ch
Feedback
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

前往频道在 Telegram

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ይህ ቻናል የተከፈተው በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ የሚሰጡ ትምህርቶች፣መልዕክቶች የሚሰራጭበት ቻናል ነው በዚህ ቻናል ማንኛውንም ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ቻናሉ በመጋበዝ ተጠቃሚ ያድርጉ የመጋበዣ ሊንክ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/sumuslim_jemaa

显示更多
1 173
订阅者
无数据24 小时
+87
+1330
吸引订阅者
七月 '26
七月 '26
+8
在0个频道中
六月 '26
+44
在4个频道中
Get PRO
五月 '26
+29
在0个频道中
Get PRO
四月 '26
+41
在0个频道中
Get PRO
三月 '26
+16
在2个频道中
Get PRO
二月 '26
+11
在0个频道中
Get PRO
一月 '26
+52
在1个频道中
Get PRO
十二月 '25
+40
在2个频道中
Get PRO
十一月 '25
+59
在0个频道中
Get PRO
十月 '25
+26
在2个频道中
Get PRO
九月 '25
+15
在2个频道中
Get PRO
八月 '25
+5
在0个频道中
Get PRO
七月 '25
+6
在0个频道中
Get PRO
六月 '25
+20
在0个频道中
Get PRO
五月 '25
+33
在3个频道中
Get PRO
四月 '25
+41
在0个频道中
Get PRO
三月 '25
+30
在2个频道中
Get PRO
二月 '25
+43
在3个频道中
Get PRO
一月 '25
+52
在1个频道中
Get PRO
十二月 '24
+52
在1个频道中
Get PRO
十一月 '24
+51
在3个频道中
Get PRO
十月 '24
+38
在4个频道中
Get PRO
九月 '24
+70
在1个频道中
Get PRO
八月 '24
+69
在3个频道中
Get PRO
七月 '24
+40
在1个频道中
Get PRO
六月 '24
+55
在2个频道中
Get PRO
五月 '24
+74
在4个频道中
Get PRO
四月 '24
+62
在6个频道中
Get PRO
三月 '24
+76
在2个频道中
Get PRO
二月 '24
+221
在4个频道中
Get PRO
一月 '24
+45
在1个频道中
Get PRO
十二月 '23
+164
在2个频道中
Get PRO
十一月 '23
+2
在9个频道中
Get PRO
十月 '23
+3
在0个频道中
Get PRO
九月 '23
+5
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+3
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+44
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+82
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+37
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+12
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+44
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+5
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+9
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+11
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+3
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+1
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+3
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+14
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+13
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+232
在0个频道中
日期
订阅者增长
提及
频道
04 七月+2
03 七月+2
02 七月+3
01 七月+1
频道帖子
ለማንኛውም የበኑ ኡመያ መስለም ከነብዩ ﷺ እና ከኸሊፋዎቻቸው ዘንድ የሚጠረጠር አልነበረም። ሂንድን በተመለከተም መስለሟን ነብዩ ﷺ ከተቀበሏት በኋላ እኛ በጥርጣሬ የምናይበት ምንም አይነት ቀዳዳ የለም። ለሐምዛ እኛ ከነብዩ ﷺ በላይ ተቆርቋሪዎች አይደለንም። ያለ አንድ መረጃ የሰዎችን ያውም የሶሐቦችን እስልምና ጥያቄ ውስጥ መክተት የባለ ^ጌዎች ስራ ነው። የሚገርመው ሐምዛን በማስ7ደል እና ጉበቱን በማኘክ ሂንድን የሚያብጠለጥሉ አካላት በቀጥታ ግድያውን የፈፀመውን ወሕሺይን ግን ሲዘምቱበት እና እስልምናውን ጥያቄ ውስጥ ሲያስገቡ አይታዩም። ስለዚህ ሂንድም በመስለሟ የተነሳ ከነብዩ ﷺ ምርጥ ሶሐብያት ሆናለች ማለት ነው። ስለሆነም ለሶሐቦች አክብሮት እንዲኖረን የተነገረን ትምህርት ሂንድንም ያካትታል። ሶሐቦችን በክፉ እንዳናነሳ የተሰጠን ማሳሰቢያም እንዲሁ ሂንድንም ይመለከታል። ደግሞም እፈሩ! አቡ ሉእሉአ ማለት ከነብዩ ﷺ በኋላ የኡማው ሁለተኛ ታላቅ ሰው የሆኑትን ኸሊፋው ዑመርን፣ ሱብሒ ሶላት እያሰገዱ በነበሩበት በመርዛማ ስለት ወግቶ የ7ደለ ነው። ይሄ ሰውዬ እሳት አምላኪ መጁሲ ሙሽሪክ ነው። ሺዐዎች ዘንድ ግን ትልቅ የአላህ ወሊይ ነው። ዑመርን መግደሉን ትልቅ ገድል በማድረግ የተንጣለለ መታሰቢያ ዶሪሕ ገንብተውለታል። ለዚያራም ይመላለሱበታል። መግቢያው ላይም አቡበክርን፣ ዑመርንና ዑሥማንን የሚራገም ፅሁፍ በደማቁ አስፍረዋል። እነዚህ የጥመት ቋቶች እና የነዚህ እርጉሞች ደጋፊዎቻቸው ነጋ ጠባ በኑ ኡመያን ሲያብጠለጥሉ ማየት የሚደንቅ ነው። እንጥፍጣፊ ሞራል ቢኖራቸው ኖሮ በዚህ ልክ ርክስ፣ ቁሽሽ ያሉ ፍጥረቶችና የነሱ ደጋፊ ጭፍራዎች ስለ በኑ ኡመያ የማውራት ሞራል አይኖራቸውም ነበር። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

2
እውን ሂንድ የሐምዛን ጉበት አኝካለችን? ~ ሂንድ ቢንቱ ዑትባህ የአቡ ሱፍያን ባለቤት፣ የሙዓዊየህ እናት ነች። ከመስለሟ በፊት የሐምዛን ጉበት አውጥታ አኝካለኝ በሚል ክስ ዛሬም ድረስ ትብጠለጠላለች። በሺዐዎች በተዘጋጀው አር-ሪሳላህ ፊልም ውስጥ ሂንድን እጅግ ጋጠ ወጥ አድርጎ የሚያሳይ በርከት ያለ ክፍል አለ። በርግጥ ይሄ ከሺዐ የማይጠበቅ አይደለም። ለአቡበክርና ለዑመር ያልተመለሱ ጠማሞች ለሂንድ ይመለሳሉ ተብሎ አይጠበቅም። የነብዩ ﷺ አጎት የሆኑት የአላህ አንበሳ ሐምዛ ብኑ ዐብዲል ሙጦሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ የኡሑድ ጦርነት ጊዜ በሐበሻዊው ወሕሺይ መገ - ደላቸው የሚታወቅ ነው። ከዚያም ሆዳቸው ተቀዶ አካላቸው ተቆራርጦ ነውረኛ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል። ታሪኩ እዚህ ድረስ ትክክለኛ መረጃ የመጣበት ነው። ከዚህ ውጭ ግን እንዲህ የሚል ዘገባ አለ። "ሂንድ ሆዱን ቀዳ ጉበቱን በማውጣት አኘከችው። ልትውጠው ግን አልቻለችም። የአላህ መልክተኛ ﷺ ሲያዩት 'ከእሱ በልታለት ይሆን?' ብለው ጠየቁ። 'አልበላችም' ሲሏቸው 'አላህ የሐምዛን አንድም ክፍል ወደ ጀሃነም እሳት እንዲገባ አይፈቅድም' አሉ።" [ሙስነድ አሕመድ፡ 4414] ይህንን ዘገባ መነሻ በማድረግ ሂንድን ዛሬም ድረስ ክፉኛ የሚያንቋሽሹ ሰዎች አሉ። ሺዐዎች እንኳ ከዚህም የከፋ ብዙ ነገር ስላላቸው ምንም ቢሉ አይደንቅም። የሚገርመው በነሱ ቅጥፈት ተመርዘው ዛሬም ሂንድን የሚኮንኑ ሰዎች ሁኔታ ነው። ይሄ አካሄድ ስሜትን በሸሪዐ ልጓም አለመቆጣጠር ነው። ሐምዛ ላይ የተፈፀመው ድርጊት እጅግ በጣም የሚያም መሆኑ ግልፅ ነው። ነገር ግን ለሐምዛ ያለን ቁጭትና መቆርቆር መነሻው ኢስላም ከሆነ ኢስላማዊ ህግጋትን ሰው እየመረጥን ልንጥስ አይገባም። በዚህ ክስ ሂንድን የሚያወግዝ አካል ቢያንስ ሁለት መሰረታዊ ነጥቦችን ጥሷል። #አንደኛው፦ ባልተጨበጠ ዘገባ ላይ ተመርኩዞ ነው ውግዘት ውስጥ የገባው። ታሪኩ የተላለፈበት ሰነድ ከ0ፋን፣ ከሐማድ፣ ከዐጧእ ብኑ ሳኢብ፣ ከሸዕቢይ፣ ከኢብኑ መስዑድ የሚል ነው። ደረጃው ለማስረጃ የሚበቃ ጥንካሬ የሌለው ደካማ ዘገባ ነው። እንዴት እንደሆነ እንመልከት፦ 1. ሸዕቢይ ከኢብኑ መስዑድ አልሰማም። አቡ ሓቲም፣ ዳረቁጥኒይ፣ ሓኪም እና ኢብኑ ሐጀር ይህንን አስረግጠው ተናግረዋል። [አልመራሲል፣ ኢብኑ አቢ ሓቲም ፡ ቁ. 591] [ጃሚዑ ተሕሲል ሊአሕካሚል መራሲል፣ አልዐላኢይ፡ 204] [መዕሪፈቱ ዑሉሚል ሐዲሥ፡ 111] [ተህዚቡ ተህዚብ: 7/419] 2. ዐጧእ ብኑ ሳኢብ ኢኽቲላጥ (የሒፍዝ መደባለቅ) የገጠመው ሰው ነው። ይህንን ኢብኑ መዒን፣ ቡኻሪ፣ ዒጅሊ፣ ኢብኑ ዐዲይ፣ ኢብኑ ቀጧን፣ ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑ ሐጀር ገልፀውታል። [አት-ታሪኹል ከቢር፡ 6/465] [አሥ-ሢቃት፣ ዒጅሊ፡ 332] [አልካሚል፡ 7/72] [ተቅሪቡ ተህዚብ፣ ኢብኑ ሐጀር፡ 1/391] [አድ-ዱዐፋኡል ከቢር፡ 3/398] [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 5/430] [ተህዚቡ ተህዚብ: 7/207] ይሄም የዘገባውን ዋጋ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሌላ ድክመት ነው። የሚከተሉት ሙሐዲሦች ደግሞ ታሪኩ ደካማ እንደሆነ በቀጥታ የገለፁ ናቸው፦ 1ኛ፦ ኢብኑ ከሢር [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 5/430] 2ኛ፦ አልሐይሠሚ 3ኛ፦ አልአልባኒይ [ፊቅሁ ሲራ፡ 279-280] ታሪኩን ሶሒሕ ወይም ሐሰን በማለት ዋጋ ለመስጠት በሞከሩት አሕመድ ሻኪርና አርነኡጥ ላይ ዘለግ ያለ አጥጋቢ ምላሽ የተሰጠበትን ትንታኔ መመልከት የፈለገ إزاحة الغمة في بيان ضعف قصة أكل هند من كبد حمزة የተሰኘውን ጥናት መመልከት ይችላል። #ሁለተኛው መሰረታዊ የዘገባው ችግር፦ ከሰነድ ባለፈ መልእክቱ ራሱ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑ ነው። ዘገባው ላይ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል የሚል አለበት:- “አላህ የሐምዛን አንድም ክፍል ወደ ጀሃነም እሳት እንዲገባ አይፈቅድም።” ይሄ ማለት ሂንድ የእሳት ነች ማለት ነው። ይሄ የተሳሳተ ነው። ሶሒሕ አይደለም እንጂ ሂንድ ድርጊቱን መፈፀሟ ቢረጋገጥ እንኳ ይሄ ተግባር ከመስለሟ በፊት የተፈፀመ ነው። መስለሟ በአስተማማኝ ሰነድ ተረጋግጧል። [ቡኻሪ፡ 3825] [ሙስሊም፡ 1714] በተለያዩ ሐዲሦች እንደተረጋገጠው ኢስላም የቀደመን ወንጀል ሁሉ ያብሳል። ይህ ከሆነ ድርጊቱን ለመፈጸሟ በቂ መረጃ የለም እንጂ ቢኖርስ ከመስለሟ በፊት በነበረ ጉዳይ እንዴት የእሳት ትሆናለች? ይሄ ከመሰረታዊ የኢስላም አስተምህሮት ጋር የሚቃረን ነው። በርካታ የምንወዳቸው ሶሐቦችኮ ከመስለማቸው በፊት ሺርክን ጨምሮ ብዙ ከባባድ ወንጀሎችን ፈፅመዋል። ልክ እነዚያ ከመስለማቸው በፊት በተፈፀመ ወንጀል እንደማይወቀሱት ሂንድም ከመስለሟ በፊት በተፈፀመ ድርጊት አትወቀስም። ልክ የሐምዛ ገዳይ የሆነውን ወሕሺይን ከመስለሙ በፊት በፈፀመው ድርጊት ከሰለመ በኋላ እንደማንወቅሰው ማለት ነው። ጌታችን እንዲህ ማለቱ ይታወስ፦ {قُلۡ یَـٰعِبَادِیَ ٱلَّذِینَ أَسۡرَفُوا۟ عَلَىٰۤ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُوا۟ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ یَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِیعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِیمُ} "በላቸው 'እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡" [አዝ-ዙመር: 53] ይህንን ከመሰሉ ሰፋፊ የአላህ የእዝነት አዋጆች ውስጥ ሂንድን ለይተን ልናወጣ ነውን? ለራሳችን ልንፈራ ይገባል። በሌላም ቦታ ጌታችን አላህ ሺርክ የሚፈፅሙ፣ ነፍስ የሚያጠፉ፣ ዝሙት የሚፈፅሙ ሰዎች አሳማሚ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በዛተበት ላይ ተውበት የሚያደርጉትን ግን እንዲህ ሲል እንደሚምራቸው ገልጿል:- {إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ عَمَلࣰا صَـٰلِحࣰا فَأُو۟لَـٰۤىِٕكَ یُبَدِّلُ ٱللَّهُ سَیِّـَٔاتِهِمۡ حَسَنَـٰتࣲۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمࣰا} "ተፀፅቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው።" [አል-ፉርቃን፡ 70] ታዲያ ሂንድን ከሰለመችም በኋላ ከነዚህ የአላህ የተስፋ ቃል ውጭ ልናደርጋት ይቻላል ወይ? አደብ ሊኖረን ይገባል። ሁሉንም ሶሐቦች አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸው። ከመስለሟ በፊት በተፈጠረ ክስተት ማብጠልጠል ለምን አስፈለገ? ምክንያቱ ወዲህ ነው። እነዚህ ባ -ለጌዎች የአቡ ሱፍያንንም፣ የሂንድንም መስለም አይቀበሉም። ሺዐዎች እና እነሱን በጥመት የተከተሉ እንደ ሰይድ ቁጥብ ያሉ የኢኽዋን አፈንጋጮች ዘንድ የበኑ ኡመያ ቤተሰቦች ኢስላምንና የነብዩን ﷺ ቤተሰቦች ለመበቀል ነው የሰለሙ የመሰሉት እንጂ ኢማን ወደ ልባቸው አልገባም። በዚህ ደረጃ የነብዩን ﷺ ሶሐቦች ከእስልምና እያስወጡ እያከ^ ፈሩ ለዘብተኛና ሚዛናዊ መስለው ሲተውኑ ስቅም አይላቸውም።
101
3
🎤ለተማሪዎች እና ለትውልድ የሚሆን የዑለሞች የማንቂያ ደውል ምክር 👉እነዚህ በአገራችን ውስጥ በአዲስ አበባ የሺዓን አስተምህሮት እያስፋፉ የሚገኙ አንጃዎች ናቸው ።ወንድሞች እና እህቶች ልንጠነቀቅ
🎤ለተማሪዎች እና ለትውልድ የሚሆን የዑለሞች የማንቂያ ደውል ምክር 👉እነዚህ በአገራችን ውስጥ በአዲስ አበባ የሺዓን አስተምህሮት እያስፋፉ የሚገኙ አንጃዎች ናቸው ።ወንድሞች እና እህቶች ልንጠነቀቅ ይገባል ! ​ታላላቅ የሱና ዑለማዎች ወጣቱ ትውልድ እራሱንና እምነቱን ከዚህ አደጋ እንዲጠብቅ የሚከተሉትን ወርቃማ ምክሮች ይለግሳሉ፦ ​ሀ. ትክክለኛውን የዓቂዳ (የእምነት) እውቀት መቅሰም ​የሺዓን ተንኮል ለመከላከል ትልቁ መሣሪያ ተውሂድንና የሰለፎችን (የቀደምት ደጎች) ዓቂዳ በሚገባ መማር ነው። ጨለማን ለማጥፋት ብርሃን እንደሚያስፈልገው ሁሉ፣ ስሕተትን ለማስወገድም ትክክለኛውን የሱና እውቀት መያዝ ግድ ይላል። ​ለ. የነብዩን ﷺ ባልደረቦች (ሶሓባዎችን) ማክበርና ለነሱም መከላከል ​የሺዓዎች ትልቁ ተንኮል የነብዩን ﷺ ሶሓባዎች (በተለይም አቡበክርን፣ ዑመርንና ዓኢሻን - ረዲየላሁ ዐንሁም) መሳደብና ማግለል ነው። ዑለማዎች እንደሚሉት፡ ​"ሶሓባዎችን መተቸት ማለት ዲኑን ለማፍረስ መሞከር ማለት ነው፤ ምክንያቱም ዲኑ ለእኛ የደረሰን በእነሱ በኩል ነውና።" ስለዚህ የሶሓባዎችን ታሪክና ደረጃ በሚገባ መማርና ማስተማር ያስፈልጋል። ​ሐ. እውቀትን ከታመኑ የሱና ዑለማዎች ብቻ መውሰድ ​በየማህበራዊ ሚዲያው (ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩብ) ላይ የሚለቀቁ ማራኪ የሚመስሉ ግን መርዛማ የሆኑ ስብከቶችን ከመስማት መቆጠብ። ነብዩ ﷺ እና ሰለፎች እንዳስተማሩት ዲንን ከማን እንደምንቀበል ማየት አለብን። ካልታወቁና ጥርጣሬ ካለባቸው አካላት እውቀት መቅሰም የተከለከለ ነው። ​መ. በቡድንና በልዩ ልዩ ስሞች ከመከፋፈል መራቅ ​ አላህ በቁርዓን ላይ እንዳዘዘው በአላህ ገመድ ስር መሰብሰብና እርስ በእርስ መተጋገዝ ይገባል።
230
4
🎓 بِسْمِ اللهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ 🎓 سَمَرَ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ 축 18ኛው ዙር ምረቃ — እንኳን ደስ አላቹህ! 🌙✨ አልሀምዱሊላህ! የሰመራ ዩኒቨርስቲ 18ኛ ዙር ምረቃ በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷል ። ዓመታትን በትጋት፣ በሥነ ምግባር፣ እና በእምነት ጉዞዋቸውን ያጠናቀቁ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን — مَبْرُوك، أَلْف مَبْرُوك!              🏆  እንኳን ደስ አላቹህ — የዋንጫ ተሸላሚዎች 🥇 አጠቃላይ Overall Trophy Winner ወንድማችን ዶ/ር መሀመድ ሀሰን ገመዳ 📚 ቬተርነሪ ሜድሲን | CGPA: 3.96 ከሙሉው ተመራቂ ተማሪዎች  አንደኛ በመሆን አጠናቋል!     ماشاءالله، بارك الله فيك             🥇 Overall Women's Trophy Winner እህታችን ሀስና ኢብራሒም አብደላ 📚 ፐብሊክ ሄልዝ ኦፊሰር | CGPA: 3.82 ከሁሉም ሴት ተመራቂዎች ተወዳድራ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች ! ماشاءالله، بارك الله فيها قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ: "مَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا، سَهَّلَ اللهُ لَهُ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّةِ" "ዕውቀትን ፍለጋ የተጓዙ ሰው ሁሉ — አላህ ወደ ጀነት መንገዳቸውን ያቀልላቸዋል።" ወደ ፊትም በዲናቹህ እንድትበረቱ ፣ማህበረሰባችሁን በሀቅ እንድታገለግሉ፣ ሁሌም የአላህን ቁርአንና የነብዩን ሐዲስ ከሁሉም በፊት ተቀዳሚ እንድታደርጉ የሰመራ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ምኞቱን ያሳውቃል። وَفَّقَكُمُ اللهُ جَمِيعًا                            አላህ ሁላችንንም ይጠብቀን! 🤲 — ሰመራ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ (SUMSG)
302
5
💎 { ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا ت
💎 { ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ }      💎   ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ  💎 🤲 اللهم صلي على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم في العالمين إنك حميد مجيد... 🕌 ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች     🚿   ገላን መታጠብ     🖇 ጥፍርን መቁረጥ     👕 ጥሩ ልብስ መልበስ     ⚱️ ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)      🥢  መፋቂያ መጠቀም    🕰  በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ    🕌  ወደ መስጂድ ሲሔዱ በተቻለ መጠን           በእግር መጓዝ    🔸ኢማሙ ሚንበር ላይ እስኪወጣ ባለው ሰዐት የሱና ሰላትን መስገድ (አልነፍል አልሙጥለቅ)    👉  በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት    📖   ሱረቱል ከህፍን መቅራት 🦻ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ    🤲 ዱዓ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት መጠባበቅ ⚡️ሌላ ሰው ቢያወራም ዝም በል አለማለት ⚡️በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ :: ===================
321
6
በያመቱ ሙሐረም አስርን እየጠበቁ አካላቸውን በስለት እየተለተሉ፣ ጥቁር ለብሰው "ሑሴን" እያሉ ሙሾ የሚያወርዱት ሺዐዎች የታላቁን ኸሊፋ፣ የዑመር ብኑል ኸጧብ 7ዳይ ለሆነው ለአቡ ሉእሉአ የጀግና መታ
በያመቱ ሙሐረም አስርን እየጠበቁ አካላቸውን በስለት እየተለተሉ፣ ጥቁር ለብሰው "ሑሴን" እያሉ ሙሾ የሚያወርዱት ሺዐዎች የታላቁን ኸሊፋ፣ የዑመር ብኑል ኸጧብ 7ዳይ ለሆነው ለአቡ ሉእሉአ የጀግና መታሰቢያ የገነቡ ናቸው። "አቡ ሉእሉአ አልመጁሲ ማለት ዑመር ብኑል ኸጧብን የሱብሕ ሶላት እያሰገዱ እያሉ በመርዛማ ሰይፍ የ7ደላቸው ሙሽሪክ ነው። በእለቱ ከዑመር በተጨማሪ ወደ ሰባት ሶሐቦችን የ7ደለ ሲሆን ሌሎች በርካቶችንም አቁስሏል። የተያያዘው ምስል ኢራን ውስጥ የሚገኝ የአቡ ሉእሉአ ዶሪሕ መግቢያ በር ነው። ቀብሩ ላይ ትልቅ ቤት ገንብተው ይዘይሩታል፣ ይመላለሱበታል። አቡ ሉእሉአ አልመጁሲ የመጁሳ (እሳት አምልኮ) ሃይማኖት ተከታይ የነበረ ቢሆንም ኢራኖች ዘንድ ትልቅ የአላህ ወሊይ ነው። ለዑመር ያላቸው ጥላቻ ነው በዚህ ርቀት የወሰዳቸው። ዑመርን በየ ሶላታቸው የሚራገሙ፣ ጣዖት ነው የሚሉ፣ እሱ ብቻ ሳይሆን ለሱ "ረዲየላሁ ዐንሁ" እያለ ዱዓ የሚያደርግም ሙሽሪክ እንጂ ሙስሊም አይደለም የሚሉ እነዚህ መጁሳዎች ለመጁሲው ግን ማስታወሻ ዶሪሕ አቁመውለታል። ታላቁን ኸሊፋ ዑመርን አውግዞ፣ ለሙሽሪኩ አቡ ሉእሉአ አልመጁሲ ሀውልት የሚያቆም የሺዐ እምነት በሑሰይን ሞት ዓመት እየጠበቀ የሚያላዝነው ለሑሰይን ተቆርቆሮ አይደለም። በሱ ተንጠላጥሎ ሌሎችን ለመንካት ነው። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
228
7
የ2018 ,18 ዙር ተመራቂዎች በከፍተኛ መዕረግ የተመረቁ ሙስሊም ተማሪዎች 🎓Congrats ... ሀስና ኢብራሒም ከሰመራ ዩኒቨርስቲ የዋንጫ ተሸላሚ ! ! !    እየሞከሩ ያሉት እርሷን እና መሰሎቿን በስኬት ላይ ላለማየት ቢሆንም ችግሩን ሁሉ ተቋቁመው ዋንጫም እየተሸለሙ ነው። ጥረታቸው ኒቃብን አስታኳ ሙስሊም ተማሪዎችን ከሁለንተናዊ ስኬት ማደናቀፍ ቢሆንም ሀስና እና መሰሎቿ ግን ጩኸታቸውን ሳይሰሙ መድረስ ካለባቸው ደርሰው እያሳዩ ነው።   ሀስና ኢብራሒም በPublic Health Department የከፍተኛ ማዕረግ ተሸላሚ ከመሆን ባሻገር ከHealth and Medicine College የሜዳልያ ተሸላሚ እንዲሁም ከሁሉም ተመራቂ ሴት ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።   እንደለበሰች ተምራለች   እንደለበሰች ትማራለች   እንደለበሰች ትመረቃለች   እንደለበሰች ከማዕረግ ከዋንጫ ትደርሳለች 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
981
8
​📢 ደዉራህ በሎጊያ ከተማ (አንሷር መስጂድ) ​📚 የሪሳላዋ ስም: الطريق إلى السلفية ("አጥ-ጦሪቁ ኢለ ሰለፊያህ") ​📖 የሪሳላዋን ፒዲኤፍ (PDF) ለማግኘት: 👉 https://t.me/durusuabihizam/3771 ​📅 የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት: አርብ እና ቅዳሜ ከመግሪብ ሶላት በኋላ ​📍 የደርሱ ቦታ: ሎጊያ — አንሷር መስጂድ ​📱 ደርሱ የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል: 👉 https://t.me/durusuabihizam
267
9
እንኳን ደስ አላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን! 🎊 📍 Samara University Muslim Students Jemea ዛሬ የምርቃት ቀናችሁ በመሆኑ ከልብ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ስኬት የእናንተን ትጋት፣ የቤተሰቦቻችሁ ድጋፍ እና የአላህ ረድኤት ውጤት ነው። 🤲 አላህ ለዚህ ትልቅ ቀን በሠላም እንዳደረሳችሁ እንደረዳችሁ፣ ወደፊትም በሕይወታችሁ ሁሉ ላይ ስኬት፣ በረከት እና መልካም መንገድ ይስጣችሁ። 🌙 ዲናችሁን የሚጠቅም እውቀት እንዲሰጣችሁ፣ ራሳችሁንና ማህበረሰባችሁን የሚጠቅም ሰዎች እንድትሆኑ አላህ ይወፍቃችሁ። ✔️እንኳን አደረሳችሁ🌿 ✔️Unkaq ruffa teenih🌿 ✔️BAGA NAGAYAAN GEESSAN 🌿 ✔️
394
10
#exit_exam ውጤት ማያ ዌብሳይቱ መስራት ጀምሯል ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ሁልጊዜም አንደኛ🏆 https://result.ethernet.edu.et/usernamepage
383
11
​✨ አዲስ የደርስ ማስታወቂያ በውርስ ሕግጋት (ፈራኢድ) ዘርፍ! ✨ ​📚 ኪታብ፦ الكتاب الثالث: "منظومة القلائد البرهانية" (መንዙመቱል ቀላኢዲል ቡርሐኒያህ) ​🎙 የደርሱ አቅራቢ፦ አቡ ሒዛም አብዱረህማን ሰዒድ ​📅 የደርሱ ቀናት፦ ዘወትር ከእሁድ እስከ ማክሰኞ ⏰ ሰዓት፦ ከመግሪብ ሶላት በኋላ ​📍 የደርሱ ቦታ፦ አፋር — ሎጊያ ከተማ — በተቅዋ መስጂድ ​📥 የኪታቡን ፒዲኤፍ (PDF) ለማግኘት፦ 👉 https://t.me/durusuabihizam/3715 ​🔗 ደርሱን በመመዝገብ መከታተልና የሙከራ ፈተናዎችን ለመውሰድ በዚህ ቅፅ ይመዝገቡ፦ 👉 https://forms.gle/QF8JthYQU9R1384X7 ​🤖 የምዝገባ ሂደቱ ካስቸገራችሁ በውስጥ መስመር ይጻፉልን፦ 👉 @forwebsiteguidancebot ​📡 ደርሱ በቀጥታ የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል፦ 👉 https://t.me/durusuabihizam ​ለብዙ ወንድሞችና እህቶች ተደራሽ እናድርገዉ። ባረከሏሁ ፊኩም!
324
12
እንኳን ደስ አላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን! 🎊 📍 Samara University Muslim Students Jemea የምርቃት ቀናችሁ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ቀርተውታል በመሆኑ ከልብ እንኳን ደስ አላችሁ
እንኳን ደስ አላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን! 🎊 📍 Samara University Muslim Students Jemea የምርቃት ቀናችሁ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ቀርተውታል በመሆኑ ከልብ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ስኬት የእናንተን ትጋት፣ የቤተሰቦቻችሁ ድጋፍ እና የአላህ ረድኤት ውጤት ነው። 🤲 አላህ ለዚህ ትልቅ ቀን በሠላም እንደረዳችሁ፣ ወደፊትም በሕይወታችሁ ሁሉ ላይ ስኬት፣ በረከት እና መልካም መንገድ ይስጣችሁ። 🌙 ዲናችሁን የሚጠቅም እውቀት እንዲሰጣችሁ፣ ራሳችሁንና ማህበረሰባችሁን የሚጠቅም ሰዎች እንድትሆኑ አላህ ይወፍቃችሁ። ✔️እንኳን አደረሳችሁ🌿 ✔️Unkaq ruffa teenih🌿 ✔️BAGA NAGAYAAN GEESSAN 🌿 ✔️
388
13
✍      ስለ ዓሹራ ጥቅል መረጃዎች!! 💫የዓሹራ ቀን ማለት; አላህ ካተለቃቸውና ዕርም ካደረጋቸው ከአራቱ ወራቶች ውስጥ አንዱ በሆነው በሸህሩል ሙሐረም ውስጥ የሚገኝ ዐስረኛው ቀን ነው። 💫ይህ ቀን; ሙስሊሞች የሚደሰቱበትና ደስታቸውን ለጌታቸው በመጾም የሚያሳልፉበት የሆነ ትልቅ ቀን ነው። 💫የዓሹራ ቀን ማለት; አላህ ነብዩላህ ሙሳ እና ተከታዮቹ ነፃ ያወጣበትና ፊርዓውንና ተከታዮቹን ያጠፋበት የሆነው ቀን ነው። በሓዲስ እንደ መጣው፦ «هذا يوم عظيم أنجى الله فيه موسى وقومه وأغرق فرعون وقومه»  «ይህ ቀን አላህ ሙሳንና ህዝቦቹን ነፃ ያወጣበት, ፊርዓውንና ህዝቦቹን ያሰመጠበት የሆነ ትልቅ ቀን ነው።» 💫የዓሹራ ጾም በጃሂሊያ ጊዜ ይጾም ነበር፤ ረመዷን ከመደንገጉ በፊትም በግዴታነት ይጾም ነበር፤ ረመዷን ከተደነገገ በኋላም በተወዳጅነት ይጾማል። በሓዲስ እንደ መጣው፦ « أن قريشا كانت تصوم عاشوراء في الجاهلية ثم أمر رسول الله صلى الله عليه وسلم بصيامه حتى فرض رمضان فقال رسول الله صلى الله عليه وسلم :  من شاء فليصمه ومن شاء فليفطره»   «ቁረይሾች በጃሂሊያ ጊዜ ሳሉ ዓሹራን ይጾሙ ነበር። ከዝያም ረመዷን እስከ ሚደነገግ ድረስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲጾም አዘዙ። ረመዷን ከተደነገገ በኋላ የፈለገ ይጹመው የፈለገ ይብላበት አሉ።» 💫ዓሹራን የሚጾምበት ምክንያት……    አላህ ለሙሳና ለህዝቦቹ በዋለው ውለታና ፊርዓውንና ህዝቦቹ ለቀጣበት ቅጣት ሙስሊሞች ደስታቸውን ለመግለፅ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ለአይሁዶች  እንዳሏቸው፦ «فنحن أحق وأولى بموسى منكم فصامه وأمر بصيامه» «እኛ ከእናንተ በላይ ለሙሳ የተገባን (የቀረብን) ሰዎች ነን። ብለው ጾሙት ሌሎችም እንዲጾሙት አዘዙ።» 💫የዓሹራ ቀን መጾም ያለፈውን ዓመት (የአንድ ዓመት) ወንጀል ያስምራል። የአላህ መልዕክተኛ እንዳሉት፦ «صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ» «የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንዲያስምርልኝ አላህ ዘንድ እከጅላለሁ (ታሳቢ አደርጋለሁ)።» 💫የዓሹራ ጾም ከረመዷን በኋላ በላጩ ጾም በሚለው ይገባል። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ስላሉ፦ «أَفْضَلُ الصِّيامِ، بَعْدَ رَمَضانَ، شَهْرُ اللهِ المُحَرَّمُ» «ከረመዷን በኋላ በላጩ ጾም ማለት የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ጾም ነው።» 💫የዓሹራ ጾም ማለት የአላህ መልዕክተኛ በጉጉት የሚጠባበቁትና የሚከታተሉት ጾም ነበር። «ما رأيت النبي صلى الله عليه وسلم يتحرى صيام فضله على غيره إلا هذا اليوم يوم عاشوراء وهذا الشهر يعني شهر رمضان» «የአላህ መልዕክተኛﷺ ከሌሎች በተለየ መልኩ የጾሙን ቱሩፋቱን ፈልገውና አስበልጠው እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር የሚጠባበቁት ጾም አላየሁም።» 💫የዓሹራ ጾም ካለው አሳሳቢነትና ደረጃ አንፃር ቀኑ የዓሹራ ቀን መሆኑን ሳያውቅ የበላ ሰው ካለ ራሱ የአላህ መልዕክተኛ የተቀረው ቀኑን እንዲጾም ያዙት ነበር። ከባልደረቦቻቸው ለአንዱ እንዲህ ብሎ እንዲጣራ ያዙታል፦ «أن من كان أكل فليصم بقية يومه ومن لم يكن أكل فليصم فإن اليوم يوم عاشوراء» «የበላ ሰው ካለ የተቀረው ቀኑን ይጹም። ያልበላ ሰው ካለም ይጹም። ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ የዓሹራ ቀን ነው።» 💫የዓሹራ ጾም ማለት ከሙሐረም ዐስረኛው ቀን ሲሆን በአላህ መልዕክተኛ ትዕዛዝ ወይም ምኞት መሰረት የሁዳዎችን ለመቃረን ተብሎ ዘጠነኛውና ዐስረኛው ቀን ይጾማል። 👉በትዕዛዛቸው ሲባል፦    በየትኛውም ሁኔታ አህለል ኪታቦችን ተቃርነን እንድንገኝ ያዙን ስለ ነበር። 👉በምኞታቸው መሰረት ሲባል፦ ከሕይወታቸው የመጨረሻ የሆነው የዓሹራ ጾም ከጾሙ በኋላ ለቀጣይ ዓመት ግን አይሁዶችን ለመቃረን «ዘጠነኛውም ቀን ጨምረን እንጾማለን» ብለው ነበር። የአላህ ውሳኔ ሆኖ ሳይደርሱ ሞቱ። በዚህም መሰረት፦     የዘንድሮው የዓሹራ ቀን የሚሆነው በአላህ ፍቃድ የፊታችን ሐሙስ ነው። ስለሆነም፦ 👇 👉 እሮብ እና 👉ሐሙስ የምንጾም ይሆናል!! ⛔ጥብቅ ማሳሰቢያ!! «ዓሹራን ከበስተ ፊቱ አንድ ቀን ወይም ከበስተ ኋላው አንድ ቀን ጹሙ» የሚለው ሐዲስ ዑለሞቻችን እንዳስቀመጡት ሐዲሱ ደዒፍ (ከነብዩ ሙሐመድ ያልተረጋገጠ) ነው። በመሆኑም "ዐስረኛውና ዐስራ አንደኛው እጾማለሁ" በሚል የእሮብ ጾም ማስመለጥ የለብንም። ኢንሻ አላህ    👉እሮብ እና     👉ሐሙስ የዓሹራ ጾማችን እንጾማለን!! 📲መልዕክቱ ለሁሉም ሙስሊሞች ይዳረስ ዘንድ ሼር አድርጉት! منقول
441
14
ጥብቅ የሳይበር ደህንነት ማስጠንቀቂያ‼ ========================= (ቴሌግራም ላይ የተሰማራው አደገኛው Botnet እና የብልግና ሊንኮች!) || 🎤ሰሞኑን በቴሌግራም መድረክ ላይ እጅግ አደገኛ እና የተራቀቀ የአካውንት ጠለፋ (Account Takeover) ዘመቻ በስፋት እየተካሄደ ይገኛል። ይህ ጥቃት እንዴት እንደሚሰራ እና እያንዳንዳችንን እንዴት አደጋ ላይ እየጣለን እንደሆነ እውነታውን ላካፍላችሁ። 1. ጥቃቱ እንዴት ይሰራል? 👉አጥቂዎቹ (Hackers) የሚጠቀሙት "Phishing Attack" እና አውቶማቲክ የሆኑ የቴሌግራም Botnets በማጣመር ነው። ስልቱ እንዲህ ነው፦   👉ማጥመጃው (The Bait)፡ የሰውን ልጅ የስነ-ልቦና ድክመት (Social Engineering) ለመጠቀም ሲሉ፣ በጣም ፀያፍ የሆኑ (የብልግና) ምስሎችን ወይም ቪዲዮዎችን ይልካሉ። ከስሩም "ሙሉውን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ" የሚል ማባበያ (Malicious Link) ያስቀምጣሉ።   👉 የታመነ ምንጭ (Trusted Sender)፡ ይህ ሊንክ የሚመጣው ከማታውቁት ሰው ብቻ አይደለም! አካውንቱ በጠላፊዎች (Hackers) ቁጥጥር ስር ከዋለ የቅርብ ጓደኛችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ፣ ወይም አብሮ አደጋችሁ ስም ሊመጣ ይችላል። 2.ሊንኩን ስትነኩት ምን ይፈጠራል? 👉ሊንኩን ክሊክ ባደረጋችሁበት ቅጽበት In a fraction of a second ሁለት ነገሮች ይፈጠራሉ፦ 1. የቴሌግራም አካውንታችሁን የመቆጣጠር መብት (Access Token/Session Hijacking) ለአጥቂዎቹ አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ። 2.  በስተጀርባ የተጻፈው (Automated Script/Bot) ወዲያውኑ የእናንተን አካውንት በመጠቀም Contacts ላይ ለሚገኙ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች እና አባል ለሆናችሁባቸው ግሩፖች በሙሉ ያንኑ  የብልግና ምስል እና ቫይረስ በእናንተ ስም ያሰራጫል። አንዴ ከተጠለፈ አካውንታችሁን መልሶ ለማግኘት (Account Recovery) እጅግ ፈታኝ ይሆናል። 3.ከሳይበር አደጋው ባሻገር፣ ይህ ነገር እጅግ ከባድ የሞራል እና የኃይማኖት ቀውስ እያስከተለ ነው። አንዳንዶች በስሜት (Curiosity) አሊያም በድንቁርና ሊንኩን ይከፍቱና፤ ለራሳቸውም ሐራም እያዩ፣ በራሳቸው አካውንት ምክንያት ደግሞ ያንኑ የብልግና ምስል ለብዙ መቶ ንጹሃን ሰዎች (ለቤተሰብ፣ ለኡስታዞች፣ ለወንድም እህቶች) ልከው በቅጽበት ሰውየውንም ሐራም እንዲያይ ያስገድዱታል። በዲናችን አስተምህሮ፡- "ወንጀልን (ፋሒሻን) ማሰራጨት እና ሰዎችን ወደ ሐራም መጋበዝ ከባድ ቅጣት አለው!" ዛሬ በእናንተ ድክመትና ስግብግብነት የላካችሁት ሊንክ የብዙ ወጣቶችን አዕምሮ ሊበክል፣ ስነ-ልቦና ሊጎዳ እና ትውልድ ሊያበላሽ ይችላል። መፍትሄወ፦ 1. አትንኩ! ከማንም ይምጣ ከማን (ከጓደኛም፣ ከዘመድም፣ ከባለቤታችሁም)፣ ፀያፍ ምስል ወይም የሚያጠራጥር ሊንክ (Link) ከተላከላችሁ በፍጹም አትንኩት ወዲያውኑ delete አድርጉት። 2. Two-Step Verification አብሩ: የቴሌግራም ሴኩሪቲያችሁን ለማጠናከር፣ Setting > Privacy and Security > Two-Step Verification ውስጥ በመግባት Password አድርጉበት! ይህ አካውንታችሁ በቀላሉ እንዳይጠለፍ ትልቅ ግድግዳ (Layer of security) ይፈጥራል። 3. ያላወቃችሁትን Session አጥፉ: ወደ Setting > Devices ገብታችሁ እናንተ ከምትጠቀሙበት ስልክ ውጪ የሚታይ ሌላ የገባ (Active) አካውንት ካለ "Terminate all other sessions" በማለት ወዲያውኑ አጥፉት። ✏️የሳይበር ደህንነታችንን መጠበቅ ዲናችንንም፣ ክብራችንንም၊ ማህበራዊ ግንኙነታችንንም መጠበቅ ነው። የብዙዎች ህይወት፣ ትዳር እና ክብር በዚህ አደገኛ ጥቃት ምክንያት እየፈረሰ ነው። እባካችሁ ንቁ! ለራሳችሁም ሆነ ለሌሎች ጥንቃቄ አድርጉ! (ይህን ማስጠንቀቂያ Share በማድረግ ወዳጅ ዘመድዎን ከዚህ አደገኛ የሳይበር እና የሞራል ወጥመድ ይታደጉ!)
535
15
💎 { ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا ت
💎 { ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ }      💎   ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ  💎 🕌የጁምዓ ግብዣ -------------- 🤲 اللهم صلي على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم في العالمين إنك حميد مجيد... 🕌 ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች     🚿   ገላን መታጠብ     🖇 ጥፍርን መቁረጥ     👕 ጥሩ ልብስ መልበስ     ⚱️ ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)      🥢  መፋቂያ መጠቀም    🕰  በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ    🕌  ወደ መስጂድ ሲሔዱ በተቻለ መጠን           በእግር መጓዝ    🔸ኢማሙ ሚንበር ላይ እስኪወጣ ባለው ሰዐት የሱና ሰላትን መስገድ (አልነፍል አልሙጥለቅ)    👉  በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት    📖   ሱረቱል ከህፍን መቅራት 🦻ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ    🤲 ዱዓ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት መጠባበቅ ⚡️ሌላ ሰው ቢያወራም ዝም በል አለማለት ⚡️በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ :: ===================
479
16
አድስ ምርጥ ነሲሀ በኡስታዝ አቡ ሒዛም ሀፊዘሁሏህ t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
486
17
አድስ ሙሐደራ ደሴ ሸዋበር መስጅድ 💉ስለ ሽርክና ተያያዥ ርዕሶች ምረጥ ምክር 🎙በኡስታዝ አቡ ሒዛም (ሀፊዘሁሏህ) t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
743
18
✅ወደ አላህ እንመለስ! ✅ወደ ራሳችን እንመለስ! 📚أَلَمۡ يَأۡنِ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن تَخۡشَعَ قُلُوبُهُمۡ لِذِكۡرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلۡحَقِّ، 🎙Dr. Hussein Ali Al_Kelaly የቴሌግራም ቻናል፦ ¤t.me/husseinali210 ¤t.me/husseinali210
547
19
+1
✅ወደ አላህ እንመለስ! ✅ወደ ራሳችን እንመለስ! 📚أَلَمۡ يَأۡنِ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن تَخۡشَعَ قُلُوبُهُمۡ لِذِكۡرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلۡحَقِّ، 🎙Dr. Hussein Ali Al_Kelaly የቴሌግራም ቻናል፦ ¤t.me/husseinali210 ¤t.me/husseinali210
1
20
በነገው ዕለት የማጠቃለያ ፈተና(Final Exam) ለምትወስዱ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ:- ከሁሉ በፊት ብዙ ነገር አልፋችሁ ለዚህ ላበቃችሁ አሏህ ምስጋና በማቅረብ  መተማመናችሁን በሱ ላይ አድርጉ። በፈተና ሰዓት ፈፅሞ መጨናነቅ እንዳይኖር። ፈተና ክፍል ገብታችሁ "አላነበብኩም እኮ!" የሚል እሳቤ ውስጥ እንዳትገቡ። ውድ ተማሪዎች የምትችሉትን ጥረት አድርጉ፣ ከዚያም በአላህ ተወከሉ። በቀደር እመኑ፤ የሚደርሳችሁ ነገር ሊያልፋችሁ አይችልም፣ ያላገኛችሁትም ነገር ሊደርሳችሁ አይችልም። «وَاعْلَمْ أَنَّ مَا أَصَابَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُخْطِئَكَ، وَمَا أَخْطَأَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُصِيبَكَ» "የደረሰብህ ነገር ሊያልፍህ አይችልም፤ ያላገኘህም ነገር ሊደርስብህ አይችልም።" (ቲርሚዚ) Just ፈተናውን እንዴት ልስራ የሚለው ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ። በተዓውዝ እና በቢስሚላህ ጀምሩት። ተወኩላችሁን በአላህ ላይ አድርጉ። then በአላህ ፈቃድ የሚጠቅማችሁ ውጤት ይመጣል። ለሌሎችም መልዕክቱን አድርሱ። መልካም ፈተና ••• መልካም ውጤት ••• ጥሩና የተገባችሁን  ዲፓርትመንት አሏህ ይወፍቃችሁ!!!! አላህ መልካሙን ይግጠማችሁ፤ የሚያስደስታችሁን፤ የምትወዱትንና የሚበጃችሁን ውጤት ይስጣችሁ። አሏህ ያገራላችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው፤ ካሰባችሁት በላይ ያቅልልላችሁ። ፈተናውን የምትሰሩትና የተሻለ ውጤት የምታስመዘግቡበት፣ በሰራችሁትም ውጤት ወደፈለጋችሁት Department የምትገቡበት እንዲያደርግላችሁ በሰላም ጀምራችሁ በሰላም የምትጨርሱ ያድርጋችሁ፤ ጥሩ የሆነን ውጤት ይወፍቃችሁ ፤ በመንገዳችሁ ላይ ከጎናችሁ በመሆን ልባዊ ስክነትና አዕምሯዊ ፍጥነትን አሏህ ይስጣችሁ !!! ፈተናውንም ተረጋግታችሁ የምትሰሩት፣ ካሰባችሁትም በላይ ቀላልና በ ''Confidence'' የምትወጡት ያድርግላችሁ። አሚንንንንንንንንንንን !!! 🌟መልካም ፈተና
704