ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
611
订阅者
-124 小时
-17 天
-1030 天
帖子存档
❤ አርያኖስም አክሚም ከተማ በደረሰ ጊዜ ኤጲስቆጶስን አባ ብኑድያኖስን ያዘውና አሥሮ ወደ አገር ውስጥ ገባ። የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም ለዲዮሰሰቆሮስና ለሰከላብዮስ ተገለጸላቸው ወደ መኰንኑም ሒደው የምስክርነት አክሊልን እንዲቀበሉ ነገራቸው እነርሱም ታኅሣሥ ሃያ ስምንት ቀን  ሃያ አራት መነኰሳት ሁነው ሔዱ። ወደ አክሚም ከተማም ሲደርሱ በመድኃኒታችን ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የከበረ የልደትን በዓል ለማክበርና ስለ ከበረ ስሙም ይሞቱ ዘንድ የክርስቲያን ወገኖችን ከሴቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ተሰብስበው አገኙአቸው ኤጲስቆጶሱ አባ ብኑድያኖስም ከእርሳቸው ጋር ገባ። በማግሥቱም አባ ብኑድያኖስ ቀደሰ አግዮስ ወደሚባለው በደረሰ ጊዜ መላእክት እንዲህ ብለው በታላቅ ድምጽ አመሰገኑ "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር አሸናፊ ፍጹም የጌትነትህ ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው"። ያን ጊዜ መድኃኒታችንን በመሠዊያው ታቦት ላይ ተቀምጦ መላእክትም በዙሪያው ቁመው ቊርባኑን እያነሣ በካህኑ እጅ ላይ በማድረግ የተሰበሰቡትን ሲያቆርባቸው ቅዱሳኑ አዩት። ❤ በዚያንም ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ደረሰ ተቆጥቶም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ስማቸው ብሕዋፋና ውኒን የሚባሉ ሁለት የአገር አለቆችን ይዞ ራሳቸውን በሰይፍ ቆረጠ ከእነርሱም በኋላ ዲያቆናትን ንፍቀ ዲያቆናትን መዘምራንን የቤተ ክርስቲያን ሹሞች ደማቸው ከቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወጥቶ ሃያ ክንድ ያህል እስቲጎርፍ ሴቶችና ልጆችንም ሳያስቀር አረዳቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሱን አባ ብኑድያስን ዲዮስቆሮስን ሰከላብዮስን ከእርሳቸውም ጋር ያሉ መነኰሳትን ከእርሱ ጋር ወሰዳቸው ለጣዖትም ይሰግዱ ዘንድ ሸነገላቸው እምቢ በአሉትም ጊዜ ዐጥንቶቻቸው እስከሚለያዩ ድረስ ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾላቸው አዳናቸው የአርያኖስም የጭፍሮቹ ታላላቆች ኮርዮንና ፊልሞና ከጭፍሮችም አርባ ሰዎች ይህን ድንቅ ተአምር አይተው በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ወደ እሳት ማንደጃም እንዲጥሏቸው አዘዘ። ተጋድሏቸውንም ታኅሣሥ ሠላሳ ቀን ፈጸሙ ከተሰበሰቡትም ውስጥ ብዙዎች የሚያስገድዳቸው ሳይኖር በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ እናምናለን እያሉ ወደ እሳቱ ማንደጃ ራሳቸውን ወረወሩ ምስክርነታቸውንም እንደዚህ ፈጸሙ። ❤ ከዚህም በኋላ ጥር አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ ታሥረው ሳሉ የመላእክት አለቃ ቅዱሰሰ ሚካኤል ተገለጠላቸውና ምስክርነታቸውን እንደመፈጽሙ አበረታቸው በነጋም ጊዜ ለአማልክት ስለ መስገድ አርያኖስ ተናገራቸው አይሆንም በአሉትም ጊዜ የዲዮስቆሮስን ዐይኖቹን ያወልቁ ዘንድ አዘዘ ቅዱሱም የወለቁ ዐይኖቹን አንሥቶ ወደ ቦታቸው መለሳቸው መኰንኑ ሉክዮስ አይቶ ከሠራዊቱ ጋር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ወደ እሳትም ወርውረዋቸው ምስክርነታቸውንም ፈጸሙ። ❤ ከዚህም በኋላ የከበሩ ሰማዕታትን ይገደሏቸው ዘንድ አርያኖስ አዘዘ ሲጸልዩም የክብር ባሌበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸው ስማቸውን ለሚጠረሠ መታሰቢያቸውንም ለሚያደርግ ገድላቸውንም ለሚጽፍ ከቅዱሳን አንድነት ይቈጥረው ዘንድ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ከዚህም በኋላ ወታደሩ ቀርቦ የቅዱስ ዲዮስቆሮስን ራሱ ቆረጠ ሰከላብዮስንም ከወገቡ ላይ ቆረጡት ሃያ አራቱን መንኰሳትም ከቁመታቸው ሠነጠቋቸው በዚች በጥር አንድ ቀን ተቆረጡ ከዘመዶቻቸው የሆነ ሳሙኤልም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበራቸው በአገረ አክሚም የተገደሉ ሰማዕታትም ቊጥራቸው ስምንት ሺህ አንድ መቶ አርባ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሁሉ ቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር1 ስንክሳር።                          ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በ­ቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ78፥10-11። የሚነበበው ወንጌል ማር13፥9-23።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ በጻሕኮ በበረከት ሠናይ። ወአንበረከ አክሊለ ዲበ ርእሱ ዘእምዕንቊ ክቡር። ሐይወ ሰአለከ ወወሀብኮ"። መዝ 20፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥32-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥51-58። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 21፥33-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃነ ልደቱ ሰሞን፣ የቅዱስ እስጢፋኖስ የልደትና የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።                 

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የተባረከ_የጥር_ወር_የመዓልቱ_ሰዓት_ዐሥር ነው ከእንግዲህ ይጨመርለታል።               ❤ #ጥር ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን #ለሊቀ_ዲያቆናት_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለልደቱና_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ከሶርያ_አገር_ለሆነ በከሀዲው መክስምኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነት ለተበቀበለ #ለቅዱስ_ለውንድዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስልሳ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_መቃርስ ዕረፍት፣ #ከከበሩ_ከአክሚም_ሰማዕታት የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ከፈጸሙ ስማቸው #ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ ዕረፍት፣ በዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ቊጥራቸው #ከካህናት_ስምትት_መቶ፣ #ከዲያቆናት_መቶ_ሠላሳ_ከመምህራን_ኃምሳ፣ #ከሦስት_ከቤተ_ክርስቲያን_ሹማምንት_ከሰማንያ_መሳፍንት_ከሠላሳ_ሁለት_ንፍቅ_ዲያቆናትና_ከመቶ_ኃምሳ_ሕዝባውያን ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                     ✝ ✝ ✝ ❤ #ቀዳሜ_ሰማዕታት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ፦ ለዚህም ለከበረ እስጢፋኖስ እግዚአብሔር ኃይልን ጸጋ የተመላ ሰው እንደነበረና በሕዝቡም መካከል ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ሥራን ይሠራ እንደነበረ የሐዋርያት ሥራ የተባለ መጽሐፍ ስለርሱ ምስክር ሆነ። ከዚህም በኋላ አይሁድ ቀኑበት የሐሰት ምስክሮች የሚሆኑ ሰዎችንም አስነሡበት "ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር  ላይ የስድብ ቃልን ሲናገር ሰምተነዋል እንዲሉ ሐሰትን አስተማሩአቸው። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችን ጸሐፊዎችንም አነሣሡአቸው አዳርሱን ብለው ከበው እየጐተቱ ወደ ሸንጎ ወሰዱት። ❤ የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት እነርሱ ይህ ሰው በቤተ መቅደስ ላይ በኦሪትም ላይ ስድብን ሲናገር ተው ብንለው እምቢ አለ። "የናዝሬቱ ኢየሱስ ቤተ መቅደሳችሁን ያፈርሰዋል ሙሴ የሰጣችሁን ኦሪታችሁንም ይሽራል" ሲል ሰምተነዋል አሉ። በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሁሉ ተመለከቱት ፊቱም የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ሁኖ አዩት። ሊቀ ካህናቱም "እውነት ነውና እንዲህ አልክ" አለው። እርሱም እንዲህ አለ "ወንድሞቻችንና አባቶቻችን ስሙ ወደ ካራን ከመምጣቱ አስቀድሞ በሶርያ ወንዞች መካከል ሳለ ለአባታችን ለአብርሃም የክብር ባለቤት እግዚአብሔር ተገለጠለት። ካአገርህ ውጣ ከዘመዶችህም ተለይ እኔ ወደማሳይህ አገርም ና" አለው። ❤ "ከዚህም በኋላ ከከላውዴዎን ወጥቶ በካራን ተቀመጠ አባቱም ከሞተ በኋላ ዛሬ እናንተ ወደ አላችሁባት ወደዚች አገር አመጣው። ከዚህም በኋላ የግዝረትን ሥርዓት ሰጠው ይስሐቅም በወለደው ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገዘረው እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን ገዘረው ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን ነገድ አባቶች ገዘረ። የቀድሙ አባቶቻችንም በዮሴፍ ላይ ቀንተው ወደ ግብጽ አገር ሸጡት እግዚአብሔር ግን አክብሮት ነበር። ከመከራው ሁሉ አዳነው በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ዕውቀትን መወደድን ሰጠው በግብጽ አገር ሁሉና በቤቱ ሁሉ ላይ ሾመው"። ነገርም በማስረዘም በሰሎሞን እጅ እስከተሠራችው ቤተ መቅደስ ያለውን ተረከላቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ድምፁን ከፍ ከፍ አድርጎ "እናንተም እንደአባቶቻችሁ ዘወትር መንፈስ ቅዱስን የምታሳዝኑት ዐይነ ልቡናችሁ የታወረ ዕዝነ ልቡናችሁ የደነቈረ አንገተ ደንዳኖች" አላቸው። "አባቶቻችሁ ከነቢያት ያላሳደዱት ያልገደሉት ማን አለ እናንተ ክዳችሁ የገደላችሁትን ገደላችኋቸው። በመላእክት ሥርዓት ኦሪት ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም"። ❤ ይህንንም ሰምተው ተበሳጩ ልባቸውም ተናደደ ተነሠሣ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። በቅዱስ እስጢፋኖስም መንፈስ ቅዱስ አደረበት ሰማይም ተከፍቶ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ የእግዚአብሔርን ክብር አየ። "እነሆ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ አያለሁ" አለ። ❤ ዶሮአቸውን ይዘው በታላቅ ድምፅ ጮኹ በአንድነትም ከበው ጐተቱት። እየጐተቱም ከከተማ ወደ ውጭ አውጥተው በደንጊያ ወግረው ገደሉት የገድሉትም ሰዎች ልብሳቸውን ሳውል ለሚባል ጐልማሳ ልጅ ያስጠብቁ ነበር። "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል" እያለ ሲጸልይ እስጢፋኖስን በደንጊያ ወገሩት። ❤ ዘለፍለፍ ባለ ጊዜም ድምፁን ከፍ አድርጎ "አቤቱ ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው በደልም አታድርግባቸው" ይህንንም ብሎ ዐረፈ። ደጋግ ሰዎችም መጥተው የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ ወስደው ቀበሩት ታላቅ ልቅሶም አለቀሱለት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ሐዋርያና ሰማዕት በሆነ በቅዱስ እስጢፋኖስ  አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ለውንድዮስ፦ የዚህም ቅዱስ ዜና እግዚአብሔርን የሚያመልክ ተጋዳይ እንደሆነ ንጉሥ መክስምያኖስ በሰማ ጊዜ ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሃይማኖቱንም ትቶ አማልክቶቹን ያመልክለት ዘንድ ብዙ ገንዘብ አቀረበለትና ይሸነግለው ጀመረ የከበረ ቅዱስ ለውንድዮስ ግን ዘበተበት ስጦታውንም  በማቃለል ክብሩን አጐሳቈለ የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመ። ❤ ያን ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ በመንኰራኵር ውስጥ ሰቅለው ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን እንዲ አሠቃዩት አዘዘ። ንጉሥ እንዳዘዘ አደረጉበት የክብር ባለቤት ጌታችን ግን ያለ ጥፋት በጤና አወጣው። ዳግመኛም በብረት ዘንጎች ይደበድቡት ዘንድ ቅባትና ስብንም በታላቅ ድስት አፍልተው ቅዱስ ለውንድዮስን ከውስጡ ይጨምሩት ዘንድ አዘዘ ይህን ሁሉ ሥቃይንም አሠቃዩት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያጸናውና ያስታግሠው ያለ ጉዳትም በጤና ያስነሣው ነበር። ❤ ማሠቃየቱንም በደከመው ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ከሥጋውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራቶች ተገለጹ ዜናውም በሶርያ አገር ሁሉ ተሰማ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተሠሩለት ከገዳማቱም በአንዲቱ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው የከበረ ሳዊሮስ በሕፃንነቱ ተጠመቀባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ለውንድዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የከበሩ_የአክሚም_ሰማዕታት_ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ፦ እክሚም በሚባል አገር ሹም የሆነ አንድ ሰው ነበር በወርቅ በብር ባለጸጋ ነው ስሙም አልሰመማልዮስ ይባላል ስማቸው ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ የሚባል ሁለት ልጆቹን ወለደ እነርሱም ከመጾምና ከመጸለይ ጋር እግዚአብሔርን በመፈራት አደጉ። አባታቸው በሞተ ጊዜ ምንኵስናን ተመኙ የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦላቸው ወደ ገዳማዊ አባ ሙሴ ገዳም እንደመሔዱ አዘዛቸው ሒደውም በዚያ መነኰሱ ድንቆች ተአምራቶችንም እያደረጉ በብዙ ተጋድሎ ኖሩ። ከጥቂት ወራትም በኋላም ዲዮስቆሮስ ቅስና ሰከላብዮስም ዲቁና ተሾሙ። ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት ክርስቶስን በካደው ጊዜ ለጣዖታት የማይሰግዱ ክርስቲያኖችን ሁሉ ይገድል ዘንድ የእንዴናው ገዥ አርያኖስን አዘዘው።

❤ በሆሣዕና ዕለት ወደ አበ ምኔቱ ሒዶ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ ፈቃድ ለመነው ፈቀደለትም በማግሥቱም ፊታቸው የሚያበራ ሦስት ሰዎች ሲጠብቁት አብሮዋቸው ሔደ። ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ የአባ ዘካርያስን ቤት ሊጐበኝ ሔደ ሦስት ታላላቅ ዘንዶዎች በምድር ላይ ሲርመሰመሱ አግኝቶ በአያቸው ጊዜ ፈራቸው እነርሱም በስሙ ጠሩት ወደነርሱም ዘወር ሲል "አባት ሆይ ሲመግበን የነበረው ጌታችን ዘካርያስ ከዚህ ወደየት ሔደ"  ብለው በሰው አንደበት ተናገሩት። አበ ምኔቱም ሰምቶ አደነቀ መብልንም ሰጣቸው። አባ ዘካርያስም ወደ መኖሪያው ተመልሶ በብዙ ተጋድሎ ኖረ። ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዘካርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 30 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15 ወይም መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 3፥15-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥12-21 እና የሐዋ ሥራ 19፥8-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃነ ልደቱ በዓል ሰሞን። ለሁላችንም ይሁንልን።                 

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ታኅሣሥ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት ለተመሰገኑ አባት አርባ ዓመት ሙሉ የሴቶች ፊት ሳያይ ለኖረ #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ለሆነ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመኰንኑ ከአርያኖስ የጥፍሮቹ ታላላቆች #ለቅዱሳን_ለኮርዮንና_ፊልሞና ከእናርሳቸው ጋር ካሉ #ከአርባ_ወታደሮች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋድይ ለሆነ #ለአባ_ዘካርያስ ዕረፍትና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ኄሮድስ ከገደላቸው #ከከበሩና_ከነጹ_ሕፃናት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                 ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህም ተጋዳይ የምንኵስና ልብስን ከለበሰ ጀምሮ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው ዜናውም በአገሩ ሁሉ ተሰማ። ይህም አባ ዮሐንስ ሁል ጊዜ የሚጐበኘው አንድ መኰንን ነበረ የመኰንኑም ሚስት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ እንዲወስዳት ባሏን ታምለውና ታስገድደው ነበር እርሱም "የከበረ አባ ዮሐንስ ከአርባ ዓመት ጀምሮ የሴቶችን ፊት አላየም" አላት።  ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሒዶ ሚስቱ ያለችውን ለአባ ዮሐንስ ነገረው አባ ዮሐንስም "በእግዚአብሔር ፈቃድ የፈለገችውን እፈጽምለሠታለሁ" አለው። ❤ በዚያችም ሌሊት የከበረ ዮሐንስ ለዚያች ሴት በሕልም ተገልጾ እንዲህ አላት "ጻድቅ ያልሆንኩ ወይም ነቢይ የኔን ፊት ታዪ ዘንድ የምትሺ አንቺ ሴት ከእኔ ምን አለሽ እኔስ ካንቺ ምን አለኝ እንግዲህስ ፊቴን ማየት አትሺ" ይህንንም ብሎ በላይዋ ጸልዮ ባረካት። በማግሥቱም የከበረ አባ ዮሐንስ በመንፈስ እንደታያት ለባሏ ነገረችው። መልኩንና አምሳያውን አመለከተችው ከዚያም በኋላ ከብዙ ሙገሳና ምስጋና ጋር ባሏን ወደ አባ ዮሐንስ ላከችው። ❤ የከበረ ዮሐንስም ባሏን በአየው ጊዜ ፈገግ ብሎ "የሚስትህ ምኞቷ የተፈጸመላት አይደለምን በዚች ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ አግኝታኛለችና" አለው መኰንኑም ሰምቶ ከትሩፋቱና ከደግነቱ የተነሣ እጅግ አደነቀ። ይህም አባ ዮሐንስ ጭንቅ በሆነ ተጋድሎ ዘጠና ዓመት ያህል ኖረ ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ❤ የአስቄጥ ገዳም አበ ምኔት አባ ዮሐንስ፦ ይህም አባት በተሾም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በራች ለብዙ ቅዱሳንም አባት ሆነ ከእርሳቸው ውስጥ ታላላቅ ከዋክብት የሆኑ አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም የአገረ ተሙዝ ኤጲስቆጶስ አባ ሚናስ የአገረ ስሐ አባ ዘካርያስ ለብዙ ሰዎች ነፍሳት ወደብ የሆኑ እነርሱን የመሰሉ ሌሎች ብዙዎች አሉ። ለሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን በሚያቈርብ ጊዜ ኃጢአተኞውና ጻድቁ ይገለጥለታና ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንም በመሠዊያው ላይ ብዙ ጊዜ አየው። ❤ በአንዲትም ዕለት ሥራው የከፋ አንዱን ቄስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጠሠ አየው ከእርሱም ጋር ያሉ ብዙዎች ርኩሳን የረቀቁ አጋንንት ከበውት አፉ ውስጥ ልጓም አድርገዋል ወደ ቤተ ክርስቲያንም ከመግባቱ በፊት የእግዚአብሔር መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ በእሳት ሰይፍ ከእርሱ ከቄሱ መናፍስትን አሳደዳቸው ቄሱም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ መቀደሻውን የክህነት ልብስ ለበሰ ሁለመናውም እንደ እሳት ሆነ ቀድሶም ለሕዝቡ ሥጋውና ደሙን አቀበላቸው። ልብሰ ተክህኖውንና የመቀደሻውን ሽልማት ከላዩ አውልቆ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜ እነዚያ የጠቆሩ መናፍስት ርኩሳን ተቀብለው እንደቀድሞው አደረጉበት። አባ ዮሐንስም ይህን ነገር ለመነኰሳቱ ሲያስረዳ እንዲህ አላቸው "በቅዳሴ አገልግሎት ጊዜ ለኃጢአተኛውና ለጻድቁ ቄስ ልዩነት የለም ስለ ሕዝቡ እምነት ያ ኅብስት ተለውጦ የክርስቲያን ሥጋ ይሆናልና ወይኑም የከበረ ደሙን ይሆናልና"። ❤ ዳግመኛም በምሳሌ እንዲህ አላቸው "በብረት በወርቅና በብር ላይ እንደሚቀረጽ እንደ ንጉሥ ማኅተም ነው። ማኅተሙም አይለወጥም እንዲሁ ከካህናትም የክህነት ጸጋ አይለወጥም እርሱ እግዚአብሔር በጊዜው ጊዜ ለሁሉም ለየአንዳዱ እንደሠራው ይከፍለዋል እንጂ"። ይህንም የከበረ ዮሐንስ ታላቅ መከራ ደርሶበታል አረማውያን በርበር ማርከው ወደ አገራቸው ወስደውታልና እያሠቃዩትም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመን ታሥሮ ኖረ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ገዳሙ መለሰው። ❤ ከመሞቱ በፊት የሚሞትበት ጊዜ አውቆ መነኰሳቱን ሰበሰባቸውና የወንጌልን ትዕዛዝ ይጠብቁ ዘንድ በሰማያዊ መንግሥት በጎ ዕድልን ርስትንም ከእርሳቸው ጋር ይቀበሉ ዘንድ እንደ ቅዱሳን አባቶች አካሄድ እንዲጓዙ አዘዛቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ ነፍሱን ሊቀበሉ የቅዱሳንን አንድነት ሲመጡ አያቸውና ፈጽሞ ደስ አለው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መነኰሳቱ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወስደው በመዘመርና በታላቅ ምስጋና ገንዘው ቀበሩት እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ከተገነዘበት ልብስ ቆርጠው በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ለሚታመም ሁሉ የሚፈውስ ሆነ የዚህም አባት ዕድሜ ዘጠና ዓመት ሆነ በግቢግ የሚልዋት መኖሪያው እስከ ዛሬ አለች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱሳን_ሰማዕታት_ኮርዮንና_ፊልሞና_አርባ_ወታደሮች፦ የሰማዕትነታቸውም ምክንያት የአክሚም ታላላቆች ከሆኑ ከሰማዕታት ዲዮስቆሮስ፣ ከሰከላብዮስና ከብኑድያስ የተደረገውን ተአምራት በአዩ ጊዜ የወታደርነት የማዕርግ ሽልማታቸውን ጣሉ በመኰንኑ አርያኖስም ፊት ቁመው "እኛ በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ የምናምን በግልጥ ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ። መኰንኑም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጥሏቸው ዘንድ አዘዘ ራሳቸውንም ሲወረውሩ ብዙዎች አዩአቸው ገድላቸውንም እንዲህ ፈጸሙ።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ተጋዳይ_አባት_ቅዱስ_ዘካርያስ፦ ይንም ቅዱስ ከመመንኰሱ በፊት በጐዳና ሲጓዝ አረማውያን በርበር ተነሡበትና ያዙት ሊያርዱትም ወደዱ በእግዚአብሔርም ፍቃድ የገዳሙ አለቃ በዚያች ጐዳና ሲያልፍ በላያቸው ጮኸ እነርሱም ሠራዊት እንደደረሰባቸው ተጠራጠሩ ፈርተውም ሸሹ ሲሸሹም ከባሕር ገብተው ሰጠሙ። ቅዱስ ዘካርያስም ከመገደል በዳነ ጊዜ ይሸጥ ዘንድ ገንዘባቸውን ይዞ ወደ ከተማ ገባ የአገሩም ገዥ ያዘው ሌባ እንደ ሆነ አስቦ ሊገለው ወደደ ግን ሥራውን በአወቀ ጊዜ ተወው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አባ ጳኲሚስ ገዳም ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ ሰይጣንም እስከ ቀናበት ድረስ በጾምና በጸሎት ተጠመደ ከዚህም በኋላ በአባቱ ተመስሎ በሕልም ታየውና "መሞቻዬ ጊዜ ደርሷልና ትቀብረኝ ዘንድ ና" አለው ቅዱሱም እውነት እንደሆነ አስቦ ወደ አባቱ ሔደ ግን በጤንነት አገኘው። የሰይጣን ተንኰልም እንደሆነ አውቆ ወደ መኖሪያው ተመለሰ ሰይጣንንም ድል እስአደረገው ድረስ በሩን ዘግቶ እየተጋደለ ኖረ።

ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቆሪል ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የአክሚም_ቅዱሳን_ሰማዕታት፦ እነርሱም በከበረ የልደት በዓል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የቊርባን ቅዳሴ አድርገው ተሰብስበው ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመሠዊያው ላይ ሥጋውንና ደሙን ለሕዝቡ ሲያቀብላቸው አዩት። በዚህም ታላቅ ደስታ ውስጥ እያሉ መኰንኑ አርያኖስ መጥቶ ከበባቸው ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብቶ ስማቸው በሕዋፋና ወኒን የሚባል ሁለቱን የሀገር አለቆች ይዞ ራሳቸውን በሰይፍ ቆረጠ። ❤ ከዚህም በኋላ ቀሳውስትን ዲያቆናትን ንፍቀ ዲያቆናትን መምህራንን የቤተ ክርስቲያንን ሹማምንት ገደለ ደማቸው ከቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ ወጥቶ ሃያ ክንድ ያህል እስቲጎርፍ ወንዶችን ሴቶችንና ልጆችንም ምንም ሳያስቀር አሳረዳቸው። ኤጲስቆጶሱን አባ ብኑድያኖስን ዲዮስቆሮስን ሰከላብዮስን ከኤጲስቆጶሱ ጋር ያሉ መነኰሳትንም እነርሱን እንደታሠሩ አርያኖስ ከእርሱ ጋር ወሰዳቸው እነሆ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ጥር አንድ ቀን ተፅፎአል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ትኑር ዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ29 ስንክሳር።                                       ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ነገሥተ ተርሴስ ወደሰያት አምኃ ያበውዑ። ነገሥተ ሳባ ወዓረብ ጋዳ ያመጽኡ። ወይሰግዱ ሎቱ ኵሎሙ ነገሥተ ምድር"። መዝ71፥10-11። የሚነበበው ወንጌል ማቴ1፥1-18።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥4-12፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥16-22። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ2፥1-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልእ ነው። መልካም የብርሃነ ልደቱ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።                 

❤ ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደገኘ በእስራኤል በበርሃ ውስጥ ከኅቱም ዐለት ውኃ እንደ ፈለቀ የደረቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደአፈራች። በሶምሶንም እጅ ወስጥ ከአህያ መንጋጋ ዐጥንት ውኃ እንደፈሰሰ። እንዲሁ የጌታችን ልደት በህቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደነደደች እጺቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁም የመለኮት እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክል ይገባል ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ኢያሱ_ነቢይ፦እርሱም ከኤፍሬም ወገን  ለእስራኤል ልጆች ከጠላት ሰልፍ መድኃኒት ሁኖ ያዳናቸው ነው። የጌታችንም መወለድ ለአዳምና ለልጆቹ መድኃኒት ሆናቸው። የርሱም የቀድሞ ስሙ ሆሴዕ ነበረ እስራኤልን ከአማሌቅ ጦርነት በራፌድ በአዳናቸው ጊዜ ኢያሱ ተብሎ ተጠራ ይህም አዳኝ ማለት ነው። ❤ ሙሴም ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር መረጠውና ለእስራኤል መስፍን አድርጎ ሾመው ልዩ ከሆኑ አሕዛብም ጦርነት አዳናቸው ርስታቸውንም አወረሳቸው ከዚህም በኋላ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ጻድቅ_ቅዱስ_አቃርዮስ፦ የርሱም ግዛቱ በሶርያ አገር ሰርሜን በምትባል ክፍል ነው እርሷም ሮሀ ናት። ❤ ጣዖትን የሚያመልክ ሆኖ ኖረ መፃጉዕም ነበረ ለባለ መድኃኒቶችም ገንዘቡን ሁሉ ሰጥቶ ሊአድኑት አልቻሉም። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሽተኞችን በማዳን አጋንንትን በማስወጣት የዕውሮችን ዐይኖች በመግለጥ ሙታንን በማስነሣት የሚሠራውን ድንቅ ተአምራቱን በሰማ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደርሱ ላከ። "የሰውን ሥጋ ለብሰህ በኢየሩሳሌም የተገለጥክ የእግዚአብሔር ልጅ ምስጋና ይድረስህ ከእርሱ ሳትለይ ወደታች ለላከህ ለቸር አባትህም ምስጋና ይድረሰው አንተ የምትስተካከለው ክርስቶስ እንደሆንክ በሕሊናየ ለገለጠልኝ መንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን። ያለወንድ ዘር በድንግልና ለወለደችህም እናትህ ምስጋና ይሁን ለሚያምኑብህ ሁሉ ሰላምታ ይድረሳቸው። እኔም በአንተ አምኜ ከንቱ ጣዖትን ከማምለክ አንተን ወደ ማምለክ ተመለስኩ በኔ ላይም ንጉሥ ትሆን ዘንድ ሀገሬንም ትባርክ ዘንድ ከበሽታዬም ታድነኝ ዘንድ ከኃጢአቴም ታነጻኝ ዘንድ ወደኔ ና ጌታዬ ሆይ የከበረ ስምህን አይሁድ ሲጠሉ ለአንተ በኢየሩሳሌም መኖር ምን ያደርግልሃል። በከንቱ ለምን ትደክማለህ መካር ያጡ ወገኖች ናቸውና በቀድሞ ዘመንም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ ከግብጽ አገር በአወጣኻቸው ጊዜ አላመኑብህም በበረሀም አርባ ዓመት መናውን በመገብካቸው ጊዜ ተቆጥተህ ለጥፋት እስከ አደረስካቸው በአንተ ላይ ምን ያህል አጒረመረሙብህ በሚራብና በሚጠማ ምድራዊ ሥጋማ ሲያዩህ እንዴት ነዋ ኀሳባቸው ከዚህ የተለየ ይመስልሃልን አንተ ከጥንት ጀምሮ የተሠወረውን ታውቃለህና ። ይኸንንና ይህን የመሰለውን ጽፎ ደብዳቤ ወደርሱ ላከ። ❤ የንጉሥ መልክተኞችም ወደ ጌታችን በደረሱ ጊዜ ሳይነግሩት የመጡለትን መልእክት አውቆ ነጭ ልብስ አንሥቶ ፊቱን አሸበት የፊቱም መልክ ወደ ልብሱ ገባ ከደቀ መዝሙሩ ከታዴዎስ ጋር እንዲህ ብሎ ላከለት ይህን የኔ መልክ የሆነውን ሥዕል ተቀበል እርሱም የምትሻውን ሁሉ ይፈጽምልሃል ከበሽታህም ይፈውስሃል ሀገርህንም ይባርካል መንግሥትህንም ያጸናል ይህ ሥዕል እኔን ነውና ይለወጥ እንደሆነ በውኃ በእሳት ፈትነው። መልክተኞችም ወደ ንጉሥ አቃርዮስ በደረሱ ጊዜ ያንን ሥዕል ሰጡት በእሳትና በውኃም ፈተነውና ምንም ምን ጥፋት አልደረሰበትም የሮሀ አገር ሰዎችም ከንጉሣቸው ጋር በጌታችን የመለኮት ሥልጣን አመኑ ይህ ሥዕል ቊጥር የሌለው ብዙ ድንቅ ተአምራትን አደረገ ንጉሡንም ከበሽታው ፈወሰው ከዚህም በኋላ ዕድሜውን ሲፈጽም በዚች ዕለት ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን።                         ✝️✝️✝️ ❤ #ቅዱስ_ቆሪል_ገመላዊ፦ እርሱም በጾም በጸሎት ተወስኖ የሚኖር ነው እግዚአብሔርም የተሰወሩ ምሥጢራት ማወቅን ሰጠው የሚገለገልባቸው ከማሳም ተልባ የሚጭንባቸው ሦስት ግመሎች አሉት። ❤ ፈራጉን በሚባል አገር ለእመቤታችን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት የሆነ አንድ ሰው ነበረ ቤተ ክርስቲያኒቱም ነገሥታትና መኳንንት በየጊዜው የሰጧት ብዙ ገንዘብ አላት በሊቀ ካህናቱም ዘንድ የዕቃው ሣጥን በሥውር ይኖር ነበር የዚያንም ዕቃ ቊጥር ኤጲስቆጶሱ ያውቃል ያ ሊቀ ካህናት በእርሱ ሥልጣን ሥር ነበርና ከዚህም በኋላ የዕቃው ሣጥን ያለበትን ለልጁ ሳይነግር ያ ሊቀ ካህናት በድንገት ሞተ። ❤ ኤጲስቆጶሱም የሊቀ ካህናቱን ሞት በሰማ ጊዜ ወደዚያች ቤተ ክርስቲያን መጥቶ ከልጁ ገንዘቧን ፈለገ ያም ልጅ አባቴ በድንገተኛ ሞት ስለተነጠቀና ስለ አልነገረኝም ዕቃው ያለበትን አላወቅሁም አለው። ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ ተቆጣ ሊአሠቃየውም ፈለገ ያም ልጅ ኤጲስቆጶሱን ዕቃው ያለበትን ቦታ እስከምፈልግ ድረስ ቆየኝ ባላገኘሁትም ጊዜ የወደድከውን ታደርግብኛለህ ብሎ ለመነው እርሱም ጊዜ ሰጠው። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ችግሩን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት። እርሷም በእግዚአብሔር ታምነህ በአባ መቃርስ ገዳም ወዳሉ አባቶች መነኰሳት ወደ ጎረቤቶቻቸውም ሒድ እነርሱ ይነግሩሃልና አለችው። ወደዚያም ሲደርስ ችግሩን ይፈጽሙለት ዘንድ ለመነኰሳቱ ነገራቸው የሚነግረውም አጥቶ ተስፋ ቆረጠ። አንድ ባሕታዊም ጠቀሰውና እንዲህ አለው "ሰምኑድ ወደሚሉት አገር ሒደህ ስለ ባለ ግመሉ ቆሪል ጠይቅ በእርሱም ዘንድ እደር እርሱም ይነግርሃል" አለው። ❤ ወደ ሰምኑድ መንደርም ደርሶ ስለርሱ ስለቆሪል ጠየቀ ሰዎችም ነገሩት ያለበትንም አመለከቱት በሔደ ጊዜም ከመኖሪያው አገኘው ሦስቱ ግመሎቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አባ ቆሪልም ፍላጎቱን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ማደሪያው አስገብቶ መብልን አቀረበለት "አባቴ ሆይ ችግሬን ሳትፈጽምልኝ እኔ አልበላም" አለው ቆሪልም "ችግርህ በጊዜው ጊዜ ይፈጸማልና አሁን ብላ" አለው። ከራትም በኋላ በየመኝታቸው ተኙ የሌሊቱም እኩሌታ ሲሆን ያ ሰው ቆሪልን ከግመሎቹ ጋር ቁሞ አየው ሲሰግድ ይሰግዳሉ ሲቆምም ይቆማሉ። በነጋ ጊዜም ተልባ ይጭንባቸው ዘንድ ወደ ማሳ ወሰዳቸው ያም ሰው ሊራዳው አብሮ ሔደ ወደ ማሳውም በደረሱ ጊዜ ቆሪል በግመል ላይ መጫን ጀመረ ያም ሰው ሁለተኛውን ገመል ወስዶ ያለ አቅሙ ሸክሙን አክብዶ ጫነው ገመሉም መንቀሳቀስ ተሳነው ሊመታው ፈልጎ በትር አነሣ።ገመሉም "አባቴ ቆሪል ሆይ በላዬ ጉዳት እንዳያደርስ ይህን ሰው አታሰናብተውም እርሱ ያለ ችሎታዬ አሸክሞኛልና" ብሎ በሰው አንደበት ጮኸ ቆሪልም መጥቶ ሸክሙን አቀለለለት ያንንም ሰው "ልጄ ሆይ በማይችለው መጠን ለምን አሸከምከው አንተ የምትአዝነው ልትሸከመው የማትችለውን ሸክም በላይህ ስለ አመጡብህ አይደለምን" አለው። ❤ ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ያ ሰው ስለ ችግሩ የዕቃውን ቦታ ይገለጥለት ዘንድ አባ ቆሪልን ለመነው እርሱም ለሌላ እንዳይናገር ከአማለው በኋላ ገለጠለት እንዲህም አለው "በዚያች ቤተ ክርስቲያን በስተ ምሥራቅ ታናሽ ዋሻ አለ ዕቃውም በዚያ አለ"። ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ለሚስቱ ነገራት በአንድነትም ወደዚያ ቦታ ሔዱ ከነገሥታት መዛግብት እንኳ የሚመስለው የሌለ መዝገብን አገኙ ከዚህም በኋላ ለኤጲስቆጶስ ነገረው ኤጲስቆጶሱም ይጠብቅ ዘንድ ለርሱ ስጠው። ይህም ጻድቅ ሰው ቆሪል ብዙ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ በመልካም ሽምግልና ዐረፈ። ለእግዚአብሔር

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም_በሥጋ_ለተወለደበት የበዐላት ሁሉ ራስ ለሆነች #ለብርሃነ_ልደቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በእዚህች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኤፍሬም ወገን ከመስፋኑ #ከቅዱስ_ኢያሱ_ልደት፣ #ከከበሩ_ከያዕቆብ_ከፈሊስ ከሌላው ሰማዕት፣ #ከቴዎድሮስ ከመታሰቢያቸው፣ #ከሮሀ_ንጉሥ_ከአቃርዮስ ዕረፍት፣ ሰምኑድ ከሚባል አገር ከሆነ ከገመላዊው #ከቅዱስ_ቆሪል ዕረፍትና #ከአክሚም_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                                                   ✝️ ✝️ ✝️ ❤ በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ #ታላቅ_የልደት_በዓል_ሆነ_የጌታችንና_የመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን_ከከበረች_ድንግል_ማርያም_የተወለደባት ዕለት ከበዓላት ሁሉ ተለይታ ከፍ ከፍ ያለች ናት። ❤ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን የከበረ የልደትን በዓል በሁለት ቀኖች ያከብሩ ዘንድ በምክራቸው ተስማሙ ከወደኋላ ባለ በሃያ ስምንት ሌሊቱ የልደት በዓል ነው በሃያ ዘጠኝ መዓልቱ ጳጒሜን ስድስት በሆነ ጊዜ በዚያች ዓመት የልደት በዓል በሃያ ስምንት ከሆነ ግን በሃያ ዘጠኝ ይሆናል ስለዚህ የበዓላት ሁሉ ራስ የሆነ የከበረ የልደት በዓል በሁለት ቀኖች እንዲከበር አዘዙ ወሠኑ። ❤ የበዓላት ራስ ስለሆነ ስለ ከበረ የልደት በዓል የከበረ ወንጌል እንዲህ አለ "በንጉሥ በኄሮድስ ዘመን በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ጌታ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ እነሆ የፍልስፍና ሰዎች ከምሥራቅ መጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ። ኮከብን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ። እሊህ ፈላስፎች ከበለዓም ወገን ናቸው እነርሱም በከዋክብት የሚፈላሰፉ ናቸው በመጽሐፋቸው በበለዓም መጽሐፍም የአይሁድ ንጉሥ ሊወለድ እንዳለው ተጽፎአል እርሱ በለዓም ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤልም ንጉሥ ብሎ ነበርና። ❤ ይቅር ባይ እግዚአብሔር በረቀቀ ጥበቡ አለበማቸው በሚያምኑበትም ሳባቸው እነርሱ ከዋክብትን በመጠባበቅ የሚፈላሰፉ ናቸውና ይህንንም ኮከብ ገለጠላቸው በአዩትም ጊዜ ደስ አላቸው መልኩ በብዙ አይነት ልውጥ ነውና። ሕፃን የታቀፈች ድንግል ብላቴናን ይመስላል እርሱም በቀን ይጓዛል በሌሊትም ይሠወራል ከሰውም ሲገናኙ ይሠወርና ሲቆሙ በሌላ አንጻር ይገለጥላቸዋል። ❤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ያ ኮከብ ተሠወራቸው እጅግ አዘኑ የሚያድረጉትንም አላወቁም ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብተው ስለተወለደው ንጉሥ ጠየቁ። የእሊህም ሰዎች ቊጥራቸው ሠላሳ ሽህ ነው ነገሥታቱ ሦስት ናቸው ለእያንዳንዳንዱ ንጉሥ ዐሥር ዐሥር ሺህ ሠራዊት አለው። ንጉሡ ኄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ ኢየሩሳሌምም በመላዋ ከእርሱ ጋር ደነገጠች። የካህናት አለቆችና የሕዝቡን ጸሐፊዎች ሁሉ ሰብስቦ "ክርስቶስ በየት ይወለዳል?" ብሎ ጠየቃቸው። "በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ነው" አሉት በነቢይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና። "የኤፍራታ ዕፃ ቤተ ልሔም አንቺም ከይሁዳ ነገሥታት አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ካንቺ ይወለዳልና"። ❤ ከዚህም በኋላ  ኄሮድስ ሰብአ ሰገልን በጭልታ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከነሱ ተረዳ። "ሔዳችሁ የዚያን ሕፃን ነገር እርግጡን መርምሩ ያገኛችሁትም እንደሆነ እኔም መጥቼ እሰግደለት ዘንድ በኔ በኩል ተመልሳችሁ ንገሩኝ" ብሎ ወደ ቤተልሔም ሰደዳቸው የነገራቸውንም ሰምተው ከንጉሡ ሔዱ እነሆ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ወደ ቤተልሔም እስኪያደርሳቸው ይመራቸው ነበር ሕፃኑ ካለበትም ዋሻ ላይ ደርሶ ቆመ። ኮከቡንም ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር አገኙት ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥናቸውንም ከፍተው ወርቅ ከርቤ ዕጣን እጅ መንሻ አቀረቡለት። ❤ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕፃኑ ጌታ ኢየሱስ በዚያች ዕለት ወደ ቤተልሔም መጡ ስለዚህም ሰብአ ሰገል አገኙአቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ናዝሬት በሌላ ቦታ አላደገምና ከተወለደም ዕድሜው ሁለት ዓመት ሁኖት ነበር። አምላክ ነውና ስለ መንግሥቱ ወርቅን ገበሩለት ክህነትም ገንዘቡ ነውና ዕጣንን ገበሩለት ማሕያዊ ለሆ ሞቱ ምልክትም ከርቤን ገበሩለት። ወደ ኄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ነገራቸው በሌላ መንገድም ወደ አገራቸው ተመልሰው ገቡ። አምላክ በሥጋ ስለመገለጡ ዓዋጅ ነጋሪዎችና ሰባኪዎች ሆኑ። ❤ ይችም ዕለት ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ስለርሷ የተናገረላት ናት እንዲህ ብሎ "እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው"። ስለዚችም የከበረች ድንግል ነቢይ ሕዝቅኤል እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "እግዚአብሔርም አለኝ ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች አትከፈትም የሚገባበትም የለም የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደተዘጋች ይገባባታልና ተዘግታ ትኑር" አለ። ❤ ነቢዩ ዳንኤልም አለ "ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቁ እንደ ሰው ልጅ በሰማይ ደመና መጣ ዘመኑን ወደ ሚያስረጅ ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነው። ❤ ዳግመኛም ኢሳይያስ "እግዚአብሔር እንደእኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጸልኝ" አለ። "አሁኑም ደግሞ አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ" አለ ሁለተኛም "ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል" አለ። ዳግመኛም "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው። ስሙም ድንቅ መካር የዘላዓለም አባት የሰላም አለቃ ይባላል" አለ። ❤ ኤርምያስም አለ "እግዚአብሔር እንዲህ አለ ለዳዊት ብርሃንን አወጣለሁ በምድር የቀና ፍርድ ያደርጋል እግዚአብሔር ያመኑበትን ያድናቸዋል"። ኤልሳዕም እንዲህ አለ "እግዚአብሔር ከሰማ ይወርዳል በእስራኤል ልጆች አደባባይም በመመላለስ ለሕዝቡ እውነትን ያስተምራቸዋል ከአብርሃም ልጅነት ልዩ ከሆነች ወገኖቹ በቀር አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል"። ናሆም ነቢይም እንዲህ አለ "እግዚአብሔር በእኔ አርአያ ይመጣል ልብሱም እንደ ልብሴ ነው"። ❤ ነቢዩ ኢዩኤልም እንዲህ ተናገረ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆነች ብላቴና ድንግልን አየሁ እርሷም እንደ እሳት ያልባት ነበር ስለርሷም ይቺ ማናት ብዬ ኪሩብን ጠየቅሁት ከአዳም ልጆች የተመረጠች የእግዚአብሔር ዙፋን ይች ድንግል ናት በርሷም የተጎሳቈሉ ይድናሉ ለአመነባትም ረድኤትና መጠጊያ ናት። ❤ ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ አለ "እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ በተዋሕዶም ወለድኩህ አለኝ። ለምን አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው"። ዳግመኛ "አብ አለ ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ከአንተ ጋር ሳለሁ ከአጥብያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ እንደ መልከጼዴቅ አንተ የዓለም አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ ከማለም አይፀፀትም"።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤         ❤ #ታኅሣሥ ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን #ለቅዱስ_አማኑኤል_ለልደቱ (ለጌና) መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእንዴናው_አገር_ሰዎች ከሆኑ በሰማዕትነት ካዐረፉ #ከመቶ_ሃምሳ_ወንዶችና #ከሃያ_አራት_ሴቶች፣ ከአባቶቻች #ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                       ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #በዚች_ዕለት_የጌና_በዓል_ሆነ፦ ይኸውም የልደት በዓል ነው”።  ይህም እንዲህ ነው በአምላካችን በረቀቀ ጥበቡ ሰዎች ሁሉ ይቈጠሩ ዘንድ ስማቸውንም ይጻፋና ይመዘገቡ ዘንድ ከንጉሥ ቄሣር ትእዛዝ መጣ። ስለዚህም ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል ማርያም ጋር ሊቆጠር ዮሴፍ ከናዝሬት ወደ ቤተልሔም የርሱንና የቡርክት ድንግል ማርያምን ስም ሊስመዘግብ ወጣ እርሱ ከይሁዳ ነገድ ከዳዊት ወገን ነውና ቤተልሔምሜ የዳዊት ቦታው ናትና። ❤ የከበረ ወንጌል እንደተናገረ ከዚህም በኋላ ከዚያ ሳሉ የምትወልድበት ቀን ደረሰ የበኵር ልጇንም ወለደች አውራ ጣቱንም አሠረችው በጨርቅም ጠቅልላ በበረት አስተኛችው ለማደሪያቸውም ቦታ አልነበራቸውምና። በዚያ ሰፈር እረኞች ነበሩ ሌሊትም በየተራቸው ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ነበር። እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ አጠገባቸው ቆመ የእግዚአብሔርም ብርሃን በላያቸው በራ ታላቅ ፍርሀትም ፈሩ መልአኩም "ለእናንተና ለመላው ዓለም ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ" አላቸው። ❤ "እነሆ ዛሬ በዳዊት አገር መድኅን የሆነ ጌታ ክርስቶስ ተወልዶላችኋልና። ለእናንተም ምልክት እንዲህ ነው ሕፃኑ አውራ ጣቱን ታሥሮ በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ" አላቸው። ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም በሰው በጎ ፈቃድ እያለ መጡ። ❤ ከዚህም በኋላ መላእክት ከእነርሱ ዘንድ ባረጉ ጊዜ እነዚህ እረኞች ሰዎች እርስበርሳቸው "ኑ ወደ ቤተ ልሔም ሔደን ይህን እግዚአብሔር የገለጠውንን ነገር እንወቅ" አሉ። ፈጥነውም ሔዱ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በበረት ውስጥ ተኝተ አገኟቸው። አይተውም የነገሩዋቸው ስለዚህ ሕፃን እንደሆነ አወቁ እረኞች የነገሩዋቸውን የሰሙ ሁሉ አደነቁ። እረኞችም ለሕፃኑ ሰግደው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቦታቸውም ተመለሱ። ከወገኖችን ሰው ሁኖ ለጐበኘንና ይቅር ላለን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 28 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ከእንዴናው_አገር_ሰዎች_የሆኑ #መቶ_ሃምሳ_ወንዶች_ሃያ_አራት_ሴቶች_በሰማዕትነት፦ እሊህም ቀድሞ ከሀዲያን ነበሩ የእንዴናው መኰንን የከበረ ሶርያዊ ጳውሎስን በሚያሠቃየው ጊዜ ከዚያ ነበሩ ሲአሠቃየውም ይመለከቱ ነበር መኰንኑም ችንካሮችን በእሳት አግለው ዐይኖቹን እንዲአወልቁ አዘዘ። ይህንንም ባደረጉበት ጊዜ ዐይኖቹ ወለቁ ከወህኒ ቤትም ጣሉት። በማግሥቱም እሊህ ሰዎች ሊያዩት በሔዱ ጊዜ ያለ ምንም ጉዳት ድኖ ጤነኛ ሁኖ አገኙት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አድኖታልና ። ❤ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው እጅግ አደነቁ ጣዖቶቻቸውም ምንም መሥራት እንደማይችሉ አስተዋሉ። የክርስቲያኖች አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ አወቁ ወደከበረ ጳውሎስ ሒደው ሰገዱለት እንዲጸልይላቸውም ለመኑት እርሱም ባረካቸው እግዚአብሔር እምነታችሁን ተቀብሎ ከሰማዕታት ጋር ይቊጠራችሁ አላቸው ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ራሶቻቸውን ቊረጡ ብሎ አዘዘና ቈረጧቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ109፥3።የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥26-57።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ 71፥15። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥3-18፣ 1ኛ ዮሐ 4፥1-9 የሐዋ ሥራ 3፥22-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ1፥1-18። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አማኑኤል በዓልና የገሐድ ጾም። ለሁላችንም ይሁንልን።               

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን #ለኤጲስ_ቆጶስ_ለአባ_አብሳዴ ለዕረፍት በዓልና #ለቸሩ_መድኃኔዓለም_ለስቅለቱ_መታሰቢያ ወራዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_ፊልጶስና ከሰማዕታት ፍጻሜ ከሆነ #ከኖላዊ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_አብሳዲና_አባ_አላኒቆስ፦ ያን ጊዜ ታላላቆች የሆኑ የላይኛው ግብጽ ኤጲስቆጶሳት አባ አብሳዲና አባ አላኒቆስ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት ሕዝቡን እንደሚያጸኑአቸው የአማልክትንም አምልኮ እንደሚሽሩ ዜናቸውን ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ መልክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጥቶ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው። የከበረ አባ አብሳዲ ግን አንዲት ቀን እንዲታገሡት መልክተኞችን ለመናቸውና የቊርባን መሥዋዕትን አዘጋጅቶ ቅዳሴ ቀድሶ ለሕዝቡ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው። በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አስተማራቸው ከዚህም በኋላ በሰላምታ ተሰናብቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ወጣ ሰውነቱንም በእግዚአብሔር ላይ ጥሎ ከመልክተኞች ጋር ሔደ ወደ እንዴናው ገዥ ወደ አርያኖስ ወሰዱት። ❤ መኰንኑም የአባ አብሳዲን ገጽ በአየ ጊዜ ከአርያውና ከግርማው የተነሣ አደነቀ ራራለትም እንዲህም አለው "አንተ የከበርክና የምታስፈራ ሰው ለነፍስህ እዘን የንጉሥንም ቃል ስማ"። አባ አብሳዲም እንዲህ ብሎ መለሰ "እኔ የንጉሥን ቃል ሰምቼ በዚህ በኃላፊው ዓለም ሕይወት መንግሥት ሰማያትን አልለውጥም" በመካከላቸውም ብዙ የነገር ምልልስ ሆነ ከበጎ ምክሪ ባልተመለሰ ጊዜ በመንኰራኵር ያሠቃዩትና ከእሳት ማንደጃ ውስጥም ይጨምሩት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ ይህን ሁሉ ታገሠ እግዚአብሔርም ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው። ❤ ከዚህም በኋላ ራሱን ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ አባ አብሳዲም ሰምቶ ደስ አለው ልብሰ ተክህኖ ለብሶ እጆቹንም ዘርግቶ አንገቱን ለሰይፍ ሰጠ የከበረች ራሱንም ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አብሳዲ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 27 ስንክሳር።                                                    ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "መላእክትኒ ተጋብኡ ምስሌሆሙ ኅብረ። ላዕለ እግዚአብሔር ወላዕለ መሲሑ። ንበትክ እምኔነ ማዕሠሪሆሙ"። መዝ 2፥2-3። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 16፥21-ፍ.ም።                              ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አንሥእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ። አምላክ ኃያላን ሚጠነ። አብርህ ገጸከ ላዕሌነ ወንድኃን"። መዝ 79፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት 16፥16-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥17-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ በግዑ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) ለሁላችንም ይሁንልን።           

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ከሮሜ_አገር_ለሆነች_ለከበረች_ለቅድስት_አንስጣስያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረች ከሰማዕት #ከቅድስት_ዮልያና ከመታሰቢያዋና #ከጻድቁ_ከቅዱስ_አቦሊ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅድስት_አንስጣስያ፦ የዚችም ቅድስት አባቷ ጣዖትን የሚያመልክ ነው እናቷ ግን ክርስቲያን ናት ይቺንም ቅድስት በወለደቻት ጊዜ አባቷ ሳያውቅ የክርስትና ጥምቀትን በሥውር አጠመቀቻት አውቆ ቢሆን ማጥመቅ ባልተቻላትም ነበር። ከዚህም በኋላ በበጎ አስተዳደግ አሳደገቻት በቀናች ሃይማኖት እስከ አጸናቻት ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማረቻት ጠባይዋን መለወጥ ለማንም አልተቻለውም። ❤ አድጋም አካለ መጠን በአደረሰችም ጊዜ አባቷ እንደርሱ ላለ ከሀዲ ሰው አጋባት እርሷ ግን እጅግ ጠላችው ልትገናኘውም አልፈለገችም በሴቶች ላይ በሚሆነው ግዳጅና አንዳንድ ጊዜም በደዌ የምታመካኝ ሆነች እንዲጠላትና ከእርሷ እንዲለይ ያደፈና የቆሸሸ የተጐሳቈለ ልብስ ትለብስ ነበር። ባሏም ወደ ሥራው ወጥቶ በተሰማራ ጊዜ እርሷም ስለ ቀናች ሃይማኖት የታሠሩ እስረኞችን ትጐበኝ ዘንድ ትሰማራለች ታገለግላቸውና የሚሹትን ትሰጣቸዋለች። ባሏም ይህን የምትሠራውን በአወቀ ጊዜ ወደ ውጭ እንዳትወጣ በቤት ውስጥ ዘጋባት እርሷም ከእጁ ያወጣት ዘንድ አዘውትራ በመረረ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር የምትለምን ሆነች ጌታችንም ልመናዋን ሰምቶ ያንን ሰው አጠፋው። እርሷም በሞቱ ደስ አላት ከዚህም በኋላ ለድኆችና ለምስኪኖች ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመታመን ለታሠሩ እሥረኞች ገንዘቧን ሁሉ ሰጠች። ❤ የሮሜ አገር ገዢም ዜናዋን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣት ስለ ሃይማኖቷም ጠየቃት ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ ታመነች ቃል ኪዳን በመግባትም ተናገራት ከበጎ ምክርዋ አውጥቶ ወደ ክህደት ሊያዘነብላት አልቻለም። በዚያንም ጊዜ በብዙ በተለያየ ሥቃይ አሠቃያት። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ባሕር ያሠጥሟት ዘንድ አዘዘ ባሕሩም በሕይወቷ ተፋት ዳግመኛም በአራት ካስማ መካከል አስተኝተው ዘርግተው አሥረው ታላቅና ጽኑዕ የሆነ ግርፋትን ይገርፋዋት ዘንድ አዘዘ መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባት ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባትም። ከዚህም በኋላ ወደ አዘጋጁላት የእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጨምርዋት ዘንድ አዘዘ በጨመርዋትም ጊዜ ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊል ተቀበለች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አንስጣስያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ  26 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለአንስጣስያ_ጣዖታ_አቡሃ_መኒና። እንተ ተለወት ፍጹመ ሃይማኖተ እማ ክርስትና። እስከ መኰንን ዕልው በዋዕየ እሳት አርሰና። ወሰላም ካዕበ #ለብፅዕት_ዮልያና። ዘተሳተፈት ክብረ ሰማዕት አሐደ ከዊና"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_26።                 

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤          ❤ #ታኅሣሥ ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት #በተወለዱ_በሦስት_ቀናቸው_ቅድስት_ሥላሴ ላመሰገኑበት ዓመታዊ ክብረ በዐል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን። በዐሉ የታላቁ ገዳም የደብረ ሊባኖስ አባቶችን ወደ ኢቲሳ ደብረ ጽላሽ ወርደው በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #አባታችን_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ቅድስት ሥላሴ እንዳመሰገኑ፦ ...   "ይህም እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችውም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው ቀን በዕለተ ሰንበት ማለት ነው። ከቀኑ በሦስት ሰዓት ይህ ብላቴና እጆቹን አንሥቶ ወደ ሰማይ ተመልክቶ እግዚአብሔርን በማመስገን እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ "ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በባሕርይ በህልውና አንድ የሚሆን አብ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በባህሪይ በሕልውና አንድ የሚሆን ወልድ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከወልድ ጋር በባህርይ በሕልውና አንድ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ አመሰገነ። ❤ በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወደደበት ስለሚወርድ ሕፃኑም መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ አይቶ እሱ እንዳስተማረው ለፈጣሪው እየተገዛ ይህን ሦስት የምስጋና ቃል አቀረበ። እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ልዩ ምስጋና ሰምታ በልቡናዋ እያደነቀች "ልጄ ፍሥሐ ጽዮን ምን ትላለህ ይህ ቃል የአባትህ ሥራ ነው። ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት ነውና"። ባሏ ጸጋ ዘአብ ተመልሶ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ልጁ የተናገረውን ነገር ሁሉ ነገረች። ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀና "ልጄ እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ። በቤተ እግዚአብሔርም እንዲህ እያልክ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለሁ" አለ። ❤ ይህንም ብላቴና መላእክት ክንፋቸውን እየጋረዱ ዘወትር ይመግቡታል። እርሱም ክንፋቸውን ሲጋርዱት ባያቸው ጊዜ ከእነሱ ጋራ ይጫወት ነበር። ሁል ጊዜ ይስቅ ነበር እንጂ ሕፃናት እንደ ሚያለቅሱ አያለቅስም ነበር ቅኖች ሰዎች ዘወትር ደስ ይላችዋልና። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት።                

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለጌታችን_ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ #ለኖላዊ  መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                           ✝ ✝ ✝ ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ በ፪ "#ኖላዊ_ዘመጽአ_ውስተ_ዓለም ወልዱ ወቃሉ #ለእግዚአብሔር፤ ዘወረደ እምላዕሉ በአቅሙ #ክርስቶስ፤ እስመ ውእቱ #እግዚአ_ለሰንበት፤ ይቤሎ #አብ_ለወልዱ_ወልድየ_ንበር_በየማንየ። ትርጉም፦ ወደ ዓለም የመጣው #እረኛ_የእግዚአብሔር_አብ ቃሉና ልጁ ነው ከላይ የወረደውም #ክርስቶስ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው። (ፍጹመ አካል ፍጹመ ክብር ነው) #የሰንበት_ጌታ እሱ ነውና #አብ_ልጁን_ልጄ_በቀኜ_ተቀመጥ_አለው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                                        ❤ " #ኖላዊ_ኄር " ❤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 21 ይህችን ዕለት "ኖላዊ ሔር" ብላ ታከብራለች። ይሕንንም ለሳምንት ያህል ታዘክራለች (ከታኅሣሥ 21-27)። በነዚህ ቀናች እሑድ የዋለበት ቀን ማኅሌት ተቆሞ ኖላዊ ተብሎ ይከበራል። መሠረታዊ መነሻዋም (ዮሐ. 10፥1) ነው። "ኖላዊ" ማለት በቁሙ "እረኛ" ማለት ሲሆን "ሔር" ደግሞ "ቸር-ርሕሩሕ-አዛኝ" እንደ ማለት ነው። ❤ ገጥመን ብንተረጉመው ደግሞ "ቸር እረኛ" የሚል ትርጉምን ይሰጠናል። ከአባታችን አዳም ስህተት በኋላ ተፈጥረው ከነበሩ ችግሮች አንዱ ቸር እረኛ ማጣት ነው። እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ። ቸር እረኛ ሆኖ በገነት አሰማርቶት ነበር። ❤ ኤዶም ገነት የለመለመች። ፈሳሾች የሞሉባት መልካም መስክ ናትና። አባታችን ቅዱስ አዳም ደግሞ እንደ አቅሙ የጸጋ እረኝነት ተሰጥቶት ነበር። ድቀት ካገኘው በሁዋላ ግን ከነፍስ እረኛው ጋር ተጣልቶ ከመልካሟ መስክ ገነት ወጣ። ❤ እርሷንና የነፍሱን እረኛ ሲሻም አለቀሰ። ተስፋ ድኅነት ሲሰጠውም ለልጆቹ ነገራቸው። ከዚያም በመንጋው ላይ በአዳም ሴት ተተካ። ከሴ፣ ኄኖስ፣ ከኄኖስ፣ ቃይናን . . . እያለ ከኖኅ ደረሰ። ❤ ከኖኅም በሴም ከአብርሃም፣ ከአብርሃምም በይስሐቅና በያዕቆብ ወርዶ ከሙሴ ደረሰ። ከሙሴም በኢያሱ አልፎ ከነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደረሰ። እነዚህ ሁሉ እረኞች ምንም እንኩዋ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በትጋት ቢሠሩም ሕዝቡን ከሲዖል ማዳን አልቻሉም። ❤ ከሲዖል የሚያድን የነፍስ እረኛ ነውና ያን ጊዜ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የራሱን የአባቶቹንና የልጆቹን ጩኸት ባንድ አድርጐ ጮኸላቸው። "ኖላዊሆሙ ለእሥራኤል አጽምዕ - የእሥራኤል እረኛ ሆይ ስማን!" አለ። (መዝ. 79:1) ❤ ጩኸቱም ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ። ይህንን የሰማ ጌታም በጊዜው ከድንግል ማርያም ተወለደ። በየጥቂቱ አድጐ ቸር እረኝነቱን ገለጠ። መድኃኒታችን እንዳስተማረን እርሱ ቸር እረኛ ነው። ❤ ከእርሱ በፊት የተነሱት ቴዎዳስ ዘግብጽና ይሁዳ ዘገሊላ (ሐዋ. 5፥36, ዮሐ. 10፥8) ሐሰተኛ እረኞች ነበሩ። እርሱ ግን እውነተኛው የበጐች በር ነውና (ዮሐ 10፥7) በእርሱ የሚገቡ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛሉ። ❤ እርሱ እውነተኛ እረኛ ነውና (ዮሐ 10፥11) ለመንጋው ራሱን አሳልፎ ይሰጣል። በእሥራኤል ባሕል እረኞች ከፊት መንጋው (በጐቹ) ከኋላ ሆነው ይሔዳሉና ገዳይ ቢመጣ መጀመሪያ የሚገድለው እረኛውን ነው። ❤ መድኃኒታችን ክርስቶስ በሞቱ ሕይወትን፤ በመራቆቱ የጸጋ ልብስን፤ በውርደቱ ክብርን: በድካሙ ኃይልን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። የማይሞት ንጉሥ ስለ መንጋው ሞተ። ሰማይን ከነግሡ ምድርንም ከነልብሱ የፈጠረ ጌታ (ዘፍ 1፥1, ዮሐ. 1፥2) ስለ በጐቹ ይህንን ሁሉ ታግሦ ከሲዖል አዳነን። ❤ በሚያርግ ጊዜም በእርሱ ፈንታ ባለ ሙሉ ስልጣን እረኞችን፤ ሐዋርያትን (ዮሐ 21፥15) ሊቃነ ዻዻሳትን (ሐዋ 20፥28) ካህናትን (ማቴ 18፥18) ሾመልን። እነርሱን እረኞች አሰኝቶ እርሱ "ሊቀ ኖሎት-የእረኞች አለቃ" ተባለ። እነርሱም እስከ ዓለም ፍጻም የክርስቶስን መንጋ ሊጠብቁ ስልጣኑም፤ ኃላፊነቱም አለባቸው። (ማቴ 28፥19) ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ፔጅ።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዚህ_ሳምንት_ምስባክ፦ "ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ። ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ። ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ"። መዝ 79፥1። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 13፥16-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥22-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የኖላዊ በዓል፣ ዕለተ ሰንበትና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።               

የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስም በጠራ ጊዜና በንጽሕና ሆኖ የክርስቶስ ሥጋና ደምን በሚቀበል ሰው ላይ ለማደር ሥልጣን የለኝም" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ የሚያስትበትን ሁሉ በዝርዝር ነገረው፡፡ ሊቀ ጳጳሳትን፣ ጳጳሳትን፣ መነኮሳትን፣ መእመናንን፣ ባለትዳሮችን፣ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችና ሕፃናትን…ሁሉንም ነገር እያንዳንዱን በምን በምን እንደሚያስት ሁሉንም ነገር በዝርዝር ነገረው፡፡ ወዲያውም የሰይጣን መልኩ ተለውጦ እንደ እሳት ነበልባል ሲሆን አባ ጳውሊ ተመልክቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ቅጽበት የታዘዘ መልአክ መጥቶ አባ ጳውሊን አበረታው፡፡ ❤ በዚያችም ሌሊት መቅሰፍት ወርዶ በዝሙት ቤት ያሉትን አጠፋቸው፡፡ ከ5 ወንዶችና ከ5 ሴቶች በቀር የተረፈ የለም፡፡ አባ ጳውሊም "ይህን ለምን ታደርጋላችሁ?" ቢላቸው "በየወሩ አንዲት ቀን ወደ ውሽባ ቤት እየገባን በሩን ዘግተን መብራት አጥፍተን ከእጃችን የገባችዋን ሴት ይዘን አንተኛለን" አሉት፡፡ "ከእናንተ ውስጥ እኅቱን ወይም ልጁን እንዴት ያውቃል?" አላቸው፡፡ "እንደ እንስሳ በመሆን እንጃ ማወቅ የለም" አሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን የክርስቶስን ወንጌል ሰበከላቸውና አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ ሥጋ ወደሙንም አቀበላቸው፡፡ በሃይማኖት ካጸናቸው በኋላ ወደ በዓቱ ተመልሶ ገድሉን ፈጽሞ ታኅሣሥ 24 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጳውለመ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ፊሎንጎስ፡- ይኽም ቅዱስ አስቀድሞ ሚስት አግብቶ አንዲት ልጅ ወለደ፡፡ ከዚህም በኋላ ሚስቱ ሞተች፡፡ እርሱም ከዚህ በኋላ የምንኩስና ልብስ ለብሶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ኖረ፡፡ ስለ መልካም ተጋድሎውትና ስለ ትሩፋቱ በአገልግሎትም ስለመጠመዱ በአንጾኪያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠው፡፡ በተሾመም ጊዜ የክርስቶስን መንጋዮች ምእመናንን በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው፡፡ ከአርዮሳውያን ከመቅዶንዮስና ከሰባልዮስ ነጣቂ ተኩላዎች በሚገባ ጠበቃቸው፡፡ በሊቀ ጵጵስናውም የሹመት ወቅት አኗኗሩን እንደ መላእክት አደረገ፡፡ መልካም የሆነ ገድሉንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ24 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አድኅነኒ እምደም እግዚአብሔር አምላክ መድኃኒትየ። ይትፌሣሕ ልሳንየ በጽድቀ ዚአከ እግዚኦ። ትከሥት ከናፍርየ ወአፉየ ያየድዓ ስብሓቲከ። መዝ50፥14-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ11፥25-ፍ.ም።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ። በእንተ ጸላኢ። ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ"። መዝ 8፥2። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 4፥11-17፣ 1ኛ ጴጥ 1፥13-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 19፥11-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ18፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደት በዓል፣ የቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ የዕረፍቱና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።