዲሁም የመንገድ ደኅንነትን እና የመንገድ ሃብት ማኔጅመንትን ያገናዘበና የሰው ኃይል አቅምን በቴክኖሎጂ የደገፈ አሠራርን በማስፈን፣ ኢትዮጵያን በቀጠናዊ ትስስርና በአፍሪካ የመሠረተ ልማት ዕድገት ግንባር ቀደም ሀገር ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት የምናጠናክርበት ነው።   የተቋማችንን 75 ዓመታት ጉዞ ስናስብ ያለፈውን ስኬት የምናወድስበት ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለችና በመሠረተ-ልማት የተሳሰረች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ቃል የምንገባበት አጋጣሚ ጭምር ይሆናል።   "ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት  መንገዳችን ፤ ኃላፊነታችን!" ምርጥ መንገዶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና! በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የሀገራችን የኢኮኖሚ ጥንካሬ መገለጫና የዘመናዊነት ጉዟችን የጀርባ አጥንት የሆነው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከተመሰረተ እነሆ 75 ዓመታትን አስቆጥሯል። ይህም ተቋሙ በኢትዮጵያ የጀመረውን የመንገድ አውታር የመዘርጋት ታሪካዊ ተልዕኮ በጽናት መወጣቱን የምናበስርበት ያለፉትን ስኬቶች የምንዘክርበትና ወደፊት ለሚጠብቀን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ዳግም ቃል የምንገባበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ተቋማችን በ1943 ዓ.ም. ሲመሰረት የኢትዮጵያን ተራራማና ወጣ ገባ መልክዓ ምድር በመንገድ ማስተሳሰር የማይታሰብ በሚመስልበት ወቅት የተጀመረው ጉዞ ባለፉት 75 ዓመታት ያስመዘገብናቸው ስኬቶች በመንገድ ርዝመት ብቻ የሚገለጹ አይደሉም። ይልቁንም የተራራቁ ወገኖቻችንን በማገናኘት የሀገራችንን የንግድ ትስስርን እንዲቀላጠፍ በማስቻል እና የጤናና የትምህርት አገልግሎቶች ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ እንዲደርሱ በማድረግ በጠቅላላው የሀገራችንን ሁለንተናዊ ትስስርና አንድነትን በመፍጠር ረገድ የተጫወትነው ሚና የተቋሙን ታላቅነት ይገልጻል። ያሳለፍነው ጉዞ በፈተናዎች የተሞላ እንደነበረ ታሪክ ምስክር ነው። በአየር ንብረት ለውጥ በመልክዓ ምድር አስቸጋሪነትና በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መዋዠቅ ሳቢያ የገጠሙንን ተግዳሮቶች በጽናት ተቋቁመን ዛሬ ላይ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ መንገዶችን ፣ የፍጥነት መንገዶችን (Expressways) እና የድልድዮችን ግንባታ በማጠናቀቅ ለሕዝብ አገልግሎት ማብቃት ችለናል። ተቋሙ በሂደት ውስጥ የራሱን የሰው ኃይል በከፍተኛ የሙያ ብቃት በማነጽ የሀገር በቀል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እንዲያድግ እና የኢትዮጵያ መሐንዲሶች በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። የወደፊት ትኩረታችን የመንገዶቻችንን ርዝመት መጨመር ብቻ ሳይሆን ጥራታቸው ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩና በዘመናዊ ዲጂታል ሥርዓት የሚተዳደሩ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ዓለማቀፋዊና ምርጥ መንገዶች ለበለጸገች ኢትዮጵያ በ2022 በሚለው ራዕያችን ኢትዮጵያን በዘመናዊ መንገድ ማስተሳሰር ብቻ ሳይሆን ስራዎቻችን በቴክኖሎጂ የረቀቁ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነባቸው እንዲሁም ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ የሚሰጡ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የታገዘ የአስተዳደር ስርዓት በመዘርጋትና በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ የግንባታ ጥራትን በማረጋገጥ ተቋማችን ለሀገራዊ ብልጽግና ያለውን የማይተካ ሚና አጠናክሮ ይቀጥላል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads