ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше4 132
Підписники
Немає даних24 години
+4577 днів
+1 19430 днів
Архів дописів
#ለወገን_ሀይል‼️
አሁን በዚህ ሰዓት (ከጠዋቱ 3:10) ከደ/ማርቆስ አንድ FSR እና አንድ ፓትሮል የአብይ መከላከያ ከወደ ዩኒቨርስቲ ወደ አደባባይ እየወጣ ነው ወዴት እንደሚሄድ አይታወቅም በአካባቢው ያለ የወገን ሀይል ዝግጁ ይሁን‼️
08/ዐ5/2018 ዓ.ም
አገዛዙ በውጊያ የተገደሉ የራሱ ወታደሮችን አ*ስ*ከ*ሬ*ን በድሮን ደበደበ!
በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ከወልድያ ከተማ ዙሪያ አከባቢዎች ጀምሮ እስከ ቃሊምና ቃሊም ዙሪያ አከባቢዎች ድረስ በተደረገው ተጋድሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል።
ውጊያው የተካሄደው ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሲሆን፡ ከ13 ሰዓታት በላይ የጨበጣ ትንቅንቅ ነው የተደረገው።
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥር 05/2018 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ፡ ከወልድያ ዙሪያ ማለትም ጥቁር ውሃ ምላሽን ይዞ እስከ ቃሊም ድረስ በወሰዱት ውጤታማ ነው በተባለ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን በመደምሰስና በርካታ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ከነ ተተኳሹ በመማረክ ድል መቀዳጀታቸውን በእለቱ ጣቢያችን መዘገቡ አይዘነጋም።
ያለምንም ማቋረጥ ለተከታታይ 13 ሰዓታት በተደረገው የጨበጣ ውጊያ፡ ከወልድያ ከተማ ዙሪያ ሚጦና ጃርሳን ጨምሮ ከጥቁር ውሃ ምላሽ ጀምሮ አላገዶ፡ አፍሪኬር፡ ቃሊም መገንጠያ፡ ዘንዶ ጅራት(ከሳምት በፊት የአየር መቃዎሚያ እስከ ኦራሉ የወደመበት ቦታ)፣ ቃሊም መገንጠያና ቃሊም ድረስ የሸፈነ ተጋድሎ ተደርጓል።
አገዛዙ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጨምሮ በወልድያ ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ስታዲየም እና በከተማዋ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ጄነራል መድፍ እንዲሁም በከተማዋ አዲሱ ማረሚያ ቤት እየተሰራ በሚገኝበት ጉቦ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጠመደው ሞርተር፣ ቢኤምና ዙ23 ታግዞ ከሁለት ዕዝ የተወጣጡ ከሦስት ክፍለጦር በላይ ወታደሮችን በሚኒሻና አድማ ብተና መንገድ መሪነት በማሰለፍ ሲዋጋ የዋለ ቢሆንም፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ግትልትል ኃይል የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራን በመከናነብ "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" ሆኖ ቀርቷል።
በምኒልክ ዕዝ ስር ከሀውጃኖ ክ/ጦር እና ከጄነራል አሣምነው ፅጌ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በወሰዱት ስኬታማ በሆነ የመከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮችን መደምሰስ ችለዋል።
የጠላት ኃይል በሚደመሰሱበት ወታደሮች ልክ ተጨማሪ ኃይል እያስገባ የዋለ ሲሆን፡ ምሽት ላይ ግን የሚጨምረውን ኃይል በማቆም ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማሰማራት ተከታታይ የዘፈቀደ ድብደባዎችን ፈፅሟል።
በዚህም በሰዓታት ልዩነት ከ12 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን፡ አገዛዙ የእሱን ስልጣን ለማራዘም ሲሉ ሲዋጉ በፋኖ የተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አ*ስ*ከ*ሬ*ን ደብድቧል።
ይህም፡ የፋኖ አባላቱ በውጊያው ከተገደሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ክላሽና ሌሎች ወታደራዊ ንብረቶችን እንዳይሰበስቡበት በማሰብ የፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ነው ሲሉ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።
በድሮን ጥቃቱ በፋኖ በኩል የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ነገር ግን በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ንፁኋኖች ተገድለዋል።
በጥቃቱ ከተገደሉ ንፁኋኖች መካከል አንድ የቤተክርስቲያን ጠባቂ አባትን ጨምሮ ሌሎች በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሴትና ህፃናት እንደሚገኙበት ታውቋል።
በተጨማሪም ከወልድያ ከተማ በሚወነጨፍ መድፍ ሕይወታቸው ያለፈና የቆሰሉ ንፁኋኖች መኖራቸው የተነገረ ሲሆን፡ የመድፍ ጥቃቱ የቤት እንስሳቶችንና ተሰብስቦ የተከመረ የማሽላና የጤፍ ነዶ ማውደሙን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ ዐምሓራ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
🕯🕯 ዝክረ ሰማዕትነት ጥር /07/2017 ዓ.ም 🕯
_🕯🕯__
ቆራጡ ፦ ሸ አለቃ እንዳሸዉ ጎሽሜ እጄን ለጠላት አልሰጥም ብሎ በኩራት ጠላትን እረፍርፎ እራሡን ሰማዕትነት ያደረገ የእኛ ዘመን ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ አርበኛ አለቃ እንዳሻው ጎሽሜ በዚህች ዕለት ቀን 08/05/2017 ዓ.ም ነበር በርሲሳይ አላላ መገንጠያ የአብይን አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይል ብዝዎችን ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ሰማዕትነት የተቀበለው። ነገሩ እንዲህ ነው
ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው፤
ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው፥
ምናሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው፥
ይላሉ የአማራ አበው በመፃፍ ዝክራቸው።
አርበኛ እንዳሻው ጎሽሜ የምድሩ ድሮኑ የሽዋው መብርቅ የሚኒልክ ልጅ ጥር 08 /05/2017 ዓ ም የማለዳዋ ያቺ የምታበራዋ ፀሐይ የዛሬን ቀን ነበር ብርሃኗን ማብራት ያቆመችው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ የአማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ጀግኖች በኤፍራታ ግድም ወርዳ ካፈራቻቸው የ7ለ70 ክፍለጦር ዘመቻ መምሪያ ኋላፊ ሁኖ በመስራት በውጊያ ስልቱ ከአባቶች በወረሰው አዋጊ ተዋጊ የተዋጣለት የይፋቴው አንበሳ በክብር ሰማዕትነት የተቀበለበት ቀን ነው።
ይህ ትግል ለእውነት ሲሉ ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው ለአማራ ህዝብ ነፃነት ከውጣ ውረድ ባለፈ አንድያ ነፍሳቸውን ሰጥተው ብዙዎቹ አልፈዋል። መውደቅን ፣መቁሠልን ፣መድማት ከምንም የማይቆጥሩት ጀግኖች እንደ ሺ አለቃ እንዳሻዉ አይነት ብዙ ዕልፍ ዓላፍ ለጠላት እጅ መስጠት ነውር መሆኑን የተገነዘቡ ለክብርና ለማንነት መውደቅን ለነፃነት መፋለምን ማሸነፍን ግባቸው ያደረጉ ብዙ ጀግኖች ተፈጥረዋል።
ብዙ ዕልፍ ዓላፍ ጀግኖች ከትናንት እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ የትግል አደራ ተሸክመው ከ33 ወር በላይ በፈጀው የጦርነት አውደ ውጊያ ለቃላቸው እየታመኑ በተኩስ ድምፅ የሚዘከሩ ለሰማዕትነት የተዘጋጁ የትግልን አላማ የትግልን መዳረሻ አውቀውና አስበው የሚራመዱ ጀግኖች ታሪካቸውን በደምና በአጥንታቸው እየፃፉ የሚልፉ የአሳምነውን ልብ የተላበሱ እንደ ይፋቱ ጀግና እንዳሻው ጎሽሜ አቤት ውጊያ ወደፊት እንጅ ወደ ኃላ የማይሉ አናብስቶች ተፈጥረዋል ።
አይለቀስ በስማቸው አይቀለድ በደማቸው፣
ወደቁ አይላቸውም ያቆሙት ህዝባቸው።
ያቆዩልን ንፁህ ስምን ያኖሩልን ነፃ ሀገርን፣
እንጠብቀዋለን ሞተን እየኖርን።
ነፃነቱን መርጦ እልፍ ሞት የናቀ፣
ለውነት ተሰልፎ ለውነት የወደቀ።
ልክ እንደ ጥንቶቹ እንደጀግኖቻችን፣
ለህዝብ መቆም ነው ምን ጊዜም ትግላችን።
ህዝብን የማይጠላ ፅንፈኛ ያልሆነ፣
በመገንጠልን ሳይሆን ባንድነት ያመነ።
ሀይማኖት አክባሪ ፍትህ ያስቀደመ፣
በደሙ ነጠብጣብ ሀገሩን ያቆመ።
የፅናት ተምሳሌት የነፃነት ጮራ፣
ስማችን ፋኖ ነው ነገደ አምሓራ።
ትናንት እነሱ አልፈው በንፁህ ደማቸው ታሪክን ፅፈዋል፣
ጠላት ሞቱ ቢልም በልባችን ማህደር ህያው ሆነዋል ።
🕯 ጀግኖች ሁሌም በልባችን ትኖራላችሁ🕯
🕯🕯ታሪክ እናወሳለን ሰማዕታትን እዘክራለን ትግል ይቀጥላል 🕯🕯
ጥር 08/05/2018 ዓ ም ከግንባር
Attention❗ በፍጥነት #Share ይደረግ
አረመኔው የአብይ አህመድ ነብሰ-በላ ስርዓት በደቡብ ጎንደርና አርማጭሆ ዙሪያ መጠነ ሰፌ የድሮን ድብደባ ዕቅዶች እንዳ'ቀደ መረጃዎች እየወጡ ስለሆነ ሰራዊታችንና መላው በቀጠናው የሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ ከጥቃቱ ራሱን ለመከላከል ከምንጊዜውም በላይ ጥረት እንዲያደርግና ለኢላማ ምቹ የሆኑ የመሰባሰቢያ ቦታዎች ላይ ማለትም ጤና ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም የአምልኮ ቦታዎች(ቤተክርስቲያንና መስጂድ) አካባቢ ከመሰባሰብ መቆጠብ እንዳለበት በአፅንዖት እንገልፃለን።
መኮንን አስፋው!
የመምህራንን ደህንነትና ህልውና እንጠብቃለን"
ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የተሰጠ መግለጫ
ጥር 7/2018 ዓ.ም
≡==================================
የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል በመቀስቀስ ጉልህ ሚና የነበረው የመንግስት ሰራተኛውና የመምህራን ንቅናቄ ከፍተኛ አሰተዋጽኦን የማይዘነጋው 206ኛ ኮር እስከ አሁን ድረስ ትግሉን ከፊት ሁነው በአመራርነት የሚመሩ የመንግስት ሰራተኞች እና የመምህራን ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም።
የአረመኔው ሰራዊት በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ ከፈፀመ በኋላ የመሰረተ ልማት ስራዎች ሙሉ ለሙሉ ተቋርጠው የሀገሪቱ ገቢ ለጥይት መግዣ ሲሆን፣ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ኮሌጆች፣ የኃይማኖት ተቋማት እና የንግድ ቦታዎች ወደ ጦር ካምፕነት መቀየራቸው ከአማራ ህዝብ የተደበቀ ሚስጢር አይደለም።
ይህንን ተከትሎ በቁጥር ለመጥቀስ በሚያዳግት ሁኔታ የጤና ባለሙያዎችና ዶክተሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች፣ ካህናት፣ ቄሶች፣ የአብነት ተማሪዎች እና ነጋዴዎች በድሮን ሲደበደቡ በርካቶች በአረመኔው ሰራዊት በግፍ ተረሽነዋል እልፎችም በማጎሪያ ጣቢያ ተወርውረዋል።
ኮሩ በሚንቀሳቀስበት የምስራቅ ጎጃም ዞን መቀመጫ ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ በ8 የወረዳ ከተሞች ያሉ መምህራን፣ መንግስት ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ስቃይና በደል እየተንገላቱ ሲሆን ህፃናት ያለ ወላጅ መቅረታቸውንም የተመለከተው ኮሩ በሚንቀሳቀስበት ሁሉም ቀጠናዎች ባሉ ወረዳዎችና ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ያሉ 417 (አራት መቶ አስራ ሰባት) የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቤቶች፣ 33 (ሰላሳ ሶስት)የሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በአረመኔው ሰራዊት ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን የኮሩ የዳሰሳ ጥናት ያረጋግጣል ።
የሀገሪቱን ሙሉ በጀት ለጦርነት እያዋለ የሚገኘው አረመኔው ስርዓት ኮሩ በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ያሉ የ11676 (አስረ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት) መምህራን የሁለት ወር ደሞዝ 326,928,000 ብር (ሦስት መቶ ሀያ ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት ሺህ ብር) በመንጠቅ ለሚኒሻና ካድሪ የአበል ክፍያ መዋሉን አረጋግጠናል ።
ከ800 በላይ ርዕሰ መምህራን እና መምህራን በደብረ ማርቆስ ፣ሉማሜ፣ አምበር፣ ደጀን፣ ቁይ፣ ረቡዕ ገበያ እና ደብረ ኤልያስ ከተሞች ማጎሪያ ጣቢያ ታስረው እየተሰቃዩ ሲሆን ከአፈናው ያመለጡ በርካታ መምህራን ቤተሰቦቻቸውን በትነው መሰደዳቸውም ታውቋል።
በዚህና መሰል የአረመኔው ሰራዊት ግፍ ቤተሰቦቻችሁን በትናችሁ የምትሰቃዩ ወገኖቻችን እና ልጆቻችሁን መመገብ የተሳናችሁ መምህራን 206ኛ ኮር በተቆጣጠረባቸው ሁሉም ቀጠናዎች በማንኛውም የስራ ዘርፍ ተሰልፋችሁ እራሳችሁንም ሆነ ቤተሰቦቻችሁን ማስተዳደር የምትችሉ መሆኑን እያረጋገጥን ኮሩ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርግ በማረጋገጥ ነው። ከአረመኔው ሰራዊት ጋር በመተባበር በወገኖቻችን ላይ መከራን የሚጭኑትንም የጠላት እጆች ተከታትሎ ኮሩ እርምጃ እንደሚዎስድ ማሳወቅ እንወዳለን ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር
ተቀራረቡ ተነጋገሩ !!
ደውለህ 'እንዴት ሰነበትክ ?' ብለህ ጠይቀው ወንድምህን። በዛው የእራስህንም ደህንነት ታውቃለህና ! እሱ ደህና ሲሆን ብቻ ነው አንተም ሰላም የምትሆነው።
ከተዳከምክ ሊበላህ ጥርሱን አግጦ ያሰፈሰፈው ብዙ ነው። ክንድህ ቢዝል አጥፊህ ዕልፍ ነው። መርጦ አይተውህም ! ለይቶ አይምርህም።
ያጠፋህ "እንዲህ ሁኖ በዚህ ሁኖ ተሳሳትኩ ይቅርታ" በለው ደፍረህ። እሱም ደፍሮ ይቅርታውን ይሰጥሃል!! አማራጭ የለውም።
"ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ ወንድምህ እሱ ነው!" ያልኩህን የ'ኔን የወንድምህን ምክር ስማ። ሌላው ሊጠቀምብህ ነው የሚፈልገው በሰበብ ለይቶ !!
ፋኖነት ✊✊
አማራነት ✊✊
የህልውና ትግላችን አጀንዳዎች
------------------------------
የአማራን ህዝብ ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ሲባል አጀንዳዎቻችን በግልፅ ከላይኛው መዋቅራችን እስከ ቡና ጠጡ ድረስ ተደራሺ መሆን አለበት።
የህልውና ትግላችን ዋና አጀንዳዎች ተቀንብበው ያለቁ፣ጊዜ እና ሁኔታ የማይሺራቸው ሆነው መቀረፅ ይኖርባቸዋል!!
በተቀረፀ እና በተቀነበበ አጀንዳ ውስጥ ያለ ትግል መሰረቱ አይናጥም!! አይለወጥም!!
ወጥነት ያላቸው አጀንዳዎች ዕሳቤያቸው ህዝባዊ መሰረት ስለሚኖራቸው ማለት ነው!!
በሌላኛው ገፅ በህልውና ትግላችን አጀንዳዎች ዙሪያ እንግዳ ሰው አይኖርም ማለት ነው።
የትግላችን አጀንዳዎች ህዝባዊ መሰረት ካለው እንግዳውስ ማን ይሆናል??
ምክንያቱም ሁሉም ባለድርሻ በግልፅ እና ፍኖተ መንገዱ ከተነገረው አድስ ሃሳብ ከየትስ ይወለዳል?? ለማንስ ያዋልዳል ??
ስለዚህ የህልውና ትግላችን አጀንዳዎች ወጥ ሆነው እንዲቀረፁ ደግሞ ሁሉም ያገባኛል የሚል የትግላችን ባለቤቶች እና ባለ ድርሻ ነኝ የሚለው ሁሉ ሊግባበት የግድ ነው።
አዎንታዊ አጀንዳዎቻችን የተግባር ስራችን ማስፈፀሚያ ናቸው።
ለተግባራዊነታቸው እና ለድርጊታችንም መነሻ የሚሆነው አዎንታዊ አጀንዳችንን በተግባር አጀንዳችን ፈፅመነው ስንገኝ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
ትግላችን በሁለንተናዊ መልኩ ለውጥ የሚያመጣው ተመሳሳይ እና ወጥነት ያላቸውን ስራዎች ማከናወን ስንችል ነው።
በተሟላ እና በብዙሃኑ የተቀረፁ አጀንዳዎቻችን ለማስፈፀም ደግሞ ስትራቴጅካዊ አንድነት፣መዋቅራዊ አንድነት እና ስልታዊ አንድነት ያስፈልጋል!!
የአማራ ህዝብ እና የልጆቹን ትግል በድል ለመቋጨት ሁነኛው መፍትሔ በሃገራዊ፣በቀጠናዊ እና በህዝባዊ አጀንዳችን ዙሪያ ተመሳሳይ የሆነ የካሜራ ዕይታ እንድኖር በትጋት ልንሰራ ይገባል!!
ለውጥ፣ትኩረት፣ራዕይ እና ብሔራዊ ብስለት ያለበት ትግል በዕለታዊ አጀንዳዎች አይንጠለጠልም!!
ስለዚህ የህልውና ትግላችን አጀንዳዎች ከዕለታዊ ስራችንና ከዕለታዊ ክንውኖች በላይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል!!
ከብርሸለቆ ህፃናት ማጎሪያ ካንፕ በማምለጥ ፋኖን ተቀላቀሉ።
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ዛሬም እንደ ትናንቱ ከእናታቸው ጉያ እየተነጠቁ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶችን በከብር እየተቀበለ የወገን አለኝታ መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል።
ዛሬም ከብር ሸለቆ ማሰልጠኛ የመጡ ቴዲ ወርቄ ፥ያሲን ቢልሳ ፥አብዲ ሙዛንቢል፥ጥላሁን ታከለ የተባሉ ወጣቶችን ከብር ሸለቆ ማሰልጠኛ ተቋም ተረክበናል።
የኢትዮጵያ እናቶች የወለዳችሁትን ልጅ እየነጠቀ የሳት አሩር ላይ የሚጥድን አብይ መራሽ አሸባሪ ቡድን እያዘገዙ ቢገኙም ከትምህርት ገበታቸው ህፃናትን በማፈን ለጦርነት እየማገዳቸው ይገኛል።
ህፃናት በሰላም ወደ እናትና አባታቸው በመላክ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት ትልቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ጥር 04/2018 ዓ.ም
+4
ያልተወራላቸው ስት ጀግኖች አሉ
ፋኖ እሸቱ በቀለ በሽዋ ክፍለ ሀገር በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በኤፍራታና ግድም አቦበር ቀበሌ የበቀለ ጀግና ነው።
ፋኖ እሸቱ በቀለ የቀድሞው ልዩ ሀይል አባል ሲሆን ብልፅግና በሴራ የአማራን ልዩ ሀይል ሲያፈርስ ወደ ፋኖ የተቀላቀ ጀግና ነው ።
ይህ ሰው በኤፋራታና ግድም ወረዳ 7ለ70 ክፍለጦር ስትመሠረት ይህ ወጣት በዲሽቃ ተኳሽ ምድብተኛ ሆኖ ስቱን አውደ ውጊያ አገት አስደፍቷል ። በውጊያ ጎን ለጎን ስት ዲሽቃ ተኳሽ አፍርቷል ።
ፋኖ እሸቱ በቀለ የሀገር መከላከያ ለመጀመሪያ ጊዜ የማረከችው 7ለ70 ክፍለጦር ስበር ሻለቃ በይፋትና ጥሙጋ በቀወት ወረዳ መግስት፣ ባራ ላይ ይቺ ሻለቃ ስትማርክ ዲሽቃ ተኳሽ እሱ ነበረ።
በሳሲት ሰላድጋይ 103 አየር ወለድ ኮማዶን ክፍለጦሩን ቀጥቅጦ
የመታ ጀግና ነው ድሽቃ ይዞ ሲጠጋ ሰራይቱ ከፊት እልል እያለ ነው የሚዋገው ድሽቃን እንደ ክላሽ አነጣጥሮነው ግባር የሚመተው እደነዚህ አይነት ስት ጀግና አለ።
ፋኖ እሸቱ በቀለ ካራለጎማ ሌተራል ጀነራሉን ቀድቦ የጣለ ጀግና ነው ። ዙ 23 አነጣጥሮ በአንድ ጥይት የቃጠለ ጀግና ነው።
አጣዬ ሞሉ ላይ መድፉን አነጣጥሮ የመታ ጀግና ነው እደነዚህ አይነት ስት ጀግኖች አሉ የሱ ተመሳሳይ ።
ጀግኖችን በይፋ አደባባይ እያወጣን እውቅና መስጠት ይሄ መብት ሳይሆን ግዴታ ነው ። የዚህን ጀግና ስም ለመጥራት የሰራቸው ስራዎች እጅግ ብዙ ናቸው።
ሌላ ጊዜ መረጃ አጠናክረን እንመጣለን !!!
ጀግናን ሲሞት ሳይሆን በቁሙ እናበረታታ !!!
ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ 15 የጠላት ኃይል በመደምሰሰ፣አንድ ብሬንና ስድስት ክላሽንኮፍ በመማረክ ተከዜ ክፍለ ጦር ታላቅ ድል ተጎናፀፉ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው ተከዜ ክፍለ ጦር ላስታ ወረዳ ኩልመስክ ከተማ ጥር 06/2018 ዓ/ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ከባድ ትንቅንቅ የብልፅግና ዙፋን አስጠባቂ የጁላን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ተከዜዎቹ ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።
የብልፅግና ሰራዊት ከሙጃ እስከ ኩልመስክ ያካለለ በመድፍ የታገዘ ውጊያ ያደረገ ቢሆንም የአካባቢያቸውን መልከዓምድር ጠንቅቀው የሚያውቁት ተከዜዎቹ እንደፈለጉ ወጥተው ወርደው ጠላትን እነርሱ በሚፈልጉት አግባብ ቃኝተው የጠላትን አንገት በማስደፋት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።
በዚህ አውደ ውጊያ 15 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ10 በላይ ቁስለኛ እንደሆነ ታውቋል፤በተያያዘም አንድ ብሬን፣ስድስት ክላሽንኮፍ፣500 የብሬን ተተኳሽና 650 የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
+5
ጥር 07,2018ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ከባህርዳር ሻለቃ ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ ለቀጣይ ስራና የግዳጅ እንቅስቃሴዎች እራሱን ዝግጁ አደረገ።
* የኮርና የክፍለጦር አመራሩ በ102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በባህርዳር ሻለቃ መካከል በመገኘት ለሰራዊቱ በትጥቅና በስና ልቦና የጠነከረ ሀይል እንዲኖር የፓለቲካና ወታደራዊ ስልጠናዎችን በመስጠትና ከምንጊዜውም በለይ ሰራዊቱን በማንቃት ለግዳጅ ዝግጁ አድርጎ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
ፋኖ አማረ ጌታቸው ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት!
ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
+7
በደድ እየሱስ አቦ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
ጥር 07/2018ዓ.ም
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር አመራሮች እና ቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስተዳደር በተገኙበት በዛሬዉ ዕለት ሰፊ ሕዝባዊ ዉይይቱ ማካሄድ ተችሏል በስብሰባውም ቀጠዊ የፖለቲካ፤ የመልካም አስተዳደር ግንዛቤ በመፍጠር የተቻለ ሲሆን ህዝቡ እኛም ሆነ ልጆቻችን ወጥተን ለመግባት የተቸገርን ስለሆነ ትግሉን እስከወዲያኛው ለመገርሰስ ድጋፋችን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት አጋሬነታቸውን የገለፁ ሲሆን የትግሉን የህዝባዊ ፊታውራሪነት ማስቀጠል እንዳለበትና የጮቄን ተራራ በአማራዊ እሴት መጠበቅ እንዳለብን የጋራ ተግባቦትና መረዳት ተፈጥሯል።
በመቀጠለም
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ጥር 07/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+2
የጠ.ላትን አባል ግንባሩን ብሎ ወደ ወንድሞቹ የተቀላቀለው ወንድማችን አቀባበል ተደርጎለታል ።
ወታደር ስንታየሁ ይባላል ከ9ወር በፊት በግዳጅ ነበር ወደ ውትድርና በአገዛዙ ታፍሶ የገባው ከዛም ምስራቅ እዝ 99ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሎ ለ3ወር የቆየ ቢሆንም አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርገው በደል እረፍት ስለነሳው የጠላ.ትን ተረኛ ጥበቃ (ዋርድያ )ግንባሩን ብሎ ከነ ሙሉ ትጥቁ አፋብሓ ቴዎድሮስ እዝ105ኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል ።
©ምስጌ ዘድንግል የ55ተኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ አጠር ያለ መግለጫ!
የምኒልክ ዕዝን ክንድ መቋቋም ያቃተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ከተግባር ይልቅ "ውሸት"ን ትልቅ የአውደ ውጊያ ግንባር ካደረገው አመታቶች የተቆጠሩ ሲሆን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሎበት በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስም የሃሰት መግለጫ እያወጣ ይገኛል::
በመሆኑም እኔን እና የአሳመነዉ ኮር ም/አዛዥ የሆነዉን ኮማንዶ ፍቅሩ ሙልዬን ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ከሚኒልክ ዕዝ በድርጅቱ ትዕዛዝ እንደታገድን አድርገዉ ምላሱ ብቻ የቀረዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በትላንታናዉ ዕለት የማስመሰል መግላጫ አዉጥቷል።
እንኳን በወሬ ልንፈታ እና ልንደነግጥ ቀርቶ ድሮኑን እና ታንኩንም አልፈራንም እናም በመላዉ ዓለም ለምትገኙ አማራዊያን እና የትግላችን ደጋፊዎች ይህ የአገዛዙ የዉሸት መግለጫ መሆኑን እንድታዉቁ እና አሁን ላይ እኔም ሆንኩ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙልዬ የተጣለብንን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣን እንገኛለን።
እናንተም በውሸታችሁ ቀጥሉ እኛም በሐቀኛ ተግባራችን! በያዝናቸው አመርቂ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎቻችን ታጅበን ለመጨረሻው ግብ ድልና ነፃነታችን እየታገልን እንገኛለን::
ግፈኞች ሆይ ጦራችሁም ወሬያችሁም አይፈታንም:: አላማችንንም ላፍታም ቢሆን አያደናቅፈውም!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 7/2018 ዓ.ም
የአብይ አህመድ ሰራዊት እርስ በእርሱ የማይደማመጥ ፣ የአንድ ብሔር የበላይነት ያለበት ፣ ጀኔራሎች እና ኮሎኔሎች ከፍተኛ ዝርፊያ የሚፈጽሙበት ፣ ብሔራዊ ዓላማ የሌለው ፣ ደካማ ስነ ልቦና ያለው ፣ ለመበተን ቋፍ ላይ ያለ ሰራዊት ሆኗል ።
በፋኖ ታሪክ ይህ የትግል ዘመን ጠንካራ የአማራ ብሔርተኝነት የሚገነባበት ፣ ጠንካራ አመራር የሚፈጠርበት ፣ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል የሚገነባበት ፣ አማራነት እንደገና የሚታደስበት ዘመን ነው ።
በየትኛውም አካባቢ ፣ በየትኛውም የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ የአማራ ወጣት ወደ ፋኖ በመቀላቀል አብይ አህመድ በዱቤ እና በብድር የገዛውን መሳሪያ መታጠቅ አለበት ።
ድል ለጀግናው አማራ
ድል ለጀግናው ፋኖ
