ar
Feedback
Seid Social

Seid Social

الذهاب إلى القناة على Telegram

አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Seid Social

تُعد قناة Seid Social (@seidsocial) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 23 211 مشتركاً، محتلاً المرتبة 10 164 في فئة الأخبار والوسائط والمرتبة 1 484 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 23 211 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 04 سبتمبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -32، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 11، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 33.51‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 19.09‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 7 778 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 4 431 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 132.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 05 سبتمبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الأخبار والوسائط.

23 211
المشتركون
+1124 ساعات
-167 أيام
-3230 أيام

جاري تحميل البيانات...

سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
سبتمبر '26
سبتمبر '26
+25
في 2 قنوات
أغسطس '26
+616
في 4 قنوات
Get PRO
يوليو '26
+106
في 8 قنوات
Get PRO
يونيو '26
+206
في 4 قنوات
Get PRO
مايو '26
+126
في 3 قنوات
Get PRO
أبريل '26
+551
في 9 قنوات
Get PRO
مارس '26
+1 965
في 10 قنوات
Get PRO
فبراير '26
+956
في 4 قنوات
Get PRO
يناير '26
+498
في 2 قنوات
Get PRO
ديسمبر '25
+1 320
في 4 قنوات
Get PRO
نوفمبر '25
+379
في 2 قنوات
Get PRO
أكتوبر '25
+816
في 8 قنوات
Get PRO
سبتمبر '25
+730
في 10 قنوات
Get PRO
أغسطس '25
+194
في 3 قنوات
Get PRO
يوليو '25
+372
في 13 قنوات
Get PRO
يونيو '25
+1 733
في 12 قنوات
Get PRO
مايو '25
+606
في 6 قنوات
Get PRO
أبريل '25
+1 100
في 9 قنوات
Get PRO
مارس '25
+675
في 5 قنوات
Get PRO
فبراير '25
+241
في 8 قنوات
Get PRO
يناير '25
+690
في 8 قنوات
Get PRO
ديسمبر '24
+1 128
في 10 قنوات
Get PRO
نوفمبر '24
+390
في 5 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+1 058
في 10 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+603
في 9 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+302
في 10 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+361
في 12 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+167
في 6 قنوات
Get PRO
مايو '24
+518
في 15 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+611
في 8 قنوات
Get PRO
مارس '24
+187
في 5 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+262
في 4 قنوات
Get PRO
يناير '24
+289
في 7 قنوات
Get PRO
ديسمبر '23
+378
في 4 قنوات
Get PRO
نوفمبر '23
+533
في 9 قنوات
Get PRO
أكتوبر '23
+496
في 3 قنوات
Get PRO
سبتمبر '23
+118
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '23
+159
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '23
+155
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '23
+230
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '23
+525
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '23
+95
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '23
+142
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '23
+88
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '23
+135
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '22
+90
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '22
+141
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '22
+229
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '22
+384
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '22
+424
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '22
+241
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '22
+376
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '22
+182
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '22
+337
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '22
+535
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '22
+74
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '22
+12
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '21
+17
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '21
+40
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '21
+384
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '21
+688
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '21
+615
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '21
+452
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '21
+338
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '21
+1 104
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '21
+150
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '21
+152
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '21
+367
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '21
+437
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '20
+1 820
في 0 قنوات
التاريخ
نمو المشتركين
الإشارات
القنوات
05 سبتمبر+2
04 سبتمبر+13
03 سبتمبر+6
02 سبتمبر+2
01 سبتمبر+2
منشورات القناة
የኢትዮጵያ ባህል እና ማንነት ስንል የኦሮሞውም ፣ የአማራውም ፣ የትግራዩም ፣ የሶማሌውም ፣ የአፋሩም ፣ የደቡቡም የሁሉም ባህልና ማንነት ውህድ ማለታችን ነው። ኢትዮጵያ ከነዚህ ብሔሮቿ ማንነት ውጭ
የኢትዮጵያ ባህል እና ማንነት ስንል የኦሮሞውም ፣ የአማራውም ፣ የትግራዩም ፣ የሶማሌውም ፣ የአፋሩም ፣ የደቡቡም የሁሉም ባህልና ማንነት ውህድ ማለታችን ነው። ኢትዮጵያ ከነዚህ ብሔሮቿ ማንነት ውጭ ሌላ ማንነት የላትም። አንድን ሰው ኢትዮጵያዊ የሚያስብለውም ከነዚህ ስብጥር ማንነቶቿ በአንዱ ሲወከል ወይንም የአንዱ ሲሆን ነው። የአንዱ ብሔር ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አካል ነው። ብቻውን ግን አይደለም። በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አካላት ከነዚህ ስብጥር ማንነቶቿ አንዱን ቢያንፀባርቁና ቢያሳዩ የወከሉትም ያንፀባረቁትም ከኢትዮጵያ ውህድ ማንነቶቿ አንዱን ነውና እነዚያ የኢትዮጵያ ወኪሎች ናቸው። እያንዳንዷን ቅፅበት በመጠቀም የበለጠ ህዝብን ከህዝብ ለማራራቅ የበለጠ ለማጣላት የበለጠ በጥርጣሬ እንዲንተያይ ለማድረግ የሚዘምቱ አካላትን ተሰሚነት ማሳጣት ከሁላችንም የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው። የኢትዮጵያ ማንነት የህዝቦቿ ማንነት እንጅ ሌላ አይደለም። እያንዳንዱ የህዝቧ ባህልም ኢትዮጵያዊነትን ይወክላል። ይህች ልጅም ያሳየቺው የባህል ልብስ ከፍተኛ አድናቆትና ሙገሳን የሚገባት የሚያደርግ እንጅ የሚያስተቻት አንድ እንኳ ምክንያት የለም። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

2
የቤልጅየሟ ከተማ ሊዩቨን የእስራኤል ክለብ በከተሜዋ የኢሮፓ ሊግን እንዳይጫወት እገዳ ጥላለች። የእስራኤሉ ክለብ ሀፒዮል ቤር ሼባ ከቤልጅየም ክለብ ጋር የኢሮፓ ሊግ ጨዋታ ያለበት ቢሆንም የከተማዋ መ+1
የቤልጅየሟ ከተማ ሊዩቨን የእስራኤል ክለብ በከተሜዋ የኢሮፓ ሊግን እንዳይጫወት እገዳ ጥላለች። የእስራኤሉ ክለብ ሀፒዮል ቤር ሼባ ከቤልጅየም ክለብ ጋር የኢሮፓ ሊግ ጨዋታ ያለበት ቢሆንም የከተማዋ መሪ ሙሀመድ ሪድዋኒ ግን በጭራሽ የእስራኤል ክለብ በስቴዲየም አይጫወቱም ብሏል።በዝግ ስቴዲየም እንኳ እንደማይፈቀድላቸው ነው የገለፀው። የቤልጅየም የትምህርት ማእከል የሆነቺው ሊዩቨን ከንቲባ ሙሀመድ ሪድዋን የእስራኤልን ክለብ የፀጥታ ስጋት በመሆኑ በከተማችን አናስተናግድም ብሏል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
3 838
3
፨ ዞህራን ማምዳኒ አሜሪካ አልተወለደም። በዘሩም አሜሪካዊ አይደለም። ሀይማኖቱ ሙስሊም ዘሩ ህንዳዊ ተወልዶ ያደገው ዩጋንዳ ሲሆን አሜሪካ ገብቶ የአሜሪካ ዜጋ ሆኖ በፖለቲካው ዘርፍ ያደረገው የነቃ ተሳትፎና ለኒውዮርክ ከተማ ህዝብ ይዞት የቀረበው አስደናቂ ፖሊሲና ሀሳብ የኒውዮርክ ገዢ እንዲሆን አስቻለው። ዘሩም ብሔሩም ሀይማኖቱም ብቃቱን ደፍጥጦ ከአመራርነት አላስቀረውም። ኒውዮርካዊያን ከሀሳቡና ፖሊሲው እንጅ ከዘሩ ደንታ አልነበራቸውም! ፨ ቦሪስ ጆንሰን የኦቶማኑ ባለስልጣን አሊ ከማል የልጅ ልጅ ልጅ የሆነ ትውልደ ቱርካዊ ቢሆንም በእንግሊዝ ላይ የፖለቲካ ቁንጮ ሆኖ እንግሊዝን ከመምራት አልከለከለውም! ፨ ባራክ ኦባማ ከኬኒያ ዘሩ የሚመዘዝ የተወለደውም ኬኒያ ቢሆንም ከአሜሪካ ታላላቅ ፕረዚዳንቶች አንዱ ከመሆን ዘሩ አልከለከለውም! ፨ ሪሺ ሱናክ ዘሩ ህንዳዊ ቢሆንም የእንግሊዝ መሪ ከመሆን አልከለከለውም! ፨ ሷዲቅ ኻን ዘሩ ፓኪስታን ሀይማኖቱ ሙስሊም ቢሆንም ታላቋን የአለማችን ከተማ ለንደንን ከመመምራት አልከለከለውም። ለንደንም በጣም ስኬታማ ከሆኑ መሪዎቿ አንዷ አድርጋ ይዛዋለች። ፨ ሰርጌ ላቭሮቭ ዘሩ አርሜናዊ ቢሆንም የሩሲያን የውጭ ግንኙነትና ድፕሎማሲ በመምራት ምናልባትም ከፑቲን በመቀጠል የሩሲያ መልክ የሆነ በአለማችንም ካሉ ስል ድፕሎማቶች አንዱ ነው። እንዲህ እንዲህ እያልን በሰለጠነው አለም ብቃት እስካለህ ድረስ መሪያቸው ሊያደርጉህ ፤ የኢኮኖሚ ማማ ላይ የቴክኖሎጂ መሪነትንም ሊያቆናጥጡህ ቅር እንደማይላቸው ማሳያ ነው። የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ጂያንቶች 60% መሪዎቹ አሜሪካ ያልተወለዱ ዘራቸው ከሌላ የሚመዘዝ የቴክኖሎጂና የቢዝነስ መሪዎች ናቸው። አውሮፓ ብትሄዱ ካናዳ ፤ አውስትሪያ ኒውዚላንድ በአጠቃላይ የሰለጠነው አለም እንዲያ ነው። ብቃት ይኑርህ አንተንም ህዝብንም የምትጠቅም ሀገራቸውን የምታኮራ ሁን ከፍ አድርገው ይጠብቁሀል። እኛ ሀገር እሳ!!?? ለማሰብም ይዘገንናል! ያው ያልሰለጠነ ማህበረሰብ አንዱ መገለጫው በዘርና ብሔርተኝነት ልጓም መለጎም ነውና ሁሉም ነገር ላይ በዘር ነው የምትመዘነው! ዶክተርነት በብሔር ኮታ ነው! አመራርነት በብሔር ኮታ ነው! ዲፕሎማትነት በብሔር ኮታ ነው! የሀይማኖት መሪነት በብሔር ኮታ ነው! አስቀዳሽ አሰጋጅ ኢማምና ቄሱም በብሔር ኮታ ሆነዋል! የትም ተቀጠር ብሔር ካርድ ተመዞ ነው! ሁለ ነገሩ በዘረኝነት የጠነባ ሀገር የጠነባን ህዝቦች የጠነባ ስርአት! ደግሞ የሚያሳዝነው እየባሰብን ነው እየሄድን ያለነው! አለም ሌላ የቴክኖሎጂ መራቀቅ ላይ እየተሽቀዳደመ ፤ በጣም ክህሎት ያላቸውን የትኛውንም ሰው የራሱ ለማድረግ እየታገለ እኛ እዚህ ዘር እየቆጠርን ከመገዳደልና ከመፎካከር የዘለለ ወይ ፍንክች! አሁንማ ፀሀዩ መንግስታችን ትምህርትንም እየገደለልን ነው ስራንም እያጠፋልን ነው ኑሮንም አሪፍ አድርጎ እያስወደደልን ነው ገና ዘር እየቆጠርን እንተናነቃታለን! አቤት ቅዱስነታችን¡ ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
4 907
4
የውጭጉዳይ ሚኒስትር የዲፕሎማቲክ አታሼ ማስታውቂያ 100 አመልካቾችን እፈልጋለሁ ብሎ ማስታወቂያ አውጥቶ ከማመልከቻ መስፈርቶች አንዱ ብሔር ነው። ብሔር የግድ ካልሞላችሁ የስራ ማመልከቻውን ማመልከት+1
የውጭጉዳይ ሚኒስትር የዲፕሎማቲክ አታሼ ማስታውቂያ 100 አመልካቾችን እፈልጋለሁ ብሎ ማስታወቂያ አውጥቶ ከማመልከቻ መስፈርቶች አንዱ ብሔር ነው። ብሔር የግድ ካልሞላችሁ የስራ ማመልከቻውን ማመልከት አትችሉም። እንግዲህ ዲፕሎማቲክ አታሼ ሀገራችሁን በአለምአቀፍ መድረክ ወክላችሁ በወታደራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፤ ንግድና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ከሀገራት እና አለምአቀፍ ተቋማት ጋር የምትሰሩበት ሀገራችሁን የምትወክሉበት ለሀገራችሁ መረጃና ጥናት የምታቀርቡበት ዘርፍ ነው። እናም ይህ ዘርፍ እንኳ ከብሔር ጦስ አልተረፈም። ብቻ የዚህች ሀገር ፖለቲካ የዚህች ሀገር ስርአት ግም ነው።ተስተካክሎ አያውቅም። የሀገሪቱን ጥቅም አስቀድሞ አያውቅም። የሀገሪቱን ውህደት አፋጥኖ አያውቅም! ሁሌም ከፋፍሎ ለስርአቱ ማራዘሚያ እንደሆነ የሚቀጥል ግም ስርአት ነው ለመቶ አመታት የተዘፈዘፈባት። ሀይማኖተኝነቷም ብሔርተኝነቷም ከመጥቀም ይልቅ ያደኸዪዋት ያቆረቆዟት ያነቀዟት የግፍና ክፋት መሳሪያ የሆኑባት ሀገር ተምሳሌት ነች። ይህቺ ሀገር ግን ኤጭ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 095
5
በሳኡዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እነዚህን አረመኔዎች ከሳኡዲ የፀጥታ ሀይል ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉ በጣም የሚያስመሰግነው ትልቅ ሰስራ ነው። እስካሁን ያ ልጁን እባክህን ለ+4
በሳኡዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እነዚህን አረመኔዎች ከሳኡዲ የፀጥታ ሀይል ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉ በጣም የሚያስመሰግነው ትልቅ ሰስራ ነው። እስካሁን ያ ልጁን እባክህን ለእናቴ አንድ ነኝ አትግደለኝ እያለ እየተማፀነ ያረደው አውሬና 5 ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ቲክቶክ ላይ እረደው ግደለው እያሉ ሞትን ሲነግዱ የነበሩ ከ 100 በላይ አረመኔዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። እንግዲህ ሳኡዲ ላይ የገደለ ፍርዱና ቅጣቱ ምን እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነውና አንጀት ያርሳል። እንኳንም ፍርዳቸው ሳኡዲ ላይ ሆነ! ይህ ሌሎች እንዲህ እየጨከንን እንቀጥላለን ማንም አይደርስብንም ለሚሉ ደም ጠጮች ትልቅ ትምህርት ነው። በሳኡዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲህ አይነት ጥረቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የንፁሀንን ህይወት እንዲታደግ የሁላችንም ጥሪ ነው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
6 613
6
ኢማም አልቡኻሪ ልክ በዛሬዋ እለት በ 60 አመታቸው ይህችን አለም በሞት ተለዩ! ታላቁ ፐርሺያዊው ( ኢራናዊው) አሊም እና ሙሀዲስ ኢማም ሙሀመድ ኢብን ኢስማኢል አልቡኻሪ በኢስላም ውስጥ ሀዲስን በመሰብሰብና በመሰነድ እጅግ ወደር የለሽ ከሆኑ ሙሀዲሶች ቀዳሚው ናቸው። ኢማም አልቡኻሪ የተወለዱት በ 810 በያኔዋ ኹራሳን በዛሬዋ ኡዝቤክስታ በምትገኘው ቡኻራ ከተማ ነው። የኢማም አልቡኻሪ ቅድመ አያት በርደዝበህ የዞራስተራኒዝም ወይንም መጁሳ ትልቅ የሀይማኖት አባት (ማጊ) የነበሩ ሲሆን አያታቸው አልሙጊራ ሀይማኖታቸውን ከመጁሳ ወደ ኢስላም በመቀየር መኖሪያቸውንም ቡኻራ ከተማ አድርገዋል። የኢማም አልቡኻሪ አባት ኢስማኢል ግን ትልቅ አሊም እና በአብደላህ ኢብኑ ሙባረክ እና ማሊክ ኢብኑ አነስ ላይ የዲን ትምህርትን ጥንቅቅ አድርገው የተማሩ ነበሩ። አባታቸው በልጅነታቸው የሞተባቸው ኢማም አልቡኻሪ የአባታቸውን ፈለግ ተከትለው ገና በህፃንነታቸው ነው ኢልምን ማሳደድ የጀመሩት። እናታቸውና ታላቅ ወንድማቸው መካ ለሀጂ ይዘዋቸው ሲመጡ ደግሞ መንገዶች የበለጠ ተመቻቹላቸው። ለኢማም አልቡኻሪ የኢልም ጉዞ እናታቸው የማይተካ ሚና ነበራቸው። ኢማም አልቡኻሪ ሙሀመድ ኢብኑ ኢስማኢል መካ ከደረሱ በሗላ እዚያው ቀሩና ኢልምን ማካበት ጀመሩ። እዚያ እያሉ ነበር ቀዲያ አሶሀባ ወታቢኢን የፃፉት። ከዚያ ወደ መዲና በማምራትም ኢልም በመቅሰም አታሪኽ አልአክበርን ፅፈዋል። ከዚያ በሗላ ኢማም አልቡኻሪ የኢልም ሀገሮች አልቀሯቸውም። ከባግዳድ እስከ ግብፅ ፤ ከኩፋ እስከ የመን ፤ ከበስራ እስከ ሶሪያ የሙስሊሙ የኢልም ማእከላትን በጠቅላላ በማዳረስ የነብያችንን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሀዲሶች ሰበሰቡ። ከነ ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል ፤ የህያ ኢብኑ ሙኢን ፣አሊ ኢብን አል መዲኒ ወዘተ ኢልምን ቀሰሙ። ኢማም አልቡኻሪን ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር የሂፍዝ ተሰጥኦቸው ነበር። ኢማሙ ከ 600,000 በላይ ሀዲሶችን የሰበሰቡና የሀፈዙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አጣርተው ሶሂህ የሆኑትን ብቻ ለይተው 7,275 ሀዲሶችን ብቻ በኪታባቸው አስተላልፈውልናል። ያ ኪታባቸውም ከቁርአን በሗላ ያለው ትልቁ ኪታብ ተብሎላቸዋል ኢማሙ ለኢልም የተሰጡ ለሀቀኝነት ብቻ የኖሩ ሙሀዲስ ነበሩ። በሀዲስ ስብሰባ ጉዟቸው ከተፈጠሩ ነገሮች አንዱ ሲወራ በእጅጉ የሚደንቅ ነው። እናታቸው ሀዲስን ከሀገር ሀገር ተንከራተው ሲፈልጉ እንዳይቸገሩ ብለው 15,000 ዲናር ሰጥታቸው ነበር። እናም በጀልባ እየተጓዙ ሳለ አንድ ይሄን ያክል ገንዘብ እንዳላቸው ያወቀ ሰው 15,000 ዲናሬን ይሄ ሰው ሰርቆኛል ብሎ ጮኸ። በዚህ ጊዜ ኢማሙ የያዙትን ገንዘብ ቀጠቅላላ ባህር ውስጥ ጣሉት ያገንዘብ የባህር ሲሳይ ሆነ። ያ ቀጣፊ ሰውየ ደነገጠ። እንደት ይህን ሁሉ ገንዘብ ባህር ውስጥ ትጥላለህ አላቸው። እርሳቸውም የኔ በሆነ ገንዘብ ተከራክሬ ማስመለስ ብችልም ግና ሰርቆ ነበር የሚል ጥርጣሬ ሰዎች ዘንድ ከተሰማ ሀዲሶቼ ጥርጣሬ ውስጥ ይገባሉና ይህን አደረኩት አሉ ይባላል። ኢማም አል ቡኻሪ አላህ ምድር ላይ ካመጣልን ሶጦታዎች አንዱ ናቸው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 838
7
የሰዎች ጉዳይ ከራሷ በላይ የሚያሳስባትና የተቸገሩን ለመርዳት ብዙ ስትለፋ የምናውቃት ሀያት አሁን ላይ ወደ ንግድ ገብታ ለመስራት እየታተረች ትገኛለች። እርሷን ማበረታታት መግዛት ደግሞ ከእኛ የሚጠበ+4
የሰዎች ጉዳይ ከራሷ በላይ የሚያሳስባትና የተቸገሩን ለመርዳት ብዙ ስትለፋ የምናውቃት ሀያት አሁን ላይ ወደ ንግድ ገብታ ለመስራት እየታተረች ትገኛለች። እርሷን ማበረታታት መግዛት ደግሞ ከእኛ የሚጠበቅ ነገር ነውና እርሷን በመግዛትና ስራዋን በማስተዋወቅ እንዲናበረታታት ይሁን። የተለያዩ የአዋቂና በየትኛውም እድሜ ያሉ የልጆች ልብሶችን ፤ ቦርሳዎችን ፤ ቆንጆ የምሳ እቃዎችን እርሷ ጋር ታገኛላችሁ። በተለይ ደቡብ ወሎ አቀስታ ያላችሁ ግዟት አበረታቷት። በስልክ ቁጥር 0910835315 ታገኟታላችሁ በቴሌግራም አካውንቱ @Umusitrella ኮንታክት አድርጓት። የትግራም ግሩፕም አላት 👇 https://t.me/hayushope
6 141
8
የዚህ ቴሌግራም ቤተሰባችንና ወንድማችን ኢብራሂም እንደሻው ልጅ ኢስሀቅ ኢብራሂም 553.75 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ትጉሆች አንዱ ነው። ኢብሮ እንኳን ደስ ያለህ አላህ
የዚህ ቴሌግራም ቤተሰባችንና ወንድማችን ኢብራሂም እንደሻው ልጅ ኢስሀቅ ኢብራሂም 553.75 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ትጉሆች አንዱ ነው። ኢብሮ እንኳን ደስ ያለህ አላህ የበለጠ ትልቅ ስኬትንና ደረጃን ያጎናፅፈው ምኞቴ ነው!
5 699
9
ረቢኡል አወልን ኡለሞች ረቢኡ ነበውይ ይሉታል። ለምን ከተባለ ከነብያችን አለይሂ ወሰለም ህይወት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ወር ነው። በእርሳቸው ሀያት የተፈፀሙ ትልልቅ ክስተቶች በአብዛኛው የተከሰቱት በ
ረቢኡል አወልን ኡለሞች ረቢኡ ነበውይ ይሉታል። ለምን ከተባለ ከነብያችን አለይሂ ወሰለም ህይወት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ወር ነው። በእርሳቸው ሀያት የተፈፀሙ ትልልቅ ክስተቶች በአብዛኛው የተከሰቱት በረቢኡል አወል ነው። 1 የተወለዱት በረቢኡል አወል ነው! 2 ለመጀመሪያ ጊዜ የወህይ ህልም ያዩት በረቢኡል አወል ነው! 3 ወደ መዲና የተሰደዱት በረቢኡል አወል ነው! 4 ለመጀመሪያ ጊዜ መስጅዳቸውን መስጅዴ ኘበውይን እና መስጅደል ቁባንም የገነቡት በረቢኡል አወል ነው! 5 ኢላ ረፊቂል አእላ ብለውም ወደጌታቸው የሄዱበት ይህችን ዱኒያ የተሰናበቱበትም ወር ይሄው ወር ነው። በአለማችን ላይ የነብያችንን ስም ለማጠልሸት ፤ የተላኩበትን የእዝነት መንገድ ስም ለማጥፋት ፤ ስብእናቸው ላይ ለመቅጠፍ ከ 60,000 በላይ መፅሀፍፍቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ፊልሞችና የካርቶን ምስሎች ተሰርተዋል። ይሁን እንጅ በአለም ላይ አሁንም ቢሆን የእርሳቸውን ያክል ተወዳጅ ተፅእኖ ፈጣሪና ብዙዎች ገና ስማቸውን ሲጠሩ እንባቸው የሚጎርፍላቸው ሰው የለም! እርሳቸው በፈጣሪም በፍጡርም እጅግ የተወደዱት ሰው ናቸው። በአለም ላይ የእርሳቸውን ስም ያክል መቶ ሚሊዮኖች ያወጡት ስም የለም። ስማቸው ይጣፍጣል! የእዝነት መልእክታቸውን ላነበበ ማንም አለመማረክ አይችልም። አላህም የእርሳቸውን መላክ ዋና አላማ ሲናገር " ለአለማት እዝነት አድርገን እንጅ አላክንህም" ይላቸዋል። ለፍጥረት ሁሉ አዛኝ ነበሩ። ለእንሰሳቱ ለሰው ዘርና ቀለም ፤ ሀይማኖትና ጎሳ ሳይለዩ የሚያዝኑ ሩህሩህ ነበሩ። ያያቸው ሁሉ የሚወዳቸው ሰው ነበሩ። እስከዚህ ተብሎ ሊደካ የማይችል ውደታ! የሚተናነሱ ነበሩ። ዛሂድ ነበሩ! ገመና ከታች አበሳሪ ነበሩ። ማክበርን ጥንፍፍነትን ያስተማሩ የጨዋ ጨዋ ፤ የለጋስ ለጋስ! ምስል :- በጣም የምወዳቸው ሸይኽ ሙሀመድ ሀሰን አልደደው
5 926
10
ግን አሁን ላይ እንደኛ እንደ ሙስሊሞች አደብ ያጣ ስነምግባር የጎደለው አለ ወይ? ኧረ ተው እንኳን ከኢስላማዊው ከሰዋዊው የስነምግባር ሀዲድ እየወጣን ነው! የሰዎችን ግለሰባዊ መብቶችን ሁሉ ጨፍለቀን አልፈን ስለሁሉም የግል ህይወት ካልፈተፈትን እያልን ነው! ሰዎች የሚያገቡትን መምረጥ ያምረናል! እኛ ራሳችንን የኢማን መስፈርት የኢማን ውሀልክ አድርገን ሌሎቹን እየለካን ነው! ምላሳችን የሞተሰ ሰው እንኳ አያስቀምጥም! መሻኣኾች ባለፉ ቁጥር ለምን አላህ ይማራቸው ትላላችሁ እያሉ ስንት አዛ የሚያደርጉ ምእመናንን አፍርተናል። ባለፈው ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪስ ሲያልፉ አላህ ይማራቸው እያሉ የፖሰቱትን ሁሉ በውስጥ እየገቡ አጥፉ ለርሳቸው አላህ ይማራቸው ማለት አይበቃም እያሉ ሲያስጠፉ የነበሩ ኡስታዝ ተብሎ የሚጠሩ በርካታ ሙተጦሪፍ ጥራዝ ነጠቆችን አይቼ በጣም ያሳዘነኝ ክስተት ነበር! እነ ኢማም ዩሱፍ አልቀረዷዊ ሲናልፉ ይህንኑ ዘመቻ ከፍተው የነበሩ በርካቶች ነበሩ! እነ ሸይኽ አቡኢስሀቅ አል ሁወይኒ ሲያልፉ በቃ ምናለፋችሁ ከጧኢፋቸው ውጭ ያለ መሻኢኽም ይሁን ሙስሊም በሞተ ቁጥር አላህ ይማራቸው አትበሉ እያሉ የፈትዋ መአት የሚያዥጎደጉዱ ስርአት አልባዎች እን። አሸን ፈልተዋል። በሁሉም ሰው ህይወት ውስጥ ያገባናል ፤ ከሚያገባው ከምታገባው እስከ አመለካከቱ በእኛዋ ቀጭን መስመር ብቻ እንቅረፅለት የሚሉ ጀግኖች! ተው ግን ተው ከዚህ ስነምግባር ዝቅጠት እንውጣ! ዛሬ በሌላ ሰው ክብር ላይ ጥሰት የምታለማምዷቸው ጀማሪዎች ነገ እናንተኑ ይረማመዱባችሗል። እያየነው ያለነውም ይሄንኑ ነው! ሙስሊም ሆነን ተሳዳቢ ፣ አነዋሪ ፣ ዋሾ ፣ መጥፎ ተናጋሪ ፣ ጨካኝ ፣ ፈራጅ ፣ የሰው ነውር አፈንፋኝ ፣ ሀሜተኛ ፣ የሰው ስም አጥፊ ፣ በማይመለከተን ሁሉ ጥልቅ የምንል ፣ አንደበታችን ያልተገራ መሆን ባልተገባን ነበር። ነብያችን አለይሂ አሶላቱ ወሰላም እንደነገሩን የውመልቂያማ ላይ የመልካም ስየምግባርን ያክል ሚዛን የሚደፋ የለም። የኢስላም መልእክትና አላማም የሰው ልጆችን በስነምግባር ማነፅ ከመጥፎ ስነምግባርም መከልከል ነው። ከዚህ የተለየ የለየለት የስነምግባር ጉድለት እያሳየን ከእኛ ውጭ ትክክለኛ ሙስሊም የለም ማለት ንፍቅና ነው! ከማውራት መሆንን ማስቀደም ኸይር ነው። ለመሆን የሚጥር ደግሞ ከሌሎች ጉድለቶች ይልቅ የራሱ ጉድለት ላይ ቢዚ ይሆናል። ለዚህ ነው ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም طوبى لمن شغله عيبه عن عيوب الناس ከሰዎች ነውር ይልቅ የራሱ ነውር እረፍት ያሳጣው ሰው ጀነት ምንኛ አማረችለት ያሉት! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
5 898
11
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለወልይነትና ቅደስና ቀርቶ እንደው በእውነቱ በጣም ስኬታማ መሪ ነው ብለንስ ልንጠቅሰው የምኝችል መሪ ነው ወይ? ያለፉት ስምንት አመታት የአመራር ዘመን ውጤቱን ስናይ የሚያሳየን እርሱን ነው ወይ? እርግጥ ነው አብይ አህመድ በተለያዩ ዘርፎች የተለያዩ ስኬቶችን መጎናፀፍ ችሏል። በተለይም በከተማ ልማት ፤ የታጣቂዎችን ግስጋሴ በመግታት ፤ ሀገሪቱን ከመበታተን በማዳን እና ግዙፍ መከላአያ ሰራዊት ስኬታማ አይደለም ብሎ ማስተባበል አይቻልም። ግና የአብይ አህመድ መንግስት የወደቀባቸው በርካታ ውድቀቶችን ዩያዘ መንግስት ነው። 👉 ሰላም እጅግ በመደፍረሱ ዜጎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ያልቻሉበት 👉 የእርስበርስ ጦርነት የሀገሪቱ ዋነኛ መገለጫ የሆነበት 👉 የዋጋ ንረቱና የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ እጅግ መዳከም አይደለም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች የመኖር ህልውና እንኳ የተፈታተነበት ድሀውን ህዝብ ተስፋ ያስቆረጠበት 👉 ሀገሪቱ በእዳ ተውጣ የኢኮኖሚ ሉአላዊነቷን አጥታ እጅና እግሯን ለ IMF ያስረከበችበት 👉 የትምህርት ስርአቱ ሙቶ ከ 10% በታች ተማሪዎች ብቻ እያለፉ እነርሱም ስራ የማያገኙበት! 👉 የዩኒቨርስቲ ትምህርቶች መክፈል ለሚችሉ ብቻ እንዲሆን እየተደረገ የመደብ ልዩነት ከ ግማሽ ምእተአመት በሗላ እንደገና የተፈጠረበት 👉 ሙስናና ብልሹ አሰራር ሀላል የወጣበት 👉 የስራ አጥነቱ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከሀገር ለመውጣት ህይወታቸውን ቀብድ አሲዘው እየተሰደዱ ያሉበት! 👉 ማህበራዊ ቀውስ የገነነበት ፤ የሀይማኖቶና የብሔር ሽኩቻ ጥላቻና መከፋፈል አየሩን የሞላበት! 👉 በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችች በረሀብ እየተሰቃዩ በትሪሊዮን የሚቆጨር ገንዘብ ውበትና ቤተመንግሥት ግንባታ ላይ የሚረጭበት 👉 የሀገሪቱ አለምአቀፍ ቅቡልነትና ተፅእኖ ፈጣሪነት የቀነሰበት 👉 ልክ ያጣ ግብርና በሌብነት የታሸ የግብር አሰባሰብ ብዙዎችን አስመርሮ ከገበያ ውጭ ያደረገበት! ኧረ ስንቱ ነው ተዘርዝሮ የሚያልቀው! እና ከስኬታማነት መሪነትም አሳልፈው ለማንቆለጳጰስ ቃል የሚያጥራቸው ሰዎች ግን እነርሱ የሚያዩበትን መነፅር ለእኛም ቢያውሱን! በመሰረቱ ለእኔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለውን የህዝብ ድጋፍ አግኝቶ በሚገባ ያልተጠቀመ መሪ ነው። ያን እድል ወደ ስትራቴጂካዊ ውጤት ቢቀይረው ኖሮ ዛሬ በዚህ የስቃይ ደረጃ አንሆንም ነበር። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
6 853
12
ኡፍ የሀይማኖት መሪ አሽቄነትኮ ግን ሲዘገንን😁 ተመልከቱ ይሄኛው ደግሞ የቤተክርስቲያን መዝሙርን ለአብይ ሲዘምር😂
ኡፍ የሀይማኖት መሪ አሽቄነትኮ ግን ሲዘገንን😁 ተመልከቱ ይሄኛው ደግሞ የቤተክርስቲያን መዝሙርን ለአብይ ሲዘምር😂
6 439
13
ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተናገሩት ይሄ ነው። " አብይ ነብይ ነው እንዳንል ከነብያችን በሗላ ነብይ አይመጣም ስለዚህ ወልይ ነው ብለነዋል" አሉ። ይሄ አይደለም ከአንድ አሊም ይቅርና ከጃሂል እይኳ
ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተናገሩት ይሄ ነው። " አብይ ነብይ ነው እንዳንል ከነብያችን በሗላ ነብይ አይመጣም ስለዚህ ወልይ ነው ብለነዋል" አሉ። ይሄ አይደለም ከአንድ አሊም ይቅርና ከጃሂል እይኳ የማይጠበቅ ውስጡ ቀፋፊ ዲናዊ ቅጥፈት ያለበት ንግግር ነው። የርሳቸው በርካታ ስህተት ያሊባቸው ንግግሮች ይስተካከላሉ ሲባል እየባሰባቸው መሄዱ ያሳስባል !
6 584
14
የዱሮ ኡለማኦች ሷሊሆቹ ኡለማኡ አስሰለፍ በጣም የሚርቁትና የማፈሩት ነገር ቢኖር ስልጣንን ነበር። ከባለስልጣናት ጋር መጣበቅን። ለዚህም ከስልጣን ለመራቅ ብዙ ስቃዮችን አሳልፈዋል ብዙ መስዋዕትነቶችን
የዱሮ ኡለማኦች ሷሊሆቹ ኡለማኡ አስሰለፍ በጣም የሚርቁትና የማፈሩት ነገር ቢኖር ስልጣንን ነበር። ከባለስልጣናት ጋር መጣበቅን። ለዚህም ከስልጣን ለመራቅ ብዙ ስቃዮችን አሳልፈዋል ብዙ መስዋዕትነቶችን ከፍለዋል። እንኳን ሌላው ቀርቶ ከመንግስት የሚመጣላቸውን ስጦታ እንኳ በፍፁም አይቀበሉም ነበር። ምክንያቱም ስጦታ ለሊላህ ብቻ የሚደረግን ስራ ለህሊና ብቻ የማፈፀምን ክዋኔ ይበክላል ይበርዛል corrupt ያደርጋል። እነ ኢማም አቡሀኒፋ ፣ እነ ሰእድ ኢብን ጁበይር ፣ እነ ኢማም አህመድ ፣ እነ ኢማም አጦበሪ ፣ እነ ኢማም አብዱልቃድር ጂላኒ ወዘተ ብዙ ዋጋ የከፈሉበት ይሄው ስልጣን እንኩ አንቀበልም ፤ ስጦታ እንኩ አንወስድም ፤ መንግስታችንን ደግፉ በዙልም አንደግፍም ትንቅንቅ ነበር። ኢማም አብዱልቃድር ጂላኒ ስልጣንን በፍፁም አልቀርብም ብለው ረሀብ ግን ይጥላቸው ነበር። ኢማም አጦበሪም እንደዚያው። በዘመናችን ግን የምናየው ተቃራኒውን ሆኗል። ከአረቡ እስከ አጀሙ ኡለማኦች የአገዛዞች መሳሪያ የግፋቸው ሸፋኝ ሆነዋል። እነ እስራኤልን የሚከላከሉ እነ አሜሪካን የሚያሞካሹ፤ ስለአገዛዝ ግፎች ትንፍሽ ከማለት ይልቅ ወልየል አምር ፤ ወልየል አህድ እያሉ የሚቀጣጥፉ ብዙዎችን አይተናል። ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋም በዚህ በኩል በሀገራችን ሪከርድ የሰበረ ንግግር ማድረጋቸውን ሰማን። የርሳቸውን ለየት የሚያደርገው ወልየነትን ሙስሊም እንኳ ላልሆነ አካል መስጠታቸው ነው። እንዲህ ያሉ ከየትኛውም ሀይማኖት በኩል ያሉ የሀይማኖት መሪዎች ሀይማኖት ላይ የበለጠ አሉታዊ አስተያየቶች እንዲዳብር የሚያደርጉ ሰውንም ከሀይማኖት የሚያሸሹ ናቸው። የሀይማኖት መሪዎቹ corrupted ሆነው ሳለ ከታች የሚመሩት ማህበረሰብ ይስተካከላል ተብሎ አይጠበቅምተ እያየን ያለነው ውጤትም ይህንን ነው። 👉 t.me/Seidsocial
6 667
15
ራትኮ ሚላዲች የቦስኒያው ጭራቅ!+1
ራትኮ ሚላዲች የቦስኒያው ጭራቅ!
7 740
16
ራትኮ ሚላዲች ሞተ! "የቦስኒያው አረመኔ" ወይንም "The Butcher of Bosnia " እየተባለ የሚጠራውና ከሙስሊሞችና ካቶሊኮች የፀዳች ኦርቶዶክሳዊት ሰርቢያን ለመፍጠር በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የመራው ራትኮ ሚላዲች ሄግ በሚገኘው አለምአቀፉ የወንጀል ፍርድቤት የእድሜ ልክ እሰራት ተፈርዶበት ሲማቅቅ ከኖረ በሗላ በዛሬው እለት በ 84 አመቱ እዚያው እስርቤት እያለ ምቷል። ስለ ስሬብሬኒካ ጄኖሳይድ ብዙ ጊዜ በሰፊው ፅፌ አስነብቤያችሗለሁ። ያንን ጄኖሳይድ የመራው ራትኮ ሚላዲች ነበር። ራትኮ ሚላዲች ካቶሊካዊቷን ክሮሺያን ለመጠቅለል ያደረገው ሙከራ አልሳካለት ሲል ሙስሊሞች የሚበዙባት ቦስኒያ ላይ ዘመተ። በሩሲያ የሚደገፈው የሰርቢያ ጦርም የቦስኒያ ዋና ከተማ ሳራጄቮን ለ 1,435 ቀናት ወይንም ለ 203 ሳምንታት በመክበብ ከ 12,000 በላይ ነዋሪዎቿን ጨፈጨፈ። ይህም በዘመናዊ የሰው ልጆች ታርክ ረጂሙ ከበባ ነበር። ከዚያም አልፎ ስሬብሬኒካ ላይ ሙስሊሞችን በመክበብ ከ 8,000 በላይ ወንዶችንና ህፃናትን በጅምላ ጨረሳቸው። ወታደሮቹ ሙስሊም ሴቶችን በጅምላ እየደፈሩ ረሸኗቸው። ይህ ግፍ አውሮፓ ምድር ላይ ሲከሰት ኔቶ ጣልቃ ገባና የሰርቢያን ጦር ደበደበ። አሜሪካ ቱርክ ኢራንና ሌሎችም ሀገራት የቦስኒያ ሀይሎችን በማስታጠቅና በማሰልጠን የሰርቢያን ጦር የሚመክትና የሚያሸንፍ ሀይል እንዲገነባ አደረጉ። ሳኡዲ አረቢያ እና ሌሎችም የአረብ ሀገራትም የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ። በዚህም 1995 ላይ የሰርቢያ ጦር ግስጋሴ ተገታና ቦስኒያ ሄርዝጎቬኒያ ራሷን የቻለች ሀገር ሆና ተመሰረተች። ሰርቢያን የኦርቶዶክስ ሀገር እንዳደርግ ከእግዚአብሔር ተልኪያለሁ ይል የነበረው ጀኔራል ሚላዲች " ሙስሊሞችን ግደሉና አቃጥሏቸው ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጠኝ ትእዛዝ ነው" ይል ነበር። "ህፃናቱን እንዳትምሩ ሲያድጉ የናንተው ጠላቶች ነው የሚሆኑት" እያለም በርካታ ህፃናትን ጨረሰ። ራትኮ ሚላዲች ለ16 አመታት ተደብቆ ከኖረ በሗላ በ 2011 አለምአቀፉ ፍርድቤት በድብቅ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር አውሎታል። በዚህ ከበርካታ የሰርቢያ መሪዎች ጋር የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር። ራሳቸውን ፍርድቤት ላይ ያጠፉም መሪዎች ነበሩ። ሚላዲች ከተያዘ ከ 15 አመታት በሗላ በእስር ላይ እያለ ዛሬ ህይወቱ አልፏል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
7 457
17
የእስራኤል አገልጋይ የሆኑት የነገስታ ኡለማእ ተብየዎች እንደዚህ በቀጥታ ስንከታተለው የነበረውን እጅግ አውዳሚ የጋዛ ድብደባን ነው ፊልም ነው ውሸት ነው ለማለት እየቀጠፉ የሚገኙት! እኔኮ ስለ ጋዛ
የእስራኤል አገልጋይ የሆኑት የነገስታ ኡለማእ ተብየዎች እንደዚህ በቀጥታ ስንከታተለው የነበረውን እጅግ አውዳሚ የጋዛ ድብደባን ነው ፊልም ነው ውሸት ነው ለማለት እየቀጠፉ የሚገኙት! እኔኮ ስለ ጋዛ ተናገሩልን ያላቸው የለ ፤ ድምፅ ሁኑልን ያላቸው የለ ፤ በቃ ምንም አልተባሉምኮ። እንደትና በምን ልክ ለእስራኤል ቢገረዱ ነው ግን በቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ ይህን ያክል ቀጣፊ የሆኑት! ከነዚህ ውሸታሞች ምንም አይነት ነገር መውሰድ መያዝ የሚቻል አይመስለኝም። ለቀሩት ቂርአት ለአላህ ለገቡት ቃል ታማኝ ያልሆኑ ለሰው ልጅ ጠላቶች ጠበቃ የሆኑትን እነርሱን የሚናገሩትንም መያዝ ሙስተሂል ነው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
6 407
18
ይህቺ ልጅ እንዲህ የምታለቅሰው የሴዶ መሸነፍ አበሳጭቷት አይደለም። እርሱ ያሸንፋል ብላ ለስራ መስሪያ ከባንክ የተበደረቺውን ብር ሳይቀር አሲዛ ቁማርጨ ስለተበላች ነው እንዲህ እብድ ያለቺው። ቁማርና
ይህቺ ልጅ እንዲህ የምታለቅሰው የሴዶ መሸነፍ አበሳጭቷት አይደለም። እርሱ ያሸንፋል ብላ ለስራ መስሪያ ከባንክ የተበደረቺውን ብር ሳይቀር አሲዛ ቁማርጨ ስለተበላች ነው እንዲህ እብድ ያለቺው። ቁማርና ሱስ ለጊዜው ተሳክቶልህ ብትደሰትባቸው እንኳ መጨረሻቸው ኪሳራ ነው። እንደ ሀይማኖታችንም ፍፁም ክልክል ከሆኑና በፍፁም እንዳንቀርባቸው ከታዘዝናቸው ነገሮች ቁማር እና ሱስ ይገኙበታል። ይሄንን ትእዛዝ ጥሶ መግባት የማይወጡበት የሱስ አዘቅት ውስጥ ነው የሚከተው። መውጬቸውም ከባድ ነው። ማቆሚያቸውም ሩቅ ነው። በቁማር የስንቶቹ አንፀባራቂ ህይወት ወደ ጨለማነት ተቀይሮ ባክኖ ቀርቷል። የቁማር አስከፊነት ላይ በደንብ ሊሰራ ይገባል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
7 462
19
ሌላው ጫት የሚያመጣው ጥፋት በሚቅምበት ወቅት አንድ ሰው ለራሱ ፈፅሞ የተጋነነ እና የሌለ ማንነት እንዳለው እንዲያስብ ማድረጉ ነው። ይህ ከስካር የሚመጣ ሽወዳ ነው። ምርቃና ልትሉት ትችላላችሁ። እና
ሌላው ጫት የሚያመጣው ጥፋት በሚቅምበት ወቅት አንድ ሰው ለራሱ ፈፅሞ የተጋነነ እና የሌለ ማንነት እንዳለው እንዲያስብ ማድረጉ ነው። ይህ ከስካር የሚመጣ ሽወዳ ነው። ምርቃና ልትሉት ትችላላችሁ። እና ያሰው በዚያ ቅፅበት ብዙ ድንበሮችን ያልፋል። ራሱን ባለከራማ እና ወልይ አድርጎ ይቆጥራል። እርሱ በእፁ ውስጥ የሚያቸው ምስሎች እርሱ ልዩ ስለሆነ የሚታዩት ይመስለዋል። የርሱ ዱአ ከሌላው ዱአ ሁሉ የተለየ ኢባዳው ከሌሎች ሁሉ የበለጠ መስለው ይታዩታል። እናም በሁሉም ነገሮ ድንበር ያልፋል። ተናንሳችሁ እና ፈርታችሁ ለምኑኝ ያለውን አላህን እርሱ ይዳፈረዋል። ትእዛዝ በሚመስል አነጋገር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አድርግ ይለዋል። ኧረ ከዚያም አልፎ ለራሱ አድርጌዋለሁ ይለዋል። ይህን ጀባ ብየሀለሁ ፤ ይሄን ሰጥቼሀለሁ ይሄን አድርጌልሀለሁ እያለ እየቆጠረ ማስረከብ ሁሉ ይጀምራል። እንዲህ አይነት መሸወዶች ዱአ እና ኢባዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በመደበኛ ህይወትም ላይ ያጋጥማሉ። የሚቅም ሰው በሚቅምበት ወቅት ሌላ አለም ላይ ያለ ነው የሚመስለው። ከዚያ ምርቃና ወይንም ስካር ሲወጣ ያያቸው ነገሮች ሁሉ እንደ ጉም ሲተኑበት ያያል። ድባቴ ውስጥ ይገባል ። እንደገና ያንን የሚያምር ምስል ለመከሰት መልሶ መቃም አለበት። እኔም ጫት አውዳሚ ነው። ከመስጅድ አይደለም ከመስጅድ አካባቢ እንኳ መኖር የሌለበት እፅ ነው። በነገራችን ላይ ባንኮች በኢስላማዊ ፋይናንስ ዘርፍ ለጫት አያበድሩም ከጫት የሚገኝንም ገቢ ወደ ወለድ ነፃ አካውንት ገቢ እንዲደረግ አይፈቅዱም። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
7 919
20
ከእስራኤል አገላጋዮች አንዱ የሆነው ኩዌይታዊው ሳሊም አጦዊል እስራኤል ጋዛን በጦር ጄቶች አልደበደበችም ፌክ ነው ፊልም ነው እያለ እያስተባበለ ነው። አጦዊል አክሎም 80 በ 12 ኪሎሜትር የሆነቺው
ከእስራኤል አገላጋዮች አንዱ የሆነው ኩዌይታዊው ሳሊም አጦዊል እስራኤል ጋዛን በጦር ጄቶች አልደበደበችም ፌክ ነው ፊልም ነው እያለ እያስተባበለ ነው። አጦዊል አክሎም 80 በ 12 ኪሎሜትር የሆነቺው ጋዛን እስራኤል በጦር ጄት ብትደበድብ ኖሮ አንድም ሰው አይተርፍም ነበር እስራኤል ስላዘነችላቸው ስላልደበደበች ነው የተረፉት እነዚህ ጋዛዊያን ሶስት አመት በጉርጓድ ውስጥ ሆነው ከእስራኤል መትረፍ የሚችሉ እንዳይመስሏችሁ ውሸት ነው እያለ ነው። የእስራኤል ጥቃት እንኳን ጋዛዊያንና ሂዝቡላህ( በርሱ አጠራር ሂዝቡሸንጧን) እና ኢራን ( በርሱ አጠራር መጁሳ) እንኳ አልተቋቋሙትም እያለ ለእስራኤል ይሞግታል። ውፍረቱና ቦርጩ አላንቀሳቀሰው እያለ የሚያውደለድለውና የእስራኤል ፕሮጀክት አስፈፃሚ የሆነው ሳሊም በጋዛዊያን ላይ መሳለቁን ዛሬም ቀጥሏል። አላህ ይይለት! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
8 748