ch
Feedback
Seid Social

Seid Social

前往频道在 Telegram

አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

显示更多

📈 Telegram 频道 Seid Social 的分析概览

频道 Seid Social (@seidsocial) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 22 876 名订阅者,在 新闻与媒体 类别中位列第 10 438,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 470

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 22 876 名订阅者。

根据 22 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -86,过去 24 小时变化为 -8,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 32.19%。内容发布后 24 小时内通常能获得 18.81% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 7 364 次浏览,首日通常累积 4 303 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 128

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

凭借高频更新(最新数据采集于 23 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 新闻与媒体 类别中的关键影响点。

22 876
订阅者
-824 小时
-587
-8630

数据加载中...

标签云
无数据
有任何问题?请刷新页面或联系我们的客服
进出提及
---
---
---
---
---
---
吸引订阅者
七月 '26
七月 '26
+63
在8个频道中
六月 '26
+206
在4个频道中
Get PRO
五月 '26
+126
在3个频道中
Get PRO
四月 '26
+551
在9个频道中
Get PRO
三月 '26
+1 965
在10个频道中
Get PRO
二月 '26
+956
在4个频道中
Get PRO
一月 '26
+498
在2个频道中
Get PRO
十二月 '25
+1 320
在4个频道中
Get PRO
十一月 '25
+379
在2个频道中
Get PRO
十月 '25
+816
在8个频道中
Get PRO
九月 '25
+730
在10个频道中
Get PRO
八月 '25
+194
在3个频道中
Get PRO
七月 '25
+372
在13个频道中
Get PRO
六月 '25
+1 733
在12个频道中
Get PRO
五月 '25
+606
在6个频道中
Get PRO
四月 '25
+1 100
在9个频道中
Get PRO
三月 '25
+675
在5个频道中
Get PRO
二月 '25
+241
在8个频道中
Get PRO
一月 '25
+690
在8个频道中
Get PRO
十二月 '24
+1 128
在10个频道中
Get PRO
十一月 '24
+390
在5个频道中
Get PRO
十月 '24
+1 058
在10个频道中
Get PRO
九月 '24
+603
在9个频道中
Get PRO
八月 '24
+302
在10个频道中
Get PRO
七月 '24
+361
在12个频道中
Get PRO
六月 '24
+167
在6个频道中
Get PRO
五月 '24
+518
在15个频道中
Get PRO
四月 '24
+611
在8个频道中
Get PRO
三月 '24
+187
在5个频道中
Get PRO
二月 '24
+262
在4个频道中
Get PRO
一月 '24
+289
在7个频道中
Get PRO
十二月 '23
+378
在4个频道中
Get PRO
十一月 '23
+533
在9个频道中
Get PRO
十月 '23
+496
在3个频道中
Get PRO
九月 '23
+118
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+159
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+155
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+230
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+525
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+95
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+142
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+88
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+135
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+90
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+141
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+229
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+384
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+424
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+241
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+376
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+182
在0个频道中
Get PRO
四月 '22
+337
在0个频道中
Get PRO
三月 '22
+535
在0个频道中
Get PRO
二月 '22
+74
在0个频道中
Get PRO
一月 '22
+12
在0个频道中
Get PRO
十二月 '21
+17
在0个频道中
Get PRO
十一月 '21
+40
在0个频道中
Get PRO
十月 '21
+384
在0个频道中
Get PRO
九月 '21
+688
在0个频道中
Get PRO
八月 '21
+615
在0个频道中
Get PRO
七月 '21
+452
在0个频道中
Get PRO
六月 '21
+338
在0个频道中
Get PRO
五月 '21
+1 104
在0个频道中
Get PRO
四月 '21
+150
在0个频道中
Get PRO
三月 '21
+152
在0个频道中
Get PRO
二月 '21
+367
在0个频道中
Get PRO
一月 '21
+437
在0个频道中
Get PRO
十二月 '20
+1 820
在0个频道中
日期
订阅者增长
提及
频道
23 七月0
22 七月+1
21 七月+1
20 七月0
19 七月+8
18 七月+5
17 七月0
16 七月0
15 七月0
14 七月+17
13 七月+4
12 七月+6
11 七月+2
10 七月0
09 七月+4
08 七月+4
07 七月0
06 七月+3
05 七月0
04 七月+1
03 七月+3
02 七月+4
01 七月0
频道帖子
የየመን ሁቲዎች በሳኡዲ ላይ የጣልነውን እገዳ ጥሰዋል ያሏቸውን ሁለት የሳኡዲ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በሚሳኤል አጥቅተዋል። ሁለቱ ግዙፍ መርከቦች በጥቃቱ ሲነዱ ታይተዋል። የሳኡዲ አየር ሀይል በየመን ላይ ድብደባ ከፈፀመ በሗላ በሁለቱ ሀይሎች መካከል ያለው ውጥረት አይሏል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

2
እስራኤላውያን ጋዛ ላይ ለመስፈር በቤን ጌቪር እየተመሩ ወደ ጋዛ እየተመሙ ነው። እንግዲህ ጋዛን ከፍልስጤማውያን አፅድቶ የእስራኤላውያን የማድረግ ዘመቻው ወደ ቀጣይ ምእራፍ ተሸጋግሯል። እስራኤል በአ+1
እስራኤላውያን ጋዛ ላይ ለመስፈር በቤን ጌቪር እየተመሩ ወደ ጋዛ እየተመሙ ነው። እንግዲህ ጋዛን ከፍልስጤማውያን አፅድቶ የእስራኤላውያን የማድረግ ዘመቻው ወደ ቀጣይ ምእራፍ ተሸጋግሯል። እስራኤል በአሁኑ ሰአት 70% የሚሆነውን የጋዛ ክፍል ተቆጣጥራ በግንብ እያጠረች ትገኛለች። 30% ብቻ ሀማስ ይቆጣጠራል። እናም እስራኤል ጋዛን የመጠቅለል ሌላኛውን ምእራፍ ጀምራለች። በእስራኤሉ ደህንነት ሚኒስትር ኢትማር ቤን ጌቪር የሚመራው የእስራኤል ሰፋሪዎች ጉዞ ወደ ጋዛ እየተደረገ ነው። በትንሽ የጋዛ አካባቢ በእስራኤል ከበባ ውስጥ የታጨቁት ፍልስጤማውያንም የእስራኤል አየር ድብደባ እየወረደባቸው ይገኛሉ። የጋዛዊያን አሳዛኝ ህይወትም በዚህ መልኩ ቀጥሏል። ወይ እስኪተርፉ ወይ ጨርሰው እስኪጠፉ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
3 110
3
እዚህች ምድር ላይ እንደ ስብእና ገደላ ( Character Assassination ) ያለ አደገኛ ነገር ያለ አይመስለኝም። ስብእና ገደላ ወይንም ስም ማጥፋት ለአጥፊዎቹ እጅግ ቀላል ስራ ጥቃቱ ለሚደርስባቸው ደግሞ ሊቋቋሙት የማይችሉት ስብራት ነው። አብዛኛው ስም ማጥፋቶች የሚፈፀሙት ውሸትና ጥላቻን መሰረት አድርገው ሲሆን ስም አጥፊዎቹ የተጎጂውን ስም ለማጥፋት እጅግ ከፍተኛ ትኩረት የሚስቡ ማጠልሻዎችን ይጠቀማሉ። አንድ ሰው የሆነን አካል ስም ለማጥፋት ምንም አይነት ወጪ የማይጠይቀውና ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት እና ህሊና አልባነት በቂው ስለሆነ ያቺን ነገር መለኮስ ብቻ ይበቃዋል። ከዚያ ስም ማጥፋት እንደ ሰደድ እሳት የሚስፋፋ ነበልባል ስለሆነ ወዲያው ይዳረሳል። አብዛኛው የሰው ልጅ ደግሞ አንድ ባህሪ አለበት። ውድቀትህን ይመኛል። ውድቀትህ ከስኬትህ በላይ ያስደስተዋል። እናም "ተዋረደ" የተባልክበትን ወሬ ሲሰማ አዳር እስከ ዳር በእልልታ ያራግበዋል። ምን የቅርብህ ሰው ቢሆን ፤ ምን ውለታ የዋልክለት ቢሆን ያኔ ዞር ብሎ አያይህም። ሁሉንም ትቶ አይንህን ላፈር ይልሀል። እናም እውነት አንተ ጋር ብትሆን እንኳ ሊሰማህ ዝግጁ አይደለም። ያንተ እውነት በውሸት ማእበል ትዋጥና እንደ ታፈነ ፍጡር ትፈራገጣለች። ህይወቷን ለማትረፍ! ግና ማእበሉ ከእርሷ አቅም በላይ ነውና እጅ ትሰጣለች። አንተም ሁሉንም ትተህ ተስፋ ቆርጠህ ወደ ድባቴ እና መገለል ትሄዳለህ። ራስህን ታጣዋለህ። ተስፋም ትቆርጣለህ። ሁሉም ነገር የተጫነህ ይመስልሀል። ከዚህ የስብእና ገደላ ጥቂቶች እንጅ አይተርፉም። ስብእና ገደላ የአካል ገደላ ቅድመ እርምጃ ነው። ስብእናህ ከጠፋ በሗላ አንተ ለቀጣይ ጥቃቶች የተመቻቼህ ህጋዊ ኢላማ ( legitimate target ) ነህ። እናም ጥቃት ቢፈፀምብህ የሚቆረቆርልህም የሚደርስልህም ለምን ብሎ የሚጠይቅልም የለም። ኢስላም እንዲህ አይነቱን ዘመቻዎች ከከባባድ ወንጀሎች መዝግቦ አስቀምጦታል። አንድ ሰው በሀሜትና ስም በማጥፋት ላይ መጠመዱ የሰውየውን ስጋ ቆራርጦ እንደመብላት እንደሚቆጠር ኢስላም ይነግረናል። አላህም በቁርአኑ ስም አጥፊና ወሬ አመላላሾይን ፋሲቅ ወይንም አፈንጋጮች ሲል ይሰይማቸዋል። የነዚህን ሰዎች ምስክርነትም ሆነ ተአማኒነት መቀበልም እንደማይገባ አላህ ይነግረናል وَلاَ تَقْبَلُوا لَهُمْ شَهَادَةً أَبَدًا وَأُوْلَئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ በማለት! ለዚህም ነው አላህ አስከትሎ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ" ያለን! ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የሀሜት የስም ማጥፋትና ነገር ማዋሰድን አደገኛነት ሲያስጠነቅቁ " ይህችን ምላሱን በመቆጣጠር ቃል የገባልኝ ሰው እኔም ጀነትን ከአላህ ዘንድ ዋስ እሆነዋለሁ " በማለት ። ሙአዝ ኢብኑ ጀበል አላህ ስራውን ይውደድለትና ነብያችንን " ጀነት የሚያስገባኝን ከጀሀነም እሳትም የሚገብቀኝን ስራ ንገሩኝ " ሲላቸው ነብያችን ምላሳቸውን አውጥተው ያዙና " ይህችን ምላስህን ተጠንቀቃት" አሉት። ሙአዝም በመገረም " አንተ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አላህ እኛን በምላሳችን ይጠይቀናል እንዴ? አላቸው። እርሳቸውም " አይ አንተ ሙአዝ ታዲያ ሰዎች በአፍጢማቸው ጀሀነም እሳት የሚደፉት ምላሳቸው ባጨደቺው ነገር አይደለም እንዴ" አሉና መለሱለት። ኡቅባ ኢብን አሚር ነብያችንን ሰላም ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ ሲላቸው " ምላስህን ተቆጣጠር ፤ በቤትህም ተብቃቃ ፤ ጌታህን ፈርተህም አልቅስ ነጃ ማለት ያ ነው" አሉት። ዛሬ እኛ ምላሳችን ፅሁፋችን የስንቶችን ቀልብ እየሰበረ እንደሆነ እናስተውል ይሆን? ስንቶች በኮሜንቶቻችን እና በፖስቶቻችን ራሳቸውን እንዲጠሉ እያደረግን እንደሆነ እናስተውል ይሆን? ፌክ አካውንቶችን ከፍተን ስንት አይነት ልብ ሰባሪ ድርጊቶችን እንደምናደርግ እናስተውል ይሆን? አላህ በፌክ አካውንቶቻችን አይጠይቀን መስሎ ይሆን የሚሰማን! አንድ የነብያችንን ሀዲስ ልጨምርና ፅሁፌን ላጠናቅቅ " ሙስሊም ብሎ ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና ከእጁ አዛዎች ሰላም የሆኑለት ነው" ሰው በምላሳችን አዛ እያደረግን ትክክለኛ ሙስሊምነት የለምና ለኛም አብሮን ለሚኖሩ ህዝቦችም ሰላም ስንል ልብ የሚሰብሩ ስብእና የሚገድሉ ነገሮችን ከማሰራጨት እንቆጠብ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
4 165
4
የየመን ሁቲዎች በሳኡዲ አረቢያ ላይ የባህር ማእቀብ መጣላቸውን ተከትሎ የአረብ ሀገራት ከሳኡዲ አረቢያ ጎን እንደሚቆሙ አስታውቀዋል። ሳኡዲ አረቢያ የመንን መደብደቧን ተከትሎ ሁቲዎች ለአፀፋ እርምጃ
የየመን ሁቲዎች በሳኡዲ አረቢያ ላይ የባህር ማእቀብ መጣላቸውን ተከትሎ የአረብ ሀገራት ከሳኡዲ አረቢያ ጎን እንደሚቆሙ አስታውቀዋል። ሳኡዲ አረቢያ የመንን መደብደቧን ተከትሎ ሁቲዎች ለአፀፋ እርምጃ ተዘጋጅተናል ብለዋል። ከእርምጃቸው ቀዳሚ ያደረጉት በሳኡዲ ላይ የባህር ከበባ ማድረግ ነው። እናም ይህንን አዋጅ አውጀዋል። የሳኡዲ አረቢያን መርከቦች ቀይ ባህር ላይ እንደሚመቱ አስታውቀዋል። ይህን ተከትሎ ታዲያ የአረብ ሀገራት መሪዎች ከሳኡዲ ጎን ቆመው የሁቲዎችን ማስፈራሪያ እንደሚታገሉ አሳውቀዋል። ሳኡዲ አረቢያ በበኩሏ በአረብ ሀገራት መካከል ያለው ወዳጅነት የበለጠ መታደስ ያለበት መሆኑን በመግለፅ ከዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙነት እንደምታድስ አስታውቃለች። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 026
5
ስንት ጠላት ያፈራሁበትን ስንት ስያሜ የተሰጠሁበትን የአታክፍሩ አጀንዳየን ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን እንዲህ ቁልጭ እጥር ምጥን አድርገው ሲናገሩት በጣም ደስ ይላል። ሙስሊሞችን ታከፍሩ ዘንዳ ማን ስልጣን
ስንት ጠላት ያፈራሁበትን ስንት ስያሜ የተሰጠሁበትን የአታክፍሩ አጀንዳየን ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን እንዲህ ቁልጭ እጥር ምጥን አድርገው ሲናገሩት በጣም ደስ ይላል። ሙስሊሞችን ታከፍሩ ዘንዳ ማን ስልጣን ሰጣችሁ??? ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 532
6
በአለማችን ላይ የስፔይን ፣ የስኮትላንድ እና የቺሊ እግርኳስ ማህበረሰብ የፍልስጤማውያን ነፃነት በመደገፍ ራሳቸውን እንደ ፍልስጤም አካል በመቁጠር በቀዳሚነት ስማቸው ይጠራል። በተለይም የስፔይኑ አትሌቲክ ቢልባኦ ፤ የስኮትላንዱ ሴልቲክ እና የቺሊው ክለብ ዲፖርቲቮ ፓለስቲኖ የፍልስጤማውያን የነፃነት ድምፆች የመብታቸውም አስተጋቢዎች ራሳቸውንም እንደ ፍልስጤም ክለቦች የሚቆጥሩ ቡድኖች ናቸው። የስፔይኑ ባስክ ክለብ አትሌቲክ ቢልባኦ ድንቅ የነፃነት ምልክት ነው። ስፔይን ውስጥ ያለ ግን ስፔናዊ ያልሆነ የባስክን ማንነት ለማስጠበቅ የሚታትር የባስካዊያን ያለመጥፋት ምልክትም ነው። ባስክ በስፔይን ግዛት ቁጥጥር ስር ላለመዋል የታገለች ቢሆንም ተረታ ገብታለች። እና እንደ ካቶሎኒያ ሁሉ የማንነት ጥያቄና የነፃነት ትግልን የሚያቀነቅኑ ህዝቦች ግዛት ነች። እናም የነፃነት ትግል የሚያደርጉ ህዝቦችን በወዳጅነት መያዝ ልምዳቸው ነው። አትሌቲክ ቢልባኦ የባስክ ተወላጅ ያልሆነን ተጫዋች አያስፈርምም አያጫውትምም። ክለቡ ለፍልስጤም ያለውን አጋርነት ለማሳየት ከፍልስጤም ተጨዋቾች ጋር የወዳጅነች ጨዋታዎችን ያደርጋል በርካታ ዝግጅቶችንም ያዘጋጃል። እገዛና ድጋፍም ያደርጋል። የስኮትላንዱ ሴልቲክ ክለብ የፍልስጤም ድምፅ የፍልስጤም ዘብም ነው። የክለቡ ደጋፊዎች የፍልስጤምን ሰንደቅ በጠቅላላ ይዘው ያውለበልቡና ስታዲየሙን አረንጓዴ ያደርጉታል። እናም ያ ደጋፊ "አረንጓዴው ብርጌድ " እየተባለ ይጠራል። ክለቡ ለፍልስጤማውያን ገንዘብ በማሰባሰብ ድምፃቸውን በማስተጋባት የሚስተካከለው የለም። በዚህ ድርጊቱ በአውሮፓ የእግርኳስ ማህበር በተደጋጋሚ ቢቀጣም ክለቡ ግን ይህንን የነፃነትና ሰብአዊነት አጋርነቱን አቋርጦ አያውቅም። ቺሊ ክለብ ዲፖርቲቮ ፓለስቲኖ ከፍልስጤም ወደ ቺሊ በፈለሱ ፍልስጤማውያን የተመሰረተ ክለብ ነው።የክለቡ ማሊያም የፍልስጤም ባንዲራ ነው። ቺሊ ከአረብ ሀገራት ውጭ ከፍተኛውን የፍልስጤም ተወላጆች የያዘች ሀገር ናት። ቺሊ ከ 500,000 በላይ የፍልስጤም ተወላጆች ይኖሩባታል። የዚህች ሀገር ህዝብ ለፍልስጤም ነፃነት በመዘመር ይታወቃል። ጨዋታዎች ሲደረጉ የስቴዲየሙ ህዝብ በርከክ ብሎ የሚገደሉ ፍልስጤማዊያን ህፃናትን ያስባል። ከየሀገራቱ እነዚህን ሶስት ክለቦች አነሳን እንጅ የነዚህ ሶስት ሀገራት ህዝቦች በአብዛኛው የፍልስጤም ነፃነት አቀንቃኞች ናቸው። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 435
7
ከአንድ ቀን በፊት ኢራን በአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ያደረሰቺው ውድመት ከተገለፀውም በላይ መሆኑ በአሜሪካ ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሯል። ከፍንዳታው ሁለት ቀን በሗላ ማንነቱን መለየት የሚያስቸገር የአሜሪካ ወ+1
ከአንድ ቀን በፊት ኢራን በአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ያደረሰቺው ውድመት ከተገለፀውም በላይ መሆኑ በአሜሪካ ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሯል። ከፍንዳታው ሁለት ቀን በሗላ ማንነቱን መለየት የሚያስቸገር የአሜሪካ ወታደር ሰውነት ቁርጥራጭ ማንኘቱን የአሜሪካ ጦር አስታውቋል። በጆርዳን በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የደረሰው ይህ የሚሳኤል ጥቃት ከባድ ውድመት ያደረሰ ሲሆን የሳተላይት ምስሎች የጉዳቱን መጠን ያሳያሉ። በጥቃቱ በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች እንደተገደሉ ሲገመት አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን የኢራን ጥቃት የጉዳቱ መጠን ከተገለፀው በጣም የከፋ መሆኑን ለኒውዮርክ ታይምስ ገልፀዋል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 457
8
እነዚህ ጋዛዊያን ናቸው እግርና እጅ የሌላቸው። የስፔይንና አርጀንቲናን ማልያ ለብሰው የአለም ዋንጫ ፍፃሜን የሚመስል ጨዋታ አድርገዋል። ለአለም ማሳየት የፈለጉት አንድ ነገር ነው " እኛምኮ ህይወት
እነዚህ ጋዛዊያን ናቸው እግርና እጅ የሌላቸው። የስፔይንና አርጀንቲናን ማልያ ለብሰው የአለም ዋንጫ ፍፃሜን የሚመስል ጨዋታ አድርገዋል። ለአለም ማሳየት የፈለጉት አንድ ነገር ነው " እኛምኮ ህይወት ይገባናል ፤ እንዲህ ሳንሆን አካላችንን ሳናጣ መኖርኮ እኛም ይገባን ነበር ። እኛም እንደናንተው ህዝቦች ነን ተጫውተን ተደስተን መኖር የምንናፍቅ የሚገባን ህዝቦች ነበርን" የሚል ነው። ጋዛዊያንን በዚህ መልኩ ማየት ልብ ይሰብራል! t.me/Seidsocial
6 163
9
ልክ በዛሬዋ እለት 711 ስፔይን በጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ በሚመራው የሙስሊሞች ሀይል ተከፈተች! ከ ዛሬ 1315 አመት በፊት በርበራዊው ጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ ሞሮኮን ተሻግሮ ጂብራላተርና ተሻግሮ ስፔይን ገባና በጊዜው ከነበረው የስፔይን ስርወመንግስት ቪሲጎቲክ ኪንግደም ጋር ተፋልሞ አሸነፈ። የቪስጎቲክ ንጉስ ሮዴሪክ ም በጦርነቱ ተገደለ። አብዛኛው የስፔይንና ፖርቹጋል ክፍል እንዲሁም ደቡብ ፈረንሳይ በሙስሊሞች ስር ገባና የኡመያድ ስርወመንግስት አካል ሆነ። ግዛቱም አንደሉስ ተባለና ስፔይን አንደሉሲያ ተብላ ተጠራች። ዋና ከተማዋ ኮርዶባ ወይንም ቁርጡባ ሆነች። ከዚያ እነ ኢማም ቁርጡቢን ጨምሮ እነ ኢማም ኢብኑ ሀዝም ፤ ሸይኽ ኢብን አረቢ ፤ እነ አማም አልሻጢቢ ፤ እነ ኢማም አልዘህራዊ ፤ እነ ኢማም ኢብን አብዲልበር ፤ እነ ኢብን በጧል ፤ እነ ኢማም አለይሲ ኧረ ስንቱ ተነግሮ የማያል አካቢር ኡለማእ ተፈለፈሉበት። ጧሪቅ ወታደሩን ይዞ ወደ ስፔይን ሲሻገር ያፈበት ደሴት የጧሪቅ ተራራ ወይንም ጀበሉል ጧሪቅ ተባለች። ዛሬ ስሟ ተንሻፎ ተንሻፎ ጂብራላተር በመባል ትታወቃለች። የሙስሊሙ ጦር እነ ሲቪያ ፣ ዛራጎዛ ፤ ሜሪዳ ፣ ግራናዳ ፣ ኮርዶባ ወዘተ የመሳሰሉትን ከተሞች ተቆጣጠረ። የሙስሊሙ ጦር ስፔይንና ፖርቹጋልን ከተቆጣጠረ በሗላ ጉዞውን ያደረገው ወደ ፈረንሳይ ነበረ። በዚያም ደቡብ ፈረንሳይን ተቆጣጠረ። መላዋን ፈረንሳይን ለመቆጣጠር ወደ ሰሜን እየገሰገሰ የነበረው የሙስሊሙ ጦር በ 732 ቱርስ በምትሰኘው የፈረንሳይ ከተማ ላይ ከፈራንኪሽ ኪንግደም ጋር ገጠመና ጉዞው ተገታ። የፈረንሳዩ ንጉስ ቻርልስ ማርቴል የሙስሊሙን ግስጋሴ መግታት ተቻለው። በዚህ ጊዜ የሙስሊሙ ሀይል የተቆጣጠረውን ግዛት አፀናና ከፍተኛ የሆነ በጊዜው ተወዳዳሪ የሌለው የስልጣኔ ብርሀንን ፈነጠቀ። በዚያ የሚኖሩ አይሁዳዚያን አውሮፓውያን የሚያደርሱባቸው በደል ስለቀረላቸው የሙስሊሙን ሀይል በደስታ ተቀበሉት። እናም አይሁዶች በሙስሊሙ ስልጣኔ ውስጥ የማይተካ ጥበብ ሳይንስና ፈጠራን አንቆጠቆጡት። የሙስሊሙ መንግስት የሀይማኖት ነፃነትን በስፔይን እና ፖርቹጋል እንዲሁም ደቡብ ፈረንሳይ አወጀ። እናም ከግሪክ እስከ ሮም ያሉ የእውቀት ቅሪቶች ወደ አንደሉሲያ ተንቆረቆሩ። አስትሮኖሚ ፣ ህክምና ፣ ሳይንስ ፣ ሂሳብ እዚያ ቦታ ናኙ። የኮርዶባ መሳጅድችና የአልሀምብራ ቤተመንግሥት እንኳን በዘመኑ አሁንም ሲታዩ በግርምት አፍዝዘው ያስቀራሉ። ሙስሊሞች ፣ አይሁዶች እና ክርስቲያኖችም ካለ እምነት ልዩነት የስልጣኔ ጡብን በጋራ ገነቡ። ዛሬ ስፔይን ታሪኮቿን ስትገልፅ እነዚያ ግሩም አሻራዎች ያኮሯታል። የአንደሉሲያ ኢስላማዊ መንግስት ከ 711 እስከ 1492 ለ 780 አመታት በአስደናቂ ከፍታ ቆየ። ስፔይን እናፖርቹጋልም ለ 800 አመታት ገደማ የሙስሊም ግዛት ሆነው ኖሩ። ይሁን እንጅ የሙስሊሙ ስረወመንግስት በመካከሉ ከፍተኛ የሆነ የስልጣን ሽኩቻና የርስበረሰስ ጦርነት ሲያጋጥመው በሌላ በኩል የፖርቹጋልና ስፔይን ክርስቲያናዊ መንግስታት እየተጠናከሩ ከፋፍሎ ማጥቃት ጀመሩ። የሙስሊም ስልጣን ጥመኞችም እርስበርሳቸው ሲዋጉ ከአንዱ የክርስቲያን ሀይል እየታገዙ ከተደካከሙ በሗላ በመጨረሻም ተሸንፈው ስፔይንን እና ፖርቹጋልን አስረክበው ወጡ። አባቱን ከድቶ ከክርስቲያኖች ጋር በመወገን አባቱን የወጋው ሙሀመድ የተባለው የመጨረሻው መሪም የመጨረሻ ይዞታው የነበረቺውን ግራናዳን ለቆ ቁልፉን ለክርስቲያን ሀይሎች አስረክቦ ወጣ። እናም ሲወጣ ከተማዋን ወደ ሗላ ዞሮ አያትና በፀፀትና ቁጭት አለቀሰ። ሁኔታውን እያየቺው የነበረቺው እናቱም " እንደወንድ ተዋንተህ ያላዳንካትን ከተማ እንደ ሴት አትነፋረቅ " አለቺው። የአንደሉሲያም ታሪክ በዚህ ተፈፀመ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
6 499
10
ሶስት በኢኮኖሚ ድቀት የተመቱ ጥገኛ ሀገራት! ሶስት ተለማማጭ መንግስታት! ሶስት ሀገሮቻቼው ለፍልስጤም ያላትን ድጋፍ ያስጠለሹ መንግስታት! ኢትዮጵያ አርጀንቲ ሶማሌላንድ ! ሶስቱም የፍልስጤምን የመብ+2
ሶስት በኢኮኖሚ ድቀት የተመቱ ጥገኛ ሀገራት! ሶስት ተለማማጭ መንግስታት! ሶስት ሀገሮቻቼው ለፍልስጤም ያላትን ድጋፍ ያስጠለሹ መንግስታት! ኢትዮጵያ አርጀንቲ ሶማሌላንድ ! ሶስቱም የፍልስጤምን የመብት ጥያቄ የሚቀበሉ የሚደግፉ የሀገርነት እውቅናም የሚሰጡ ነቀሩ። ያው ሶማሌላንድ ገና ሀገር ያልሆነች መሆኗ እንዳለ ሆኖ! አርጀንቲና እና ኢትዮጵያ በእዳና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሲመቱ መሪዎቻቼው አንድ መፍትሄ አድርገው የወሰዱት ከእስራኤል ጋር መወዳጀት ነው። የእስራኤል ወዳጅ የሆነ የአሜሪካም ይሆናል በሚል ብሂል። በርግጥ ለጊዜውም ቢሆን ብድርም አግኝተዋል የእዳ እፎይታም ተደርጎላቸዋል። አሁን ደግሞ ማን ትቀላቀላቸዋለች? ሌላኛው የፍልስጤም ወዳጅ የነቀረቺው ኮልምቢያ! እና ነገሩ ውስብስብ ነው! ሀይልና ገንዘብ ይኑርህ ሁሉም እምነታዊ ክልክላቱን ጥሶ ሳይቀር ይሰግድልሀል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
6 080
11
ሁለቱ የፍልስጤማውያን ወዳጅ ህዝቦች ስፔይንና አርጀንቲና ዛሬ ለዋንጫው ይፋለማሉ። ሁለቱም ህዝቦች የፍልስጤም መብትን የሚያቀነቅኑት ዛሬ ከጋዛው ዘር ማጥፋት በሗላ ሳይሆን ያኔ ከብዙ አስርት አመታት+3
ሁለቱ የፍልስጤማውያን ወዳጅ ህዝቦች ስፔይንና አርጀንቲና ዛሬ ለዋንጫው ይፋለማሉ። ሁለቱም ህዝቦች የፍልስጤም መብትን የሚያቀነቅኑት ዛሬ ከጋዛው ዘር ማጥፋት በሗላ ሳይሆን ያኔ ከብዙ አስርት አመታት በፊት ነበር። የአርጀንቲናዊያንና የስፔያዊያን ድጋፍ ከሀማስም ከፋታህም መመስረት የቀደመና ገና እስራኤል በፍልስጤማውያን መሬት ላይ ሶትመሰረት የጀመረ ነበር። ሁለቱም ሀገራት ያኔ በ 1947 የፍልስጤም ምድር ለሁለት የሚከፍለውን የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ ያልደገፉ ሀገራት ናቸው። በ 1974 ስፔይን የፍልስጤምን የተመድ አባል ሀገር የመሆን ውሳኔ ስትደግፍ በ 1976 ከሁለት አመት በሗላ አርጀንቲና የፍልስጤምን ሀገርነት የሚደግፈውን ውሳኔ ያሳለፈች ሲሆን አርጀንቲና የእስራኤል ወረራ በተመድ ተወካይዋ ካርሎስ ኦርቲዝ ዲ ሮዛስ አማካኝነት በማውገዝ ለፍልስጤም ያላትን አጋርነት አሳይታ ነበር። ያ ከዛሬ 50 አመት መሆኑን ልብ ይሏል። ሁለቱም ሀገራት ለያሲር አረፋት ድጋፍ የነበራቸው ሲሆን በተለያዩ የተመድ ውሳኔዎች ላይ ለፍልስጤም ድጋፋቸውን ሲለግሱ ኖረዋል። በ 1999 ፍልስጤም በአርጀንቲና ኢምባሲዋን የከፈተች ሲሆን በ 2010 ሙሉ የሀገርነት እውቅና ሰጥታለች። ስፔይንም አርጀንቲና እውቅና ከሰጠች ከ 14 አመት በሗላ በ 2025 ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠቷ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አርጀንቲና በኢኮኖሚ ቀውስ መመታቷን ተከትሎ ስልጣኑን የተረከበው የጃቪየር ሚሊዬ መንግስት የእስራኤል ዋነኛ ወዳጅ በመሆን በ 2024 የእስራኤልን አጀንዳ ተሸካሚ ሆኗል። ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን የአርጀንቲና ህዝብ ለፍልስጤም ከፍተኛ ድጋፍ ካላቸው ህዝቦች አንዱ ነው። የስፔይን እና አርጀንቲና ህዝብ ድምፁን ለፍልስጤማውያን በማሰማት አደባባይና መንገዶችን በስሙ በመሰየምና አብሮነቱን የሚገልፅ ህዝብ ነው
6 529
12
ኢራን ምሽቱን በጆርዳን በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በፈፀመቺው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች እንደተገደሉ እየተገለፀ ሲሆን የአሜሪካ ወታደራዊ ማእከላዊ እዝ ባወጣው መግለጫ 3የአሜ
ኢራን ምሽቱን በጆርዳን በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በፈፀመቺው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች እንደተገደሉ እየተገለፀ ሲሆን የአሜሪካ ወታደራዊ ማእከላዊ እዝ ባወጣው መግለጫ 3የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውን ገልፆ ሌሎች ወታደሮች አድራሻቸው እንደጠፋና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የአሜሪካ ወታደሮች ደግሞ ወደ ጆርዳን ከፍተኛ ሆስፒታል እንደተወሰደ አሳውቋል። ኢራን የአፀፋ እርምጃ እየወሰደች ሲሆን ጦርነቱ ተባብሶ የሚቀጥል ይመስላል። አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ዜጎቿ ለመልቀቅ እንዲዘጋጁ አዛለች። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 978
13
ኤርዶጋን በተአምር የተረፈበት መፈንቅለ መንግስት ሲታወስ! እነሆ ድፍን 10 አመት ወደ ሗላ! ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የቱርኩን የአታቱርኩን የፖለቲካ ሀይል CHP ን የፖለቲካ የበላይነት ገርስሶ እርሱ አቋቁሞ ወደፊት ባመጣው የ የኢስላሚስቱ AK ፓርቲን የበላይነት ለመገርሰስ የ CHP ሰዎች ብዙ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም ነበር። በፊት ወዳጅ በሗላ ጠላት የሆኑት ፈትሁሏህ ጉለን እና ኤርዶጋን ወደ ለየለት ባላንጣነት ሳቀየሩ ጉለን ከውጭ አጋዦቻቼው ጋር በመሆን በኤርዶጋን ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ተስማሙ። በዚህም ከወታደራዊ አመራሮች ጋር በሚስጥር በመምከር ኤርዶጋን ቤተመንግስቱን በሚለቅበት ጊዜ እና ቦታ ተመቻችቶ እቅድ ተወጠነ። የተደገሰለትን ያላወቀው ኤርዶጋን እረፍት ለማድረግና ለመዝናናት ወደ ማርማራ ከተማ አመራ። እዚያ እያለም የመፈንቅለ መንግስቱ አዘጋጆች ወይ እንዲገደል አሊያም እንዲያዝ ወሰኑ። እናም በዚያው ሁኔታም የኢስታንቡልን እና አንካራ ቤተመንግስቶችን ተቆጣጠሩ። የቱርኩን መገናኛ ብዙሀን TRT ን በመቆጣጠር ለቱርክ ህዝብ ኤርዶጋን መገልበጡንና እርምጃ እንደተወሰደበት አዲስ የቱርክ የሽግግር መንግስ መመስረቱንም አወጁ። ታንኮችና ከባድ ብሰት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ከተሞችን ሞሏቸው። በዚህ ሁሉ መሀል ነው ኤርዶጋን የግድያ ፕሮግራሙን ለትንሽ ቀድሞ በማወቁ ከነበረበት ሆቴል ቀይሮ በአስቸኳይ ተነስቶ ወደ ኢስታንቡል መብረር የጀመረው። ይህ መፈንቅለ መንግስት ሲደረግ ወታደራዊ ሀይሉ ለሁለት ተከፈለ። የኤርዶጋን አጋዥና ተቃዋሚ ሆኖ! እናም እርስበርስ መተኳኮስ ተጀመረ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው በመንግስታቸው ላይ መፈንቅለ መንግስት መፈፀሙን የሰሙት ቱርካዊያን ተቃዋሚ ደጋፊ ሳይሉ ንቅል ብለው ከቤታቸው በመውጣት የፍንቀላውን ሀይሎች የተጋፈጡት። ሀገር ወዳድነትና ጀግንነት በዚያች ቀን ታየች! አለም በቱርክ ህዝብ ፅናትም ተደመመ። ቱርካዊያኑ በሚሸከረከሩ የመፈንቅለ መንግስቱ ጥር ታንኮች ስር እየሄዱ ይተኙ ነበር። እኛን ጨፍልቃችሁን ነው መፈንቅለ መንግስቱን የምታደርጉት አሉ። ታንኮች ላይ እየወጡ ወታደሮችን ባዶ እጃቸውን መጋፈጥ ያዙ። በዚህ ቅፅበት ነበር ኤርዶጋን በአይሮፕላን እየተመለሰ ሳለ በስካይፒ በሲኤንኤን ቱርክ ላይ በቅ ያለው። " እኔ ደህና ነኝ እየመጣሁላችሁም ነው ጀግናው የቱርክ ህዝብም ይህን መፈንቅለ መንግስት ያክሽፍ" የሚል ትእዛዝ አስተላለፈ። የሀገሪቱ ህዝብ የመሪውን ድምፅ ሲሰማ ከዳር እስከ ዳር ተነቃነቀ። ብታምኑም ባታምኑም የሀገሪቱ 55% ህዝብ ወይንም 50 ሚሊዮን ህዝብ አደባባይ ወጣ። ኤርዶጋንም በፍፁም ጀግንነት በአደገኛ ሁኔታ ኢስታንቡል ተመለሰ። የመንግስቱ ደጋፊ ወታደሮች ፈንቃዮች ላይ የበላይነት መያዝ ጀመሩ። አየር ሀይሉ እርምጃ መውሰድ ጀመረ። F-16 የጦር ጄቶች በኢስታንቡል ሰማይ ላይ አጓሩ። ቱርክ ሌላ ሀገር መሰለች። ከታንክና ብረት ለበስ ተሽከሪካሪ ጋር ከተጋፈጡት ቱርካዊያን 300ዎቹ ለሀገራቸው መፅናት መስዋዕትነትን ከፈሉ። ኤርዶጋን በጀግንነት ስልጣኑን መልሶ ተቆጣጠረ። የፖሊስና ሌላው የፀጥታ ሀይል ያሳየው ጀግንነት እጅግ ከሚጠበቀው በላይ ነበር። ቱርክና ኤርዶጋን የዚያን ቀን ተረፉ። ከመፈንቅለ መንግስቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሁሉ እየተለቀሙ ታሰሩ። ኤርዶጋን ከመፈንቅለ መንግስቱ ጀርባ አሉ ካላቸው ምእራባውያን ጋር ተቃቃረ። ከዚያ በሗላ ኤርዶጋን ከመገናኛ ብዙሀን እስከ ጦር ተቋማት በጠቅላላ በእርሱ ቁጥጥር ስር እንዲገቡ ሆነ። እናም በህዝብ መስዋዕትነት እና በኤርዶጋን ቆራጥ አመራር ቱርክ የተረፈችበትን እለት ሰሞኑን እያሰበች ትገኛለች። ከዚያ በፊት ቱርክ ሁለት መፈንቅለ መንግስት የተደረጉባት ቢሆንም ይህኛውን ግን 50 ሚሊዮን የቱርክ ህዝብ አከሸፈው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
6 112
14
የፍልስጤም ወዳጇ ኮሎምቢያ በፅዮናዊ መሪ ስር ገብታለች። የነፃነት ድምፁና ጋዛ ድረስ ሂጄ እዋጋለሁ የሚለው ጉስታቮ ፔትሮም ከእንግዲህ የኮሎምቢያ መሪ አይደለም። ኮሎምቢያ ከእንግዲህ ሌላኛዋ አርጀንቲ+1
የፍልስጤም ወዳጇ ኮሎምቢያ በፅዮናዊ መሪ ስር ገብታለች። የነፃነት ድምፁና ጋዛ ድረስ ሂጄ እዋጋለሁ የሚለው ጉስታቮ ፔትሮም ከእንግዲህ የኮሎምቢያ መሪ አይደለም። ኮሎምቢያ ከእንግዲህ ሌላኛዋ አርጀንቲና ነች። በአሜሪካና እስራኤል ዘመም መሪዎች እጅ ከገቡት የላቲን አሜሪካ ሀገራትም አንዷ ሆናለች። ጉስታቮ ፔትሮ የስልጣን ዘመኑን ማጠናቀቁን ተከትሎ አቤላርዶ ዴ ላ ኢስፕሬላ የኮሎምቢያ መሪነትን አሸንፏል። በዚህም ኮሎምቢያ የእስራኤል ወዳጅ ሀገር ትሆናለች። አቤላርዶ ኮሎምቢያን የእስራኤል ጥብቅ ወዳጅ ሀገር አደርጋታለሁ ብሏል። በእስራኤል እና ኮሎምቢያ መካከልም ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንደሚፈፀም አረጋግጧል። ኮሎምቢያ ኢምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም እንደምታዘዋውርም አረጋግጧል። ኮሎምቢያ ከደቡብ አፍሪካ ጋር እስራኤልን በአለምአቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድቤት ከሳ እየተሟገተች የነበረ ቢሆንም አቤላርዶ ኢሶፕሬላ ግን ኮሎምቢያን ከዚህ ከሳሽነት እንደሚያወጣና ከእስራኤል ጎን እንደሚያሰልፋትም አስታውቋል። በጉስታቮ ፔትሮ መሪነት ኮሎምቢያ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን አቋርጣ የነበረች ሲሆን አለም አቀፍ ጦር ተቋቁሞ ለጋዛ እንዋጋ ስትል የነበረች ሀገር ነበረች። በአሜሪካ እና እስራኤል ደጋፊነት ወደ ስልጣን የመጣው አቤላርዶ ከእንግዲህ ልክ እንደ አርጀንቲናው ዣቪየር ሜሊዪ ሁሉ ሌላኛው ፅዮናዊ የላቲን መሪ ይሆናል። ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አቅምህ ሲፈረጥም ማንንም አንስተህ ማስቀመጥ ትችላለህ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
7 527
15
ኡስታዝ ሙሂቡዲን አጦበሪ በአልቢናእ የቲክቶክ ገፅ ላይ ሰፊ ዲናዊ ውይይት ያደርጋል። ገብታችሁ ለመከታተልና ለመወያየት በሚከተለው ሊንክ ጆይን ማድረግ ትችላላችሁ https://vt.tiktok.com/ZS9MEkYysbx59-SEu3W/
6 571
16
በአሁኑ ሰአት ስለዘረኝነት ማውራት ያለበት የመጨረሻው ህዝብ የአፍሪካ ህዝብ ነው። የአፍሪካን ያክል በዘረኝነት የተጨማለቀ አንድም ህዝብ የለም። በብሔር ተመራርጦ በየቀኑ ሲገዳደልና ሲተራረድ ነው የሚ
በአሁኑ ሰአት ስለዘረኝነት ማውራት ያለበት የመጨረሻው ህዝብ የአፍሪካ ህዝብ ነው። የአፍሪካን ያክል በዘረኝነት የተጨማለቀ አንድም ህዝብ የለም። በብሔር ተመራርጦ በየቀኑ ሲገዳደልና ሲተራረድ ነው የሚውለው። ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ ከምእራብ እስከ ምስራቅ ጫካውን የሞሉት ታጣቂዎችም ሆነ ቤተመንግስቱን የሞሉት ፖለቲከኞች በዘረኝነት የመጡ ለዘረኝነትም የሚኖሩ ናቸው። ኢትዮጵያ ላይ ያለውን የዘረኝነት እልቂት ያክል የት አለም አለ? እንኳን ሀገር ቤትና ኑሮ አስመርሮት በባህር ተሰዶ እንኳ የመን በረሀ ላይ በዘር ተመራርጦ የሚገዳደል ህዝብ ነውኮ ያለን። ደግሞ ትእቢትና ኩራታችንስ! ባዶ መኮፈሳችንስ ! በድህነትና መግደል የምንፎካከር እርጉሞች አይደለንም ወይ? በሀይማኖት መሪዎቹ ደግሞ ይብሳል! አፍሪካ ስታዩት መንፈሱ ራሱ ያስፈራል። ስለ ሱዳን እንኳን ማየት መስማት ይዘገንናል። ደቡብ ሱዳን ውስጥ በዘር ተቧድነው እሳት ውስጥ በማቃጠልኮ ነው የሚቀጣጡት! ኮንጎ እንደት ያለ የዘር ጭካኔ ምድር! ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰው ቀረጣጥፈው እሳት እያነደዱት የሚሞቁ ጎበዞች ያሉበት ነው። ደቡብ አፍሪካ ያለ ዘረኝነት ክርፋቱ! ቻድ ፣ ማሊ ፣ ቤኒን ስንት ቀፋፊ ነገር ነው ያለው! ናይጀሪያ ሁሌም ከሞትና እገታ ነፃ የማይወጣ የዘርና ሀይማኖት ግጭት ማእከል! ሰሜን አፍሪካ ብትሄዱ ራሳቸውን እንደ አፍሪካም አያዩም። ጥቁርነትን ይፀየፋሉ። ሞሮኮ በበርበሮች ላይ ምንድነው የምታደርገው? ሊቢያ ላይ ጥቁሮች ምንድነው የሚደርስባቸው?! እና አዩሀል አፍሪካውያን ወ ኢትዮጵያን ስለ ሌላው አለም ዘረኝነት ያውም አጋናችሁ ለማውራት ስትሞክሩ ታስቃላችሁ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
7 022
17
አርጀንቲና ኬበቀለቻቼው የነፃነት ሰዎች የእኩልነት ሰባኪዎች አንዱ አቡነ ፍራሲስ ኩዝ ነበሩ። እርሳቸው ከአርጀንቲና የተገኙ የካቶሊክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ ለሰው ልጆች ሰላም ፤ ስለ ፍትህ ፤ ስ+3
አርጀንቲና ኬበቀለቻቼው የነፃነት ሰዎች የእኩልነት ሰባኪዎች አንዱ አቡነ ፍራሲስ ኩዝ ነበሩ። እርሳቸው ከአርጀንቲና የተገኙ የካቶሊክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ ለሰው ልጆች ሰላም ፤ ስለ ፍትህ ፤ ስለ ሰው ልጆች እኩልነትና ስለ ጭቁኖች ነፃነት ሲታገሉ የነበሩ ዴግ መሪ ነበሩ። በተለይም ለፍልስጤማውያን ያላቸው እዝነትና መቆርቆር ይለይ ነበር። እርሳቸው በተለይ ወረራው ወቅት ሁሌ ማታ እየደወሉ ፍልስጤማውያንን ያናግሩ እርዳታም ይልኩ ነበር። ሊሞቱ ሰአታት በቀራቸው ወቅትም " ትላንት ህፃናት በቦምብ እየጋዩ ነበር ። ይህ አረመኔነት እንጅ ጦርነት አይደለም ። ህፃናቱ የሚፈፀመው ጭካኔ ልቤን ስለሚነካኝ ልናገረው ወደድኩ " ።ጳጳሱ ይህን የተናገሩት ትንፋሽ እያጠራቸው እየተዳከሙ ነበር። አቡነ ፍራንሲስ ሲሞቱ የሚጓዙባት መኪና ወደ አምቡላንስነት ተቀይራ ለጋዛዊያን ትሰጥ ዘንዳ ተናዘው ነው የሞቱት። እናም ኑዛዚያቸውም ተፈፀመ። ጳጳሱ የቀብር ስነስርአታቸው ሲፈፀምም በፍልስጤም ባንድራ ታጅበው አርጀንቲናዊ ወይንም ቫቲካናዊ ሳይሆን ፍልስጤማዊ መስለው ነበር የተሸኙት። አቡነ ፍራንሲስ ላበረከቱት ደግነት ሁሌም በነፃነት ወዳዶች ዘንድ ይታወሳሉ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
7 480
18
ጋዛዊያን ከፍርስራሹ ስር የአርጀንቲና እና እንግሊዝን ጨዋታ እንዲህ ደምቀው ሲመለከቱና ሲደግፉ ነበር። ህይወት መሪር በሆነችባት ፤ ሀዘንም ከሰማይ ባጠለለባት ጋዛ እግርኳስን የሚወደው ህዝቧ የማራዶና
ጋዛዊያን ከፍርስራሹ ስር የአርጀንቲና እና እንግሊዝን ጨዋታ እንዲህ ደምቀው ሲመለከቱና ሲደግፉ ነበር። ህይወት መሪር በሆነችባት ፤ ሀዘንም ከሰማይ ባጠለለባት ጋዛ እግርኳስን የሚወደው ህዝቧ የማራዶናዋ ሀገር እንግሊዝ ጋር ያደረጉትን ትንቅንቅ እንዲህ ነበር ያዩት። አላህ ለነዚህ ህዝቦች ሰላማቸውን ደስታቸውን ይመልስላቸው!
6 342
19
ዛሬ እንግሊዝ እና አርጀንቲና የሚያደርጉት ጨዋታ አይደለም ጦርነት ነው። የሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ሁልጊዜም ሲገናኙ ውጥረቱ እጅግ ይበረታል። ከእግርኳስ ይልቅ ፖለቲካዊው ሽኩቻ አይሎ የፎክላንድ
ዛሬ እንግሊዝ እና አርጀንቲና የሚያደርጉት ጨዋታ አይደለም ጦርነት ነው። የሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ሁልጊዜም ሲገናኙ ውጥረቱ እጅግ ይበረታል። ከእግርኳስ ይልቅ ፖለቲካዊው ሽኩቻ አይሎ የፎክላንድ ጦርነት ዳግም በእግርኳስ ሜዳ ይስተናገዳል። ከዛሬ 40 አመት በፊት በማራዶና የሚመራው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን እንግሊዝን አሸንፎ የአለም ዋንጫን ሲበላ አርጀንቲናዊያን ከ ዚያ ጨዋታ 4 አመት በፊት በእንግሊዝ የደረሰባቸውን ሽንፈት የተበቀሉ ነበር የመሰላቸው። ፎክላንድ ከአርጀንቲና አጠገብ የምትገኝ ደሴት ነች። አርጀንቲና ደሴቷን ግዛቴ ናት ስትል እንግሊዝ በበኩሏ ሺህ ኪሎሜትር ርቃ አርጀንቲና አጠገብ ሂዳ ፎክላንድን የኔ ነው አለች። በዚህ ጊዜ አርጀንቲና ፎክላንድን በሀይል ተቆጣጠረች። የአርጀንቲናው መሪ ጄኔራል ሊዮፖልዶ ጋልታየሪ ፎክላንድ ሲይዝ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቼር 127 የጦር መርከብና በርካታ የጦር አይሮፕላኖችን ወደ አርጀንቲና በመላክ ከአርጀንቲና ጋር ከባድ ጦርነት ገጠሙ። በ 1982 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የተካሔደው ይህ ጦርነት ለ 74 ቀናት ያለማቋረጥ ተደረገ ። በጦርነቱ እንግሊዝ 6 የጦር መርከቦችን ጨምሮ 10 የጦር አይሮፕላኖችን 24 ሄሊኮፕተሮችን ፣ በርካታ ታንኮችን ስታጣ አርጀንቲና ከ 6 በላይ መርከቦችን ከ 50 በላይ የጦር አይሮፕላኖችን 24 ሄሊኮፕተሮችን ጨምሮ በርካታ ኪሳራዎችን አስተናገደች። በጦርነቱ 649 የአርጀንቲና ወታደሮች ሲገደሉ 255 የእንግሊዝ ወታደሮችም ተገደሉ። ጦርነቱም በእንግሊዝ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። እናም አርጀንቲና እና እንግሊዝ ያደረጉት ያ ከባድ ጦርነት ዛሬ ላይ ላላቸው የእግርኳስ ባላንጣነት ዳርጓቸዋል። ሁለቱ ሀገራት ዛሬም ሲገናኙ ድባቡ በዚህ የጦርነት ቁጭት ተሞልቶ ነው። t.me/Seidsocial
7 622
20
በታሪክ በጥቁሮች ላይ እጅግ ከፍተኛ በደል ከፈፀሙና በጥቂርነታቸው ብቻ የአንድን አህጉር ህዝብ ወደ ባርነት ከቀየሩ ሀገራት መካከል ፖርቹጋልን የሚስተኣከላት አንድም ሀገር የለም። ፖርቹጋል በአለም ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድን ገና በ 1440 በመጀመር በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ጥቁሮችን በማደን ወደ ብራዚል ፣ አርጀንቲና ፣ ሰሜን አሜሪካና ካሪቢያን በማጓጓዝ በጥቁሮች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን ጠባሳ ፈፅማ ያለፈች ሀገር ነች። የፖርቹጋል የጥቁር ግፍ ያበቃው ከዛሬ 50 አመት በፊት ብቻ ነበር። ከፖርቹጋል በመቀጠል ቤልጅየም ስፔይን እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በቅደም ተከተል ይከተላሉ። እነዚህ አውሮፓውያን ሀገራት በአፍሪካውያን ላብ በአፍሪካውያን የተፈጥሮ ሀብት በመካበት በአለም ላይ ቀዳሚዎቹ ሀብታሞች ለመሆን በቅተዋል። እነ ፖርቹጋል ከአርጀንቲና እስከ ካናዳ ድረስ እያጋዙ የሸጧቸው ባሪያዎች 50 ሚሊዮን አካባቢ ሲሆን ይህም የአፍሪካን እድገት በማጨለም ህዝቡን በማመናመንና ማህበራዊ ስሪቱን በማፍረስ በሗላም ለቅኝ ግዛት እንዲመቻች አድርገውታል። ወደ ላቲን እና ሰሜን አሜሪካ የሚጓዙት ባሪያዎች በጣሙን በሚያሳዝን መልኩ እግራቸው ከሆነ ለአግልግሎት የሚፈለገው እጃቸው ይቆረጣል እጃቸው ከሆነ ደግሞ እግራቸው ተቆርጦ እዚያ ቦታ ላይ ሆነው እስኪሞቱ ድረስ ያለ እረፍት ይሰሩ ነበረ። እዚያ የሄዱት ባሪያዎች ከፍተኛ መገለል መናቅና መሸማቀቅ ይደርስባቸው ነበር አሁንም ድረስ! ፖርቹጋል እና ስፔይን በአብዛኛው በጋራ በመንቀሳቀስ ኢስላምና አይሁዶችን ከአውሮፓ ምድር የማጥፋት ዘመቻንም በመምራት አሁን ያለውን ሀገራቸውን ምስል ፈጥረዋል። ቤልጅየም ከኮንጎ ምድር ጥቁሮችን ለማጥፋት በፈፀመቺው ዘመቻ ብቻ ከ 15 ሚሊዮን በላይ ኮንጓዊያንን ጨርሳለች። የእንግሊዝ እና ፈረንሳይ ያው የሚታወቅ ነው። በባርነት ሲጓዙ ለማምለጥ የሚሞክሩ አፍሪካዊያን ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ይወረወሩና የአሳ ቀለብ ይሆኑ ነበር። በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ተጥለዋል። በሽታ የጨረሳቸው ሚሊዮናትም ረግፈው ቀርተዋል። ውሸት የመሰለው በማስረጃ ይሞግተኝ! ላቲን አሜሪካ ማለትም አርጀንቲና ፣ ብራዚል ፣ ኮሎምቢያ ፣ ቺሊ፣ ፓራጓይ ወዘተ የመሳሰሉ ሀገራት ላይ የጥቁሮች ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
6 725