ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
2 956
المشتركون
+424 ساعات
+147 أيام
+38830 أيام
أرشيف المشاركات
ፖከቲካችን ያልተጠቀመበት ሃብት ነው። ውድ የአማራ ህዝብ ሆይ አይዞህ በርታ!! እነዚህን ዘረፈጆች እናንበረክካቸዋለን። ውድ ኢትዮጲታውያን ወገኖቻችን ሆይ አይዟችሁ በርቱ። ከተባበርን ያናፋል እንጅ ቀሽም ጠላት ነው ያለን። እናንበረክከዋለን። በያለንበት እንነሳ። ይህን ፀረሰው ቡድን ከዙፋኑ ላይ እናንሳ። ጭቆና በካቴናም በምቾትም ይመጣልና ሳንዘናጋ በአንድ እንነሳ። ለሁሉም በሁሉም የሆነች፥ በበጎ ታሪኳና እሴቶቿ ላይ የቆመች ነፃና ደስተኛ ምድር እንፍጠር።እጣፋንታችን እጃችን ላይ ነው ያለው። ሁሉም የራሱ ሙሴ ራሱ ነው። እንበርታ!እንነሳ! እምቢ እንበል-እምቢተኝነት ታንክ አልቦ ውጊያ ነው።ስለዚህ በአንድ እምቢ እንበል! ድል ለአማራ ህዝብ! ክፋት ለማንም፥ በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥ አዲስ ተስፋ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ሞት ለአብይ አህመድ እና ቡድኑ! ግንቦት 23-2018 አም። 23/ዐ9/2018 ዓ.ም

ጤና ይስጥልኝ! እንዴት ሰነበታችሁ?እግዚ አብሄር ይመስገን እኔ ደህና ነኝ! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ከአንቡላንሶች በስተቀር የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ ካወጀ ዛሬ ግንቦት 23/2018 አም ሶስተኛ ቀኑ ላይ እንገኛለን።በየአቅጣጫው ያለ ህዝባችንና መላው የፋኖ ሰራዊት ይህንን መመሪያ አጠናክሮና ተጠናክሮ እንዲያስከብር ገና መልእክቴን ስጀምር አደራ ለማለት እወዳለሁ። ተስፋ የቆረጠው ዘርና ሃገር አጥፊ ጠላት ያዘጋጀው ምርጫ ይሉት እቃ እቃ ጨዋታ  ለአለም ይታይ፥ ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ድራማውን በመፀየፍና ፥ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለይ የድራማው እለት  ጠላት ያቀደው ሽብር ህዝባችንን አደጋ ላይ እንዳይጥል የእንቅስቃሴ ገደቡ አስፈላጊ ነበር። አውጀነዋል፥ ሙሉ በሙሉ ተተግብሯል። እስከመጨረሻው ጥብቅ ክትትል ይደረግበታል። ካርድ አላወጣም ስላሉ ብቻ በአደባባይ  የተገደሉና የተሰቀሉ  ወገኖች በጣም ብዙ ናቸው። ለገበያ በሄዱበት እጃቸው ተይዞ ካርድ ተሰጠው አንዳች አሮጌ አቁማዳ ውስጥ እንዲጨምሩ ተደርጎ መረጣችሁ  የተባሉ ወገኖች በብዙ ሽህዎች ናቸው። በዴሞክራሲና በምርጫ ስርአት ታሪክ ውስጥ እንደዚህ አይነት ቅሌት በየትኛውም አህጉር ታይቶ አይታወቅም።እንደዚህ አይነት አሳፋሪ ነገር በመንግስታት ታሪክ ውስጥ አልተመዘገበም።የአብይ ዘመን የሰው ልጅ አይቷቸው የማያውቁ ነውሮችና ጉዶች መገለጫ ዘመን ሆኗል።ሰውዬውም ጉድ፥ ስብስቡም ጉድ፥ ድርጊታቸውም ጉዶች ናቸው። ቀን መቁጠር ካልሆነ በስተቀረ በካድሬ እጅ እየፈረመና ምልክት እያደረገ ኮሮጆ ሞልቶ ካስቀመጠ አንድ ወር አልፎታልና አይኑን በፍልውሃ ታጥቦ አሸንፍሁ ማለቱ አይቀርም።ያም ሆኖ እንደ ህዝብ እስከመጨረሻው እምቢተኝነታችን ማሳየት ይገባናል ።ይህን ዘረፈጅ ስብስብ እምቢ ማለት ያስፈልጋል። በኛ በኩል፦ በአንድ እጃችን የድርጅታችን መዋቅር  እያስተካከልን በሌላ እጃችን ስትራቴጅካዊ የሆኑ ወታደራዊይና ፖለቲካዊ ስራዎችን በጥልቅ አቅደናል። ወደ ተግባርም እየገባን ነው።ግዙፍ ወታደራዊ፥ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን እያስመዘገብን ነው።በመጭዎቹ ወራት  ይለይልናል። ህዝባችን ለዚህ ይዘጋጅ። ከጥይት በላይ ፍርሃት በየቀኑ ደጋግሞ ይገድላል። ይህ ትውልድ ከአንድ መራራ ሃቅ ፊት ቆሟል፦ ወይ ህልውናውን ወይ ጥፋቱን ይመርጣል። ህዝባችንና ቀያችን የሃያላን ሃገራት ድሮንና የዘመናዊ መድፎች የመግደል አቅም መሞከሪያ ሆኗል። ይህ የመጨረሻው ምእራፍ ነውና ሁሉም ይዘጋጅ።ሁሉም አማራና ኢትዮጲያዊ በእጁ ያለውን ሁሉ ወደጠላት ሊወረውር የሚገባው ወቅት ላይ ነን።ብዙ ጊዜ ህዝብ በእጁ ያለውን አቅም በውል ስለማይረዳ ወይንም እንዳይረዳ ስለሚደረግ የአብይ አይነት ጭራቆች ተጨማሪ የመግደያ እድሜ ያገኛሉ።ከፈጣሪ በታች ትልቁ ሃይል ያለው ህዝብ መዳፍ ላይ ነው። አምባገነኖች በቁጣ ያልተጨበጡ የህዝብ መዳፎች ላይ  ይፋፋሉ።በኛና በነፃነታችን መካከል ያለው ግድግዳ ፍርሃትና ጥርጣሬ ነው። የደፋር ጭቁን የለም።ቀጥ ብለን እንሂድበት የፍርሃት ግድግዳው ይወድቃል። ህልውናችን ይረጋገጣል፥ ሃገርና ባንዴራም ያርፋል። ወታደራዊ ስራችን ዋናው ስራችን ነው።ስትራቴጅካዊ ጉዟችን ለማሳለጥ  ማዘጋጀት ያለብንን አዘጋጅተን ጨርሰን የማሟሟቂያ እርምጃ ውስጥ ነን። የፖለቲካ፥ የህዝብ ግንኙነት፥ የፕሮፓጋንዳና የዲፕሎማሲ ስራችንም እንደዚሁ መልክ እየያዘ ነው። ዲያስፖራው ውስጥ ያለውን ግዙፍ አቅም ለመጠቀም የሚሰሩ ስራዎችም በሚቀጥሉት ወራት ከሚከወኑ ዋና ዋና ትኩረቶቻችን መካከል ይሆናሉ። በአንድ መቆም ዘመን የወለደው ግዴታ ነው። ያለበለዚያ በየተራ መጥፋት ዘመን ያመጣው እጣፋንታ ይሆናል። በሃገርና በቀጠና ደረጃም የዛሬ መቀራረብ ለነገ አብሮነትም ዋስትና ነው። እኛ ማንም ርእዮተአለም ፅፎ ሰጦን ትግል አልጀመርንም። አንድ መስመር ሃሳብ፥ አንድ አንቀፅ ርእዮት ከማንም አልተዋስንም።በራሳችን መስመር በራሳችን መንገድ አቢዮት አስነስተን እዚህ ደርሰናል።ለህባችን የሚበጀውን ነገርና የትግላችን ቀይ መስመሮች ጠንቅቀን እናውቃለን፥ ከአላማችን ፈቅ ሳንል በብልሃት  እንጓዛለን።አንዲት ግራም ጥቅማችን አሳልፈን አንሰጥም፥ የሰውም አነካም።በዙሪያችን ከተገኘ ጤዛም ብትሆን ልሶ ግን አቅም መፍጠር ያስፈልጋል። በተረፈ ከሌሎች መንግስታትና የፖለቲካ ሃይሎች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ግዴታም ጭምር ነው።ምክንያቱም ነገ መንግስት ነንና። የቀጠናውን ሃይሎች ነክሶ ጨርሶ ብቻውን የቆመ ሰውና ስብስብ ከማን ጋር መቆም እንዳለብን ሊነግርን አይችልም። አንድ ሊያጠፋህ ሲያደባ ኖሮ ምቹ ጊዜ ያገኘ መስሎት በይፋ ባደባባይ ሊገልህ ለአለም ነገሮ የመጣ ሰው እንዴት ከከበደና ከአለሙ ጋር ቁምም አትቁምም ይልሃል?ምን አገባው? የአማራ ብሄራዊ የህልውና ትግል ለሌሎች ወገኖች የተስፋ እንጅ የስጋት ምንጭ አይሆንም። አማራ ብቻውን ታግሎ ማሸነፍ ይችላል፥ የአማራ ብቻ ሃገረመንግስት መፍጠር ግን አይችልም። አይገባምም።ምክንያቱም ኢትዮጲያ የልዩ ልዩ ወገኖች ሃገር ናትና።ስለዚህ አላማውንና ጥቅሙን ከማይፃረሩ ሃይሎች ጋር የሚያደርገው ትብብር ፍፁም ጤናማ ነው።ይቀጥልበታል። እኛ  በፍፁም ወንድማማችነትና በጊዜ የለንም መንፈስ ስራ ላይ ነው ያለነው። የፖሊት ቢሮው ተከታታይ ስብሰባዎችን እያደረገ አቅጣጫ እየሰጠ ነው። ለልዩ ልዩ ጉዳዮች ኮሚቴዎች ተዋቅረው ስራ እየሰሩ ነው።አፋብን ስራ ላይ ነው።  ከዚህም ከዚያም የሚሰሙ ድምፆች ደግሞ ይኖራሉ፥ ትግሉ እስካለ ይቀጥላሉ። የሚጠቅሙትን እየወሰዱ የማይጠቅሙትን እየተውም በቁርጠኝነት እየታገሉና እያስተካከሉም መጓዝ የኛ ድርሻ ነው። አንድ ድርጅት አቁመናል። የትም አቅጣጫ ጉንፋን ቢገባ በተቋሙ ይታከማል። ጎንደር ታሞ ጤና የሚያድር አማራ የለም።ጎጃም ጎብጦ ቀና የሚል ትግል አይኖርም። ስለሆነም ኮሽ ሲል ድርጅቱ ፈጥኖ ደርሶ ያስተካክላል።አንዳንድ ተፈጥሯዊ የትግሉ ሂደት ወይንም ድክመቶቻችን የፈጠሯቸው ችግሮች ብቅ ባሉ ቁጥር ጠላት የምንወድቅ መስሎት የአፍታ  የቀበሮ ደስታ ውስጥ ይገባል። በደምና በአጥንት የተሰራ፥ በሰቆቃ የተጠራ አቢዮት ያለመው ቦታ ሳይደርስ አይወድቅም፥ አይቆምም።ቁርጣችሁን እወቁት። ይህን ትግል እኛ ሰዎቹ ብንተወው በአቢዮቱ የጋለው ምድር ያበቀላቸው ዛፎች የሚያስቀጥሉትና ዳር የሚያደርሱት  ያክል ማሸነፋችን ላይ ተጠራጥረን አናውቅም። የታሪክ ምህረት አልባ ጉዞ ያስነሳውን ማእበል የሚያቆመው ድል የተባለ መዳረሻ ብቻ ነው።ችግሮች ይፈጠራሉ፥ይፈታሉ። እንደገና ይፈጠራሉ፥ እንደገና ይፈታሉ። ይፈጠራሉ ይፈታሉ።በዚህ መልኩ ወደፊት ይጓዟል። ይህ የትግል ተፈጥሮ፥ የህይወት ቀመር ነው። 👉በየደረጃው ያለን መሪዎች እንበርታ።አይናችን ግባችን ላይ ለቅፅበትም አንንቀል።ጓደኛችን ዋርካው ምሬ ወዳጆ እንደሚለው "መሪና መንገድ አንድ ናቸው።አላፊ አግዳሚው ይረግጣቸዋል"።ይህ የመሪ ወጉ፥ የመሪነት ደሞዛችን ነውና በፈገግታ ተቀብለነው በኪሳችን መተነው ወደፊት መጓዝ ነው።"ትልቁ ምላሽ ምንም አለመመለስ ነው" እንዲሉ ጫጫታና ግርግር ትኩረታችን ሳይሰርቀን፥ ለሁሉም ነገር ምላሽ መስጠት ሳይገደን ወደፊት መጓዝ ነው። ፅናት ከስናይፐራችን በላይ የድላችን በር የሚከፍት ቁልፍ ነው።በጎ ምኞቶች ጫፍ የሚያደርስ የራሳቼው እግዜር አላቼው። በጎ ምኞታችን ላይ ሃቀኛ ጥረት ከጨመርን ድል ያለበት ሃገር ካፍንጫን ይቀርባል።ይህ  የመሳሪያና የቅንነት አቢዮት ነው።ቅን እንሁን። ቅንነት የማያከስር ፖከቲካችን ያልተጠቀመበት ሃብት ነው።

Baye Desta Per በደብረ ማርቆስ ከተማ የወንበዴው ስርዓት በግዳጅ የሰጠውን የውሸት ምርጫ ካርድ ቤት ለቤት እየሰበሰበ ይገኛል። በዛሬው እለት በተፈፀመው ኦፕሬሽን የወንደበዴዎች የምርጫ ጣቢያ
+5
Baye Desta Per በደብረ ማርቆስ ከተማ የወንበዴው ስርዓት በግዳጅ የሰጠውን የውሸት ምርጫ ካርድ ቤት ለቤት እየሰበሰበ ይገኛል። በዛሬው እለት በተፈፀመው ኦፕሬሽን የወንደበዴዎች የምርጫ ጣቢያ ከተቃጠለ በኋላ በከተማዋ ያሉ ባጆች እና ታክሲዎች እንዳይንቀሳቀሱ ታግደዋል። የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ጭር እንዳሉ ናቸው።

አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ዋሲል ክ/ጦር እና 71ኛ ሳጅን አባ ናደው ክፍለጦር በጋራ በመሆን በዘመቻ አንሻ ሰይድ በአደርጉት የምሽት ኦፕሬሽን በብልፅግናው ወንበር አሰጠባቂ ሰራዊት ላይ በልጓማ ከተማና በደገር ከተማ ዙሪያ እርምጃ ወስደዋል። ግንቦት 22/2018 ዓ/ም በደገር  ከተማ ዙሪያ ላይ በሜካናይዝድ የታገዘ ማለትም በሞርተር 82፣በሞርተር 120 እና በዙ 23 እየደበደበ የተሰማራው የጥቁር ናዚው ፤አስመሳዩ እና ከሀዲው   አብይ አህመድ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂው ሰራዊት ላይ ጀግናው የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ  ወደ አለበት አካባቢ ለመንቀሳቀስ ሙከራ ቢያደርግም የሁለቱ ክፍለ ጦር አናብስቶች የምኒልክ ልጆች በሁሉ ነገር ፈጣሪ በአደለው ጀግንነት ከወታደራዊ ጠበብትነት በአደለው ራስ አርበኛ ፊታውራሪ ድርሳን ብርሃኔ ስብሳቢነት የሚመራው  አፋብን የምኒልክ ዕዝ ልጆች  እጅ የሚጋረፍ  የጋለ ብረት ሆኖበት እንደ አባቶቻቸው ተማርከው ወደ ላይኛው ቤት የሚሸኙት ተሸኝተው እነ ውርደት ብርቁ ተዋርደው ወደ መጡበት በውርደት ተመልሰዋል።ምክንያቱም የአማራ ህዝብ ታሪክ ከታሪክ ድርሳናት በቅንጭቡ  ሲዳሰስ እንኳን ለዚህ ልፍስፍስ የታሪክ አተላ ሀገር ሻጭ  ለሀገር መሪነት አይደለም ራሱን መግዛት የማይችል የሁሉ ነገር ድኩማን ድንክ አይደለም የአማራ ህዝብ በዚያን ዘመን ዘመናዊ መሳሪያ ባልነበረበት ለነጮችም በሰማይ ፤በምድር ጥይት እንደ በረዶ ሲፈስባቸው አገራቸውን የያላስደፈሩ ለሀገረ ግንባታ ጉልህ ሚና የተጫወቱ ሀገራቸውን ለባንዳ አሳልፈው ያልሰጡ ጀግና የባለ ታሪክ ልጆች እጃቸው ለአፍታም ያልዛለ ኩሩ ጀግና ህዝብ መሆኑ አለም ያወቀው ፅሀይ የሞቀው እውነታ ነው። ይኸን እውነታ በወጉና በአግባቡ ያልተረዳ በተዛባ የሀሰት ትርክት የሰከረው ከሀዲውና አሰመሳዩ የፓለቲካው ድንኩ አብይ አህመድ የሀገር ሻጩ ወንበር አሰጠባቂው ግንቦት  23/2018 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 እስከ  ጥዋቱ 2:00 ሠዓት በተደረገው ኦፕሬሽን በልጓማ ከተማ የብልፅግናን ምርጫ እናስመርጣለን ብለው በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ ጀብደኗቹ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል። በተመሳሳይ ጀግናው የአማራ አለኝታ የአማራ ፋኖ ሰራዊታችን የአውደ ውጊያ አድማሱን አስፋፍቶ በከለላ ወረዳ ዙሪያ እያካሄደ ያለው የተቀናጁ ውጊያ አይነቱ ለየት ያለ ድል እየተጎናፅፈ ሲሆን በርካታ የሚኒሻ አባልና የመከላከያ ሠራዊት  ቁስለኛና አሰክሬን በአንቡላንስ ወደ ደሴ ሆስፒታል እያመላለሰ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ33ኛ ዋሲል  ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል። ህልዉናችን በተባበር ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ  ዕዝ ሕዝብ ግንኘነት መምሪያ ግንቦት 23/2018 ዓ/ም

በደብረ ማርቆስ ከተማ ንጉስ ተክለሃይማኖት ክ/ከተማ ቀበሌ 10 ጎተራ አካባቢ የነበረው የወንበዴው ም*ርጫ ማስፈፀሚያ ቢሮ ከሁለት ሚኒሻዎች ጋር በቦምብ ተቃጥሏል።       (206ኛ ኮር) ግንቦት 23/2018 ዓ.ም ======================================= የ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ከሌሊቱ 8:00 በደብረ ማርቆስ ከተማ ንጉስ ተክለሃይማኖት ክ/ከተማ ቀበሌ 10 የወንበዴዎች ም*ርጫ ማስፈፀሚያ ቢሮ ላይ በፈፀመው የቦምብ ጥቃት ሁለት ሚኒሻዎች ሲደመሰሱ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ ሰነዶችና መዝገቦች መቃጠላቸው ተረጋግጧል። በዚህ የተደናገጠው የብልፅግና ስርዓት በደብረ ማርቆስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ክልከላ አድርጓል። የባጃጅ ሹፌሮች፣ ወጣቶች እና ነጋዴዎችን እያፈሰ ወደ ማጎሪያ ጣቢያም እየወሰዳቸው ነው። በተየያዘም በትናትናው ዕለት አመሻሽ ሉማሜ ከተማ በመውጣት የአዋባል ወረዳ አስተዳዳሪ ብዙነህ ይዞ ሲንቀሳቀስ በነበረው ፓትሮል ላይ 34ኛ ክ/ጦር የጎደና አካባቢ በተፈፀመው የደፈጣ ጥቃት አጃቢው ሶስት አድማ ብተና አባላት ሲደመሰሱ የአስተዳዳሪው አጃቢ ከባድ ቁስለኛ ሁኗል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በዘመቻ አንሻ ሠይድ አዊ ዞን ዚገም ወረዳ ጎሃ ቀበሌ መሽጎ በነበረ የሚሊሻ ስብስብ ላይ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109 ኮር 88ኛ ክ/ጦር ድል ተቀዳጀቷል! በትናንትናው ዕለት ግንቦት 22/2018 ዓ.ም በአዊ አዮ ጓጉሳ ወረዳ አምበላ ቀበሌ ማህበረሰብን ለማወያየት ወደ ቀበሌዋ የተንቀሳቀሰ የአብይ አህመድን ጨፍ#ጫፊ ሠራዊት እና ዚገም ወረዳ ጎሃ ቀበሌ የመሸገን የአገዛዙ ሚሊሽ ስብስብና አስተዳድራዊ መዋቅር ላይ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109 ኮር 88ኛ ክ/ጦር አመርቂ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሟል። አምበላ ቀበሌ የገባው የአገዛዙ ጨፍ#ጫ#ፊ ስብስብ የሰበሰበውን ህዝብ በትኖ እግሩ እስኪላጥ ፈርጥጦ ወደ መጣበት አዘና ተመልሷል። ዚገም ወረዳ ጎሃ ቀበሌ የነበረው የሚሊሻ ስብስብ ሙትና ቁስለኛ ሲሆን የብልፅግና አስተዳድርዊ መዋቅር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል። #ጨፍ#ጫፊ ቡድኑ በርካታ አባላቱን ሙትና፣ ቁስለኛ የሆኑበት ሲሆን 5 ክላሽ ከ720 ተተኳሽ ጋር እና  2 አብራራው በክንደ ነበሎባሎቹ 88ኛ ክ/ጦር ተማርኳል። ግንቦት 06/2018 ዓ.ም አምበላ ቀበሌ ያለው የጠላት አስተዳድርን በ88ኛ ክ/ጦር መደምሰሱ የሚታወስ ነው። ምንጭ፦በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር  ህዝብ ግንኙነት ክፍል! ዘመቻ አይሻ ሰይድ!

የፋኖ ኃይላችን በበርካታ የሸዋ አካባቢዎች በወራሪው ኃይል ላይ ድል  ሲቀዳጁ በአንፃሩ ዙፋን ጠባቂው ወራሪ ኃይል እራሱን ለመከላከል በከባድ መሳሪያ ተራራዎችን እና የንፁሃን መንደሮችን ሲደበድብ ዋለ::      አ.ፋ.ብ.ን   ሽ/ጠ/ግ አሳምነው ዕዝ      የጨረባ ምርጫ  ለማስፈፀም መነሻውን  ከግሼ  እራቤል  ከተማ  አድርጎ  ወደ ጦርመሳያና  ሸበቶ የተቀሳቀሰው የ105ኛ   ኩማንዶ  ሰራዊት ሸበቶ፥ጦርመሳያና  ጫጋ   ላይ ከሻለቆች የተውጣጡ አካልና   ቃኝዎች   ጫጋ በር  ከሚባለው  ቦታ ላይ ፊት ለፊት  በመግጠም  የብልፅግና  ወራሪ ሀይል የስልጣን  ማራዘሚያ  የጨረባ  ምርጫ  አስመራጭ  ግዞተኛ ስብስብ  ላይ  መብረቃዊ ጥቃት በመሰዘር አይቀጡ ቅጣት  በመቀጣት  ሙትና  ቁስለኛ  አድርገውታል። ጫጋበር  የገባው  ሀይል  ከባድ ጉዳት  በማስተናገዱ  በጦር  መሳያ  ጀበራ  ሜዳ  ሰፍሮ የነበረውን  አንድ  ሻለቃ  ወደ ጫጋበር  ተጫማሪ  አድርጎ  በማስገባት  ሙትና  ቁስለኛውን  ለማውጣት  ቦታውን  አስፍቶ በመያዝ የሞት ሽረት ውጊያ  እያደረገ  ቢሆንም  የክፍለጦሩ  አናብስቶች  ክንድ  የማይቀመስ ሆኖ አምሽቷል ። ግዛቱን ለማስፋት ለሊት  23/09/2018 ዓ/ም ወደ በሽሃደብስ የተንቀሳቀሰው የጠላት ሃይል በልዩ ደፈጣ ሙትና ቁስለኛው የተዝረከረከ ሲሆን ይህ ዜና እስከተሰራበት ጊዜ ደረስ ውጊያው እደቀጠለ ነው::   በሌላ ዜና በከሰም ፪ኛ ኮር በኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦርና በነበልባል ክፍለ ጦር ቀጠና ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር የሚደረገው አውደ ውጊያ አሥደማሚ ድል  መመዝገቡን የደረሰን የግንባር መረጃችን ያመላክታል::      የአገዛዙ ሰራዊት መነሻውን ከሀገረማርያም ከተማ ሾላ 01 ቀበሌ መዳረሻውን  ወደ ጎርፎ ቀበሌ በማድረግ ያቀና ሲሆን ከኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር የፋኖ ሻለቃዎች በጥምረጥ ከለሊቱ 11:30 ጀምሮ እሰከ ቀን 8:30 ሰዓት የቀጠለ አውደ ውጊያ በማካሄድ ላይ ሲሆን በዚህም ውጊያ ፋኖ የጠላት ኃይልን ከበባ ውሥጥ በማሥገባት በጎርፎ ቀበሌ: በገበሬሸንጎና በወለሌ ሚካኤል በተባሉ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የማጥቃት ሥልት በመጠቀም ጠላትን ላይ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ችሏል::  በፋኖ ከፍተኛ ምት  ጉዳት የደረሰበት የአገዛዙ ኃይል ከሀገረ ማርያም ተጨማሪ 2 አይሱዚ ሀይል በማሥገባት እና የተጎዳበትን ሰራዊት በአምቡላን ወደ ሀገረማርያም ጤና ጣቢያ ሲያመላልሥ አርፍዷል።   በዚህም ውጊያን መቀጠል ያቃተው የአብይ ወታደር ሙትና ቁሥለኛውን በመሰብሰብ  ወደ ኋላ አፈግፎጎ ዙ_23 እና ሞርተር በመጠቀም በርቀት አትምጡብኝ በሚል ፍርሃት 13 ጊዜ የሞርተር ቅንቡላ ወደ ንፁሃን መንደር እና ተራሮች ላይ በደመ ነፍስ የወረወረ ሲሆን አውደ ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ነው።   በመንጃር ሸንኮራ በነበልባል ክፍለ ጦር ቀጠና በሁለት አቅጣጫ ወደ  ተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች የተንቀሳቀሰው የጠላት ሀይል በነበልባል ክፍለ ጦር  የተለያዩ ሻለቃዎች በተቀናጀ ጥቃት ጠላት መቋቋም አቅቶት ከአቅሙ በላይ መሆኑን ሲያውቅ ያሰበው ሳያሳካ በፍጥነት ወደኋላ በመመለስ አረርቲ ከተማ ገብቶ እራሱን ከውርደት ታዲያጕል:: ክብር  ለትግሉ  ሰማዕታት ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !! አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 23/2018 ዓ/ም

የድል ዜና!!! ሰራዊቱም ተመታ ምርጫውም ቅጥ አጣ ከትናንት ማለትም ግንቦት 22/2018 ጀምሮ በተደረገ አውደውጊያ በሽፋ ከተማና አቅራቢያ ቦታዎች አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ)  ኮር ካራማራ ክ/ር እና ኦሜድላ ክ/ር ዳግማዊ ቴዎድሮስ ብርጌድ በጣምራ በጠላት ሀይል ከፍተኛ የሆነ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራን ከማድረስ ባሻገር የጨበራ ምርጫውን ሙሉ በሙሉ ቀጠናው ላይ እንዲቋረጥ ሆኗል። ነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች የአገዛዙን የቅዠት የምረጡኝ ህልም በዜሮ ብዜት በጣምራ በተሰራ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ውርደትን ተከናንቦ ሙሉ ቀኑን እስከ ምሽት ድረስ መውጫ መግቢያ አጦ ሙትና አስከሬኑን እያዝረከረከ ህዝብን ተገን ወዳደረገበት ወደ ሽንፋና ወደ ዱባባ ከተማ ፈርጥጦ ገብቷል። እንዲሁም በአሁኑ ስአት ሽንፋ ጤና ጣቢያ ንፁሀን ታካሚዎችን ሙሉ በሙሉ በማስወጣት የአገዛዙ ቁስለኛ ሰራዊት እየታከመበት ይገኛል ሲል የካራማራና የኦሜድላ ክ/ር የህ/ግ አርበኛ ቴዎድሮስ ይግዛው እና አርበኛው አስቻለው አለባቸው መረጃውን አድርሰውናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሽንፋ ከተማ ከቅርብ እርቀት ጥሎት የሄደውን የጠላት ከፍተኛ ቁጥር ያለው አስክሬን የአካባቢው ነዋሪ አርሶአደር በዛሬው እለት ግንቦት 23/2018 በየስርቻው የወደቀውን በማንሳት የቀበሩት ሲሆን አስክሬኑን መሸከፍ ያቃተው የምርኮኛው የብርሀኑ ጁላ ጦር በንፁሀን የገጠር ቤቶች ላይ የከባድ መሳሪ ጥቃት አድርሷል በተለይ አፍኳንቻ የተባለች ጎጥ ላይ ያሉ መንደሮችን በዙ-23 ሙሉ በሙሉ አውድሟቸዋል። የተመዘገበ ድል: አንድ አስር ጎማ ሬሽን፣ ተተኳሽ እና ሰራዊት እንደያዘ ጋይቷል ከአስር ጎማው ውጭ ከ63 በላይ የተደመሰሰ ሲሆን ከ39 በላይ ከፍተኛ ቁስለኛ ሆኗል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ ክፍል       ግንቦት 23/2018

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የተሰጠ ጥብቅ መመሪያ በአስገዳጅነት ለምርጫ ለተመዘገባችሁ አማራውያን ወገኖቻችን፤ አምባገንኑ የብልፅግና አገዛዝ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን በመፍራት፣ በየቀበሌውና በየመንደሩ ካድሬዎቹንና ታጣቂዎቹን በማሰማራት የ"ምርጫ ምዝገባ" በግድ እና በማስፈራራት መፈፀሙን እንረዳለን። ነገር ግን እውነታው፤ ምርጫው ተካሄደ አልተካሄደ ብልፅግና ራሱን መርጦ የጨረሰ መሆኑ ነው! ግንቦት 24 ቀንን የፈለገው ለዓለም ሕዝብ የውሸት ሕጋዊነትና መስፈርት ያሟላ መስሎ ለመታየት ብቻ ነው። ስለሆነም፣ የምርጫ ካርድ የያዛችሁ ወገኖቻችን የገዥው አካል የድራማ መሣሪያ እንዳትሆኑና ወደተዘጋጁት የምርጫ ጣቢያዎች እንዳትሄዱ እያሳሰብን፣ የሚከተሉትን መመሪያዎች በአስቸኳይ ተግባራዊ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፦ 1. ለጠቅላላው ሕዝባችን፦ በዕለቱ (ግንቦት 24) ማንኛውም ዜጋ ለድራማ ወደተዘጋጁት የምርጫ ጣቢያዎች ባለመሄድ፣ ለህልውናው መከበር ያለውን ፅኑ አቋም በተግባር እንዲያረጋግጥ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 2. ለሕዝብ አገልግሎት ተቋማት ሠራተኞች፦ ሥርዓቱ በአስገዳጅነትና በጥቅማጥቅም የራሱ መጠቀሚያ ሊያደርጋችሁ እንደሚፈልግ እናውቃለን። በመሆኑም ከመደበኛ የሥራ ጫናና ከሥርዓቱ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ራሳችሁን እንድታቅቡ፣ መላው የመንግሥት ሠራተኛ ከእሁድ ጀምሮ በቤቱ ቁጭ በማለትና ለጥሪዎች ምላሽ ባለመስጠት የሕዝብ ወገንተኝነቱን በተግባር እንዲያሳይ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። 1. ለአስገዳጅ ካድሬዎችና አጎብዳጅ ታጣቂዎች የተሰጠ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ፦ ሕዝባችንን እያስፈራራችሁ የጥፋት የምርጫ ምዝገባ የምታድሉና በዕለቱ አስገድዳችሁ ለማስመረጥ ያቀዳችሁ የአገር ውስጥ ባንዳዎች ድርጊታችሁን በአስቸኳይ አቁሙ! የእያንዳንዱ አስገዳጅ ስም ዝርዝር እየተመዘገበና እየተጠናቀቀ መሆኑን በውል እወቁት! ክብር ለትግሉ ሰማዕታት! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

የስቦ ማስከዳት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል የጠላት ከምፕ እየፈራረሰ ነው ========================== ግንቦት 23/2018 ዓ.ም ህፃናትን በግዳጅ እያፈሰ ለውትድረና እየማገደ ያለው የአብይ
+2
የስቦ ማስከዳት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል የጠላት ከምፕ እየፈራረሰ ነው ========================== ግንቦት 23/2018 ዓ.ም ህፃናትን በግዳጅ እያፈሰ ለውትድረና እየማገደ ያለው የአብይ ስርአትን በመተው ሰራዊቱ ከመርጦ ለማርያም እና ከድጎ ፅዮን በመውጣት ወደ 201ኛ ኮር 74ኛ እና 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። 1.ተፈራ አድማስ .........አድማ በትን  2.አለቃ ተሜ ............አድማ በትን 3.አንማው ሀብቴ...........ሚሊሻ 4.ደረጃው ገደፋው....... .ፓራኮማንዶ 5.እውነቴ በቃሉ..........ፓራኮማንዶ 6.ስማቸው የኔአለም.........ፓራኮማንዶ ከዚህ በሗላ ምንም አይነት ሰራዊት የመታገል ፍላጎት የለውም እኛም የገባነው የትጥቅ ችግር ስላለብን ነው በማለት ሀሳባቸውን የገለፁ ሲሆን በክፍለጦር አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 2ዐ1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በአማራ ክልል የከተሞች ውጥረት እና የደህንነት ስጋት አሳሳቢ ሆኗል ​ወልዲያ እና ጎንደር — በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተባባሰ በመጣው ግጭት እና ውጥረት ሳቢያ የሲቪል ነዋሪዎች እና የን
+3
በአማራ ክልል የከተሞች ውጥረት እና የደህንነት ስጋት አሳሳቢ ሆኗልወልዲያ እና ጎንደር — በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተባባሰ በመጣው ግጭት እና ውጥረት ሳቢያ የሲቪል ነዋሪዎች እና የንብረት ደህንነት ላይ ስጋት መደቀኑ ተሰማ። ​በወልዲያ ከተማ ጎንደር በር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ፣ የብልጽግና ፓርቲ (ብአዴን) የጸጥታ ኃይሎች በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸማቸው ተዘግቧል። ጥቃቱ የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ​በተያያዘም፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት ምሽት በጋራ ሆነው የእግር ኳስ ጨዋታ በመመልከት ላይ እያሉ በደረሰ የቦምብ ጥቃት፣ በበርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል። ​የአካባቢው ነዋሪዎች እና የህዝብ ተወካዮች እንደሚሉት፣ ገዢው ፓርቲ በተለይም ፋኖ በምርጫ ሂደት ላይ ያወጣውን መመሪያ ህዝቡ በስፋት እየተገበረ መሆኑን ተከትሎ፣ ስርዓቱ በየከተማው እየወሰደ ያለው እርምጃ የበቀል እና የሽብር መገለጫ ነው ሲሉ ይከሳሉ። ​በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ከተሞች በጸጥታ ኃይሎች እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች መላውን ህዝብ ለከፍተኛ ስጋት እየዳረጉ ይገኛሉ። በመሆኑም፣ በየአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ ተመሳሳይ የሽብር ተግባራትን ከግምት በማስገባት፣ ህዝቡ በንቃት እንዲጠነቀቅ እና አስፈላጊውን የደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

አስቸኳይ ከአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም የተሠጠ መግለጫ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? በትብብር ስም የተሰባሰበ ባንዳ በምርጫ ታዛቢነት ሽፋን በሚሰራ ሸፍጥ የሚቆም ትግል ዛሬም የለም ነገም አይኖርም! አማራ ብልሃትንና አርቆ አሳቢነትን እንደ ምኒልክ የወረሰ፣ ደግነትን እንዲሁም ሀገር ወዳድነትን ደግሞ እንደ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ የተላበሰ፣ እንደ ዐፄ ቴዎድሮስ የተንቀለቀለ የአንድነት ስሜት ያለው፣ እንደ ገብርዬ ታማኝ፣ ኩሩ ጨዋ ሰውና ሀገር ወዳድ ሕዝብ ነው። ይኸን ታላቅ ሕዝብ ያለበትን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ የተቋቋመው የአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም መነሻችን የአማራ ሕዝብ ችግር መዳረሻችን የአማራ ሕዝብ ታላቅነት ራዕይና ተልዕኮ አድርጓ ፈተናን እየፈተነ በእሳትና በሞት ጥላ ስር ሆኖ ሁለተናዊ ትግል እያደረገ ይገኛል። ይሁን እንጅ ለአማራ ጥፋት የተመሰረተው የጨርቦሌ ፖለቲካ ! አማራ "ታላቅ ነበርን ታላቅም እንሆናለን"  ህልም ለማጨገፍ በትብብር ስር የተሰባሰቡ የፓለቲካ ቁማርተኞች በባህርዳር : አዲስ አበባ:ቻግኒ:እጅባራና ሌሎች ከተሞች በሲቪክ ማሕበራችን ስም ልቅምቃሚ ገንዘብ ለማግበስበስ የትብብሩ ታዛቢ እየመረጡ እንደሚገኙ በማስረጃ ደርሰንበታል። ይህ ባንድነት እንዲቆም ጥረት ብናደርግም ከዚህ እኩይ ተግባር አልተቆጠቡም ። ባንዳ ማለት «ከሃዲ»፣ «አገር ሸክም» ወይም ለገዛ አገሩና ወገኑ ሳይሆን ለጠላት የሚያግዝ እና የሚሰልል ሰው ማለት ነው ይህ ቃል በዋነኝነት ጥቅም ላይ የዋለው በኢትዮጵያ የጣሊያን ወረራ ዘመን (1928-1934) ሲሆን፤ በወቅቱ ለወራሪው ኃይል አድረው አገራቸውን የሸጡና ወገናቸውን ያስጨፈጨፉ ግለሰቦችን ለመግለጽ ይጠቅም ነበር ዛሬም በፓርቲ ስም በባንድነት ተግባር የተሰማሩ ሆድ አደሮች የሕዝባችን የጀርባ ቁስል ሁነዋል። የባንዳ መገለጫዎች በአማርኛ ቋንቋ የባንዳነት ባህሪ ተብለው የሚታወቁት፡ ክህደት፡ ለጥቅም ወይም ለግል ፍላጎት ሲባል አገርን ለጠላት አሳልፎ መስጠት ቅጥረኛነት፡ የውጭ ኃይሎች ወይም የጠላት አላማ አስፈጻሚ መሆን የውስጥ ሰላይነት፡ የጠላት መንገድ መሪና የስንቅ አቅራቢ መሆን ከላይ የተጠቀሱ መገለጫን ስምና ልብስ ያደረጉ ፍርፋሪ ለቃሚዎች በምርጫ ስም የግል ኪሳቸውን ለማድለብ የሚፈፅሙት ተግባር መላው ሕዝቡ እንዲውቀው ታላቅ ትግል የምናደርግ መሆኑን ከወዲሁ በማሳወቅ የአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም በፖለቲካ ፓርቲም ሆነ በሲቢክ ማሕበር ስም በምርጫ ታዛቢነትም ሆነ ምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የሌለው መሆኑን በማሳወቅ ከሁሉም ማስተዋል ይቅደም እያልን በ1960ዎቹ የስልጣን ጥመኝነት ጥላቻ የቅኝ ገዥ ፍላጎት አስፈፃሚ የኢትዮጵያን የወቅቱን የፖለቲካ አሰላለፍ ያልተረዱ የተዘበራረቀ የፖለቲካ አላማ ያላቸው እና በስሜት ያበዱ የጨርቦሌ ፖለቲካ የልጥ ፓርቲ ቅዥት ዛሬ  ነገም የሚቆም የአማራ ሕዝብ ትግል እንደሌለ በማሳወቅ ጭምር ነው። ታላቅ እንደነበርን ታላቅ እንሆናለን ግንቦት 23 /2018 ዓ.ም አማራ - ባህርዳር