የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 106 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 309,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 094 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 106 名订阅者。
根据 01 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 660,过去 24 小时变化为 29,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.96%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.05% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 477 次浏览,首日通常累积 331 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 02 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 106
订阅者
+2924 小时
+2067 天
+66030 天
帖子存档
16 093
በሕይወታችን ወስጥ የነበሩ አሁን ላይ ግን አይናችንን ጨፍነን ስንገልጥ አጠገባችን ላጣናቸው ሰዎች ከራሳችን ያስቀደምናቸውን ያክል ለራሳችን ጊዜ ሰተን ቢሆን እና ጊዜውን ለራሳችን ተጠቅመነው ቢሆን ኖሮ ያሁኑ ብቸኝነት ተቀይሮ በሰዎች እንከበብ ነበር
16 093
አትመጪም አውቃለው
ያንን ሁሉ ታሪክ እንዴት በዚች ቃል
በምላስ በሳሳች በቻው ብቻ ያልቃል?
ደሞ ናፍቀሺኛል
አንቺ መጨከንሽን መሄድሽን መች ያምናል??
አትመጪም አውቃለው
እኔ ግን ሁልጊዜ ከበሩ ዳር ቆሜ እጠብክሻለው
አንቺኮ ይሄኔ ረስተሺኝ ይሆናል ከነመፈጠሬ
አጠራጥሮሽ ኖሯል የበር መቀርቀርያ የወንድነት ክብሬ
እኔ ግን አሁንም እጠብቅሻለው
ግን ምን ዋጋ አለው
እኔኑ ፍለጋ እንደማትመለሽ አይሆንም አውቃለው
ደሞ ናፍቀሺኛል....
ልቤ አንቺን ናፍቁአል
አንቺን ይፈልጋል
አንቺኑ ይመኛል
አንቺን አንቺን ብቻ አምጣልኝ ይለኛል
ነግሬሽ አውቃለው??...
ሰውነት አካሌ ከኔውጋ እየዋለ
ስብከነከንብኝ ስላንቺ እያሰበ በአንቺ እንደማለ??
ነግሬሽ አውቃለው??...
ልቤን ስጋርደው ለመርሳት ስሞክር
ላሳየሽ ስጣጣር የወንድነቴን ክብር
ይሄ ሞኙ ልቤ
ይሄ መጥፎ ልቤ በሩ እንደተዘጋ
ጭራሽም ብሶበት መርሳትም አቅቶት መቼ ተረጋጋ 🥺🥺
አሁን ላይ ብትመጪ ብትመለከቺኝ
ፍቅርሽ አቅሌን ሰብሮ ከራሴ እንዳጣላኝ
ትውስታ ትዝታሽ አቅም እንዳሳጣኝ
ታይልኝ ነበረ
ታዝኚልኝ ነበረ
የድሮ ፍቅራችን ድንገት ከልብሽ ውስጥ የቅንጣት ከቀረ
ታይልኝ ነበረ
ታዝኚልኝ ነበረ
መክሳቴ መጥቆሬ
መቁሰል መጫጫሬ
መነሳት መውደቄ
አንቺን መናፈቄ
ከበሩ ዳር ቆሜ አንቺን መጠበቄ
ድንገት ካሳዘነሽ ልብሸን ካራራ
እባክሽ አትቅሪ ተመለሽ አደራ
ምክንያቱም...
ልቤ አንቺን ናፍቁአል
አንቺን ይፈልጋል
አንቺኑ ይመኛል
አንቺን አንቺን ብቻ አምጣልኝ ይለኛል
ግን አንቺ ቀርተሻል
አትመጪም አውቃለው
ቢሆንም ሁልጊዜ ከበሩ ዳር ቆሜ እጠብቅሻለው
መቼ ትመጫለሽ የትጋ ልጠብቅሽ የቱጋ ደርሰሻል
ልቤ በሄድሽበት መንገድ አንቺኑ ፍለጋ ያማትርልሻል
እንደ ምፀአት ቀን
ጉአጉቶ እንደሚጠብቅ የጌታውን መምጫ
በረሃ የቆየ
እንደሚናፍቀው ቅንጣት ጥርኝ ውሃ ለጥሙ መጠጫ
በናፍቆትሽ ባህር ሰምጨልሻለው
መምጫሽን ባላውቅም በተውሺኝ ቅያስ ጥግ እጠብቅሻለው
ሊገባኝ ያልቻለው 🤔🤔.....
አብረን ያሳለፍነው ደስታችን ሳቃችን
ቃል የገባናቸው የተማማልናቸው በልብ ምታችን
ዛሬ ተሰርዞ
የፀብ ካርድ ተመዞ
አበቃ ማለት ነው የኔና ያንቺ ጉዞ???...
ቆይ ግን....
ያንን ሁሉ ታሪክ እንዴት በዚች ቃል
ለምላስ በሳሳች በቻው ብቻ ያልቃል???
ብቻ....
እንደማትመለሽ ልቤ ቢረሽም
ቃሌን አከብራለሁ እጠብቅሻለሁ ተስፋ አልቆርጥብሽም
አዎ እጠብቅሻለው
አትመጭም አውቃለው
ቢሆንም ሁልጊዜ ከበሩ ዳር ቆሜ እጠብቅሻለው
ግጥሙን በደምፅ ከፈለጋችሁ tiktok ላይ አለ ሊንክ ከስር ያለውን ንኩት
👇👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMSaf5PmM/
16 093
ብረት ካሰረው ታሳሪ ራሱን ያሰረ ታሳሪ ነፃነትን ማግኘት ይከብድበታል! ራስህን ስታስር መውጫው ክፍት ቢሆን እንኳ ላንተ እስራቱ ነው ሚታይህ።
16 093
ዋጋ የሰጠህ የሰው ልብ ዋጋ ቢስ እንድትሆንም ያደርግሃል ያኔ ቦታውን ካሳጣህ በላይ ቦታውን ያጣኸው አንተ ትጎዳለህ! ምንም እንደሆንክ ያህልም ይሰማኸል ተጠንቀቅ!!!
16 093
የፈራነውን እና የጠላነው ነገር የመሆን እድሉ እንደሰፋ ሁሉ ውስጣችን ማግኘት የሚሻውን እና ለማግኘት የሚጓጓለትን አለመፈለግ እና ጥላቻ ብናሳየው ውጤቱ ምን ይመስል ይሆን?!
16 093
የተሰጡን ከሰጠናቸው ጋር አለመመሳሰላቸው የተገቡን የትኞቹ እንደሆኑ ግራ ይገባናል! ያኔ ሒወት ላይ ቁማር እንጫወታለን ለአንዱ ልዩ ለ አንዱ አንዳይነት በመስጠት ዕጣ ማውጣት!!!
16 093
በንቀት ሳይሆን በብልሃት ዝምም በል!!!
ይሄ ሰው መናገር አይችልምዴ እስክትባሉ ድረስ ዝምታን ምረጡ።ከህሊና በላይየሆነ ሰላምን ከፈለክ ሁሉን በንግግር እፈታለሁ አትበል።አንዳንድ ጥያቄዎች ልክእንደ ወይን ናቸው፤ቆይተው ነው የሚመለሱት።መልሳቸውም ዝምታ ብቻ ነው።እኛ ዝም ስንል ፈጣሪ ስለኛ መናገር ይጀምራል።ለአንዳንድ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የሚሰጠው እኛ ሳንሆን ጊዜና የጊዜው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ሰው ከመከረው ጊዜ የመከረው ይበልጣልና፣ዝምታ የመለሰው እውነት ከብርሃን የበለጠ በጨለማ ይገለጣልና በንቀት ሳይሆን በብልሃት ዝምምም እንበል!!
እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን __ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው።
16 093
ቀን ላንተ እና ቀን ባንተ ላይ ሲሆን ትርጉሙ ይለያያል! ባንተ ሲሆን ታጋሽና ተስፈኛ ሁን! ላንተ ሲሆን ደግሞ ጥጋብህን ግራ ፤ድንበር የሳተም ማንነት አይኑርህ።
16 093
እስኪነገርህ አትጠብቅ…..
አንድ ጠበቃ የውሃ ጉድጓዱን ለመምህር ሸጠለት። ከሁለት ቀን በኋላ ጠበቃው ወደ መምህሩ መጥቶ እንዲህ አለው፡ ''ጌታዬ፣ ጉድጓዱን ሸጥኩልህ እንጂ በውስጡ ያለውን ውሃ አልሸጥኩልህም! ውሃውን መጠቀም ከፈለግክ ተጨማሪ መክፈል አለብህ።"
መምህሩ ፈገግ አለና እንዲህ ሲል መለሰ፡ ''አዎ፣ እኔም ወደ አንተ ልመጣ ነበር። ልልህ የነበረው ውሃህን ከእኔ ጉድጓድ ውስጥ እንድታወጣ ነው፣ አለበለዚያ ከነገ ጀምሮ ኪራይ መክፈል ትጀምራለህ።"
ይህን ሲሰማ ጠበቃው ተደናግጦ "ኦ! ዝም ብዬ እየቀለድኩ ነበር!' አለዉ።መምህሩ እየሳቀ "እንደ አንተ ያሉ ሰዎች እኮ ከእኛ ዘንድ ተምረው ነው ጠበቃ የሚሆኑት!'' አለው ይባላል።
በህይወታችን አንዳንድ ሰወችም እንደዚሁ ናቸው፡፡አይቶ እንዳላየ፣ሰምቶ እንዳልሰማ ሆናችሁ ስታልፏቸው አላዋቂ፣ሞኝ ያደርጓችሁና በክህደት አይናችሁን ጨፍኑ ላሙኛችሁ ይሏችኋል።
16 093
የሰረቀሽ መንገድ
ምነው ሀቁ ጠፋ
ለማ'ግኘት ለቆመ
ፍቅሩን ለተገፋ
መልስን
ማን ሰረቀው
ህልምሽ ከማን ዋለ
ለዘላለሜ ብሎ
እንዳልተማማለ?!
የት ነሽ!
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
16 093
ወንዶች ስለሴት የሚያውቁት ነገርን ለመፃፍ የተነሳው "EVERYTHING MEN KNOW ABOUT A WOMAN" የተሰኘው መፅሀፋ 120 ገፆቹ ባዶ ናቸው !
16 093
ልዕልት ኳጃር ትባላለች በሀገርዋ
በ persia የቁንጅና ምልክት ማሳያ ናት!
13 ወንዶች እሷ ስላልወደደቻቸው
ብቻ እራሳቸውን አጥፍተዋል በለው ቁንጅና😳😅
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
