Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 950 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 312,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 242 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 950 名订阅者。
根据 23 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 397,过去 24 小时变化为 -13,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.83%。内容发布后 24 小时内通常能获得 11.01% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 117 次浏览,首日通常累积 1 755 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 29。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 24 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 950
订阅者
-1324 小时
+1467 天
+39730 天
帖子存档
፨የ ፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔት ፨
#ነሐሴ ሰባት ጽንሰታ #ለማርያም_ድንግል
#ጴጥርቃ እና #ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ:: ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ፡፡
፨፨፨
አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን ፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ #ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ #ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ #7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ #ጨረቃዋም #ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
፨፨፨
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧችኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ #ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ #የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:፡
፨፨፨
ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ፤ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት፤ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፤ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት ፤ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደችውን ሃናን ወለደች:: ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም፡፡ ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች፡፡ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቧት::
፨፨፨
እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡-
ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡
ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።
፨፨፨
ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ ፤ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው፤ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው፡፡
፨፨፨
ሃናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱ ንጽህናዋ : ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው::
፨፨፨
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሏችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡:
፨፨፨
እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት ፤ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት ፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፤አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማኋቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው ፤ በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ::
፨፨፨
እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን አሜን ፡፡
‹‹#ያገለገለህነሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ 38÷26
( እያዘንን ጻፍንላቹ )
ደብራችንን ለ54 ዓመታት ያገለግሉትነ መሪጌታ ይሁኔ ፈቃዱ አጭር የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
#መሪጌታ ይሁኔ ፈቃዱ (አጋፋሪ)
#ትውልድ ፣ዕድገት እና ት/ት
አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ከአባታቸው መሪጌታ ፍቃዱ ተሰማ እና ከእናታቸው ከ ወ/ሮ ለምለም ወርቁ በ 1933 ዓ.ም በጎንደር ክፍለ ሃገር በ ደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ደብረ ሲና ማርያም በሚባል ቦታ ተወለዱ መሪጌታ ይሁኔ ፍቃዱ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ ከ አስኳላው ትምህርታቸው ጎን ለጎን ከ አባታቸው ከ መሪጌታ ፍቃዱ ከ ቁጥር እስከ ዳዊት ተምረዋል በዲቁና ሃገራቸው ያገለግሉ ነበር:: ከዛም በመቀጠል በደብረ ሲና ማርያም ፀዋአቶ ዜማ ተምረው ካጠናቀቁ በኃላ ወደ ምዕራብ ጎጃም አዊ ዞን ጋጋስታ ጊዮርጊስ በመሄደ ከ መምህር ቢንያም ቅኔን ከነ አገባቡ እና ከነጓዙ ተምረዋል ፡፡
አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ በ1954ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከመንፈሳዊው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአስኳላው ትምህርት በመዝለቅ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ በሂሳብ ትምህርት (አካውንቲንግ) ዲፕሎማቸውን ይዘዋል ፡፡
ትምህርት እና #አገልግሎት
አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ወደ አዲስ አበባ ከመጡበት ከ1954 ዓ.ም ጀምሮ ማረፊያቸውን በ ታላቁ ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በማድረግ አቋቋም ከመምህር ገብረ ማርያም ጠንቅቀው በመማር ከዛም ደብራችን እስከ ህልፈተ ሕይወታቸው ቀን ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ካላቸው የቃለ እግዚአብሔር ፍቅር በቀና አገልግሎት ለ54 ዓመታት በጽናት ሲያገለግሉ ኖረዋል ፡፡
አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ከመንፈሳዊው አገልግሎታቸው በተጨማሪ በተማሩበት የቀለም ት/ት በመንግስት ልዩ ካቢኔ እንዲሁም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሚኒሊክ ሆስፒታል በዋና ገንዘብ ያዥነት ለበርካታ አመታት በቅንነት እና በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተው እድሜያቸው ለጡረታ ሲደርስ በክብር ተሸኝተዋል ፡፡
አጋፋሪ ይሁኔ ልዩ በሆነው ድምጻቸው እና የቀጨኔ ደብረሳለም የአቋቋም ይት ባህልን ጠንቅቆ በማወቅ እናም ከሰንበት ት/ቤታችን ጋር በመሆን በድምጽ ተቀርጾ እንዲቀር በማድርቅ፤ በልዩ የዜማ እና የድምጽ ፀጋቸው፤
እናወቃቸዋለን ፤ እናስታውሳቸዋልነ ፡፡
#ሕይወት
አጋፋሪ ይሁኔ ከትዳር አጋራቸው 2 ወንድ እና 1 ሴት ልጅ አፍርተው 1 የልጅ ልጅ አይተዋል አጋፋሪ ይሁኔ ቅን ታማኝ እና ልዩ የቃለ እግዚአብሔር ፍቅር ያደረባቸው ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር እና በስምምነት የሚኖሩ ትልቅ ትንሽ ሳይሉ ሁሉን በፍቅር የሚያዩ የትህትና አባት ነበሩ ::
#ኅልፈት
ለጥቂት ቀናት ብቻ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ቃለ እግዚአብሔርን ከ አፋቸው ሳይነጥሉ በ80 ዓመታቸው አርፈዋል
ሥርዓተ ግብዐተ መሬታቸው ለ 54 ዓመታት ባገለገሉበት እና ብዙ ደቀ መዛሙርትን ባፈሩበት በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም እና ደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በወርኃ ሰኔ ቀን 24 2012 ዓ.ም ተፈጸመ፡፡
ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እንዲሁም ለዘመናት በአንድ መቅደስ ውስጥ አብረው ሲያገለግሉ ለኖሩት ሊቃውንት እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድልንን፡፡
በረከታቸው ይደርብን
አጭር ሺድዮ ይመልከቱ
https://youtu.be/8ZwyVQwEzUg
‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት
#ሐምሌ 7/2012 ዓ.ም በሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነምሕረት ገዳም #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው የሰ/ት/ቤታች አባል ወንድማችን #እንዳልካቸው_አወቀ ከእህታችን #መስታዎት_ይርጋለም ጋር የፈጸምከው ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሣራን፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ #ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኀላ ይከተላቹ፡፡
<<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ-ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>> ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበስ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡
<ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስተ አንድ አካል ናችሁ፡፡ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፈቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፈ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡
