ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 042 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 280,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 240 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 042 名订阅者。

根据 29 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 518,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.50%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.35% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 090 次浏览,首日通常累积 1 660 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 33。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 30 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

16 042
订阅者
+124 小时
+917 天
+51830 天
帖子存档
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ዘነሐሴ_፰_ ፠#አልዓዛር_ወሰሎሜ_ብእሲቱ_ወውሉዱ#፯ቱ_ወአሞን_፡፡ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፱፥፳፬-ፍጻ ፤ ወንሕነ እሙንቱ እለ ጸውዐነ ውስተ ክብሩ፡፡
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ዘነሐሴ_፰_ ፠#አልዓዛር_ወሰሎሜ_ብእሲቱ_ወውሉዱ#፯ቱ_ወአሞን_፡፡ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፱፥፳፬-ፍጻ ፤ ወንሕነ እሙንቱ እለ ጸውዐነ ውስተ ክብሩ፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፬፥፲፪-ፍ ፤ አኃዊነ ኢታንክርዋ ልእንተ ትመጽአክሙ:: † የሐዋ.፲፮÷፴፭-ፍ ፤ ወጸቢሖ ለዐኩ መኳንንት፡፡ #ምስባክ_መዝ. ፶፯፥፰ ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ፡፡ ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ፡፡ ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኀጠክሙ፡፡ (ትርጕም፤እሳት ወደቀች ፀሐይንም አላየኋትም፤ እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል፡፡) ማቴ.፯፥፲፪-፳፮ ፤ ኵሎኬ ዘትፈቅዱ ይገበሩ ለክሙ ሰብእ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ ፤ ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ፡፡

#5ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ
+1
#5ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡ ፠ ከነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 11 የመጻሕፍት ሽያጭና የመጻሕፍት ማሰባሰብ ይካሄዳል፡፡ ፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00 ሰዐት በቅዱስ ገብርኤል አዳራሽ ከዝክረ ቅዱስ ያሬድ ጋር ግብሩ አብሮ ታላላቅ የመጻሕፍት መምህራንና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይካሄዳል፡፡ ‹‹ስትመጣ …. ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ፡፡›› **ቤተ መጻሕፍታችንን ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ማኅበረ ምዕናንንና ማኅበረ ካህናትን ታሳቢ አድርጎ የተደራጀ መሆኑ ነው፡፡

/ከጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ የተወሰደ/

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፯#ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ #ነሐሴ_፯_ፅንሰታ_ለማርያም_ወተስእሎተ_ቂሣርያ_ወጢሞቴዎስ_ሊቀ_ጳጳሳት_ወልደቱ_ለዮሴፍ_ወልደ_ራሄል_ወናዖድ_ንጉሠ_ኢትዮጵያ_ #የቅዳሴ_ንባብ ፠† ዕብራ. ፱፥፩- ፲፯፤ ወለቀዳሚትኒ ደብተራ፡፡ ፠ † ፩ኛጴጥ.፪፥፮-፲፰፤ እስመ ከመዝ ጽሑፍ ናሁ እሠይም፡፡ ፠ † የሐዋ.ሥ.፲፥፩-፴፤ ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ፡፡ #ምስባክ_መዝ. ፺፫፥፲፪ ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ፡፡ ወዘመሀርኮ ሕገከ፡፡ ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት፡፡ (ትርጕም፤ አቤቱ አንተ የገሠጽከው ሰው ብፁዕ ነው፤ ሕግህንም ያስተማርሀው፤ ከክፉዎች ዘመናት ይርቅ ዘንድ፡፡) #ወንጌል_ማቴ.፲፮፥፲፫-፳፬፤ ወበጺሖ ኢየሱስ ብሔረ ቂሣርያ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ_ጐሣዕ_ልብየ_ቃለ_ሠናየ #ነሐሴ_ሰባት_ጽንሰታ_ለማርያም_ድንግል፤ #ክፍል_፩_ የዓለም ኹሉ ደስታን ወዳመጣችው ዕለት አደረሳችኁ፤ አደረሰን፡፡ ነሐሴ ሰባት ቀን የባሕርያችን መመኪያ የምትኾን ንጽሕተ ንጹሐን፥ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአባቱ ከኢያቄምና ከእናቷ ሐና የተፀነሰችበት ዕለት ነው፡፡ ይኽቺን ዕለት ያልናፈቀ ትውልድ የለም፡፡ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ለኾነባቸው ቅዱሳን አበው ወእማት ተስፋቸው የሚፈጸመው በዛሬው ዕለት በተጸነሰችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነውና፡፡ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ከፈጣሪያችን እግዚአብሔር ቀጥሎ ከፍጥረታት እንደ እመቤታችን ከፍ ከፍ የምታደርገው ፍጥረት የሌለው ስለዚኹ ነው፡፡ መትሕተ ፈጣሪ፥ መልዕልተ ፍጡራን፤ (ከፈጣሪ በታች ፥ ከፍጡራን በላይ) ናትና፡፡ ሊቃውንቱ፤ “ሐና አንቺን የጸነሰችበት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤” ብለው የሚዘምሩላትም ይኽን ምሥጢር በልቡናቸው ቋጥረው ነው /አባ ጽጌ ድንግል፤ ማኅሌተ ጽጌ ቁ.፵፬/፡፡ ስለ እመቤታችን ከመናገር በላይ እመቤታችንን ለመምሰል እንደ ዓቅሚቲ መጣጣር የተሻለ ዋጋ አለው ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ” እንዳለን ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ከመተረክ በላይ ቅዱስ ጳውሎስን ለመምሰል ልንተጋ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ “ቅዱሳን አባቶቻችን መጽሐፍ ቅዱሱን በአንድ ወገን፤ የትርጓሜ መጻሕፍትን በአንድ ወገን፤ የገድላትና የድርሳናት መጻሕፍትንም በሌላ ወገን አድርገው በብልት በብልት ከፋፍለው ያስቀመጡልን የድኅነት መንገድን ለማስረዘም አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን እንድናነበው፤ ቢጸንብን በትርጓሜያት እንድንረዳው፤ በገድላቱና በድርሳናቱ ደግሞ እንደምን ተግባራዊ እንደሚኾን እንድንገነዘበው እኛም በዚያ ሕይወት ለመመላለስ እንድንጣጣር ነው እንጂ፡፡” እውነት ነው!!! የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሕይወት በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በአንድምታ ትርጓሜያትና በተለያዩ ድርሳናትና ተአምራት ተከፋፍሎ መቅረቡም ለዚኹ ዓላማ ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንብበው የማይጨርሷት እጅግ ትልቅ መጽሐፍ ናት፡፡ ከአዕምሮ በላይ የኾነ፥ ግን ደግሞ የተፈጸመ ሕይወቷን ስናነበው የእኛንም ሕይወት ስናየው፥ “የእመቤታችን አምላክ ሌላ ነው እንዴ?” ያስብላል፡፡ እስኪ ለማንኛውም ምንም እንደ ርሷ ባንኾንም የዓቅማችንን ያኽል ክርስቲያን እንኾን ዘንድ እመቤታችንን እናንብባት፤ እንማርባትም፡፡ ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያምን_የሚያክል_ንጹሕ_ፍጥረት_በሰማይም_በምድርም_ፈጽሞ_የለም_፡፡ እግዚአብሔር አብ በሰማያት ኾኖ ምሥራቁንና ምዕራቡን፣ ሰሜኑንና ደቡቡን ቢመለከት እንደ እመቤታችን ያለ ንጹሕ ፍጥረት አላገኘም፡፡ ንጽሕናዋ ልዩ ነው፡፡ “ወኢረኵሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በኅሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ - ከፈጠራት ዠምሮ በምንም በምንም ከድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ አልተለወጠችም (አልበደለችም)” /ሃይ.አበ. ዘቴዎዶጦስ ፶፫፡፳፪/፡፡ ምንም ኀጢአት በሌለበት በሰማይ ለመላዕክት ያልተቻላቸውን ንጽሕናና ቅድስና፥ እመቤታችን እንደ ባሕር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በደል በበዛበት ዓለም ኾና ኑሯለች፡፡ እኛ የተቸገርነው ፈቃዳችንን እንደ እመቤታችን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው፡፡ መለወጥ እንፈልጋለን፤ ፈቃዳችን ግን ከእኛ ጋር ነው፡፡ እመቤታችን ግን ፈቃዷን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ያስረከበች ብጽዕት ናት፡፡ ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_የጸሎት_የዝማሬና_የተመስጦ_ሕይወት_ነበራት_፡፡ ዘመዷ ኤልሳቤጥን በጐበኘቻት ጊዜ ያመሰገነችውን ምስጋና ስንመለከት ይኽን እውነት ፍንተው አድርጐ ያሳየናል፡፡ ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሲበተኑ የእመቤታችን ተግባር እነርሱን በጸሎቷ መርዳት ነበር፡፡ ክንፍ የሌላት ወፍና የጸሎት ሕይወት የሌለው ክርስቲያን አንድ ናቸው፡፡ ጸሎትና እመቤታችን ግን ለቅጽበት ስንኳ ተለያይተው የማያውቁ ወዳጆች ናቸው፡፡ የእመቤታችንን የተመስጦ ሕይወት ስናነብ ደግሞ እጃችንን በአፋችን እንጭናለን፡፡ “ማርያምሰ ተዓቅብ ዘንተ ኵሎ ነገረ ቀትወድዮ ውስተ ልባ እመቤታችን ግን ይኽን ነገር ታስተውለው ነበር፤ በልቡናዋም ታኖረው ነበር” እንጂ ለሰው አታወራውም ነበር፡፡ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፤ “የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር” ይላል፡፡ ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ቃለ_እግዚአብሔርን_ዕለት_ዕለት_የምታነብ_ነበረች፡፡ “ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም” ተብሎ እንደተጻፈ ቃለ እግዚአብሔር የዕለት ተዕለት ምግቧና መጠጧ ነበር፡፡ በሉቃ.፩፡፵፯-፶፭ በምናነበው ድንቅና ጥልቅ ምስጋናዋ ላይ የምናስተውለው ነገር ቢኖር ምን ያኽል ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደምታነብና እንደምታውቅ ነው፡፡ ማወቅ ብቻ አይደለም፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ ትጠቀምበት ነበር፡፡ መልዐኩ መጥቶ “ትፀንሲ” ሲላት “እም አይቴ ረከብከ ዘከመዝ ብሥራት ዘእንበለ ምት እም ድንግል ፅንሰት ወዘእንበለ ዘርዕ እምድር እትወት - ምድር ያለ ዘር ታፈራ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ ትፀንስ ዘንድ እንዲኽ ያለ የምሥራች ከማን አገኘኸው?” ያለችው ተሰምቶም ታይቶም የማይታወቅ ስለኾነ ነው፡፡ አንድ እንግዳ ነገር በሕይወታችን ሲመጣ እውነትነቱን የምንመዝነው በቃሉ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ሲባል ከቃሉ ባለቤት ከእግዚአብሔር ጋር መጨዋወት መነጋገር ማለት ነውና፡፡ እግዚአብሔርም ለዚያ ቃሉን ለሚያነብ ሰው ፈቃዱ ምን እንደኾነ ይገልጥለታልና፡፡ ለዚኽም ነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲኽ በማለት የሚመክረን፡- “ዕለት ዕለት ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነብ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ መጻሕፍትን የማያነቡ ብዙ ሰዎች ሕገ እግዚአብሔርን ካለማወቅ የተነሣ ክሕደት የተባለ ክፉ ልጅን ወልደዋልና፡፡ ኃጢአት የተባለ ክፉ ዛፍም ዳግም በተወለደው ሰውነታቸው ላይ አብቅለዋልና፡፡ ደጋግመው ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነቡ ግን ቢወድቁ እንኳ ተመልሰው ይነሣሉ፡፡ ልጆቼ! እናንተም ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብ ቸል አትበሉ፡፡ በጣም ተቸግራችኁ ለተከታታይ ዐሥር ቀናት ብቻ ይኽን ብትለማመዱት ከዚያ በኋላ ልምድ ይኾንላችኋል፡፡ በርግጥ ይኽ ልምምድ ለንባብ ብቻ ሳይኾን ለሌላ መንፈሳዊ ሕይወታችኁም ብትጠቀሙበት መልካም ነው፡፡” ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ከቤት ረስተነው ወደ ሥራ ቦታ ብንሔድ ምን ይሰማናል? ቃሉን ስንረሳውስ? /…. ክፍል ፪ን ነገ ይጠብቁ/ /ምንጭ፤ ምክረ አበው ቁጥር 5/

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፮ #የቅዳሴ_ምንባባት † ፩ኛ ቆሮ.፫፥፲-፳፪ ወበከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፫፥፩-፯ ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና፡፡ † የሐዋ.ሥ.፲፮÷፲፫ ወወፃዕ
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፮ #የቅዳሴ_ምንባባት † ፩ኛ ቆሮ.፫፥፲-፳፪ ወበከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፫፥፩-፯ ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና፡፡ † የሐዋ.ሥ.፲፮÷፲፫ ወወፃዕነ በዕለተ ሰንበት እምአንቀጸ ሀገር፡፡ #ምስባክ_መዝ. ፵፬፥፲፪ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፡፡ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፡፡ ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፡፡ (ትርጕም፤ የጢሮስ ልጃገረዶች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል፤ የምድር ባለጸጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ፡፡ ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ፡፡) #ወንጌል_ማር.፲፮፥፱-፲፱፤ ወተንሢኦ በጽባሕ በእሑድ ሰንበት፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ አው (ግሩም)፡፡ ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ፡፡

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፬ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፲፪፥፲፮-ፍጻ ወከመዝ ሐልዩ ምስለ ቢጽክሙ፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፭፥፮-፲፪ አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ † የሐዋ.ሥ.፲፯÷፳፫ ወበጺሕየ ዝየ ርኢኩ
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፬ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፲፪፥፲፮-ፍጻ ወከመዝ ሐልዩ ምስለ ቢጽክሙ፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፭፥፮-፲፪ አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ † የሐዋ.ሥ.፲፯÷፳፫ ወበጺሕየ ዝየ ርኢኩ ጣዖተክሙ #ምስባክ_መዝ. ፳፥፲፪ እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ፡፡ ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ፡፡ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ፡፡ (ትርጕም፤ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደሰታል፤ በማዳንህም እጅግ ተድላ ደስታ ያደርጋል፤ የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው፡፡) #ወንጌል_ሉቃስ.፲፬፥፴፩-ፍጻ፤ ወእመኒ ፈቀደ ንጉሥ ይሑር ይጽብአ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ አው (ዘቄርሎስ)፡፡ ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ (ኀቤከ እግዚኦ)

ሳምንታዊ የዐርብ ጕባኤያችን ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ስለ፡፡ #ክብረ_ድንግል_ማርያም በተለያዩ ሊቃውንትና መምህራን›› ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ድረስት የሆነው #የመሐረነ_አብ_ጸሎት /
ሳምንታዊ የዐርብ ጕባኤያችን ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ስለ፡፡ #ክብረ_ድንግል_ማርያም በተለያዩ ሊቃውንትና መምህራን›› ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ድረስት የሆነው #የመሐረነ_አብ_ጸሎት /በተለያዩ ገዳማት ከሚደርሱ የመሐረነ አብ ጸሎቶች እንደ ንብ ተቀስሞ የተዘጋጀው/ ይደርሳል፡፡ #140ኛ_ሳምንት_ዐርብ_ነሐሴ_3 /የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፡፡/

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፫ #ነሐሴ_፫#ስምዖን_ዘዓምድ_ወቅድስት_ሶፍያ #የቅዳሴ_ንባብ ፠፩ኛተሰሎ. ፫፥፩-ፍጻሜ ፤ ወሥዒነነ ተዐግሦ አብደርነ ንንበር አቴና፡፡ ፠፩ኛጴጥ. ፫፥፰-፲፭፤ ወዘሰ
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፫ #ነሐሴ_፫#ስምዖን_ዘዓምድ_ወቅድስት_ሶፍያ #የቅዳሴ_ንባብ ፠፩ኛተሰሎ. ፫፥፩-ፍጻሜ ፤ ወሥዒነነ ተዐግሦ አብደርነ ንንበር አቴና፡፡ ፠፩ኛጴጥ. ፫፥፰-፲፭፤ ወዘሰ ያፈቅራ ለሕይወት ወይፈቱ ይርአይ ፠ሐዋ.ሥራ ፲፬፥፳-ፍጻሜ፤ ወበሳኒታ ሖረ ምስለ በርናባስ፡፡ #ምስባክ_/መዝ. ፵፬፥፲፪/ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፡፡ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፡፡ ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፡፡ #ወንጌል_ሉቃስ.፲፰፥፱-፲፰ ወይቤሎሙ ለእለ ያጽድቁ ርእሶሙ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ_ጐሣዕ_ልብየ_ቃለ_ሠናየ

ሕንጼሃ ለደብረ ጅጅጋ ማርያም፤ (እንኳን ደስ አለን) ልክ የዛሬ ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ርኵስ መንፈስ ባደረባቸውና ባነሳሳቸው ሰዎች የጅጅጋ ማርያም መቃጠሏን ዘግበንላችሁ ነበር፡፡ ልክ በዓመቱ ሐምሌ
+3
ሕንጼሃ ለደብረ ጅጅጋ ማርያም፤ (እንኳን ደስ አለን) ልክ የዛሬ ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ርኵስ መንፈስ ባደረባቸውና ባነሳሳቸው ሰዎች የጅጅጋ ማርያም መቃጠሏን ዘግበንላችሁ ነበር፡፡ ልክ በዓመቱ ሐምሌ 22 መንፈስ ቅዱስ ባደረባቸውና ባነሳሳቸው ምዕመናንና የሌላም እምነት ተከታዮች አስተዋጽዖ ጭምር ሕንፃዋ ታድሶ ተመርቋል፡፡

#የመጻሕፍት_ማሰባሰቢያ_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን በመጻሕፍት ማስነበብና ማዋስ ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን መጻሕፍትን የምናሰባስ
+2
#የመጻሕፍት_ማሰባሰቢያ_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን በመጻሕፍት ማስነበብና ማዋስ ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን መጻሕፍትን የምናሰባስብበት ልዩ መርሐ ግብር፡፡ ፠ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 11 የመጻሕፍት ሽያጭና የመጻሕፍት ማሰበብ ይካሄዳል፡፡ #ነሐሴ 11 ዝክረ ቅዱስ ያሬድና ልዩ መርሐ ግብሩ አብሮ ይካሄዳል፡፡ ፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00 ሰዐት በቅዱስ ገብርኤል አዳራሽ ታላላቅ የመጻሕፍት መምህራንና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይካሄዳል፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡ ‹‹ስትመጣ …. ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ፡፡›› **ቤተ መጻሕፍታችንን ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ማኅበረ ምዕናንንና ማኅበረ ካህናትን ታሳቢ አድርጎ የተደራጀ መሆኑ፡፡

ጾመ ፍልሰታ #ጾም_በሐዲስ_ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አብነት በማድረግ ጾምን በአዋጅ እንድንጾም በቀኖናዋ (በሥርዐቷ) ደንግጋለች፡፡ በቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡- 1. ✣ ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ) 5. ✣ ጾመ ነነዌ 2. ✣ ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ) 6. ✣ጾመ ጋድ 3. ✣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) 7. ✣ ጾመ ፍልሰታ 4. ✣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) #ጾመ_ፍልሰታ ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው። እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅድስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች አስከሬኗን ገንዘውና ከፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለእመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው። ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ ዛሬም ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል። በአጠቃላይ የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ሐዋርያት ያገኙን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን። ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ ለሌሎችም እንዲዳረስ የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/publishing_tools/?section=PUBLISHED_POSTS&sort[0]=published_time_descending እንዲሁም የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me/medihanaelem

(#እንዲጠይቅላችሁ_የምትፈልጉትን_ጥያቄዎች_በፌስቡክና_ገጻችን_inbox_በቴሌግራም_ላይ_Message_ወይም_በ0922851374_ማሳወቅ_ትችላላችሁ_፡፡) ፌስቡክ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/publishing_tools/?section=PUBLISHED_POSTS&sort[0]=published_time_descending ቴሌግራም፤ FINOTE HIWOT የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት /የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፡፡/

ልዩ የምክረ አበው መርሐ ግብር፤ ለ4 ሳምንት በተከታታይ ሲሰጥ በቆየው የኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት ላይ ማጠቃለያ በጥያቄና መልስ በሊቃውንት አባቶችና ወንድሞች ትምህርቱና ውይይቱ ይሰጣል፡፡ እንዳያ
+1
ልዩ የምክረ አበው መርሐ ግብር፤ ለ4 ሳምንት በተከታታይ ሲሰጥ በቆየው የኦርቶዶክሳዊ የጾታ ትምህርት ላይ ማጠቃለያ በጥያቄና መልስ በሊቃውንት አባቶችና ወንድሞች ትምህርቱና ውይይቱ ይሰጣል፡፡ እንዳያመልጥዎ!!! እንዳያመልጥዎ!!! #ዐርብ_ሐምሌ_26/2011ዓ.ም. ከቀኑ 11፡30 -2፡00፡፡ (139ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ፡፡) በጕባኤው፤ #ስለ_መንፈሳዊ_ሕይወትና_ፈተናዎች #ስለ_እጮኝነት_አመራረጥና_የእጮኝነት_ጊዜ #ስለ_ድንግልና_ሕይወትና_ጋብቻ (#እንዲጠይቅላችሁ_የምትፈልጉትን_ጥያቄዎች_በፌስቡክና_ገጻችን_inbox_በቴሌግራም_ላይ_Message_ወይም_በ0922851374_ማሳወቅ_ትችላላችሁ_፡፡) ፌስቡክ፤ https://www.facebook.com/%25E1%258B%25A8%25E1%2589%2580%25E1%258C%25A8%25E1%258A%2594-%25E1%258B%25B0%25E1%2589%25A5%25E1%2588%25A8-%25E1%2588%25B0%25E1%2588%258B%25E1%2588%259D-%25E1%2588%2598%25E1%258B%25B5%25E1%258A%2580%25E1%258A%2594%25E1%258B%2593%25E1%2588%2588%25E1%2588%259D%25E1%258A%2593-%25E1%258B%25B0%25E1%2589%25A5%25E1%2588%25A8-%25E1%2589%25B5%25E1%258C%2589%25E1%258 ቴሌግራም፤ FINOTE HIWOT የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት /የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፡፡/

#ታላቁ_ሰማዕት_ቅዱስ_መርቆሬዎስ፤ የወላጆቹ አገር አስሊጥ የምትባል ስትኾን እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሯቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሯቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡ መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብረውት ነበሩ፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሯቸውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡ ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ ✤ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እንዲሁም ጎርጎርዮስን ረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ በስዕሉ ላይ ያለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ይዞ ከተሳለው ጦር ጫፍ ላይም ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ✤ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡ መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስሏቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኰሳትን አፍርቷል፡፡ /ምንጭ፤ ከገድላት አንደበት/ LIKE & INVITE የፌስ ቡክ ገጻችንን Finote Hiwot ወይም <<የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት››