ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 950 подписчиков, занимая 5 312 место в категории Религия и духовность и 2 242 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 950 подписчиков.

Согласно последним данным от 23 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 397, а за последние 24 часа — -13, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 25.83%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 11.01% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 117 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 755 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 29.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 24 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 950
Подписчики
-1324 часа
+1467 дней
+39730 дней
Архив постов
#ነሐሴ ሰባት ጽንሰታ #ለማርያም_ድንግል #ጴጥርቃ እና #ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ:: ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ፡፡ ፨፨፨ አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን ፤ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት፡፡ እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ #ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ #ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ #7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ #ጨረቃዋም #ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው:: ፨፨፨ እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምህረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧችኋል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ #ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ #የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:፡ ፨፨፨ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ፤ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት፤ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፤ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት ፤ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደችውን ሃናን ወለደች:: ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም፡፡ ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች፡፡ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቧት:: ፨፨፨ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡- ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ፨፨፨ ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ ፤ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው፤ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው፡፡ ፨፨፨ ሃናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱ ንጽህናዋ : ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: ፨፨፨ እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሏችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡: ፨፨፨ እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ፡፡ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት ፤ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት ፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፤አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማኋቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው ፤ በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ:: ፨፨፨ እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች:: ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን አሜን ፡፡

‹‹#ያገለገለህነሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ 38÷26 ( እያዘንን ጻፍንላቹ ) ደብራችንን ለ54 ዓመታት ያገለግሉትነ መሪጌታ ይሁኔ ፈቃዱ አጭር የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ #መሪጌታ ይሁኔ ፈቃዱ (አጋፋሪ) #ትውልድ ፣ዕድገት እና ት/ት አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ከአባታቸው መሪጌታ ፍቃዱ ተሰማ እና ከእናታቸው ከ ወ/ሮ ለምለም ወርቁ በ 1933 ዓ.ም በጎንደር ክፍለ ሃገር በ ደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ደብረ ሲና ማርያም በሚባል ቦታ ተወለዱ መሪጌታ ይሁኔ ፍቃዱ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ ከ አስኳላው ትምህርታቸው ጎን ለጎን ከ አባታቸው ከ መሪጌታ ፍቃዱ ከ ቁጥር እስከ ዳዊት ተምረዋል በዲቁና ሃገራቸው ያገለግሉ ነበር:: ከዛም በመቀጠል በደብረ ሲና ማርያም ፀዋአቶ ዜማ ተምረው ካጠናቀቁ በኃላ ወደ ምዕራብ ጎጃም አዊ ዞን ጋጋስታ ጊዮርጊስ በመሄደ ከ መምህር ቢንያም ቅኔን ከነ አገባቡ እና ከነጓዙ ተምረዋል ፡፡ አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ በ1954ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከመንፈሳዊው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአስኳላው ትምህርት በመዝለቅ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ በሂሳብ ትምህርት (አካውንቲንግ) ዲፕሎማቸውን ይዘዋል ፡፡ ትምህርት እና #አገልግሎት አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ወደ አዲስ አበባ ከመጡበት ከ1954 ዓ.ም ጀምሮ ማረፊያቸውን በ ታላቁ ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በማድረግ አቋቋም ከመምህር ገብረ ማርያም ጠንቅቀው በመማር ከዛም ደብራችን እስከ ህልፈተ ሕይወታቸው ቀን ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ካላቸው የቃለ እግዚአብሔር ፍቅር በቀና አገልግሎት ለ54 ዓመታት በጽናት ሲያገለግሉ ኖረዋል ፡፡ አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ከመንፈሳዊው አገልግሎታቸው በተጨማሪ በተማሩበት የቀለም ት/ት በመንግስት ልዩ ካቢኔ እንዲሁም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሚኒሊክ ሆስፒታል በዋና ገንዘብ ያዥነት ለበርካታ አመታት በቅንነት እና በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተው እድሜያቸው ለጡረታ ሲደርስ በክብር ተሸኝተዋል ፡፡ አጋፋሪ ይሁኔ ልዩ በሆነው ድምጻቸው እና የቀጨኔ ደብረሳለም የአቋቋም ይት ባህልን ጠንቅቆ በማወቅ እናም ከሰንበት ት/ቤታችን ጋር በመሆን በድምጽ ተቀርጾ እንዲቀር በማድርቅ፤ በልዩ የዜማ እና የድምጽ ፀጋቸው፤ እናወቃቸዋለን ፤ እናስታውሳቸዋልነ ፡፡ #ሕይወት አጋፋሪ ይሁኔ ከትዳር አጋራቸው 2 ወንድ እና 1 ሴት ልጅ አፍርተው 1 የልጅ ልጅ አይተዋል አጋፋሪ ይሁኔ ቅን ታማኝ እና ልዩ የቃለ እግዚአብሔር ፍቅር ያደረባቸው ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር እና በስምምነት የሚኖሩ ትልቅ ትንሽ ሳይሉ ሁሉን በፍቅር የሚያዩ የትህትና አባት ነበሩ :: #ኅልፈት ለጥቂት ቀናት ብቻ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ቃለ እግዚአብሔርን ከ አፋቸው ሳይነጥሉ በ80 ዓመታቸው አርፈዋል ሥርዓተ ግብዐተ መሬታቸው ለ 54 ዓመታት ባገለገሉበት እና ብዙ ደቀ መዛሙርትን ባፈሩበት በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም እና ደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በወርኃ ሰኔ ቀን 24 2012 ዓ.ም ተፈጸመ፡፡ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እንዲሁም ለዘመናት በአንድ መቅደስ ውስጥ አብረው ሲያገለግሉ ለኖሩት ሊቃውንት እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድልንን፡፡ በረከታቸው ይደርብን አጭር ሺድዮ ይመልከቱ https://youtu.be/8ZwyVQwEzUg

‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት #ሐምሌ 7/2012 ዓ.ም በሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነምሕረት ገዳም #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው የሰ/ት/ቤታች አባል ወንድማችን #እንዳልካቸው_አወቀ ከእህታችን #መስታዎት_ይርጋለም ጋር የፈጸምከው ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሣራን፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ #ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኀላ ይከተላቹ፡፡ <<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ-ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>> ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበስ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡ <ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስተ አንድ አካል ናችሁ፡፡ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፈቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፈ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡