☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
前往频道在 Telegram
☀ሁዳ መልቲሚዲያ - 🇭🇺🇩🇦 🇲🇺🇱🇹🇮🇲🇪🇩🇮🇦 -قناة هدى الاسلامية ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ንፁህ ኢስላማዊ እውቀት ይደርሳቸው ዘንድ እንሰራለን! ለአስተያየት @nuugaa
显示更多📈 Telegram 频道 ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA 的分析概览
频道 ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA (@huda4eth) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 21 121 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 3 596,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 631 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 21 121 名订阅者。
根据 07 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 0,过去 24 小时变化为 -4,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 10.54%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.26% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 2 227 次浏览,首日通常累积 1 322 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 11。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“☀ሁዳ መልቲሚዲያ - 🇭🇺🇩🇦 🇲🇺🇱🇹🇮🇲🇪🇩🇮🇦 -قناة هدى الاسلامية
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ንፁህ ኢስላማዊ እውቀት ይደርሳቸው ዘንድ እንሰራለን!
ለአስተያየት @nuugaa”
凭借高频更新(最新数据采集于 08 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
21 121
订阅者
-424 小时
-237 天
无数据30 天
帖子存档
እንኳን ልንቀር ልናረፍድ ማይገባበት ልዩ የሆነ የዳእዋ ፕሮግራም
ኮልፌ 18 ዝቅ ብሎ በሚገኘው በዑስማን ኢብኑ ዐፍን መስጂድ እና መድረሳ
በኡዝታዝ ካሚል ጧሃ
አላህ በሰጠን ጊዜ እና ሰአት እሱ በሚወደው ቦታ!! እናሰልፍበት
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
ያግኙን
ሰዕድ ቢን አቢወቃስ
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
ያግኙን
በአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የተዘጋጀው የክፍለ ከተሞች የእግር ኳስ ውድድር ነገ በታላቅ ድምቀት ይጀመራል! ⚽
——————————
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የሚያዘጋጀው የክፍለ ከተሞች የእግር ኳስ ግጥሚያ ነገ ጁሙዓ የመክፈቻ ጨዋታውን ያካሂዳል።
📅 ቀን፦ የፊታችን ጁሙዓ መስከረም 29
⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ (ከጁሙዓ ሰላት በኋላ)
ቦታ፦ ዘነብወርቅ በሚገኘው የአወሊያ ሜዳ
ኮልፌ ቀራኒዮ 1 🆚 ንፋስ ስልክ 1
በዚህ በታላቁ የመክፈቻ መርሃ-ግብር ላይ፦ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የስራ ባልደረቦቻቸው
የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ሀይደር ኸድር እና አመራሮች በክብር እንግድነት በመገኘት ፕሮግራሙን ያደምቁታል።
በመቀጠልም ሌሎች ክፍለ ከተሞች ጨዋታዎች በተዘጋጀላቸው ፕሮግራም መሰረት ለተከታታይ 3 ቀናት የሚጋጠሙ ይሆናል!
የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ወዲያውኑ የሁለቱ ክፍለ ከተሞች ጨዋታ በደመቀ ሁኔታ ይከናወናል!
እግር ኳስ ወዳዶችና ደጋፊዎች በሙሉ ከቀኑ 9:00 በአወሊያ (ዘነብ ወርቅ) ሜዳ በመገኘት ጨዋታውን እንድትታደምቁና ቡድኖቻችሁን እንድታበረታቱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!
#AddisAbabaMuslimYouthCouncil #የእግርኳስውድድር #አወሊያ #JumuahMatch
"አህሉል ፉርቃን" ልዩ የቁርአን ምሽት
======================
በአይነቱ ለየት ያለ እጅግ ዉብ ድምፅ ባላቸዉ ቁራዕዎች ቁርአንን የምናዳምጥበት በታላላቅ ኡስታዞች ስለ ቁርአን የሚሰበክበት ዉብ ምሽት መርካቶ ሀደሬ ሰፈር በሚገኘዉ ባዩሽ መስጂድ የፊታችን ሀሙስ ምሽት ይከናወናል
በፕሮግራሙ ላይ ማንኛዉም ቁርአን ሲቀራ ማዳመጥ የናፈቀዉ ሁሉ ይመጣ ዘንድ ተጋብዟል
ዕለተ ሀሙስ
⭕️ቦታ ባዩሽ መስጂድ
⭕️ሰዓት ምሽት 12:30
እስከ 3:30
የወንድ ድርሻ ላይ
ልሳተፍ ካለች ነገር ይበላሻል
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
ያግኙን
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የሀገር ማሳደግና የልማት ጉዞ በጠንካራ መሠረት ላይ እየቀጠለ ይገኛል።
የሀገርን ሰላምና አንድነት በማደፍረስ፣ ሀገርን አሳልፈው ለመስጠትና ለማፍረስ የሚሰሩ ከሀዲያንና የጥፋት ኃይሎች ጥምረት ግን በፍጹም አይሳካላቸውም።
ሀገራችን በጽናት ታሸንፋለች፤ በልማትና በዕድገት ወደፊት ትገሰግሳለች! 🇪🇹✨
#ኢትዮጵያ #ልማት #አንድነት #እድገት
✍ የውድድሩ ሂደት
ለአንድ ወር የተመረጠውን መጽሐፍ ማንበብና ማጥናት
ለአንድ ሳምንት የሙከራ ፈተና መለማመድ
በመጨረሻ የማጠቃለያ ኦንላይን ፈተና ባሉበት ሆኖ መፈተን
የንባብ ውድድራችን ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
ይህ እድል አያምልጣቹ ተሳተፉ የምትወዱትን ሁሉ አሳትፉ ......
⬇️የንባብ ውድድሩን ለመመዝገብ⬇️
በዌብሳይት www.sulmahira.et/register?ref=005
⚡️በቴሌግራም ቦት ለመመዝገብ = https://t.me/gharuhirabot?start=ref=005
🏢በአካል ለመመዝገብ: አዲስ አበባ አብነት አደባባይ ኖህ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ በመምጣት
እንዲሁም ካላችሁበት ቦታ ሆናችሁ በኦንላይን
በቴሌግራም
በዋትሳብ
በኢሞ መመዝገብ ትችላላችሁ
0946248626
0942189967
የቃመ ተለቀመ
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
ያግኙን
ቋንጤ!! ከላይ የቀጠለ ፅሁፍ
የማኅበረሰቡን ሰላምና አብሮነት ያደፈረሱና መኮነን የሚገባቸው ዋና ዋና ድርጊቶች፦
- የጥላቻና የመከፋፈል ስብከት፦ ህዝቡ በሰላምና በተቻቸለ መንፈስ እየኖረ ባለበት፣ በየመድረኩና በየጁሙዓ ኹጥባው ምእመኑን እርስ በእርሱ የሚያጋጩ፣ ወንድምን በወንድሙ ላይ የሚያነሳሱና የጥላቻ መርዝ የሚያረጩ እኩይ ቅስቀሳዎች መካሄዳቸው።
- አካታችነትን አለመቀበልና ንቀት፦ በየደረጃው ያሉ የሚመለከታቸው አካላትና የመጅሊስ መዋቅሮች ሰላምን ለማስፈን ያቀረቡትን አካታች የቂርኣትና የዳዕዋ ፕሮግራም የመዘርጋት ጥሪ በመጣስ፣ የመስጅዱን አገልግሎት ለአንድ ወገን ብቻ ለማድረግ የተሄደበት ግትር አካሄድ።
- አረመኔያዊ የኃይል ጥቃት፦ ምእመናን የዒባዳ ፕሮግራማቸውን ጨርሰው በሰላም በመውጣት ላይ እያሉ፣ አስቀድመው በተደራጁ አካላት አማካኝነት የተፈጸመው የዱላና የድንጋይ ጥቃት የአላህን ቤት ደጃፍ ደም ያፈሰሰና ከማንኛውም ሃይማኖታዊና ሰብዓዊ እሴት ያፈነገጠ የጭካኔ ተግባር ነው።
- የህግ እና የወንጀል ከለላ፦ ወንጀል የፈጸሙና ጥቃት እንዲካሄድ ከበስተጀርባ በገንዘብና በአሳች መመሪያ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ አካላት በህግ ጥላ ስር ከማረፍ ይልቅ በገንዘባቸው ተማምነው ከህግ ለማምለጥ የሚያደርጉት ጥረትና የተወሰኑ የመንግስት አመራሮች ለአጥፊዎች የሰጡት ከለላ የፍትሕ ሚዛንን ያጎደለ ተግባር ነው።
የምናስተላልፈው ጥሪ እና ጥያቄዎቻችን፦
- ንጹሐን በአስቸኳይ ይፈቱ፦ ጥቃት ደርሶባቸው በተመሳሳይ ሰዓት ያለምንም ጥፋታቸው የታሰሩ ንጹሐን ምእመናን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ።
- አጥፊዎች በህግ ይጠየቁ፦ የጥላቻ ስብከት ሲያደርጉ የነበሩ የአህባሽ እንቅስቃሴ መሪዎች፣ ጥቃቱን በቀጥታ የፈጸሙ፣ ያስተባበሩና ከበስተጀርባ በገንዘብና በሀሳብ ሲረዱ የነበሩ አካላት በሙሉ ለሕግ ቀርበው ተገቢውን ፍትሕ እንዲያገኙ።
- አካታች አስተዳደር ይፈጠር፦ መስጅዱ የሁሉም ሙስሊም የጋራ ቤት በመሆኑ፣ አድሏዊ አሰራሮች ፈርሰው ሁሉንም ምእመናን በእኩልነት የሚያስተናግድና ፍትሐዊ የፕሮግራም ክፍፍል የሚያደርግ አዲስ አካታች ኮሚቴ እንዲሰየም።
የፍትሕ አካላት፣ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መዋቅር እንዲሁም የመጅሊስ አመራሮች የተጀመሩትን የህግ ማስከበር እርምጃዎች አጠናክረው በመቀጠል ለቋንጤ ህዝብ ዘላቂ ሰላምና ፍትሕን እንዲያረጋገጡ አደራ እንላለን!
ፍትሕ በገንዘብና በሥልጣን ሽፋን ሊታፈን አይችልም!
+2
በአላህ ቤት ውስጥ ጥላቻ አይሰብክም፤ ፍትሕ ለቋንጤ አቡበክር ሲዲቅ መስጅድ ምእመናን!
መስጅድ የአላህ ቤት፣ የሰላም፣ የፍቅርና የወንድማማችነት ተምሳሌት እንጂ የልዩነትና የደም መፋሰሻ ማዕከል አይደለም።
በጉራጌ ዞን፣ ጌታ (ጌቶ) ወረዳ በሚገኘው የቋንጤ አቡበክር ሲዲቅ መስጅድ አካባቢ በወንድማማችነትና በጥሩ ጉዞ ላይ በነበረው ማኅበረሰብ መካከል ከውጭ በተኮረጁና ከሰላማዊው አስተሳሰብ ያፈነገጡ ጽንፈኛ ስብከቶች ምክንያት ትልቅ የማኅበራዊ እሴት መሸርሸርና የግጭት ደመና ደምኖ ይገኛል። ፅንፈኛው አህባሽ የማህበረሰብ ሰላምን ማደፍረስና እርስ በእርስ ማጋጨት ዋና ስራው እንደሆነ በበርካታ የመስጂዶች ተሞክሮዎቹ እንደምታውቁት ነው።
ቴሌግራም Ad ማሳየት ጀምሯል!
ባለፈው አንዱ የቴሌግራም ፔጃችን ተከታይ ከስር ያያያዝኩትን ማስታወቂያ ልኮልን እናነተ ናችሁ ወይ የፖሰታችሁት? ሲል ጠይቆ ነበር!
በሁኔታው ግራ ተጋብተን ነገሩን ለማጣራት ስንሞክር ለካስ አጅሬ ቴሌግራም አድ ማሳየት ጀምሮ ኖሯል!
ከዚህ በፊት ቴሌግራምን ስናውቀው ከአድሚኑ በኩል ከተለቀቀ መልክት ውጪ ሌላ መልክት በአንድ ቻናል የማናይ የነበረ ሆኖ ኖሯል። ሌላ መልክት የፈለገ ሌላ ቻናል መግባትና መከታተል ያስፈልገው ነበር!
አሁን ደግሞ ግዜው ተቀይሮ አጅሬ ቴሌግራም ሰሞኑን ባለቻናል ደንበኞቹን "ክፈሉኝና ቻናላችሁን በሌሎች ቻናሎች ላስተዋውቃችሁ ብሎ ጥሩ ቢዝነስ በመጀመሩ የተነሳ አሁን ላይ በየትኛውም የቴሌግራም ቻናል የሌሎች ቻናሎች ማስታወቂያ ከፊት ለፊት በፎቶው እንደሚታየው ሊመጣ ይችላል።
በዚህ በሁዳ ቻናል ሲተዋወቅ ካገኘናቸው ከጅልባብ ማስታወቂያ በተጨማሪ ይህ pixel harbour guide የተሰኘ ቻናል ይገኛል!
ይህን ማስታወቂያ አጥፋልኝ ስትሉት ደግሞ አይኑን በጨው አሽቶ "አንተም ክፈለኝና ላጥፋልክ" ማለቱ ይደንቃል!
እንደ ሁዳ ለግዜው ይህን የማስታወቂያ Ad ልንከላከልበት የምንችልበት ዘዴ እስካሁን የተገኘለት ባይመስለንም ወደፊት የሚፈጠረው አይታወቅም ዘዴ ካገኘን እናጠፋዋለን! ነገር ግነወ ስጋታችን ቴሌግራም በየፔጁ ምን አይነት ማስታወቂያዎችን ሊለጥፍ እንደሚችል መገመት ይከብደናል። አላህ ኸይር ኸይሩን ያሰማን
ወሰላሙ አለይኩም
ካለመቻል እና ከስንፍና በአላህ መጠበቅ
ሸይኽ ኢልያስ አህመድ
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
ያግኙን
ሲጀመር ያፈጣሪ
እንዳለ አላመንክም
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
ያግኙን
📢 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
የኡመር ኢብኑል ኸጣብ (26) መስጂድ እና መድረሳ
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የቁርአን እና ሸሪዓዊ ትምህርቶች መምህራን (ኡስታዞች/ኡስታዛዎች) አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
💼 የሥራ መደብ
ብዛት፦ 8 — 5 ወንድ እና 3 ሴት
የሥራ ሰዓት፦ ሰኞ–ዓርብ ከአስር ሰላት እስከ መግሪብ፤ ቅዳሜ ከቀኑ 8:00
እስከ መግሪብ
ደመወዝ፦ በስምምነት
📋 ተፈላጊ መስፈርቶች
ቃዒደቱ ኑራኒያን በዜማ ማስቀራት የሚችል/የምትችል።
1 ቁርአንን በትክክለኛ ተጅዊድ የቀራ/ች እና ሙሉ ቁርአን የሀፈዘ/ች፤ ሸሃዳ/ምስክር ወረቀት ወይም ኢጃዛ ያለው/ላት።
2 የተጅዊድ ህግጋትን በደንብ የሚያውቅ/የምታውቅ እና ማስተማር የሚችል/ምትችል፤ አጫጭር ኪታቦችን የማስቀራት ልምድ ያለው/ላት።
3 ትክክለኛ ዓቂዳ፣ መልካም ስነ-ምግባር እና ሸሪዓዊ አለባበስን የጠበቀ/ች።
4 ተማሪዎችን እንደየባህሪያቸው ተንከባክቦ/ታ ለማስተማር ፍላጎትና ትዕግስት ያለው/ላት።
5 ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ፣ የመድረሳውን ህግና ደንብ የሚያከብር/የምታከብር እና በመድረሳው ካሪኩለም ለመመራት ፈቃደኛ የሆነ/ች።
6 የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል።
📅 የመመዝገቢያ ጊዜና ቦታ
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ፦
በአካል፦ መድረሳው ግቢ በመገኘት።
በተጠቀሱት ቁጥሮች በመደወልና ሰነዶችን በቴሌግራም በመላክ።
📌 አድራሻ፦ አብነት አደባባይ ገባ ብሎ፣ ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (26) መስጂድ
+251 98 899 1356
+251 94 316 8482
+251 93 663 4922
የእውነተኝነት ዋጋ
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
ያግኙን
🔊ደማቅ የሙሐደራ መድረክ🔊
✍ ከማለፊያህ ለማረፊያህ
በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
⏰ ከረፋድ 5፡00 ጀምሮ
ቀን
🗓 እሁድ መስከረም 17/2019
🕌 ቦታው ፡- አለም ባንክ ኢማሙ አህመድ አል-ጋዚ መስጂድና መድረሳ
አዘጋጅ፦ ኢማሙ አህመድ መስጂድ ወጣት ጀምዓ ከሸሪዓ ቦርድ ጋር በመተባበር
