የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU 的分析概览
频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 434 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 048,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 328 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 434 名订阅者。
根据 27 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 543,过去 24 小时变化为 21,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 36.43%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 252 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 33。
📝 描述与内容策略
尚未提供频道描述。
凭借高频更新(最新数据采集于 28 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
14 434
订阅者
+2124 小时
+1247 天
+54330 天
帖子存档
በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች
የመንፈስ ቅዱስ መሰንቆ የቃኛቸው አባቶች በመንፈሳዊ ሥልጣን ላይ ሲቀመጡ ራሳቸውንም ሌሎችንም ይጠቅማሉ። በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች በፈቃደ እግዚአብሔር ስለሚመሩ ክርስቲያኖች ሁሉ እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ እንዲጓዙ ያደርጋሉ። እንዲህ ማድረጋቸው ሃይማኖት እንዲጸና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲጠበቅ ሳይታክቱ ይሠራሉ። መሥራት ብቻ ሳይሆን ራሳቸው አርአያ ሆነው ፈጽመው ያሳያሉ።
ማንበብ ይቀጥሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://eotc-gssu.org/a/በመንፈስ-ቅዱስ-የተቃኙ-አባቶች/
በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
✍️ FaceBook 👇
https://www.facebook.com/EOTC.GSSU
✍️Telegram 👇
https://t.me/EOTCNSSU
✍️Website👇
https://eotc-gssu.org/a/
✍️Twitter👇
https://twitter.com/tibeb_feleg
"የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ።" መዝ 114፡13
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት!
✍️Youtube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
"ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።" ማቴ 6፡33
https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion/video/7293950430143450410?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7288000334784579078
#ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ
ገብረ ክርስቶስ አባቱ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ እናቱ ንግሥት መርኬዛ ሲሆኑ በስለት ያገኙት ብቸኛ ልጃቸው ነው፡፡ ሥጋዊና መንፈሳዊ ትምህርትን እያስተማሩት በምግባር አሣድገውታል፡፡ ለአካለ መጠን ሲደርስም የአባቱን ንግሥና በመውረስ ቁስጥንጥንያን እንዲገዛ በማሰብ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ አጭተው አጋቡት፡፡ እርሡ ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ፣ የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም የተዘጋጀ ነበርና ሌሊት በኾነ ጊዜ ወደ ሙሽራይቱ ገብቶ እጇን ይዞ ጸሎተ ሃይማኖትን እስከ መጨረሻው ደግሞ፣ እንዳትናገር ቃል አስገብቶ፣ የተሞሸረበትን ልብስ አውልቆ ‹‹እኅቴ ሆይ እንደ ጉም ተኖ እንደ ጢስ በኖ ከሚጠፋ ተድላ ሥጋ አልገባም፤ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኑር ከሰይጣን ሥራ ያድንሽ የአባቴ መንግስት ኀላፊ ጠፊ ነውና እኼዳለኹ እንዳትናገሪ›› ብሎ የእራሱንም የሙሽራዋንም ድንግልና እንደጠበቀ በሌሊት ወጥቶ ሄደ፡፡
ከዚያም በመርከብ ተሳፍሮ የብዙ ቀን መንገድ የሚሆን ጎዳና በአንድ ቀን ተጉዞ አርመንያ ደረሰ፡፡ በዚያም በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን ከነድያን ጋር በመቀላቀል እየለመነ ያገኘውንም ለሌሎች እየመጸወተ በጾም በጸሎት ተጠምዶ ዐሥራ አምስት ዓመት ሲኖር እመቤታችን ለገበዙ ተገልጻ ‹‹ገብረ ክርስቶስን ይዘኽ ከቤተ ክርስቲን አግባው›› አለችው፡፡ ገበዙም ኺዶ ‹‹እመቤቴ አዛኛለችና ገብተኽ ሥጋ ወደሙን ተቀበል፡፡›› አለው፡፡ ገብረ ክርስቶስም የታዘዘውን ከፈጸመ በኋላ ‹‹ዋጋዬን በውዳሴ ከንቱ ሊያጠፉብኝ ነው›› ብሎ ከእመቤታችን ፊት ቆሞ ‹‹ምሥጢሬን ለምን ገለጽሽ አኹንም ወደ ሚሻለኝ ምሪኝ›› ብሎ በመጸለይ ሥዕሏን ተሳልሞ ወደ ሌላ ሀገር ሊኼድ በመርከብ ተሳፍሮ ከእናት አባቱ ሀገር ደረሰ፡፡ የጌታ ፈቃድ ነው ብሎም ማንነቱን እንደደበቀ ሣያውቁት ከንጉሥ አባቱ ደጅ የኔቢጤ /ለማኝ/ ሆኖ ለአባቱ ውሾች የሚሰጠውን ፈርፋሪ እየተመገበ ሠላሳ ዓመት በዚያ ተቀመጠ፡፡
የአባቱ አሽከሮች እንኳን እጣቢና ቆሻሻውን ሁሉ እየደፉበት ሲያሰቃዩትና ውሾች እንዲናጠቁትም የሥጋ ውሃ ሲደፉበት ውሾቹ ግን ቁስሉን ይልሱለት ነበር፡፡ እርሱም በደል እንዳይሆንባቸው በመጸለይ፣ እየለመነ ያገኘውን እየመጸወተ፣ በጾም በጸሎት እየተጋደለ ኖረ፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ጌታችን ስሙን ለሚጠራ፣ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃልኪዳን ከሠጠው በኋላ እርሱም ታሪኩን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ጽፎ በእጁ እንደጨበጠው ጥቅምት ዐሥራ አራት ቀን ዐርፏል፡፡
የቁስጥንጥንያው ሊቀጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ በቅዳሴ ላይ ሳለ ‹‹ብእሴ እግዚአብሔርን በንጉሥ ቴዎድዮስ ቤት ፈልጉት፡፡›› የሚል ቃል ሰማና ቢሔድ ባረፈበት ቦታ ክርታሱን እንደጨበጠ አገኙት ሊያዩት ፈልገው አልለቅ ብሎ ፈጽሞ እምቢ አላቸው፡፡ ብዙ ምሕላና ጸሎት ከተደረገ በኋላ ለቆላቸው ቢያነቡት የንጉሥ ልጅ መኾኑንና ያሣለፈውን ተጋድሎ ተረድተዋል፡፡ እያለቀሱና ደረታቸውን እየደቁ ሥጋውን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት እጅግ ብዙ ተዓምራቶች በድውያንና ሕመምተኞች ላይ ተፈጽሟል፡፡ ብዙዎች ዳሰውት ከተፈወሱ በኋላ በአንጻረ መቅደስ ቀብረውታል፡፡
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
✍️ FaceBook 👇
https://www.facebook.com/EOTC.GSSU
✍️Telegram 👇
https://t.me/EOTCNSSU
✍️Website👇
https://eotc-gssu.org/a/
✍️Tiktok👇
https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion
አቡነ አረጋዊ ከእለታት አንድ ቀን እናቱ እድና ዜናውን ሰምታ ልትጠይቀው በመጣች ጊዜ ‹‹ለምን መጣሽ›› አላት፡፡ ‹‹ልጄ አንተ በሕጻንነትህ የናቅኸው ዓለም ለእኔ ምን ይረባኛል ብዬ ነዋ›› አለችው፡፡ እሱም አመንኩሶ ከሴቶች ገዳም አስገባት፡፡ ከሰባት ዓመት በኋላ ዘጠኙ ቅዱሣን በእምነት ወደ ምትመስላቸው ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ መጥተዋል፤ እናቱም አብራ ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች፡፡ ከእነዚህም በይበልጥ የአባ ቴዎድሮስ እና የአባ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር የነበረ አባ ዘሚካኤል /አቡነ አረጋዊ/ በገዳመ አስቄጥስ በነበረበት ሰዓት ስለ እመቤታችን ከተጻፈው ነገረ ማርያም ጌታችን ኢትዮጵያን ዐሥራት እንደሰጣት በመስማቱ ሰባቱን አስከትሎ ወደ ኢትዮጵያ በንጉሥ አልዓማዳ ዘመን መጥተዋል፡፡ ከአባ ጰጉሚስ እንደተማሩት ሥርዐተ ምንኩስናን ማስተማር ማመንኮስ ጀመሩ፡፡ አቡነ ዘሚካኤል መጽሐፈ መነኮሰትን ከጽርእ ቋንቋ ወደ ግእዝ መልሶታል፤ የሱርስትን ቋንቋ ዐዋቂ ስለነበረ አስቀድሞ በቤተ ቀጢን ሰባት ዓመት የግእዝን ቋንቋ ከሰባቱ ጋር ተምሯል፡፡ አባ ገሪማ እስከዚህ ድረስ በሮም ነግሶ ይኖር ነበርና መልእክትን ልከውበት መንግስቱን ትቶ መጥቶ ዘጠነኛ ኹኗል፡፡ ከዐሥራ ሁለት ዓመት በኋላም በየእራሳቸው ተበታትነው ገዳም መስርተዋል፡፡
አቡነ አረጋዊም እናቱ አድናን እና ተማሪው ማትያስን አስከትሎ በአክሱም በስተ ምስራቅ ሰባ ኪሎ ሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው ወደ ዳሞ ተራራ ኺዷል፡፡ ወደ ተራራው የሚወጣበት አጥቶ ባሰበ ጊዜ የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስልሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ በቅዱስ ሚካኤል ጠባቂነት ከተራራው ራስ አድርሶታል፡፡ እንዳደረሰውም ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ›› ብሎ በማመስገኑ “ደብረ ሃሌ ሉያ” ተብሏል፡፡ ቦታው ዙሪያው ገደል በመኾኑ መውጫ አልባ የኾነውን ታላቁን የደብረ ዳሞን ገዳም የመሠረተ ሲሆን ይኽም የሀገራችን የመጀመሪያው ገዳም ነው፡፡ በአቡነ አረጋዊ ጥያቄም መሠረት በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ዐጼ ገብረ መስቀል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ቤተ ክርስቲያን አሠራ፡፡ ለሰራተኞች መውጪያና መውረጃ የተሰራው ደረጃ ስለተነሳ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማንም ሰው ወደ ገዳሙ የሚደርሰው በአምሳለ ዘንዶ ከላይ በሚለቀቅለት ዐሥራ ስድስት ሜትር የተጎነጎነ ጠፈር ወገቡን ታስሮ በመጎተት ሲሆን ወደ ገዳሙ መውጣት የሚችሉት ወንዶች ብቻ ናቸው፡፡ ለሴቶች በእግረ ደብር ገዳም መሥርቶ እድናን እመመኔት አድርጎ ሹሞላቸዋል፡፡ ከዘጠኙ ቅዱሣን መካከል አቡነ አረጋዊ በግብጽ አባ እንጦንስ በመሠረቷት ገዳም በተማረው መሠረት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ገዳማዊ ኑሮ መስራች አባት ነው፡፡ አቡነ አረጋዊ ከዐጼ ገብረ መስቀል እና ከቅዱስ ያሬድ ጋር በደቡቡ የሀገራችን ክፍል እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲያስተምር ጋሞጎፋ ውስጥ ውሃ ከሌለበት ቦታ ደርሶ መሬቱን በመስቀል ባርኮ በአንድ ስፍራ ላይ በተዓምር አርባ ምንጮችን አፍልቋል፤ በዚህም ከተማው አርባ ምንጭ ተብሏል፡፡ በዚያም መስዋዕተ ኦሪት ይሰዋባቸው ከነበሩ ገዳማት አንዷ የሆነችውን ብርብር ማርያም ገዳምንም በመጎብኘት ወንጌልን በመስበክ አከባቢውን ባርኳል፡፡
በመጨረሻም ጌታችን ተገልጾ ‹‹መንግስትን ትተህ ስላገለገልከኝ መንግስተ ሰማያትን እርስኸለኹ…›› በማለት ልዩልዩ ቃልኪዳንን ከገባለት በኋላ ‹‹…ሞት አያስደነግጥኽም›› በማለት ተስፋውን ነግሮታል፡፡ ከዚያም መነኮሳቱን ሰብስቦ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም›› በማለት በእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ሔኖክና ኤልያስ ጥቅምት ዐሥራ አራት ቀን ከሞት ፊት ተሸሸገ /ተሰወረ/፡፡
አቡነ አረጋዊ ወገብረ ክርስቶስ
#አቡነ አረጋዊ /ዘሚካኤል/
አቡነ አረጋዊ ሀገሩ ሮም ሲሆን አባቱ ንጉሠ ሮም ይስሐቅ እናቱ እድና ይባላሉ፡፡ እናት አባቱ ገብረ አምላክ ብለው ሲጠሩት፤ ዘሚካኤል የሚለው በመነኮሰበት ወቅት የወጣለት ስም ነው፤ አረጋዊ የሚለውን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በቤተ ቀጢን በነበሩበት ጊዜ በፍጹም ፍቅርና ትሕትና ስላገለገለ ወንድሞቹ አረጋዊ ብለውታል፡፡
ጥበብ መንፈሳዊ ሲማር አድጎ ዐሥራ አራት ዓመት ሲኾነው ከነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስትን ቢያጩለት እምቢ ብሎ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ገዳም ገብቶ ማዕረገ ምንኩስናን ተቀበለ፡፡ በዚህም ከእንጦንስና፣ ከመቃርስ፣ ከጳኩሚስም የምንኩስና ወይም መንፈሳዊ ሐረግ አራተኛ ትውልድ ነው፡፡
የንጉሥ ልጅ በሕጻንነት ምንኩስና መቀበሉን የሰሙ ሰባት ደጋግ ቅዱሳን ከያሉበት ተሰባስበው አባ ጳኩሚስ ገዳም በመግባት ማዕረገ ምንኩስናን ተቀብለው ሁሉንም ነገር ከአባ ጳጉሚስ ጠንቅቀው እየተማሩ ለብዙ ዓመታት ከእርሱ ጋር ተቀመጡ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን አባ ጰንጠሌዎን፣ አባ ይምዓታ፣ አባ ጉባ፣ አባ አፍጼ፣ አባ ጽሕማ፣ አባ ሊቃኖስ እና አባ አሌፍ ናቸው፡፡
ደቂቀ ሰላም ወፍቅር በመጋቤ ብርሃናት ቆሞስ አባ ተክለያሬድ ጎርጎርዮስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ
https://vm.tiktok.com/ZMjbKw38P/
የትምህርት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ተደረገ።
ጥቅምት 13/02/2016 (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
የ2016 ዓ.ም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ሰንበት ትምህርት ቤቶች የትምህርት ማስጀመርያ መርሐ ግብር ባሳለፍነው ቅዳሜና አሁድ ተደርገው አልፈዋል። የዝግጅት ክፍላችን በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች ባደረገው ዳሰሳ በአጠቃላይ ከ38 በላይ ሰ/ት/ቤቶች የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የጀመሩ ሲሆን በአያት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፣ በየረር ቅዱስ ኡራኤል፣ በአራብሳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት በአካል በመገኘት ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ ላይኞቹ ክፍሎች ለመማር ማስተማር ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በማማሏት ትምህርት መጀመራቸውን ለመመልከት ተችሏል።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
✍️ FaceBook 👇
https://www.facebook.com/EOTC.GSSU
✍️Telegram 👇
https://t.me/EOTCNSSU
✍️Website👇
https://eotc-gssu.org/a/
✍️Tiktok👇
https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion
"አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።" ሮሜ 8፡30
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት!
✍️Youtube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
ቡርክታዊት በደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት አገልጋይ ስትሆን በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትና 617 በማምጣት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም አልፋለች።
https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion/video/7293209441581698347?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7288000334784579078
ከወርቃማው ሕግ አትንሸራተቱ
የተከበራችሁ የማኅበራዊ ሚዲያችን ተከታታዮች አስቀድምን ባስነበብነው የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ሰው በእግዚአብሔር አርአያ እና ምሳሌ የተፈጠረ የፍጥረታት ንጉሥ፣ ከሌሎች ፍጥረታት ተለይቶ ዐዋቂ እና ሕያውነት ያለው፣ በፍጥረታት ላይ የሠለጠነ ባለጸጋ ፍጡር መሆኑን አቅርበን ነበር። በዚህም ምክንያት ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ሲጠፋ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ “እስመ በፈቃዱ፣ ወበሥምረተ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ መጽዐ አድኀነነ” እንደ ተባለው ሰው ሆኖ ሰውን ከውድቀት አነሣው። ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላእክት ትቶ አንዱን ነገድ ሰውን ለመፈለግ ሰው የሆነው ለሰው ካለው ጽኑ ፍቅር የተነሣ ነው።
ማንበብ ይቀጥሉ...
👇👇👇👇👇👇
https://eotc-gssu.org/a/ከወርቃማው-ሕግ-አትንሸራተቱ-የነገረ-ሰብ/
ከወርቃማው ሕግ አትንሸራተቱ (የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ ክፍል ሁለት)
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
