ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 130
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+4197 أيام
+1 13230 أيام
أرشيف المشاركات
+1
ናትናኤል መኮንን በፈረንጆቹ አዲስ አመት ይኼንን መበጥረቅ ትቀንሳለህ ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ።ነገር ግን ብሶብህ አጠናክረህ መጥተሀል 😁😁😁
የአርበኛ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጦር
ሐውጃኖ ክፍለ ጦር የማረከችውን
ምስል ሞጭልፈህ ተከታዮችህን ታስጨፍራለህ ?? ምን ጉድ ነህ በፈጣሪ ?
የብልጽግና የፕሮፓጋንዳ ክንፍ ምን ያክል የወረደና ግራ የገባቸው መሆኑን ነው በቂ ማሳያ ነው::
የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ በየዕለቱ እየፈራረሰ ነው ።ይህ የምታዩት አድስ ከተቋቋመው 11ዕዝ 16 ክፍለጦር ተቋሙ የግለሰብ ሆኖ ህሌና እማይቀበለው ግፍ እንድሰራ መታዘዝ ልቀበል አልችልም በማለት አፋብሀ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል።የክፍለጦሩ አመራሮችም ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።
©አርበኛ ሱልጣን የሱፍ የየጎፍ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ!
06/ዐ5/2018 ዓ.ም
#የጥንቃቄ_መልክት‼️
የብልፅግና ስርአት ይፋዊ ጦርነት ከጀመሩ 33 ወር በላይ አልፈውታል በመሆኑም በተለያዬ የአማራ ከተሞች ፋኖ ወደ ከተማ ለማጥቃት እየገባ በሚል ምክንያት የአብይ አህመድ አረመኒያዊ ወንበር አስጠባቂ መከላከያ እና ሚኒሻ ወጣቶችን አፈሳ እያደረገ ይገኛል።
ሁኖም ወጣቶች ራሳችሁን ንፁህ ነን ብለችሁ የስር አቱን አስከፊ እና ጨፍጫፊነት እያወቃችሁ ከጠላት እራሳችሁን እንድትጠብቁ ስንል እናሳስባለለን።
ዛሬ ከምሽቱ 10:00 ጀምሮ ከአስራ አንድ(11) ግዜ በላይ የአረመኒው አብይ አህመድ ኃይል በእሳት ያአቃጣላትን ከተማ ማለትም አጣዬ ቅዳሜ ገብያ አደይ አበባ ግሮሰሪ እና በተለያዩ ፑል ቤት፣መጠጥ ቤት እና የመሳሰሉት በመሰባሰብ የምትንቀሳቀሱ ወጣቶች መንግስት ጥናት በመስራት አፈሳ የጀመረ መሆኑን እየገለፅን ራሳችሁን ከዚህ አረመኔ ስርአት አድኑ።
ጥር 06/ዐ5/2018 ዓ.ም
በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሦስት የአገዛዙ ሠራዊት አባላት ወደ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ‼️
ጥር 06/2018 ዓ.ም
በአማራ ጠል ርዕዮተ ዓለም ተወጥኖ ሕዝበ አምሐራን በጅምላ በመፍጀት ሰይጣናዊ ግብሩን በይፋ እያሳየ የሚገኘው የብልጽግና ሥርዓቱ በገዛ ሠራዊቱ እየተከዳ ይገኛል።
በገንዘብ ጥቅማ ጥቅም እየደለለና በግዳጅ እያፈሰ የራሱ እኩይ ሴራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ በርካታ የድኃ ኢትዮጵያውያን እናቶችን ልጆች ቢሰበስብም አረመኔው አገዛዝ ከጣለባቸው ድንዛዜ የነቁ አያሌ የብልጽግና ሠራዊት አባላት ሲያውቁ በድፍረት ሳያውቅ በስህተት የበደሉትን ሕዝባቸውን ይቅርታ እየጠየቁ ወደ ሕዝባቸውና ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለትም በቀለ ሙሊሳ፣ እንየው ቸኮልና ጌትነት ወርቁ የተባሉ ሶስት የብልጽግና ሠራዊት አባላት ከደብረ ማርቆስ ከተማ ወጥተው የ14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
©የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል
06/ዐ5/2018 ዓ.ም
ካፕቴን ማስረሻ ያሰርሸነው ወንድም
ከከዱ ላይቀር እንዲህ ነው። አስቀድመህ ፋኖንን ስትከዳ፣ የገዛ ቤተሰቦችህን፣አማራነትህን፣እምነትህንና ማንነትህን ነበረ የከዳሃው።
ይህንን ወጣት ፋኖ ጨምሮ በሸዋ የተሰው ወንድሞቻችንን ነፍስ፤እግዚአብሔር በሰማዕትነት ይቀበልልን!!!
⚫️የራያ ቆቦ ወርቄ የአገዛዙ ሚሊሻዎች በራያ ሮቢት ሶስት በመግደልና አምስት በማቁሰል ስምንት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ጨፈጨፉ⚫️
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና አገዛዝ ጋር በመወገን የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ ያሉት የራያ ወርቄ ሚሊሻዎች በትናትናው ዕለት ጥር 5/2018 ዓ.ም ከብልፅግና መከላከያ ጋር ሆነው ካላኮርማ ክፍለ ጦር ጋር ባደረጉት ውጊያ በደረሰባቸው ከባድ ሽንፈት ሸሽተው ወደ ሮቢት ከተማ በመግባት ስምንት ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በጥይት ጨፍጭፈዋል::
በነፃነት ታጋዩ ፋኖ ሲሸነፉ ፈሪ ሁሌም አህያውን ትቶ ዳውላውን ነውና እነዚህ ህዝቡ በአደባባይ የሚያውቃቸውና ነገን በተስፋ እየጠበቀ በፍፁም ትግስት የያዛቸው ህዝብን ከህዝብ የማፋጀት አላማ ያነገቡ የወርቄ ታጣቂዎች ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ገብተው ንፁሃንን በግፍ ሲጨፈጭፉ አገዛዙም የሚፈልገው ድርጊት በመሆኑ በዝምታ ማየትን መርጧል::
እነዚህ ፀረ-አማራ ታጣቂዎች ስራቸው የሚመዘዘው ከኦህዴድ ብልፅግና ሲሆን የተሰጣቸውን ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት አላማ አንግበው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ንፁሃን ያልታጠቁ አማራዎችን በግፍ እየጨፈጨፉ ቀጥለዋል::
በዚህም በትናትናው ዕለት ጥር 5/2018 ዓ.ም ራያ ቆቦ ሮቢት አቶ ሽመልስ ሲሳይ የተባለ ጋሪ እየገፋ በቀን ስራ የሚተዳደር ግለሰብ እና ሁለት ወንድና ሴት (ትግስት እና አያሌው መለሰ) የተባሉ የሆቴል አስተናጋጆችን በጥይት ደብድበው ሲገድሉ አምስት ተጨማሪ በማቁሰል ባጠቃላይ ስምንት ንፁሃን ያልታጠቁ አማራዎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል::
ከዚህ ግፍ በተጫማሪም ፀረ-አማራ ሚሊሻዎቹ ሮቢት ከተማ የተለያዩ ሱቆችንና የንግድ ቦታዎችን ንብረት ዘርፈው መሄዳቸውን ከከተማው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ችለናል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 6/2018 ዓ.ም
06/ዐ5/2018 ዓ.ም
የሁሉም የአማራ ባንዳ ሚኒሻና ፖሊስ መጨረሻ እንዲህ ነው የፋኖ ጥይት ብልት አይቶ ነው የሚመታው ተው እርፍ ተብለሃል
በመካነሰላም ግንባር የ45ተኛ ክፍለ ጦር አንድ ቲም የሚሆኑ አባላት ተደመሰሱ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ሰራዊት ሰሞኑን ለተከታታይ ቀናት በተደረገ ግምገማ መሰረት የአመራር ሪፎርም ከተደረገለት በኃላ በትናንትናው እለት በመካነሰላም ግንባር ድል ቀንቶታል:: ከመካነሰላም ከተማ በመነሳት ወደ ሰኞ ገበያ አቅጣጫ ተንቀሳቅሶ በወገን ኃይል ላይ ጉዳት ለማድረስ ተኩስ የከፈተውን ጠላት በመልሶ ማጥቃት ጉዳት ያደረሱበት የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር 1ኛ ጥላሁን ፈንታው ሻለቃ እና 2ተኛ ጌታሰው አስረስ ሻለቃ ፋኖዎች አንድ ቲም የሚሆኑ ወታደሮችን ሲደመስሱ 3 አቁስለዋል::
ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ ስንደው ገዜ እና የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ኮማንዶ ጀንበሩ ጌታቸው በመሩት በትናንቱ ኦፕሬሽን ያልታሰበ ጉዳት የደረሰበት የጠላት ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ተደናግጦ ስለነበር የወረዳው ካቢኔ አባላት ጭምር ከተማይቱን ለቀው ሜዳ ላይ ማደራቸው ተርጋግጧል:: የተደመሰሱ አባላቱን አስከሬን በ3 አምቡላንስ ጭኖ መካነሰላም ከተማ ወደሚገኘው ጁኒየር ትምህርት ቤት የወሰደው ጠላት ጁኒየር ትምህርት ቤትን ካምፕ አድርጎት መክረሙ አንሶት እንደ መካነ-መቃብር እየተጠቀመው መሆኑ ይታወቃል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም
አሳምነው ክፍለ ጦር ወልድያ እና ቃሊም ዙሪያ በመካናይዝድና በድሮን የታገዘ ማጥቃት ያደረገውን የፋሽስቱ ሰራዊት በመቶዎች ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
ምስራቅ አማራ ኮር አንዶቹ አሳምነው ክፍለጦር ከሐውጃኖ ክፍለ ጦር ጋር በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ጥር 5/2018 ዓ.ም ንጋት ከወልድያ ከተማ በመነሳት ስድስት ሻለቃ እግረኛ ሰራዊትና መካናይዝድ እንዲሁም በድሮን ታግዞ ወደ ቃሊምና አካባቢው ማጥቃት ያደረገ ሲሆን የአሳምነው ልጆች ባግባቡ በመመከትና ስበው ከበባ ውስጥ በማስገባት በመቶዎች የሚቆጠር ጠላት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በአስር የሚቆጠር በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ባለፉት ጥቂት ቀናቶች በአሳምነው ክፍለ ጦር ዙ23 የተማረከውና ከወልድያ ላሊበላ ጋሼና ባህርዳር መስመር በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብቶ ከባድ ወታደራዊ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ኪሳራ የደረሰበት ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ይህንን ኪሳራ አካክሳለሁ ብሎ አቅዶ በከፈተው ውጊያም በመቶዎች የሚቆጠር ሰራዊቱን እንዲሁም በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሱን አጥቶ ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዷል::
አሳምነው ክፍለ ጦር በተጋድሎው በርካታ የጠላት ሃይል ከመደምሰስ ባሻገር ከ20 በላይ ክላሽ እና ከ7000 በላይ የተለያየ ተተኳሽ እንዲሁም ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርከዋል::
በዚህም ተደጋጋሚ ሁለንተናዊ ኪሳራ የደረሰበት ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ቃሊም ከተማ ዙሪያ ስድስት ጊዜ የድሮን ጥቃት በመፈፀም ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎች ላይ የሞትና የአካል መጉደል ጉዳት አድርሷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 5/2018 ዓ.ም
ካላኮርማ ክፍለ ጦር ጉባላፍቶ እና ራያ ቆቦ ወረዳ በሁለት ግንባር ከባድ ውጊያ በማካሄድ ድል አስመዘገቡ::
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጥር 5/2018 ዓ.ም ጦር ጉባላፍቶ ወረዳ በቅሎ ማነቂያ እና ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ በሁለት ግንባሮች ከባድ ውጊያ በማካሄድ በርካታ ጥምር ዙፋን ጠባቂ አገር አፍራሽ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ካላኮርማ ክፍለ ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሻለቃ ከእንጃፋት ወንዳች ኩልመስክና ድልብ የመጣንና በቅሎ ማነቂያን ይዞ ወደ ቃሊም ማጥቃት ያደረገን ጠላት ባግባቡ መክተው በመዋልና በርካታ ሰራዊቱን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ምሽግ ያደረገውን በቅሎ ማነቂያ ከተማና ዙሪያውን በማስለቀቅ ወታደራዊ ገዥ መሬት መቆናጠጥም ችለዋል::
በሌላኛው ግንባር ካላኮርማ ክፍለ ጦር 1ኛ እና 4ኛ ሻለቃ እንዲሁም የ5ኛ ሻለቃ ቃኝ ጥር 5/2018 ዓ.ም ቀትር አካባቢ ጀምሮ ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ የፋሽስቱ አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት በማድረስ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::
በዚህም የምስራቅ አማራ ኮር ሁለቱ ካላኮርማ ክፍለ ጦር በሁለት ግንባሮች ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ቃሊምና ወልድያ ዙሪያ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ ካደረጉት ከምስራቅ አማራ ኮር አንድ አሃዶች ጋር የተናበበና የተቀናጀ ሚዛን ጠባቂ ግዳጅ በመፈፀም አመርቂ ድል አስመዝቧል::
የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ረሽኗል:: መረጃውን በዝርዝር ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 5/2018 ዓ.ም
አፄ ቴዎድሮስ
፤
እኛ የምዕራብ አማራ ቀጠና ልጆች በትውልዱ የደም ዝውውር ውስጥ የሚመላለሰው ‘አፄ ቴዎድሮስ’ የዕዝ ስያሜ መጠሪያችን ነው። ቴዎድሮስን ስናስብ፦
👉🏿የኃሳብና የተግባር አንድነትን፦
ለህዝብና ሀገር ከዘመን ቀድሞ ማሰብን፣ በአንድ መሰለፍን፣ መተባበርና ማስተባበርን፤
፤
👉🏿ፅናትና የአይበገሬነት መንፈስ፦
የኮሶ ሻጭ ልጅነት ያላኮሰመነውን፣ በጊዜ ሂደት ገፍቶ የወጣ እምቅ አቅምን፤
፤
👉🏿ሩቅ ማለምና ዘመንን ተሻግሮ ማየት፦
ዓርብ ዓርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም መባልን፣ ጋፋትን መትከል፤ ለዘመናዊ አስተሳሰብ ልብ መክፈትን፣ ለውጥ መናፈቅን፤
፤
👉🏿ለክብርና ለዓላማ በፅናት የሚከፈል ቁርጠኝነት፦
በተጠማ አንጀት ባሩድን መጠጣትን፣ እጅ አለመስጠትን፣ ሞትን መናቅ፣ እስከ ህቅታ ለክብርና ዓላማ መታመን፣ በሞት ዕለት መወለድ ያየንበትን፤
፤
የካሳ ኃይሉን የውጣ ውረድ ጉዞን እየተከተልን ነው።
መልካም ልደት ቴዎድሮስ 👑
@ማንችሎት
አሳዛኝ ዜና
የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ታናሽ ወንድም እና የቅርብ አጃቢው አብርሀም ሰጤ በመከላከያ ሰራዊት ተገደለ"
ጥር 6/ 2018 ዓ.ም
===================================
የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ታናሽ ወንድም እና የቅርብ አጃቢው አብርሀም ሰጤ በታላቅ ወንድሙ ታላቅ ክህደት ከተፈፀመበት በኋላ በደብረ ብረሀን ወረዳ ሳሲት ኪዳነምህረት ትንሽ ከተማ ከጓደኞቹ ጋር እያለ በአረመኔው ሰራዊት ተገድሏል።
የአብይ አህመድ የፖለቲካ ሸቀጥ አከፋፋይ በመሆን የአማራን ህዝብ በመካድ ተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራርሚያለው የሚለው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ የራሱ ወንድም ያለበትን ካምፕ በመጠቆምና መረጃ በመስጠት በፈፀመው ክህደት ታናሽ ወንድሙን ጨምሮ የ25 የወንድሞቻችንን ህይወት አስበልቷል።
የአፍሐድ አመራሮችን ያነጣጠረ ጥቃት በማድረግ በሳሲት ኪዳነ ምህረት በተፈፀመ ጥቃት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ለጠላት መረጃ በማቀበል የእናቱን ልጅ ለአብይ አህመድ ገብሯል ከከዳህ ላይቀር እንዲህ አድርገህ ክዳ! የአንተሰ ቅጥ አጣ።
ወንድሜ አብርሃም ሰጤ ፈጣሪ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያሳርፍ
ጊዜ መስታወት ነው፤ ታሪክ ደግሞ እንደ አልማዝ እንቁና የማይጠፋ አሻራ ነው። በትግል ታሪክ ውስጥ ታሪካቸውን በርካሽ ዶላር የሚለውጡና ክብራቸውን በጊዜያዊ ሹመት የሚቀይሩ ሰዎች እንደሚኖሩ ማሰብም ሆነ መገመት የሚጠበቅና ግልጽ የሆነ ነገር ነው። ትናንት ወንድሞቻችን የነበራችሁ ከሃዲዎች እየሰጣችሁ ያላችሁት እጃችሁን ወይስ ክብራችሁን?
በውጊያ ውስጥ ጣላትን መጣልና መውደቅ፣ መሸነፍና ማሸነፍ፣ እጅ ማሰጠትና እጅ መስጠት ወይም መማረክና መማረክ በጦርነት ታሪክ ውስጥ ዓለም ላይ ያለ፣ የነበረ እና የሚኖር ሁነት ነው። በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ውስጥ ግን ይሄን ሁሉ አፈ-ታሪክ ያደረገ እና በውጊያ መሃል ሰራዊታችን የራሱ ማጥፊያ ጥይት ቢጨርስ እንኳ ደረቱን ለጥይት ለማስመታት ድንጋይ ይዞ የሚፋለጥ ሰራዊት በተገነባበትና መስዋዕትነቱን በቅድስና የሚቀበል ትውልድ በተፈጠረበት፤ ዛሬ ላይ የክህደትን ጥግ ያሳዩን ወንድሞች ያደረጉት ግነ ክብር መሸጥ እሽቅድምድም በጥቁር መዝገብ ላይ የሚቀመጥ ታሪክ ነው፡፡ ክብርን መሸጥ ደግሞ ከሞት ሁሉ የከፋው የሞራል ሞት ነው። በአማራ ባህል እጅ መስጠትን ያክል ውርደት የለም። ምናልባትም በመሰሎቻችሁ ቸርነት ብልጭልጩን ቪላ እና መኪና ታገኙ ይሆናል። ግን እውነት እንነጋገር ከተባለ፣ የምታገኙት ሁሉ (ካገኛችሁ እንኳ) ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል በታች ነው፡፡ በሰው ሰውኛ ቢታሰብ እንኳ የድል ቺቦአችንን ካበራነው በኋላ ከምታገኙትም በታች ነው። የት ላይ ተቀምጣችሁስ ልትበሉት አምሯችሁ ነው? "የዳውንቱ ድርድር" የምትሉት የሽያጭ ውልም፣ በታሪክ መዝገብ ላይ "ባንዳ" የሚል ሥም ተሰጥቶት የአዲሱ ጀግና ትውልድ መማርያ ሆኖ ይቀጥላል::‘’ሱልልታ ስንደርስም የሚክደን ይኖራል” ብለናችሁ እነደነብርም አትርሱ፡፡ ዛሬ ዶላሩ ሲያልቅ እና የጥቅም ገመዱ ሲበጣጠስ የወዳጅ ጠላት ሁሉ እየሾለከ እየጠፋ ይገኛል፡፡
ትግል የብረት ብቻ ሳይሆን የሞራልም ጦርነት በመሆኑ፣ "ተገፋሁ" ፣ "ተበደልኩ" ወይም የሌለ political narration በመስራት "ከነከሌ ጋር ልንሰራ ነው" የሚል የተስፋ መቁረጥ ትኬት መቁረጫ መላና የሽንገላ ቃላት እጅ ለመስጠት እንደ "ቪዛ" ሊያገለግሉ አይችሉም። ዛሬ ላይ የምናየው "የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ" የሚል አይነት የውሽልል መንገድ የአማራን ስሪት እና ስነልቦና የማይገልጽ አሳፋሪ የሞራል ውድቀት ሲሆን፣ በተለይ እንደነ ኮሎኔል ሙሀባ እና ማስረሻ ሰጤ ላሉ ተራጋፊዎች "ተገፋሁ" ወይም ከነከሌ ጋር ሊሰሩ ነው የሚል የፈጠራ ታሪክ ለአላማ የመጽናት ችግር ሲገጥም እንደ ማጭበርበሪያ የሚጠቀሙት ሰበብ የከዳተኞችና የፈሪዎች መሸሸጊያ ብቻ ነው።
በድሮን፣ በቢኤም፣ በመድፍና በክላሽ በጅምላ ከተጨፈጨፈው ህዝባችን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የሰራዊታችን አባላቶች ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ሰማዕትነትን የተቀበሉ ጓዶቻችን አላማን ዳር ለማድረስ፤ ይህ ታላቁ የአማራ ህዝብ የመኖርና ያለመኖር የህልውና አደጋ ተጋርጦበት ህልውናውን በክንዱ ለማረጋገጥ የድል ባለቤት ለመሆን ቆርጦ የተነሳ እውነተኛ ታጋይ፣ በውስጥ አለመግባባት ወይም "ቦታ ተነፈግሁ" በሚል የጎጥ ሰበብ ወደ ገዳዩ ብብት ስር አይሸጎጥም። የውስጥ ትግል (ጓድን የማረምና መስመር የማስያዝ) አካል ተደርጎ የሚወሰድ እንጂ ከወንድሙ ጋር ተጣልቶ ለጠላቱ እጅ የሚሰጥ አካል ከመጀመሪያውም ለህዝብ ነጻነት ሳይሆን ለግል ክብሩ፣ ለዝና፣ ለጠላቶቻችን አላማ ሰርጎ የገባ፣ ለዝርፊያ ወይም ለኢጎው ሲደክም የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። መገፋትም ሆነ መበደል ቢኖር እንኩን በትግል ጉዞ ውስጥ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች እንጂ ወደ ባንዳነት ለመቀየር በቂ ምክንያት ሊሆኑ ከቶውን አይችሉም።
በሌላ በኩል፣ የሚዲያው ሰራዊትና ደጋፊው አካል ሁነቶችን ያለገደብ በማራገብና ከልክ በላይ በመበሻሸቅ የጠላት መሳርያ ከመሆን ሊታቀብ ይገባል። በትግል ሂደት ውስጥ አቋም ከአላማ አንጻር ሊቃኝ ይገባል እንጂ፣ በየቀኑ በሚፈጠር ወሬና አሉባልታ ውስጥ መዋኘት ለጠላት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ያለፈ ምንም ስትራቴጂካዊ ትርፍ የለውም። በትግል ዳገት ላይ "ዛለብኝ ጉልበቴ" ብሎ የወደቀንና የከዳን ግለሰብ የአጀንዳ ማዕከል አድርጎ ማራገብ ለጠላት ስነ-ልቦናዊ ነዳጅ ማቀበል በመሆኑ ትኩረት መደረግ ያለበት በግለሰቦች መምጣትና መሄድ ላይ ሳይሆን በማይናወጠው ዓላማችን ላይ ብቻ ሊሆን ይገባል። ስክሪን ላይ ያለው ዲስኩርና ሜዳ ላይ ያለው እሳት መለያየቱን ተገንዝቦ፣ ትግሉን በሚዲያ በርቀት እየተቆጣጠሩ ለመምራት ከመሞከር ይልቅ፣ ለህልውናው የሚዋደቀውን የፋኖ ክንድ በሚመጥን የሞራል ልዕልና መቆም የታሪካዊ አደራም ግዴታም ነው።
ውድ ደጋፊዎቻችንና የቁርጥ ቀን ታጋዮች ሆይ! አንዳንድ ቅጠሎች ስለረገፉ ዛፉ አይደርቅም፤ ይልቁንም የደረቁት ሲረግፉ ዛፉ ይበልጥ ይለመልማል፣ በምትኩ ብዙ አዳዲስ ቅርንጫፎችንም ያወጣል። የማንኛውም ግለሰብ እጅ መስጠት የሚቀንሰው የትግል ወኔ የለም፤ ይልቁንም ገለባው ሲለይ ስንዴው እየጠራ ይሄዳል። ትናንት በጣት ከሚቆጠሩ ዲሽቃዎች ተነስተን ዛሬ ላይ በሁለት መቶዎች የሚቆጠር ዲሽቃዎች፣ ከሰማንያ በላይ ሞርተር ለቁጥር የሚያዳግት መትረየስና ስናይፐር፣ ሹተርና ዙ-23 ታጥቀን፤ በየወረዳው ከነበረው ከሰላሳዎች የማይበልጥ የሰው ሃይል ተነስተን አሁን ላይ International Military Standard ያሟላ በሻለቃ፣ በክፍለጦር፣ በኮርና በዕዝ አደራጅተንና ተደራጅተን ሃገር መረከብና ሉአላዊነቷን መጠበቅ የሚችል ሰራዊት እየገነባን እንገኛለን። ይሄን እያዩ በ11ኛው ሰዓት እየከዱን ስታዩ ትግሉ አደጋ ላይ የወደቀ የመሰላችሁ የትግሉ ደጋፊዎች ትግላችን ያለበት ቁመና ከወትሮ በተለየ በየቀኑ እየተሻሻለና በአላማውን የታጠቀ ሰራዊት ግንባታ ላይ እንደሆን አውቃችሁ እገዛችሁን አጠናክራችሁ መቀጠል ላይ ብቻ ትኩረት ማረግ ይኖርባችኋል።
እኛ የያዝነው ክላሽም ሆነ ብዕር የሚፈርመው የውርደት ውል ሳይሆን የነጻነት ታሪካዊ ሰነድ ላይ ነው። የእኛ እስክሪብቶ ሲፈረጥ፣ የሚወጣው ቀለም ሳይሆን የድል ታሪክ ነው። ወርቅ በእሳት ሲፈተን እንደሚጠራ ሁሉ፣ እኛም በዚህ ፈተና ውስጥ ስናልፍ ቢገፉት የማይወድቅ ተራራ ሆንን እንዘልቃለን፡፡ ዛሬ በረሃ ላይ የምንከፍለው መስዋዕትነት፣ ነገ በልጆቻችን ታሪክ ላይ በወርቅ ቀለም ይጻፋል። ፈርጣጭ ለሆዱ ያድራል፣ እኛ ለሕዝባችን ጣምነን እንቀጥላለን ትክክለኛውን ነጻነትም እናረጋግጣለን።
የአማራን ህዝብ ከሚጨፈጭፍ እና ሃገርን ከሚሸጥ ስርዓት ጋር መፋለም ጽድቅ ነው። አላማችን የጸና፣ ክንዳችን የጠነከረ ሆኖ ይቀጥላል። መጨረሻችንም በክንዳችን እናብጃጀዋልን! በድል ወደ ዓላማችን እንገሰግሳለን! አሸንፈንም በህዝባችንና በታሪክ ፊት አቁመን እንፋረዳችኋለን።
“ዶላሩም ያልቃል፤ የወዳጅ ጠላትም ሲያምሰን ከርሞ ሹልክ ይላል”!
የፀና ድልን ይቀናጃል!
ድል ለአማራ ህዝብ!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
Simeneh Mulatu Tafere የቴዎድሮስ ዕዝ ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ
+2
#ማርከናቸዋል_ተቀብለናቸዋል‼️
አብይ አህመድ ገዝቶ በብርሀኑ ጁላ ትዛዝ በድሀ ልጆች ባለቤትነት የተላከልን ሀብት #ማርከናቸዋል_ተቀብለናቸዋል።
አፋብኃ በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር✊
ይቀጥላል....💪💪💪
06/ዐ5/2018 ዓ.ም
---የድሮን አሰሳ
በእግረኛው ሀይል የማይተማመነው አገዛዙ ፋኖ በተቆጣጠረባቸው ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ የድሮን አሰሳ እያደረገ ይገኛል
አሁን ከሌልቱ 4:00 ሰዓት ላይ በሽዋ ኤፍራታ ግድም ወረዳ ደብር ብርሃን ከሰም እንዲሁም ግሸ ወርኢሉ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የድሮን አሰሳ ስላለ ጥንቃቄ ይደረግ!
ቻናላችን ሸር ጆይን አድርጉ ቤተሰብ
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ጥምር ኃይል ርስበርስ ተመታትቷል🔑
ጥር 05/2018ዓ.ም
የአቢይ አሕመድ ዙፋን ጠባቂ ቅጥረኛ መከላከያ እና አድማ ብተና አካላት በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር መዳረሻ ''ዋንዛዬ'' ከተማ ላይ በጠዋቱ ተመታትተዋል። ቅጥረኞቹ የተለያዬ ጎራ ተሰልፈውና ምሽግ ይዘው ከጠዋቱ 01:30 ላይ ተመታትተዋል። የንጹሐን ዓምሐሮች ደም ያሰከራቸው የአቢይ ቅጥረኞች ምንነቱ ባልታወቀ ሁኔታ የከፋ ጉዳትን አሥተናግደዋል።
በአገዛዙ የርሥበርሥ ተኩሥ ልውውጥ 03ቱ ወድያውኑ ሲሞቱ 08ቱ ደግሞ ከባድ ቁሥለኛ ሆነው ወደሕክምና ተወስደዋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊
አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
+8
➮ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል‼️
በሁለት እጁእነሴ ወረዳ በጥሩ ሰላም እና ቦዳ በረዲ ቀበሌወች የ201ኛ ኮር 54 ክፍለ ጦር ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል።
➻➻➻➻➻➻➻◊◊➻➻➻➻➻➻➻
በውይይቱ መድርኩ:-
➛ የትግሉን ወቅታዊ ሁኔታ
➛ ከፍትህ አሰጣጥ ጋር በተያየዘ
➛ ፋይናስ እና ሎጄስቲክ አሰባሰብ
➛ የቀበሌ የፀጥታ ጉዳይ እና የወጣቶች ተወካዮችን በማስመረጥ በማስገምገም በአዲስ የማዋቀር ስራ የተሰራ ሲሆን ህዝባችን ከተደቀነበት የህልውና ችግር ለመውጣት አገዛዙ በህዝባችን ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በአመራሮች ግንዛቤ ተሰጥቷል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ጥር 04/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በበቅሎ ተጭነውና በከዘራ ተደግፈው ወጥተው በአውሮፕላን የሚመለሱ ጡረተኞች ጉዳይ ሊያሳስብን አይገባም።
ትግሉ የሕልውና በመሆኑ።
በትግላችን መፃኢ ውጤት ላይ የሚለውጠው አንዳች ነገር የለም።አገዛዙን አሸንፈነዋል።ጨርሰን ደግሞ ለግብዓተ መሬት እናበቃዋለን። በዚህ አትጠራጠሩ።
ለምን፦
1ኛ= እኛ አማሮች፣ ትጥቅ አንስተን የምንሞትለት በቂ መሰረታዊ መታገያ ምክንያት ስላለን። እሱም፦በአገዛዙ የተከፈተብን የዘር ማጥፋት አደጋ ነው። ሕልውናችን (ዘራችን) እንዳይጠፋ የጀመርነው ትግል በመሆኑ።
2ኛ= የገጠመንን የሕልውና አደጋ በልኩ ተረድቶ በመደራጀት አንድያ ህይወቱን ሳይሰስት የሚሰጥ በርካታ የአማራ የቁርጥ ቀን ተዋጊ፣አዋጊ፣ፖለቲከኛና ምሁር ዛሬም በየ ጠቅላይ ግዛቶቹ እንደ አሸን እየተፈለፈለ መሆኑና በመኖሩ።
3ኛ= በባዶ እጁ ትግል የጀመረው ይህ የእሳት ሰደድ የአማራ ወጣት ዛሬ ላይ እራሱን ከፈፅሞ መጥፋት የሚከላከልበት በቂ ትጥቅ ከአገዛዙ እየማረከ በመታጠቁና በቂ የትጥቅ አቅም በመፍጠሩ።
4ኛ= የአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግል፣በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጠንካራ ህዝባዊ ድጋፍና ቅቡልነት ስላለው።
ለዚህ በቂ ማሳያው፦ ስንቃችን፣መረጃችን፣ደጋፊያችንና ተዋጊያችን ራሱ የህልውና አደጋው ባለቤት የሆነው ህዝባችን በመሆኑና ፋኖነትን ከአማራው መነጠል ስለማይቻል።
5ኛ= የትግሉ ባለቤት እጃቸውን አንከርፍፈው ለጠላት የሚገብሩት ጥቂት ግለሰቦች ሳይሆኑ፣በኢትዮጵያ ላለፉት 50 ዓመታት በተከታታይ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት እየተፈፀመበት የሚገኘው ታላቁ የአማራ ህዝብ በመሆኑ።
6ኛ=የፋኖ የትጥቅ ትግል፣ከዚህ ቀደም በጎረቤት አገራት በትጥቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለብሔር ነፃነት "እንታገላለን" በሚል ተደራጅተው እንደነበሩት በሌሎች አገራት ነፃ ቀጠናዎች የተቋቋመ ባለመሆኑና በአጭር ጊዜ ውስጥ ትግል በጀመረባቸው የአማራ አፅመ ዕርስቶቹ አብዛኛውን ቀጠና ከጠላት ነፃ በማውጣት ጊዜያዊ መንግስት መስርቶ መገኘቱ። ከአገዛዙ መቀመጫና የፋኖ የትጥቅ ትግል መዳረሻ ከሆነችው አዲስ አበባ በጥቂት ኪ.ሜ ርቀት መገኘቱ።
7ኛ=የፋኖ የውጊያ ብቃትና ዲሲፕሊን፣ምርኮኛ አያያዝ፣በቀጠናው እየፈጠረው የመጣው ተፅዕኖ በሂደት ዓለምአቀፋዊ እውቅናና ተቀባይነትን እያስገኘለት መምጣቱ የጎረቤት አገራትን ትኩረት እንዲስብ አስችሎታል። ይህ ደግሞ ወታደራዊ ሎጀስቲክስና የፋይናንስ ድጋፍ ወደ ፊት እንዲያገኝ በር ከፋች እድሎችን ፈጥሯል። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ፈጥሮ በማሳደጉ ረገድ የተሻለ ቁመና ላይ በመገኘቱ።
8ኛ= የአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግል፣ በአጠቃላይ አንድ የሽምቅ ተዋጊ ማሟላት ያለበትን መሰረተዊ ነገሮች ከሞላ ጎደል ያካተተ በመሆኑ።
እነዚህም፦ ማኀበረሰባዊ ንቅናቄና እምቢተኝነት፣ወታደራዊ ኀይል/ተቋም፣ፖለቲካዊ ተቋምና ኢኮኖሚያዊ አቅም ናቸው።
9ኛ= አማራው፣የሕልውና የነፍጥ ትግሉን መሸነፍ፣መተው፣መበተንም ሆነ ቸል ማለት ሊያስከትለው የሚችለው ውጤት አደገኛ መሆኑንን ጠንቅቆ ያውቃል። ይኸውም በራስ ስንፍናና ፈቃድ ከምድረ ገፅ መጥፈት ነው። ስለዚህ ለላመጥፋት መሸነፍ አይደለም መሳሳት አይቻልም።
10ኛ= በዚህ የሕልውና ትግል በርካታ ጀግና ወንድሞቻችንን ገብረናል።በርካታ የአማራ እናቶች አጣላስ አጥልቀዋል። ሚስት ያለ ባል፣ልጆች ያለ ወላጅ ቀርተዋል። በርካታ ሀብት ንብረት ወድሟል። በአማራ ባህል ከጠላት ጋር ደም ተቃብቶና ተሸንፎ ገብሮ መኖር ፍፁም ነውር ነው። የተሸናፊነት ታሪክም የለንም። ይህ ደግሞ የከፋ የሚያደርገው ከላይ እንደተጠቀሰው፣ የመጥፋትና ያለ መጥፋት የህልውና ትግል መሆኑ ነው። በማስረሻና በሙሃቤ እንዲሁም አጋሮቻቸው ገብሮ መግባት የሚቆም ትግል ያለ የሚመስለው ካለ የዓለማችን ጅል መሆን አለበት። ስለዚህ የአማራ ህዝብ በየ ዕለቱ በድሮን አረር ለሚጨፈጭፈው፣ ዘር አጥፊው አብይ አህመድ አገዛዝ ገብሮ ይኖራል ብሎ ማሰብ ከንቱነት ነው።
መውጫ፦ የአማራ ፋኖ የሕልውና ትግል፣በአገር ቤት የገጠመው አገዛዙን ነው። የአገዛዙ ደንገጡር በመሆን የራሳቸውን ወገን የሚያስፈጁት ደግሞ ብአዴኖች ናቸው። ብአዴኖች ስንል አማሮች ማለት ነው። አረጋ ከበደ፣ተመስገን ጥሩነህ፣ይርጋ ሲሳይ፣አብዱ ሁሴን፣ዳንኤል ክብረት...ወዘተ ናቸው። ልክ እንደነዚህ አሽከሮች ሁሉ ማስረሻ ሰጤ፣ፋንታሁን ሙሃቤ፣ፀዳሉ..ወዘተ የመሳሰሉት ትግሉን ለቀው ሲከዱ እንደ ብአዴኖች ሆነዋል። የምናያቸውም ሆነ የምንታገላቸው እንደዛ ይሆናል ማለት ነው። አሁን ከባህር የወጡ አሳዎች ሆነዋል።በመሆኑም እነዚህ ካሃዲ ግለሰቦችን አጀንዳ ከማድረግ እንውጣ። በእጅ አዙር የአገዛዙ አጀንዳ አራጋቢዎች አንሁን። ይልቁንስ የፋኖ ድርጅታዊ አንድነት አልቆ ወደ መዳረሻ ግባችን በድል እንድናመራ መሬት ላይ የሚገኙ ኀቀኛ ፋኖዎችንና አደረጃጀቶችን እናግዝ።አንከፋፍል!!
አሸናፊዎች ነበርን፤ ነገም እናሸንፋለን!!
