1 756
订阅者
-124 小时
+97 天
+2630 天
帖子存档
Grade 11 Mathematics work sheet for mid exam 2018 E.C
Mathematis Second Semester Work sheet for mid exam 2018.docx0.32 KB
አልፋ ቀራንዮ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
ለመላው የት/ቤታችን የክርስትና እምነት ተከታይ
መምህራን፣ አስተዳደር ሠራተኞች፣
የተማሪ ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ የት/ቤታችን መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የተማሪ ወላጆች፣ ተማሪዎች እንዲሁም የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የመተሳሳብ እንዲሆን እንመኛለን።
መልካም በዓል
ት/ቤቱ
Repost from Tikvah-University
#ጥቆማ
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነው?
በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ አጋዥ የትምህርት ይዘቶች እና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድረ-ገፅ ያገኛሉ።
ይለማመዱ 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
@tikvahuniversity
Repost from Addis Ababa Education Bureau
12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸው የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎችን ይፋ ሆኑ።
(መጋቢት 24/2018 ዓ.ም) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎችን ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሠረት ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች በተፈጥሮ ሳይንስ እንግሊዝኛ ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዝክስ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ እንግሊዝኛ ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።
ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል።
የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት ላይ ያተኩራል።
ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
