uk
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Відкрити в Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Канал ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 13 331 підписників, посідаючи 1 756 місце в категорії Транспорт та 2 541 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 13 331 підписників.

За останніми даними від 17 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 95, а за останні 24 години на 18, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 41.14%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 15.24% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 5 485 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 2 032 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 16.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 17 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Транспорт.

13 331
Підписники
+1824 години
+417 днів
+9530 день
Архів дописів
የኢተያ - ሮቤ - ሴሩ መንገድ የአስፓልት ስራ ተጠናቀቀ ። አራት ወረዳዎችን የሚያገናኘውና 75.6 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ኢተያ-ሮቤ- ሴሩ ሎት 1 ኢተያ ሮቤ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፓልት ስራው ተጠናቋል ። ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ቻይና ሬል ዌይ ቁጥር 3 ኢንጅነሪግ ግሩፕ የተሰኘው አለም አቀፍ የሥራ ተቋራጭ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን የሚሰራው ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን የትራንስፖርት ዘርፍ ነው፡፡ መንገዱ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አንፃር ደረጃውን ጠብቆ ከአንድ ቢሊየን ሶስት መቶሀያ አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳአራት ሺህ አምስት መቶ አስር ብር (1,324,234,510.32) በላይ በሆነ ወጪ የኢትዮጵያ መንግስት ሸፍኖ ወደ አስፋልት ኮንክሪት ደረጃ አድጓል ፡፡ የመንገድ ስራው ያካተተው የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የድሬኔጅ ፣ ስትራክቸር ስራዎች፣ የሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣የቤዝ ኮርስ እንዲሁም ሙሉ የአስፋልት ንጣፍ የተከናወነ ሲሆን ቀሪ ስራዎች ማለትም የቀለም ቅብ፣ የዲች ክዳን እና የመንገድ ትከሻ ና የእግረኛ መሄጃዎች ተጠቃሽ ነው ። የመንገድ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ የጎን ስፋት በወረዳና በከተማ ከ 19 – 21 ሜትር ፣ በቀበሌ 15 ሜትር ፣ በገጠር ደግሞ 10 ሜትር ስፋት ያለው ነው፡፡ የመንገዱ መገንባት በአርሲ ዞን ውስጥ የሚገኙትን የሄጦሣ፣ የሎዴ ሄጦሳ፣ የዲክሲስ እና ሮቤ ወረዳዎችን እና ቦሩ ሌንጫ፤ጎበያ፤አርብ ገበያ፤እድገት ፋና፤ቡላላ ቀበሌዎችን አስተሳስሮ ከዚህ በፊት ይወስድ የነበረውን የጉዞ ጊዜ በአራት ሰአት አሳጥሮ ምቹ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲኖር አስችሏል ፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው ላይ የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን ስንዴ፤ገብስ እና ከአትክልቶችም እንደ ሽንኩርት፤ድንች እና ቲማቲም በአካባቢው ላይ ስለሚመረቱ በቀላሉ ወደ መሃል አገር እንዲቀርብ በማድረግ የአምራች ገበሬዎችን ተጠቃሚነት ያሳድጋል ተብሎ ይታሰባል ። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኢተያ - ሮቤ - ሴሩ መንገድ የአስፓልት ስራ ተጠናቀቀ ። አራት ወረዳዎችን የሚያገናኘውና 75.6 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ኢተያ-ሮቤ- ሴሩ ሎት 1 ኢተያ ሮቤ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፓልት ስራው ተጠናቋል ። ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ቻይና ሬል ዌይ ቁጥር 3 ኢንጅነሪግ ግሩፕ የተሰኘው አለም አቀፍ የሥራ ተቋራጭ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን የሚሰራው ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን የትራንስፖርት ዘርፍ ነው፡፡ መንገዱ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አንፃር ደረጃውን ጠብቆ ከአንድ ቢሊየን ሶስት መቶሀያ አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳአራት ሺህ አምስት መቶ አስር ብር (1,324,234,510.32) በላይ በሆነ ወጪ የኢትዮጵያ መንግስት ሸፍኖ ወደ አስፋልት ኮንክሪት ደረጃ አድጓል ፡፡ የመንገድ ስራው ያካተተው የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የድሬኔጅ ፣ ስትራክቸር ስራዎች፣ የሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣የቤዝ ኮርስ እንዲሁም ሙሉ የአስፋልት ንጣፍ የተከናወነ ሲሆን ቀሪ ስራዎች ማለትም የቀለም ቅብ፣ የዲች ክዳን እና የመንገድ ትከሻ ና የእግረኛ መሄጃዎች ተጠቃሽ ነው ። የመንገድ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ የጎን ስፋት በወረዳና በከተማ ከ 19 – 21 ሜትር ፣ በቀበሌ 15 ሜትር ፣ በገጠር ደግሞ 10 ሜትር ስፋት ያለው ነው፡፡ የመንገዱ መገንባት በአርሲ ዞን ውስጥ የሚገኙትን የሄጦሣ፣ የሎዴ ሄጦሳ፣ የዲክሲስ እና ሮቤ ወረዳዎችን እና ቦሩ ሌንጫ፤ጎበያ፤አርብ ገበያ፤እድገት ፋና፤ቡላላ ቀበሌዎችን አስተሳስሮ ከዚህ በፊት ይወስድ የነበረውን የጉዞ ጊዜ በአራት ሰአት አሳጥሮ ምቹ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲኖር አስችሏል ፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው ላይ የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን ስንዴ፤ገብስ እና ከአትክልቶችም እንደ ሽንኩርት፤ድንች እና ቲማቲም በአካባቢው ላይ ስለሚመረቱ በቀላሉ ወደ መሃል አገር እንዲቀርብ በማድረግ የአምራች ገበሬዎችን ተጠቃሚነት ያሳድጋል ተብሎ ይታሰባል ።

የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጠናቀቀ ጅግጅጋ፣ የካቲት 22/2018 (ኢ መ አ):- በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት መጠናቀቁን ተከትሎ ደረጃውን የጠበቀ የትራፊክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ 6 ነጥብ 93 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣ 30 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ተገንብቷል። መነሻውን ጅግጅጋ ከተማ መግቢያ አድርጎ ቶጎ-ጫሌ አደባባይ ላይ ያበቃው ይህ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላ  እና ሌሎች ጥቃቅን ስራዎች እየተከናወኑ ነው። በተጨማሪም የእግረኛ እና የብስክሌተኞች መተላለፊያ  ግንባታ ተካቷል። ሀገር-በቀሉ ይርጋለም ኮንስትራክሽን ግንባታውን ያከናወነው ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ኤልዳ አማካሪ ድርጅት ከዳምራ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ጋር  በጋራ ሰርተውታል። ለግንባታው ማስፈጸሚያ የዋለውን 672,098,730.28 (ስድስት መቶ ሰባ ሁለት ሚሊየን ዘጠና ስምንት ሺህ ብር ሰባት መቶ ሰላሳ ብር ከሃያ ስምንት) ወጪ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግስት በጀት ተሸፍኗል። የተለዋጭ መንገድ ግንባታው መጠናቀቅ በጅግጅጋ ከተማ ውስጥ እንዲሁም መግቢያ እና መውጫ  ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያቃልላል። ከቶጎ ጫሌ  እንዲሁም ከደገሀቡር የሚመጡ የከባድም ሆነ ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች ጅግጅጋ ከተማን ሳያቋርጡ ለማለፍ አማራጭ መንገድ ሆኖ ያገለግላል። ከዚህም ባለፈ የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት እና ውበት በማሳለጥ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የአጣጥ ማዞሪያ - ጉንችሬ - ቆሴ - ሌራ - ጌጃ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት 56 በመቶ ተጠናቀቀ ጉንችሬ፣ የካቲት 20/2018 (ኢ መ አ):- የጉራጌ፣ ስልጤ እና ሃዲያ ዞኖችን እንዲሁም 6 ወረዳዎችን የሚያስተሳስረው የአጣጥ ማዞሪያ - ጉንችሬ - ቆሴ - ሌራ - ጌጃ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ከአጠቃላይ የግንባታ ሥራው 56 በመቶው ተጠናቅቋል። የመንገድ ፕሮጀክቱ 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በፌደራል መንግሥት በጀት ተይዞለት በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል። አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ክፍል 47 ኪሎሜትሩን በአስፋልት የማልበስ ሥራ ተከናውኗል። ከዚህ ጎን ለጎንም የመሬት ጠረጋ፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ፣ የአስፋልት ንጣፍ እንዲሁም የስትራክቸር ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ። የግንባታውን አፈጻጸም በተሻለ ሁኔታ ለማስቀጠል በተቋማችን በኩል የቅርብ ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ ይገኛል። የመንገድ ፕሮጀክቱ ወደ አጣጥ ሆስፒታል፣ ጉንችሬ፣ ዲንቁላ እና ጌጃ ከተሞች የሚወስዱትን አገናኝ መንገዶች ጨምሮ አጠቃላይ 97 ኪሎሜትር ይሸፍናል። ሀገር - በቀሉ ዓለማየሁ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የመንገድ ግንባታውን በማከናወን ላይ ይገኛል። ኤስጂ የምህንድስና አማካሪዎች የፕሮጀክቱን ጥራት እና ቁጥጥር ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል። የመንገድ ፕሮጀክቱ በሦስቱ ዞኖች ውስጥ የሚገኙትን የቸሃ፣ እኖር፣ ኤነርና መገር፣ እንደጋኝ፣ አመካ እንዲሁም ምዕራብ አዘርነትን ጨምሮ የ6 ወረዳዎች ሁለንተናዊ ትስስር ያጠናክራል። በአካባቢው የሚገኙትን የተለያዩ የግብርና ምርት ውጤቶች በስፋት ወደ ማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የጎላ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ይኖረዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የቆሼ - ሚቶ - ወራቤ አስፋልት መንገድ ግንባታ በቀጣይ ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው ወራቤ፣ የካቲት 18/2018 (ኢ መ አ):- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 5 ወረዳዎችን የሚያስተሳስረው የቆሼ - ሚቶ - ወራቤ አስፋልት መንገድ ግንባታ 79 ነጥብ 5 በመቶው የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱን ዋና ዋና ሥራዎች በቀጣይ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል። በመንገድ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የ47 ኪሎሜትር አስፋልት ንጣፍ፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የሰብቤዝ እንዲሁም የቤዝኮርስ ሥራዎች ተከናውነዋል። የሁለት ድልድዮች ግንባታም በፕሮጀክቱ ተካትቷል። ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ አሁን ላይ 58 ኪሎሜትሩ ወይንም 79 ነጥብ 5 በመቶው ተጠናቅቋል። የግንባታውን ዋና ዋና ሥራዎች በቀጣይ ዓመት ታኅሣሥ ወር ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። የመንገድ ፕሮጀክቱ 73 ኪሎሜትር የሚሸፍን ኾኖ፣ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው። የመንገድ ግንባታውን ሀገር-በቀሉ የንኮማድ ኮንስትራክሽን የሚያከናውን ሲኾን፥ የጥራት እና ቁጥጥር ሥራውን ፕሮሚነንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ ያከናውናል። ለግንባታ የተመደበው 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በፌደራሉ መንግሥት ይሸፈናል። የመንገዱ ነባር ገጽታ 63 ኪሎሜትሩ በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲኾን፥ ቀሪው ምንም ዓይነት የመንገድ መሠረተ ልማት አልነበረውም። አሁን ላይ መንገዱ በወረዳ የእግረኛ መንገድን ሳይጨምር 14 ሜትር፣ በገጠር ቀበሌ የመንገድ ትከሻን ሳይጨምር 7ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በመገንባት ላይ ነው የሚገኘው። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የማረቆ እና የስልጤ ሕዝብ ማኅበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ትስስር ያጠናክራል። ከዚህ ቀደም ከቆሼ ከተማ ተነስቶ የስልጤ ዞን መናገሻ ወራቤ ከተማ ለመድረስ የሚፈጀውን 3 ሰዓት የጉዞ ጊዜ በ2 ሰዓት በማሳጠር፣ በአካባቢው በስፋት የሚታወቁትን የበርበሬ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ጤፍ እና መሰል የጥራጥሬ እና የአዝርዕት ምርት ውጤቶች በፍጥነት እና በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ ያስችላል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኮልፌ 18 ማዞሪያ (ኮልፌ ሃይስኩል)- አሸዋ ሜዳ - ኬላ መንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17/ 2018 ዓ.ም ( ኢመአ ) ፡ የአዲስ አበባ ከተማን ከተለያዩ የክልል ከተሞች ጋር ከሚያገናኙ ዋና ዋና መግቢያና መውጫ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የኮልፌ ሃይስኩል - አሸዋ ሜዳ - ኬላ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከአጠቃላይ የመንገድ ይዞታ 14 .73 ኪሎ ሜትር ውስጥ 8 ኪሎ ሜትር መንገድ የአስፋልት ንጣፍ ተደርጎለታል ፡፡ የመንገድ ፕሮጀክቱ በኢመአ የራስ ሃይል ( ዓለም ገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ) እና በሀገር-በቀሉ የሥራ ተቋራጭ ብሪጅ ኮንስትራክሽን በጋራ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ የማማከሩን ሥራ ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እየተወጣው ይገኛል፡፡ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆነው ወጪ ዘጠኝ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ስድስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ብር ( 9, 254 586 980 ) የሚሸፈነው በፌደራል መንግሥት ሲሆን፣ መንገዱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ( ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ) እና ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ( ሸገር ከተማ አስተዳደርን ) አቋርጦ በማለፍ ከምዕራቡ የሀገራችን ክፍል ጋር የነበረውን ቁርኝት ያጠናክራል ፡፡ መንገዱ የአዲስ አበባ መግቢያና መውጫ እንደመሆኑ መጠን በቦታው የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ እና የመንገዱን ደረጃ ለመጠበቅ ሲባል ማስፋፊያ በማድረግ የእግረኛ እና የሳይክል መንገዶች በዲዛይኑ በማካተት በአዲስ መልክ እየተገነባ ይገኛል፡፡ መንገዱ አጠቃላይ 50 ሜትር የጎን ስፋት ይኖረዋል። የመንገድ ግንባታው ከአስፋልት ንጣፍ ጎን ለጎን የአቃፊ ግንብ ፣ የውኃ መፋሰሻ ፣ የመንገድ አካፋይ ፣ የከልቨርት እንዲሁም ቀሪ የአፈር ቆረጣ ፣ የሰብ ቤዝና የቤዝ ኮርስ ስራዎች እየተከናወኑለት ይገኛል ፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ከማድረጉም ባሻገር የጉዞ ጊዜን ፣ ወጪና እንግልትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ፡፡ በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ለገበያ እንዲቀርቡና በአካባቢው ብዛት ያላቸውን የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማእከላዊ ገበያ ተደራሽ የማድረግ ጠቀሜታ ይኖረዋል ፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የመረዋ - ሰሞዶ - ሰቃ እና ሰሞዶ ሊሙ መገንጠያ መንገድ ግንባታ 64 በመቶ ደረሰ አዲስ አበባ፣ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢመአ) ፦ 93.95 ኪ.ሜ የሚረዝመው የመረዋ - ሰሞዶ - ሰቃ እና ሰሞዶ ሊሙ መገንጠያ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃጸም 64 በመቶ ደርሷል፡፡ እስካሁን ባለው የግንባታ ሂደት 42.65 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን የአፈርጠረጋ 88.49% እና የአፈር ሙሌት ስራው ደግሞ 80.32% ደርሷል። በተጨማሪም የአንድ ድልድይ እና 49 የውሃ መፋሰሻዎች ግንባታ ለማጠናቀቅ ተችሏል። የመንገዱ ግንባታ በቻይና ቲሲጁ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በተባለ የሥራ ተቋራጭ እየተከናወነ ሲሆን፤የማማከርና የቁጥጥር ሥራው በተባበሩት የምሕንድስና አማካሪዎች አማካኝነት ነው እየተሰራ የሚገኘው። መንገዱ በገጠር 10 ሜትር፣ በቀበሌ ከተሞች 12 ሜትር እንዲሁም በወረዳ ከተሞች 19 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል። ለግንባታው የሚውለው 2 ነጥብ 58 ቢሊዮን ብር ወጪም በኢትዮጵያ መንግሥት የተሸፈነ ነው። በግንባታው ወቅት ባጋጠመ የተራዘመ ዝናብና በወሰን ማስከበር ምክንያት ያጋጠሙ መዘግየቶችን ለማካካስ፤ በበጋ ወቅትም የሥራ ሰዓትን በማራዘም፣ ተጨማሪ ማሽነሪዎችን በማሰማራትና የወሰን ማስከበር ሂደቱን ለማጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት የግንባታ ሥራው ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል። ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በጅማ ዞን ውስጥ የሚገኙትን የሊሙ ገነት፣ የሊሙ ኮሳ እና የማና ወረዳዎችን እንዲሁም በስራቸው የሚገኙ ቀበሌዎችን በማስተሳሰር እና የጉዞ ጊዜን በከፍተኛ ሁኔታ በማሳጠር የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል። ከዚህም ባሻገር በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን እንደ ቡና፣ በቆሎ እና አቮካዶ ያሉ የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ለማድረስ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም ባለፈ፤ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማነቃቃትና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የድሬዳዋ - ሽንሌ እና የድሬዳዋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ ድሬዳዋ ፣ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢመአ): የድሬዳዋ ከተማን ከሽንሌ ከተማ ጋር የሚያገናኘው የድሬዳዋ - ሽንሌ እና የድሬዳዋ ከተማ ተለዋጭ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ፤ የቀልም ቅብ ስራዎች እና ሌሎች ጥቃቅን ስራዎች ተገባደዋል። አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 29 ነጥብ 29 ኪሎ ሜትርን የሚሸፍን ሲሆን በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው የተገነባው። ዓለም - አቀፉ ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የመንገዱን ግንባታ ያካሄደው ሲሆን የማማከር እና የቁጥጥር ሥራው በቤዛ ኢንጂነሪንግ ኬንያ ሊሚትድ ተከናውኗል። ፕሮጀክቱን ለማስፈፀም የዋለው 1,146,143,392 ( አንድ ቢሊዮን አንድ መቶ አርባ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ሲሆን ሙሉ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኗል፡፡ የመንገዱ መገንባት የድሬዳዋ እና የሽንሌ ከተሞችን ደረጃውን በጠበቀ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ያገናኛል። ከዚህም ባሻገር ከጂቡቲ በድሬዳዋ ደወሌ መንገድ በኩል የሚመጡ የጭነት ተሸከርካሪዎች ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ሳይገቡ የሚያልፉ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ አስቀርቶታል፡፡ በተጨማሪም አሽከርካሪዎች ይወስድባቸው የነበረውን የጉዞ ጊዜ አሳጥሯል። በአካባቢው በስፋት የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን በቀላሉ ወደ ገበያ በማውጣት የገበያ ትስስርን ለመፍጠር ያስችላል፡፡ መንገዱ በወረዳ 21.5 ሜት ር ፣ በከተማ 25 ሜትር እንዲሁም በገጠር 7 ሜትር አጠቃላይ የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads