የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU 的分析概览
频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 356 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 146,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 357 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 356 名订阅者。
根据 23 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 507,过去 24 小时变化为 14,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.68%。内容发布后 24 小时内通常能获得 13.08% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 681 次浏览,首日通常累积 1 875 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 28。
📝 描述与内容策略
尚未提供频道描述。
凭借高频更新(最新数据采集于 24 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
14 356
订阅者
+1424 小时
+1027 天
+50730 天
帖子存档
+6
በ2016 ዓ.ም የወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተስፋ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሕፃናትን ጨምሮ ከ1-12ኛ ክፍል በተዘረጋው ሥርዓተ ት/ት መሠረት ሲያስተምር ቆይቶ የዓመቱን ማጠቃለያ መርሐ ግብር ሐምሌ 14 2016 ዓ.ም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም የተማሪ ወላጆች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ በሰንበት ት/ቤቱ ከየክፍሉ እና ከአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
መረጃውን ከተስፋ ሕይወት ሚድያ አግኝተነዋል።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok+6
ብፁዕ አብነ አብርሃም በኹለተኛው የአኅጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና ላይ በመገኘት አባታዊ መምሪያና ቡራኬ አስተላለፉ።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) 12/11/2016 ዓ.ም
ብፁዕ አብነ አብርሃም በኹለተኛው የአኅጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና ላይ በመገኘት አባታዊ መምሪያና ቡራኬ አስተላለፉ። በመልዕክታቸውም <<የሥራ ጊዜ ዛሬ ነው፤ ነፍሳትን የማዳን ሥራ ዛሬ ነው።>> በሚል መነሻ << እስካሁን የመጣንበትን የቃል ትምህርት ይዘን አሁን ደሞ ዘመኑን የሚዋጅ ዘመናዊ የትምህርት መስጫ መንገድ ያስፈልጋል። በተለይ ሕፃናት ልዩ አቀራረብ ይፈልጋሉ በሚመጥናቸው መንገድ ማቅረብ ደግሞ የኛ ድርሻ ነው ለዚህም እናንተ አደራ አለባቹ>> በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን ከተለያየ አኅጉረ ስብከት ለመጡ የሰንበት ት/ቤት መምህራን አስተላልፈዋል።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥር በሚገኙ አጥቢያዎች የ፬ [4] ኛ , የ፮ [6] ኛ እና የ፲ [10] ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የማጠቃለያ ምዘና ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም ይሰጣል !!!
#የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
+4
ኹለተኛ ዙር የአኀጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጀመረ።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) 08/11/2016 ዓ.ም
ኹለተኛ ዙር የአኀጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና ከ16 ሀገረ ስብከት ለመጡ ከ 200 በላይ ሠልጣኞች መሠጠት ተጀመረ።
ጉባኤው ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ሊቀ ጳጳስ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወ/ትንሣኤ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሐላፊ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም ሰብሳቢ በተገኙበት ተጀምሯል።
ብፁዕነታቸው ሥልጠናው እርስ በእርስ የምትተዋወቁበት ልምድ የምትለዋወጡበትና የምትተጋገዙበት ብሎም ለቤተ ክርስቲያን መልካም ፍሬን የምታፈሩበት ይሁን በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዎል።
ሥልጠናው ለተከታታይ 20 ቀናት በመደበኛ መርሐ ግብር በቀንና በማታ በክህሎት ፤ በእውቀት ፣ በዶግማና አስተዳደር ዘርፍ የሚሰጥ ይሆናል።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
Repost from የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
#ከሐምሌ_22_እስከ_ሐምሌ_28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ።
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል። ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው እግዚአብሔር ምልጃን ለማቅረብ ነው።
"ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል " ያለው ቋሚ ሲኖዶስ " በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር ፦
✤ መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣
✤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣
✤ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣
✤ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል።
በዚህም በመላ የሀገራችን ክፍልና ሌሎች አህጉራተ ዓለም የሚገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብለው የምሕላ ጸሎት እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል።
በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀርም እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንዲይዙ ፣ ቋሚ ሲኖዶስ ከአደራ ጋር አሳስቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርገውት መደበኛው ሥራቸውን በያሉበት ቦታ እየሰሩ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆነው በጾም በጸሎት እንድተጉ ጥሪ ተላልፏል።
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
