FastMereja.com
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 FastMereja.com 的分析概览
频道 FastMereja.com (@fastmereja) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 47 221 名订阅者,在 教育 类别中位列第 3 810,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 745 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 47 221 名订阅者。
根据 12 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -528,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 13.36%。内容发布后 24 小时内通常能获得 8.16% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 6 312 次浏览,首日通常累积 3 858 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 23。
📝 描述与内容策略
尚未提供频道描述。
凭借高频更新(最新数据采集于 13 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 教育 类别中的关键影响点。
47 221
订阅者
无数据24 小时
-847 天
-52830 天
帖子存档
47 221
1 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የባህል አምባሳደር አዋርድ 2019 የፍጻሜ ውድድር ሊካሄድ ነው
#FastMereja I በባህላዊ ትወና፣ በሀገርኛ ሙዚቃና በውዝዋዜ ዘርፎች የተዘጋጀው እና የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያስገኘው «የባህል አምባሳደር አዋርድ 2019» የመጨረሻ መርሃ ግብር ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ። በዮድ አቢሲኒያ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ መረዳት እንደተቻለው፤ ውድድሩ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር «ክብር ያለው እኛ ጋር ነው» በሚል መሪ ቃል በ77 ተወዳዳሪዎች ተጀምሮ፣ አሁን ላይ በሦስት የውድድር ምድቦች ተለይተው የመጨረሻውን ዙር የተቀላቀሉ 15 ምርጥ ተወዳዳሪዎችን አሳልፏል።
በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጆቹ እንደገለጹት፤ የፍጻሜው አሸናፊዎች የሚለዩት በ60 በመቶ የባለሙያ ዳኞች ግምገማ እና በ40 በመቶ የህዝብ ድምፅ ተደምሮ ይሆናል። በዚህም መሰረት ለውድድሩ አንደኛ ለወጣ ተወዳዳሪ የ1 ሚሊዮን ብር፣ ለሁለተኛ 300 ሺህ ብር እንዲሁም ለሦስተኛ ደረጃ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ተነግሯል፡፡ ከዚህ ባለፈም ሦስቱም አሸናፊዎች ወደ ሕንድ በመጓዝ የባህል ልምድ ልውውጥ የማድረግ ወርቃማ ዕድል እንደሚያገኙ የውድድሩ አዘጋጅ አቶ ዳንኤል ጥሩነህ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ተወዳዳሪዎቹ ያዘጋጁትን «ይህቺ ናት ሀገሬ» የተሰኘ ህብረ ዜማ በማህበራዊ ሚዲያ በተለየ የፈጠራ መንገድ የሚያስተዋውቅ ማንኛውም ማህበረሰብ አባል ከተወዳዳሪዎቹ ጋር ወደ ሕንድ የማቅናት ልዩ ዕድል እንደተመቻቸለት ይፋ ተደርጓል።
በዝግጅት አደረጃጀትና አፈጻጸም ላይ ከአዘጋጆቹ ጋር በጋራ የሚሰራው የአጋፔ ኤቨንት ኦርጋናይዘርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሚኪያስ ግርማ እንደተናገሩት፤ የመጨረሻውን ፕሮግራም ታሪካዊው ሮሃ ባንድ ከተወዳዳሪዎች እንዲሁም ከአንጋፋ እና ታዋቂ ድምፃውያን ጋር በመሆን በሙዚቃ ያደምቀዋል። ይህ ውድድር የወጣቶችን ችሎታ ከማበረታታት ባሻገር የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴቶች ለማስተዋወቅ፣ የባህል ልምድ ልውውጥን ለማጠናከር እና ለወጣት ተሰጥኦዎች አዲስ የዕድል በር ለመክፈት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ከወጣው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
47 221
ታላቁ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በፎርብስ አፍሪካ የ15ኛ ዓመት «አይኮኖች» ዝርዝር ውስጥ ተካተተ
#FastMereja I ታዋቂው የኢትዮጵያ አትሌት እና ስኬታማ የንግድ ሰው ሀይሌ ገብረሥላሴ በአፍሪካ አህጉር ዘላቂ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከፈጠሩ ታላላቅ መሪዎች መካከል በመመረጥ በፎርብስ አፍሪካ (Forbes Africa) የ15ኛ ዓመት ልዩ የዕውቅና መድረክ ላይ መካተታቸው ተገለጸ።
እንደ ፎርብስ አፍሪካ ይፋዊ መረጃ ዘገባ፣ ይህ ልዩ የዕውቅና ዝርዝር በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ላለፉት ዓመታት አርአያነት ያለው ሥራ በማከናወን ትልቅ ለውጥ ያስመዘገቡ እና የበርካቶችን ሕይወት የቀየሩ 15 ባለዕይታ ግለሰቦችን ታሪክ የሚዘክር ነው። በስፖርቱ ዓለም በበርካታ የዓለም ክብረ ወሰኖች እና የወርቅ ሜዳሊያዎች የኢትዮጵያን ስም ከፍ ያደረገው ሀይሌ ገብረሥላሴ፣ ከሩጫ ማስተማሪያ ውጪም በኢንቨስትመንት እና በስራ ፈጠራ ዘርፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ አህጉራዊ አድናቆት ተችሮታል።
መጽሔቱ በዘገባው አትሌቱን ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር Generational Legend ሲል የገለጸው ሲሆን፣ በስፖርትም ሆነ በቢዝነስ ዓለም ውስጥ ያስመዘገበው ስኬት ለበርካታ ወጣቶች መነሳሳት መሆኑን አፅንዖት ሰጥቷል።
47 221
“ለምን ዝም አላችሁ?” የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው
#FastMereja I ብለ ብሎ ሩዥ ፋውንዴሸን (BBRF) የውባንቺ ፕሮጀክት ከእንግሊዝ አገር ከመጣው የካዙም አርትስ (Kazzum Arts) የቴአትር ጥበባት ቡድን ጋር በመተባበር “ለምን ዝም አላችሁ?” በሚል መሪ ቃል በፆታዊ ጥቃት ዙርያ የተዘጋጀ ታላቅ የታዳጊዎች የጥበባት ዐውደ ርዕይ እና የሙዚቃዊ ተውኔት ትርዒት መርሃ-ግብር ይፋ ማድረጉን አስታወቀ።
እንደ ፋውንዴሸኑ ገለጻ፣ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ፌስቲቫል ካለፈው ዓመት ከረምት ጀምሮ በሞባይል ፎቶግራፊ፣ በቴአትር፣ በሙዚቃ እና በዳንስ ስልጠና እና ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ታዳጊዎች የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበት እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደደውን የሴቶች ጾታዊ ጥቃት ችግር በጥበብ መነጽር የሚሞግቱበት ታላቅ መድረክ ነው።
የBBRF የውባንቺ ቤተሰብ አስተባባሪ ኮሚቴ በሳፋየር ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ እንዳደረገው፣ የፌስቲቫሉ ዋና ዋና መርሃ-ግብሮች:-
📌 የኪነጥበብ ትርዒት መድረክ፦ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ልዩ ልዩ ሙዚቃዊ ድራማዎች፣ ሥነ-ግጥሞች፣ የሙዚቃ እና የዳንስ ትርዒቶች ለሕዝብ ይቀርባሉ።
📌 የሞባይል ፎቶግራፊ አውደ ርዕይ፦ ከጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት በሚገኘው ከሪኤቲቭ ሃብ (Creative Hub) የፎቶ ኤግዚቪሽን ሴንተር ውስጥ በታዳጊዎች የተነሱ ድንቅ የሞባይል ፎቶግራፎች ለ15 ቀናት ያህል ለሕዝብ ክፍት ሆነው ይቆያሉ።
📌 የ #ውባንቺ ማኅበራዊ ሚዲያ ውድድር፦ ሕዝቡን በንቃት ለማሳተፍ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ስለ ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ማቆም መልዕክት ያላቸውን የሞባይል ፎቶግራፎች በ #ውባንቺ ሃሽታግ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ከሚያጋሩ ተሳታፊዎች መካከል አሸናፊ ለሚሆን አንድ ተሳታፊ ልዩ የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል።
ዝግጅቱ ታዳጊዎች በጥበብ አማካኝነት የማኅበረሰብ ለውጥ ለማምጣት ያላቸውን አቅም የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ ጥቃትን በጋራ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተመላክቷል።
47 221
8ኛው ግራንድ አፍሪካን ረን በአሜሪካ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
#FastMereja | 8ኛው ዓመታዊ የግራንድ አፍሪካን ረን (Grand African Run) ትናንት፣ ኦክቶበር 10፣ 2026 በአሜሪካ በደማቅ ሁኔታ መካሄዱ ተገለጸ።
ይህ ዓመታዊ የሩጫ ዝግጅት የአፍሪካውያንን አንድነት፣ አብሮነትና በማኅበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር ታስቦ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ዘንድሮም ለ8ኛ ጊዜ መካሄዱ የመርሃ ግብሩን ቀጣይነት የሚያሳይ ሆኗል። ዳሸን ባንክ በዚህ ዝግጅት ላይ በአጋርነት በመሳተፍ፣ ከአፍሪካውያን ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ጋር የሚያገናኙ ማኅበራዊና የአብሮነት መርሃ ግብሮችን የመደገፍ ሚናውን አሳይቷል፡:
47 221
በደቡብ ወሎ ድንገተኛ የእሳት አደጋ 56 ቤቶች ወደሙ
#FastMereja I በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 18 ቀበሌ «ምስትንክር» በተባለ ጎጥ በተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ 56 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለጸ። ከተቃጠሉት ቤቶች መካከል 52ቱ የሳር እንዲሁም 4ቱ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መሆናቸው ታውቋል።
በዚህ ድንገተኛ አደጋ የ30 አበወራ እና እማወራ አባላት የሆኑ 171 የህብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል። ከቤቶቹ ውድመት በተጨማሪ 348 ኩንታል እህል፣ የቤት እንስሳት እና ሙሉ የቤት እቃዎች በእሳቱ መቃጠላቸው ተረጋግጧል።
የወረዳው አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቡድን በአደጋው ምክንያት ለተጎዱትና መጠለያ አልባ ለሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች አስቸኳይ የድንገተኛ እርዳታ እንዲደረግ የደላንታ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጥሪ አቅርቧል።
47 221
ኦሮሚያ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱን ከ105.7 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱን አስታወቀ
#FastMereja I ኦሮሚያ ባንክ በ2025/2026 የበጀት ዓመት በሁሉም ዋና ዋና ቁልፍ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ። የባንኩ 17ኛው መደበኛ እና 6ኛው አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የተካሄደ ሲሆን፤ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አስፋ ስሜ ለጉባዔው ዓመታዊ የስራ ሪፖርት አቅርበዋል። እንደ ባንኩ መግለጫ፣ የፋይናንስ ዘርፉ በአለም አቀፍ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች እየተፈተነ ቢገኝም፣ ባንኩ ለፈተናዎቹ ሳይበገር ጠቅላላ ሀብቱን ከ105.7 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል። ይህ አፈፃፀም ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ24 በመቶ እድገት አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 88.1 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታል በ14 በመቶ በማደግ 7.8 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ካፒታል ደግሞ 14 ቢሊዮን ብር ደርሷል። እንዲሁም በሂሳብ ዓመቱ 15.24 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ከዲሲፕሊን ጋር ከተመራ የወጪ አስተዳደር ጋር ተዳምሮ ከታክስ በፊት 3.82 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ተገኝቷል። ይህ የትርፍ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም የባንኩ የተበላሸ ብድር (NPLs) ምጣኔ 2.43 በመቶ በመሆን በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የተሻለ የብድር ጥራት ካላቸው ቀዳሚ ባንኮች ተርታ አሰልፎታል። የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 5.7 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ባንኩ ከአለም አቀፍ የዲጂታል ክፍያ መሪ ከሆኑት ቪዛ (Visa) እና ፕሪሚየር ስዊች ሶሉሽንስ (PSS) ጋር በመተባበር “ኦሮ ቪዛ ክላሲክ”፣ “ጎልድ” እና “ፕላቲንየም” የተሰኙ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን ለአገልግሎት አብቅቷል። በጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይም ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የኮርፖሬት ገቨርነንስ መመሪያ መሰረት ለቀጣይ 3 ዓመታት ባንኩን የሚመሩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዷል።
47 221
አድማስ ዩኒቨርሲቲ 18ኛውን ዓመታዊ ዓለም አቀፍ ጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ አካሄደ!
#Fastmereja:-አድማስ ዩኒቨርሲቲ 18ኛውን ዓመታዊ ዓለም አቀፍ ጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በዛሬዉ እለት በፍሬንድሽፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሂዷል።
ኮንፍረንሱ “በምስራቅ አፍሪካ የግል ከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት ዋና ተልዕኮዎች፣ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና
እድሎች፡ ጥራት ያለው የትምህርት አቅርቦት፤ ተገቢ
ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል ነዉ የተካሄደዉ።
መድረኩ የምርምር ባህልን ለማጠናከር እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ያለመ ሲሆን በኢትዮጵያ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የውስጥና የውጭ የቁጥጥር ስልቶች በጥብቅ እየተተገበሩ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በቅርቡ ከተካሄዱ ውይይቶችና ቃለ-መጠይቆች እንደተመለከተው፣ የትምህርት ጥራት በአንድ ጊዜ ተጠናቆ የሚቋጭ ሳይሆን ከጊዜና ሁኔታዎች ጋር አብሮ የሚሻሻል ቀጣይነት ያለው ሂደት መሆኑ ተገልጿል።
በዘርፉ የተሰማሩ አመራሮች እንዳመለከቱት፣ ተቋማት ጥራታቸውን የሚያረጋግጡት በራሳቸው የጥራት ማረጋገጫ ቢሮዎች (Quality Assurance Offices) እና በመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት በሚወጡ መስፈርቶች አማካይነት መሆኑን አስረድተዋል።
በየደረጃው ያሉ የትምህርት ፕሮግራሞች (የመጀመሪያ፣ የሁለተኛና የሶስተኛ ዲግሪዎች) በየአምስት ዓመቱ የፈቃድ እድሳት ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት በተካሄደ የዳግም ምዝገባ ግምገማ በአዲስ አበባ ከተማ ከተገመገሙ ተቋማት መካከል ጥቂቶቹ ብቻ መስፈርቱን አሟልተው ማለፋቸው ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥናትና ምርምር ስራዎች ከባህላዊ የምዕራባውያን መጻሕፍትን ከማስታወስ ወጥተው፣ ከሀገሪቱ ወቅታዊ እውነታዎችና ማህበረሰባዊ ችግሮች ጋር የተገናኙ (Relevant Research) እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቷል።
የምርምርውጤቶች በመደርደሪያ ላይ ከመቀመጥ ይልቅ ለፖሊሲ አውጪዎች መረጃ የሚያስገኙ፣ ውስብስብ የአካዳሚክ ግኝቶችን ወደ ተጨባጭ ምርቶችና አገልግሎቶች በመቀየር የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ችግሮች የሚፈቱ መሆን እንዳለባቸው ጥሪ ተደርጓል።
በዚሁ መድረክ ላይ ታዋቂው የኢትዮጵያ ምሁርና የአካዳሚ መሪ ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ሀይሌ በባዮሎጂ እና ስነ-ምህዳር መስክ ያደረጓቸውን ጥናቶችና ትምህርታዊ አስተዋጽኦዎች ያቀረቡ ሲሆን፣ ምርምርን መሠረት ያደረገ ትምህርት ለሀገር እድገት ያለውን ወሳኝ ሚና አስረድተዋል።
47 221
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ 1ሺህ 102 ተማሪዎችን አስመረቀ
#FastMereja I በአቪዬሽን ዘርፍ ፍቃድ በማግኘት ቀዳሚው የግል ኮሌጅ እንደሆነ የሚነገርለት ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ፣ አሁን ወደ ኤሮስፔስ ዩኒቨርሲቲ ከፍ ለማለት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታወቀ። ተቋሙ ይህንን የገለጸው ለ13ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ባስመረቀበት መርሃ ግብር ላይ ነው።
በዕለቱ ከተመረቁት ከ1 ሺህ 102 ተማሪዎች ውስጥ ከ400 በላይ የሚሆኑት በቀጥታ በአቪዬሽን ዘርፍ የሠለጠኑ ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል። ኮሌጁ በአውሮፕላን ጥገና ቴክኒሻንነት፣ በፍላይት ኦፕሬሽን፣ በበረራ አስተናጋጅነት፣ በአደገኛ ዕቃዎች አስተዳደር እና በክሩ ሀብት አስተዳደር ለማስተማር ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እውቅና አግኝቷል። በተጨማሪም ከካናዳ ሞንትሪያል ከተማ ከመጣው ዓለም አቀፍ የኤር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) እና ከእንግሊዝ ሀገር ሃምፕሻየር ከሚገኘው Institute of Commercial Management (ICM) ዓለም አቀፍ እውቅናዎችን ማግኘቱ ተመላክቷል።
የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል እና የናሽናል ኤርዌይስ እህት ኩባንያ የሆነው ይህ ተቋም፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሙያና ቴክኒክ እንዲሁም በአቪዬሽን ፕሮግራሞች የሰለጠኑ ምረቃዎችን አስመርቋል። አሁን ላይ እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀው በ2020 ዓ.ም የትምህርት ፈቃዱ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅና ተቋሙ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከፍ እንደሚል የኮሌጁ ዲን ጉሩም ተስፋዬ ለፋስት መረጃ ገልጸዋል። ይህ ሲሆንም በዘርፉ በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የግል ኤሮስፔስ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያስብለው ዲኑ አክለው አስረድተዋል።
47 221
🩸🩸TOMI TOMI TOMI TOMI 🩸🩸
TOMI PHOTO VELO AND MEKEUP 💯
አዲሱን አመት በማስመልከት ልዩ ልዩ packag ይዘንሎት መተናል ከ 9,500studio package ጀምሮ እስከ 68,900ብር studio + musk + transoprt ያጠቃለለ lexury package ያገኛሉ
በስራችን ደስተኛ እደምትሆኑ ጥርጥር የለንም👍🙏🙌🏻
አዲስ ባስገባነው እጅግ ውብ እና ዘመናዊ ቬሎዎች 💯🎁TOMI PHOTO VELO AND MEKEUP 💯
የደንበኞቻችንን አንጀት የሚያርስ ሁሉንም በአንድ የያዘ እና ጥራት ያለው የመስክና የስቱዲዩ ፎቶ ፕሮግራም እና ሙሉ አልባሳት በአንድ ጥቅል አዘጋጅተናል፡፡
ይምጡና ይጎብኙን!
🛑Tomi photo and velo 🛑
* የመስክ እና ስቱዲዩ ፎቶ
* ሜካፕ፣ ጥፍር፣ ፀጉር
* ቬሎ፣ ሱፍ፣ ካባ፣
* ሌሎች አልባሳትን የያዙ ጥቅሎች
🛑 Tomi Tomi Tomi Tomi 🛑
🩸Tomi Luxry package 58,000 ብር
• Mesk video
• Laminate album 30 X 90 -10(20) page
• Board photo 60*90(ባለመስታወት)
. Hexagon (ተገጣጣሚ) board _ 10 pc
. 3 pc frame photo
• Sign board 1
• Thank you cared -200
• Save the date 5 photo
• Slideshow
• All soft copy
የሰርግ አልባሳት
• 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት)
• 2 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት) 1 color
• ካባ (በመረጡት አይነት)
• 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት)
. የ አፍሪካ ልብስ
• የሀበሻ ቀሚሽ
• የእራት ቀሚስ
• ሜካፕ 👰🏻
• ጥፍር
• ፀጉር
. የ መስክ እና ስቱዲዮ አበባ (1)
• የወንዶች የውበት ሳሎን
. ትራንስፖት ጨምሮ
ይህን ሁሉ 🔥በ58,000 ብር ብቻ
🩸Luxry package 45,000 ብር
•musk video
• Laminate album 30 X 90 -10(20) page
• Board photo 50*80
. bourd photo 40*60
• 8 pc hexagon photo
• Sign board 1
• Thank you cared -200
• Save the date 5 photo
• Slideshow
• All soft copy
የሰርግ አልባሳት
• 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት)
• 2 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት) 1 color
• ካባ (በመረጡት አይነት)
• 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት)
. የ አፍሪካ ልብስ
• የሀበሻ ቀሚሽ
• የእራት ቀሚስ
• ሜካፕ 👰🏻
• ጥፍር
• ፀጉር
. የ መስክ እና ስቱዲዮ አበባ (1)
• የወንዶች የውበት ሳሎን ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ45,000 ብር ብቻ
🩸Luxry package 40,000 ብር
• Musk vedio
• Laminate album 30 X 90-10(20)page
• Board photo 50X80-1
• Sign board 1
. 6 pc hexagon
• Thank you cared -200
• Save the date 5 photo
• Slideshow
• All soft copy
የሰርግ አልባሳት
• 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት)
• 2 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት) 1 color
• ካባ (በመረጡት አይነት)
• 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት)
. የ አፍሪካ ልብስ
• የሀበሻ ቀሚሽ
• የእራት ቀሚስ
• ሜካፕ 👰🏻
• ጥፍር
• ፀጉር
• የወንዶች የውበት ሳሎን ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ40,000ብር ብቻ
🩸Premium pakage 2 -34,000ብር
• Laminate album 30 X 90 -10 (20) page
• Board photo 50X80-1
• Sign board 1
• Thank you cared -200
• Save the date 5 photo
• Soft copy All
• Slideshow
የሰርግ አልባሳት
• 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት)1 color
• 1 ቬሎ የስቱዲዩ (በመረጡት አይነት)
• ካባ (በመረጡት አይነት)
• 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት)
. የ አፍሪካ ልብስ
• የሀበሻ ልብሽ
• የእራት ቀሚስ
• ሜካፕ 👰🏻
• ጥፍር
• ፀጉር
• የወንዶች የውበት ሳሎን ጨምሮ ይህን ሁሉ 🔥በ34,000ብር ብቻ
🩸Special package (2) -26,000
መስክ ወይም ስቱዲዩ
• Laminate album 30 X 90 -10 (20) page
• Sign board 1
• Thank you cared -200
• Soft copy All
• Save the date 5 photo
.Make up👰🏻
. ጥፍር
. ፀጉር
የሰርግ አልባሳት
• 2 ቬሎ የመስክ ወይም የ ስቱዲዮ (በመረጡት አይነት)1 color
• ካባ (በመረጡት አይነት)
• 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት)
• የሀበሻ ልብስ
. የ አፍሪካ ልብስ ጨምሮ ይህን ሁሉ
🔥በ26,000ብር ብቻ
🩸Mini package 1 (studio or musk) 20,000
መስክ ፎቶ እና የሰርግ አልባሳት
• Bourd photo 50*80
• Soft copy All
• Save the date 5 photo
. Make up👰🏻
. ትፍር
. ፀጉር
የሰርግ አልባሳት
• 2 ቬሎ የመስክ ወይም የ ስቱዲዮ (በመረጡት አይነት)1 color
• ካባ (በመረጡት አይነት)
• 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት)
ይህን ሁሉ 🔥በ20,000ብር ብቻ
🩸Luxury Musk package 15500
👉የመስክ ፎቶ እና የሰርግ አልባሳት
.Musk Vedio
• Soft copy All
• Save the date 5 photo
. Make up👰🏻
. ጥፍር
. ፀጉር
• 2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት)1 color
• 2 ሱፍ (በመረጡት አይነት)
• ካባ
• የሀበሻ ልብስ
•የ አፍሪካ ልብስ
ይህን ሁሉ ጨምሮ 🔥በ15500 ብር ብቻ
🩸only studio package በ9,500ብር ብቻ)
. 1 ቬሎ (በመረጡት አይነት)
. 1ሱፍ ( በመረጡት አይነት)
.የ ሀበሻ ልብስ
. ካባ
. All soft copy
ይህን ሁሉ 🔥በ 9,500ብቻ
👉አድራሻ: ቁ.1 አዲስ አበባ 22 ከ አክሱም ሆቴል ወረድ ብሎ ትጋት ህንፃ 2ተኛ ፎቅ F1-03
✅አሁኑኑ ደውለው ኦርደር ያርጉ👇
☎️ 0926455964 (አአ)
☎️ 0916715634
47 221
“ለምን ኦሮሚያ ዘፈን ታወጣለህ ተብዬ የዘረኝነት ስድብ መመልከቴ አሳዝኖኛል ” ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ
#FastMereja I ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በሥራዎቹ እና በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ሲሰነዘሩ ለነበሩ አከራካሪ አስተያየቶች ምላሽ መስጠቱን ከራሱ ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ መልእክት ለማወቅ ተችሏል። ድምፃዊው አብዛኛውን ጊዜ ከሥራዎቹ ባሻገር በቃላት ምልልሶች ውስጥ የመሳተፍ ልምድ እንደሌለው በመግለጽ፣ በቅርቡ በተመለከታቸው አንዳንድ አስተያየቶች የተሰማውን ቅሬታና ሀዘን ገልጿል።
ጃኪ ጎሲ ቀደም ሲል ባቀረባቸው በርካታ ሙዚቃዎች በአማርኛ፣ በትግርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች በመጠቀም ኢትዮጵያዊነቱን በተግባር ለማሳየት መሞከሩን አምላክቶ፣ ወደፊትም በዚህ መንገድ ከመቀጠል ወደኋላ እንደማይል አረጋግጧል። ሆኖም አሁን በለቀቀው ነጠላ ዜማ ምክንያት በተወሰኑ ወገኖች ዘንድ የሚሰነዘሩትና ዘረኝነትን የሚያስፋፉ አስተያየቶች ለትውልድ አርአያ የማይሆኑና ደስ የማያሰኙ መሆናቸውን ጠቁሟል።
“ነገሮችን ለምን በመልካም መንገድ አናይም?” ሲል ጥያቄ ያቀረበው ድምፃዊው፣ “በትንሹ ነገር እንዲህ እየተለያየን እንዴት ነው በአንድ ሀገር አንድ ሆነን መኖር የምንፈልገው?” በማለት የህብረት እና የፍቅር አስፈላጊነትን አሳስቧል። በመጨረሻም የፍቅር እና የአንድነት መልእክቱን በማስተላለፍ አድናቂዎቹ እና ህዝቡ ለተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች አዎንታዊ እይታ እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርቧል።
47 221
ቃል ኢንተርናሽናል የውበት ማሰልጠኛ ተቋም በተለያዩ በዉበት መስኮች ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች አስመረቀ!
#Fastmereja:ቃል ኢንተርናሽናል የዉበት ማሰልጠኛ ተቋም ለ47ተኛ ዙር በተለያዩ የዉበት መስኮች ያሰለጠናቸዉን ከ50 በላይ ተማሪዎችን በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ።
በዛሬዉ እለት በሜካፕ፣ በጥፍር፣ በጸጉር በአይላሽ ሽፋሽፍት የውበት ሞያ ዘርፎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነዉ ያስመረቀዉ።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የዲጂታል እና የመደበኛ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች፣ በውበት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች/የድርጅት ባለቤቶች እና የተማሪዎች ወዳጅ ዘመዶችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የቃል ኢንተርናሽናል የዉበት ማሰልጠኛ ተቋም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የውበት ትምህርት ለማድረስ ካለው ቁርጠኛነትና ትጋት ባለፈ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ እና ከፍለው መማር የማይችሉ ሴቶችን በመደገፍና በማበረታታት የሞያ ባለቤት በማድረግ ብሩህ ተስፋ ያላቸውና የፋይናንስ ነጻነት ያላቸው አምራች ዜጎች እንዲሆኑ እድሎችን በማመቻቸት ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ስመጥር ድርጅት ነው፡፡
ቃል ኢንተርናሽናል የዉበት ማሰልጠኛ ተቋም ከተለያዩ የአውሮፓ ተቋማት ጋር የሀገራችን የውበት ኢንዱስትሪ ደረጃ ለማሳደግ እና ለተማሪዎች የስራ እድሎችን ለማስፋት በስፋት እየሰራም የሚገኝ ሲሆን በአሁን ወቅት ተደራሽነቱን በማስፋት በካናዳ በተለያዩ ስቴቶች በርካታ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ትገኛለች።
47 221
ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የሴንቸሪ ሪል እስቴት ይፋዊ የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ!
#Fastmereja:- ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (ሴንቸሪ ሪል እስቴት) ተወዳጁን ድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ይፋዊ የብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾመ።
ድርጅቱ አምባሳደሩን ይፋ ያደረገው “ደሞ በዚህ ላይ… ሥራዎቻችን ምስክሮቻችን!” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ልዩ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ-ግብር ላይ ነው።
በኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በብረታ ብረት እና በማዕድን ዘርፎች የ70 ዓመታት የንግድ ታሪክ ያለው ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ባለፉት 30 ዓመታት በሪል እስቴት ዘርፍ ጠንካራ ስም መገንባት ችሏል።
ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ በአዲስ አበባ 16 ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይለንግድ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ የሚሆኑ ዘመናዊ ህንፃዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል።
ከተጠናቀቁና ለባለቤቶቻቸው ከተረከቡ ፕሮጀክቶቹ መካከል በቦሌ መድኃኒያለም የሚገኘው ሴንቸሪ
ራዲያንስ፣ በቦሌ ብራስ የሚገኘው ሴንቸሪ አዲስ ትሬዠር፣ በቦሌ አትላስ የሚገኘው ሴንቸሪ ሼባ ሆምስ፣ በካሳንቺስ የሚገኘው ሴንቸሪ ሴንትራል፣ በተክለሃይማኖት የሚገኘው አስመን ተክለሃይማኖት እንዲሁም በቦሌ ቡልቡላ የሚገኘው ኦክ አፓርትመንት ይጠቀሳሉ።
ከንግድ እንቅስቃሴው በተጨማሪ ድርጅቱ ሁለገብ ማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል ለ2,000 በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣ በየካ ክፍለ ከተማ በገነባው የምግብ ማዕከል በየቀኑ ለ250 በላይ ወገኖች የምግብ አገልግሎት መስጠት፣ከ500 በላይ አረጋውያንን በቋሚነት በበጀት መደገፍ ይጠቀሳል።
እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከ50 በላይ አዳዲስ ቤቶችን ገንብቶ ማስረከብ እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ፣ በሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች (በገበታ ለትውልድ፣ በገበታ ለሀገር፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በኮሪደርልማት) ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይገኙበታል።
ሴንቸሪ ሪል እስቴት ከአዲሱ የብራንድ አምባሳደሩ ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ ጋር በመሆን በኦሎምፒያ፣ ሜክሲኮ፣ ቦሌ ሰላም መንገድ እና ሴቶች አደባባይ አካባቢ የሚያከናውናቸውን አዳዲስ ግንባታዎች አፋጥኖ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጿል።
47 221
አዋሽ ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር አምስት አዳዲስ የክፍያ ካርዶችን ይፋ አደረገ
#FastMereja I አዋሽ ባንክ ከአለም አቀፉ የክፍያ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ማስተርካርድ ጋር በመተባበር፣ የደንበኞችን ፍላጎት ያማከሉ አምስት አዳዲስ እና ልዩ ጥቅም የሚያስገኙ የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም የሀገር ውስጥ የክፍያ ካርዶችን ይፋ አደረገ። ባንኩ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. በኢሊሊ ሆቴል ባካሄደው ይፋዊ ስነ-ስርዓት፣ አዲሶቹን የካርድ ክፍያ አማራጮች ለግል ተጠቃሚዎች እና ለድርጅት ደንበኞች አስተዋውቋል። አዲሶቹ ካርዶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ገበያን ለማሻሻል ካወጣው መመሪያ ጋር ተጣጥመው የተዘጋጁ መሆናቸው ተገልጿል።
በዚህም መሰረት ይፋ ከተደረጉት አምስት የካርድ አይነቶች መካከል ለአለም አቀፍ ግብይት የሚያገለግሉት፡- “አዋሽ ወርልድ ኤሊት ዴቢት” (Awash World Elite Debit)፣ “አዋሽ ፕላቲነም የቅድመ ክፍያ” (Awash Platinum Prepaid)፣ “አዋሽ ጎልድ የቅድመ ክፍያ” (Awash Gold Prepaid) እና ለድርጅቶች የታለመው “አዋሽ ኮርፖሬት የቅድመ ክፍያ” (Awash Corporate Prepaid) ካርዶች ይገኙበታል። በተጨማሪም በሀገር ውስጥ በኤቲኤም (ATM) እና በPOS መሳርያዎች ላይ በንክኪ አልባ (Contactless) ቴክኖሎጂ የሚሰራው “አዋሽ ፕላስ” የዴቢት ካርድ ለተጠቃሚዎች ቀርቧል።
እነዚህ ካርዶች የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ላላቸውም ሆነ ለሌላቸው ዜጎች፣ ለኦንላይን (E-Commerce) ግብይት፣ ለጉዞ እና ለተለያዩ የድርጅት ወጪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሺፈራው እንደገለጹት፤ አዲሶቹ የካርድ ምርቶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወሰደው የፋይናንስ ሪፎርም መሰረት የተዘጋጁ እና የደንበኞችን የዲጂታል ክፍያ ፍላጎት ዘመናዊ በሆነ መንገድ የሚያሟሉ ናቸው። የማስተርካርድ ምስራቅ አፍሪካ እና ህንድ ውቅያኖስ ደሴቶች ሲኒየር ምክትል ፕሬዚዳንት እና ካንትሪ ማኔጀር ሸህሪያር አሊ በበኩላቸው፣ ከአዋሽ ባንክ ጋር የተደረገው ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ስነ-ምህዳርን ለማጠናከር እና አካታች የፋይናንስ አገልግሎትን ለማስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
አዲሶቹ የካርድ ምርቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉ የዲጂታል ክፍያዎችን በቅልጥፍና እንዲፈጽሙ የሚያስችሉ መሆናቸው ተመላክቷል።
47 221
“ዞር ስል ወደ ኋላ ታሪኬ ሚናገረው ባወራው ማላፍርበት ረዳቴ እግዚአብሔር ነው’’ አዲሱ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዶክተር አ
“ዞር ስል ወደ ኋላ ታሪኬ ሚናገረው ባወራው ማላፍርበት ረዳቴ እግዚአብሔር ነው’’ አዲሱ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዶክተር አክሊሉ ታደሰ
#FastMereja I አዲሱ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዶክተር አክሊሉ ታደሰ በተሰጣቸው አዲስ የመንግሥት ሹመት ዙሪያ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የተጣለባቸውን ከፍተኛ አደራና ኃላፊነት በመረዳት ሀገራቸውን በታማኝነትና በአገልጋይነት መንፈስ ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ። ሚኒስትሩ በሰጡት አጭር መግለጫ፣ የተሰጣቸው አደራ ትልቅ ክብር ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ሸክም መሆኑን ጠቁመው፣ የተጣለባቸውን እምነት ምክንያት በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ ጸጋዎች ያሏት ታላቅ ሀገር ብትሆንም አሁንም ድረስ ያሉባትን ተቃርኖዎችና ፈተናዎች ለመቅረፍ በትጋት መስራት እንደሚገባ ዶክተር አክሊሉ አሳስበዋል። በተለይም የወጣቶችን አቅም በማስተባበርና የጋራ ጥረት በማድረግ፣ በኢኮኖሚ የበለፀገች፣ የተረጋጋችና አንድነቷ የጸናች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የበኩላቸውን ታሪካዊ ድርሻ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
”ያለብን ኃላፊነት ሉዓላዊነቷና አንድነቷ የተጠበቀ፣ የምታመርትና የበለፀገች ሀገር ግንባታ ላይ ክንዳችንን ማረባረብ ነው” ያሉት አዲሱ ሚኒስትር፣ በጋራ በመስራትና በትጋት በመንቀሳቀስ የበለፀገች ሀገር መሰረት የመጣል ታሪክ እንደሚጻፍ እምነታቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም “እኛ እንሮጣለን ፈጣሪ ያሳካልናል” ሲሉ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።
47 221
ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት «ጀቢና» ፊልም መስከረም 30 ቀን በነፃ ለዕይታ ይቀርባል!
#Fastmereja:- በወ/ሮ ሄለን ሸቱ እውነተኛ የሕይወት ታሪክ ላይ የተመሠረተው «ጀቢና» (Jebena) የተሰኘው አዲስ የፊልም ሥራ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም በሕፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ለሕዝብ በነፃ እንደሚታይ በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገለፀ።
«ሐበሻ ቪው» (Habesha View) የፊልም ስትሪሚንግ ፕላትፎርም ከፊልሙ አዘጋጆች ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ልዩ መርሃ ግብር ዙሪያ የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ሳሙኤል ተሻገር እንዲሁም የ«ሐበሻ ቪው» ተወካዮች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው የሀገር ውስጥ ፊልሞችን ለማስፋፋት፣ የተቀዘቀዘውን የሲኒማ ባህል ለማጠናከር እና የዲጂታል ስትሪሚንግ አማራጮችን ከባህላዊ የሲኒማ እይታ ጋር ለማስተዋወቅ ታስቦ መሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።
ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት «ጀቢና» ፊልም ከ170 በላይ ተዋንያን እና ከ30 በላይ የፊልም ሙያተኞች የተሳተፉበት ሲሆን፤ ቀረጻው በወንጂ፣ በአዳማ ቆቃ እና በአዲስ አበባ ከተሞች መከናወኑ ተጠቅሷል። ፊልሙ ቀደም ሲል እ.አ.አ በ2018 በለንደን በተካሄደው 6ኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ለአይታ መቅረቡም ይታወሳል።
በዕለቱ ከፊልሙ ማሳያ በተጨማሪ የታሪኩ ባለቤት የወይዘሮ ሄለን ሸቱ ምሰሶዋ የተሰኘ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ለተመልካቾች የሚቀርብ ሲሆን፣ ታዳሚዎች ከታሪኩ ባለቤትና ከፊልሙ አዘጋጆች ጋር ጥያቄና መልስ የሚያደርጉበት መድረክ እንደሚመቻች ተገልጻል።
መርሃ ግብሩ ሙሉ በሙሉ በነፃ የተዘጋጀ በመሆኑ ማንኛውም የፊልም አፍቃሪ ከቤተሰቡ ጋር በመገኘት የኪነ-ጥበብ ምሽቱ አካል እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
47 221
በ8 ወራት ተጠናቆ የሚረከበው የሜሪት ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ የንግድ ህንጻ ኤክስፖ ተከፈተ!
#Fastmereja:- ሜሪት ፕሮፐርቲስ (Merit Properties) በመርካቶ ተክለሃይማኖት አካባቢ በ6,700 ካሬ ሜትርየቦታ ስፋት ላይ የሚያስገነባውንና ሙሉ በሙሉ ለንግድ ሱቆች እንዲሁም ለኮሜርሻል አገልግሎት የሚውል ባለ 5 ፎቅ (G+5) ዘመናዊ የንግድ ህንጻ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ይፋ አደረገ።
ይህ የንግድ ህንጻ በ8 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለደንበኞች የሚረከብ ሲሆን፣ አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱም በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
ህንጻው ከ11 እስከ 32 ካሬ ሜትር እና ከዚያ በላይ ስፋት ያላቸውን የንግድ ቦታዎች ለነጋዴዎችና ለባለሀብቶች አማራጭ አድርጎ አቅርቧል።
ሜሪት ፕሮፐርቲስ በዘርፉ ከተለመደው አሰራር ወጥቶ አዳዲስ አሰራሮችን መተግበሩን የጠቆመ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የንግድ ቦታዎችን በኔት ኤሪያ (Net Area) ብቻ መሸጥ፣ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ (No Escalation Rate) በቋሚ ዋጋ ማረከብ እና ህንጻውን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ (Fully Finished) ማስረከብ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
ድርጅቱ ለደንበኞቹ ከ10% ጀምሮ በሚከፈል ቅድመ ክፍያ ሽያጭ የጀመረ ሲሆን፣ እንደ ክፍያ ሁኔታቸው እስከ 20% የሚደርስ ቅናሽ ማዘጋጀቱ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ኩባንያው የግንባታውን ሂደት በአካል ለማሳየት ያዘጋጀው ልዩ «ሜሪት ኤክስፖ» በዛሬው እለት የተከፈተ ሲሆን፣ እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል።
በኤክስፖው ወቅት በ4ኛ እና 5ኛ ፎቅ ላይ ለሚገዙ ደንበኞች እስከ 25% የሚደርስ ልዩ የዋጋ ቅናሽ መደረጉ ተብራርቷል።
47 221
ኦሮሚያ ባንክ ዓለም አቀፍ የቪዛ ካርድ አገልግሎት ማስጀመሩን ይፋ አደረገ
#FastMereja I ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ. የዲጂታል ባንክ አገልግሎቱን ለማስፋፋት እና ለደንበኞቹ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ የሆነ የክፍያ አማራጭ ለማቅረብ ከቪዛ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የቪዛ ካርድ አገልግሎት በይፋ ማስጀመሩን አስታወቀ።
የማስጀመር ስነ-ስርዓቱ ዛሬ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፤ በስነ-ስርዓቱ ላይ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተወካዮች፣ የቪዛ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የኦሮሚያ ባንክ የቦርድ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች፣ የባንክ ዘርፍ መሪዎች፣ የንግድ አጋሮች እንዲሁም የብዙኃን መገናኛ ተወካዮች ተገኝተዋል።
ይህ አዲስ አገልግሎት ኦሮሚያ ባንክ እያካሄደ ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚያፋጥንና የደንበኞችን የፋይናንስ ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። በአዲሱ የቪዛ ካርድ አገልግሎት አማካኝነት ደንበኞች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የቪዛ ክፍያ ተቀባይ ቦታዎች ላይ ህጋዊ ደንቦችን፣ የካርድ ገደቦችን እና የአገልግሎት ውሎችን በማክበር ግብይት መፈጸም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳሰረውን የክፍያ መረብ መጠቀም ይችላሉ።
አገልግሎቱ ደንበኞች ወደ ውጭ አገር በሚጓዙበት ወቅት ከፍተኛ የሚሰጥ ሲሆን፤ ኦንላይን ግብይቶችን ለመፈጸም፣ ለዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ክፍያ ለመክፈል እና ሌሎች ህጋዊ የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን ለማከናወን ያስችላቸዋል።
ካርዱ Classic፣ Gold እና Platinum የተሰኙ ሦስት ዓይነት ዓለም አቀፍ የቪዛ ካርዶች ናቸው።
የባንኩ አመራሮች እንደገለጹት፣ ከቪዛ ጋር የተደረገው ይህ አጋርነት ባንኩ ደንበኞቹን ከዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ጋር ለማገናኘት፣ የክፍያ አማራጮቹን ለማስፋፋት እና የዲጂታል ባንክ አገልግሎቱን ለማጠናከር ለያዘው ሰፊ ስትራቴጂ ትልቅ ማሳያ ነው።
47 221
ሐበሻ ቢራ ኢትዮጵያ ቡናን በ60 ሚሊዮን ብር ስፖንሰር አደረገ
#FastMereja I ሐበሻ ቢራ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩውን ከሚያከብረው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ጋር የነበረውን አጋርነት ማደሱን ይፋ አደረገ። የመጀመሪያ ምርቱን ለገበያ ከማውጣቱ ከአንድ ዓመት በፊት ከክለቡ ጋር አብሮ መስራት የጀመረው ሐበሻ ቢራ፤ አሁን ደግሞ ድጋፉን በማሳደግ ከእያንዳንዱ የቢራ ጠርሙስ ሽያጭ ድርሻ ማጋራት የሚያስችለውን አዲስ ስምምነት ተፈራርሟል። የስምምነት ፊርማው የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ተከናወኗል።
በዚህ አዲስ ስምምነት መሠረት ሐበሻ ቢራ የዘንድሮውን ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ያደገ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእያንዳንዱ የሐበሻ ቢራ ሽያጭ ላይ ለክለቡ ተጨማሪ ገቢ ለማጋራት ወስኗል። ይህም የቢራ ፋብሪካው ባደገ ቁጥር ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የሚሰጠው ድጋፍ አብሮ የሚያድግበትን አሰራር የዘረጋ መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ ክለቡ አዳዲስ አመራሮችን ወደ ኃላፊነት እያመጣ ባለበት ወቅት የተደረገ ሲሆን፣ ሐበሻ ቢራም የዚህ አዲስ ምዕራፍ አካል ለመሆን ያለውን ጽኑ ፍላጎት አረጋግጧል።
የሐበሻ ቢራ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደገለጹት፤ “12 ቁጥር ለባለ 12 ለባሾቹ የቡና ደጋፊዎች ለክለባቸው ያላቸው ፍቅር እና ድጋፍ በከፍታውም በዝቅታውም ጊዜ እንደማይቋረጥ ሁሉ፤ እኛም እንደዚሁ ነን” ብለዋል። አክለውም ድጋፋቸው ከክለቡ ጎን ለመቆም ባላቸው የማይናወጥ ጽኑ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው፤ የክለቡ የተሳካ የ50 ዓመታት ጉዞ የሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ደጋፊዎች የጋራ ጥረት ድምር ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና ሀበሻ ቢራ ስፖንሰርሺፕ በ45 ሚሊዮን ብር ተፈራርሟል። በተጨማሪም ከቢራ ሽያጭ ላይ የሚሰበሰበ ከ13 እስከ 15 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ ከ58 እስከ 60 ሚሊዮን ብር ይደርሳል። ክለቡ ዋንጫ ካነሳ ተጨማሪ 15 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገብቷል። በአጠቃላይ በሶስት አመት 180 ሚሊዮን ብር ተፈራርሟል።
በመጨረሻም ሐበሻ ቢራ ለክለቡ እና ታማኝ ለሆኑት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል። በተጨማሪም ባለፉት አምስት አሥርታት ክለቡን ከጀርባውም ከፊቱም ሲደግፉ ለቆዩ ወገኖች በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።
47 221
ሐበሻ ቢራ ኢትዮጵያ ቡናን በ45 ሚሊዮን ብር ስፖንሰር አደረገ
#FastMereja I ሐበሻ ቢራ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩውን ከሚያከብረው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ጋር የነበረውን አጋርነት ማደሱን ይፋ አደረገ። የመጀመሪያ ምርቱን ለገበያ ከማውጣቱ ከአንድ ዓመት በፊት ከክለቡ ጋር አብሮ መስራት የጀመረው ሐበሻ ቢራ፤ አሁን ደግሞ ድጋፉን በማሳደግ ከእያንዳንዱ የቢራ ጠርሙስ ሽያጭ ድርሻ ማጋራት የሚያስችለውን አዲስ ስምምነት ተፈራርሟል። የስምምነት ፊርማው የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ተከናወኗል።
በዚህ አዲስ ስምምነት መሠረት ሐበሻ ቢራ የዘንድሮውን ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ያደገ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእያንዳንዱ የሐበሻ ቢራ ሽያጭ ላይ ለክለቡ ተጨማሪ ገቢ ለማጋራት ወስኗል። ይህም የቢራ ፋብሪካው ባደገ ቁጥር ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የሚሰጠው ድጋፍ አብሮ የሚያድግበትን አሰራር የዘረጋ መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ ክለቡ አዳዲስ አመራሮችን ወደ ኃላፊነት እያመጣ ባለበት ወቅት የተደረገ ሲሆን፣ ሐበሻ ቢራም የዚህ አዲስ ምዕራፍ አካል ለመሆን ያለውን ጽኑ ፍላጎት አረጋግጧል።
የሐበሻ ቢራ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደገለጹት፤ “12 ቁጥር ለባለ 12 ለባሾቹ የቡና ደጋፊዎች ለክለባቸው ያላቸው ፍቅር እና ድጋፍ በከፍታውም በዝቅታውም ጊዜ እንደማይቋረጥ ሁሉ፤ እኛም እንደዚሁ ነን” ብለዋል። አክለውም ድጋፋቸው ከክለቡ ጎን ለመቆም ባላቸው የማይናወጥ ጽኑ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው፤ የክለቡ የተሳካ የ50 ዓመታት ጉዞ የሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ደጋፊዎች የጋራ ጥረት ድምር ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና ሀበሻ ቢራ ስፖንሰርሺፕ ለመጪው 3 አመታት 45 ሚሊዮን ብር ተፈራርሟል። በተጨማሪም ከቢራ ሽያጭ ላይ የሚሰበሰበ ከ13 እስከ 15 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ ከ58 እስከ 60 ሚሊዮን ብር ይደርሳል። ክለቡ ዋንጫ ካነሳ ተጨማሪ 15 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገብቷል።
በመጨረሻም ሐበሻ ቢራ ለክለቡ እና ታማኝ ለሆኑት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል። በተጨማሪም ባለፉት አምስት አሥርታት ክለቡን ከጀርባውም ከፊቱም ሲደግፉ ለቆዩ ወገኖች በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።
