ch
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 369 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 619,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 193

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 369 名订阅者。

根据 24 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -18,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.10%。内容发布后 24 小时内通常能获得 8.16% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 551 次浏览,首日通常累积 1 254 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

凭借高频更新(最新数据采集于 25 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 369
订阅者
+124 小时
+477
-1830
帖子存档
በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ

በአሰበ ተፈሪ /ጭሮ/ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእመናን እየወረወሩና ተኩስ መጀመራቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጹ። ምእመናን ከጠዋት ጀምረው ቤተ ክርስቲያኗን ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን የዞኑ የጸጥታ ኃይል "በሁለታችሁ አንገባም" በማለት ገለልተኛ ለመሆን ሞክሮ ውሏል። ነገር ግን ከመሼ ከክልል የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የክልሉ ልዩ ኃይልን ጨምሮ ተኩስ በመክፈት አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእምናን እየወረወረ መሆኑን ምእምናን በስልክ ገልጸውልናል። መረጃውን ያደረሱን ምእመናን አክለውም የጸጥታ ኃይሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከብቦ እየተኮሰና እያወከበ ቢሆንም ምእመኑ ግን ከግቢ አልወጣም ብሏል።

መንግሥት በአስቸኳይ መልስ የማይሰጥ ከሆነ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ! ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እሑድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በመላው ዓለም ተፈጻሚ የሚሆን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አደረገ። መንግስት የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ለተነሱ ወራሪ ቡድኖች ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱ ጾመ ነነዌን መላው ኦርቶዶክሳውያን ጥቁር ልብስ በመልበስ እና ወደ እግዚአብሔር በመፀለይ እንዲያሳልፉ ያዘዘ መሆኑ ይታወሳል። ሆኖም መንግስት በተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ከሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መነሻቸውን ያደረጉ እና ወደ መስቀል አደባባይ እና ወይም ወደ ባሕረ ጥምቀት ሐድረሻቸውን ያደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መመሪያ ሰጥቷል።

በአሁኑ ሰዓት የጸጥታ ኃይሉ የሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ሰብሮ በመግባት ውስጥ በሚገኙት ምእመናን ላይ እየተኮሰ በመግደል ላይ እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን በእንባ ጭምር ገልጸውልናል። (c)tmc

አሰላ +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ የከተማው ህዝብ በሌለበት ከበቆጂ የሌላ እምነት ተከታዮችን በአይሱዚ በማምጣት መንበረ ጵጵስናውን ሰብረው ገብተዋል። ስድስት ፓትሮል መኪና ያጀባቸው የክልሉ ልዩ ኃይል ሲሆን ከገቡ በኋላ በተሿሚው የገዳሟን ምዷየ ምጽዋት በመሥበር ለአጃቢዎቹ የፀጥታ ሰዎች ሕገ ወጥ ተሿሚው ገንዘቡን አድለዋል። የከተማው ፖሊስ ሊቀ ጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ያሬድን አፍኖ ምሽት ከከተማው ማስወጣቱ ይታወቃል።

#አስቸኳይ! ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል። +++++++++++++++++++++++++++++++++++ (ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ) የጸጥታ ኃይሉ ፎቅ ላይ በመሆን በቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ወዳሉት ምእመናን በስናይፐር እየተኮሰ ሲሆን በዚህም አንዲት ሴት ተገድላለች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናንና ምእመናት ቆስለዋል። ከውጪ በኩልም ሕገ ወጡ ቡድን ብር በመክፈል ያደራጃቸው ቡድኖች ድንጋይ በመወርወር ላይ ናቸው በዚህም የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብረውታል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ጌዲዮና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በተለያየ አቅጣጫ እየተተኮሰ እንደሆነና የጸጥታ አካላት የመከላከል ሥራ እንዳልሠሩ ገልጸዋል። የከተማዋ ነዋሪ ያልሆኑ ግለሰቦችን በመኪና ጭነው እያስገቡ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፣ ምእመናን አሁንም በጽናት እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አስቸኳይ! ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በስናይፐር የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል። የጸጥታ ኃይሉ ፎቅ ላይ በመሆን በቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ወዳሉት ምእመናን በስናይፐር እየተኮሰ ሲሆን በዚህም አንዲት ሴት ተገድላለች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናንና ምእመናት ቆስለዋል። ከውጪ በኩልም ሕገ ወጡ ቡድን ብር በመክፈል ያደራጃቸው ቡድኖች ድንጋይ በመወርወር ላይ ናቸው በዚህም የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብረውታል።

"መንግስት ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው" - ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ) ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን አስመልክቶ ጥሪ አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤተ ክርስቲያን እና በክርስቲያኖችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የማሳደድ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቀዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ እናስከብራለን በሚል በትግራይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነውም ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል። የተፈጸመው ድርጊት ከዘር ጭፍጨፋ የሚተናነስ አይደለም ያሉት ብፁዕነታቸው የሕዝቡን ሰብዓዊ መብት ካላስከበረ መንግሥትነቱ ምን ላይ ነው ሲሉም ጠይቀዋል። ብፁዕነታቸው ለሻሸመኔ እና ምዕራብ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ከዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ያልተናነውን ይህንን ዘመን በጾም በጸሎትና በክርስቲያናዊ ጥንካሬ እንዲያልፉ ያሳሰቡ ሲሆን የፌደራልና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚፈስሰውን በግፍ የኦርቶዶክሳውያን ደም እንዲያስቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። #TMC_Addia_Ababa