ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

前往频道在 Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

显示更多
未指定国家未指定类别
319
订阅者
+124 小时
-47 天
+5530 天
帖子存档
📍الآدَابُ المُهِمَّةُ لِنساءِ الأُمَّةِ ~ክፍል .⓵ t.me/https_Asselfya/11735 ~ክፍል .➁ t.me/https_Asselfya/11739 ~ክፍል .➂ t.me/https_Asselfya/11746 ~ክፍል .⓸ t.me/https_Asselfya/11751 ~ክፍል .⓹ t.me/https_Asselfya/11756 ~ ክፍል .⓺ t.me/https_Asselfya/11767 ~ክፍል .⓻ t.me/https_Asselfya/11775 ~ክፍል .➇ t.me/https_Asselfya/11784 ~ክፍል .⓽ t.me/https_Asselfya/11802 ~ክፍል.➉ t.me/https_Asselfya/11814 ~ክፍል.⓵⓵ t.me/https_Asselfya/11830 ክፍል .⓵➁ t.me/https_Asselfya/11837 🔍የኪታቡ pdf ~t.me/https_Asselfya/11734 📍በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል ...!

​"አንዳንድ ሰዎች አሉ ከልባችን ውስጥ… ቀስ በቀስ የሚወጡ ከእይታችን ውስጥ… በሂደት የሚጠፉ ሰዎች አሉ! ይህንን የምናደርገው… እኛ ሳንሆን የገዛ ሥራቸው ነው። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

ኩን ፈየኩን !!! በጨለማ ውስጥ የተዋጠችን አንዲት ደረቅ መሬት በዓይነ ህሊናህ ተመልከት። ድርቅ አጥቅቷታል አፈሯ ተሰነጣጥቋል የህይወት ጠረን ከእርሷ ርቋል። ለዓመታት የውሃ ጠብታ አላየችም። በውስጧ የተቀበረችው አንዲት ትንሽ ዘር ተስፋ ቆርጣ እረፍት አድርጋለች። የሰው ልጅ እውቀት ይህች መሬት ሞታለች ዳግም አታቆጠቁጥም ብሎ ይፈርዳል። ነገር ግን የዓለማቱ ጌታ አሏህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ህይወት እንዲዘራባት ሲሻ ምንም አይነት ማሽን ምንም አይነት የሰው ጉልበት አይጠይቅም። ውሳኔው በአንዲት ቃል ብቻ የተገደበ ነው። "ኩን!" (ሁን) ልክ ይህች  ቃል ስትነገር ያቺ የሞተችው መሬት በቅፅበት ትነቃለች። ከየት መጡ የማይባሉ ጥቁር ደመናዎች ሰማዩን ይሸፍናሉ የእዝነት ዝናብ ይወርዳል ያቺ በድርቅ ውስጥ የነበረች ዘር አፈሩን ሰንጥቃ አረንጓዴ ቅጠሏን ታወጣለች። "ፈየኩን" (ወዲያውኑም ሆነ)! ይህ ነው የአላህ ውሳኔ። የሰው ልጅ ሂይወትም እንዲሁ ነው ። በሀዘን ተውጦ በበሽታ አልጋ ላይ ወድቆ ሀኪሞች ከዚህ በኋላ ተስፋ የለውም ያሉት ታካሚ አለ። በሮች ሁሉ የተዘጉበት የጭንቀት ማዕበል የሚያንገላታው እና "አበቃልኝ" ብሎ እጁን የሰጠ ምስኪን አለ። ዙሪያው በጨለማ ተከቧል መውጫ ቀዳዳው ጠቧል። ነገር ግን አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ለእርሱ እፎይታን ሲሻ መላእክትን አያዘምትም ሰራዊትን አያሰልፍም። ሰባቱን ሰማያት አቋርጣ የምትመጣው ያቺ ቃል ብቻ በቂ ናት ! "ኩን!" በዚያች ቅፅበት ሀኪሞች የደነገጡለት ተዓምር ይፈጠራል። በሽታው ከውስጡ ተነቅሎ ይወጣል የተዘጋው በር በሰፊው ይከፈታል ጨለማው በብርሃን ይዋጣል። ያ የማይቻለው የማይታሰበው እና የሰው ልጅ አእምሮ ሊቀበለው የማይችለው ነገር በአላህ ፊት ከቅፅበትም ባነሰ ጊዜ ውስጥ እውን ይሆናል። "ፈየኩን!" ሰማያት ያለ ምሰሶ የቆሙት ተራሮች እንደ ሚስማር የተተከሉት እና ማዕበል የተሞላው ባህር ድንበሩን እንዳያልፍ የታዘዘው በዚህች ቃል ነው። አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የሆነ ነገር እንዲሆን ሲፈልግ ምክንያቶችን አይፈልግም ምክንያቶችን ራሱ ይፈጥራል። ስለዚህ በህይወትህ ውስጥ ምንም አይነት ከባድ ፈተና ቢያጋጥምህ መንገድህ ሁሉ ቢዘጋ እና ሰዎች ሁሉ ጀርባቸውን ቢሰጡህ በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ። ያንተን ጭንቀት ወደ ደስታ ለመቀየር  ያንተን ህመም ወደ ጤና ለመቀየር ያንተን ሀዘን ወደ ሳቅ ለመቀየር አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የሚያስፈልገው አንዲት ቃል ብቻ ናት ። "ኩን!" ያቺ ቃል ስትመጣ ህይወትህ በሙሉ "ፈየኩን" በሚለው አስደናቂ እውነታ ውስጥ ታበራለች። እናም... አብሽሩልኝ አህባብ ! ✋ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- = t.me/FKR_ESKE_JENET

ለአህሉል-አሰር ጀግኖች ማበረታቻ ትሁንልኝ... 🔥አህሉል አሰር...✅ ----------------------- የነዚያ የጀግኖች ሶሀቦች ተከታይ፡ ሲተገብር እንጂ ሲያወራ እማይታይ፡ ታማኝ ሞደሎቹን በህሌና እሚስል፡ በመንሀጅ የፀና ከቶ እማያስመስል፡ የሹብሀ ኮተት የሌለበት ቁስል፡ ሌት ቀን የሚተጋ እውቀት ለመሸመት፡ የሒዝብዮች ጠላት ሁሌ እማይገመት፡ በብርሀን ተጓዥ የሌለበት ፅልመት፡ መረጃን የያዘ ማንም የሚመራው፡ ፀባዩ በእምነቱ ፀንቶ የተሰራው፡ አሰርይ የሆነ በአንሷሮች ፋና፡ ውብ ሙሀጂሮችን የሚናፍቅ ጀግና፡ ሐቅን የሚያስተምር በመረጃ ቀርቦ፡ ተውሒድ የሚያሰራጭ ወጣቱን ሰብስቦ፡ አህሉል አሰር ለኔ እንደዚያ ነው አቦ፡ በመልካም ለጠራው አዝኖ ፈጥኖ ደራሽ፡ ዝና የማይገታው ቤሳቢስቲ ቁራሽ፡ እውቀት የሚቀስም ሽርክን የሚዋጋ፡ ተውሒድን ለማስፈን ሌት ቀን የሚተጋ፡ ሐቅን ለማስፋፋት የሚከፍል ዋጋ፡ አህሉል-አሰር... ሰለፍይ የሆነ የትውልዱ ሞራል፡ ትናንትናም ዛሬ ሁሌም ይከበራል፡ መፋለም የሚችል የቢዲዓን ካንሰር፡ ማን እንደ ሰለፍይ ማን እንደ አህሉል አሰር፡ ሰለፍዩ ሆይ ከመውደድ አይበልጥም ክብርህ፡ ከአይንህ ላይ ይታያል ፍቅርህ፡ መልካምነት ዜማ ሆኖ ዝቅታህ እያሸነፈኝ፡ በለዘብታ ቃል ተከሽኖ ፀባይህ እያከነፈኝ፡ ከልቤ ወደድኩህና ያውና ስንኝ አፃፈኝ!! በርታ ተጓዝማ ለነገ ግባችን፡ ሱና ላይ ከፀናን ጀነት ነው ቤታችን፡ አሰርይ ከሆን ሰላም ነን ሁላችን፡ የስሟ ነጋዴ ቢበዛም ተጣሞ፡ ቅዠታሙ ሁሉ ቢጠብቅም ቆሞ፡ ይቀራታል እንጂ በክፋቱ ታሞ፡ ሒዝብይ እንደ አሰርይ አይሆንም ፈፅሞ፡ በርታ እንዳትሰላች ተነስ ተንቀሳቀስ፡ ሙሽሪክ ሒዝብያውን በመረጃ ውቀስ፡ ሞራልህን ሙላው ውብ ወኔህን ንቀስ፡ ድሉ ከፊትህ ነው መጣልህ ቀስበቀስ፡ ዝና እንዳይደልልህ አትግባ ባቋራጭ፡ መርሁን ተከተል አንተ ነህ ተመራጭ፡ ቅራታቸው ላይ ቁም በቀደምቶች ቦታ፡ እሱን ብቻ ስበክ በጧት በቀን ማታ፡ በተቻለህ አቅም ወጣቱን አንፀው፡ በተውሒድ በሱና በፀባይ ቅረፀው፡ በስደት በሀገር ቤት በየትም ተራመድ፡ ወጥር የትም ቦታ የሱናውን ገመድ፡ አሏህ ይረዳሀል እንዳታመነታ፡ ጠንቅቀህ እወቀው ይህንን እውነታ፡ የሽርኩን ጨለማ የቢዲዓን ካንሰር፡ ነቃቅሎ ለመጣል ጠፍሮ ለማሰር፡ ወጧቱ ተዘጋጅ ተነስ አህሉል አሰር፡ ...በኑረዲን አል-አረብ...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሙሓዶራዎችን ለማግኘት በዚህ በኩል https://t.me/yedaewachannel/1534