Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 613 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 374,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 203 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 613 名订阅者。
根据 07 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 51,过去 24 小时变化为 11,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 7.91%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.59% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 235 次浏览,首日通常累积 716 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 08 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 613
订阅者
+1124 小时
+707 天
+5130 天
帖子存档
መጻጉዕ ነኝ እኔ ፥ ኀጢአት ያቆሰለኝ ፤
የነገውን ሳይሆን ፥ ዛሬን አይተህ ማረኝ ።
ኋላም እንዳልክድህ ፥ አቁመው መስካሪ ፤
አድርገኝ ጌታዩ የሰንበት ተማሪ ።
፠፠ከገጽ ተከታያችን የተላከ | ኀ/ገብርኤል | 2013 ዓ.ም
#መፃጕዕ፤ አራተኛው ሳምንት
አራተኛው ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡ በመፃጕዕ የተሰየመው የእርሱ ስህተት ለእኛ ትምህርት፥ ተግሳጽ እንዲሆነን እንጂ፤ በዚህ ሳምንት የሚታሰበው ጌታችን ሕሙማን መፈወሱን፣ ሙት ማስነሳቱ ነው ፡፡ ስለ ረቂቁ የነፍስ ደዌ ስለ ኀጢአትና ስለ ድኅነታችን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ማቴ. 8፥1-37፣ ማር. 7፥13-37፣ ሉቃ. 17፥1-9፣ ዮሐ. 5፥1-18
በቤተክርስቲያን በሽተኞች በሦስት ስያሜ ይጠራሉ፡-
፨ #በሽተኛ፤ የዕለት ሕመም ወይም እስከ አንድ ዓመት የታመመ ሰው፡፡
፨ #ድውይ፤ እስከ አምስት ዓመት ሕመሙ የቆየበት፡፡
፨ #መፃጕዕ፤ ከአምስት ዓመት በላይ ሕመሙ የጸናበት፤ ሲሆን ድውይ፥ በሕመም የሚማቅቅ፥ የዐልጋ ቊራኛ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ #መፃጕዕ የተባለው ስለሕመሙ #38_ዓመታት_መጽናት_እንጂ ስሙ አይደለም፡፡
በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ትርጕሙ /የምሕረት ቦታ/፤ በግእዙ ቀላየ አባግዕ (የበጎች መዋኛ) በተባለች ምጥምቃት ዘጵሩጳጥቄ በምትባል የጠበል መጠመቂያ ኩሬ ዳር የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፥ እውሮች፥ አንካሶች፥ ልምሾች፥ ሰውነታቸው የሰለለ የደረቀና ያበጠ ብዙ ድውያን ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የምሕረት ፈውስ ይዞ በሳምንት አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ባርኮ ሲሄድ ቀድሞ የገባው በሽተኛ ይፈወስ ነበር፡፡
ተስፋ ሳይቈርጥ ለ38 ዓመታት ድኅነትን እየጠበቀ በሕመሙም እተሰቃየ በዚያ የተኛ አንድ ሰው ነበር፡፡ ጌታችን ይህን ሁሉ ዓመት እንደተሰቃየ አውቆ ድኅነት ሊሰጠው ወዶ መጣ፡፡ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡
መጠየቁ ፍጹም የሰውን ሥጋ እንደተዋሐደ ሲያጠይቅ ነው፡፡ በተጨማሪም በዕለተ ዐርብ ‹‹ራሱ አዳነኝ እንጂ መቼ አድነኝ አልኩት!›› ብሎ ለመክሰስ ምክንያት እንዳያገኝ ጠየቀው፡፡
‹‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም›› አለው፡፡ ‹‹እንዲህ ያለው የ30 ዓመት ጎልማሳ ነውና አንስቶ ይጨምረኛል›› ወይም አምስት ገበያ የሚያህል ሕዝብ ይከተለው ነበርና ‹‹ከእነርሱ መካከል አዞልኝ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል›› ብሎ ነው እንጂ እንዲሁ ይፈውሰኛል ብሎ አልነበረም፡፡ ጌታ ግን ለመዳን መውደዱን ተመልክቶ ‹‹ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› አለው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኘው ፍጹም ድኅነት ነውና ወዲያው ሰውየው ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሔደ፡፡ ያን ሰውም ጌታችን በምኵራብ አገኘውና እነሆ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል እወቅ አለው፡፡
አልጋውንም ተሸክመህ ሂድ ያለው 38 ዓመት የተሸከመችው ጠንካራና የብረት አልጋ ስለተሸከመ ፍጹም መዳኑ እንዲታወቅ ነው፡፡ መጻጕዕ የተፈወሰው በእለተ ቀዳሚት ስለነበረ ፤ በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት፣ ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር፡፡
በሽተኛው የተደረገለትን ተአምር ረስቶ በዕለተ ዐርብ ጌታን ከሰሰው፤ በጥፊም መታው ወዲያው እጁ ሰለለ፡፡
#ቅዱስ_ያሬድም ጌታችን ሰንበትን ለዕረፈት ስለፈጠራት፤ ሕሙማንን በመፈወስ (#የመቶ አለቃውን ልጅ በመፈወስ ማቴ. 8፥1-15፤ #የዕውራንን ዓይኖች በማብራት ማቴ. 20፥24-30፤ ዮሐ. 9፤ #ሽባ የነበረውን በመፈወስ) #በዕለተ_ሰንበት_ከበሽታቸው_እንዲያርፉ_አደረገ፡፡
በእኛ በሰው ልጆች ላይ በሽታ በተለያየ ምክንያት ይመጣል፡፡
† በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ፡፡ ዘኍ. 21፥4-9
† የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገለጥ ዘንድ የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ ዮሐ. 9፥13
† ሰዎች ከእግዚአብሔር ዋጋ እንዲያገኙበት ከዲቢያሎስ የሚመጣ የፈተና በሽታ አለ እንደ ጻድቁ ኢዮብ፡፡ መጽ.ኢዮብ
† ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ እንዳይታበዩ ማሳወቂያ የሚሆን በሽታ አለ፤ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ራስ ምታት፡፡
† የበደለውን የሚቀጣበት በሽታ አለ፤ እንደ ሳዖል አጋንንት አድሮበት ይሰቃይ ነበር፣ የመጻጕዕ እጁ የሰለለው በሁለተኛ በደሉ ነው፡፡
† ያልታመመው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን፥ የታመመው ምሕረትን እንዲለምን የሚመጣ በሽታ አለ፡
https://t.me/medihanaelem
http://www.finotehiwotsundayschool.com
እጅግ ውብ ጥቅሶችን በድረ ገጻችን 👉
www.finotehiwotsundayschool.com
የሰንበት ትምህርት ቤታችንን ድረ-ገጽ ይጎብኙ ። ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ያግኙ ።
www.finotehiwotsundayschool.com
የሰንበት ትምህርት ቤታችንን ድረ-ገጽ ይጎብኙ ። ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ያግኙ ።
www.finotehiwotsundayschool.com
ፍርድ ቤቱ የሕገወጥ ቡድኑን መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከጠየቀችው ዘጠና ቀናት ውስጥ የ፵፭ ቀናት የእግድ ትዕዛዝ ወሰነ።
(©ኢኦተቤ ቴቪ የካቲት ፴/፳፻፲፭ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጸመው ሕገወጥና ኢቀኖናዊ ድርጊት ምክንያት በሕግ አግባብ የሚፈቱ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ መብት እና የአማኞችን ሁለንተናዊ መብት እንደከበር ያስችል ዘንድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ ባለሙያዎች የጠበቆች ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዮችን በሕግ አግባብ እንዲፈቱ እየጠየቀችና እየተከታተለች እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ መሠረት የጠበቆች ቡድኑ ዛሬ የካቲት ፴/፳፻፲፭ ዓ/ም በዋለ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ችሎት የሰጠውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በጥልቅ ማብራሪ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም ፍርድቤቱ የቤተ ክርስቲያኗን ሕጋዊ ጥያቄ በሕግ አግባብ መልካም ውሳኔ የሰጠበት መሆኑን ግልጽና ጥልቅ በሆነው ገለጻው ተጠቁሟል።
የጠበቆች ቡድኑ በመግጫው ሕገወጦቹ ያቀረቦቻው የመቃወሚያ ጉዳዮች እንደነበሩ አብራርቶ ፍርድቤቱ በውሳኔ ውድ አድርጓቸዋል ብሏል።
ፍርድቤቱ ውድቅ ካደረጋቸው መቃወሚያ መከራከሪያ ነጥቦች መካከል
፩. ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ሰውነት ያላት በመሆኑ የመክሰስና የመከሰስ መብት የለት መሆኑንና በጉዳዩ ላይ ክስ መመስረት እንደምትችል።
፪. ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የመብት ጥሰት የንብረት ባለቤትነት ያለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት የሚችል መሆኑ በመጥቀስ የሕገወጡ ቡን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድ አድርጓል።
በአጠቃላይ በሕገወጡ ቡድን የቀረቡ መቃወሚያዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረግ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጡ ሹመት ላይ በተሳተፉ ፳፮ቱ ግለሰቦች ላይ ክስ እንድትመሠርት ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ በጠየቀችው የሦስት ወር እግድ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤቱ ፵፭ ቀናት ከሦስቱ "አባቶች" በስተቀር ፳፮ (26)ቱም ግለሰቦች
ከዚህ ቀደም የገቡበትን መንበረ ጵጵስና እና አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ "የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሏትን ይዞታዎች፣ አህጉረ ስብከት፣ገዳማት እና አድባራት፤ አብያተ ክርስቲያናት ንብረቶቿን፤ ታሪካዊ ቅርሶች፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ መገልገያ እንዳይጠቀሙ፣ ወደ ቅጥሯ እንዳይገቡ፤ ንብረቶቿን እንዳይወስዱ፣ እንዳይገለገሉ፣ ዓርማዋንና ስሟን እንዳይጠቀሙ ይህ ጊዜያዊ የዕግድ ትዕዛዝ ለአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀናት ብቻ (ከየካቲት ፫/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ድረስ ብቻ ተሰጥቷል"።
መባሉን የጠበቆች ቡድን በመግጫው አሳውቋል።
ከዚሁ ጋር የኦርዶክሳውያን የእስር ሁኔታ የተነሳ ሲሆን በአብዛኛው እየተፈቱ መሆናቸውን ጠቅሶ በሻሸመኔና በአርሲ ነገሌ አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን እስረኞ ለመጋቢት ፯፳፻፲፭ ዓ/ም ፍርድ ቤት እንደተቀጠሩም ተጠቅሷል።
በዚህ ረገድ የሕግ ተርጓሚ አካላት ላይ የሚታየው ፍትሕን የማስፈን ተጠቃሽ ሥራዎችን በመመዘርዘር በፍርድ ቤቶች የሚስተዋለው ፍትሕን የማስፈን መንገድ የሚበረታታና የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሰው የጠበቆች ቡድኑ በአስፈጻሚ አካላት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የታየው የፍረድ ቤቶችን ውሳኔ ያለማስፈጸም ሁኔታዎች በእጅጉ ሊታረሙ እንደሚገባም ገልጿል።
በሌላ በኩል "በፓስተር ዮናታን" እና "በፓስተር ኢዩ ጩፋ" የቀረበው ክስ ምን ላይ ደረስ? ለሚለውም በምላሹ ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን እያስኬደው እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የጠበቆች ቡድኑ የሕጉን መንገድ ተከትሎ የቤተ ክርስቲያን መብትና ማስጠበቅ ሁነኛ ግቡ መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን ይሁን እንጂ የትኛውም መንገድ ይሁን ድርጊት ከቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ከአባቶች ቃል የማይቀድምና የማይበጥል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የምትከተላቸውን የይቅርታና የስምምነት አቅጣጫዎችን በማክበረ እንደሚቀጥል ገልጿል።
#የሚዳሰሰው_መጽሐፍ ፤ በዓላት ምን ? ለምን ? እንዴት ?
#የመጽሐፉ_ይዘት ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለምታከብራቸው በዓላትና ምክንያት፣ ስለ በዓላት ምንነትና የት መጣነት፣ በበዓላት ላይ ስለሚነሱ ጥያቄዎች ለተሳሳቱ አረዳዶች በማስረጃና በአመክንዮ የሚያቀርብ መጽሐፍ ነው ።
#ሐሙስ የካቲት 30 ምሽት 12 ፡ 30
#Orthodox_Book_Review
መረጃ!
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት መቀመጫ አሰላ ከተማ መንበረ ጵጵስናው በሚገኝበት ደብረ ምጽላል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የዛሬ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ሥርዓተ ቅዳሴ ታጉሏል።
ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው ለዚህ ምክንያቱ ለሀገረ ስብከቱ ተሹሜያለሁ ያለው ግለሰብ ከሌሎች ሦስት ተሿሚዎች ጋር በመሆን በ5 ፓትሮል መኪና የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች ታጅቦ ቤተ ክርስቲያኗን ለመውረር እየሞከረ በመሆኑና ውጥረት በመንገሱ ነው።
በትናንትናው ዕለት የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በሕገ ወጥ መንገድ “ኤጲስ ቆጶስነት” ከተሾሙት ግለሰቦች መካከል አንዱ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነኝ በማለት ወደ ሀገረ ስብከቱ መምጣታቸው ተገልጿል፡፡
የግለሰቡን ወደ ሀገረ ስብከቱ መግባት ተከትሎ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውጭ አንቀበልም በማለት ከአገልግሎት ቦታቸው ሳይገኙ ቀርተዋል።
ይህንን መነሻ በማድረግ ሕገ ወጥ ተሿሚው ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሥራ እንድትገቡ የሚል የማስጠንቀቂያ መልእክት የተጻፈላቸው ሲሆን ማስጠንቀቂያውም የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ የአርሲ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በሚል በሕግ ዕውቅና የሌለው ማኅተም የተጻፈ ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ውስጥ በጋራ ሃገራዊ እና ማኅበረሳባዊ ጉዳዮች ላይ በአንድነት ይሰራል ተብሎ ከሚታመንበት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት በዚህ መልኩ ለማበላሸት በመሪዎቹ አማካይነት ለሰራው ሕገወጥ ሥራ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል። tmc
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደረ ገጽ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መረጃዎችን በይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና ተቋማዊ የመረጃ ፍሰትን ለመተግበር አዲስ ድረ ገጽ ከፍታለች፤ ድረ ገጹ በተለይም በውጭ አገራት የሚገኙ ምዕመናንን በእጅጉ የሚጠቅም ስለሆነ በማስተዋወቅ እንድትተባበሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።ሁላችሁም ሼር አድርጉት።
ድረ ገጹ https://eotceth.org
ድረ ገጻችንhttp://www.finotehiwotsundayschool.com
መረጃ!
በሻሸመኔ ከተማ ከአርባ በላይ ኦርቶዶክሳውያን በጸጥታ አካላት እንዲገደሉ ያደረገው ሕገ ወጡ ቡድን በዚህ ሰዓት የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን በመውረር ጸሎተ ምሕላ እያደረሰ ይገኛል።
እንደ መረጃ አድራሾቻችን ገለጻ ይህ ድርጊት በጊዜ መፍትሔ ካልተሰጠው ተጨማሪ እልቂት መፈጠሩ የማይቀር ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
