(የወጣቶች አለም)🌏 عَالَمُ الشَّبَاب
前往频道在 Telegram
🌟 እንኳን ወደ "የወጣቶች አለም" በሰላም መጣችሁ! 🌟 በኢስላማዊ እሴቶች፣ በአኽላቅ፣ በቁርኣን እና በሐዲሥ ብርሃን የወጣቶችን የዱንያ እና የአኺራ ስኬት ለማጎልበት የተዘጋጀ ልዩ መድረክ። 💡 ኢስላማዊ እውቀት | 🚀 አነቃቂ ምክሮች | 📚 የመልካም ስነ-ምግባር መመሪያዎች💥1ታሪክ 💥2የትዳር ተሞክሮዎች 💥3ኢስላማዊ የእውቀት ፈተና ተቀላቀሉን፤ በእስልምና ብርሃን አብረን እንደግ! 🌙✨
显示更多未指定国家未指定类别
331
订阅者
+424 小时
+157 天
+4530 天
帖子存档
ለፈገግታ
አንዲት ሴት እንዲህ ትላለች፦
አማቴ በጋብቻችን ፈጽሞ ደስተኛ አልነበረችም። ባለቤቴ ከሥራ ሲመለስ በር ላይ እየጠበቀች 'ሚስትህ ስትሰድበኝ ነው የዋለችው!' እያለች ትከሰኛለች።😭
▢ አንድ ቀን ባለቤቴ '#አይዞሽ_እናቴ፣ እኔ ልክ አስገባታለሁ' ብሏት ወደ ፎቅ ቤታችን ወጣና... ትራስ በኃይል መምታት ጀመረ፤ እኔ ደግሞ እየተመታሁ እንደሆነ ለማስመሰል በከፍተኛ ድምፅ እጮኻለሁ።
▢ ጠዋት ማለዳ ማንም ሳይነቃ፣ እናቱ ሳታውቅ በድብቅ ወስዶ ቤተሰቦቼ ቤት አደረሰኝ። ከዚያም በኔ ላይ በር የቆለፈ አስመስሎ ለእናቱ 'ስርዓት እንድትይዝ ብዬ ክፍሏ ውስጥ ቆልፌባታለሁ፤ ከሥራ እስክመለስ አትወጣም!' አላት።
ማታ ከሥራ ሲመለስ እናቱ አግኝታው፦
'አንተ ከወጣህ ሰዓት ጀምሮ እኮ ሚስትህ ከበሩ ጀርባ ሆና ስትሰድበኝ ነው የዋለችው!'
Mother😭
ከመጥፎ አማት ይጠብቀን 🤲🏻
☘☘☘የወጣትነት ጊዜ እና የፅናት መንገድ
አላህ ወደ እርሱ ተመላሽ የሆኑ ወጣቶችን በጣም ይወዳል።
በወጣትነት ጊዜ ስሜትን ገትቶ ለአላህ መታዘዝ ደግሞ ትልቅ የነፍስ ጀግንነት ነው። አላህም በወጣትነታቸው እርሱን በሚገዙ ወጣቶች በመላእክቱ ፊት ይኩራራባቸዋል።
ስለዚህ መንገድ የጠፋብን ካለን ሳናመነታ ወደ እርሱ እንመለስ አላህ ተውበት አድራጊዎችን ይወዳልና።በዚያ በቂያማ ቀን የፀሐዩ ሐሩርና ጭንቅ በበረታበት አስፈሪ ወቅት በአላህ ጥላ ስር ከሚያግኙት ሰባት የሰዎች ስብስብ መካከል በወጣትነቱ አላህን በመገዛት ያደገ ወጣት አንዱ ነው! ጥቂት የምናስባቸው ነጥቦች ወርቃማው እድሜ፦ ወጣትነት ጉልበትና ፍላጎት የሚበዛበት ወቅት ነው። በዚህ እድሜ አላህን መምረጥ አላህ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው።
የቂያማ
ቀን
ጥያቄ በቀጣዩ ዓለም ከተለዩት ጥያቄዎች አንዱ "ወጣትነትህን በምን ላይ አሳለፍከው?" የሚለው ነው።የተውበት በር አልተዘጋም፦ የትኛውም ያህል ብንሳሳት አላህ ወደ እርሱ የተመለሰን ሰው ይምረዋል ስህተቱንም ወደ ጥሩ ይለውጥለታል።
አላህ በቃሉ የሚጸኑ በመንገዱም ላይ የሚያበረታቸው ወጣቶች ያድርገን!✍ Zakiree
☘☘ስናድግ ዝምታም አብሮን ያድጋል። ለሰዎች ከምናወራው በበለጠ ወደውስጥ የምናወራው መብዛት ይጀምራል። ከራሳችን ጋር የምንመላለሰው የውይይት ሀሳቦች መሀል የሚገራርሙ መመሰጦች ውስጥ እንገባለን። የመገለል ፍላጎት ይቆጠጠረናል። ለብቻ የመሆን። ብዙም ቅልቅል አለመውደድ። ጥሩ ስሜት አለው።
💐 الصلاة خير من النوم
☀️ أذكار_الصباح
اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لاَ يَغْفِرُ الذُّنوبَ إِلاَّ أَنْتَ
🌹
🌟اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلًا مُتَقَبَّلًا
Z✍..
☘☘‹‹ነፍሴ ኢኽላስ እንዲኖራት
የታገልኳትን ያክል በምንም ነገር ላይ
አልታገልኳትም ⚡️
ከሰለፎች አንዱ 🥀በሉ ሰናይ ለይል 🌈 Z...✍
20 ዙልቀርነይን ከሕዝቦቹ ለሰራላቸው ግድግዳ ክፍያ/ግብር ሲያቀርቡለት ምን አላቸው?
19 የቁርኣን ምሁራን እንደሚሉት ዙልቀርነይን ንጉሥ ከመሆኑም በላይ ምን ዓይነት ስብዕና ነበረው?
18የእጁጅና መእጁጅ ህዝቦች ዘር አቆጣጠር ከትክክለኛው ምንጭ ሲመዘዝ የማን ልጆች ናቸው?
17ዙልቀርነይን ለአዛኝነቱና ለፍትሃዊነቱ ማስረጃው በቁርኣን እንደተጠቀሰው ለበደለኞችና ለአማኞች ያለው አቋም ምን ነበር?
16የእጁጅና መእጁጅ አስከሬን በምድር ላይ ሲበተን አላህ ምድርን እንዲያፀዱ የሚያልከው ምንድን ነው?
14የእጁጅና መእጁጅ ህዝቦች በብዛትና በኃይል ሲወጡ በነቢዩ ዒሳ (ዐ.ሰ) እና በምእመናን ላይ ምን እንዲያደርጉ ነው አላህ ያዘዛቸው?
13 የእጁጅና መእጁጅ ህዝቦች ሲወጡ የትኛውን ሀይቅ ውኃ ጠጥተው እንደሚያደርቁት በሐዲስ ተጥቅሷል?
12 በእስልምና አስተምህሮ መሠረት የእጁጅና መእጁጅ መውጣት ከየትኞቹ ምልክቶች ይመደባል?
11 የእጁጅና መእጁጅ ህዝቦች ከግድግዳው በስተጀርባ የሚወጡበት ጊዜ የሚሆነው መቼ ነው?
