Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹 的分析概览
频道 Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹 (@mudcpr) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 10 007 名订阅者,在 政治 类别中位列第 4 991,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 3 308 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 10 007 名订阅者。
根据 06 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 82,过去 24 小时变化为 5,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 10.81%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.98% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 081 次浏览,首日通常累积 498 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 6。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 政治 类别中的关键影响点。
10 007
订阅者
+524 小时
+297 天
+8230 天
帖子存档
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
+3
በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት እና የላቀ አመራር ልምድ ልውውጥ ላይ የሚሳተፈውን ልዑክ ከመሩት የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር ተወያይተናል።
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የበርካታ ብሔረሰቦች፣ የብዙ ባህሎች እና የከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር ባለቤት የሆኑ ሀገራት ናቸው። ይህም የሁለቱን ሀገራት ትብብር አጠናክረን ለማስቀጠልና የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መልካም ዕድል ይሰጠናል።
+8
ያለፉትን የለውጥ ዓመታት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርን በሚኒስትርነት የመሩት ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከመስከረም 18/2019 ዓ.ም ጀምሮ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርገው መሾማቸው ይታወቃል።
ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታዎች የመልካም ምኞታቸውን በጽ/ቤታቸው በመገኘት ገልጸዋል።
ዘርፉን በተሻለ የአመራር ብቃት በመምራት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ቤተሰብ እንዲሁም መላው የከተማ ነዋሪ ያመሠግኖታል በሚሄዱበት ሁሉ መልካም ሁሉ እንዲገጥምዎ ከልብ ይመኛል፡፡
መልካም የሥራ ዘመን!!
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን፣ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባው ነው ያፀደቀው፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የመንግሥት ተወካይ የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ግልጽና ውጤታማ የሆነ የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት በመፍጠር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና የተጠሪ ተቋማት የውልና የተናጠል ተግባር በግልጽ በማስቀመጥ ረገድ ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት እና ዓላማ በተመለከተ አስረጂ ሆነው የቀረቡት የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች የተከበሩ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እና ክብርት ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ በዝርዝር ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
በመንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት መስሪያ ቤቶች በአለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የታዩትን ውስንነቶች ለመቅረፍ ረቂቅ አዋጁ እንደሚያግዝ እና የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲአዊ መብቶች እንዲከበሩና የህዝቡ የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል እና የአገልግሎት ዘርፉን ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ሰፊ ጥናት የተደረገበት እና ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ከተጠሪ ተቋማት ጋር ውይይት በማድረግ በቂ ግብአት ማግኘት መቻሉን አስረድተዋል፡፡
የተቋማትን አደረጃጀት በግልጽ ማስቀመጥ የመንግስትና የህዝብ ሃብት የስራ ኃላፊዎች በአግባብ እንዲጠቀሙ ለማስቻል ረቂቅ አዋጁ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ አንዳንድ የተጠሪ ተቋማት ለወጥ በደንብ የስራ ባህሪያቸውን እና ያላቸውን ፋይዳ ያገናዘበ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ቀልጣፋና ውጤታማ አደረጃጀት በመፍጠር የተቋማትን የማስፈጸም አቅምን ለማሳደግ ረቂቅ አዋጁ ሚናው የጎላ መሆኑን የምክር ቤት አባላቱ አያይዘውም ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱ ባካሄደው ልዩ ስብሰባው፤ የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት ፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1440/2019 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
#HoPR
7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ ፣ አደረጃጀት ፣ ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ መክሯል ።
መስከረም 27/2019 ዓ.ም
ለም/ቤቱ በቀረበው ማብራሪያ ከዚህ በፊት በነበሩት 22 አስፈፃሚ አካላት ላይ የቁጥር ልዩነት እንደሌለና ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ይህም ሆኖ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ብቻ የስያሜ ለውጥ መደረጉንና ሁለት ሚኒስቴሮች አንደ አዲስ መቋቋማቸው ተብራርቷል።
እንደ አዲስ የተቋቋሙት ሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች ፦
👉 ቀድሞ " የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር " የነበረው በአዲሱ " የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር " በሚል
👉 ቀድሞ " የቱሪዝም ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ " የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር " በሚል መቋቋማቸው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ቀድሞ " የፕላንና ልማት ሚኒስቴር " የነበረው " የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር " በሚል ተቀይሯል።
ቀድሞ " የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር " የነበረው " የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር " በሚል ስያሜው ተቀይሯል።
በሚኒስቴር መ/ቤቶቹ ላይ ማሻሻያው ያስፈለገበት ምክንያት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም ከተልዕኳቸው ጋር ለማጣጣም ነው ተብሏል።
#HoPR
በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የቀረቡ የ2019 ዓ.ም የመንግስት ዋና ዋና ትኩረቶች ፦
1. ሰላም ለኢትዮጵያ እድገት እና ብልጽግና ያለው ዋጋ ያጤነና እና ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ ህብረትን፣ ትብብርን እና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር የሚከናወን ይሆናል።
2. ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል።
3. ትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከሉ ያደረገ ልማት ይፋጠናል።
4. ለእድገታችን ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪ እና የግብርና ግብአቶች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አቅማችን ራሱን እንዲችል ይደረጋል።
5. የፕሮጀክት እና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይሰራል።
6. የታክስ መሰረትንም በማዘመን፣ ዕዳን ወግ ባለው መልኩ ማስተዳደር እንዲሁም የመንግስት ገቢ እና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም ያድጋል።
7. በፌደራል መንግስት እና በክልሎች መካከል ያለው የሰራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ኩነት የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋ እና እንከን አልባ እንዲሆን ይደረጋል።
8. የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ በተለይም ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለቀጣናዊ ሰላም እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጥ ተነሳሽነቶች ያሉት እና አለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል።
#የመደመር_መንግሥት
+2
"የምታወጧቸው ሕጎች እና ተግባሮቻችሁ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚወስዱ ሊሆኑ ይገባል" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የምክር ቤቱ አባላት የሕዝብን አደራ በብቃት እንዲወጡ እና ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚያራምዱ ሕጎችን እንዲያወጡ አሳሰቡ።
ፕሬዚዳንቱ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ይህ ታላቅ ምክር ቤት ሥልጣን በሕዝብ ይሁንታ ብቻ የሚገኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፣ አባላቱ ይህንን ተገንዝበው የተጣለባቸውን አደራ በታማኝነት ሊፈጽሙ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
የምክር ቤቱ ቀዳሚ ትኩረት መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና የሀገራችንን ኢኮኖሚ ማሳደግ ላይ ሊሆን እንደሚገባ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ በተለይም ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን መግታት የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ የላቀ ትኩረት እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የጤና እና የትምህርት ዘርፎችን ከፍ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም መሠረተ ልማቶችን በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገት ከፍታ የሚያሸጋግሩ ተግባራት ሊከናወኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንቨስትመንት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በቴክኖሎጂ እና በመሳሰሉት መስኮች የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ላቀ ውጤታማነት ማደግ እንዳለባቸው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በመልዕክታቸው አስምረውበታል።
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
የሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ
7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል::
በምክር ቤቶቹ የጋራ መክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ንግግር ያደርጋሉ
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ማካሄዱ ይታወሳል
Repost from FDRE Government Communication Service
+2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
"ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ።
ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ለአህጉሩ አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው። አጋርነታችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እንደምናጠናክር ተስፋ አለኝ::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
+9
ያለፉትን ስብራቶች መርምረን፣ በፍጥነት እና በፈጠራ መንገድ ሪፎርም እያደረግን፣ የሚመጣውን ዓለም ለመቃኘት እየተዘጋጀን ነው።
#የመደመርመንግሥት
+3
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቃላ መሃላ ፈጽመዋል
***
በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
*
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።
በዚህም ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።
አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
***
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።
በዚህም አቶ አሕመድ ሽዴን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።
አቶ ደስታ ሌዳሞ የፌዴሬሸን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
***
የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።
በዚህም አቶ ደስታ ሌዳሞን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።
ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
***
የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።
በዚህም ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።
