ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 613
المشتركون
+1324 ساعات
+4187 أيام
+1 05630 أيام
أرشيف المشاركات
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማር ታዘዘ የፊስቡክ አካውንት ፒጁ ሪስክ ስላለው ከታች በአለው ሊንክ እየገባችሁ free meta በሉለት https://www.facebook.com/profile.php?id=61581657125998
የፋኖ አመራርና ሰራዊት ያለበትን ቀጠና አጠቃለሁ ብሎ የተንቀሳቀሰው የጁላ ሰራዊት ሁለት ዲሽቃ ተኳሾቹን አስደምስሶ አንድ ብሬን አስማርኮ ተመለሰ!
መጋቢት:-07/2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር አመራርና ሰራዊት ያለበትን ቀጠና አጠቃለሁ በማለት የተንቀሳቀሰው ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ዕዝ የብልፅግና ሰራዊት በዋግ፣ ላስታ፣ መቄትና ቡግና በሰፊው የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ጠላት ባላሰበውና ባልጠበቀው ሁኔታ ተመቶ ተመልሷል።
መጋቢት 05/2018 ዓ/ም መነሻውን ከላሊበላ በሹምሽሃ በሦስት አቅጣጫ ማለትም በእርፋ፣ በጉልበት ተራራ እና በሙጫ በረት ያደረገው የጠላት ኃይል 19ኛ ክፍለጦርን አጠቃለሁ በሚል በሌሊት የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ጠላት ባላሰበውና ባልጠበቀው የተቀጠቀጠ ሲሆን 10 ሲደመሰስበት ከ17 በላይ ቁስለኛውን በአምቡላንስ ይዞ ተመልሷል።
በዚህ አውደ ውጊያም ላስታ ወረዳ ገለሶት ቀበሌ ከመንገድ ዳር ቤቱ የሆነው አባት አርበኛ መልካሙ አበራ ጠላት ተሰልፎ ወደ ወገን ቀጠና እየመጣ መሆኑን ሲረዳ ከጣት ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ የወረረው ደሙ እንደ እቶን እሳት የተንቀለቀለው የአባቶቹ ልጅ አርበኛው መሳሪያውንና ትጥቁን አሟልቶ ብቻውን ቀድሞ ደፈጣና ምሽግ በመያዝ የገጠማቸው ሲሆን ስድስቱን እንደደመሰሰ ተኳሹ እንዳለቀበት እና ጠላት እንደደረሰበት ሲያውቅ አንዲት ፍሬ ጥይት ስትቀረው ለራሱ በመጠቀም ታላቅ ገድል፣ ለትውልድ የሚተላለፍ አኩሪ ታሪክ ሰርቶ ተሰውቷል።
መጋቢት 06/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ጠላት በሦስት አቅጣጫ ማለትም በድሐና አምደወርቅ ወደ ቆብ፣ ከአይና ቡግና በብርኮ ወደ ቆብ እንዲሁም በዶሮላባ ጎንደር በር ቅዱስ ሀርቬይ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ብርኮ ላይ በተደረገው ውጊያ 19ኛ ክፍለ ጦር በአምስት ቦታዎች ማለትም በምሳናው በር፣ በጭቃው፣ በቴሌው፣ በውርምሽና ብርኳኳ ላይ ማጥቃት የተደረገ ሲሆን ብርኮ እና ብርኳኳ ላይ ሁለት ድሽቃ ተኳሾችን ጨምሮ 27 የጠላት ሰራዊት ሲደመሰስ 14 ጥቁር ክላሽ ከነ ሙሉ ትጥቁ ተማርኳል።
በሌላ መረጃ 19ኛ ክፍለ ጦር አባት አርበኞች በድሐና አምደወርቅ የመጣውን የጠላት ኃይል ሲያርበደብዱት የዋሉ ሲሆን አንድ ብሬን፣ ስምንት ጥቁር ክላሽ ሲማርኩ ስምንት የጠላት ኃይልን ደምስሰዋል።
በመጨረሻም የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ደቡብ ዕዝ 204ኛ ኮር 38ኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑት አስር አለቃ ዮሐንስ ወንድሙና ም/አስር አለቃ ሙሐመድ ሰይድ ሁለት ጥቁር ክላሽ፣ስድስት ካዝና፣ ሁለት የደረት ትጥቅ፣ 420 የክላሽ ተተኳሽ፣ ስድስት የዕጅ ቦምብ በመያዝ 30ኛ ክፍለ ጦርን መጋቢት 07/2018 ዓ/ም ተቀላቅለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ መምህር ቢሆነኝ
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 7/2018 ዓ.ም
ጠላት ያሰለጠነው ፓራ ኮማንዶ ጦር አየተናደ የምረት አዋጅን በመጠቀም ዛሬም ፋኖን በመቀላቀል ላይ ናቸዉ ‼️⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰⛰
........መጋቢት 07/2018 ዓ.ም
እነ አረጋ ከበደ ለ45 ቀን አሰልጥነው አማራን ለማስጨፍጨፍ ተማምነው ያስቀመጡት ሚሊሻ ስብስብ ፓራኮማንዶ የተባለው ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም ነው እና ሃይል እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ በተለያየ መንገድ እየተገለፀ ሲሆን ዛሬም፦
1.እርጥባን የኔነህ....1 ኮርያ ክላሽ ከግንደወይን ከተማ
2.እንዳለው ጥላሁን.. 1 ኮርያ ክላሽ ከግንደወይን
3.ስላባት አዝመራው... 1 ኮርያ ክላሽ በመያዝ ከደ/ወርቅ የፓራኮማንዶ አባላት በመውጣት 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
"አኩሪ ታሪካችን በክንዳችን ይፃፋል!"
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
♦️የአፋብን በላይ እዝ ፋኖዎች በጓህላ ከፍተኛ ቦታዎች የጠላትን ኃይል በጥይት አረር ሲቆሉት መዋላቸው ተገለጸ።
ዛሬ መጋቢት 07/2018 ዓ.ም አፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮርና ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር አንድ ብርጌድ በጥምረት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በ4 የአውደ ውጊያ ግንባሮች ስቦ በማስገባት ቴክኒክ ዘው ብሎ የገባውን የጠላት ኃይል የጥይት ዶፍ ሲያወርዱበት ውለዋል ።
ጓህላ ከተማን ወዲያውኑ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን ሞርተር የተባለውን የቡድን መሳሪያ በሰፊው መጠቀምም ተችሏል።
የሞርተር ድምጽን ሲሰማ የሚርበተበተው ጠላት ከተማውን ለቆ ከከተማዋ በስተ ምእራብ አቅጣጫ ከሚገኘው መሽጉ ፈርጥጦ ሊገባ ችሏል።
ከጠላት ምሽግ ድረስ ዘልቆ በመግባት በቦምብና ጨበጣ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አድርገዋል።
ከጓህላ በስተ ደቡብ አቅጣጫ ጨውጫዊት ከሚባለው ከፍተኛ ቦታ ላይ የመሸገው ጠላት በፋኖ ድሽቃ ከፍተኛ ምትን ያስተናገደ ሲሆን ለሰዋዊና ፖለቲካዊ ኪሳራም ተዳርጓል።
በዚህም ሰበብ ከመሸገበት ቦታ ተወስኖ ብቻ እንዲቀመጥ ተደርጓል።
♦️በጠለቀ የጀግንነት ወኔ እየፎከረና እየሸለለ የገባው የወገን ኃይል የስነ ልቦና የበላይነት ከመጎናጸፋም በላይ የጠላትን ኃይል የማከናወን አቅም እንዲሟሽሽ ማድረግም ተችሏል።
➛ በዛሬው አውደ ውጊያከተገኙ ድሎች
✔️11 እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።
✔️ 06 ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል። ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ2 ቀናት በፊት ማለትም በቀን 05/2018 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አህዶች ወርሃላ ዙሪያ ፣ ማዛርብ ፣ስሁር ፣ አላንጌ እና ፈንጣን ጨምሮ ከብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል ጋር ውጊያ የተካሄደ ሲሆን በውጊያውም 06 ጠላት ኃይል ክፉኛ ቁስለኛ መሆኑ ታውቋል።
ብልጽግና የመጭውን ስርዓታዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ በፋኖ ፈርጣማ ክንድ የለቀቃቸውን ከተሞች መልሶ ለመያዝ በሰማይና በምድር የታገዘ ውጊያዎችን እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ የካቲት 07/2018 ዓ.ም
#ሰበር_ዜና‼️
በሬማ ከተማ ዙሪያ የሚኖሩ የድሬ ቀበሌ ነዋሪዎችን ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ መጠን የተጣለበት የገንዘብ ተመን ካላዋጣችሁ በሚል በኃይል በመደብደብ ላይ በነበሩ የብልፅግናው ሰላም አስከባሪ ወንበዴዎች ላይ ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን አስታወቀ❗️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
መጋቢት 07 ቀን 2018 ዓ.ም
የአገዛዙን ዕድሜ በማራዘም፣ በህዝባችን ላይ ተጨማሪ የመከራና የጭቆና ዓመታትና የባርነት ዘመንን ለመጫን፣ በአገዛዙ ወታደሮች በየቀኑ እየተጨፈጨፈ ያለውን የአማራን ህዝብ በጉልበት በማስገደድና በኃል ድብደባ በፈፀሙ የዘመናችን ጥቁር ጣልያኖች ላይ ሰራዊታችን ያለምንም ርህራሔ ለአገዛዙ ዕድሜ ማራዘሚያ የሚሆን የገንዘብ መዋጮ በሚጠይቁ ካድሬዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወስድ ከድርጅቱ በወረደለት ትዕዛዝ መሰረት በሬማ ከተማ የሚገኙ የአገዛዙ ሎሌ ወንበር አስጠባቂዎች ላይ የመጀመሪያውን ቅጣት በጀግኖቹ የአስማረ ዳኜ ልጆች መወሰዱን ኮሩ አስታወቀ።
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ የሚዳና ሬማ ወረዳ በሬማ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ መጋቢት 07 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ላይ በከተማው ዙሪያ ያሉ የድሬ ቀበሌ ነዋሪዎችን ያለ ፈቃዳቸው በኃይል ለብልፅግና ፓርቲ መዋጮ እንዲከፍሉ በ30 የሚሊሻ አባላት ከየቤታቸው ተደብድበው በአስገዳጅነት የተፈፀመውን ኢ-ዲሞክራሲ በሆነ መንገድ በወንጀል ስራ ላይ በነበሩ የወረዳው ሰላም አስከባሪዎች ላይ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የአፄ ዳዊት ክፍለጦር በጀግናው አስማረ ዳኜ ፩ኛ ሻለቃ መብረቃዊ ርምጃ መውሰዱን ኮሩ በግንባር መረጃው አስታውቋል።
መረጃው እንደደረሳቸው በቦታው ላይ ተወርውረው የተገኙት የክፍለጦሩ አስማረ ዳኜ ፩ኛ ሻለቃ ቃኝዎች በወሰዱት ድንገተኛ ጥቃት በሬማ ከተማ ዙሪያ የድሬ ቀበሌ ነዋሪዎችን ያለ ፈቃዳቸው ለአገዛዙ ዕድሜ ማራዘሚያ የተጣለባቸውን ገንዘብ እንዲከፍሉ ኃይልን በመጠቀም በድብደባ ላይ በነበሩ ባንዳዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ ሲወስዱ ቀሪዎቹ እግሬ አውጭኝ ብለው በመፈርጠጥ ነብሳቸውን ያተረፉ ሲሆን ከባድ ጉዳት ያስተናገዱትን የሚሊሻ አባላት ወደ አለም ከተማ እናት ሆስፒታል በሪፈር መላካቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ሀኪም አበበ አላዩ ገልጿል።
አርበኛው በመልዕክቱ እንደገለፀው የአስማረ ዳኜ ፩ኛ ሻለቃ በወሰዱት መብረቃዊ ጥቃት የአገዛዙ የሰላም አስከባሪ አባል በሆነው አቶ ሽትዬ አባቡን ጨምሬ በሌሎች ለጊዜው ስማቸው ባልታወቀ አባላቱ ላይ ርምጃ በመውሰድ ለወንጀል መስሪያ ሲጠቀሙበት የነበረውን ሁለት ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ መማረካቸውን ያስታወቀ ሲሆን አሁንም ከጠላት ጋር በመሰለፍ ህዝባችንን ለተጨማሪ ጥቃት አሳልፎ የሚሰጥን ማንኛውንም አካል የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂዎች ላይ ሰራዊታችን የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አሳስቧል።
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ከግንባር መረጃዎችን አጠናቅሮ አድርሶናል።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!
ድል ለአፋብን!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
አንድነታችን አሸናፊነታችን!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
መጋቢት 07 /2018 ዓ.ም
ጄኔራል ተፈራ ማሞ - የአፋብን ወታደራዊ አዛዥ ለኮማንዶ ተመራቂዎች ያስተላለፉት መልዕክት!
አፋብን💪
የክህደት ድግስና የማይበገረው የአማራ ህዝብ የአድማስ ጋሻ
በቤተ-መንግሥቱ ጨለማ ኮሪደሮች ውስጥ የክፋት አዝመራቸውን ለመሰብሰብ የሚጣደፉ አፈ-ቀላጤዎች ተሰብስበዋል። እነ ቂስ ሞገስ ዳንኤል ክስርት የቃላት መርዛቸውን እንደ ማር እያጣፈጡ፣ የአማራን ሕዝብ ታሪክ ከመጽሐፈ-ሕይወት ለመደምሰስ ይዶልታሉ። እነዚህ የአገዛዙ ዳይፐሮች የጌታቸውን የጥፋት ጉዞ በውሸት ሽቶ ለመቀባት ቢሞክሩም የሴራቸው ጠረን ግን ከአድማስ ባሻገር ይከረፋል።
ቢሳካላችሁማ የአማራን ዘር ከምድር ገጽ አጥፍታችሁ በታሪክ መቃብር ላይ የክህደት ድንኳን ትተክሉ ነበር። ነገር ግን ይህ ሁሉ የፕሮፓጋንዳ ጩኸትና የመንገድ ላይ ስልት ከውድቀታችሁ በፊት የምታሰሙት የባዶነት ድምፅ መሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም ግን በአድማስ ማዶ አንድ ታላቅ ኃይል እንደ ንጋት ኮከብ በርቶ ይታያል።
የአማራ ዲያስፖራው ለወገኑ የማይናወጥ ደጀን ለአብይ አህመድና ለተከታዮቹ ደግሞ እንደ አረም ማጥፊያ መድኃኒት ሆኖ ብቅ ብሏል። ጠላቶቻቸው በድንጋጤ የሚመለከቱት ይህ ኃይል፣ የጥፋት መርዛቸውን የሚያክሽፍ እውነተኛ ጋሻ ነው።
አሁን ሰዓቱ የንግግር ሳይሆን የሥራ ነው፤ የጩኸት ሳይሆን የጥበብ ነው። በውጭ የሚኖረው ወገን ነገሮችን በብስለት የሚመዝንበት፣ ሥራዎችን በብልጠትና በስትራቴጂ የሚመራበት የመጨረሻው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። ታሪክ ይመሰክራል የጥላቻው ማዕበል በአለት ላይ ተጋጭቶ ይፈራርሳል፣ የሕዝቡ ጽናት ግን እንደ ዐባይ እየገሰገሰ ይቀጥላል። Dawit Amhara ከግንባር
+3
ሶስት የአድማ ብተና አባላቶች ፋኖን ተቀላቀሉ!
ሎሌውና ግርድና ግብሩ የሆነው ብአዴን ያደራጀው ሰራዊት አድማ ብተና 24ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻንበል አባል የሆኑ ሶስት አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ በወልድያ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ቀጠናዎች መሸጎ የሚገኘው አድማ ብተና እየፈርሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው። በዚህም ሶስት አባላቶች ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው የፋኖን ትግል ተቀላቅለዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 7/2018 ዓ.ም
ከ3400 ሰራዊት በላይ የከዳበት ብልፅግ ገመና
ብልፅግና በተደጋጋሚ ወጣቱን እያፈነ በጦላይ፣ በብርሸለቆ እና በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠነኛ ካንፕ ቢያሰለጥንም የታጠቀውን መሳሪያ እየያዘ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል። በአማራ ክልል በግዳጅ ከሰለጠነ የሚሊሻና አድማ ብተና አባላት ውስጥ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከ3400 ሰራዊት በላይ መክዳቱን ብልፅግና በግመገማው አረጋግጧል።
ብልፅግና 27, 000 ቻይና ስሪት ክላሽ ግዥ መፈፀሙ የሚታወቅ ቢሆንም ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሰራዊት የተሰጠውን መሳሪያ ይዞ ፋኖን መቀላቀሉ ግማሹም የደረሰበት መጥፋቱ ተረጋግጧል።
ከሰለጠነው ሰራዊት 70% የሚሆነው መሳሪያውን እንደያዘ የከዳ ሲሆን 3,400ውቹ ከነመሳሪያዎቻቸው ፋኖን የተቀላቀሉ መሆኑን ብልፅግና በዝግ ስብሰባው በማረጋገጡ ጭንቅ ውስጥ ገብቷል ።
በዚህም የተነሳ ለመልሶ ማደራጀት እና ስልጠና ይሆን ዘንድ በአማራ ክልል ውስጥ ሃብት አሰባሳቢ አዲስ ኮማንድ ፖስት ተመስርቷል:: ይሄም ደግሞ በክልሉ በቢሮ ሃላፊዎች ደረጃ በተዋረድ ለሰራተኞቻቸው እቅዱን በማወያየት ሰራተኛው ከደሞዙ በተከፈተው አካውንት ገቢ እንዲያደርጉና ሰራተኞች በሚገናኙበት ማህበረሰብ ክፍል ላይ ስለሃብት ማሰባሰብ እንዲሰብኩ አቅጣጫ ተሰጥቷል::
በዚህ የኑሮ ውድነት ውስጥ ያለው የመንግስት ሰራተኛ እና ነጋዴው ማህበረሰብ ይህን የሚሸከም ትክሻ ስለሌለው ፋኖን እንዲቀላቀልና ትግሉን በአጭር ጊዜ በጋራ እንድንቋጭ ጥሪ እናቀርባለን።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
መጋቢት 07/2018ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና‼️
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር በባንዳ ሚኒሻ አባል ላይ እርምጃ በመውሰድ አስደማሚ ድል ተቀደጀ ።
መጋቢት 6/07/2018 ዓ.ም፡ የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚና መሃንዲስ ተወርዋሪ ነብሮ ሻለቃ አስገራሚ ጀብድ መፈፀሙ ታውቋል ። የብልፅግናው መንግስት የጫረው እሳት ፋኖን በመውለድ መልሶ እራሱን እየለበለበው እና እያቃጠለው በሚገኝበት ሰዓት በዝርፊያ የግብር አባታቸው የሆነውን ብልፅግናን ለማዳን ከወገናቸው እና ከአብሮ አደጋቸው ይልቅ ከርሳቸውን የሚሞላላቸውን ብልፅግናን በመምረጥ በባንዳ ሚሊሻነት ለስርዓቱ ያጎበደዱ ሆድ-አደር ፥ የአማራ ነቀርሳዎች መፈጠራቸው የዘመናችን ብቸኛ ከሃዲ ያደርጋቸዋል ።
ታዲያ እነኝህ የዘመናችን ልዩ ከሃዲ ባንዳ ሚሊሻዎች በህዝባችን ላይ በሚያደርሱት በደልና ግፍ እንዲሁም ዘረፋዎች ሲፈፀም በመረዳት የአማራ ልጅ ፋኖ ደግሞ በእነዚህ ህዝባቸውን አሳልፈው የሸጡ ወመኔዎች ላይ በተለየ እልህ እና ቁጭት የተሞላበት ወኔ በተሞላበት በቁርጥ በመነሳት የገቡበት እየገባ ማፅዳቱንና መደምሰሱን መቀጠሉን የነበልባል ክ/ጦር አስታውቋል ።
➣ አቶ ወንድዬ ስራው፡ የተባለ የዘመናችን ምሰለኔ ባንዳ ሚሊሻ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6:00 ሰዓት አከባቢ ቦሎ ስላሴ በሚባል አካባቢ በክፍለ ጦሩ ቃኚ በነብሮ ሻለቃ ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት እስከ ወዲያኛው በመሸኘት የያዘውን ሁለት እግር ታጣፊ ክላሽ በመማረክ በሰላም መመለሳቸው ነው የታወቀው ።
የብልፅግናው መንግስት ይጠብቁኛል በማለት በልመና ከሀገር ሀገር ዞሮ ያመጣውን አዲስ ሁለት እግር ታጣፊ ክላሽ ልዩ ነብራ ቁጥሩ (70226697) ለሚኒሻ ቢያስታጥቅም አሳረኛው ፋኖ እነሱን ወደ ሰባተኛው ገሃነብ በመላክ የያዙትን መሳሪያ ገቢ እያደረገው ይገኛል ።
የሞኝ ለቅሶ መልሶ መልሶ እንደተባለው ሁሉ የብልፅግናው መንግስትም የፋኖን ትግል ለማጣጣልና ለማሳነስ በሌሎች ሀገሮች ተረድተው ነው የሚል ታርጋ ቢለጥፍም፤ ነበልባሉ ፋኖ ግን በጀግንነቱ በመማረክ እና የራሱን የብልፅግና ሰራዊት በስቦ ማስከዳት ከነፍስ ወከፍ እስከ ከባድ መሳሪያ የታጠቀ እንደሆነ ማንኛውም የፋኖ ደጋፊ ሊያቀው ይገባል ለዚህም ማረጋገጫ የዛሬው መጀመሪያም እንዳልሆነና መጨረሻም እንደማይሆን ማሳወቅ እንወዳለን፤ በማለት የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርታራችን መረጃውን ከግምባር አድርሶናል ።
© አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ሚዲያ ክፍል ኃላፊ አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ።
- አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ።
ዋርካው ምሬ ወዳጆ ለምልምል ሰልጣኝ ኮማንዶዎች ምን አለ!?
አይኔ አያይም፣ ጆሮዬ አይሰማም ምናምን ሳትል አስተውለህ👀 አድም🧏🏽
አማራ ጠላቶቹን በክንዱ💪🏽አሸንፎ ህልውናውን በሰላም ያስቀጥላል✊🏽
5. ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ
የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ዘመናት በብዙ መከራና ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፈ ስለመሆኑ ከዓለም የተሰወረ አይደለም። አምባገነኑ ኮሎኔል ዐብይ አህመድ የሚመራው አገዛዝ ሀገሪቱን ወደ ባሰ መከራ፤ ቀጠናውንም መውጫ ወደሌለው ትርምስ እየመራው ባለበት በአሁኑ ወቅት ‹‹ምርጫ አደርጋለሁና እወቁልኝ›› የሚል ለፈፋ አገዛዙ ለማደናገር የሚሁድበትን እርቀት የሚያሳይ መሆኑን ተገንዝባችሁ ቀጠናውን ለባሰ ቀውስ እና ትርምስ ከሚዳርግ፣ ዜጎቹን ከጅምላ ስደትና እንግልት ከሚያጋልጥ እና ቋሚ መርሁ ቀውስና ትርምስ፤ ጦርነትና ግጭት መሆኑን በገቢር ከገለጸው አገዛዝ፤ ኢትዮጵያ ትድን ዘንድ ከአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ጎን በመቆም፤ ሥርዓታዊ ለውጥና የሽግግር ጊዜ እንዲመጣ ከጎናችን ይሆን ዘንድ የከበረ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
6.አገዛዙን እየታገላችሁ ለምትገኙ የፀረ ብልፅግና ኃይሎች
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በታሪኳ አይታው በማታውቅ የታሪክ አጋጣሚና እጅግ አደገኛ በሆነ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ስልጣኑን የተቆጣጠረው አገዛዝ የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ወደ ጎን በመተው ሀገሪቱን ወደማያለቅ የጦርነት አዙሪት፣ ማህበራዊ መፈናቀልና የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ ከቷታል፡፡ ሀገራዊ አንድነታችንም አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ በመሆኑን ይህንን ታሪካዊ ውድቀት ለመቀልበስ እና የኢትዮጵያን ውድቀት ለመታደግ ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበን አገዛዙ ይህንን የማጭበርበሪያ ምርጫ አድርጎ ተጨማሪ የመግደያ ጊዜ ሳያገኝ በጋራ ሀገራዊ ዓላማ በመሰለፍ እና የተቀናጀ ስትራቴጅ በመንደፍ በአንድነት እንድንታገል ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
7.ለመምህራን፣ ለትምህርት ተቋማት አመራሮች እና የመንግስት ሰራተኞች
አገዛዙ ለማደናገሪያነት ሊያደርግ ያቀደውን ምርጫ እንድታስፈፅሙለት በዋነኝነት እናንተን ለመጠቀም ውሳኔ የተላለፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡ መምህራን እና የመንግስት ሰራተኞች ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት የምትገኙ እንደመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ደም አፈሳሽ ጦርነት ከእናንተ በላይ የሚያውቅ የለም፡፡ በመሆኑም ይህንን የአገዛዙን ደርጊት ባመቀበል ለህዝባችሁ ያላችሁን ወገናዊነት በተግባር እንድታሳዩ አደራ እንላለን፡፡
በመጨረሻም ይህንን ጥሪያችንን ተላልፎ ከጠላት ጋር በመሰለፍ ህዝባችንን ለተጨማሪ ጥቃት አሳልፎ የሚሰጥ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ የምንወስድ ስለመሆኑ ለመላው ሰራዊታችን ትዕዛዝ የተላለፈ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
