ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 033 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 277,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 233 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 033 名订阅者。

根据 24 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 493,过去 24 小时变化为 95,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 24.10%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.99% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 864 次浏览,首日通常累积 1 601 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 26。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 25 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

16 033
订阅者
+9524 小时
+1537 天
+49330 天
帖子存档
‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሐምሌ 5/2012 ዓ.ም በቀ/ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ቤ/ክ #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው የሰ/ት/ቤታች አባል እና #ሰብሳቢ_ዲያቆን_ታምራት_ሙሉነህ እና፤ የሰ/ት/ቤታችን አባል የሆንሽው #ሮማን_ለማ፤ የፈጸማቹሁት ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሣራን፣ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላችሁ፡፡ <<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>> ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡ <ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ፡፡ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፈቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡

#ሐምሌ_ቂርቆስ #ወሥርዓተ_ማኅሌት ሐምሌ 19 ቀን የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከሚነደው እቶን እሳት ያዳነበት ዕለት ነው፡፡ ሦስት ዓመት እንኳን ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በሕዳር 15 ቀን ተወለደ፤ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ከልጆችና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ›› ሲል እንደተናገረ ፡፡ቅዱስ ቂርቆስም በከሃዲው ንጉሥ ፊት የጌታችንን ክብር በመሰከረ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን በውስጡ ጨምሮ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ ንጉሡ እስክንድሮስ ጭፍሮቹን "ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምሩበት" ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ከፈጸሙ በኀላ መጥተው "ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል" አሉት፡፡ "ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ይወጣል፡፡ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ" አሉት፡፡ ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በክርስቶስ ስም ስላመኑ በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡ "ነገር ግን እናቴ ሆይ አናንያንና አዘርያን፣ ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከዕቶን እሳት እንዳወጣቸው እወቂ፤ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናቴ ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች? እናቴ ሆይ ይህን አትርሺ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ የእግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይመስገን አለ፡፡ እኛም ይህንን መከራ ልንታገስና የተጠበቀልንን ልንከተል ይገባናል..." እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገር ግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋቸት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፡- በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ስጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንነሣ" አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው። ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አፍና አፍንጫ መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳውም እንዳውም ምግብ ሆነው፡፡ ዳግመኛም ጨውና በርበሬ በዐይኑ አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካውም፡፡ ከዚህም በኀላ ሹም እስክድሮስም አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች ያመጡ ዘንድ ዳግመኛ አዘዘ፡፡ ሰባቱን በእናቱ አካል ሰባቱን በሱ አካል ውስጥ ይተክሉ ዘንድ ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዓይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይተክሉ ዘንድ አዘዘ፡፡ በሕፃኑም ላይ ሹሙ እንዳዘዘው አደረጉበት፡፡ አሁንም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና ፈወሳቸው፡፡ ዳግመኛም የሕጻኑን እራስ ከነቆዳው ገፈው በእሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አንድ ሹም አዘዘ፡፡ እንዲሁም አደረጉበት፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ይህንን መከራ ከሕፃኑ አራቀለት፡፡ ዳግመኛም ሹሙ በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ከዚህም መከራ መልአኩ አዳነው፡፡ በዛሬዋ ዕለት ሐምሌ 19 ቀን በዓሉን በታላቅ ድምቀት የምናከብረው ይህንን ሁሉ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት በማሰብ ነው፡፡ የፊታችን እሁድ የሊቀ መልአኩ እና የሁለቱ ቁዱሳን ታቦታት ባሉባቸው አቢያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን ሙሉ የማኅሌቱ ሥርዓት አቅርበንላችኋል፡፡ መልካም የምስጋና ሌሊት ይሁንላችሁ!!! የቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ምልጃ ጸሎት ከእኛ ጋር ትሁን፡፡ የሊቀ መልአኩ ጠብቆት አይለየን፡፡

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸችው #ዛሬ_ሰኔ_20 በ51ዓ.ም ነበር፡፡ አናጺውም ደግሞ እራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቦታው #ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ
የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸችው #ዛሬ_ሰኔ_20 በ51ዓ.ም ነበር፡፡ አናጺውም ደግሞ እራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቦታው #ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ #በእመቤታችን ስም ነበር። ✥ ✥ ✥ “…እግራችሁ ሁል ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም እንደማይናወጥ የብረት ችንካር በቤተ እግዚአብሔር የተተከለ ይሁን…” (ቅዳሴ አትናቴዎስ) ✥ ✥ ✥ #ፎቶ_ፍኖተ_ሕይወት

“ከሰው ልጆች እንደእኔ ጠዋትም ማታም የሚተክዝ የለም፤ ከመላእክትም እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያጽናና መልአክ የለም። አንተን አውቄ ፈልጌሃለሁና #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ አረጋጋኝ፤ ድምጽህንም አሰማኝ፤
“ከሰው ልጆች እንደእኔ ጠዋትም ማታም የሚተክዝ የለም፤ ከመላእክትም እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያጽናና መልአክ የለም። አንተን አውቄ ፈልጌሃለሁና #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ አረጋጋኝ፤ ድምጽህንም አሰማኝ፤ የማቀርብልህ የጸሎቴ ፍሬ ይህ ነውና።” (#መልክአ_ገብርኤል) ✥✥✥ #ፎቶ_ፍኖተ_ሕይወት