ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
前往频道在 Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
显示更多未指定国家未指定类别
319
订阅者
-124 小时
-27 天
+5430 天
帖子存档
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጧሊበል ዒልም እና ኪታብ
~
1- ኪታብ ስንገዛ አቅም በፈቀደ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀውን እንግዛ። በተለይ የሚታወቅ አታሚ ወይም የሚታወቅ ሰው ያዘጋጀው ቢሆን መልካም ነው። ወይም ሰው ብናማክር ጥሩ ነው።
2- በጥንቃቄ እንያዝ። በጥንቃቄ ስለማንይዛቸው ስንት ኪታቦቻችን የሽፋን ፅሁፋቸው ደብዝዟል ወይም ጠፍቷል?! ስንቱ ወረቀታቸው ተነቃቅሏል?! ስንቱ ተቀዳደዋል?! ስለዚህ ውስጣቸው እርሳስና እስኪርቢቶ ማስቀመጥ፣ ወረቀት እያጥጠፉ ምልክት ማድረግ፣ ስርአት በሌለው መልኩ ላያቸው ላይ መለቅለቅ እና መሰል ልማዶችን መተው ይገባል። ይልቁንም ሽፋናቸውን በላስቲክ ወይም በፕላስተር መለጠፍ ይገባል። የምናስቀምጥበት ቦታም ጥሩ ቦታ ሊሆን ይገባል።
3- ሌላኛው ጥንቃቄ የሚፈልገው ማዋስ ላይ ነው። በጥንቃቄ በመያዝ፣ በጊዜ በመመለስ ለምታውቁት ካልሆነ በስተቀር ኪታብ አታውሱ። ብዙ ሰው የረባ የንባብ ልማድ ሳይኖረው እንዲሁ ጓጉቶ ይዋስና ወስዶ የትም ይጥለዋል። መጨረሻ ከማን እንደተዋሰው እንኳን አያስታውስም። በዚህ መልኩ ስንት ኪታብ ጠፍቶብናል? ስንት ኪታብ ጥለናል? አሁንም ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ ሁሉ ኪታቦቻችሁን ፈትሹ። የተዋሳችኋቸውን ኪታቦች መልሱ። አማና ላይ አትዘናጉ። የምታውሱ ደግሞ የተዋሹን እና የኪታቡን ስም የተዋሰበት ቀን ጋር መዝግቡ።
4- ኪታቦች ላይ ወሳኝ ማስታወሻ ወይም እርምት ስትፅፉ ኪታቡን በማያበላሽ መልኩ ይሁን። በመጀመሪያ የረባ ዋጋ የሌለው ነገር መፃፍ አይገባም። ሁለተኛ ቢቻል እርሳስ ብንጠቀም ጥሩ ነው። ሶስተኛ በተቻለ መጠን ስርአት ባለው በሚነበብ መልኩ እንፃፈው። በችኮላ ፅፈነው ኋላ የራሳችንን ፅሁፍ ማንበብ የምንቸገር እንኖራለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኪታብ በማስተማር ላይ ለተሰማራችሁ
~
1- ለተማሪዎችህ የሚማሩትን ኪታብ መምረጥ። አቅማቸውን፣ የጎደላቸውን፣ የሚያስፈልጋቸውን እንጂ እንዲሁ የጠየቁትን ሁሉ አትጀምር። ተማሪ ያላቅሙ ትልቅ ኪታብ መጀመር ሊፈልግ ይችላል። ተማሪው በጥሩ ደረጃ ላይ ካለ የጠየቀውን ብትቀበልም ችግር የለውም።
2- የምታቀርበው ትምህርት፣ የምትመልሰው ጥያቄ ታዳሚህን ያገናዘበ ይሁን። ሰፊ ህዝብ የሚታደምበት ደርስ ላይ የሚኖርህ አቀራረብ በ'ቂራአት' ገፋ ካደረጉ ተማሪዎች ጋር ከሚኖርህ ጋር በይዘቱም፣ በቋንቋውም፣ በመጠኑም ሊለይ ይገባል። ለምሳሌ ከመግሪብ እስከ ዒሻ መስጂድ ውስጥ የሚሰጥ ደርስ ላይ ጠለቅ ያለ ኺላፍ አትተንትን። ይሄ ማስተማር ሳይሆን ማደናገር ነው። ኺላፍ ጆሯቸውን ከመታቸው ተማሪዎች ጋር ስትሆን ደግሞ በተቻለ መጠን 'ራጂሕ' እና 'መርጁሑን' ባቅማቸው መጠን ለይተህ አቅርብ። ብዥታዎችን ግፈፍ። የምታቀርበው ነገር ግልብ ከሆነ ደርስህን ጣዕም ያጡበታል። ባጭሩ ትምህርት ታዳሚዎችህን ያገናዘበ ይሁን።
3- ተዘጋጅተህ ቅረብ። ቢያንስ ገረፍረፍ አድርገው። ተማሪዎችህ ፊት አትደናበር። በቅጡ ሳትይዝ ቀርበህ ሸርሕ ላይ በፍለጋ አትባዝን። የቀለም ትምህርት ላይ እንኳ አስተማሪዎች ተዘጋጅተው ነው የሚቀርቡት። የዲን ጉዳይ የበለጠ ጥንቃቄ ይፈልጋል።
4- ካ'ቅምህ በላይ ካልሆነ በስተቀር ቀሪ አታብዛ። ደርስ አታቆራርጥ። ይሄ የተማሪዎችን ሞራል በጣም ያቀዘቅዛል።
5- ተማሪዎችን አታሸማቅ። አንዳንዱ አስተማሪ ጥያቄዎችን በቅንነት አይረዳም። ሁሉ ነገር መፈታተን ይመስለዋል። ይሄ መሆን የለበትም። መፈታተን የሚፈልግ፣ ልታይ ልታይ የሚል፣ መጥፎ አቀራረብ ያለው ተማሪ ካለ እንዳስፈላጊነቱ በጥቅል ወይም በተናጠል ለይተህ ምከር። ካልሆነ ጠንከር አድርገህ ገስፀው። ነገር ግን ቁጣችን የራሳችን ድክመት መሸፈኛ ሊሆን አይገባም። በአስተማሪዎች ከባድ ባህሪ የተነሳ ስንት ደርስ ተበትኗል! ስንት ተማሪ ተሰናክሏል! ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል!
6- ድንገት ያልገባህ ነገር ከገጠመህ ወይም የማታውቀው ጥያቄ ከተጠየቅክ አትደንግጥ። አንተ ሁሉን እንደማታውቅ ይታወቃል። አይቼ እመጣለሁ፣ አላውቀውም በል። እንጂ እርግጠኛ ባልሆንክበት በግምት እንዳትመልስ። አደራ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ዳእዋ ብቻ الدعوة فقط
በሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች
❶ ኡሱሉ ሰላሳ
❷ ኡሱሉ ሲታ
❸ሸርህ ቀዋዒዱል አርበአ
❹ ሸርህ ኡሱሉ ሱናህ
❺ ሸርህ ሉምአቱል ኢዕቲቃድ
❻ አቂደቱል ዋሲጢያ
❼ አቂደቱል ኢስላምያህ
❽ ሹሩጡ ላኢላሃ ኢለሏህ
❾ ሸርህ መንዙመቱል በይቁኒያ
❿ ተይሲሩል ሙስጠለሀል ሀድስ
❶❶ ሸርህ ቀዋኢዱል ሙስላ
❶❷ ሸርሁ ሱና ሊል በርበሀሪ
❶❸ ኪታቡ ተውሂድ የፈውዛን
❶❹ መንሀጁ ሳሊኪን
❶❺ ኑሩ ተውሂድ
❶❻ ሀዚሂ ዳእወቱና
❶❼ ሸርሁል መትኑል ወረቃት
❶❽ ፊቅሁል ሙየሰር
❶❾ ሸርሁ ነዝሚል ወረቃት ሊሸይኽ ሙሀመድ ብኑ ሷሊህ አል ኡሰይሚን
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
👉ሞት ቅርብ ነው።
ለምትወዱትን ሰው ፍቅራችሁን ሳትገልፁለት ፣ ሞት እንዳይቀድማችሁ!
ነገሮችን ለነገ አታሳድሩ
ማድረግ የምትፈልጉትን ዛሬ አድርጉለት መናገር የምትፈልጉትንም ዛሬ ተናገሩ።
ከሞተ በኋላ ቁጭት አይጠቅምም።
ዛሬ እንተሳሰብ፣
ዛሬ እንደማመጥ፣
ዛሬ እንከባበር፣
ዛሬ እንተዋወቅ...ወዳጃችሁን በወረትና በተረት አትቀይሩት #ውደታ የአካል ጥምረት ሳይሆን የመንፈስ ውህደት ነው።
...ኑር...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
የማይቋረጥ ደስታን የፈለገ ቁርዓንን አጥብቆ ይያዝ!
የማይከዳን፣የሚያፅናናን፣የሚያስደስተን፣ሳንከፍል እየተከፈለን የምንደሰትበት ነገር ቢኖር ቁርዓንን መሀፈዝና ለመሀፈዝ የምናደርገው ድግግሞሽ ላይ የሚሸልመንን ሽልማት በአይናችን አሁኑኑ ብናይ ኑሮ አንድም ሰው ጓደኛ ዘመድ ቤተሰብ እያለ ግዜውን ባላባከነ ነበር።
ነገር ግን የኛ የአማኞች ዋናውና ትልቁ እምነታችን በሩቅ በገይብ ማመናችን ነው የምንመነዳውን ካላየን ሳይሆን እምንለው ምንዳችን ወደር የለውና ልጣር ልልፋ መልካምን ልከስብ፣የሚል የአማኞች እምነት ነው።አልሀምዱሊላህ!
ስለዚህ ነገ እድለኛ መሆን የፈለገ ቁርዓንን ጓደኛው ያድርግ። ወላሂ ርካታውን የሚያውቀው ያየው ሰው ነው ሞክሩት ትርፋማ ንግድ ነው።
የተወሰደ
Repost from Hussein Ali (Durus & Fewa'id)
የጥንቃቄ መልእክት
ውድ ወንድሞችና እህቶች ዛሬ ዛሬ ሌቦች ይበልጥ በማያሰነቃ ሁኔታ የሱናን አለባበስ ተላብሰው ሰዎች ዘንድ በጣም አሏህን ፈሪ በመምሰል ሞባይል እየሰረቁ ስለሆነ ማንነቱን የማተውቁትን ግለሰብ ባለባበሱ ተማርካችሁ ሙሉ እምነት ልትሰጡ አይገባም ። ይህ ምስሉን የምታዩት ግለሰብ በአወሊያ መስጅድ ግቢ አስደውሉኝ በማለት ሞባይል አታሎ ይዞ የሄደ ሰው ነው። ሲያደርጋቸው የነበሩት ተግባሮች ሁሉ በካሜራ ተቀርፆ ተቀምጧል። እሱም ከዚህ ሰራው ይታቀብ ዘንድ ሌሎች ወንድምና እህቶች እንዳይታለሉ በማሰብ ፎቶውን አያይዣለሁ
http://t.me/husseinali210
Repost from قَناةُ وفَوا ئِد أبي فَوزان الْحَبَشِيِّ
የተውሒድ ፍሬዎች!
ثَمَرَات التوحيد
🎙;-በሸይኽ ዐብዱል'ዐዚዝ አልቡረዒይ حفظه الله
🔷👉https://t.me/abujemila25
🔷👉https://t.me/abujemila25
Repost from ዳእዋ ብቻ الدعوة فقط
በኡስታዝ ሑሰይን ዐሊይ አቡ አመቲ ረሕማን አል ከላልይ ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች
❶ ሸርሕ ኪታቡ ተውሒድ የሸይኽ ፈውዛን
❷ ቀውሉል ሙፊድ
❸ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጢያ
❹ ሸርሑ ከሽፊ ሹቡሃት
የኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁሏህ
❺ ሸርህ ኡሱሉ ሲታ
❻ አቂደቱል ኢስላምያ
❼ አተኽዚር ሚል ቢደአ
❽ ኡሱሊ ሱንና ሊል ኢማሚ አሕመድ ከሸይኽ ኢብኑ ጂብሪን ሸርሕ ጋር
❾ ሚን ወሷያ ሰለፊ ሊሸባብ
የሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር
❿ አተ ተመሱኩ ቢሱነቲ ነበዊያህ
የሸይኽ ኢብራሂም ብን ዐብዲላህ
❶❶ ሙጅመሉ ዐቂደቲ ሰለፊ ሷሊሕ የሸይኽ ሷሊሕ ብን ፈውዛን አል-ፈውዛን
❶❷ አሠሩ አት ተመሱኪ ቢሱንና ፊ አውቃቲል ፊተን የሸይኽ ዐብዱሏህ ዐብዱረሒም አልቡኻሪ
❶❸ ሹሩጡ ላኢላሃ ኢለሏህ
❶❹ ሙንከራቱን ሻኢዐህ ፊልሙጅተመዓቲ የጅብ አልሐዘሩ ሚንሃ
❶❺ ማ ሂየ አስሰለፊያ
የሸይኽ ዐብዱላህ ዐብዱረሒም አልቡኻሪ
❶❻ ሸርሑ መንዙመቱል ሓኢያ ፊ ዐቂደቲ አህሊ ሱነቲወልጀመዓ የሸርሑ አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን ሐፊዞሁሏህ
❶❼ ሽርሑ ኡሱሊል ኢማን የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁሏህ
❶❽ ቀዋዒዱል ሙስላ
Repost from دروس وفوائد أبي حزام عبدالرحمن بن سعيد
القلائد البرهانية - ١٣
https://t.me/durusuabihizam?livestream=71eb5133b2bbf73858
Repost from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ]
ኪታብ ስንገዛ ዎጋው ተወደደብን ብለን እንደዋዛ ማሳለፍ የለብንም ነጌ ላናገኘው እንችላለን !
🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ
~ t.me/Darutewhide
Repost from هَذِهِ عَقيدَتُنَا
➺ሰለፎች ለነቢዩ ﷺ ከእኛ የበለጠ ፍቅር ነበራቸው፤ ነገር ግን መውሊድን አላከበሩም። ይህ ነገር መልካም ቢሆን ኖሮ፣ መጀመሪያ የሚፈጽሙት እነርሱ ነበሩ። ስለዚህ ነቢዩን ﷺ መውደድ የሚገለጸው በሱናቸውን በመከተል እንጂ፣ በሰለፎች ያልተፈጸመ አዲስ አምልኮ በመፍጠር አይደለም።
➺ሰሞኑን አህባሾች መውሊድ ቀርቦዋል እያሉ እያጨበጨቡ ነው . አሏህ ህዳያ ይስጣቸው
🏷ሼር አድርጉላቸው እስቲ ☝️
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
«የሱና ዑለማኦች መከባበር»
ሸይኽ ሱለይማን አርሩሐይሊይ እንዲህ ይላሉ፦
«ረቡዕ ዕለት ከመግሪብ ሶላት በፊት በነቢዩﷺ መስጊድ ውስጥ ከተከበሩት ሸይኽ አብዱስሰላም አሽሹወይዒር ጋር ተገናኘን። ፊታቸው በደስታ በራ፤ እጅግ አጥብቀውም አቀፉኝ። እንዲህም አሉ፦ "በአላህ ይሁንብኝ ሸይኻችን! ለእርስዎ ካለኝ ከፍተኛ ፍቅር የተነሳ ከልቤ ውስጥ ባስገባዎት ደስ ይለኝ ነበር።"
ይህም ከእሳቸው መልካም ባህሪና ትህትና የተነሳ ነው። አክለውም፦ "እኔ ወርሃዊ ትምህርቴን (ደርሴን) ከቀኑ 5:30 እስከ መግሪብ ያደረግኩት ከእርስዎ ትምህርት ጊዜ ጋር እንዳይጋጭብኝ ነው"
አሉኝ። እኔም አልኩ፡ "እውቀት በባለቤቶቹ መካከል እንደ ዝምድና ነው፤ የሱና መሻይኾችን በእሱ (በአላህ) የሚዋደዱ ስላደረጋቸው አላህን አመሰግናለሁ።"
ጌታዬ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ የሱና መሻይኾችን ሁሉ እርሱ ለሚወደው እንዲወፍቃቸው፣ ስማቸውን እንዲያገዝፍ፣ ማዕረጋቸውን ከፍ እንዲያደርግና በእሱ ዘንድ ባሉት መላእክት ፊት እንዲያወሳቸው እለምነዋለሁ። እንዲሁም የሱና ሰዎችን በሙሉ በመልካም አንድነትና ስምምነት ላይ እንዲረዳቸው አላህን እለምናለሁ።»
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from ✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
ዲን ያላትን አግባ የተባልከው በምክንያት ነው፤ ለራስህም የኑሮህ ማጣፈጫ ቅመም ነች።ሌላው ደግሞ ልጆችህንም በስነ ምግባር እና በዲን አንጻ ጥሩ ደረጃ ታደርሳቸዋለች።
እናት!!
እናት!!
እናት!!
⭕️ አል-ቡኻሪን ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ አሽ-ሻፊዒይን ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ አህመድ ኢብኑ ሀንበልን ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ ሙሐመድ አል-ፋቲህ የቁስጥንጥንያ (ኮንስታንቲኖፕል) ፈታሂ ይሆን ዘንድ ያሳደገችው እናቱ ናት።
⭕️ አል-ሀፊዝ ኢብኑ ሀጀርን ያሳደገችው እህቱ ናት።
⭕️ የኢብኑ ተይሚያ እናት "ተይሚያ" ትባል ስለነበር በሷ ስም ተጠራ፣ በሱም ታወቀ።
⭕️ የኢማም ማሊክ እናት የዑለሞችን (የሊቃውንትን) አልባሳት ታለብሰውና “ወደ ረቢዓ ሂድ፤ ከእውቀቱ በፊት ከሥነ-ምግባሩ ተማር” ትለው ነበር።
⭕️ የሱፍያን አሥ-ሠውሪ እናት፡ “እውቀትን ፈልግ፤ እኔ በእንዝርት ሥራዬ እመግብሃለሁ/እረዳሃለሁ” ትለው ነበር።
⭕️ ኢማም አል-አውዛዒይን እናቱ የቲም አባት የሌለው) ሆኖ ሳለ የሻም ህዝቦች ኢማም እስኪሆን ድረስ አሳደገችው።
⭕️ አብደላህ ኢብኑ አዝ-ዙበይርን ያሳደገችው እናቱ አስማእ ቢንት አቢ በክር ስትሆን፣ በጀግንነትና በጽናት ላይ ኮትኩታ አሳደገችው።
🌿 ሴቶች የወንዶች መቅረጫ ናቸው፤ ሴት ልጅ ከተስተካከለች/ካመረች ቤቱ ያምራል፣ ቤቱም ከተስተካከለ ማህበረሰቡ ያምራል።
🌿 እናት (የህዝብ) እኩሌታ ናት፤ ሌላኛውን እኩሌታ ደግሞ የምታሳድገው እሷው ናት፤ ስለዚህ (ህዝብ) የሚነሳው/የሚበለፅገው በሷ መልካምነትና ጥንካሬ ነው።
Repost from ዳእዋ ብቻ الدعوة فقط
ማውጫ በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች ዝርዝር
1⃣-ሉምዐቱል ኢዕቲቃድ
2⃣አል ኡሱል ሚን ኢልመል ኡሱል ሸይኽ ሷሊህ አል ኡሰይሚን "
3⃣ ኡሱሉ ሱና
4⃣አርበዒን ሀድስ
5⃣ኩን ሰለፊየን አለል ጃዳ
6⃣አቂደቱል አህለ ሱነቲ ወልጀመአ
7⃣ኪታቡ ተውሂድ
8⃣ኡምደቱል አህካም
9⃣ሙስጦለሀል ሀድስ
🔟ኹዝ አቂደተክ
1⃣1⃣"' ኩና ፊ ጃሒሊያ"
1⃣2⃣ሙምቲዕ ሸርሑ አጅሩሚያ"
1⃣3⃣ኢስቲቅባሉ ሸህሪ ረመዳን
1⃣4⃣ሚንሀጁ ፊርቀቱ አናጂያህ
1⃣5⃣ተብሲሩል ባዲዒን ቢስጢላሓት አል ሙሓዲሲን
1⃣6⃣አል ቀዋዒዱል ሙስላ ፊ ሲፋቲላሒ ወዓስማኡል ሁስና
1⃣7⃣ረውደቱል ባዲዒን ሚን አሓዲሲ ሰይዲል ሙረሰሊን "
1⃣8⃣ብሉግ አል መራም ሚን አዲለቲል አሕካም
1⃣9⃣ተንቢሑ ዘዊል አፍሐም ኢላ ረእቢ ሰድኢ ወልዊአሚ አላ መንሐጅ ሰለፊል ኪራም
2⃣0⃣ሸርሁ ኡስሉ ሲታ ሊል ዑሰይሚን ""
2⃣1⃣ ሀዚሂ ደዕወቱና ወዓቂደቱና ""
2⃣2⃣ሸርህ ከሽፉ ሹብሀት
2⃣3⃣ኪታቡ አት—ተቅሪብ አተድሙሪያ ""
ኪታቡ ተውሒድ ሸይኽ ፈውዛን
2⃣4⃣ተብሲሩል ኸለፍ
2⃣5⃣"'አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ አኒል አስኢለቲ አልመናሒጂል ጀዲዳህ "
2⃣6⃣ሸርሁ ነዋዊዱል ኢስላም ሊሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን "
2⃣7⃣"'ጂናየቱ ተምዩዕ አለል መንሃጂ ሰለፍ"
"2⃣8⃣'ቱህፈቱ ሰኒያ ሸርህ መንዙቱል ሓኢያ "
2⃣9⃣ሸርህ አቂደቱል ዋሲጢያ ሊል ኻሊል ኻራስ
3⃣0⃣ኡሱሉ ሰላሳ
3⃣1⃣"'ሙተሚመቱል አጅሩሚያ "
3⃣2⃣አዳቡ ጣሊበል ኢልም
3⃣3⃣መትኑል አጂሩምያ
