Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 411 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 577,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 191 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 411 名订阅者。
根据 11 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 64,过去 24 小时变化为 24,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 24.26%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.47% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 737 次浏览,首日通常累积 1 458 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 23。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 12 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 411
订阅者
+2424 小时
+237 天
+6430 天
帖子存档
#የዐርብ_ፎቶ_ስብስብ_፬፤ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ፤ ስቡሐ ዘተሰብሐ፡፡ /ጸሎተ ሙሴ ፩/
ይባርክዎ ኵሉ ግብረ እግዚእ ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፡፡ /መዝ.ሠለ.ደቂቅ ፩/
ንኡስ አነ እምአኃውየ፤ /መዝ.፻፶(፻፶፩)፥፩-፰/
ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ፡፡ /መዝ.፻፴፭፥፩/
እግዚኦ ኢትጸመመኒ ፤ ለይሁዳ ወልዱ ወለውሉደ ውሉዱ ይደምሰስ፡፡ /መዝ.፻፰፥፩/
ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥአን ፤ ከአንባቢው ጋር ያስተዛዝሉ:: /መዝ.፩፥፩/
(2ቱ ፎቶዎች ከ2008ዓ.ም. ከመዛግብችት ክምትችት ክፍላችን የተወሰዱ ናቸው፡፡/
#የዐርብ_ፎቶ_ስብስብ_፫፤ ጥብጣብ ወ፬፻ እግዚኦታ
#የዐርብ_ፎቶ_ስብስብ_፪፤ ዐርብ፤ ኪራያላይሶን ኪራያላይሶን ኪራያላይሶን፡፡ (በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ)
#የዐርብ_ፎቶ_ስብስብ_፩፤ ኪራያላይሶን ኪራያላይሶን ኪራያላይሶን፡፡ (በቤተ ክርስቲያን ውስጥ) በሥራና በትምህርት ለራቃችሁ፤ የቀጨኔው ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ውል ውል ለሚልባችሁ ይኸው ውሎውን ዘግበንላችኋል፡፡
ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘዐርብ ሰሙነ ሕማማት፡፡
እየሰገድን የምንላቸው ቃላት፡፡ እግዘኦ ተሣሃለነ፣ ለከ ኀይል፣ ለአምላክ ይደሉ፣ ኪራያላይሶን ኪራያላይሶን፡፡ ……..
፠፩ኛ ስግደት፤ የወንጌል ምንባብ እንዳበቃ በማስከተል ተግሣጽ ተነቦ እንደተፈጸመ፤ ‹‹ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ መካን›› የሚለውን ካህኑ ሲመራና ዲያቆኑ በየምዕራፉ ቃጭል ሲደውል፤ ሕዝቡ እየተቀበሉ እግዚኦ ተሣሀለነ (አቤቱ ይቅር በለን) በማለት ፳፪ት ጊዜ በግእዝ፥ በዕዝልና በአራራይ ዜማ እያዜሙ ይሰግዳሉ፡፡
፠፪ኛ ስግደት፤ በመቀጠል ‹‹ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት›› የሚለውን ምቅናይ በመሪና በአንሺ ወገን መቀባበል ፲፪ ጊዜ ይበሉ፤ በመጨረሻም በ፲፫ኛው ከ‹‹ለከ ኃይል›› እስከ ‹‹ዕብል በአኰቴት›› ድረስ አንድ ጊዜ በኅብረት ይበሉ፡፡ /ከሆሳዕና ሠርክ እስከ ሰኞ ሰርክ መሪ በቀኝ፤ ተመሪ በግራ ሲሆን፡፡ ከማክሰኞ ሠርክ ጀምሮ ግን መሪ የነበረው ተመሪ፤ ተመሪ የነበረው መሪ ይሆናል፡፡/
#ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም፤
አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፤
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም፤
ኃይልየ ወፀወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት፤
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፥ ትምጻእ መንግሥትከ፥ ወይኩን ፈቃድከ፥ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር፥ ሲሳየነ ዘለለዕለትነ፥ ሀበነ ዮም፥ ኅድግ ለነ፥ አበሳነ ወጌጋየነ፥ ከመ ንህነኒ ንኅድግ፥ ለዘአበሰ ለነ፥ ኢታብአነ፥ እግዚኦ ውስተ መንሱት፥ አላ አድኅነነ፥ ወባልሐነ፥ እምኵሉ እኩይ፥ እስመ ዚአከ፥ ይእቲ መንግሥት፥ ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም፡
፠፫ኛ ስግደት፤ በመቀጠል ‹‹ለአምላክ ይደሉ››ን መጀመሪያ በመሪ እየቀደሙ በአንሺ እየተከተሉ አንድ ጊዜ ይዝለቁ፤ በ፪ኛው ክፍል ደግሞ እያስተዛዘሉ ፩ድ ጊዜ ይበሉ፡፡
ለአምላክ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለሥሉስ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለማሕየዊ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለዕበዩ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለዕዘዙ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለመንግሥቱ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለሥልጣኑ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለምኵናኑ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለኢየሱስ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለክርስቶስ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለሕማሙ ይደሉ፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ለመስቀሉ ይደሉ (ለዐርብ ብቻ)፤
ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡
ቀጥሎ ያለውን የመዝጊያ ጸሎት እያዜሙና እየሰገዱ ፫ት ጊዜ መላልሰው ይዝለቁት፡፡
ለከ ይደሉ ኃይል፥
ወለከ ይደሉ ስብሐት፥
ወለከ ይደሉ አኰቴት፥
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም፡፡
፠፬ኛ ስግደት፤ ዜማው አሁንም በቀኝና በግራ በመቀባበል ነው የሚባለው፡፡ በመሪ ወገን እየቀደሙ፤በአንሺ ወገን ደግሞ እየተከተሉ ፩ድ ጊዜ ይዝለቁ፤ ቀጥለውም በመሪና በተመሪ ወገን እያስተዛዘሉ ፩ድ ጊዜ ይዝለቁ፡፡
መሪ፤ ክርስቶስ አምላክነ፥ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ፥ በሕማማቲሁ ቤዘወነ፤
ተመሪ፤ ንሰብሖ፥ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፥ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በብዝኀ (በዕበየ) ሣህሉ፡፡ /በዐርብ፤ ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ/
#ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን
ኪርያላይሶን፥ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ እብኖዲ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ታኦስ
ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ማስያስ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ኢየሱስ
ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ክርስቶስ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ አማኑኤል
ናይናን/ናይን/፥ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ትስቡጣ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፡፡
ኪርያላይሶን የሚለውን ብቻ በመሪ ፳፩ ጊዜ፥ በተመሪ ወገን ፳ ጊዜ ይበሉ፤ ድምሩ ፵፩ ኪርያላይሶን ይኾናል፡፡
የየሰዐቱን መልክአ ሕማማት ያድርሱ፡፡
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/
‹‹ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል፡፡›› መዝ. 40፥1
የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት በከተማችን ብሎም በሃገራችን በትንሣኤ በዓል ነዳያንን በማስፈሰክ አገልግሎት ቀዳሚው እንደኾነ ይታወቃል፤ ይህንንም አገልግሎት ለከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በ1961ዓ.ም. በአንድ በግ ተጀምሯል፤ ሲጀመርም ነዳያንንና በአካባቢው ያሉ የአቅም ማነስ ያለባቸውን ምዕመናንን ታሳቢ አድርጎ ነው። በ1964ዓ.ም. ደግሞ ወደ 2 በግና አንድ እናት ባመጡት 1 ሌማት እንጀራና 1 ብረት ድስት ወጥ ከፍ አለ፨ እያደረ ወደ በሬ አደገ፨ በየዓመቱ እንደሚደረገው ዘንድሮም ነዳያንን፣ በጸበል ቦታ ያሉትን፣ በገዳም ውስጥ ያሉትን መነኰሳትና የአብነት ተማሪዎች ለማስፈሰክና ለመርዳት የሚያስፈልጉትን (ገንዘብ፣ ልብስ፥ ሳሙና፥ ንጽሕና መጠበቂያ፣ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፣ የተማሪዎች የመማሪያ ቊሳቊሶችን) እንድትረዱ በመድኀኔዓለም ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
#ጸሎተ_ሐሙስ_ወሕጽበተ_እግር_
ሐዋርያቲሁ ከበበ፥
እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ፤
ኮኖሙ አበ ወእመ፤
ወመሐሮሙ ጥበበ፡፡
(ሐዋርያቱን ሾመ፤
የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ፤
አባትና እናት ኾናቸው፤
ጥበብንም አስተማራቸው፡፡)
/ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ/
