ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
前往频道在 Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
显示更多611
订阅者
-124 小时
-17 天
-1030 天
帖子存档
❤ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ተቆጣ ከሥጋው ምንም ምን ሳያስቀሩ ይበሉት ዘንድ ሁለት የተራቡ አንበሶችን በላዩ እንዲሰዱ አዘዘ። የከበረ አግናጥዮስም አንበሶች ወደርሱ ሲቀርቡ በአያቸው ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሕዝብን እንዲህ አላቸው "ከዚህ የተሰበሰባችሁ እናንተ የሮሜ ሰዎች ቃሌን ስሙ እወቁም እኔ ይህን ሥቃይ የታገሥኩት በትዕቢትና በትምክህት አይደለም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታዬና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እንጂ። አሁንም እኒህ አንበሶች እንደ ሥንዴ ይፈጩኝ ዘንድ ነፍሴ ወደደች የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ልትሔድ ነፍሴ ሽታለችና"።
❤ ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ አደነቀ ድንጋጠረም አድሮበት እንዲህ አለ "የክርስቲያኖች ትዕግሥታቸው ምን ይብዛ ስለ አምልኮት ከአረማውያን በእንዲህ ያለ ሥቃይ ላይ የሚታገሥ ማን ነው" አለ። እነዚያ አንበሶችም ወደ ቅዱሱ ቀረብ ብለው ደንግጠው ቆሙ። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ እጁን ዘርግቶ አንገቱን ያዘው በዚያንም ጊዜ ደስ ብሎት ነፍሱን በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ ልመናውንም ፈጸመለት።
❤ ለእነዚያ አንበሶችም ሥጋውን ይዳስሡት ዘንድ አልተቻላቸውም የክብር ባለቤት ክርስቶስ ዳግመኛ እስከ ሚመጣ የተጠበቀ ሆነ እንጂ ከዚህም በኋላ በክብር በምስጋና ከከተማ ውጭ ቀበሩት እንደዚህም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመልካም ተጋድሎ ምስክርነቱን ፈጸመ ለምእመናንም ጠቃሚ ይሆን ዘንድ ገድሉን ጻፉ የበዓሉንም መታሰቢያ አደረጉለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ በቅዱስ አግናጥዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአሚናዳብ_ልጅ_ቅድስት_አስቴር፡- የአይሁድ ወገን የሚሆን ስሙ መርዶክዮስ የሚባል የኢያኤሩ ልጅ ከብንያም ወገን የተወለደ የቄስዩ ልጅ አንድ ሰው በሱሳ አገር ነበረ፡፡ ከኢሩሳሌምም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ የተማረከ ነው፡፡ ያሳደጋት ልጅ ነበረችው፡፡ እርሷም የአባቱ ወንድም የአሚናዳብ ልጅ አስቴር ናት፡፡ ከዘመዶቿ ተለይታ በወጣች ጊዜ ልጅ ትሆነው ዘንድ አሳደጋት፡፡ እርሷም እጅግ መልከ መልካም ነበረች፡፡ በአንዲትም ዕለት ንጉሥ አርጢክስስ ብዙ ተድላ ደስታ አድርጎ መኳንንቶቹን ሁሉ ጠራ፡፡ የመኳንንቶቹንም አለቃ አማሌቃዊውን ሐማንንም ጠራው፡፡ እርሱ ከሁሉም መኳንንት የከበረ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሥ 7ቱን ባለሟሎቹን ጠርቶ ንግሥቲቱን አስጢንን አምጥተው የእቴጌነት ዘውድ ያቀዳጇት ዘንድ እርሷ መልከ መልካም ናትና ለአሕዛብም አለቆች ሁሉ መልኳንና ውበቷን ያሳዩ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ ንግሥቲቱ አስጢን ግን የንጉሡን ትእዛዝ ባለመቀበል እምቢ አለች፡፡ ከባለሟሎቿም ጋር ትመጣ ዘንድ ባለወደደች ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተናዶ ከንግሥትነቷ ሻራት፡፡ ከዚህም በኋላ 127 ከሚሆኑ ከሚገዘቸው አገሮች አንድ ሺህ ቆነጃጅቶችን ይመርጡለት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ ከሺህ መቶ፣ ከመቶ ዓሥር፣ ከዓሥር ሦስት መረጡ፡፡ ከሁሉም በመልክ፣ በውበት፣ በደም ግባትም አንደኛ ሆና አስቴር ተመረጠች፡፡ ንጉሡም አስቴርን አነገሣት፡፡
❤ ንጉሡም አስቴርን እጅግ አድርጎ ወደዳት፣ በሴቶቹም ሁሉ ላይ የበላይ አድርጎ ሾማት፡፡ ከዚህም አስቀድሞ መርዶክዮስ አገሩንና አደባባዩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ ባለሟሎች ጋር በአደባባይ ኖረ፡፡ እነርሱም ስማቸው ታራ እና ገቦታ ይባላል፡፡ እርሱም እነዚህ ሁለቱ በንጉሡ ላይ ያሰቡትን ተንኮላቸውን ሰማ፡፡ ንጉሥ አርጤክስስን ይገድሉት ዘንድ ወንጀልን እንዳዘጋጁ ባወቀ ጊዜ መርዶክዮስ ሄዶ ለንጉሡ ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገራቸውን መርምሮ ቀጣቸውና ይህን ነገር ታሪክና ወግ በሚጻፍበት ላይ ጻፈው፡፡ ሐማ ግን አማሌቃዊ ነበረና መርዶክዮስንና እስራኤላውያንን ይጠላቸው እጅግ ነበርና የአይሁድን ወገን ሁሉ ለማጥፋት ተነሣ፡፡ መርዶክዮስም ይህንን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀዶ ማቅ ለበሰ፡፡ መርዶክዮስም የሀዘኑን መርዶ ለአስቴር እንዲደርሳት አደረገ፡፡ አስቴርም "እስከ ሦስት ቀን ጹሙ ጸልዩ እኔም ደንገጡሮቼም እንጾማለን" ብላ ላከችለት፡፡ ሱባኤዋንም እንደጨረሰች የማቅ ልብሷን አውልቃ ጥላ ወደ ንጉሡ አዳራሽ በገባች ጊዜ "እስከ መንግሥቴም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁና የሆንሽውን ንገሪኝ" አላት፡፡ በዓልንም አደረገና ሐማንና መኳንንቱን ሁሉ ጠራ፡፡ በበዓሉም ላይ ድጋሚ "ላደርግልሽ ፈቅጂውን ንገሪኝ" አላት፡፡
❤ ንጉሡም ለመርዶክዮስ ውለታ ያደረገለትን ሲያስብ ምንም እንዳላደረገለት ዐወቀ፡፡ ወዲያውም ሐማ መርዶክዮስን በመስቀል ላይ ሰቅሎ ሊገድለው እንደሆነ ተነገረ፡፡ ንጉሡም ሐማን "ንጉሥ የወደደውን ሰው ምን ያደርግለት ዘንድ ይገባል?" አለው፡፡ ሐማም "ይህስ ለእኔ ነው" ብሎ "በክብር ይሾም ዘንድ ሹመቱም አዋጅ ይነገርለት ዘንድ ይገባዋል" አለ፡፡ ንጉሡም ለሐማ ይህን ጊዜ "መልካም ተናግረሃል፣ ለመርዶክዮስ እንዲሁ ይደረግለታል" አለው፡፡ ሐማም የንጉሡን ትእዛዝ ተቀብሎ መርዶክዮስን በፈረስ አስቀምጦ በከተማው በማዞር በክብር መሾሙን በአዋጅ አስነገረለት፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡና አስቴር ለማዕድ አብረው በተቀመጡ ጊዜ ንጉሡ "ጉዳይሽን የማትነግሪኝ ለምንድነው?" አላት፡፡ እሷም ይህን ጊዜ "ንጉሥ ሆይ ዝም ባልኩ በወደድኩ ነበር ነግር ግን ወገኖቼና እኔ ለሞት ተላልፈን ተሰጥተናል" በማለት ሐማ እስራኤላውያንን በአዋጅ ሊያጠፋ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም "ማነው ይህን በማድረግ የደፈረኝ?" አላት፡፡ እሷም ሐማ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም ሐማ መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው መስቀል ላይ ራሱ ሐማን እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ሐማም ተሰቅሎ ሞተ፡፡ የእስራኤል ወገኖችም ሁሉ በጻድቂቱ አስቴር መዳናቸው በእርሷ ተደርጓልና ሁሉም አመሰገኗት፡፡ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ የእስራኤል ወገኖች ሁሉ ድኅነታቸው በእርሷ ተደርጓልና ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ጳውሊ_ዘሀገረ_ሰሎንቅያ፡- ሰሎንቅያ በምትባል በምስር አገር ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ያነጋገሩትና ብዙ ምሥጢርን እንዲናገር ያደረጉት ታላቅ አባት ናቸው፡፡ የሰሎንቅያ አገር ሰዎች የሄሮድስ ወገን የሆኑ ክፉዎች ናቸው፡፡ ከዱሮ ጀምረው ሴቶችና ወንዶች ሆነው በጋራ በአንድነት ወደ አንድ ክፍል ገብተው እንስሳዊ ግብራቸውን ይፈጽማሉ፡፡ ብዙ ሆነው ገብተው በሩን ዘግተው መብራት አጥፍተው በእጃቸው የገባውን ይዘው ያድራሉ፡፡ እኅቱም ትሁን ልጁ ወደዚያ ቤት የገባ ሰው ሌላውን አይለየውም፡፡ ይህም ሰይጣናዊ ተግባራቸው ባሕላቸው ሆኖ በወር አንድ ጊዜ ያደርጉታል፡፡
❤ አባ ጳውሊም ይህን ባየ ጊዜ ስለ ኃጢአታቸው በጣም አዝኖ "ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?" ቢላቸው እነርሱም "አባቶቻችን ያዘዙን ትእዛዝና ባሕላችን ነው" አሉት፡፡ አባ ጳውሊም ወደዚያ ቤት ሲገቡ አይቶ እጅግ በማዘን ወደ ጌታችን ጸለየ፡፡ ጸሎቱንም እንደፈጸመ አንድ ጥቁር ሰው ከዝሙት ቤቱ ዕራቁቱን ሆኖ የእሳት ሰይፍ ተሸክሞ መጣ፡፡ አባ ጳውሊም ካማተበበት በኋላ "አንተ ማነህ? ማንንስ ትሻለህ?" አሉት፡፡ ጥቁሩም ሰው "እኔ ሰይጣን ነኝ፣ አንተ ወደ ጌታህ በለመንህ ጊዜ ላከኝ" አለው፡፡ አባ ጳውሊም "የምታስትበትን ነገር ሁሉ ትነግረኝ ዘንድ እጠይቅሃለሁ" አለው፡፡ ሰይጣንም "የምትሻውን ጠይቀኝ" አለው፡፡ አባም "ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ በሰው ላይ ታድር ዘንድ ምክንያት እንዴት ታገኛለህ?" አለው፡፡ ሰይጣንም "ሰው በእግዚአብሔር ሕግ ጸንቶ ሳለ
ከንቱ የሆነ ጣዖትን ከማምለክ ሰዎችን ስለሳብኳቸውና ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ስለአስገባኋቸው በእኔ ላይ ትቆጣለህን ለረከሱ ጣዖቶችህስ እንድሠዋ ታዘኛለህን እኔ ግን ቃልህን ተቀብዬ ለሰይጣናት አልሠዋም ለእውነተኛ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሠዋለሁ እንጂ" አለው።
❤ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ተቆጣ ከሥጋው ምንም ምን ሳያስቀሩ ይበሉት ዘንድ ሁለት የተራቡ አንበሶችን በላዩ እንዲሰዱ አዘዘ። የከበረ አግናጥዮስም አንበሶች ወደርሱ ሲቀርቡ በአያቸው ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሕዝብን እንዲህ አላቸው "ከዚህ የተሰበሰባችሁ እናንተ የሮሜ ሰዎች ቃሌን ስሙ እወቁም እኔ ይህን ሥቃይ የታገሥኩት በትዕቢትና በትምክህት አይደለም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታዬና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እንጂ። አሁንም እኒህ አንበሶች እንደ ሥንዴ ይፈጩኝ ዘንድ ነፍሴ ወደደች የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ልትሔድ ነፍሴ ሽታለችና"።
❤ ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ አደነቀ ድንጋጠረም አድሮበት እንዲህ አለ "የክርስቲያኖች ትዕግሥታቸው ምን ይብዛ ስለ አምልኮት ከአረማውያን በእንዲህ ያለ ሥቃይ ላይ የሚታገሥ ማን ነው" አለ። እነዚያ አንበሶችም ወደ ቅዱሱ ቀረብ ብለው ደንግጠው ቆሙ። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ እጁን ዘርግቶ አንገቱን ያዘው በዚያንም ጊዜ ደስ ብሎት ነፍሱን በፈጣሪው ክርስቶስ እጅ ሰጠ ልመናውንም ፈጸመለት።
❤ ለእነዚያ አንበሶችም ሥጋውን ይዳስሡት ዘንድ አልተቻላቸውም የክብር ባለቤት ክርስቶስ ዳግመኛ እስከ ሚመጣ የተጠበቀ ሆነ እንጂ ከዚህም በኋላ በክብር በምስጋና ከከተማ ውጭ ቀበሩት እንደዚህም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመልካም ተጋድሎ ምስክርነቱን ፈጸመ ለምእመናንም ጠቃሚ ይሆን ዘንድ ገድሉን ጻፉ የበዓሉንም መታሰቢያ አደረጉለት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ በቅዱስ አግናጥዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአሚናዳብ_ልጅ_ቅድስት_አስቴር፡- የአይሁድ ወገን የሚሆን ስሙ መርዶክዮስ የሚባል የኢያኤሩ ልጅ ከብንያም ወገን የተወለደ የቄስዩ ልጅ አንድ ሰው በሱሳ አገር ነበረ፡፡ ከኢሩሳሌምም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ የተማረከ ነው፡፡ ያሳደጋት ልጅ ነበረችው፡፡ እርሷም የአባቱ ወንድም የአሚናዳብ ልጅ አስቴር ናት፡፡ ከዘመዶቿ ተለይታ በወጣች ጊዜ ልጅ ትሆነው ዘንድ አሳደጋት፡፡ እርሷም እጅግ መልከ መልካም ነበረች፡፡ በአንዲትም ዕለት ንጉሥ አርጢክስስ ብዙ ተድላ ደስታ አድርጎ መኳንንቶቹን ሁሉ ጠራ፡፡ የመኳንንቶቹንም አለቃ አማሌቃዊውን ሐማንንም ጠራው፡፡ እርሱ ከሁሉም መኳንንት የከበረ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሥ 7ቱን ባለሟሎቹን ጠርቶ ንግሥቲቱን አስጢንን አምጥተው የእቴጌነት ዘውድ ያቀዳጇት ዘንድ እርሷ መልከ መልካም ናትና ለአሕዛብም አለቆች ሁሉ መልኳንና ውበቷን ያሳዩ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ ንግሥቲቱ አስጢን ግን የንጉሡን ትእዛዝ ባለመቀበል እምቢ አለች፡፡ ከባለሟሎቿም ጋር ትመጣ ዘንድ ባለወደደች ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተናዶ ከንግሥትነቷ ሻራት፡፡ ከዚህም በኋላ 127 ከሚሆኑ ከሚገዘቸው አገሮች አንድ ሺህ ቆነጃጅቶችን ይመርጡለት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ ከሺህ መቶ፣ ከመቶ ዓሥር፣ ከዓሥር ሦስት መረጡ፡፡ ከሁሉም በመልክ፣ በውበት፣ በደም ግባትም አንደኛ ሆና አስቴር ተመረጠች፡፡ ንጉሡም አስቴርን አነገሣት፡፡
❤ ንጉሡም አስቴርን እጅግ አድርጎ ወደዳት፣ በሴቶቹም ሁሉ ላይ የበላይ አድርጎ ሾማት፡፡ ከዚህም አስቀድሞ መርዶክዮስ አገሩንና አደባባዩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ ባለሟሎች ጋር በአደባባይ ኖረ፡፡ እነርሱም ስማቸው ታራ እና ገቦታ ይባላል፡፡ እርሱም እነዚህ ሁለቱ በንጉሡ ላይ ያሰቡትን ተንኮላቸውን ሰማ፡፡ ንጉሥ አርጤክስስን ይገድሉት ዘንድ ወንጀልን እንዳዘጋጁ ባወቀ ጊዜ መርዶክዮስ ሄዶ ለንጉሡ ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገራቸውን መርምሮ ቀጣቸውና ይህን ነገር ታሪክና ወግ በሚጻፍበት ላይ ጻፈው፡፡ ሐማ ግን አማሌቃዊ ነበረና መርዶክዮስንና እስራኤላውያንን ይጠላቸው እጅግ ነበርና የአይሁድን ወገን ሁሉ ለማጥፋት ተነሣ፡፡ መርዶክዮስም ይህንን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀዶ ማቅ ለበሰ፡፡ መርዶክዮስም የሀዘኑን መርዶ ለአስቴር እንዲደርሳት አደረገ፡፡ አስቴርም "እስከ ሦስት ቀን ጹሙ ጸልዩ እኔም ደንገጡሮቼም እንጾማለን" ብላ ላከችለት፡፡ ሱባኤዋንም እንደጨረሰች የማቅ ልብሷን አውልቃ ጥላ ወደ ንጉሡ አዳራሽ በገባች ጊዜ "እስከ መንግሥቴም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁና የሆንሽውን ንገሪኝ" አላት፡፡ በዓልንም አደረገና ሐማንና መኳንንቱን ሁሉ ጠራ፡፡ በበዓሉም ላይ ድጋሚ "ላደርግልሽ ፈቅጂውን ንገሪኝ" አላት፡፡
❤ ንጉሡም ለመርዶክዮስ ውለታ ያደረገለትን ሲያስብ ምንም እንዳላደረገለት ዐወቀ፡፡ ወዲያውም ሐማ መርዶክዮስን በመስቀል ላይ ሰቅሎ ሊገድለው እንደሆነ ተነገረ፡፡ ንጉሡም ሐማን "ንጉሥ የወደደውን ሰው ምን ያደርግለት ዘንድ ይገባል?" አለው፡፡ ሐማም "ይህስ ለእኔ ነው" ብሎ "በክብር ይሾም ዘንድ ሹመቱም አዋጅ ይነገርለት ዘንድ ይገባዋል" አለ፡፡ ንጉሡም ለሐማ ይህን ጊዜ "መልካም ተናግረሃል፣ ለመርዶክዮስ እንዲሁ ይደረግለታል" አለው፡፡ ሐማም የንጉሡን ትእዛዝ ተቀብሎ መርዶክዮስን በፈረስ አስቀምጦ በከተማው በማዞር በክብር መሾሙን በአዋጅ አስነገረለት፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡና አስቴር ለማዕድ አብረው በተቀመጡ ጊዜ ንጉሡ "ጉዳይሽን የማትነግሪኝ ለምንድነው?" አላት፡፡ እሷም ይህን ጊዜ "ንጉሥ ሆይ ዝም ባልኩ በወደድኩ ነበር ነግር ግን ወገኖቼና እኔ ለሞት ተላልፈን ተሰጥተናል" በማለት ሐማ እስራኤላውያንን በአዋጅ ሊያጠፋ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም "ማነው ይህን በማድረግ የደፈረኝ?" አላት፡፡ እሷም ሐማ መሆኑን ነገረችው፡፡ ንጉሡም ሐማ መርዶክዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው መስቀል ላይ ራሱ ሐማን እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ሐማም ተሰቅሎ ሞተ፡፡ የእስራኤል ወገኖችም ሁሉ በጻድቂቱ አስቴር መዳናቸው በእርሷ ተደርጓልና ሁሉም አመሰገኗት፡፡ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ የእስራኤል ወገኖች ሁሉ ድኅነታቸው በእርሷ ተደርጓልና ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ጳውሊ_ዘሀገረ_ሰሎንቅያ፡- ሰሎንቅያ በምትባል በምስር አገር ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ያነጋገሩትና ብዙ ምሥጢርን እንዲናገር ያደረጉት ታላቅ አባት ናቸው፡፡ የሰሎንቅያ አገር ሰዎች የሄሮድስ ወገን የሆኑ ክፉዎች ናቸው፡፡ ከዱሮ ጀምረው ሴቶችና ወንዶች ሆነው በጋራ በአንድነት ወደ አንድ ክፍል ገብተው እንስሳዊ ግብራቸውን ይፈጽማሉ፡፡ ብዙ ሆነው ገብተው በሩን ዘግተው መብራት አጥፍተው በእጃቸው የገባውን ይዘው ያድራሉ፡፡ እኅቱም ትሁን ልጁ ወደዚያ ቤት የገባ ሰው ሌላውን አይለየውም፡፡ ይህም ሰይጣናዊ ተግባራቸው ባሕላቸው ሆኖ በወር አንድ ጊዜ ያደርጉታል፡፡
ከንቱ የሆነ ጣዖትን ከማምለክ ሰዎችን ስለሳብኳቸውና ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ስለአስገባኋቸው በእኔ ላይ ትቆጣለህን ለረከሱ ጣዖቶችህስ እንድሠዋ ታዘኛለህን እኔ ግን ቃልህን ተቀብዬ ለሰይጣናት አልሠዋም ለእውነተኛ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሠዋለሁ እንጂ" አለው።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ለልደት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ሰሎንቅያ በምትባል በምስ አገር ለሆኑ ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ላነጋገሩ ለታላቁ አባት #ለአባ_ጳውሊ ለዕረፍት በዓል፣ #ለአሚናዳብ_ልጅ_ለጻድቂቱ_ለቅድስት_አስቴር ለዕረፍቷ መታሰቢያና ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎድሮስ_ኃይለ_መነኰስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአንጾክያ አገር ሊቀ ጳጳስ ከከበረ #ከአባት_ፊሎንጎስ ዕረፍት፣ የእግዚአብሔር መልአክ ከነገራቸው #በከዲህ_ከአሉ_ጻድቃን በአንዲት ቀን ዕረፍታቸው ከሆነና #ከአዝቂርም ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአባታችን_የአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ልደት፦ ... ከዚህም ቀጥሎ ከዘጠኝ ወር በኋላ በታኅሣሥ በሃያ አራት ቀን ፍስሐ ጽዮን ተወለደ። በዚያችም ቀን በጸጋ ዘአብ ቤት ታላቅ ደስታ ተደረገ መካን የነበረች ሚስቱ እግዚእ ኃረያ ወንድ ልጅ ወልዳለችና። መልኩ እጅግ ድንቅ ነው እንደ ብርሌ እንደ መስታወት የሚያንጸባርቅ ነው። ቅላቱም እንደ ጽጌ ረዳ ነው ለነዳያንም ግብዣ አድርገው ዋሉ። ለአገራቸውም ሰዎች እንደየማዕርጋቸው ምሳ አደረጉላቸው።
❤ በዓሉንም ካከበሩ በኋላ ለእግዚእ ኃረያና ለጸጋ ዘአብ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን በጐ ሥራውን ሁሉ እያደነቁ ወደ የቤታቸው ተመልሰው ገቡ። ይህም እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችውም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው ቀን በዕለተ ሰንበት ማለት ነው። ከቀኑ በሦስት ሰዓት ይህ ብላቴና እጆቹን አንሥቶ ወደ ሰማይ ተመልክቶ እግዚአብሔርን በማመስገን እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ "ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በባሕርይ በህልውና አንድ የሚሆን አብ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በባህሪይ በሕልውና አንድ የሚሆን ወልድ በአካል በስም ልዩ ነው። ከአብ ከወልድ ጋር በባህርይ በሕልውና አንድ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ አመሰገነ።
❤ በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወደደበት ስለሚወርድ ሕፃኑም መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ አይቶ እሱ እንዳስተማረው ለፈጣሪው እየተገዛ ይህን ሦስት የምስጋና ቃል አቀረበ። እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ልዩ ምስጋና ሰምታ በልቡናዋ እያደነቀች "ልጄ ፍሥሐ ጽዮን ምን ትላለህ ይህ ቃል የአባትህ ሥራ ነው። ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት ነውና"። ባሏ ጸጋ ዘአብ ተመልሶ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ልጁ የተናገረውን ነገር ሁሉ ነገረች። ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀና "ልጄ እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ። በቤተ እግዚአብሔርም እንዲህ እያልክ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለሁ" አለ።
❤ ይህንም ብላቴና መላእክት ክንፋቸውን እየጋረዱ ዘወትር ይመግቡታል። እርሱም ክንፋቸውን ሲጋርዱት ባያቸው ጊዜ ከእነሱ ጋራ ይጫወት ነበር። ሁል ጊዜ ይስቅ ነበር እንጂ ሕፃናት እንደ ሚያለቅሱ አያለቅስም ነበር ቅኖች ሰዎች ዘወትር ደስ ይላችዋልና። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ም16።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ቴዎድሮስ_ኃያል_መነኰስ፦ አገራቸው ሮም ሲሆን በ27 ዓመታቸው በአባ ጳውሊ እጅ መነኰሱ። የታላቁ አባት ጳኲሚስ ረዳት የነበሩ ሲሆን መጽሐፍ ሊቀ ጳጳሳትም ይላቸዋል። የመነኰሳት ቁጥር ከጀመሠሪው ከአባ እንጦስ እስከ ቴዎድሮስን ያለው ትውልድ ይባላል። በድንቅ ተአምረሠታቸው ዓለምን ያደነቃቸው ተሰዓቱ ቅዱሳን የተነሱት በዚህ ጻድቅ መናኝ ጊዜ ስለነበር ከፊሎቹንም ያመነኰሷቸው እሳቸው ናቸው። ይለብሱት የነበረው የብረት ልብስ ነበር።
❤ እንጦስ በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል እጀሰ መነኰሱ፤ እንጦንስም መቃርስን አመነኰሱ፤ መቃርስም ጳኲሚስን አመነኰሱ፤ ጳኲሚስም እኚህን ታላቅ መነኰስ ቴዎድሮስን አመነኰሱ። እርሳቸውም እነ አቡነ አረጋወመንና ሌሎቹንመሰ ቅዱሳን አመነኰሰዋል።
❤ በዐፄ ገላውዲዮስና በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን ወደ አገራችን የገባውን ቅዱስ ገድላቸውን ፊልክሲዮስ፣ ገብረ ክርስቶስ፣ አረጋዊና መንፈሳዊና ማር ይስሐቅ ናቸው የተረጐሙት።ጻድቁ የተወለዱባትን ሮምን በከሃዲነቷ በእጅጉ ይጠሏት ነበር። ሮም የእነ ልዮንን የኑፋቄ ትምህርተሰ ተከትላ ሁለት ባሕሪይ በማለቷ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ሆነው አውግዘዋል። በስማቸው የተሠሩ ቤተ ክርስቲያኖች በጎንደር በትግራይ ሁለት አሉ። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_አግናጥዮስ_ምጥው_ለአንበሳ፦ ይህም ቅዱስ የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙሩ ነው። በስብከተ ወንጌልም በማገልገል ከእርሱ ጋር ብዙ አገሮችን ዙሮ አስተምሮአል ከዚህም በኋላ በአንጾኪያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው በውስጥዋመሰ ሕይወተሰ የሆነ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ብዙዎችንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በትምህርቱም ልቡናቸውን አበራላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ጣዖትን ለሚያመልኩ ስሕተቻተውን በገለጠላቸው ጊዜ ተቆጡ። ወደ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጠራብዮስ ሔደው ከሰሱት እንዲህም አሉት "አግናጥዮስ የአማልክቶችህን አምልከሸ ይሽራል እኮን ሰዎችንም እያስተማረ ክርስቶስን ወደ ማመን ያስገባቸዋል"። በዚያንም ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስመጣውና "አግናጥዮስ ሆይ ለምን ይህን አደረግህ የአማልክቶቼን አምልኮስ ለምን ሻርክ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ አስገብተሃቸዋልና" አለው። አግናጥዮስም "ንጉሥ ሆይ ቢቻለኝስ ያክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ክርስቶስ አምልኮት ባስገባሁህ ነበር" አለው ንጉሡም "ይህን ነገር ትተህ ለአማልክቶቼ ሠዋ አለዚያ በታላቅ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። "በእኔ ላይ የምትሻውን አድርግ እኔ ግን ለረከሱ አማልክቶችህ አልሠዋም ሥቃይህንም እሳትም ቢሆን አንበሳንም ቢሆን አልፈራም ከሕያው ንጉሥ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው። ይህንንም ሲሰማ ንጉሡ ተቆጣ ያሠቃዩትም ዘንድ አዘዘ በተለያዩ በብዙ ሥቃዮችም አሠቀሠዩት በእጆቹም ውስጥ እሳት አድርገው ከእጆቹ ጋር በጉጠት ይዘው አቃጠሉት።
❤ ከዚህም በኋላ በዲንና በቅባት እያነደዱ ጎኖቹን አቃጠሉ በሾተሎችም ሥጋውን ሠነጠቁ። ከማሠቃየትም በደከሙ ጊዜ የሚያደርጉበትን እስከመክሩ ድረስ ከወህኒ ቤት ጨመሩት ብዙ ቀኖችም በዚያ ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ አስታውሱት ከወህኒቤትም አውጥተው በንጉሡ ፊት አቆሙት ንጉሡም "አግናጥዮስ ሆይ አማልክቶቼን ብታያቸው ውበታቸው ባማረህ ነበር" አለው። ቅዱሱም "ንጉሥ ሆይ አንተ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ብታምን ሙታኖችን የምታሥነሣቸው በሽተኞችንም የምትፈውሳቸው ባደረገህ ነበር"። ንጉሡም "ለፀሐይ ከመስገድ የተሻለ የለም" አለ የከበረ አግናጥዮስም "መንግሥቱ የማያልቀውን ፈጣሪ ትተህ ለተፈጠረ ፀሐይ ትሰግዳለህን?" ብሎ መለሰ ንጉሡም "ለራስህ መልካም አልክ ግን በመተላለፍ የአንጾኪያና የሶርያን ሰዎች ስበሕ ወደ ክርስቶስ አምልኮት አስገባሃቸው እንጂ" አለው። የከበረ አግናጥዮስም ተቆጥቶ "ንጉሥ ሆይ
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ለስሒት መኑ ይብልዋ። እምኅቡአትየ አንጽሐኒ። ወእምነኪር መሀኮ ለገብርከ"። መዝ 18፥12-13 ወይም መዝ 88፥19-20። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 2፥8-19፣ 1ኛ ጴጥ 5፥2-8 እና የሐዋ ሥራ 13፥30-44። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 22፥31-46። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ዳዊት የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ ቅዱስ ዳዊትም እጁን ወደ ድጉ ሰዶ አንዲት ደንጊያ አውጥቶ ወነጨፋት ያንንም ኢሎፍላዊ ግንባሩን ገመሰው ያቺም ደንጊያ ከግንባሩ ገብታ ናላውን በጠበጠችው በምድር ላይም በግንባሩ ተደፋ። ዳዊትም ሩጦ የገዛ ሰይፉን አንሥቶ ራሱን ቆረጠው ከእስራኤልም ልጀጆች ስድብን አራቀ። ቅዱስ ዳዊትም መላው ዕድሜው ሰባ ነው መንግሥትን ሳይዝ ሠላሳ ዓመት ኖረ ከያዘ በኋላ አርባ ዓመት ኖረ። የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከመምጣቱ በፊት በሽህ አንድ መቶ ሃያ ዓመት ውስጥ ትንቢት የተናገረበት ዘመን ነው በሰላምም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በልበ አምላክ በቅዱስ ዳዊት በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የከበሩ_ቅዱሳን_አባቶቻችን_አባ ሳሙኤል_አባ_ስምዖንና_አባ_ገብርኤል፡- አባ ሳሙኤል የተባለው ይኽም ቅዱስ ባሕታዊ ሆኖ ቀርጣሚን በምትባል አገር የሚኖር ነው፡፡ በዚያም አቅራፎስ የሚባል ሰማዕት ዐፅም ስለነበር ከእርሱ በረከትን እየተቀበለ እየተሳለመ ይኖር ነበር፡፡ ሰሊባ የሚባል አንድ መኮንን ነበር፡፡ እርሱም ስምዖን የሚባል ልጅ አለው፡፡ ልጁም ለሞት በሚያበቃ ጽኑ ሕማም ታመመ፡፡ መኮንኑ በልጁ ላይ ይጸልይ ዘንድ ወደ አባ ሳሜኤል ላከ፡፡ ነገር ግን አባ ሳሙኤል ሲደርስ ልጁ ሞቶ አገኘው፡፡ አባ ሳሙኤልም በጸሎቱ ከሞት አስነሣው፡፡ ልጁ ስምዖንም ከሞት ከተነሣ በኋላ የአባ ሳሙኤል ደቀመዝሙሩ ሆነ፡፡ ሁለቱም በጋራ በተጋድሎ አብረው ኖሩ፡፡
❤ ቅዱስ ስምዖን ውኃ ሊቀዳ ሲሄድ ሰይጣን እንስራውን ሰበረበት፡፡ አባቱም ሌላ መቅጃ ቢሰጠው እርሱንም ሰበረበት፡፡ የታዘዘ መልአክ ተገለጠላቸውና ወደ ሌላ ቦታ ሄደው ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ አዘዛቸው፡፡ ንጉሥ አንስጣስዮስም ቤተ ክርስቲያኑን ሠራላቸው፡፡ እነርሱም ለመነኮሳትና ለነዳያን መኖሪያ 500 መኖሪያ ቤቶችን ሠሩ፡፡ አባ ሳሙኤልም ባረፈ ጊዜ መነኮሳት ልጆቹን ለአባ ስምዖን አስረክቦ በሰላም ዐረፈ፡፡ መነኮሳቱም 12 ሺህ እስኪሆኑ ድረስ በዙ፡፡ አባ ስምዖንም በሚገባ ይመራቸው ነበር፡፡ በዘመኑም "ትንሣኤ ሙታን የለም" የሚል ሰይጣን በልቡ ያደረ አንድ መናፍቅ ተነሣ፡፡ አባ ስምዖንም ቢመክረውና ቢያስተምረው የማይለስ ሆነ፡፡ አባ ስምዖንም በሞተ ሰው ላይ ጸልዮ ያንን ሙት አስነሥቶ እንዲመሰክርለት ቢያደርገው አላምን አለው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ስምዖን ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያንን መናፍቅ አቃጠለውና ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ አባ ስምዖንም አገልግሎቱን ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡
❤ ከአባ ስምዖንም በኋላ አባ ገብርኤል ተሹሞ መለኮሳቱን የሚጠብቅ እረኛ ሆነ፡፡ እርሱም ምግባሩ ያማረ ሃይማኖቱ የሰመረ በትሩፋት በተጋደሎ ያጌጠ ነው፡፡ ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ፡፡ ከዕለታም በአንደኛው ቀን መነኮሳቱ ለእንጀራ ማቡኪያ የሚሆን እጅግ ትልቅ የሆነ የድንጋይ ገንዳ ወደ ገዳሙ ሊያስገቡ ቢሉ ከክብደቱ የተነሣ እምቢ አላቸው፡፡ አባ ገብርኤልም በዚህ ጊዜ በገዳሙ ያሉት ሁሉ ወጥተው እንዲራዱ በቃላቸው ባዘዙ ጊዜ 10 ሺህ ሰዎች ከሙታን ተነሡ፡፡ አባ ገብርኤልም ይህን አይቶ "እናንተን ያልኩ አይደለም በሕይወት ያሉትን ነው እንጂ" አሏቸውና ወዲያው ወደ መቃብራቸው ተመለሱ፡፡
❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አንድ ሰው ብዙ የሆነ ወርቁን ከአንዱ መነኩሴ ዘንድ በአደራ አስቀምጦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፡፡ ሰውየውም በተመለሰ ጊዜ መነኩሴው ለማንም ሳይናገር በሞት ዐርፎ አገኘው፡፡ የመነኩሴውም ረድእ አባቱ ያስቀመጠበትን ቦታ እንዳልነገረው አስረዳ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ገብርኤል ወደሟቹ መነኩሴ መቃብር ሄዶ መቃብሩን ስለዚያ ወርቅ ጠየቀው፡፡ ሟቹም መነኮሴ ወርቁን ያኖረበትን ቦታ ለአባ ገብርኤል ነገረውና ወስዶ ለባለቤቱ ሰጠው፡፡ ባለወርቁም እጅግ እያደነቀ ወርቁን ተቀብሎ በሰላም ሄደ፡፡
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ጢሞቴዎስ፡- ደጋግ የሆኑ ወላጆቹ የቤተ ክርስቲያንን ትምህት እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ በደገም ጊዜ ዓለምን ንቆ መንሶ ገዳም በመግባት በተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ መጻተኞችንና ጦም አዳሪዎችን ይመግባቸው ዘንድ ከገዳሙ አቅራቢያ መኖሪያን አበጀ፡፡ ነዳያንንም እየመገበ በመንፈሳዊ ተጋድሎው እየጸና 5 ዓመት ያህል ከኖረ በኋላ የበጎ ነገር ጠላት የሆነ ሰይጣን በቅናት ተነሣበትና የእጅ ሥራውን ትገዛ ዘንድ አንዲት ጋለሞታን ወደ እርሱ አመጣበት፡፡
❤ እርሷም ወደ አባ ጢሞቴዎስ ከመመላለሷ የተነሣ የኃጢአት ፍቅር አድሮባቸው በመብል ጊዜ አብረው የሚመገቡ ሆኑ፡፡ ከዚህም በኋላ ከእርሷ ጋር በኃጢአት ወደቀና በኃጢአት ሥራ ውስጥ 7 ወር ያህል ኖረ፡፡ እግዚአብሔር ሁለቱንም አልጣላቸውምና በዕለተ ምፅዓት በፊቱ የሚቆሙ መሆናቸውን አሳሰባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጢሞቴዎስ ተነሥቶ ጥቅጥቅ ወዳለ ጫካ ገብቶ በዚያ እየታደለ ብዙ ዘመን ኖረ፡፡ እግዚአብሔርም ጣፋጭ የሆነች የውኃ ምንጭንና ቴምርን አዘጋጀለት፡፡ እርሷን እየተመገበ በተጋድሎ ሲኖር ሰይጣን ዳግመኛ በቅናት ተነሣበትና አስጨናቂ የሆድ ሕማም አመጣበት፡፡ አባ ጢሞቴዎስ ከሕማሙ ጽናት የተነሣ በግንባሩ ምድር ላይ የወደቀ ሆኖ ቀረ፡፡ በዚህም ጊዜ ነፍሱን ‹‹ነፍሴ ሆይ ይህ የሠራሽው የኃጢአትሽ ፍሬ ነውና በዚህ ደዌሽ ታገሺ›› ይላት ነበር፡፡ በዚህም አስጨናቂ ሕማም ውስጥ ሆኖ 4 ዓመት ኖረ፡፡
❤ ከ4 ዓመትም በኋላ መሐሪና ይቅር ባይ የሆነ እግዚአብሔር ለአባ ጢሞቴዎስ መልአኩን ላከለት፡፡ መልአኩም የአባ ጢሞቴዎስን ሆድ በእጁ አሸው፡፡ ጎኑንም በጣቱ ሰነጠቀና ጨንጓራውንና አንጀቱን አፀዳለት፡፡ በኋላም ወደቦታው መልሶ እንደቀድሞው አያይዞ አዳነውና "እነሆ እንግዲህ ጤነኛ ሆንክ፣ ዳግመኛ አትበድል ከዚህ የከፋ እንዳይደርስብህ" አለው፡፡ አባ ጢሞቴዎስም በበረሃ እየተጋደለ 40 ዓመት ኖረ፡፡ ከዚያ በፊት በገዳም 17 ዓመት በዋሻ 10 ዓመት ኖሯል፡፡ በእነዚህም ዘመናቱ ከልብስ ተራቁቶ ኖረ፡፡ የራሱም ፀጉር ከፊትና ከኋላ ሸፍኖት ነበር፡፡ ስለ አገልግሎቱ፣ ስለ ተጋድሎውና ስለ አምልኮቱ የዱር አራዊት እስኪደግዱለትና የእግሩን ትቢያ እስኪልሱለት ድረስ እግዚአብሔር ትልቅ ጸጋን ሰጠው፡፡ አገልግሎቱንም ፈጽሞ ታኅሣሥ23 በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 23 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለዳዊት_ትሕትናሁ_ሶበ_ርእየ። ወየውሀቶ ፍጹም ዘአልቦ እከየ። #እግዚአብሔር ይቤ እንዘ ይነብብ ሰደየ። እምነ ሕዝብየ አልዓልኩ ኅሩይየ። ወረከብክዎ #ለዳዊት_ገብርየ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_23።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወአልዐልኩ ኅሩይየ እምሕዝቡ። ወረከብክዎ ለዳዊት ገብርየ። ወቀባዕክሙ ቅብዐ ቅዱስ"። መዝ 88፥19-20። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥19-ፍ.ም።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፳፫ (23) ቀን።
❤ እንኳን #ለልበ_አምላክ_ለእሴይ_ልጅ ለእስራኤል ንጉሥ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ዳዊት_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ተጋዳይ አባት ለገዳማዊ #ለአባ_ጢሞቴዎስ_ዕረፍት በዓል፣ ለቅዱሳን #ለአባ_ሳሙኤል_ለአባ ስምዖን_ለአባ ገብርኤል ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከይስሐቅ_ከአባ_አሞን፣ #ከአባ_አቦሊ_ከመቃርስ_ከአይተለአትካ_ከፊልጦስ_ከመርቆሬዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ልበ_አምላክ_ነቢዩ_ንጉሥ_ቅዱስ_ዳዊት፦ ይህም ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት መልካም ጒዞን የተጓዘ ከእራኤልም ነገሥታት ሁሉ እውነተኛ ፍርድን ያደረገ ነው እርሱም አገሩ ቤተልሔም የሆነች ከይሁዳ ነገድ ነው ሳኦልም የእግዚአብሔር ትእዛዝ በተላለፈ ጊዜ ለእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ መረጠው ነቢይ ሳሙኤልንም ቅብዐ መንግሥትን የእሴይን ልጅ ይቀባ ዘንድ ላከው። ሳሙኤልም ታላቁን ኤልያብን ተመለከተ መልኩ ያማረ አካሉም የጸና ነበርና እግዚአብሔር ግን አልመረጠውም። "የኤልያብ ፊቱን አትይ የመልኩንም ማማር አትመልከት እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ የሚያይ አይደለምና" አለው እንጂ "ሰው መልክ ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን" ያያል።
❤ ከእሴይ ከሰባቱ ልጆች በኋላ ነቢይ ሳሙኤል ዳዊትን በእስራኤል ልጆች ላይ ይነግሥ ዘንድ ቀባው እግዚአብሔርም በሥራው ሁሉ ከእርሱ ጋር ሆነ። ከልቡናው ንጽሕና ከየዋህነቱም ብዛት የተነሣ ጠላቱን ሳኦልን ብዙ ጊዜ ሲያገኘው በላዩ ምንም ምን ክፉ ነገር አላደረገበትም። በአንዲትም ዕለት ሳኦል ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትን ከሰዎቹ ጋር ይፈልገው ዘንድ ዋሊያዎች ወደሚታደኑበት ሔዶ በጐዳና አጠገብ ያሉ ዘላኖችም ወደሚሠማሩበት ደረሰ በዚያም ዋሻ ነበር ሳኦልም ይናፈስ ዘንድ ወደዚያች ዋሻ ውስጥ ተቀምጠው ነበር። ዳዊትም ተነሥቶ ቀስ ብሎ ከልብሱ ጫፍ ቆረጠ። በሁለተኛም ጊዜ በድንክ አልጋ ላይ ተኝቶ ወዳለበት ከአቢሳ ጋር ገብቶ ከራስጌው ጦሩንና ውኃ ያለበትን ረዋቱን ይዞ ተመልሶ ሔደ ክፉ ነገርንም አላደረገበትም ሰዎቹም ጠላትህ ሳኦልን ግደለው በአሉት ጊዜ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን ልዘረጋ አይገባኝም ብሎ መለሰላቸው።
❤ ስለ ሳኦልም መገደል አንድ ሰው በነገረው ጊዜ ዳዊትም "ያንን ሰው ማን ገደለው" አለው ሰውዬውም "እኔ ገደልሁት" አለው ዳዊትም እጅግ አዘነ ልብሱንም ቀደደ ያንንም ሳኦልን እኔ ገደልሁት ያለውን ሰው ገደለው። እግዚአብሔር በዚህ በጻድቅ ዳዊት ልብ ብዙ ትሩፋትን፣ ትሕትናን፣ የዋህነትን፣ ቅንነትን፣ ትዕግሥትን ፍቅርን አከማቸ ክብር ያለው ንጉሥ ሲሆን ራሱን ውሻ ትል እንስሳም አድርጎ ይጠራል ስለዚህም ከምድር ነገሥታት ሁሉ ከፍ ከፍ አደረገው እንዲህም ብሎ አመሰገነው "የእሴይን ልጅ ዳዊትን እንደ ልቤ ሆኖ አገኘሁት ፈቃዴን ሁሉ የሚያደርግ ታማኝ ሰው ነው"።
❤ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች ኢየሩሳሌምንም ስለ ዳዊት ደግነት ብዙ ጊዜ ጠበቃቸው እርሱ ካለፈ በኋላም በነቢያቶቹ አንደበት አከበረው ነገሥታትንም ከእርሱ ዘር አደረገ። እርሱም በሁሉ ዓለም የታወቀ የመዝሙሩን መጽሐፍ ደረሰ ይኸውም በሰይጣናት ላይ ጋሻና ጦር የሆነ መልካም ቃልንም የተመላ በሰማይና በምድርም ያሉ በእርሱ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ነው።
❤ ቅዱስ ዳዊትም ፊቱ እንደ ሮማን ቀይ ነው ቁመቱም መካከለኛ የሆነ አካሉም የጸና ብርቱ ነበር ታናሽ ብላቴናም ሁኖ ሳለ እርሱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አንበሳ ወይም ተኵላ መጥቶ ከመንጋው ውስጥ በግ ነጥቆ በሚወስድ ጊዜ ተከትሎ ገድሎ ከአፉ ያስጥለው ነበር ሊጣላውም ቢነሣበት ጒረሮውን ይዞ ይሠነጥቅዋል። ከፍልስጥዔማውያንም ጋራ ሰልፍ በሆነ ጊዜ ብርቱ ሰው ስሙ ጎልያድ የሚባል ከጌት ሰዎች የተወለደ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር የሆነ ከኢሎፍላውያን ሰፈር ወጣ። በራሱ ላይ የነሐስ በርቦርቴ ደፍቷል የነሐስ ጽሩርም ለብሷል በርሱ ላይ ያለ የብረቱና የነሐሱ ሁሉ ሚዛኑ አምስት ሽህ ወቄት ነበር። በእግሮቹ ባቶችም ላይ የነሐስ ሰናፊል ታጥቆ ነበር በጫንቃውም መካከል የነሐስ እባቦች ነበሩ። የጦሩም ዛቢያ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ሁኖ በላዩ ሽቦ ነበረበት የጦሩም ብረት መጠን ስድስት መቶ ወቄት ነበር ጋሻ ጃግሬውም በፊቱ ይሔድ ነበር።
❤ ቁሞም ወደ እስራኤል ሰፈር ይጮህ ነበር "ከእኛ ጋር ትዋጉ ለምን ወጣችሁ እኔ የኤሎፍላውያን ወገን ነኝ ከእናንተ የሳኦል ባሮች አይደላችሁምን ከእናንተ አንድ ሰው መርጣችሁ ወእኔ ይውረድ ከእኔ ጋር መዋጋት ችሎ ቢገድለኝ ባሮች እንሆናችኋለን እኔ ከርሱ ጋራ ችዬ ብገድለው እናንተ ባሮች ሁናችሁ ትገዙልናላችሁ" አላቸው። ያም ኢሎፍላዊ ለወገኖቹ "ዛሬ በዚች ቀን አንድ ሰው ስጡኝና ሁለታችን ለብቻችን እንደዋጋ ብሎ የእስራኤልን አርበኞች እነሆ ተገዳደርኳቸው" አላቸው። እስራኤል ሁሉና ሳኦልም ይህን የኢሎፍላዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ እጅግም ፈሩ የእራኤልንም ወገኖች እንዲህ እየተገዳደራቸውና እየተመካባቸው አርባ ቀኖች ያህል ኖረ ከእስራኤልም ወገን ወደርሱ ይወጣ ዘንድ የደፈረ የለም።
❤ በዚያም ወራት ቅዱስ ዳዊት ወንድሞቹን ሊጐበኝ ወጣ ያንንም የኢሎፍሊ ወገን የሆነ ሰው የእግዚአብሔር ወገኖችን ሲገዳደራቸው በአየው ጊዜ አምላካዊ ቅናትን ቀና ሳኦልንም እንዲህ አለው "እኔ ሔጄ ይህን ያልተገረዘ ቈላፍ ገድዬ ዛሬ ከእስራኤል ሽሙጥን አርቃለሁ። ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔርን አርበኞች ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ቁም ነገር ነው ከድብ አፍና ከአንበሳ አፍ ያዳነኝ እርሱ እግዚአብሔር ከዚህ ካልተገረዘ ኢሎፍላዊ እጅ ያድነኛል"። ሳኦል "ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ዳዊትም ወንጭፋን በእጁ ያዘ ከወንዝ መካከልም ሦስት ደንጊያዎችን መረጠና ወደዚያ ኢሎፍላዊ ሔደ። ጎልያድም ዳዊትን በአየው ጊዜ ናቀው እንዲህም አለው "ደንጊያና በትር ይዘህ ወደኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ውሻ ነኝን" ዳዊትም "ከውሻ የምትሻል አይደለህም ከውሻ ትብሳለህ እንጂ" ቈላፍ ጎልያድም ዳዊትን በጣዖቶቹ ስም ረገመው።
❤ ያም ኢሎፍላዊ ዳዊትን "ወደ እኔ ና ሥጋህን ለሰማይ ወፎችና ለዱር አራዊት እሰጣሁ" አለው ዳዊትም ያንኑ ኢሎፍላዊ "አንተ ጦር ሰይፍና ጋሻ ይዘህ ወደኔ ትመጣለህ እኔ ግን አሸናፊ በሚሆን በእግዚአብሔር ስም ወዳንተ እመጣለሁ። ዛሬ የእስራኤልን አርበኞች የተገዳደርክ አንተን ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ይጥልሃል እገድልህምአለሁ ራስህንም እቆርጣለሁ የኢሎፍላውያን ሠራዊት ሬሳና ያንተን ሬሳ ዛሬ ለዱር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጣለሁ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ ሠራዊትም ሁሉ እግዚአብሔር በጦርና በሰይፍ የሚያድን እንዳይደለ ያውቃሉ ድል የእግዚአብሔር ገንዘብ ነውና"።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን #እመቤታችንን_ቅድስት_ድንግል_ማርያምን የከበረ_ሊቀ መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል በአበሠራት መሠረት #ቅዱስ_ደቅስዮስ_በዓል_ላከበረት_ለብሥራት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና የእመቤታችንን ተአምረ ማርያም መጽሐፍ ለጻፈው #ለቅዱስ_ደቅስዮስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ መልአክ ከመላእክት አለቃ #ከቅዱስ_ገብርኤል ከበዓሉ መታሰቢያ ዳህና በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ ከተሠራችበትና ከከበረችበት ተአምራትም ካሳየበትና ከአገር ኤጲስቆስ #አባ_አርኬላዎስ ምስክር ከሆነበት፣ ከእስክድርያ አገር ሠላሳ ስድስተኛ ጳጳስ ከከበረ ከአባት #ከአባ_አንስጣስዮስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ደቅስዮስ_በዓለ_ብሥራትን_ማክበሩ፦ በዓልን የማክበሩ ምክንያትም እንዲህ ሆነ ይህ ኤጲስቆጶስ ደቅስዮስ ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ አስቦ በመትጋት የተአምራቷን መጽሐፍ ሰብስቦ አዘጋጀላት። የምእመናን ክብር የሆነች አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ማርያምም ተገለጸችለትና መጽሐፋን በእጅዋ አንሥታ ይዛ "ወዳጄ ደቅስዮስ ሆይ ይህን መጽሐፍ ስለ ጻፍክልኝ ባንተ ደስ አለኝ አመሰገንኩህም" አለችው ከዚህም በኋላ ከእርሱ ተሠወረች። ቅዱስ ደቀስዮስም ይህን ነገር በራይ ባየ ጊዜ ክብርት ድንግል እመቤታችን ማርያምን ከመውደዱ የተነሣ ፈጽሞ ደስ አለው እርሷንም ስለ ወደደ ፍቅርዋ እንደ እሳት አቃጠለው የሷን ክብር አብዝቶ ይጨምር ዘንድ ምን እንደሚያደርግ የሚሠራውን ያስብ ጀመር።
❤ ከዚህም በኋላ በዚያን ጊዜ ጾም ስለነበር ሰዎች አስቀድመው ሊአከብሩት ያልተቻላቸውን የመላእክት አለቃ የከበረ ቅዱስ ገብርኤል ባበሠራት ቀን በዓሏን አከበረ። እርሱም የከበረ የሚሆን የልደትን በዓል ከማክበር አስቀድሞ በስምንት ቀን አደረገ ይኸውም ታኅሣሥ በባተ በሃያ ሁለት ቀን ነው በጵጵስናውም ዘመን ተሠርታ እስከዚች ቀን ጸንታ ትኖራለች። ሰዎችም በዓሉን በአከበሩት ጊዜ ፈጽሞ ደስ አላቸው።
❤ ደግነትን ምሕረትን ቸርነትን የምትወድ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ማርያም በእጅዋ የከበረ ልብስ ይዛ ዳግመኛ ተገለጸችለትና "አገልጋዬ የሆንክ ወዳጄ ደቅስዮስ ሆይ በእውነት አመሰገንኩህ በአንተም ደስ አለኝ ሥራህንም ወደድሁ። በእኔም ደስ እንዳለህና የከበረ መልአክ ገብርኤል እኔን በአበሠረበት ቀን በዓሌን ስለአከበርክ ሰውንም ሁሉ ስለ እኔ ደስ ስለአሰኘህ እኔም ዋጋህን ልሰጥህ አንተ በዚህ ዓለም እንዳከበርከኝም በሰው ሁሉ ፊት አከብርህ ዘንድ እወዳለሁ" አለችው። እሷም "ትለብስ ዘንድ ይችን ልብስ እነሆ አመጣሁልህ በላዩም ትቀመጥ ዘንድ ይህን ወንበር አመጣሁልህ ከሰው ወገን አንድ ስንኳ ይህችን ልብስ ሊለብሳት በዚህም ወንበር ላይ ሊቀመጥ የሚቻለው የለም። ይህን ነገሬን የሚተላለፍ ቢኖር እኔ እበቀለዋለሁ" አለችው ይህንንም ተናግራ ከእርሱ ተሠወረች።
❤ ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ22 ቀን በዐረፈ ጊዜ ሌላ ኤጲስቆጶስ ተሾመ ያቺንም ልብስ ለበሳት በወንበሩም ላይ ተቀመጠ ወዲያውኑ ከወንበሩ ላይ ወድቆ ሞተ ይህንንም ያዩ ከእመቤታችን ማርያም ተአምር የተነሣ አደነቁ እጅግም ፈርተው እመቤታችንን አከበሩዋት ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ለእርሱም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ #የቅዱስ_ገብርኤል_የበዓሉ_መታሰቢያ ዳህና በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራችበት ተአምራትም ያሳየበትና በዚች ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ የከበረችበት ነው የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ አርኬላዎስ ምስክር የሆነበት ነው።
❤ ይህም መልአክ ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር የታመነ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተላከ "የደስታ መገኛ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ" አላት።
❤ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድም ካህኑን ዘካርያስን ያበሠረው እርሱ ነው ይህ መልአክ እጅግ የከበረ የተመረጠ ገናና የሆነ ነውና ስለ እኛ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ዘንድ ልባችንን አንጽተን ወደዚህ የከበረ መልአክ እየለመንን መታሰቢያውን ልናደርግ ይገባል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ22 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_እብል_ለደስቅዮስ_ባሕርያ። ኤጺስቆጶስ ዘሀገረ ጥልጥልያ። በእንተ ዘጸሐፈ ላቲ ትምእምርተ ዜናሃ ወጸጋ ዕበያ። እንተ ወሀበቶ ወላዲተ አምላክ ማርያ። ልብሰ ሰማያዊት እስከ ዮም ነያ"። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ22።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ማኅሌቱ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስመከ። መዝ 137፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥26-39።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ። ወትሠይም(ሚ)ዮሙ መላእክተ በኵሉ ምድር። ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ"። መዝ 44፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 1፥8-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9-18 እና የሐዋ ሥራ 12፥7-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የብሥራት ቅዱስ ገብርኤል በዓል፣ የቅዱስ ደስቅዮስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ የስሙ ትርጓሜ የመረጋጋት ልጅ ለሆነ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_በርናባስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱና #ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ለወራዊ መታሰቢያ በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰቡ፦ ከአባ ይስሐቅ ከዕረፍቱ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የእመቤታችን_አምላክን_የወለደች_የቅድስት_ድንግል_ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው። እርሷ የባህርያች መመኪያ ናትና በእርሷ በእናቱ አማላጅነት ጌታችን ይጠብቀንና ያድነን ዘንድ መታሰቢያዋን እያደረግን ወደርሷ እንለምን ዘንድ ይገባል። እርሷን ሕይወትን መድኃኒትን አድርጎ ለሰጠን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_በርባስ፦ ይህም ቅዱስ ሐዋርያ ከሊዊ ነገድ የሆነ አገሩ ቆጵሮስ ነው የቀድሞ ስሙ ዮሴፍ ነው ክብር ይግባውና ጌታችን ከመከራው በፊት ይሰብኩ ዘንድ ከላካቸው ከሰባ ሁለት አርድእት ጋር መረጠው ስሙንም በርናባስ ብሎ ጠራው። ከጌታ ዕርገትም በኋላ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ እርሱም ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ። የእርሻ ቦታ ነበረውና ሽጦ ዋጋውን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር በታች አኖረው።
❤ ቅዱስ ጳውሎስም በጌታችን አምኖ ወደ ሐዋርያት በመጣ ጊዜ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ እርሱ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ ሐዋርያት አላመኑትም ነበር። ይህ በርናባስ ጌታችን በመንገድ እንደ ተገለጸለትና እንደአነጋገረው እርሱም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በደማስቆ እንደ አስተማረ ነገራቸው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙ ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ "ሳውልና በርናባስን እኔ እነርሱን ለመረጥኩት ሥራ ለዩልኝ" አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ጹመው ጸልየው እጆቻቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው። ከመንፈስ ቅዱስም ተሹመው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ ከዚያም ወደ ቆጵሮስ ሔዱ የእግዚአብሔርንም ቃል በአገሩ ሁሉ አስተማሩ። ልስጥራን በተባለ አገርም ልምሾ የነበረውን ሰው በአዳኑት ጊዜ የልስጥራን ሰዎች መሥዋዕትን ሊሠዉላቸው ወደዱ። ሐዋርያት ቅዱስ ጳውሎስና በርናባስም በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀድው ወደ ሕዝቡ ሔዱ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሏቸው "እናንት ሰዎች ይህ ነገር ምንድን ነው እኛማ እንደናንተ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን ይህን ከንቱ ነገር ትታችሁ ሰማይና ምድርን ባሕርንም በውስጧቸው ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ እናስተምራችኋለን" አሏቸው እንዲህም ብለው መሠዋትን በጭንቅ አስተዋቸው።
❤ ከዚያም ብዙ አገሮችን ከአስተማሩ በኋላ ቅዱስ በርናባስ ከቅዱስ ጳውሎስ ተለይቶ ቅዱስ ማርቆስን ይዞ ወደ ቆጵሮስ ሔደ በዚያም አስተማረ ብዙዎችን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳቸውና የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።
❤ በቆጵሮስ አገር የሚኖሩ አይሁድም ቀኑበት በመኳንንትም ዘንድ ወነጀሉት በእግር ብረትም አሥረው ጽኑ ግርፋትን ገረፉት ከዚህም በኋላ በደንጊያ ወገሩት ዳግመኛም ወስደው ከእሳት ጨመሩት ምስክርነቱንም ፈጸመ። ቅዱስ ማርቆስም ከርሱ ጋር አለ ግን እግዚአብሔር ጠብቆ አተረፈው። እርሱም ቅዱስ በርናባስን ከእሳት ውስጥ አወጣው ሥጋውንም እሳት ከቶ አልነካውም በአማሩ ልብሶችም ገንዘውና ተሸክሞ ወስዶ ከቆጵሮስ ከተማ ውጭ በዋሻ ውስጥ አኖረው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያ ቅዱስ በርናባስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 21 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለበርናባስ በማእሠረ ጌጋይ ዘኢትእኅዘ። #ከመ_መንፈስ_ቅዱስ_አዘዘ። ሥርዓተ ፈጺሞ ወመልእክተ ቃለ አዚዘ። በዋዕየ እሳት ሶበ እምዓለም ግዕዘ። ለወንጌላዊ ማርቆስ በእዱ ተገንዘ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ 21።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ማኅሌት_ምስባክ፦ "ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሐይ ሤመ ጽላሎቶ"። መዝ 18፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 2፥1-14፣ ቈላ 4፥1-ፍ.ም ወይም ይሁ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥23-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥17-34። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ በርናባስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት የገና (ጾም) ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካች_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለንዑስ በዓል ለአንዱ #ለብርሃን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፮ "አቅዲሙ ነገረ በኦሪት አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ #ይመጽእ_ወልድ_በስብሐት ዘይዜንዋ ለጽዮን ቃለ ትፍሥሕት ወካዕበ ይቤ #በአፈ_ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ #በስመ_እግዚአብሔር_ብርሃን_ዘመጽአ_ውስተ_ዓለም_ዘያበርህ_ላዕለ_ጻድቃን መርዓዊሃ #ለቤተ_ክርስቲያን ይርዳእ ዘተኃጒለ ያስተጋብእ ዝርዋነ ኃቤነ"። ትርጉም፦ ዳግመኛ #በዳዊት_አፍ እንደነገረ #በእግዚአብሔር_ስም_የሚመጣ_እርሱ_ምስጉን ነው፣ ለጽዮን የደስታን ቃል የሚነግራት ወልድ በክብር እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ተናገረ፣ #ወደ_ዓለም_የመጣ_ብርሃን_በጻድቃን ላይ የሚያበራ #የቤተ_ክርስቲያን_ሙሽራ የጠፋውን ሊፈልግ የተበተነውን ሊሰበስብ ወደ እኛ መጣ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ "ዕለተ ብርሃን" ፦ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱስ ያሬድን አስተምሕሮ መሠረት አድርጋ ታኅሣሥ 14 ቀን "ዕለተ ብርሃን" ትለዋለች። ሳምንቱን (ከታኅሣሥ 14-20 ነው)። በእነዚህ ዕለታት እሑድ በዋለበትን ቀን ማኅሌት ተቁሞ ብርሃን ተብሎ ይከበራል። ደግሞ "ሰሙነ ብርሃን" ስትል ታስባለች::
❤ "ብርሃን" በቁሙ የእግዚአብሔር ስሙ፤ አንድም የባሕርይ ገንዘቡ ነው። "እግዚአብሔር ብርሃን ነውና:: ጨለማም በእርሱ ዘንድ የለችምና።" (ዮሐ 1፥4)
❤ በዚህ ዕለት "ብርሃን" በሚል መነሻ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ታስተምሠራለች:-
1.እግዚአብሔር ብርሃን መሆኑን። (ዮሐ 1፥5)
2.አምላካችን በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን (በዕለተ እሑድ) ዲያብሎስ ቅዱሳን መላእክትን ሲረብሽ "ለይኩን ብርሃን" ብሎ ብርሃንን መፍጠሩን። (ዘፍ. 1፥2 አክሲማሮስ)
3.ነቢያት አበው በጨለማው ዓለም ሆነው መከራ ሲበዛባቸው "ፈኑ ብርሃነከ - ብርሃንህን ላክልን" እያሉ መጮሃቸውን። (መዝ 42፥3)
4.ጩኸታቸውን የሰማ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ (እውነተኛው ብርሃን) ወደዚህ ዓለም መምጣቱን። (ሉቃ 1፥26)
5."እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ሲል የባሕርይ ብርሃንነቱን እንደ ነገረን። (ዮሐ 8፥12)
6.ብርሃነ መለኮቱን በገሃድ መግለጡን። (ማቴ 17፥1)
7.ብርሃን የሆነችውን ሕግ፤ ወንጌልን እንደ ሠራልን:: (1ዮሐ 2፥9)
8.ድንግል እመቤታችን ብርሃን፤ የብርሃንም እናቱ መሆኗን። (ሉቃ 1፥26፣ ራዕ 12፥1)
9.ቅዱሳኑ ብርህን መባላቸውን። (ማቴ. 5፥14)
10.እኛ በሰው ፊት ሁሉ እንድናበራ መታዘዛችን። (ማቴ 5፥16) ሁሉ ይታሰባል።
❤ እርሱ ፈጣሪያችን ክርስቶስ ጨለማውን በምሕረቱ አርቆልናልና ዳግመኛ ወደ ጨለማ እንዳንሄድ እየለመንን እናመስግነው።
❤ "ክርስቶስ ብርሃን ዘአሰሰልከ ጽልመተ።
ላዕለ ኪሩቤል ነቢረከ ዘትሬኢ ቀላያተ።
ስቡሕኒ ወልዑል አንተ"። (መልክአ ኢየሱስ) ምንጭ፦ ከዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ ፔጅ የተወሰደ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ፈኑ ብርሃንከ ወጽድቀከ። እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ"። መዝ 42፥3። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 13፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 26፥12-19። የሚነበው ወንጌል ዮሐ1፥1-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ አትናቴዎስ ወይም ቅዳሴ እግዚእነ ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃን በዓል፣ ዕለተ ሰንበትና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቅ ለታላቁ አባት #እግዚአብሔር_አምላክ ብዙ ቃል ኪዳን ለገባላቸው #ለአቡነ_አባለ_ክርስቶስ ለዕረፍት በዓል፣ ተንቤን ውስጥ የሚገኘውን አስደናቂውን የውቅን #ቅዱስ_ገብርኤል ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ለሠሩት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዳንኤል_ዘተንቤንና መልአከ ሞት ከበራቸው ላይ ለሦስት ወር ላቆሙ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ስነ_ኢየሱስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_አባለ_ክርስቶስ፦ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ አባለ ክርስቶስ ዘደብረ መድኃኒት ጻድቁ አቡነ አባለ ክርስቶስ ከአባታቸው ቅዱስ አቃርዮስ እና ከእናታቸው ቅድስት ታውክልያ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በየካቲት 19 810 ዓ.ም በአክሱም ከተማ የተወለዱ ጻድቅ ሲሆኑ ከሰውነታቸው ማሀል ዲካባ፣ ማርትያስ፣ ክስብኤል የሚሉ ኅቡአን የሥላሴ አስማት ተጽፎውላቸው የተወለዱ ጻድቅ ናቸው።
❤ በዚሁ መሰረት ከጻድቁ አቡነ ጰንጠሌዎን በሠላሳ ሁለት ዓመታቸው ሙንኲስናን ከተቀብሉ በኋላ ጽላትን ለ24 ዓመታት ያህል እያጠኑ ከቆዩ እንደ ሌሎቹ ቅዱሳን ዛሬ ገደማቸው በሚገኝበት እና አፅማቸው ካረፈበት ገዳማቸው ተጋድሎን በመፈጸም ከፈጣሪያቸው በታሕሳስ 19 ቀን ቃልኪዳን ተቀብለው በ332 ዕድሜያቸው ያረፉ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ናቸው።
❤ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣቸው ቃል ኪዳን "ዝክርህን የዘከረ ስምህን የጠራ እስከ 24 ትውልድ ምሬልሀለሁ" አላቸው። "ስምህን በመጥራት የተራቡ ያበላ የተጠሙ ያጠጣ የታረዙትን ያለበሰ ለቤተ ክርስቲያንህ የተለያዩ ምፅዋት የሰጠ እስከ 28 ትውልድ አድነዋለሁ" አላቸው። ማየ ጸሎትህም፣ ፀበልህ፣ የተጠመቁ፣ የታጠቡ እስከ 27 ትውልድ አድነዋለሁ" አላቸው። ገዳምህን ለመሳለም፣ ለመሳም፣ አስበው ያልተሳካላቸው 26 ትውልድ አድነዋለሁ" አላቸው። ቤተ ክርስተያንህን የሰራ በመንግስተ ሰማያት እስከ 33 ትውልድ የብርሃን ማደርያ እሰራለታለሁ አላቸው። ዝክርህን፣ መታሰብያህን፣ ሊያደርግ ብሎ ያሰበ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ሳይሳካለት የቀረ እሰከ 25 ትውልድ አድነዋለሁ" አላቸው።
❤ "በገዳምህ በየዓመቱ እና በየወሩ ቅዱስ ቊረባን የተቀበለ እስከ 35 ትውልድ አድነዋለሁ" አላቸው:: መፅሓፍህን የፃፈ፣ ያነበበ፣ የተረጎመ፣ የሰማ እስከ 28 ትውልድ አድነዋለሁ" አላቸው። "ይህች የምታርፍባት የነበርክ ድንጋይ የመካናት ማህፀን ፈትታ ልጅነት ትሰጣለች" አላቸው። ሰውነታቸው በተለያዩ ሕመሞች፣ በሽታዎች የተያዙ አለቱን ቤተክርስቲያኑን በምትፈለፍልባት የነበርክ በትርህ ታሽቶው ይደናሉ" በማለት በማይሻር ቃሉ ይሀንን ቃል ኪዳንገበቶላቸው በክብር ወደ ሰማያት አረገ።
❤ ገዳሙ የምገኘው ከአክሱም ወደ ማሕበረ ጻድቃን ዴጔ 17 ኪሎሜትር ተጉዘው ማሕበረ ጻድቃን ዴጔ ከተማ ላይ እንደደረሱ ወደ ግራ በመንገጠል 25 ኪ.ሜ እንደተጓዙ ጠላዕ በምትባል ትንሽ ከተማ ቀበሌ ሲደርሱገዳሙ አስደናቂ በሆነ አቀማመጥ ከሚያስደንቅ ሸለቆ ከአለት ተፈልፍሎ የተሰራ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ባለ ቃል ኪዳንገዳሙ ያገኙታል። በገዳሙ በየዓመቱ ታሕሳስ 19 ቀን የጻድቁ በዓለ ዕረፍት ፥ የካቲት 19 ቀን የጻድቁ በዓለ ልደታቸው ዓበይት በዓላት ብዙ ምእመናን በተሰበሰቡበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ጻድቁ ገድለኛ እና ታአምረኛ በመሆናቸው በእሳቸው እጅ ከአለት ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ፣ቅኔ ማህሌት፣ ምቋም ሰዓታት እና ቤተ አንድነት በገዳሙ ውስጥ ይገኛል። ያርፉባት የነበረች ድንጋይ እብነ ሕይወት ተብላ እንድትጠራ እና የመካናት ማህፀን ፈትታ ልጅ እንድ ትሰጥ ቃል ኪዳንየተሰጣት ድንጋይ እና ቤተ መቅደሱን የሚፈለፍሉባት የነበረች በትረ ትእምርት ለምስክር ያህል እስከ አሁን ብዙ ህሙማን እና መካናት እየተፈወሱ በገዳሙ ውስጥ ይገኛሉ።
❤ በገዳሙ ካሉ ቅርሳቅርሶች ከ1000 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው መዛግብተ እክል፣ ጎተራዎች፣ ሰፍየዶች፣ ከሸክላ የተሰሩ ፅዋዎች እና ጋኖች በአስገራሚ ሁኔታ እስከ አሁን በገዳሙ ውስጥ ተጠብቀው ይገኛሉ። እንዲሁም በገዳሙ ውስጥ የሚገኙሁለት ዓይነት ጠበል ማለትም መጀመርያ ወደ ገዳሙ ሲገቡ በመስቀላቸው ባርከው ከዐለት ያፈለቁት ማየ ጸሎት እና በዕረፍታቸው ቀን ከመቃብራቸው ከቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚመነጭ ማየ ጸሎት ብዙ ህሙማን እየተፈወሱበት የሚገኝ ታሪካዊ ገዳም ነው። ከአባታችን ከአቡነ አባለ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ Tmihrt Fikre Debre Birhan።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ዳንኤል_ዘተንቤን፦ አገራቸው ትግራይ ዘተንቤን ነው። ዳንኤል ሐዲስ በሚል ስያሜም ይታወቃሉ። በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የነበሩ ሲሆን ለዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከሰማይ የወረደላቸውን መስቀል ይይዙት ስለነበር ዛሬ ያንን መስቀል። ትግራይ ወስደውት ውቄን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ውስጥ በክብር አስቀምጠውታል። የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብንም መጽሐፈ ነገሥት ተርጓሚ ነበሩ። ጻድቁ እህል ሳይበሉ ውኃም ሳይጠጡ 40ቀንና 40ሌሊት ይጾሙ የነበሩ መናኝ ባሕታዊ ናቸው። እንደ ነቢዩ ኤልሳዕም ሁለት ሙት አስነሥተዋል። ከአባታችን አቡነ ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
✝ ✝ ✝
❤ #ጻድቅ_አቡነ_ስነ_ኢየሱስ፦ መልአከ ሞት መስከረም 19 ቀን መጥቶ "ጊዜ ዕረፍትህ ደርሷል" ቢላቸው "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም" ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ከበራቸው ላይ ያቆሙት አቡነ ስነ ኢየሱስ በደመና ተጭነው በመዘዋወር በሀገራችን ወንጌልን ሰብከዋል፡፡ ገዳማቸው ታች አርማጭሆ ከሳንጃ ከተማ በእግር የ3 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
❤ ጻድቁ ከሽዋ ምድር ተነሥተው ወደ ታች አርማጭሆ በመሄድ በበረሃ ውስጥ በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ በዚያም የሰማዕቱ የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን ገዳም ገድመዋል፡፡ አቡነ ስነ ኢየሱስ ብዙ መናንያን አርድእትን ያፈሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ አስገራሚ ተአምራትን በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ከበራቸው ላይ ካቆሙትና በዓሉን ካከበሩ በኃላ በዚኽች ዕለት ታሕሳስ 19 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ከአባታች ከአቡነ ስነ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን #ለመጋቤ_ሐዲስ_ለሊቀ_መላእክት #ለቅዱስ_ገብርኤል_አናንያን_አዛርያን_ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከነደደ እሳት ለዳናቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከካህናት ወገን ከሆነ #ከሀገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የመላእክት_አለቃ_የመልአኩ_ቅዱስ_ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና።
❤ በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ።
❤ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ገብርኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሥዓትን ሠሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 12 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የአገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ_አባ_ዮሐንስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጅቹ የከበሩ ናቸው እነርሱም ከገንዘባቸው ለድኆችና ለችግረኞች ይሰጡ ነበር ወላጆቹም በአረፉ ጊዜ የተዉለትን ገንዘብ ወስዶ ቤተ ክርስቲያን ሠራ ዳግመኛም የእግዳ ቤት ሠራ በውስጡም መጻተኞችንና በሽተኞችን ሰብስቦ የሚያገለግላቸው ሆነ የሚሹትንም ሁሉ ያቀርብላቸዋል።
✝ በዚያም ወራት ወደርሱ አንድ መነኵሴ መጣ የምንኵስናንም ሥራ አመሰገነለት ክብሩንም ገለጠለት ያ መነኵሴም ከሔደ በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ሰጥቶ አባ ዳንኤል ለአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሁኖ በነበረበት ወራት ወደ አስቄጥስ ሒዶ በአባ ዳንኤል ዘንድ መነኰሰ በዋሻ ውስጥም ብቻውን ሁኖ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ስለ መልካም ተጋድሎውም ሰይጣናት ቀኑበት ብዙ ዘመንም ታሞ ከኖረ በኋላ በደዌ መቅሠፍት ቀሠፉት።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈወሰውና ኃለኛ ጽኑዕ አደረገው በእግዚአብሔርም ፈቃድ ቡርልስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶሰነት ተሾመ በዘመኑም በአገሮች ውስጥ ብዙ ኑፋቄ ነበር እርሱም እንክርዳዱን ከሥንዴ መካከል ይነቅል ዘንድ ብዙ ድካምን ደከመ ከላይኛው ግብጽ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ብዙ ነገርንም ይቀርባጥር ነበር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምሥጢር ይገልጥልኛል በማለት እርሱ ብዙ ሰዎችን አሳታቸው ይህንንም በአወቀ ጊዜ ይዘው ይገርፋት ዘንድ አዘዘ ስሕተቱንም አመነ ከአገርም አሳደዱት።
❤ ነቢይ ዕንባቆም ይታየኛል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥልኛ የሚል ሌላ ሰው ነበር ብዙዎችም ተከተሉት እርሱንም አሳደደው ትምህርቱንም አጠፋ መጻሕፍቱንም ቀደደ የሳቱትንም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ይህ አባ ዮሐንስ መሥዋዕት ለማሳረግ በሚቀድስ ጊዜ ፊቱ እሳት ይሆናል ሥጋውም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ እንደወጣ ይሆናል ዕንባውም እንደ ዝናብ ይዘንባል የመላእክትን ሠራዊት በመሠዊያው ዙሪያ በመሠዊያው ዙሪያ በግልጥ ያያቸዋልና። ኅብስቱ በሚፈተት ጊዜ ሦስቱን የመፈተቻ ምስጋናዎች አንብቦ ጽዋውን ሲባርከው እንደ ፍም የጋለ ሁኖ ጽዋውን ያገኘዋል።
❤ በኋላ በዘመኑ በቀን ከበሉ በኋላ በአንድ ቀን ሁቸተኛ የሚቆርቡ ክፉዎች ሰዎች ተነሡ አስተምራቸው ገሠጻቸው ባልተመለሱም ዳግመኛ አወገዛቸው ባልተመለሱም ጊዜ ስለርሳቸው ጌታን ለመነው እሳትም ከሰማይ ወርዶ አለቃቸውን አቃጠለው የቀሩትም ይህን አይተው እጅግ ፈሩ ተጸጽተውም ወደ ቀናች ሃይማኖት ተመለሱ።
❤ ከዚህም በኋላ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም እግዚአብሔር ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ ቅዱሳን አባ እንጦስና አባ መቃርስን ወደርሱ ላካቸው እነርሱም ዕረፍቱ እንደ ደረሰ አስረዱት ሕዝቡንም ሰብስቦ ሕግና ሥርዓትን እንዲጠብቁ እርስ በርሳቸውም ይፋቀሩ ዘንድ በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ በመኝታው ላይ ጋደም ብሎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 19 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ማኅሌት_ምስባክ፦ "ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵሎሙ መላእክቲሁ። ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ። ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ። መዝ 102፥20-21 ወይም መዝ 137፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥29-34 ወይም ሉቃ 1፥11-21። መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፰ (18) ቀን።
❤ እንኳን #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ቶማስ ለሥጋው ፍልሰት በዓልና ለሐዋርያው #ቅዱስ_ጳውሎስ_ደቀ_መዝሙር_ለቅዱስ_ቲቶ ሥጋው ከአቅራጥስ ከሚባል አገር ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ለፈለሰበት ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከኢርቅና በሰማዕትነት ከሞተ በብሕትውና ከሚኖር #ከቀሲስ_ፊልሞና ከዕረፍታቸው መታሰቢያ፣ #የፍርክዮን_ከኢልኮዮስ_ከበሳንቅስ፣_ከዮናስ፣ ከባልጀሮቻቸው ሰማዕታትም ከመታሰቢያቸው፣ #ከአርሲስ_ከዳስያና_ከዲሞንም ከሥጋቸው ፍልሰት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የሐዋርያ_ቅዱስ_ቶማስ_የሥጋው ፍልሰት መታሰቢያ ሆነ ከሥጋውም አስደናቂዎች የሆኑ ብዙ ተአምራት በተገለጡ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በጸሎቱ ይማረን በከቱም ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 18 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የቅዱስ_ቲቶ_የሥጋ_ፍልሰት ወደ #ቊስጥንጥንያ_ከተማ፦ ይህም እንዲህ ነው ታላቁ ጻድቅ ቈስጠንጢኖስ በእግዚአብሔር ፈቃድ በነገሠ ጊዜ ስለ አብያተ ክርስቲያናት ሥራ አስቦ በሚገዛቸው አገሮቹ ሁሉ ሠርቶ በመልካም ጌጥ አስጌጣቸው በዕንቊዎችና በከበሩ ደንጊያዎችም ይልቁንም በቊስጥንጥንያ ከተማ እርሷ መናገሻ ከተማው ናትና። የሐዋርያትንም ሥጋቸውን ከሁሉ ቦታ ከከበሩ ሰማዕታትም ብዙውን ሰበሰበ ስለ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ሥጋ አቅራጥስ በሚባል አገር እንዳለ በሰማ ጊዜ የካህናትን አለቆች ከብዙ ገንዘብ ጋር ላካቸው እነርሱም የቅዱስ ቲቶን ሥጋ በታላቅ ክብር ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት ንጉሡም ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠራለት ሥጋውንም ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥ አኖረ።
❤ እግዚአብሔርም ታላላቅ አስደናቂዎች ተአምራትን ከሥጋው ገለጠ ከዕብነ በረድ የተሠራ ሥጋው ያለበትን ሣጥን በተሸከሙ ጊዜ ከአንድ ሰው ላይ ወድቆ እግሩን ቀጥቅጦ ሰበረው እርሱም ከቅዱስ ቲቶ ሥዕል ፊት ካለው የመብራት ቅባት የተሰበረ እግሩን ቀብቶ ሲያመው እየጮኸ አሠረው። ወደ ቤቱም መሔድ ባልቻለው ጊዜ የቅዱስ ቲቶ ሥጋ ሣጥን በአለበት በዚያ አደረ። በማግሥቱም አይቶ በውስጡ መድኃኒት ሊያደርግ እግሩን በፈታው ጊዜ ከቶ ምንም ምን ሕማም እንዳላገኘው እንደሁለተኛው ደኅና ሁኖ አገኘው ግን የደም ፍለጋ ምልክት አለ ይህን ድንቅ ሥራ ያዩ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት እርሱም የዳነው ፈጽሞ እያመሰገነ ወደ ቤቱ ገባ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_እብል_ለፍልሰተ_ሥጋሁ_በዘምሮ። #ለረድአ_ጳውሎስ_ቲቶ_እግዚአብሔር_እንተ አፍቀሮ። ሣፁነ ሥጋሁ ዘዕብን አመ ለብእሲ ሰበሮ። ረከበ ፈውስ ወጥዒና ከመ መንፈስ ቅዱስ አምከሮ። እምቅብዐ ማኅቶት ዘገጸ ሥዕሉ ሶበ ቀብዐ እግሮ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_18።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 7፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ይሁ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 5፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 11፥9-17። የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የሲመት በዓልና የሐዋራዊው ቅዱስ ቶማስና የቅዱስ ቲቶ የሥጋ ፍልሰት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን #ለአርማንያ_ሊቀ_ጳጳስ ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት ለሆነ #ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ሉቃስ_ዘአምድና_ከአባ_ይምላህ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአርማን_አገር_ኤጲስቆጶስ_አባ_ጎርጎርዮስ፦ ይህንንም ቅዱስ የንጉሡን ትእዛዝ ስመተላለፋና ለአማልክት አልሠዋም ስላለ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ አሠቃይቶ ጥልቅ ወደ ሆነ ደረቅ ጒድጓድ ውስጥ ጨመረው በዚያ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር አንዲቷን አሮጊትም ሁል ጊዜ ምግቡን እነሰድታመጣለት አደረጋት ሕያው እንደሆነም የሚያውቅ የለም።
❤ ንጉሥ ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ለማግባት ሽቶ ነበርና በእርሷ ምክንያት ደናግሎችን ገደላቸው። የእሊህ ደናግልም ሥጋቸው በተራራ ላይ እንደ ወደቀ ነበር ንጉሡም ስለ ገደላቸው ደናግል ይልቁንም ውበቷንና ደም ግባቷን እያሰበ ስለ ቅድስት አርሴማ አብዝቶ የሚያዝንና የሚጸጸት ሆነ።
❤ ከዚህም በኋላ ወገኖቹ ለመኑት እንዲህም አሉት አውሬ ታድን ዘንድ በፈረስ ተቀመጥና ወደ ዱር እንውጣ የልብህም ኀዘን ይወገድልሃል። በዚያንም ጊዜ አውሬ ለማደን በፈረሱ ተቀምጦ ወደ ዱር ወጣ። የሚነክስ ሆነ ወገኖቹንም ነከሳቸው እግዚአብሔርም መልኩን ለውጦ እንደ እሪያ አደረገው ያገኘውን ሁሉ የሚነክሰ ሆነ። እንዲሁም ከቤተ መንግሥት ሰዎች በብዙዎቹ ላይ ሰይጣን አደረባቸው ታላቅ ድንጋጤም ሆነ ይህም ሁሉ የሆነ ስለ ቅዱሳት ደናግልና ስለ ቅድስት አርሴማ ነው።
❤ የንጉሡ እኅት ግን "ጎርጎርዮስን ከጒድጓድ ካላስወጣችሁት ድኅነት የላችሁም" የሚላት ሰው በራእይ አየች ይህንንም ለወገኖቿ ነገረች እርሱ አስቀድሞ በጒድጓድ ውስጥ የሞተ ስለ መሳላቸው ደነገጡ። በዚያንም ጊዜ ወደ ጒድጓድ ሔዱ በሕይወት እንዳለም ያወቁ ዘንድ ወደ ጒድጓዱ ውስጥ ገመዶችን አወረዱና ገመዶቹን እንዲይዝ ወደርሱ ጮኹ እርሱም ገመዶችን ያዘ ስበው አወጡት አጥበውም ንጹሕ ልብስን አለበሱት በበቅሎም አስቀምጠው ወደ ቤተ መንግሥት አደረሱት። በዚያንም ጊዜ በሰማዕትነት ስለሞቱ ደናግል ሥጋ ጠየቀ እነርሱም የደናግሉ ሥጋቸው ወዳለበት መርተው አደረሱት የዱር አራዊትና አዕዋፍ ሳይበሏቸው በደኅና አገኛቸው ያማሩ ቦታዎችን አዘጋጅተው በውስጣቸው ያኖሩዋቸው ዘንድ አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡን ያድነው ዘንድ ሕዝቡ ለመኑት ንጉሡም ወዳለበት ዱር አደረሱት እርሱም "ከክፉ ሥራህ ትመለሳለህን? ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታምናለህን?" አለው። እሪያ የሆነውም ንጉሥ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አድርጎ አመለከተ በዚያንም ጊዜ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸለየ ከንጉሡም ላይ በእሪያ አምሳል ሰይጣንን አስወጣው። የንጉሡም አእምሮውና መልኩ እንደ ቀድሞው ተመለሰለት ነገር ግን ዳግመኛ እንዳይታበይ ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር አስቀረ ፈጣሪውም ተገዢ ይሆን ዘንድ ዳግመኛም የቤተ መንግሥት ሰዎችን ሁሉንም አዳናቸው ከላያቸውም አጋንትን አስወጥቶ ሰደዳቸው።
❤ ከዚህም በኋላ የአርማንያን ሰዎች ሁሉንም ሰበሰባቸውና ሥርዓትን ሠራላቸው ስምንት ቀንም እንዲጾሙ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ የእግዚአብሔርንም ሕግ እያስተማራቸው ኖረ። ዳግመኛም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆኑን አስተማራቸው ታላቆችም ታናናሾችም ትምህርቱን ተቀበሉት ለአርማንያ ሰዎች ሃይማኖትን የመቀበላቸው ምክንያት ይህ ነው።
❤ ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቃቸው ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ለመኑት እርሱም "እኔ ካህን ስለአልሆንኩ አይገባኝም ነገር ግን የሚያጠምቃችሁን ካህን ይልክላችሁ ዘንድ ወደሮሜ ሊቀ ጳጳሳት መልክተኞችን ላኩ" አላቸው። በዚያንም ጊዜ ከርሱ ጋር ወደ ንጉሥ አኖሬዎስና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ መልክተኞችን ልከው የአርማንያ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር እንደተመለሱ አስረዱአቸው ንጉሡም ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምተው ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ ለአርማንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሾመው ወደ አርማንያን ንጉሥ ወደ ድርጣድስም በክብር ላከው።
❤ ቅዱስ ጎርጎርዮስም ተሹሞ ወደ አርማንያ አገር በደረሰ ጊዜ በመምጣቱ ደስ ተሰኙበት እርሱም የአርማንያን ሰዎች ሁሉንም አጠመቃቸው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም ስም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው ሃይማኖንትም ከአጸናቸውና መልካም ጉዞንም ከፈጸመ በኋላ ታኅሣሥ15 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ15 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለሉቃስ_ዘፃመወ_ፃማ። በልብሰ ኀፂን ይትጋደል ወይትቃተል ምስለ መስቴማ። መዋዕለ ጾሙ ስዱስ እስከ ይትፌጸማ። ለዕርቅት ከርሡ እንዘ ይሠርዕ ዓቅማ። በዕለተ ሰንበት ይሴሰይ አሐደ ጳኵሲማ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_15።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ቀብፁኒ እምልብ ከመ ዘሞተ። ወኮንኩ ከመ ንዋይ ዘተኀጒለ። እስመ ሰማዕኩ ድምፀ ብዙኃን እለ ዐገቱኒ ዐውድየ"። መዝ 30፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 2፥5-12፣ ያዕ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31 ወይም 8፥18-26። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 15፥11-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ቆራይ የዕረፍታቸ በዓል፣ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ የመታሰቢያቸው በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
