ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 130
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+4197 أيام
+1 13230 أيام
أرشيف المشاركات
+2
የጠ.ላትን አባል ግንባሩን ብሎ ወደ ወንድሞቹ የተቀላቀለው ወንድማችን አቀባበል ተደርጎለታል ።
ወታደር ስንታየሁ ይባላል ከ9ወር በፊት በግዳጅ ነበር ወደ ውትድርና በአገዛዙ ታፍሶ የገባው ከዛም ምስራቅ እዝ 99ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሎ ለ3ወር የቆየ ቢሆንም አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርገው በደል እረፍት ስለነሳው የጠላ.ትን ተረኛ ጥበቃ (ዋርድያ )ግንባሩን ብሎ ከነ ሙሉ ትጥቁ አፋብሓ ቴዎድሮስ እዝ105ኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል ።
©ምስጌ ዘድንግል የ55ተኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ አጠር ያለ መግለጫ!
የምኒልክ ዕዝን ክንድ መቋቋም ያቃተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከተግባር ይልቅ "ውሸት"ን ትልቅ የአውደ ውጊያ ግንባር ካደረገው አመታቶች የተቆጠሩ ሲሆን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሎበት በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስም የሃሰት መግለጫ እያወጣ ይገኛል::
በመሆኑም እኔን እና የአሳመነዉ ኮር ም/አዛዥ የሆነዉን ኮማንዶ ፍቅሩ ሙልዬን ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ከሚኒልክ ዕዝ በድርጅቱ ትዕዛዝ እንደታገድን አድርገዉ ምላሱ ብቻ የቀረዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በትላንታናዉ ዕለት የማስመሰል መግላጫ አዉጥቷል።
እንኳን በወሬ ልንፈታ እና ልንደነግጥ ቀርቶ ድሮኑን እና ታንኩንም አልፈራንም እናም በመላዉ ዓለም ለምትገኙ አማራዊያን እና የትግላችን ደጋፊዎች ይህ የአገዛዙ የዉሸት መግለጫ መሆኑን እንድታዉቁ እና አሁን ላይ እኔም ሆንኩ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙልዬ የተጣለብንን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣን እንገኛለን።
እናንተም በውሸታችሁ ቀጥሉ እኛም በሐቀኛ ተግባራችን! በያዝናቸው አመርቂ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎቻችን ታጅበን ለመጨረሻው ግብ ድልና ነፃነታችን እየታገልን እንገኛለን::
ግፈኞች ሆይ ጦራችሁም ወሬያችሁም አይፈታንም:: አላማችንንም ላፍታም ቢሆን አያደናቅፈውም!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 7/2018 ዓ.ም
የአብይ አህመድ ሰራዊት እርስ በእርሱ የማይደማመጥ ፣ የአንድ ብሔር የበላይነት ያለበት ፣ ጀኔራሎች እና ኮሎኔሎች ከፍተኛ ዝርፊያ የሚፈጽሙበት ፣ ብሔራዊ ዓላማ የሌለው ፣ ደካማ ስነ ልቦና ያለው ፣ ለመበተን ቋፍ ላይ ያለ ሰራዊት ሆኗል ።
በፋኖ ታሪክ ይህ የትግል ዘመን ጠንካራ የአማራ ብሔርተኝነት የሚገነባበት ፣ ጠንካራ አመራር የሚፈጠርበት ፣ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል የሚገነባበት ፣ አማራነት እንደገና የሚታደስበት ዘመን ነው ።
በየትኛውም አካባቢ ፣ በየትኛውም የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ የአማራ ወጣት ወደ ፋኖ በመቀላቀል አብይ አህመድ በዱቤ እና በብድር የገዛውን መሳሪያ መታጠቅ አለበት ።
ድል ለጀግናው አማራ
ድል ለጀግናው ፋኖ
➺➺➺➺➺➺ማስጠንቀቂያ!
ደ/ማርቆስ ዩንቨርስቲ ለጥላት የቁሳቁስ ድጋፍ አደርጋለሁ ሲል ቃል ገባ
========
የደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ጠላት ደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ ለሚሰጠው የሚሊሻ ስልጠና የሚውል ፍራሽ ለመስጠት በዩንቨርስቲው ሴኔት ( በማኔጅመንት ) እንደወሰነ ተጨባጭ መረጃ ደርሶናል።
ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ከአብዮቱ መፈንዳት በፊትም ሆነ በሗላ የአማራህዝብ የሚከፍለውን ዋጋ በውል የሚረዱ ምሁራን የሞሉት የነበረ ሲሆን የአሁኖቹ እንክርዳዶች በምን ፍጥነት እንደበቀላችሁበት አግራሞትን የሚያጭር ነው።
የዩንቨርስቲው ማኔጅመንት አባላት ይህ ውሳኔ ዩንቨርስቲውን ታሪካዊ ጥላሸት የሚቀባ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ውሳኔው ተፈፃሚ የሚሆን ከሆነ በግለሰብ ደረጃም እያንዳንዳችሁን ዋጋ እንደሚያስከፍል መሆኑን ልታውቁት ይገባል።
ዩኒቨርስቲ የመፍትሄ አካል መሆን እንጅ አንድ ጀኖሳይድ ለሚፈፅም አካል ተባባሪ ሊሆን ከቶ አይገባም። ከዚህ በፊት ሴት አስገድደው ሲደፍሩ የነበሩ እና በስርቆ ተሰማርተው የነበሩ ከ11በላይ የፌደራል ፖሊስ ዓባላትን እጅ ከፈንጅ ከዩኒቨርስቲው ንጉስ ተክለሀይማኖት ብርጌድ አውጥታ 11መሳሪያ ታጥቃ እንደነበር ሊታወስ ይገባል።
ዘር የሚያጠፋን አረመኔ ሰራዊት በዩኒቨርስቲ ደረጃ በማኔጅመት ወስኖ እረዳለሁ ካለ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን ልናረጋግጥ እንወዳለን።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
በድሮን ጥቃት ከ105 በላይ የአገዛዙ ሚሊሻዎችና ንፁሃን ወገኖች በበለሳ ተገደሉ!!
በቅርቡ በዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጥር 01/2018 ዓ.ም ከባድ ድምሰሳ ሽንፈት የተጎነጨው የአብይ ሰራዊት የሞራል ማካካሻ የአየር ጥቃት ለማድረስ በማቀድ ከሰሞኑ በሳህላ እና በበለሳ ቀጠና ተደጋጋሚ የአየር ቅኝት እያደረገ የሰነበተ ሲሆን በዛሬው ዕለት ጥር 07/2018 ዓ.ም ረፋድ ዋግ ህምራ ዞን ሳህላ ወረዳ ሰየም ድልድይ የተባለ ቦታ በርካታ የራሱ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ ዓባላትና ተገደው የተሰበሰቡ ንፁሃን ወገኖቻችንን የሰው አልባ አይሮፕላን (ድሮን) ጥቃት አድርሶባቸዋል።
እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ከ65 በላይ የሚሊሻ ዓባላት የሞቱ ሲሆን ከ40 በላይ ንፁሃን ወገኖች በአየር ጥቃቱ የህይወት መስዕዋትነት እንደከፈሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ ቁስለኛ መሆናቸውም ታውቋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በላይ ዕዝ የሰራዊት ዓባላትን ለማጥቃት ሲቃጥት የሰነበተው አገዛዙ በዛሬው ዕለት የአካባቢውን ሚሊሻና ንፁሃን ወገኖችን እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በጅምላ ጨፍጭፏቸዋል።
በቀጣይ መረጃዎችን ለህዝባችን በይፋ እየተከታተልን የምናሳውቅ ሁኖ የንፁሃን ወገኖቻችንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በአገዛዙ ላይ በማነጣጠር የአፀፋ ምላሽ እንደምንሰጥ እያሳወቅን በጅምላ የአየር ጥቃት ህይወታቸው ላለፈ ወገኖቻችን በላይ ዕዝና ጎንደር ጠ/ግዛት ዕዝ በሚንቀሳቀሱበት የሰሜን አማራ ቀጠና (ጎንደር) በቀጣይ ቀናት ለሰማዓት ወገኖቻችን የሚመጥኑ ህዝባዊ የሀዘን አዋጅ ሊታወጅ እንደሚችል እናሳውቃለን።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ በላይ ዕዝ
ጥር 07/2018 ዓ.ም
አፋብኃ በላይ ዕዝ ህ/ግንኙነት መምሪያ
መነሻውን ከደሃና አምደወርቅ አድርጎ ሲንቀሳቀስ በነበረ የሚኒሻና ፖሊስ ኃይል ላይ በተወሰደ እርምጃ 46 ወታደሮች ሲገደሉ 29 የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ እንዲሁም 24ቱ ምርኮኛ መደረጋቸውን መረብ ሚዲያ መዘገቡ አይዘነጋም።
በውጊያው 48 የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 2ሺ 860 ተተኳሽ፣ 56 የወገብ ትጥቅ ተማርኳል።
ከ24ቱ ምርኮኞች መካከልም የድሃና ወረዳ ፖሊስ ምርመራ ሂደት ኃላፊ ኢንስፔክተር ሸጋ አያናውና የድሃና ወረዳ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ምስጋናው እንደሚገኙበትም ነው ጣቢያችን በወቅቱ የዘገበው።
እንሆ የምስል ማስረጃ‼️
07/ዐ5/2018 ዓ.ም
የተባረከችው ማህፀነ ለምለሟ የአማራዎች እናት ለአማራነት በፋኖነት መልኩ በአርበኝነት መልኩ ደግማ ደጋግሞ ጀግና ጀግና ትሰጣለች✊
ታላቅ እና ታናሽ ወንድማማቾቹ
ኮማንዶ ሳሙኤል ባለዕድል 🔥🔥
ኮማንዶ ዮሐንስ ባለዕድል 🔥🔥
አስቸኳይ ‼️
የጥንቃቄ መረጃ
ጃዊ መተከል እስከ ቋራ ባለው ቀጠና ከ ንጋቱ 11:00 ሰዓት PM የድሮን ቅኚት እየተደረገ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ መልክቱን አዝምት።
ጂቡቲ በኢትዮጵያ ግዛት የፈፀመችው የድሮን ጥቃት!
በትላንትናው እለት ጥር 5/2018 ዓ.ም በአፋር ክልል በኤሊዳር ወረዳ የገጠር ቀበሌ ላይ በደረሰው የድሮን ጥቃት ኢትዮጵያውያን የአፋር አርብቶ አደሮች ሰላባ መሆናቸው ታውቋል።
በድሮን ጥቃቱ አንዲት እናት ወዲያውኑ ስትሞት ሌሎች ሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል።
የጂቡቲ መንግስት ከወራት በፊትም በዚሁ ቦታ ላይ በቀብር ስነ ስርዓት ላይ ባሉ አፋሮች ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸው የሚታወስ ነው!
#Afar
ለውጥ ያለ መሰዋትነት የለም !!!
የአማራን የህልውና ትግል ስንመለከተው በዚህ ከ33 ወራት በላይ በተከታታይ ወራት በተፈጠረው ተጋድሎ በብዙዎቹ ቦታዎች ላይ ፋኖ ድል እየተጎናፀፈ ነው። ትግሉም በአጭር ስዓት በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል ሲያድግ እየጠራ መሄዱ አይቀርም ይሄ እውነታ ነው።
ትግሉ መስመር ሲይዝ የአስተሳሰብ ድሆች ሰውን ሊጎዱ ስለሚችሉ ጠንካራ ታጋዎች ከየትኛውም በተለየ መልኩ እራሳችሁን መጠበቅ ይኖርባችኋል። ምክንያቱም በእናንተ በስተጀርባ ለእናንተ የሚቆረቆሩ እና ተሰፍ ያላቸው ብዙ ናቸው ።
ማንኘውም ፍኖ ትግሉ ዳር እዲደርስ ከተፈለገ ማንኘውም በተጠቀቅ መኖር ግዴታ ነው ማንኘውም ፍኖ የራሱን ጥላ መጠራጠር ግዴታ ነው ።
ፍኖ በማንኘውም ስዓት የቆቅ ንሮን መኖር አለበት ማለትም መደበኛ አሳማ የሆነ ጠላት ብልፅግና አለበት ።
ለአማራ አስር ጠላቶች ቢኖሩት ጀግና የአማራ ቁርጥ ቀን ልጆች ሚሊየን ናቸው !!! አርበኛ ኤፍሬም ባዩ
ማሸነፍ ግዴታ ነው!!!
+3
109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር የሁለት ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
==================================
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር የሁለት ወር የግዳጅ አፈጻጸም በቀን 06/05/2018 ዓ.ም የገመገመ ሲሆን ጠንካራና መስተካከል ያለባቸው ድክመቶችን በማንሳት በጥልቀት ተወያይቷል። ክ/ጦሩ ጠንካራ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አመራሮችን በማበረታታት የወደፊት የስራ አቅጣጫወችን በማስቀመጥ የዕለቱን ፕሮግራም በስኬት አጠናቋል።
አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!
109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
ጥር 06/2018 ዓ.ም
በዚህ ወቅት ንጉሠ ነገሥቱ አባቷን ራስ ውቤን አስረዋቸው
ነበር። ራስ ውቤ የሰሜን፣ወልቃይት ፣ፀገዴ፣ትግራይ፣ ሰራየ፣
ሐማሴንና አንጎት (ሰሜን ወሎ) አስተዳዳሪ ሲሆኑ ከዓፄ
ፋሲለደስ የሚወለዱ ስለነበሩ ለንጉሥነት የሚገዳደሩ ነበሩ።
የጥሩወርቅ (ጥሩነሽ) እናት ደግሞ ወይዘሮ ላቂያየ የተባሉ
የትግራይ መሳፍንት ዘር ነበሩ። ከኒህ ሚስታቸው ደጃዝማች
ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የተባለውን ከሁሉ በላይ የሚወዱትን፣
እርሳቸውን እንዲተካ ያጩትን ልጅ ወለዱ። ዓፄ ቴዎድሮስ
በአጠቃላይ ፬ ጊዜ ሲያገቡ ፮ ወንድና ፫ ሴት ልጆች ነበሯቸው፣
እነርሱም፦
ወንድ ልጆች ሴት ልጆች ያልተረጋገጠ
፩) ራስ እንግዳ ቴወድሮስ - (የተዋበች ወይም እንግዳወርቅ?
ልጅ) 1833 ላይ የተወለዱ። በመቅደላ ጦርነት የተገድሉ። 3ቱ
ልጆቹ በእንግሊዞች የታሰሩ። ፩) ወይዘሮ አልጣሽ ቴዎድሮስ --
(ከሁለተኛ ሚስት) መጀመሪያ ጊዜ ከዳግማዊ ምኒልክ ጋር ጥር
1856 ላይ በመቅደላ የተዳሩ። ሁለተኛ ጊዜ ከራስ ባሪያው
ጳውሎስ፣ የትግራይ መስፍን ጋር ተጋቡ። ጥቅምት 1882 አረፉ
፩) ፒተር ኡስቲኖቭ - የእንግሊዙ ታዋቂ ጸሃፊ፣ ተዋናይና ድራማ
ሰሪ ፒተር ኡስቲኖቭ ቅድም አያቱ የቴወድሮስ ሴት ልጅ
እንደነበረች ይናገራል። ተመራማሪወች ቅድም አያቱ እሳተወርቅ
የተባለች መቃዶ የተባለ የጎንደር ወታደር ልጅ ናት ይላሉ።
፪) ራስ መሸሻ ቴወድሮስ - (የተዋበች ልጅ) 1840 ላይ
የተወለዱ። ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክን ከመቅደላ እንዲያመልጡ
የረዱ። በአባታቸው የደጃዝማችነት ማዕረግ ተሰጧቸው በኋላ
በዳግማዊ ምኒልክ ራስ የሆኑ። ልጆቻቸው
• ደጃዝማች ካሳ መሸሻ - የጎንደር አስተዳዳሪ
፪)ስማቸው ያልታወቀ
፫) ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ - (የጥሩነሽ ውቤ ልጅ) 1853
ላይ የተወለዱ። ሊድስ፣ ዮርክሻየር፣ እንግሊዝ አገር በ1870
ዓ.ም ያረፉ። ፫)ስማቸው ያልታወቀ ... ልጅ አላማ ጉዋሉን
ያገቡ
፬) ልጅ ኃይለማርያም ቴዎድሮስ - (ሁለተኛ ሚስት)
፭) ልጅ ይማም ቴዎድሮስ -- (ላቀች ወይም ጣይቱ)
፮) ልጅ ተሰማድንገት ቴዎድሮስ --(ሁለተኛ ሚስት)
ወጣቱ ኃይሉ ካሳ
ውልደትና ትምህርት ቤት
ካሳ ኃይሉ በ1811 ዓ.ም. አባታቸው ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ
በሚያስተዳድሩት ቋራ፣ ከእናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ተወለዱ።
ቋራ በምዕራቡ ኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበር የሚገኝ ሲሆን በዘመኑ
ከሱዳኖችና ክግብፆች ዘንድ ብዙ ወረራ ይደርስበት የነበር ክፍል
ነው። ደጅ አዝማች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳን ጋር በተደረገ
ጦርነት ሲያልፉ፣ በ1813 ዓ.ም ወይዘሮ አትጠገብ ህጻኑን
ቴወድሮስ ይዘው ወደተወለዱበት ጎንደር ከተማ ተመለሱ።
ወይዘሮ አትጠገብ በነበራቸው ገቢ መጠን ልጃቸውን በጥሩ
ሁኔታ ማሳደግ ስላልቻሉ ክንፉ ሃይሉ ህጻኑን ቴወድሮስ
በጎንደርና በጣና ሃይቅ መካከል በሚገኘው ቸንከር በተባለ ቦታ
የተክለ ሃይማኖት ገዳም ለትምህርት ላኩት። ቀጥሎ የሆነውን
በጊዜው የነበር ደብተራ ዘነበ እንዲህ ሲል ይዘግባል፡
በልጅነትዎ፡ቸንከር፡ትምርት፡ሲማሩ፡ከገዳሙ።ደጃች፡ማሩ፡
በደምቢያ፡ሸፈቱ።ያነ፡ጊዜ፡የቤጌ፡ምድር፡ሁሉ፡ገዢ፡እራስ፡ይማም፡
ነበሩ። ደጃች፡ማሩን፡ለማሳደድ፡በመጡ፡ጊዜ፡ገዳሙን፡ሰበሩት።
አብረው፡የሚማሩዋቸውን፡፵፰አሽከሮች፡ሰልቦ፡ልጅ፡ካሳን፡
ትቷቸው፡ሄደ፡በውስጥ፡ሳሉ።
ይህም በህጻኑ ላይ የማይጠፋ የአይምሮ ጠባሳ ትቶ ያለፈ ኩነት
ነበር።
ህጻኑ ወደ አጎቱ ወደ ደጃዝማች ክንፉ ቤት ተመልሶ በአጎቱ ቤት
የአስተዳደርን፣ የወታደራዊ ዘዴንና ስልትን ተማረ። ማንበብና
መጻፍን በዚሁ ወቅት በሚገባ ተለማመደ። የወደፊቱ ቴወድሮስ
እጅግ ማንበብን የሚወድ ሰው ነበር፣ የኢትዮጵያን ጥንታዊና
ጊዜያዊ ድርሳናትን፣ የአውሮጳን ጥንታዊ እና ጊዚያዊ ታሪክ
በደንብ እንዳጠና መረጃ አለ። የሼክስፒርን ስራወችና መጽሃፍ
ቅዱስን ሳይቀር እንዳጠና በጊዜው የነበሩ አውሮጳውያን
ሳይመዘግቡ አላለፉም። ለነበረበት ዘመን በደንብ የተማረ ሰው
ነበር።
ጥር 6 የካሳ ኃይሉ በኃላ (ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ ) የልደት ቀን ለማሰብ ተፃፈ።
+3
➺➺➺#ከብዙ_ጀግና_ሴቶች_መካከል_አንዷ ፦
ፋኖ ገነት ሰዋገኝ ትባላለች ። የሴት ጀግና ትምህርቷን ጠንቅቃ የተማረች ።በቴክኒክና ሙያ እሰከ ደረጃ 4 አጠናቃለች ። በመቀጠልም ዲግሪዋን በማኔጅመት ይዛለች ። በመከላከያ ኮንስትራክሽን ውስጥ ተቀጥራ ከ2 ዓመት በላይ አገልግላለች ።ከተቀጠረችበት መስሪያቤት ደሞዟንም ፣ቤተሰቧንም ትታ ወደ ትግል የተቀላቀለች እንስት። ለአማራ የህልውና ትግል ስትል ሁሉ ነገሯን ትታ ቡሬ አካባቢ ሲንቀሳቀስ በነበረው ቡሬዳሞት ፋኖን ከመመስረት እስከ አሁን ድረስ በፅናት የአረመኔውን ሰራዊት ከእግረኛ እሰከ አመራር በመሆን እየተፋለመች ትገኛለች።
የአማራን ህልውና ለማስቀጠል በሚደረገው ትንቅንቅ ሴትነቷ አላገዳትም ።ከወንዶች እኩል መሳሪያ በመያዝ የአረመኔውን ሰራዊት እያርበደበደችው ትገኛለች። ከቁጭ እሰከ ሽንዲ በተለያዩ ግንባሮች ፊለፊት ተፋልማለች።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች እንዲህ በጀግንነት የሚፋለሙት ትልቁ ምክንያት የህልውና አደጋ የተጋረጠበት ማህበረሰብ አካል መሆናቸው ነው። ላለመደፈር ፣ ላለመገደል ፣ ራስን ለመከላከል እየተደረገ ባለ ትግል ላይ ይገኛሉ።
ይህን ስርዓት እስከ መጨረሻው ለመቅበር ሁሉም የሚጠበቅበትን በማድረግ ላይ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
'ቴዎድሮስ ንብረት (ሳተናው ) ከተከሰሰበት ዜና መካከል
''ማታ በቴሌቪዥን አቢዮቱን ለማስቀልበስ ሲሞክሩ የነበሩት ኮረኔል አጥናፉ አባተ ተገደሉ። ብሎ ኢቲቪ ዘገበ'' ለቅሶ ጀመርን ወይዘሮ ዉባንቺ ቢሻዉ ጠዋት ለቅሶ ወጣች ። የእማየ ወዳጅ ነበረች ማልቀስ ጀመረች እናቴ እሷን አቅፋ ''ባሌን ባልሽ ገደለዉ''እያለች ተያይዘዉ ተላቀሱ።
እነሱን ታግሎ ለዚህ ያበቃ ሰዉ ሶሻሊዝም ለኢትዮጵያ አይሆንም ባለ፤ የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬት ባለቤት ባደረገ፣ሰዉ ዝም ብለን አንግደል ባለ ፣ ስልጣን ለህዝብ መልሰን ወደ ካምፕ እንመለስ ባለ በግፍ ተገደለ።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲህ ሆኖ ቀጠለ አቢዮት ልጇን በላች የተጀመረዉ በኮረኔል አጥናፉ አባተ እና በኮረኔል መንግስቱ ቢሆንም አቢዮት አሁንም ልጇን መብላት ቀጠለች በ2008 ዓ.ም ወጣቱ ለለዉጥ ተነሳ አመፀ ተገደለ። ወደ ስልጣን የመጡት ግን ፀረ ለዉጥ ሐይሎች ነበሩ እስክንድር ነጋ ፣ ዘመነ ካሴ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ብቻ ብዙዎቹ ለለዉጥ አንቅተዉናል ታስረዋል ተገድለዋል። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ተገድለዉ እነ እስክንድር ታስረዉ እነ አርበኛ ዘመነ ካሴ ኤርትራ በርሃ ገብተዉ ያመጡትን ለዉጥ ተመልሶ እነሱን ሊበላ ሶስት አመት አልፈጀም። በሰሜኑ ጦርነት ሰላማዊ ዜጎች ንፁሐን የፀጥታ ሐይሎች ተገደሉ። መሪዎች ግን በሲጋራ ችርስ ተባባሉ። እንደተወለደ የከሸፈዉ አብን የመሰረቱት የታሰሩ የተገደሉ ከባድ ዋጋ የከፈሉት ተገፍተዉ ዛሬ ለወንበር ብለዉ ከአብን እና ከህዝብ ጥቅም የሸፈቱ የአድር ባይነት ጌቶች አለቃ ሆነዋል።
አቢዮት ጀማሪ ከፍፃሜዉ ሳይደርስ አጨብጫቢዉ ቀድሞ በመድረስ ጌትነትን ይናጃል። እንደ ኮረኔል አጥናፉ አባተ ደርግን አምጦ ወልዶ በደርግ የተበላ ብዙ ነዉ። በላይ ዘለቀ ተዋግቶ ነፃ ሐገር ፈጠረ ከለዉጥ በኋላ የመጡ ሹመኞች ግን ከተደበቁበት ወጥተዉ ወንበሩን ተቆጣጠሩ። በላይ ጣሊያንን ፈርተዉ በኮበለሉ ባለስልጣናት በገመድ ታንቆ ተገደለ አቢዮት ልጇን ስትበላ እርህራሔ የላትም። የሚሉ እና ሌሎች ብዙ ዘገባዎችን ቴዎድሮስ ንብረት በሳተናዉ ሚዲያ አሰራጭቷል።
64ኛ ክፍለ ጦር ሶስት ቀን የፈጄ የስራ ስምሪት ግምገማ አካሂዶል።
ጥር 06/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና የእነማይ ወረዳ እና የሸበል በረንታ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የክፍለ ጦሩ የአንድ ወር የስራ ስምሪት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አድረጓል።
የውይይት መድርኩን የመሩት የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የቴዎድሮስ ዕዝ ም/ል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ አስረስ ማር ዳምጤ፣ አርበኛ ጥላሁን አበጄ እንዲሁም የክ/ጦሩ ዋና ሰብሳቢ ፋኖ ጥላሁን ሽፈራው ሲሆኑ በክፍለ ጦሩ የአንድ ወር የስራ ቸክ ሊስት የተሰጡ ስራዎችን በማገማገም ለአመራሩ ወታደራዊ እና ፓለቲካዊ ግንዛቤዎች በሰፊው ተሰጥተዋል።
በስራ ቸክ ሊስቱ በወታደራዊ ፕወዛ፣ ወታደራዊ ስራዎች፣ በፋይናስ አሰባሰብ፣ በፍትህ አሰጣጥ፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና መሰረተ ልማት፣ በህዝብ ንቅናቄ የውይይት መድርኮች፣ በአስተዳደር ፀጥታ እና ተተኪ አመራር የማብቃት ስራዎች ላይ የክፍለ ጦሩ እና የወረዳው ጊ/መንግስት አመራር በሰፊው በመወያየት ድርጅቱ በእየ ዘርፉ የሰጠውን የስራ ሐላፊነት ገምግመዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጥር 06/2018 ዓ.ም
