ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 042 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 280 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 240 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 042 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 29 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 518، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 1، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.50‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.35‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 090 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 660 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 30 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 042
المشتركون
+124 ساعات
+917 أيام
+51830 أيام
أرشيف المشاركات
#3ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት!!! ፠#በ1966ዓ.ም.#አገልግሎቱን_ለጀመረው_አንጋፋ_ቤተ_መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡ ፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00 ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ

#ክርስቲያን_እንኾን_ዘንድ_እመቤታችንን_እናንብባት_እንማርባትም_ክፍል_፪:: ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_እጅግ_ትሑት_ነች_፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስን ስታነብና “ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች” በሚለው አንቀጽ ስትደርስ “ምነው እኔ በኾንኩኝ?” አላለችም፤ “ምነው በዘመኗ ደርሼ ይኽቺን ድንግል ባገለገልኳት?” አለች እንጂ፡፡ መልዐኩ “ተፈስሒ” ሲላት “ይገባኛል” አላለችም፤ “ነየ አመተ እግዚአብሔር - የእግዚአብሔር ገረዱ እነሆኝ” አለች እንጂ /ሉቃ.፩፡፴፰/፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ “የጌታዬ እናቱ እመቤቴ ወደኔ ትመጭ ዘንድ እኔ ምንድነኝ?” ስትላት “ልክ ነሽ፤ ይደልወኒ - ይገባኛል፤ አምላክን ፀንሻለኹና” አላለችም፤ “የባርያይቱን ውርደት ተመልክቷልና” አለች እንጂ፡፡ ብትል እኮ ያምርባታል፡፡ ነገር ግን አላለችም፡፡ ምንም ሳንሠራ “ይገባኛል” የምንል የማን ልጆች እንኾን? እመቤታችን ኤልሳቤጥ እንዳረገዘች ሰምታ ትጠይቃት ዘንድ መሔዷ የትሕትናዋን ጥልቀት ያሳያል፡፡ ለልማዱ ባርያ ወደ ጌታው ይሔዳል፡፡ አኹን የኾነው ግን እንዲኽ አይደለም፡፡ የመጣችው ኤልሳቤጥ አይደለችምና፤ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ሔደች እንጂ፤ ያውም በዚያ ተራራማው ስፍራ፡፡ የእመቤታችን ትሕትናዋ ግሩም ነው፡፡ ትሕትና ሰዎችን አማልክት ዘበጸጋ ታደርጋለች፤ ትዕቢት ደግሞ ቅዱሳን መላዕክትን ታዋርዳለች፡፡ ትዕቢት እጅግ ክፉ ነው፡፡ ትዕቢት ሰዎች ከተለመደው ባሕርያቸው አስወጥቶ ያደነዝዛቸዋል፤ የስንፍናን ካባ ያጐናጽፋቸዋል፡፡ ትዕቢት እንደ ዕብድ ያናግራል፡፡ አንድ ሰው ቁመቱ ሦስት ክንድ ከስንዝር ቢኾን እንኳን ትዕቢቱ ተራራን ያሳክሏል፤ ተራራን ባያክልም እንደዚያ እንደኾነ እንዲያስብ ያደርጓል፡፡ ትዕቢት ከዕብደት የከፋ በሽታ ነው፡፡ ምክንያቱም ትዕቢት በእኛ ፈቃድ የሚይዘን በሽታ ሲኾን ዕብደት ግን ሳናውቀው ሊይዘን የሚችል የጤና እክል ነውና፡፡ ወዮ! መቼ ይኾን ከዚኽ በሽታ የምንላቀቀው? ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_እጅግ_የምታምንና_ታዛዥ_ነበረች_፡፡ ሕይወቷ ኹሉ “ይኵነኒ በከመ ትቤለኒ - እንደ ቃልኽ ይደረግልኝ” በሚል የተመላ ነው፡፡ ወላጆቿ ለቤተ እግዚአብሔር ቢያስረክቧት “ይኵነኒ”፤ ካህናት “ቤተ መቅደሳችንን ታረክስብናለች” ብለው ቢያስወጧት “ይኵነኒ”፤ “በድንግልና ፀንሰሽ በድንግልና ትወልጃለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ “ከሦስቱ ቅዱስ አንዱን ቅዱስ በበረት ትወልጂዋለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ “የስዱዳን ተስፋቸውን አዝለሽ ትሰደጃለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ ሽፍቶች ቢያስደነግጧት “ይኵነኒ”፤ ማየ ሕይወትን አዝላ ውኃ ቢጠማት አንድም ልጇ ቢጠማው “ይኵነኒ”፤ አባቶቿ ፵ ዓመት የፈጀባቸውን መንገድ በልጅነት ዕድሜዋ “ልጅ አዝለሽ ትሔጃለሽ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ “ሄሮድስ ሞቷልና ተመለሺ” ስትባል “ይኵነኒ”፤ አንዱን ልጇ ሲያሰቃዩባት ሲገርፉባትና ሲገድሉባት “ይኵነኒ”፡፡ ታዛዥነቷ ከአዕምሮ የሚያልፍ ነው፡፡ ሄሬኖዎስ የተባለው ቅዱስ አባት የእመቤታችንን ታዛዥነት ለምን እንደኾነ ሲያስተምር እንዲኽ አለ፡- “እነሆ ጌታ የራሱ ወደኾኑት በግልጥ (በለቢሰ ሥጋ) መጣ፡፡ ትዕዛዙን ተላልፎ በዕጽ የሞተውን አዳም በዕጽ ላይ ታዝዞና ካሣውን ከፍሎ፣ ወደ ጥንተ ተፈጥሮው ይመልሰው ዘንድ በራሱ ጥበብ ከፍጥረቱ ተወለደ፡፡ ለአንድ ወንድ የታጨችው ድንግል በምክረ ከይሲ ያመጣችውን ያለመታዘዝ ኃይል የእውነት መልዐክ ለአንድ ወንድ ለታጨችው ድንግል ባበሠራት ጊዜ ፈራረሰ፡፡ ቀዳማይቱ ሔዋን ከእግዚአብሔር እንድትርቅና ቃሉን እንድትቃወም ክፉ መልዐክ አታለላት፡፡ ዳግማይቱ ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ደጉ መልዐክ ይዞት የመጣው መልካሙን ዜና እንድትቀበለውና እግዚአብሔርን በከዊነ ቃሉ እንድትወልደው አመነች፡፡ ቀዳማይቱ ሔዋን እግዚአብሔርን እንዳትታዘዘው ክፉ መልዐክ አታለላት፤ ወደቀችም፡፡ ዳግማይቱ ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን እግዚአብሔርን እንድትታዘዝ ቅዱስ መልዐክ አሳመናት፤ ርሷም ሔዋንን ረዳቻት፡፡ ነገደ አዳም በአንዲት ድንግል አለመታዘዝ ምክንያት ሞት ተፈረደበት፣ ኾኖም በሌላይቱ ድንግል መታዘዝ ምክንያት ዳነ፡፡” በሕይወታችን “ይኵነኒ” ማለትን መልመድ ጸጋ እግዚአብሔርን በሕይወታችን ማትረፍረፍ ነው፡፡ እንላለን ወይ ነው ቁምነገሩ? እግዚአብሔርን የሚጋርዱብን ነገሮች (ለምሳሌ ሥራ፣ ውበት፣ ሥልጣን፣ ሀብት፣…) ከሕይወታችን ይወገዱ ብንባል “ይኵነኒ” ለማለት ምን ያኽል ዝግጁዎች ነን? ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ርኅሪኅተ_ኅሊና_ናት_፡፡ እጅግ አዛኝ እናት!!! ሊቃውንት እንደሚያስተምሩት ምኅረት (ምጽዋት) ሦስት ዓይነት ነው፡፡ ምኅረት ሥጋዊ፣ ምኅረት መንፈሳዊና ምኅረት ነፍሳዊ፡፡ ምኅረት ሥጋዊ የታረዘን ማልበስ፣ የተራበን ምጉረስ ነው፡፡ ምኅረት መንፈሳዊ የተጨነቀን ወይም ያዘነን ሰው መርዳት፣ ወይም ማጽናናት ነው፡፡ ምኅረት ነፍሳዊ ደግሞ ሰዎች የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኙ መርዳት ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሰውስ ይቅርና ለተጠማ ውሻም ሳይቀር በወርቅ ጫማዋ ውኃን ያጠጣች ርኅርኅተ ኅሊና ናት፤ ምኅረት ሥጋዊ፡፡ እናቶቻችንን በምጥ ጊዜ እንዴት እንደምትረዳቸው መናገርም ለቀባሪ ማርዳት ነው፤ ምኅረት መንፈሳዊ፡፡ ክርስቲያን፥ በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ኾኖ ከእመቤታችንን ርኅራኄ (ምልጃና ቃል ኪዳን) ያልቀመሰ የለም፤ ምኅረት ነፍሳዊ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በቅዳሜ ውዳሴው ላይ “የዚኽ ዓለም ሰዎች አማልዱኝ ቢሏቸው ነገር አጽንተው ይመለሳሉ፡፡ ርሷ ግን ማእምንት ሰአሊተ ምኅረት - የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት” ያለውም ስለዚኹ ነው፡፡ እኛስ ምን ያኽል ርኅሩኀን እንኾን? ኧረ በወርቅ ጫማ ቀርቶብን በንጹሕ ሳህን ለመመጽወት ልቡናችን በራራ? ኧረ ለውሻው ቀርቶብን ለሰዉም ባዘንን? የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሕይወት ገና ስንዠምር እንደተናገርነው በሕይወት ዘመን አንብበው የማይጨርሱት እጅግ ትልቅ መጽሐፍ ነውና አንድ ኹለት ብለን መቁጠር አይቻለንም፡፡ ማንበብ ከቻልን ሕይወቷ ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን አስተማሪ ነው፡፡ “ማርያም ፊደል ናት ….” ብለን መዘመራችንም ስለዚኹ ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ! እንኪያስ የምንዘምር ብቻ አንኹን፤ እናንብባትም ጭምር እንጂ፡፡ የምናነብ ብቻ አንኹን፤ እንለወጥም ጭምር እንጂ፡፡ ማንበቡንማ ዲያብሎስም ያነባል፡፡ እንኪያስ አንብበን እንለወጥና በእውነት የድንግል ልጆች እንኹን፡፡ ይኽን እንድናደርግ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን ወአሜን፡፡ /ምንጭ፤ ምክረ አበው ቁጥር 5/ /ከጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ የተወሰደ/

#4ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት!!! ፠#በ1966ዓ.ም.#አገልግሎቱን_ለጀመረው_አንጋፋ_ቤተ_መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ
#4ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት!!! ፠#በ1966ዓ.ም.#አገልግሎቱን_ለጀመረው_አንጋፋ_ቤተ_መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡ ፠ ከነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 11 የመጻሕፍት ሽያጭና የመጻሕፍት ማሰባሰብ ይካሄዳል፡፡ ፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00 ሰዐት በቅዱስ ገብርኤል አዳራሽ ከዝክረ ቅዱስ ያሬድ ጋር ግብሩ አብሮ የመጻሕፍት መምህራንና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይካሄዳል፡፡ ‹‹ስትመጣ …. ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ፡፡›› **ቤተ መጻሕፍታችንን ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ማኅበረ ምዕናንንና ማኅበረ ካህናትን ታሳቢ አድርጎ የተደራጀ መሆኑ ነው፡፡ ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት::

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ዘነሐሴ_፰_ ፠#አልዓዛር_ወሰሎሜ_ብእሲቱ_ወውሉዱ#፯ቱ_ወአሞን_፡፡ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፱፥፳፬-ፍጻ ፤ ወንሕነ እሙንቱ እለ ጸውዐነ ውስተ ክብሩ፡፡
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ዘነሐሴ_፰_ ፠#አልዓዛር_ወሰሎሜ_ብእሲቱ_ወውሉዱ#፯ቱ_ወአሞን_፡፡ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፱፥፳፬-ፍጻ ፤ ወንሕነ እሙንቱ እለ ጸውዐነ ውስተ ክብሩ፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፬፥፲፪-ፍ ፤ አኃዊነ ኢታንክርዋ ልእንተ ትመጽአክሙ:: † የሐዋ.፲፮÷፴፭-ፍ ፤ ወጸቢሖ ለዐኩ መኳንንት፡፡ #ምስባክ_መዝ. ፶፯፥፰ ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ፡፡ ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ፡፡ ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኀጠክሙ፡፡ (ትርጕም፤እሳት ወደቀች ፀሐይንም አላየኋትም፤ እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል፡፡) ማቴ.፯፥፲፪-፳፮ ፤ ኵሎኬ ዘትፈቅዱ ይገበሩ ለክሙ ሰብእ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ ፤ ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ፡፡

#5ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ
+1
#5ት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን #መጻሕፍትን_የምናሰባስብበት_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡ ፠ ከነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 11 የመጻሕፍት ሽያጭና የመጻሕፍት ማሰባሰብ ይካሄዳል፡፡ ፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00 ሰዐት በቅዱስ ገብርኤል አዳራሽ ከዝክረ ቅዱስ ያሬድ ጋር ግብሩ አብሮ ታላላቅ የመጻሕፍት መምህራንና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይካሄዳል፡፡ ‹‹ስትመጣ …. ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ፡፡›› **ቤተ መጻሕፍታችንን ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ማኅበረ ምዕናንንና ማኅበረ ካህናትን ታሳቢ አድርጎ የተደራጀ መሆኑ ነው፡፡

/ከጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ የተወሰደ/

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፯#ምስባኩ_ከድምፅ_ጋር_ #ነሐሴ_፯_ፅንሰታ_ለማርያም_ወተስእሎተ_ቂሣርያ_ወጢሞቴዎስ_ሊቀ_ጳጳሳት_ወልደቱ_ለዮሴፍ_ወልደ_ራሄል_ወናዖድ_ንጉሠ_ኢትዮጵያ_ #የቅዳሴ_ንባብ ፠† ዕብራ. ፱፥፩- ፲፯፤ ወለቀዳሚትኒ ደብተራ፡፡ ፠ † ፩ኛጴጥ.፪፥፮-፲፰፤ እስመ ከመዝ ጽሑፍ ናሁ እሠይም፡፡ ፠ † የሐዋ.ሥ.፲፥፩-፴፤ ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ፡፡ #ምስባክ_መዝ. ፺፫፥፲፪ ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ፡፡ ወዘመሀርኮ ሕገከ፡፡ ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት፡፡ (ትርጕም፤ አቤቱ አንተ የገሠጽከው ሰው ብፁዕ ነው፤ ሕግህንም ያስተማርሀው፤ ከክፉዎች ዘመናት ይርቅ ዘንድ፡፡) #ወንጌል_ማቴ.፲፮፥፲፫-፳፬፤ ወበጺሖ ኢየሱስ ብሔረ ቂሣርያ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ_ጐሣዕ_ልብየ_ቃለ_ሠናየ #ነሐሴ_ሰባት_ጽንሰታ_ለማርያም_ድንግል፤ #ክፍል_፩_ የዓለም ኹሉ ደስታን ወዳመጣችው ዕለት አደረሳችኁ፤ አደረሰን፡፡ ነሐሴ ሰባት ቀን የባሕርያችን መመኪያ የምትኾን ንጽሕተ ንጹሐን፥ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአባቱ ከኢያቄምና ከእናቷ ሐና የተፀነሰችበት ዕለት ነው፡፡ ይኽቺን ዕለት ያልናፈቀ ትውልድ የለም፡፡ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ለኾነባቸው ቅዱሳን አበው ወእማት ተስፋቸው የሚፈጸመው በዛሬው ዕለት በተጸነሰችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነውና፡፡ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ከፈጣሪያችን እግዚአብሔር ቀጥሎ ከፍጥረታት እንደ እመቤታችን ከፍ ከፍ የምታደርገው ፍጥረት የሌለው ስለዚኹ ነው፡፡ መትሕተ ፈጣሪ፥ መልዕልተ ፍጡራን፤ (ከፈጣሪ በታች ፥ ከፍጡራን በላይ) ናትና፡፡ ሊቃውንቱ፤ “ሐና አንቺን የጸነሰችበት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤” ብለው የሚዘምሩላትም ይኽን ምሥጢር በልቡናቸው ቋጥረው ነው /አባ ጽጌ ድንግል፤ ማኅሌተ ጽጌ ቁ.፵፬/፡፡ ስለ እመቤታችን ከመናገር በላይ እመቤታችንን ለመምሰል እንደ ዓቅሚቲ መጣጣር የተሻለ ዋጋ አለው ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ” እንዳለን ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ከመተረክ በላይ ቅዱስ ጳውሎስን ለመምሰል ልንተጋ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ “ቅዱሳን አባቶቻችን መጽሐፍ ቅዱሱን በአንድ ወገን፤ የትርጓሜ መጻሕፍትን በአንድ ወገን፤ የገድላትና የድርሳናት መጻሕፍትንም በሌላ ወገን አድርገው በብልት በብልት ከፋፍለው ያስቀመጡልን የድኅነት መንገድን ለማስረዘም አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን እንድናነበው፤ ቢጸንብን በትርጓሜያት እንድንረዳው፤ በገድላቱና በድርሳናቱ ደግሞ እንደምን ተግባራዊ እንደሚኾን እንድንገነዘበው እኛም በዚያ ሕይወት ለመመላለስ እንድንጣጣር ነው እንጂ፡፡” እውነት ነው!!! የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሕይወት በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በአንድምታ ትርጓሜያትና በተለያዩ ድርሳናትና ተአምራት ተከፋፍሎ መቅረቡም ለዚኹ ዓላማ ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንብበው የማይጨርሷት እጅግ ትልቅ መጽሐፍ ናት፡፡ ከአዕምሮ በላይ የኾነ፥ ግን ደግሞ የተፈጸመ ሕይወቷን ስናነበው የእኛንም ሕይወት ስናየው፥ “የእመቤታችን አምላክ ሌላ ነው እንዴ?” ያስብላል፡፡ እስኪ ለማንኛውም ምንም እንደ ርሷ ባንኾንም የዓቅማችንን ያኽል ክርስቲያን እንኾን ዘንድ እመቤታችንን እናንብባት፤ እንማርባትም፡፡ ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያምን_የሚያክል_ንጹሕ_ፍጥረት_በሰማይም_በምድርም_ፈጽሞ_የለም_፡፡ እግዚአብሔር አብ በሰማያት ኾኖ ምሥራቁንና ምዕራቡን፣ ሰሜኑንና ደቡቡን ቢመለከት እንደ እመቤታችን ያለ ንጹሕ ፍጥረት አላገኘም፡፡ ንጽሕናዋ ልዩ ነው፡፡ “ወኢረኵሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በኅሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ - ከፈጠራት ዠምሮ በምንም በምንም ከድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ አልተለወጠችም (አልበደለችም)” /ሃይ.አበ. ዘቴዎዶጦስ ፶፫፡፳፪/፡፡ ምንም ኀጢአት በሌለበት በሰማይ ለመላዕክት ያልተቻላቸውን ንጽሕናና ቅድስና፥ እመቤታችን እንደ ባሕር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በደል በበዛበት ዓለም ኾና ኑሯለች፡፡ እኛ የተቸገርነው ፈቃዳችንን እንደ እመቤታችን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው፡፡ መለወጥ እንፈልጋለን፤ ፈቃዳችን ግን ከእኛ ጋር ነው፡፡ እመቤታችን ግን ፈቃዷን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ያስረከበች ብጽዕት ናት፡፡ ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_የጸሎት_የዝማሬና_የተመስጦ_ሕይወት_ነበራት_፡፡ ዘመዷ ኤልሳቤጥን በጐበኘቻት ጊዜ ያመሰገነችውን ምስጋና ስንመለከት ይኽን እውነት ፍንተው አድርጐ ያሳየናል፡፡ ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሲበተኑ የእመቤታችን ተግባር እነርሱን በጸሎቷ መርዳት ነበር፡፡ ክንፍ የሌላት ወፍና የጸሎት ሕይወት የሌለው ክርስቲያን አንድ ናቸው፡፡ ጸሎትና እመቤታችን ግን ለቅጽበት ስንኳ ተለያይተው የማያውቁ ወዳጆች ናቸው፡፡ የእመቤታችንን የተመስጦ ሕይወት ስናነብ ደግሞ እጃችንን በአፋችን እንጭናለን፡፡ “ማርያምሰ ተዓቅብ ዘንተ ኵሎ ነገረ ቀትወድዮ ውስተ ልባ እመቤታችን ግን ይኽን ነገር ታስተውለው ነበር፤ በልቡናዋም ታኖረው ነበር” እንጂ ለሰው አታወራውም ነበር፡፡ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ፤ “የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር” ይላል፡፡ ፠#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ቃለ_እግዚአብሔርን_ዕለት_ዕለት_የምታነብ_ነበረች፡፡ “ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም” ተብሎ እንደተጻፈ ቃለ እግዚአብሔር የዕለት ተዕለት ምግቧና መጠጧ ነበር፡፡ በሉቃ.፩፡፵፯-፶፭ በምናነበው ድንቅና ጥልቅ ምስጋናዋ ላይ የምናስተውለው ነገር ቢኖር ምን ያኽል ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደምታነብና እንደምታውቅ ነው፡፡ ማወቅ ብቻ አይደለም፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ ትጠቀምበት ነበር፡፡ መልዐኩ መጥቶ “ትፀንሲ” ሲላት “እም አይቴ ረከብከ ዘከመዝ ብሥራት ዘእንበለ ምት እም ድንግል ፅንሰት ወዘእንበለ ዘርዕ እምድር እትወት - ምድር ያለ ዘር ታፈራ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ ትፀንስ ዘንድ እንዲኽ ያለ የምሥራች ከማን አገኘኸው?” ያለችው ተሰምቶም ታይቶም የማይታወቅ ስለኾነ ነው፡፡ አንድ እንግዳ ነገር በሕይወታችን ሲመጣ እውነትነቱን የምንመዝነው በቃሉ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ሲባል ከቃሉ ባለቤት ከእግዚአብሔር ጋር መጨዋወት መነጋገር ማለት ነውና፡፡ እግዚአብሔርም ለዚያ ቃሉን ለሚያነብ ሰው ፈቃዱ ምን እንደኾነ ይገልጥለታልና፡፡ ለዚኽም ነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲኽ በማለት የሚመክረን፡- “ዕለት ዕለት ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነብ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ መጻሕፍትን የማያነቡ ብዙ ሰዎች ሕገ እግዚአብሔርን ካለማወቅ የተነሣ ክሕደት የተባለ ክፉ ልጅን ወልደዋልና፡፡ ኃጢአት የተባለ ክፉ ዛፍም ዳግም በተወለደው ሰውነታቸው ላይ አብቅለዋልና፡፡ ደጋግመው ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነቡ ግን ቢወድቁ እንኳ ተመልሰው ይነሣሉ፡፡ ልጆቼ! እናንተም ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብ ቸል አትበሉ፡፡ በጣም ተቸግራችኁ ለተከታታይ ዐሥር ቀናት ብቻ ይኽን ብትለማመዱት ከዚያ በኋላ ልምድ ይኾንላችኋል፡፡ በርግጥ ይኽ ልምምድ ለንባብ ብቻ ሳይኾን ለሌላ መንፈሳዊ ሕይወታችኁም ብትጠቀሙበት መልካም ነው፡፡” ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ከቤት ረስተነው ወደ ሥራ ቦታ ብንሔድ ምን ይሰማናል? ቃሉን ስንረሳውስ? /…. ክፍል ፪ን ነገ ይጠብቁ/ /ምንጭ፤ ምክረ አበው ቁጥር 5/

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፮ #የቅዳሴ_ምንባባት † ፩ኛ ቆሮ.፫፥፲-፳፪ ወበከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፫፥፩-፯ ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና፡፡ † የሐዋ.ሥ.፲፮÷፲፫ ወወፃዕ
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፮ #የቅዳሴ_ምንባባት † ፩ኛ ቆሮ.፫፥፲-፳፪ ወበከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፫፥፩-፯ ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና፡፡ † የሐዋ.ሥ.፲፮÷፲፫ ወወፃዕነ በዕለተ ሰንበት እምአንቀጸ ሀገር፡፡ #ምስባክ_መዝ. ፵፬፥፲፪ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፡፡ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፡፡ ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፡፡ (ትርጕም፤ የጢሮስ ልጃገረዶች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል፤ የምድር ባለጸጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ፡፡ ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ፡፡) #ወንጌል_ማር.፲፮፥፱-፲፱፤ ወተንሢኦ በጽባሕ በእሑድ ሰንበት፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ አው (ግሩም)፡፡ ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ፡፡

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፬ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፲፪፥፲፮-ፍጻ ወከመዝ ሐልዩ ምስለ ቢጽክሙ፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፭፥፮-፲፪ አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ † የሐዋ.ሥ.፲፯÷፳፫ ወበጺሕየ ዝየ ርኢኩ
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፬ #የቅዳሴ_ምንባባት † ሮሜ ፲፪፥፲፮-ፍጻ ወከመዝ ሐልዩ ምስለ ቢጽክሙ፡፡ † ፩ኛ ጴጥ.፭፥፮-፲፪ አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ † የሐዋ.ሥ.፲፯÷፳፫ ወበጺሕየ ዝየ ርኢኩ ጣዖተክሙ #ምስባክ_መዝ. ፳፥፲፪ እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ፡፡ ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ፡፡ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ፡፡ (ትርጕም፤ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደሰታል፤ በማዳንህም እጅግ ተድላ ደስታ ያደርጋል፤ የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው፡፡) #ወንጌል_ሉቃስ.፲፬፥፴፩-ፍጻ፤ ወእመኒ ፈቀደ ንጉሥ ይሑር ይጽብአ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ አው (ዘቄርሎስ)፡፡ ጐሣዕ ልብየ ቃለ ሠናየ (ኀቤከ እግዚኦ)

ሳምንታዊ የዐርብ ጕባኤያችን ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ስለ፡፡ #ክብረ_ድንግል_ማርያም በተለያዩ ሊቃውንትና መምህራን›› ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ድረስት የሆነው #የመሐረነ_አብ_ጸሎት /
ሳምንታዊ የዐርብ ጕባኤያችን ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት ስለ፡፡ #ክብረ_ድንግል_ማርያም በተለያዩ ሊቃውንትና መምህራን›› ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ድረስት የሆነው #የመሐረነ_አብ_ጸሎት /በተለያዩ ገዳማት ከሚደርሱ የመሐረነ አብ ጸሎቶች እንደ ንብ ተቀስሞ የተዘጋጀው/ ይደርሳል፡፡ #140ኛ_ሳምንት_ዐርብ_ነሐሴ_3 /የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፡፡/

#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፫ #ነሐሴ_፫#ስምዖን_ዘዓምድ_ወቅድስት_ሶፍያ #የቅዳሴ_ንባብ ፠፩ኛተሰሎ. ፫፥፩-ፍጻሜ ፤ ወሥዒነነ ተዐግሦ አብደርነ ንንበር አቴና፡፡ ፠፩ኛጴጥ. ፫፥፰-፲፭፤ ወዘሰ
#የጾመ_ፍልሰታ_ምንባባት_ዘነሐሴ_፫ #ነሐሴ_፫#ስምዖን_ዘዓምድ_ወቅድስት_ሶፍያ #የቅዳሴ_ንባብ ፠፩ኛተሰሎ. ፫፥፩-ፍጻሜ ፤ ወሥዒነነ ተዐግሦ አብደርነ ንንበር አቴና፡፡ ፠፩ኛጴጥ. ፫፥፰-፲፭፤ ወዘሰ ያፈቅራ ለሕይወት ወይፈቱ ይርአይ ፠ሐዋ.ሥራ ፲፬፥፳-ፍጻሜ፤ ወበሳኒታ ሖረ ምስለ በርናባስ፡፡ #ምስባክ_/መዝ. ፵፬፥፲፪/ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፡፡ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፡፡ ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፡፡ #ወንጌል_ሉቃስ.፲፰፥፱-፲፰ ወይቤሎሙ ለእለ ያጽድቁ ርእሶሙ፡፡ #ቅዳሴ_ዘእግዝእትነ_ጐሣዕ_ልብየ_ቃለ_ሠናየ

ሕንጼሃ ለደብረ ጅጅጋ ማርያም፤ (እንኳን ደስ አለን) ልክ የዛሬ ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ርኵስ መንፈስ ባደረባቸውና ባነሳሳቸው ሰዎች የጅጅጋ ማርያም መቃጠሏን ዘግበንላችሁ ነበር፡፡ ልክ በዓመቱ ሐምሌ
+3
ሕንጼሃ ለደብረ ጅጅጋ ማርያም፤ (እንኳን ደስ አለን) ልክ የዛሬ ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ርኵስ መንፈስ ባደረባቸውና ባነሳሳቸው ሰዎች የጅጅጋ ማርያም መቃጠሏን ዘግበንላችሁ ነበር፡፡ ልክ በዓመቱ ሐምሌ 22 መንፈስ ቅዱስ ባደረባቸውና ባነሳሳቸው ምዕመናንና የሌላም እምነት ተከታዮች አስተዋጽዖ ጭምር ሕንፃዋ ታድሶ ተመርቋል፡፡

#የመጻሕፍት_ማሰባሰቢያ_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን በመጻሕፍት ማስነበብና ማዋስ ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን መጻሕፍትን የምናሰባስ
+2
#የመጻሕፍት_ማሰባሰቢያ_ሳምንትና_ልዩ_መርሐ_ግብር_ከነሐሴ_1_እስከ_ነሐሴ_11_፡፡ ፠በ1966ዓ.ም. አገልግሎቱን በመጻሕፍት ማስነበብና ማዋስ ለጀመረው አንጋፋ ቤተ መጻሕፍታችን መጻሕፍትን የምናሰባስብበት ልዩ መርሐ ግብር፡፡ ፠ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 11 የመጻሕፍት ሽያጭና የመጻሕፍት ማሰበብ ይካሄዳል፡፡ #ነሐሴ 11 ዝክረ ቅዱስ ያሬድና ልዩ መርሐ ግብሩ አብሮ ይካሄዳል፡፡ ፠ የመጨረሻ መርሐ ግብሩ #ቅዳሜ_ነሐሴ_11_ቀን_2011_ዓ.ም. ከ11፡30 - 2፡00 ሰዐት በቅዱስ ገብርኤል አዳራሽ ታላላቅ የመጻሕፍት መምህራንና ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት ይካሄዳል፡፡ ፠#ቅዱስ_ያሬድ_ለቤተ_ክርስቲያናችን_ድንቅና_ዕንቊ_የሆኑ_5ት_መጻሕፍትን_ደርሶ_አብርክቶልናል_እኛስ_ለቤተ_መጻሕፍቶቻችን_ምን_ያህል_መጻሕፍት_አስተዋጽዖ_አድርገናል_??፡፡ ‹‹ስትመጣ …. ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ፡፡›› **ቤተ መጻሕፍታችንን ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ማኅበረ ምዕናንንና ማኅበረ ካህናትን ታሳቢ አድርጎ የተደራጀ መሆኑ፡፡