Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 042 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 280,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 240 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 042 名订阅者。
根据 29 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 518,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.50%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.35% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 090 次浏览,首日通常累积 1 660 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 33。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 30 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 042
订阅者
+124 小时
+917 天
+51830 天
帖子存档
ታሪከ አቡነ ተክለሃይማኖት ወቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ፡፡ /ከቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/
✤✣✤ #ቅዱስ_ቶማስ_ዘመርዓስ_
የመርዓስ ኤጵስ ቆጶስ የነበረው አባት አባ ቶማስ ክርስቶስን በማመን በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ፣ ቀንና ሌሊት በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖችም በመራራት ተጠምዶ የሚኖር ነበር። በዚህ ፅናቱ የክብር ባለቤት ጌታችን መርዓስ ለሚባል አገር ኤጲስ ቆጶስ ይሆን ዘንድ መንጋውንም ይጠብቅ ዘንድ መረጠው አባታችን ቶማስም ሐዋርያዊ ተልዕኮውን እየፈፀመ፣ ሕዝቡን እየመራ ሳለ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሱ ላይ፣ በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ላይም ተነሳባቸው፣ ክርስቲያኖችንም ያሰቃያቸው ጀመር በአንድ ወቅት ከመኳንንቶች አንዱ የነበረው፣ ቅዱስ ቶማስን ወደ እርሱ ያቀርቡት ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ እነርሱም እየደበደቡ በምድር ላይ እየጎተቱ ወሰዱት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ ከዚህም በኋላ መኮንኑ ቅዱስ ቶማስን ለአማልክት ስገድ አለው ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት «እኔ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ ጣኦታት አልሰግድም ለረከሱ ጣዖታት የሚሰግድ ሁሉ የተረገመ ነውና» በዚህም ጊዜ መኮንንኑ በጣም ተቆጥቶ እጅግ የበዛ ስቃይን አሰቃየው የነዳጅ ድፍድፍን አፍልተው በላዩ በአፉና በአፍንጫው እስከመጨመርም ደረሱ ልባቸው እንደ ድንጋያ የፀና ስለ ነበር ቅዱስ ቶማስን ገድለው ቶሎ ማሣረፍ አልፈለጉም ይልቁንም የስቃዩን ዘመን አስረዘሙ እንጂ እርሱም ስለ ስህተታቸው ይዘልፋቸው ነበር፣ እንደ ማይመልስም ሲገባቸው በጨለማ ቦታ ጣሉት በየዓመቱም ወደ እርሱ እየሄዱ ከሕዋሳቱ አንድ፣ አንዱን ይቆርጡ ነበር፡፡ በዚህም ለሃያ ሁለት(፳፪) ዓመት ቆየ ሲቆይ ግን አፍንጫውን፣ ከንፈሮቹን፣ ጆሮዎቹን፣ እጆቹንና እግሮቹን ቆርጠው ነበር፤ በዚህም ምክንያት የአገሬው ሰው ሞቷል ብለው አስበው በየዓመቱ መታሰቢያ ያደርጉለት ነበር ይህ ለምን ሳይሞት ቢሉ ጊዜው ሲረዝም ቢሞት ነው እንጂ እስካሁንማ ይመጣ ነበር ብለው ስላሰቡ ነበር፤ ነገር ግን ከሕዋሳቶቹ አብዛኛው ክፍል ቆርጠው ቢጥሉትም አካሉ ግን ተቆራርጦ ሲጣል አንዲት ሴት አየችው፣ ይህችም ሴት በሌሊት ወደርሱ ተሠውራ በመሔድ ትመግበው ነበር፡፡
ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም እስከነገሠና የቀናች የክርስቶስን ሃይማኖት ክብር እስከገለጥ ድረስ እንዲህ ሲሰቃይ ኖረ፡፡ ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ ስለክርስቶስ በመታመን የታሠሩ እስረኞች ሁሉ እንዲፈቱ በማዘዙ ሁሉም ተፈቱ፡፡ ቅዱስ ቶማስ ግን የተጣለበት ቦታ፤ በሕይወት ያለም ስላልመሠላቸው አላወጡትም ነበር፤ ነገር ግን ይህን አዋጅ ትመግበው የነበረችው ሴት ሰምታ ነበርና ወደ ካህናቱ ዘንድ ሄዳ ስለ ቅዱስ ቶማስ ሃያ ሁለት ዓመት በዚያ ስለመኖሩ ነገረቻቸው ቦታውንም አመለከተቻቸው እነርሱም ባገኙት ጊዜ አንስተው ተሸከሙት እየዘመሩና እያመሰገኑም ወደ ቤተ ክርስቲያን አደረሱት በቤተ መቅደስ ፊት ለፊት በወንበሩ ላይ አስቀመጡት ምእመናንም ሁሉ ወደርሱ እየመጡ ከርሱ ይባረኩና የተቆረጡ ሕዋሳቱንም ይሳለሙ ነበር፡፡ ከቦታ ቦታ ይዘዋወር የነበረውም በቅርጫት ኹኖ በዘህያ ላይ ተጭኖ ነው፡፡
ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ የከበሩ ፫፻፲፰ ኤጲስ ቆጶሳትን (ሠለስቱ ምዕት) የአንድነት ጕባኤን በኒቂያ አገር በሰበሰበ ጊዜ ይህ አባት (ቅዱስ ቶማስ) ከሠለስቱ ምዕት አንዱ ነበር፤ ወደ ኒቅያ ጕባኤ በቅርጫት ሁኖ በአህያ ተጭኖ እየሄደ መሆኑን አርዮሳውያን ሲሰሙ፤ ቶማስማ በጕባኤው ከተገኘ ተከራክሮ ይረታናል አንችለውም በማለት መንገድ ላይ ባደረበት ይዘውት ይጓዙት የነበሩትን አህዮች በጨለማ በሰይፍ መተዋቸዋል፤ ነገር ግን ሌሊት ሊነጋጋ ሲል ለመንገድ ሲነሱ ቶማስ በተዓምራት አግልጋይ ረድኡን የተቆረጡትን የአህያዎቹን አንገታቸውን ከሰውነታቸው አጋጥመው ይነሳሉ ብሎ ሲያዘው የአንዱን አህያ ከሌላኛው አህያ ቢያጋጥመውም ቅሉ አህዮቹ ሕይወት አግኝተው ጕባኤ ኒቅያ አድርሰውታል፤ በዚያም አርዮስን መልስ እስኪያጣ ድረስ በጽናት ሲከራከረውና መልስ ሲያሳጠው የጕባኤው ሊቀ መንበር ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እስኪደነቅ ድረስ በማየቱ ሃይመኖትስ የእነ ቶማስ ዘመርዓስ ነች ብሎ አጽንቶ ወስኗል፡፡ በጕባኤውም አርዮስን ተከራክረው ከረቱ በኋላ አውግዘው ለይተውታል፤ ከዚህ በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራቸውና እንደመራቸው የሃይማኖትን ትምህርት በአንደበታቸው ተናገሩ፤ ሕግና ሥርዐትን ሥጋዊና፤ መንፈሳዊ ፍርድንም ሰሩ። ቅዱስ ቶማስ ወደ መንበረ ሢመቱ ከተመለሰ በኋላ ካህናቱና መንጋዎቹን ሁሉ ሰብስቦ አነበበላቸው እርሱንም እንዲያስተውሉት እንዲጠበቁትም በመጠበቅም እንዲጸኑ አዘዛቸው፡፡ ይህ አባት ለ፵ ዓመት ያህል በሢመቱ አገልግሎ በነሐሴ ፳፬ ቀን አርፋል፡፡
ታሪከ አቡነ ተክለሃይማኖት ወቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ፡፡ /ከቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/
✤✣✤ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_
አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1186 ዓም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ (እቲሣ) ተወለዱ፡፡ አባታቸው ጸጋ ዘዓብ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው አካባበቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻንና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡
በሰባት ዓመታቸው ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለክህነት መጠራት በዚህ ዓለም ትዳር መሥርቶ፣ የዓለሙንም ሥራ ሠርቶ መኖር አያስፈልግም ከሚል ፍልስፍና የመነጨ አይደለም፡፡ ከ8ኛው መክዘ ጀምሮ በሀገሪቱ የመንፈስ መቀዛቀዝ ይስተዋል ነበር፡፡ ዮዲት ጉዲት መንግሥቱን ይዛ በክርስትናው ላይ ከዘመተች በኋላ ሰሜኑ እና ደቡቡ ተቆራርጧል፡፡ የሐሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ኢትዮጵያዊ ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህ ነው የተክለ ሃይማኖት የጥሪ ምክንያት፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባታቸው ዕረፍት በኋላ ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው ለወንጌል ስብከት ወጡ፡፡ የዋልድባው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ከመሄዳቸው በፊት ቅስናን ተቀብለው በሸዋ እና በዳሞት ማገልገላቸውን ይገልጣል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዳሞት እና በሸዋ ካገለገሉ በኋላ መጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ላይ ገዳማቸውን ደብረ ጎል ገድመው ወደሚገኙት ታላቁና ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወደኾኑት ጻድቅ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ዐሥር ዓመት (12 የሚልም አለ) በትምህርት እና በሥራ (በአርድእትነት) አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡
ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እንደሚለው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ሐይቅ የገቡት በሠላሳ ዓመታቸው ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን በሸዋ እና በወላይታ ያገለገሉት ገና በወጣትነታቸው ጊዜ መሆኑን ነው፡፡ በ1216 ዓም አካባቢ ወደ ሐይቅ የገቡት አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሐይቅ ከመመንኰሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኰሱም በኋላ ሦስት ዓመት በትምህርት፣ በሥራና በአገልግሎት ቆይተዋል፡፡
ሐይቅ እስጢፋኖስ በዚያ ዘመን እንደ አዳሪ ትምህርት ቤት ያለ ዩኒቨርሲቲ ነበረ፡፡ ወደዚያ የሚገባ ሁሉ ሦስት ነገሮችን ይማራል፡፡ ትምህርት፣ የጥበበ እድ ሥራና ሥርዓዐተ ምንኵስና፡፡ ትምህርቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን መላ ትምሀርት ያካትታል፡፡ የሞያ ትምህርቱም መጻፍ፣ መደጎስ፣ ሕንፃ ማነጽ፣ ልብስ መሥራት፣ እርሻ፣ የከብት ርባታና የሥዕል ሥራን ይመለከታል፡፡ ከእነዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ጽሙድ እንደ ገበሬ፥ ቅኑት እንደ በሬ እንዲሆኑ ሥርዐተ ምንኩኵስናን ይማራሉ፡፡
በእነዚህ ትምህርቶች የታነፁት መነኮሳት ከገዳሙ ሲወጡ ዛሬ የፒኤች ዲ ተማሪ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚያቀርበው የተማሩትን ጽፈው አንድ የብራና መጽሐፍ አዘጋጅተው ይወጣሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ሐይቅ ከስምንት መቶ መነኰሳት በላይ በአንድ ጊዜ የሚማሩባት በመኾኑ በመጻሕፍት የበለጸገች መካነ አእመሮ (ዩኒቨርሲቲ) ነበረች፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እዚህ ገዳም ዐሥር ዓመታትን አሳልፈዋል፡፡
ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዐተ ምንኵስና እና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ ሄዱ፡፡ በዚያም ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ሥርዐተ ምንኵስና እና ጥበበ እድ ሲማሩ ሰባት ዓመት አሳለፉ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡ በደብረ ዳሞ የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው በገመድ ሲወርዱ ሰይጣን በቅንዐት መጥቶ ገመዱን በጠሰባቸው እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወቅት ነበር የሚበሩበትን እንደ መላእክት ክንፍ የሰጣቸው፡፡
ቀሪዎቹን አምስት ዓመታት ሌሎችን የትግራይ ገዳማትና ዋልድባ ገዳምን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆይተው ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለዐሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ በስብከታቸው እንደገና ለነቃው ለመካከለኛው እና ለደቡብ ኢትዮጵያ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኵስና፣ ትምህርትና ሥራ፡፡ መነኰሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡
ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፍተው ካደላደሉ በኋላ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡
አቡነ ተክለሃይማኖት አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ ሃያ አራት ቀን 1287 ዓም በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡ ጸሎታቸውና በረከታቸው ረድኤታቸውና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
እንኳን ለዕረገተ ማርያም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ሥርዐተ ማኅሌቱን እነሆ ብለናል፡፡
ምስባኩ ከድምፅ ጋር ዘነሐሴ ፲፭
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_#ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ዘነሐሴ_፲፭_#ክርስጢና_ስማዕት_ወ፫፼፰ወ፪#ማኀበራኒሃ_ወዕንባምሬና_ቅድስት_ወተጋብኦተ_ሐዋርያተ_ለግንዘተ_እሙ_ለእግዚእነ_ወለውረንዮስ_ሰማዕት_፡፡
#የቅዳሴ_ምንባባት
† ፩ኛቆሮ.፲፪፥፲፰-ፍጻ፤ ወይእዜኒ አስተናበሮ እግዚአብሔር፡፡
† ይሁዳ ፩፥፲፯-ፍጻ፤ ወአንትሙሰ አኃዊነ ተዘከሩ ቃለ ዘነገሩክሙ::
† የሐዋ.፩÷፲፪-፲፭፤ ወእምዝ ተሠውጡ ኢየሩሳሌም፡፡
#ምስባክ_መዝ. ፲፰፥፬
አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ፤
አው (ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ)፤
ወእስከ አጽናፍ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፡፡
ወውስተ ፀሐይ ሤመ ጽላሎቶ፡፡
(ትርጕም፤ቃላቸው ያልተሰማበት ነገራቸው ያልደረሰበት የለም፤ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ፤ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ፤ ጥላውንም በፀሐይ አኖረ፡፡)
#ወንጌል_
ማቴ. ፲፥፩-፲፭፤ ወጸውዖሙ ለ፲ወ፪ አርዳኢሁ፡፡
#ቅዳሴ_ዘሐዋርያት፤ ነአኵተከ እግዚኦ በፍቊር ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ፡
ምስባኩ ከድምፅ ጋር ዘነሐሴ ፲፬
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፲፬
#የቅዳሴ_ምንባባት
† ፩ኛ ቆሮ.፩፥፲-፲፱፤ አስተበቊዐክሙ አኀዊነ በስሙ ለእግዚእነ፡፡
† ያዕ. ፲፪፥-፳፪፤ ወብፁዕ ብእሲ ዘይትዔገሣ ለእኪት፡፡
† የሐዋ.ሥ.፲÷፴-፵፬፤ ወይቤሎ ቈርኔሌዎስ ረቡዐ ዮም፡፡
#ምስባክ_፵፫፥፬
ዘአዘዝከ መድኃኒቶ ለያዕቆብ፡፡
ብከ ንወግኦሙ ለኵሎሙ ፀርነ፡፡
ወበስምከ ናኀሥሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ፡፡
(ትርጕም፤ ለያዕቆብ ድኅነትን ያዘዝኽለት፤ በአንተ ጠላቶቻችንን እንዋጋቸዋለን፤ በጠላትነት የነሡብንንም በስምህ እናዋርዳቸዋለን፡፡)
#ወንጌል_
ማቴ.፲፯፥፲፬-፳፬፤ ወበጺሖሙ ኀበ አሕዛብ ቀርበ ኀቤሁ፡፡
#ቅዳሴ_
ዘእግዝእትነ (ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ፡፡ አው (ወይም) ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ (ላዕለ ይኵን ኅሊናክሙ በሰማይ የሀሉ ልብክሙ)፡፡
#አጋፋሪ_ይደግሳል_፡፡
#አጋፋሪ_ይደግሳል_፡፡
፩ኛ ትርጕም አጋፋሪ፤ አሁን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ደረጃ የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር አጋፋሪ ሲባል፤ ምክትሉ መጨኔ ይባላል፡፡
፪ኛ ትርጕሙ፤ አጋፋሪ፤ በቀድሞ ዘመን በሃገራችን በተለይም በቤተ መንግሥት ያለ ሹመት ሲሆን፤ (በጎንደር ፥ በሸዋ ፥ በትግሬ ፥ በወለጋ፥ በአሊባቡር፥ በሐረርጌ፥ በጅማ፥ በወሎ አጋፋሪ ተብሎ ሲጠራ በጎጃም መጨኔ ይባላል/
ሁለቱንም በቀድሞ ዘመንም ሆነ አሁን ባለው ሁኔታ ትርጕሙን እናያለን ፤
፠፠፩ኛ ፠፠ አሁን ካለው የቤ/ክን አገልግሎት አንጻር፤ አጋፋሪ ማለት የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር ሲሆን ምክትሉ መጨኔ ይባላል፡፡ ይህ አጋፋሪ በደብረ ታቦር በዓል ላይም በቅዱስ ሚካኤል ተመስሎ፤ ‹‹ሆያ ሆዬ›› ይባላል፡፡ ይኸውም
‹‹#ሆያ_ሆዬ_ሆ_››፤ ማለት ጌታው ሆዬ ፥ እሜቴ ሆዬ ለማለት ነው፡፡
‹‹#እዚያ_ማዶ_ጢስ_ይጤሳል_›› የተባለው፤ እስራኤላውያን በበረሃ ለ40 ዓመታት ሲጓዙ ደመና እየጋረዳቸው (እየጤሰ) ስለመራቸው ነው፡፡
‹‹#አጋፋሪ_ይደግሳል_››፤ የተባለው አጋፋሪው /አለቃው/ ቅዱስ ሚካኤል ሲሆን፤ ይደግሳል መባሉ እስራኤላውያንን ‹‹በዕደ መልአኩ ይዕቀበነ ፥ ሰላመ ዚአሁ የኀበነ›› እንዲል፤ በአምላክ ትዕዛዝ ቅዱስ ሚካኤል መናን ከደመናን ፥ ውኃን ከጭንጫ ዓለት እያፈለቀ (እየደገሰ) መርቷቸዋልና ነው፡፡
****እንዲሁም የአብነት (የቆሎ) ተማሪዎች በክረምት ሲለምኑ የቆዩትን አጠራቅመው፤ የደብረ ታቦር ዕለት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ ለኛም እንዲገልጥልን ብለው፤ ደግሰው ለሕዝቡ ያበላሉ ፥ ያጠጣሉ፡፡ /ይህ ሥርዐት በደብራችንም የሚከናወን ድርጊት ነው፡፡/
‹‹#ያችን_ድግስ_ውጬ_ውጬ_››፤ የተባለውና በድግስ የተመሰለው መና ሲሆን፤ በደጋሹ ቅዱስ ሚካኤል አማካይነት እስራኤል 40 ዓመታት መመገባቸውን (መና መዋጣቸውን) መናገር ነው፡፡
‹‹#ከድንክ_አልጋ_ተገልብጬ_›› ፤ ድንክ አልጋ የምትመች እንደሆነች ሁሉ ፥ በድንክ የምትመሰለውንና የምትመቻቸውን ተስፋዪቱ ምድር ኢየሩሳሌምን መውረሳቸው መናገር ነው፡፡
‹‹#ያቺ_ድንክ_አልጋ_አመለኛ_፥ #ያለአንድ_ሰው_አታስተኛ_››፤ መባሉ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ 600,000 ሆነው ሲሆን፤ ሁሉም በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሳት ሴትና ሕፃናት ሳይቈጠሩ፤ አንድ ኢያሱና አንድ ካሌብ ናቸው ለማለት ነው፡፡
፠፠፪ኛ ፠፠ አጋፈረ፤ግስ ሲሆን በቤተ መንግሥት ፥ በግብዣ ቦታ፥ …. በር ላይ ቆሞ የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው አስተናበረ አስተናገደ፡፡
*አጋፋሪ፤ ቅጽል ሲሆን፤ ቃሉ የቀድሞ አማርኛ ሲሆን አስተናባሪ (ብዙውን ጊዜ በግብዣ ወይም በቤተ መንግሥት በር ላይ በመቆም ሥርዐት የሚያስከብር ማለት ነው፡፡
*አጋፋሪ፤ የድግስ አለቃ ፥ አስተናጋጅ ነገሥታት ግብር ሲያገቡ (ግብዣ ሲጋብዙ ፥ ድግስ ሲደግሱ) ወደ አዳራሹ (ወደ ድግሱ) እንዲገቡ የሚፈቅድ ፥ የማይገባቸውንም የሚከለክል፤ ከገቡም በኋላ እንደ የክብራቸውና እንደየማዕርጋቸው አንተ በዚህ ሁን ፥ አንተ በዚህ ተቀመጥ እያለ የሚያስቀምጥ፤ ኋላ የድግሱ ምግብና መጠጥ መታደል ሲጀምርም፤ እንጀራና ጠጅ አሳላፊዎችን የሚያዝና የሚቈጣጠር ትልቅ ሹም ነው፡፡
* አጋፋሪ፤ የሚለው መጠሪያ በ17ኛወና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የታወቀ የቤተ መንግሥት ሹም መጠሪያ ነው፡፡ ‹‹ህዱግ ራስ›› በመባል የሚታወቅም ነው፤ በቤተመንግሥት የሚካሄዱ ሥራዎችንና የፍርድ ሂደቶች ያስተባብራል፤ አንዳንዴ ደግሞ የክፍላተ ሃገር የፍርድ ሰጪ ሰዎች ስም ሆኖም ያገለግላል፤ የስሜን (ከጎንደር በስተሰሜን የሚገኝ ግዛት ነው) አስተዳደር የሚገዛ ሰው ደግሞ የሰሜን አጋፋሪ እየተባለም ይጠራል፤ (ለምሳሌም አፄ ሱስንዮስ ልጃቸውን ፋሲለደስን የስሜን አጋፋሪ ብለው ሹመወት ነበር፤ ይህ የስሜን አጋፋሪ የሚለው ሹመትም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቶ ነበር፡፡
#ቡሄ_፤
ቡሄ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት የነሐሴ 13 ቀን መጠሪያ ስሙ ነው የሚሉ ሊቃውንት እንዳሉ ሁሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤
ቡሄ የሚባለው፤ ከነሐሴ 13 በኋላ እስከ መስከረም 17 መስቀል ድረስ ሲሆን፤ በተለይም ይህ በዓል የሚታወቀው በሸዋና ወሎ /እስከ ጋይንት ጫፍ መጋጠሚያ) ድረስ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ክርስትና አባት ለክርስትና ልጁ ተማሪ ከሆነ መጻሕፍትን (ዳዊት፣ …)፣ እንዲሁም አልባሳትን፣ በግና ሙክት ፍየልን የሚሰጥበት ነው፡፡ ሕፃናትና ወጣቱም ‹‹ቡሄ ፥ ሆ ….. ›› እያለ ይጨፍራል ፤ የሚሰጠውንም ሙክትና በግ እስከ መሰቅል ድረስ ሲያጠራቅም ከርሞ ለመስቀል ዕለት አርዶ ይበላል ፥ ደስታን ያደርጋል፡፡
ምንጭ፤ የቃል ትምህርት
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/
#ዜና_እረፍት_
‹‹ያገለገለህን ሰው ሞት ቸል አትበል፡፡›› ሲራክ 38፥26
#የሰ/ት/ቤታችን#አባል_ንጉሤ_አወቀ_ያገለግለው_የነበረው_መድኀኔ_ዓለም_ጠርቶት_ስላረፈ_፤ #የምሽት_መርሐ_ግብር_እሑድ_ነሐሴ_2_ከምሽቱ_12_ሰዐት_ላይ_ይካሄዳል_፡፡
#ቤቱ_2ኛው_መንገድ_ከሚሲዮን_ት/ቤት_ገባ_ብሎ_፡፡
፠ወንድማችን አወቀ ንጉሤ፤ ከ2001-2003 ዓ.ም. በሰ/ት/ቤታችን ይሰጥ የነበረውን የሦስት ዓመታት ተከታታይ ትምህርት የተማረ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ደግሞ በሰ/ት/ቤታችን ታሪክ ወደ ራብዓይ ክፍል በ2004ዓ.ም. ከተሸጋገሩ 19ኝ የተከታታይ ትምህርት (Course) ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
፠ወንድማችን በኪዳን ተአምራት ምንባብ ጊዜ ተዓምራትን በማሳለም፤ በቅዳሴ ጊዜ የቅዳሴ ጠበል ለምዕመናን በማድረስ የሚያገለግለን ወንድማችን ነው፡፡
፠በጾመ ፍልሰታ ወቅት ዘወትር የሚያገለግለውን ግልጋሎት እስከ ነሐሴ 5 ሲሰጥ ቆይቶ፤ ሰኞ ነሐሴ 6 ወደ ጅሩ ቅድስት አርሴማ ገዳም ሄዶ ሥጋ ወደሙን ተቀበለ (ቈረበ)፤ በዚያው ገዳም 3ት ቀናትን ከቆየ በኋላ ኀሙስ ነሐሴ 9 ከሰዐት ላይ አረፈ፤ እዚያ ገዳም ያረፈ ሰው እዚያው ግብዐተ መሬት የሚከናወንለት ቢሆንም ገዳማውያን አባቶችን በማስፈቀድ ወደ አዲስ አበባ ሌሊቱን አስከሬኑ ተመልሷል፤ በነጋታውም ዐርብ ነሐሴ 10/2011 ዓ.ም. ከ9-10 ሰዐት፤ ከልጅነቱ ጀምሮ ዕለት ዕለት በተማረበትና በተለያዩ ግልጋሎት ባገለገለበት በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ ሥርዐተ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል፡፡
‹‹ወእመኒ ሐየውነ ለእግዚአብሔር ነሀዩ፤ ወእመኒ ሞትነ ለእግዚአብሔር ንመውት፡፡
/በሕይወት ብንኖር ለእግዚአብሔር እንኖራለን፤ ብንሞትም ለእግዚአብሔር እንሞታለን›› ሮሜ. 14፥17
(የቀ/ደ/ሰ/መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍ/ሕ/ሰ/ት/ቤት::)
፩ ቀን ቀረው
በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን መጻሕፍትን የምናሰባስብበት
ልዩ መርሐ ግብር ነሐሴ 11፤ ከ11፡30 - 2፡00
፩ ቀን ቀረው
ቅዱስ ያሬድ ለቤተ ክርስቲያናችን ድንቅና ዕንቊ የሆኑ ፭ት መጻሕፍትን ደርሶ አብርክቶልናል እኛስ ለቤተ መጻሕፍቶቻችን ምን ያህል መጻሕፍት አስተዋጽዖ አድርገናል፡፡
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡
ምስባኩ ከድምፅ ጋር ዘነሐሴ ፲
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_#ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ዘነሐሴ_፲_ማኀበረ_በኵር_ወመጥራ_ሰማዕት_ወሐርስጥፎሮስ_ወቢካቦስ_ወዮሐንስ_፡፡
#የቅዳሴ_ምንባባት
† ዕብ.፲፪፥፳፪-ፍጻ ወአንትሙሰ በጻሐክሙ ኀበ ጽዮን፡፡
† ፩ኛ ጴጥ.፩፥፮-፲፫ ወባሕቱ ኀዳጠ ይእዜ ሀለውክሙ::
† የሐዋ.፬÷፴፩-ፍ ወእንዘ ይጼልዩ አድለቅለቀ ውእቱ መካን፡፡
#ምስባክ_መዝ. ፸፫፥፪
ተዘከር ማኀበረከ ዘአቅድምከ ፈጢረ፡፡
ወአድኀንከ በትረ ርስትከ፡፡
ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ፡፡
(ትርጕም፤ አስቀድመህ የፈጠርከውን ምኅበርህን አስብ፡፡ የርስትህንም በትር አዳንክ፡፡ በውስጧ ያደርክ የጽዮን ተራራን፡፡)
#ወንጌል_
ሉቃ. ፲፯፥፲፮-፱፤ ወአነሂ እብለክሙ ግበሩ ለክሙ አዕርክተ፡፡
#ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ ፤ ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ፡፡
#3ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት!!!
፠#በ1966ዓ.ም.#አገልግሎቱን_ለጀመረው_አንጋፋ_ቤተ_መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡
፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡
፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00
ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ
#ክርስቲያን_እንኾን_ዘንድ_እመቤታችንን_እናንብባት_እንማርባትም_ክፍል_፪::
፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_እጅግ_ትሑት_ነች_፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስን ስታነብና “ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች” በሚለው አንቀጽ ስትደርስ “ምነው እኔ በኾንኩኝ?” አላለችም፤ “ምነው በዘመኗ ደርሼ ይኽቺን ድንግል ባገለገልኳት?” አለች እንጂ፡፡ መልዐኩ “ተፈስሒ” ሲላት “ይገባኛል” አላለችም፤ “ነየ አመተ እግዚአብሔር - የእግዚአብሔር ገረዱ እነሆኝ” አለች እንጂ /ሉቃ.፩፡፴፰/፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ “የጌታዬ እናቱ እመቤቴ ወደኔ ትመጭ ዘንድ እኔ ምንድነኝ?” ስትላት “ልክ ነሽ፤ ይደልወኒ - ይገባኛል፤ አምላክን ፀንሻለኹና” አላለችም፤ “የባርያይቱን ውርደት ተመልክቷልና” አለች እንጂ፡፡ ብትል እኮ ያምርባታል፡፡ ነገር ግን አላለችም፡፡ ምንም ሳንሠራ “ይገባኛል” የምንል የማን ልጆች እንኾን?
እመቤታችን ኤልሳቤጥ እንዳረገዘች ሰምታ ትጠይቃት ዘንድ መሔዷ የትሕትናዋን ጥልቀት ያሳያል፡፡ ለልማዱ ባርያ ወደ ጌታው ይሔዳል፡፡ አኹን የኾነው ግን እንዲኽ አይደለም፡፡ የመጣችው ኤልሳቤጥ አይደለችምና፤ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ሔደች እንጂ፤ ያውም በዚያ ተራራማው ስፍራ፡፡ የእመቤታችን ትሕትናዋ ግሩም ነው፡፡
ትሕትና ሰዎችን አማልክት ዘበጸጋ ታደርጋለች፤ ትዕቢት ደግሞ ቅዱሳን መላዕክትን ታዋርዳለች፡፡ ትዕቢት እጅግ ክፉ ነው፡፡ ትዕቢት ሰዎች ከተለመደው ባሕርያቸው አስወጥቶ ያደነዝዛቸዋል፤ የስንፍናን ካባ ያጐናጽፋቸዋል፡፡ ትዕቢት እንደ ዕብድ ያናግራል፡፡ አንድ ሰው ቁመቱ ሦስት ክንድ ከስንዝር ቢኾን እንኳን ትዕቢቱ ተራራን ያሳክሏል፤ ተራራን ባያክልም እንደዚያ እንደኾነ እንዲያስብ ያደርጓል፡፡ ትዕቢት ከዕብደት የከፋ በሽታ ነው፡፡ ምክንያቱም ትዕቢት በእኛ ፈቃድ የሚይዘን በሽታ ሲኾን ዕብደት ግን ሳናውቀው ሊይዘን የሚችል የጤና እክል ነውና፡፡ ወዮ! መቼ ይኾን ከዚኽ በሽታ የምንላቀቀው?
፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_እጅግ_የምታምንና_ታዛዥ_ነበረች_፡፡ ሕይወቷ ኹሉ “ይኵነኒ በከመ ትቤለኒ - እንደ ቃልኽ ይደረግልኝ” በሚል የተመላ ነው፡፡ ወላጆቿ ለቤተ እግዚአብሔር ቢያስረክቧት “ይኵነኒ”፤ ካህናት “ቤተ መቅደሳችንን ታረክስብናለች” ብለው ቢያስወጧት “ይኵነኒ”፤ “በድንግልና ፀንሰሽ በድንግልና ትወልጃለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ “ከሦስቱ ቅዱስ አንዱን ቅዱስ በበረት ትወልጂዋለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ “የስዱዳን ተስፋቸውን አዝለሽ ትሰደጃለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ ሽፍቶች ቢያስደነግጧት “ይኵነኒ”፤ ማየ ሕይወትን አዝላ ውኃ ቢጠማት አንድም ልጇ ቢጠማው “ይኵነኒ”፤ አባቶቿ ፵ ዓመት የፈጀባቸውን መንገድ በልጅነት ዕድሜዋ “ልጅ አዝለሽ ትሔጃለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ “ሄሮድስ ሞቷልና ተመለሺ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ አንዱን ልጇ ሲያሰቃዩባት ሲገርፉባትና ሲገድሉባት “ይኵነኒ”፡፡ ታዛዥነቷ ከአዕምሮ የሚያልፍ ነው፡፡ ሄሬኖዎስ የተባለው ቅዱስ አባት የእመቤታችንን ታዛዥነት ለምን እንደኾነ ሲያስተምር እንዲኽ አለ፡- “እነሆ ጌታ የራሱ ወደኾኑት በግልጥ (በለቢሰ ሥጋ) መጣ፡፡ ትዕዛዙን ተላልፎ በዕጽ የሞተውን አዳም በዕጽ ላይ ታዝዞና ካሣውን ከፍሎ፣ ወደ ጥንተ ተፈጥሮው ይመልሰው ዘንድ በራሱ ጥበብ ከፍጥረቱ ተወለደ፡፡ ለአንድ ወንድ የታጨችው ድንግል በምክረ ከይሲ ያመጣችውን ያለመታዘዝ ኃይል የእውነት መልዐክ ለአንድ ወንድ ለታጨችው ድንግል ባበሠራት ጊዜ ፈራረሰ፡፡ ቀዳማይቱ ሔዋን ከእግዚአብሔር እንድትርቅና ቃሉን እንድትቃወም ክፉ መልዐክ አታለላት፡፡ ዳግማይቱ ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ደጉ መልዐክ ይዞት የመጣው መልካሙን ዜና እንድትቀበለውና እግዚአብሔርን በከዊነ ቃሉ እንድትወልደው አመነች፡፡ ቀዳማይቱ ሔዋን እግዚአብሔርን እንዳትታዘዘው ክፉ መልዐክ አታለላት፤ ወደቀችም፡፡ ዳግማይቱ ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን እግዚአብሔርን እንድትታዘዝ ቅዱስ መልዐክ አሳመናት፤ ርሷም ሔዋንን ረዳቻት፡፡ ነገደ አዳም በአንዲት ድንግል አለመታዘዝ ምክንያት ሞት ተፈረደበት፣ ኾኖም በሌላይቱ ድንግል መታዘዝ ምክንያት ዳነ፡፡” በሕይወታችን “ይኵነኒ” ማለትን መልመድ ጸጋ እግዚአብሔርን በሕይወታችን ማትረፍረፍ ነው፡፡ እንላለን ወይ ነው ቁምነገሩ? እግዚአብሔርን የሚጋርዱብን ነገሮች (ለምሳሌ ሥራ፣ ውበት፣ ሥልጣን፣ ሀብት፣…) ከሕይወታችን ይወገዱ ብንባል “ይኵነኒ” ለማለት ምን ያኽል ዝግጁዎች ነን?
፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ርኅሪኅተ_ኅሊና_ናት_፡፡ እጅግ አዛኝ እናት!!! ሊቃውንት እንደሚያስተምሩት ምኅረት (ምጽዋት) ሦስት ዓይነት ነው፡፡ ምኅረት ሥጋዊ፣ ምኅረት መንፈሳዊና ምኅረት ነፍሳዊ፡፡ ምኅረት ሥጋዊ የታረዘን ማልበስ፣ የተራበን ምጉረስ ነው፡፡ ምኅረት መንፈሳዊ የተጨነቀን ወይም ያዘነን ሰው መርዳት፣ ወይም ማጽናናት ነው፡፡ ምኅረት ነፍሳዊ ደግሞ ሰዎች የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኙ መርዳት ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሰውስ ይቅርና ለተጠማ ውሻም ሳይቀር በወርቅ ጫማዋ ውኃን ያጠጣች ርኅርኅተ ኅሊና ናት፤ ምኅረት ሥጋዊ፡፡ እናቶቻችንን በምጥ ጊዜ እንዴት እንደምትረዳቸው መናገርም ለቀባሪ ማርዳት ነው፤ ምኅረት መንፈሳዊ፡፡ ክርስቲያን፥ በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ኾኖ ከእመቤታችንን ርኅራኄ (ምልጃና ቃል ኪዳን) ያልቀመሰ የለም፤ ምኅረት ነፍሳዊ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በቅዳሜ ውዳሴው ላይ “የዚኽ ዓለም ሰዎች አማልዱኝ ቢሏቸው ነገር አጽንተው ይመለሳሉ፡፡ ርሷ ግን ማእምንት ሰአሊተ ምኅረት - የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት” ያለውም ስለዚኹ ነው፡፡ እኛስ ምን ያኽል ርኅሩኀን እንኾን? ኧረ በወርቅ ጫማ ቀርቶብን በንጹሕ ሳህን ለመመጽወት ልቡናችን በራራ? ኧረ ለውሻው ቀርቶብን ለሰዉም ባዘንን?
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሕይወት ገና ስንዠምር እንደተናገርነው በሕይወት ዘመን አንብበው የማይጨርሱት እጅግ ትልቅ መጽሐፍ ነውና አንድ ኹለት ብለን መቁጠር አይቻለንም፡፡ ማንበብ ከቻልን ሕይወቷ ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን አስተማሪ ነው፡፡ “ማርያም ፊደል ናት ….” ብለን መዘመራችንም ስለዚኹ ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ! እንኪያስ የምንዘምር ብቻ አንኹን፤ እናንብባትም ጭምር እንጂ፡፡ የምናነብ ብቻ አንኹን፤ እንለወጥም ጭምር እንጂ፡፡ ማንበቡንማ ዲያብሎስም ያነባል፡፡ እንኪያስ አንብበን እንለወጥና በእውነት የድንግል ልጆች እንኹን፡፡
ይኽን እንድናደርግ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን ወአሜን፡፡
/ምንጭ፤ ምክረ አበው ቁጥር 5/
/ከጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ የተወሰደ/
#4ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት!!!
፠#በ1966ዓ.ም.#አገልግሎቱን_ለጀመረው_አንጋፋ_ቤተ_መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡
፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡
፠ ከነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 11 የመጻሕፍት ሽያጭና የመጻሕፍት ማሰባሰብ ይካሄዳል፡፡
፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00 ሰዐት በቅዱስ ገብርኤል አዳራሽ ከዝክረ ቅዱስ ያሬድ ጋር ግብሩ አብሮ የመጻሕፍት መምህራንና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይካሄዳል፡፡
‹‹ስትመጣ …. ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ፡፡››
**ቤተ መጻሕፍታችንን ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ማኅበረ ምዕናንንና ማኅበረ ካህናትን ታሳቢ አድርጎ የተደራጀ መሆኑ ነው፡፡
ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ
የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት::
