ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 613
Suscriptores
+6624 horas
+5877 días
+1 04130 días
Archivo de publicaciones
የክህደት ድግስና የማይበገረው የአማራ ህዝብ የአድማስ ጋሻ
በቤተ-መንግሥቱ ጨለማ ኮሪደሮች ውስጥ የክፋት አዝመራቸውን ለመሰብሰብ የሚጣደፉ አፈ-ቀላጤዎች ተሰብስበዋል። እነ ቂስ ሞገስ ዳንኤል ክስርት የቃላት መርዛቸውን እንደ ማር እያጣፈጡ፣ የአማራን ሕዝብ ታሪክ ከመጽሐፈ-ሕይወት ለመደምሰስ ይዶልታሉ። እነዚህ የአገዛዙ ዳይፐሮች የጌታቸውን የጥፋት ጉዞ በውሸት ሽቶ ለመቀባት ቢሞክሩም የሴራቸው ጠረን ግን ከአድማስ ባሻገር ይከረፋል።
ቢሳካላችሁማ የአማራን ዘር ከምድር ገጽ አጥፍታችሁ በታሪክ መቃብር ላይ የክህደት ድንኳን ትተክሉ ነበር። ነገር ግን ይህ ሁሉ የፕሮፓጋንዳ ጩኸትና የመንገድ ላይ ስልት ከውድቀታችሁ በፊት የምታሰሙት የባዶነት ድምፅ መሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም ግን በአድማስ ማዶ አንድ ታላቅ ኃይል እንደ ንጋት ኮከብ በርቶ ይታያል።
የአማራ ዲያስፖራው ለወገኑ የማይናወጥ ደጀን ለአብይ አህመድና ለተከታዮቹ ደግሞ እንደ አረም ማጥፊያ መድኃኒት ሆኖ ብቅ ብሏል። ጠላቶቻቸው በድንጋጤ የሚመለከቱት ይህ ኃይል፣ የጥፋት መርዛቸውን የሚያክሽፍ እውነተኛ ጋሻ ነው።
አሁን ሰዓቱ የንግግር ሳይሆን የሥራ ነው፤ የጩኸት ሳይሆን የጥበብ ነው። በውጭ የሚኖረው ወገን ነገሮችን በብስለት የሚመዝንበት፣ ሥራዎችን በብልጠትና በስትራቴጂ የሚመራበት የመጨረሻው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። ታሪክ ይመሰክራል የጥላቻው ማዕበል በአለት ላይ ተጋጭቶ ይፈራርሳል፣ የሕዝቡ ጽናት ግን እንደ ዐባይ እየገሰገሰ ይቀጥላል። Dawit Amhara ከግንባር
+3
ሶስት የአድማ ብተና አባላቶች ፋኖን ተቀላቀሉ!
ሎሌውና ግርድና ግብሩ የሆነው ብአዴን ያደራጀው ሰራዊት አድማ ብተና 24ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻንበል አባል የሆኑ ሶስት አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ በወልድያ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ቀጠናዎች መሸጎ የሚገኘው አድማ ብተና እየፈርሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው። በዚህም ሶስት አባላቶች ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው የፋኖን ትግል ተቀላቅለዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 7/2018 ዓ.ም
ከ3400 ሰራዊት በላይ የከዳበት ብልፅግ ገመና
ብልፅግና በተደጋጋሚ ወጣቱን እያፈነ በጦላይ፣ በብርሸለቆ እና በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠነኛ ካንፕ ቢያሰለጥንም የታጠቀውን መሳሪያ እየያዘ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል። በአማራ ክልል በግዳጅ ከሰለጠነ የሚሊሻና አድማ ብተና አባላት ውስጥ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከ3400 ሰራዊት በላይ መክዳቱን ብልፅግና በግመገማው አረጋግጧል።
ብልፅግና 27, 000 ቻይና ስሪት ክላሽ ግዥ መፈፀሙ የሚታወቅ ቢሆንም ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሰራዊት የተሰጠውን መሳሪያ ይዞ ፋኖን መቀላቀሉ ግማሹም የደረሰበት መጥፋቱ ተረጋግጧል።
ከሰለጠነው ሰራዊት 70% የሚሆነው መሳሪያውን እንደያዘ የከዳ ሲሆን 3,400ውቹ ከነመሳሪያዎቻቸው ፋኖን የተቀላቀሉ መሆኑን ብልፅግና በዝግ ስብሰባው በማረጋገጡ ጭንቅ ውስጥ ገብቷል ።
በዚህም የተነሳ ለመልሶ ማደራጀት እና ስልጠና ይሆን ዘንድ በአማራ ክልል ውስጥ ሃብት አሰባሳቢ አዲስ ኮማንድ ፖስት ተመስርቷል:: ይሄም ደግሞ በክልሉ በቢሮ ሃላፊዎች ደረጃ በተዋረድ ለሰራተኞቻቸው እቅዱን በማወያየት ሰራተኛው ከደሞዙ በተከፈተው አካውንት ገቢ እንዲያደርጉና ሰራተኞች በሚገናኙበት ማህበረሰብ ክፍል ላይ ስለሃብት ማሰባሰብ እንዲሰብኩ አቅጣጫ ተሰጥቷል::
በዚህ የኑሮ ውድነት ውስጥ ያለው የመንግስት ሰራተኛ እና ነጋዴው ማህበረሰብ ይህን የሚሸከም ትክሻ ስለሌለው ፋኖን እንዲቀላቀልና ትግሉን በአጭር ጊዜ በጋራ እንድንቋጭ ጥሪ እናቀርባለን።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
መጋቢት 07/2018ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና‼️
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር በባንዳ ሚኒሻ አባል ላይ እርምጃ በመውሰድ አስደማሚ ድል ተቀደጀ ።
መጋቢት 6/07/2018 ዓ.ም፡ የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚና መሃንዲስ ተወርዋሪ ነብሮ ሻለቃ አስገራሚ ጀብድ መፈፀሙ ታውቋል ። የብልፅግናው መንግስት የጫረው እሳት ፋኖን በመውለድ መልሶ እራሱን እየለበለበው እና እያቃጠለው በሚገኝበት ሰዓት በዝርፊያ የግብር አባታቸው የሆነውን ብልፅግናን ለማዳን ከወገናቸው እና ከአብሮ አደጋቸው ይልቅ ከርሳቸውን የሚሞላላቸውን ብልፅግናን በመምረጥ በባንዳ ሚሊሻነት ለስርዓቱ ያጎበደዱ ሆድ-አደር ፥ የአማራ ነቀርሳዎች መፈጠራቸው የዘመናችን ብቸኛ ከሃዲ ያደርጋቸዋል ።
ታዲያ እነኝህ የዘመናችን ልዩ ከሃዲ ባንዳ ሚሊሻዎች በህዝባችን ላይ በሚያደርሱት በደልና ግፍ እንዲሁም ዘረፋዎች ሲፈፀም በመረዳት የአማራ ልጅ ፋኖ ደግሞ በእነዚህ ህዝባቸውን አሳልፈው የሸጡ ወመኔዎች ላይ በተለየ እልህ እና ቁጭት የተሞላበት ወኔ በተሞላበት በቁርጥ በመነሳት የገቡበት እየገባ ማፅዳቱንና መደምሰሱን መቀጠሉን የነበልባል ክ/ጦር አስታውቋል ።
➣ አቶ ወንድዬ ስራው፡ የተባለ የዘመናችን ምሰለኔ ባንዳ ሚሊሻ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6:00 ሰዓት አከባቢ ቦሎ ስላሴ በሚባል አካባቢ በክፍለ ጦሩ ቃኚ በነብሮ ሻለቃ ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት እስከ ወዲያኛው በመሸኘት የያዘውን ሁለት እግር ታጣፊ ክላሽ በመማረክ በሰላም መመለሳቸው ነው የታወቀው ።
የብልፅግናው መንግስት ይጠብቁኛል በማለት በልመና ከሀገር ሀገር ዞሮ ያመጣውን አዲስ ሁለት እግር ታጣፊ ክላሽ ልዩ ነብራ ቁጥሩ (70226697) ለሚኒሻ ቢያስታጥቅም አሳረኛው ፋኖ እነሱን ወደ ሰባተኛው ገሃነብ በመላክ የያዙትን መሳሪያ ገቢ እያደረገው ይገኛል ።
የሞኝ ለቅሶ መልሶ መልሶ እንደተባለው ሁሉ የብልፅግናው መንግስትም የፋኖን ትግል ለማጣጣልና ለማሳነስ በሌሎች ሀገሮች ተረድተው ነው የሚል ታርጋ ቢለጥፍም፤ ነበልባሉ ፋኖ ግን በጀግንነቱ በመማረክ እና የራሱን የብልፅግና ሰራዊት በስቦ ማስከዳት ከነፍስ ወከፍ እስከ ከባድ መሳሪያ የታጠቀ እንደሆነ ማንኛውም የፋኖ ደጋፊ ሊያቀው ይገባል ለዚህም ማረጋገጫ የዛሬው መጀመሪያም እንዳልሆነና መጨረሻም እንደማይሆን ማሳወቅ እንወዳለን፤ በማለት የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርታራችን መረጃውን ከግምባር አድርሶናል ።
© አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ሚዲያ ክፍል ኃላፊ አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ።
- አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ።
ዋርካው ምሬ ወዳጆ ለምልምል ሰልጣኝ ኮማንዶዎች ምን አለ!?
አይኔ አያይም፣ ጆሮዬ አይሰማም ምናምን ሳትል አስተውለህ👀 አድም🧏🏽
አማራ ጠላቶቹን በክንዱ💪🏽አሸንፎ ህልውናውን በሰላም ያስቀጥላል✊🏽
5. ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ
የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ዘመናት በብዙ መከራና ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፈ ስለመሆኑ ከዓለም የተሰወረ አይደለም። አምባገነኑ ኮሎኔል ዐብይ አህመድ የሚመራው አገዛዝ ሀገሪቱን ወደ ባሰ መከራ፤ ቀጠናውንም መውጫ ወደሌለው ትርምስ እየመራው ባለበት በአሁኑ ወቅት ‹‹ምርጫ አደርጋለሁና እወቁልኝ›› የሚል ለፈፋ አገዛዙ ለማደናገር የሚሁድበትን እርቀት የሚያሳይ መሆኑን ተገንዝባችሁ ቀጠናውን ለባሰ ቀውስ እና ትርምስ ከሚዳርግ፣ ዜጎቹን ከጅምላ ስደትና እንግልት ከሚያጋልጥ እና ቋሚ መርሁ ቀውስና ትርምስ፤ ጦርነትና ግጭት መሆኑን በገቢር ከገለጸው አገዛዝ፤ ኢትዮጵያ ትድን ዘንድ ከአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ጎን በመቆም፤ ሥርዓታዊ ለውጥና የሽግግር ጊዜ እንዲመጣ ከጎናችን ይሆን ዘንድ የከበረ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
6.አገዛዙን እየታገላችሁ ለምትገኙ የፀረ ብልፅግና ኃይሎች
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በታሪኳ አይታው በማታውቅ የታሪክ አጋጣሚና እጅግ አደገኛ በሆነ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ስልጣኑን የተቆጣጠረው አገዛዝ የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ወደ ጎን በመተው ሀገሪቱን ወደማያለቅ የጦርነት አዙሪት፣ ማህበራዊ መፈናቀልና የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ ከቷታል፡፡ ሀገራዊ አንድነታችንም አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ በመሆኑን ይህንን ታሪካዊ ውድቀት ለመቀልበስ እና የኢትዮጵያን ውድቀት ለመታደግ ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበን አገዛዙ ይህንን የማጭበርበሪያ ምርጫ አድርጎ ተጨማሪ የመግደያ ጊዜ ሳያገኝ በጋራ ሀገራዊ ዓላማ በመሰለፍ እና የተቀናጀ ስትራቴጅ በመንደፍ በአንድነት እንድንታገል ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
7.ለመምህራን፣ ለትምህርት ተቋማት አመራሮች እና የመንግስት ሰራተኞች
አገዛዙ ለማደናገሪያነት ሊያደርግ ያቀደውን ምርጫ እንድታስፈፅሙለት በዋነኝነት እናንተን ለመጠቀም ውሳኔ የተላለፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡ መምህራን እና የመንግስት ሰራተኞች ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት የምትገኙ እንደመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ደም አፈሳሽ ጦርነት ከእናንተ በላይ የሚያውቅ የለም፡፡ በመሆኑም ይህንን የአገዛዙን ደርጊት ባመቀበል ለህዝባችሁ ያላችሁን ወገናዊነት በተግባር እንድታሳዩ አደራ እንላለን፡፡
በመጨረሻም ይህንን ጥሪያችንን ተላልፎ ከጠላት ጋር በመሰለፍ ህዝባችንን ለተጨማሪ ጥቃት አሳልፎ የሚሰጥ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ የምንወስድ ስለመሆኑ ለመላው ሰራዊታችን ትዕዛዝ የተላለፈ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም
ከጠላት ጋር በመሰለፍ ህዝባችንን ለተጨማሪ ጥቃት አሳልፎ የሚሰጥን ማንኛውንም አካል አንታገስም!!!
(መጭውን የአገዛዙ “ምርጫ” አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ!)
የአማራ ህዝብ በጨፍጫፊው የብልጽግና ሥርዓት የዘር ማጥፋት ጦርነት ተከፍቶበት ህፃን፣ አዛውንት፣ ሴት ወንድ፣ ወጣት ሽማግሌ ሳይል፤ በአየር በምድር እየተጨፈጨፈ ይገኛል። የአማራ ህዝብም ሊያጠፋው ከመጣው አረመኔ አገዛዝ ራሱን ለመከላከል ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ በድል እየገሰገሰ ነው፡፡ ይህ አገዛዙ የለኮሰው ጦርነቱም በአማራ ህዝብ ላይ ብቻ ሳይወሰን በሌሎችም የሀገሪቱ ግዛቶች ደም አፋሳሽ ሁኖ ቀጥሏል፡፡ በእዚህ የአገዛዙ ጦረኛ ባህሪ የተነሳ በመላ ሀገሪቱ ሰላም ከጠፋ ዓመታት እየተቆጡሩ ነው።
ሀገራችን በጦርነት እና በግጭት እየታመሰች፣ ዜጎች በአገዛዙ ወታደሮች እየተጨፈጨፉ፣ ሚዲያዎችም ታፍነው እና ተዘግተው ባሉበት በአሁኑ ሰዓት አገዛዙ በተፎካካሪ ስም የተደራጁ ካቢኔዎቹን እና በሀገር መከላከያና በፀጥታ ተቋማት አመራር ስም ያስቀመጣቸውን ዘር ጨፍጫፊ ጀነራሎቹን ይዞ ምርጫ ቅስቀሳ ጀምሯል፡፡ ይህ አገዛዝ የሚያወራው "ምርጫ" ነፃና ገለልተኛ ሊሆን ቀርቶ ከዚህ ቀደም ከነበሩት አሳፋሪ ምርጫዎች የባሰ እንደሚሆን የአገዛዙን ባህሪ የሚያዉቅ ሁሉ የሚረዳው ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህ ምርጫ አገዛዙ የአማራን ህዝብ እና መላው ኢትዮጵያውያንን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለመግደል የሚያስችለውን ሰርተፍኬት ለማግኘት ያቀደው እንደሆነ ይገነዘባል።
በመሆኑም በዚህ የአማራን ሕዝብ በታቀደ መልኩ በድሮን እና በሜካናይዝድ ጨምሮ በማንኛውም የጦርኑት ስልት እየጨፈጨፈው ያለው ዘረ ፈጅ የማደናገሪያ “ምርጫ” በተመለከተ የሚከተሉትን ማሳሰቢያወች እና ጥሪወች እናቀርባለን።
1. ለፖለቲካ ፓርቲዎች
በአሁኑ ወቅት የአማራ ህዝብ በታሪኩ አይቶት የማያውቅ የህልውና አደጋ ተጋርጦበት ይገኛል። አገዛዙ በህዝባችን ላይ የከፈተው የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ዛሬም በከፋ መልኩ ቀጥሏል።አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ የአደባባይ ምስጢር ነው። ንጹሃን በገዛ ቀያቸው እየታረዱ፣ ከተሞች በከባድ መሳሪያ እየፈረሱና ህዝባችን የማንነት ጥቃት እየደረሰበት ይገኛል። በመሆኑም የምናደርገው ትግል በመደበኛው የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ሊመለስ የማይችል ህዝብን ከጥፋት የማዳን የህልውና ትግል ነው።
ይህ ጨፍጫፊ አገዛዝ ህዝብን መዋሸት፣ ማታለል፣ መካድ፣ ማስመሰል እና ጥላቻ መሰረታዊ የአገዛዝ ስልት እና የባህሪወቹ ናቸውና ምርጫን አጀንዳው ቢያደርግ ብዙም አያስገርምም። ምርጫን እንደ መርህ የሚያየው ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የአገዛዙን ባህሪ ተረድቶ ጆሮ የነፈገዉን ይህንን የማጭበርበር ስልት የተቋማት መሪዎች፤ የሚዲያ ሰወች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማጀብ በሂደት ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል። ይህም የአገዛዙ የጭፍጨፋ እቅድ ተባባሪነታቸውን ያሳዩበት ወይም ከልክ ያለፈ አድርባይነታቸውን የሚያሳይ አስፈሪና አሳፋሪ ክስተት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአማራ ህዝብ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት በግልፅ ጦርነት እየተለበለበ ባለበት ድምፃቸውን አጥፍተው አንዳንዶችም ከጨፍጫፊው ጎን ቆመው ያየናቸው አካላት፤ ዛሬ የተለመደውን የቁማር ምርጫ እናሟሙቃለን ብለው መነሳታቸው፤ የአማራ ሕዝብ የሚያደርገውን ተጋድሎ ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ህልዉናም ጭምር የካዱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ህዝብን በጅምላ ለመጨፍጨፍ የሚያስችል ሰነድ ለማግኘት በማሰብ የሚደረገውን ምርጫ የሚያጅቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና በማንኛውም መንገድ የሚያግዙ አካላት ከአገዛዙ እኩል የአማራ ህዝብ ጠላት መሆናቸውን ለማሳወቅ እንወዳለን።
በመሆኑም አገዛዙ ሊያደርግ ያሰበው ምርጫ የኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግር እንደማይፈታና ህዝብን ማደናገሪያ መሆኑን አውቃችሁ ከሂደቱ እራሳችሁን እንድታገሉ እየጠየቅን ጥያቂያችንን ወደ ጎን በመተው በዚህ የደም ድግስ ላይ አገዛዙን የማጀብና ዕውቅና የመስጠት ተግባራችሁን የምትቀጥሉ ከሆነ ከአገዛዙ እኩል እንደምናያችሁና እንደምንታገላችሁ እናሳስባለን።
2. ለመላው የአማራ ህዝብ
ሁሉንም የሰላማዊ የትግል አማራጮችን ከሚጠበቅበት የትዕግስት እርከን በላይ የአንተን ያህል የተጠቀመ ሕዝብ አለ ማለት አይቻልም። ነገር ግን አገዛዙ ፍትሀዊ እና ህጋዊ ጥያቄዎችህን በመመለስና ችግሮችን በመፍታት ፋንታ መልሱ የጅምላ ጭፍጨፋ ነው፡፡ ይህ አገዛዙ የሚያደርገው ምርጫም አንተን ለማጥፋት ተጨማሪ ጊዜ የሚገዛበት ለመሆኑ የተሰወረ አይደለም፡፡ አገዛዙ በየቀኑ በድሮን በጅምላ እየጨፈጨፈህ፣ ልጆችህ በአገዛዙ ማጎሪያዎች እየተሰቃዩ ባሉበት ሁኔታ ይህ የአገዛዙ የምርጫ ድራማ ሞትህን እንደመፍቀድ መሆኑን ተረድተህ እያደረክ ያለውን ሁለንተናዊ ትግል አጠናክረህ እንድትቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
3.ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ
የተከበርከው የሀገራችን ሕዝብ ሆይ፤ መቸም የአማራ ሕዝብ እያሳለፈ ያለውን ያልተቋረጠ መከራ ለአንተ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው ብለን እናምናለን። የብልጽግናው ጨፍጫፊ ሥርዓት፤ በአየር፣ በሜካናይዝድ፣ በእግረኛ ሰራዊት ለተከታታይ ሦስት ዓመታት መጨፍጨፉን በመካድ፤ ‹ሰላም ነንና ሰላማዊ ምርጫ እናደርጋለን› እያለ በሚዲያዎቹ ደጋግሞ ሲናገር ይደመጣል። የሥርዓቱ ቃል አቀባዮችና ምስለኔዎችም ሀፍረት አልፈጠረባቸውምና እንደተለመደው ዓይናቸውን በጨው አጥበው፤ የሰላም ቃላትን መደርደሩን ጀምረውታል።
በመሆኑም የአገዛዙ ተጨማሪ ጊዜ ከተሰጠው ሀገራችንን ከእዚህ በላይ የከፋ አደጋ የሚጋጥም መሆኑን ተገንዝባችሁ ለአገዛዙ የይስሙላ ምርጫ ትብብር በመንፈግ ይልቁንም ህዝባዊ እንቢተኝነት በማቀጣጠል በቅርብ ጊዜ ለምናደርገው የመጨረሻው የትግል ምዕራፍ ለሚቀርበው ጥሪ፤ በንቃት እንድትጠብቁና ከትግላችን ጎን እንድትሰለፉ፤ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከወዲሁ ጥቆማውን ለማቅረብ ይወዳል።
4. ለሚዲያ ተቋማት
የአምባገነኑ ዐቢይ አህመድ አገዛዝ፤ የራሱን ሕዝብ በጅምላ ከመጨፍጨፍ አልፎ፤ ሀገራችን መልካም ጎረቤት እንዳይኖራት በሁሉም አቅጣጫ ጦር እየሰበቀ ይገኛል፡፡ ከሠለጠኑት ሀገራት ጋር በሚያደርገው ግንኙነት፣ ውይይትና ጉዞ፤ የልማትና የእድገት ማሳለጫ ማሽነሪዎችን ሳይሆን ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያዎችን፣ የሰላም ስምምነት ሳይሆን ጠብ ጫሪ ውሎችን እየተፈራረመ ይገኛል፡፡ ይህ አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ በማደናግርና በማጭበርበር የመንግስትነት በትረ ስልጣኑን ከያዘ ጀምሮ አንድም ቀን ሰላም ሳያገኝ የኖረ ቢሆንም፤ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ ደግሞ፤ በጅምላ እየጨፈጭፈው ያለው የአማራ ሕዝብ አልበቃው ብሎ፤ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የሀገሪቱ አጠቃላይ ቀጠናዎች የጦርነትና የግጭት በር ወለል ብሎ እንዲከፈት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ተራዛሚና አውዳሚ የዘር ማጥፋት ጦርነት በገባችበትና፤ የአማራ ሕዝብ ያለማቋረጥ ለሶስት ዓመታት እየተጨፈጨፈ ባለበት ሰዓት ምርጫ ስለማድረግ አይደለም ማሰብ የማይቻል መሆኑን ተገንዝባችሁ ሕዝብን ለማገልገል የተቋቋማችሁ የሚዲያ ተቋማት፤ ሀገራችን በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለዓለም ህዝብ እንድታደርሱ፣ ለህሊናቸውና ለሙያቸው ክብር ሲሉ ከእውነት ጎን የሚቆሙ ምሁራንን በመጋበዝ፤ አሁናዊ ሃቁን ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጡ በማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ የከበረ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በቁይ ከተማ ከምሽቱ 1:20 በፈፀመው የቦምብ ጥቃት የጠላት ሰራዊት መገደላቸው ተረጋግጧል።
መጋቢት 6/2018ዓም
አነፍናፊ የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ፣ አምበር፣ ወጀል ከተሞች ከፈፀሙት የተጠናከረ የቦምብ ጥቃት በኋላ አዳሩን በቁይ ከተማ ሰርጎ በመግባት አሰንዳቦ ላይ በሚገኘው በአረመኔው ሰራዊት ምሽግ ከምሽቱ 1:20 በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት 4(አራት) የመከላከያ ሰራዊት ሲገደሉ 2(ሁለት) ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
ጠላት በመሸገባቸው ከተሞች በመዘዋወር የጠላትን አንገት ሚያስደፋው አዳኝ ቡድኑ ያለ ምንም አይነት መስዋትነት ተከታታይ ግዳጆችን በብቃት እየተወጣ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የአማራ ምድሪቱ ለዘመናት በከባድ ጭጋግ ተከልላ ቆይታለች። ያ ጭጋግ ግን ተፈጥሯዊ አልነበረም ይልቁንም በረቂቅ ሴራ የተሸመነ በክፉ ድግምቶች የተተበተበና የአንድን ታላቅ ህዝብ እርምጃ ለመግታት የተዘረጋ የጨለማ መጋረጃ እንጂ አማራው በዚህ መጋረጃ ውስጥ ሆኖ፣ እግሮቹ በማይታዩ ሰንሰለቶች ታስረው፣ ትከሻውም በክዳን ተጭኖ ለብዙ ዘመናት የዝምታን ዋጋ ከፈለ።
በየጓዳው የሚሰሙት የሴራ ድምፆች ህዝቡን ከራሱ ጋር ለማጣላትና የታሪክ መሰረቱን ለማናጋት የታለሙ ነበሩ። ያ ተንኮል እንደ ሸረሪት ድር ስስ ቢመስልም፣ እንደ ብረት ሰንሰለት ጠንክሮ በህዝቡ ጫማ ስር ተቀብሮ ቆየ። ትናንት የክብርና የጀግንነት ማማ የነበረው ምድር በነዚህ ሸፍጦች ምክንያት የጥርጣሬና የቆይታ አውድማ ሆኖ ከረመ።
ነገር ግን የጊዜው ሰዓት ደረሰ ንጋቱ ሳይታለም መጣ። ያ በሴራ ተተብትቦ የነበረው ግዙፍ ህዝብ፣ ከውስጡ የሚቀጣጠለውን የቁጭትና የነፃነት እሳት አቀጣጠለው። ልክ እንደ አንበሳ ጎፈር ትከሻውን ነቅንቆ ተነሳ። ያኔ ለዘመናት የተሸረቡት የሴራ ድሮች እንደ ሸንኮራ አገዳ ተሰባበሩ። በጨለማ ሲደገሙ የነበሩት የተንኮል መተት ተገለጠባቸው ሰንሰለቱም በህዝቡ አንድነት ኃይል ተበጣጠሰ።
ዛሬ ያ ጭጋግ እየተገለጠ ነው። አማራው አቧራውን አራግፎ በኩራት ቀና ብሎ ወደ ፊት እየገሰገሰ ይገኛል። ዛሬ እርምጃው የፈሪ አይደለም፤ ዛሬ ጉዞው የሴራ ሰለባ ለመሆን አይደለም። ይልቁንም ታሪክን በራሱ ብዕር ለመጻፍ የነገውን ብርሃን በራሱ እጅ ለመጨበጥ ወደ ፊት እየተመመ ነው። ተንኮልና ሸፍጥ የገነቡት ግድግዳ ተንዶ የህዝቡ የድል ጎዳና ዛሬ በሰፊው ተከፍቷል።
ጉዞው ወደ ከፍታ ነው ጉዞው ወደ ጽናት ነው! Dawit Amhara ከግንባር
+8
በ201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ጥምር ሀይሉ ጋር የግዳጅ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ‼️
~~~~~~~~~~~~~~~~~
መጋቢት 06/2818 ዓ.ም
የ54ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ሀይል እንደ ንስር በአዲስ መልኩ ታድሶ እየመጣ ነው።ጦሩ በፊት ከነበረው በትጥቅም በስንቅም ራሱን በማጎልበት በቂ የሆነ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት በተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን ከግዳጅ መልስ ችግር ፈች የሆኑ ውይይቶቾን ማካሄድ ተችሏል።
በውይይቱ የኮር አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች እና የሚዲያ በቀጣይ መሰራት ያለባቸውን አቅጣጫወች አመላክተዋል። በተያያዘ በህልውና ትግሉ አልፋና ኦሜጋ ከሆነው ማህበረሰባችን ጋር ስለሚኖሩ ሁለተናዊ መስተጋብር በልዩ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ትግላችን ማስቀጠል እንዳለብን የጋራ መግባባት ስራ ተሰርቷል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወርዳ ቁጥር 32 በኮለቦና በመርኮታ ሊካሄድ የነበረው የፋሽስቱ ብልፅግና ስብሰባ ተበተነ።
አፋብን ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር በ35ኛ ክፍለ ጦር በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ በኮለቦ ለስብሰባ ከመረሳ በፋሽስቱ እግረኛ ሰራዊት ታጅቦ የመጠዋን የወራዳ ካድሬ በተከፈተበት ተኩስ ያሰበውን አላማ ሳያሳካ ፈርጥጦ እንድመለስ ተደረጓል።
ለምርጫ ቅስቀሳና የባህር በር እናስመልሳለን ወጣቶችን ወደ ስልጠና ግቡ የሚል የውሸት ድስኩር ለመደስኮር አላማ አንግቦ ህዝቡን ለመዋሸት አስቦ የነበረ ቢሆንም ሳያገኝ አይበገሬወቹ 35ኛ ክፍለ ጦር ብትትኑ እንዲወጣ አድርገውታል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ
መጋቢት 6/2018 ዓ ም
ዘጠኝ ኮማንዶዎች ከአመራሮቻቸው ጋር ሆነው የፋሽስቱ አብይ አህመድን ሰራዊት ከድተው የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ!
የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ አካል ከሆነችው 105ኛ ክፍለ ጦር በመክዳት 9 ሆነው በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::
መብረቅ ክፍለ ጦርን ከተቀላቀሉት እነዚህ ኮማንዶዎች መካከል የ105ኛ ክፍለ ጦር የሰው ሐብት ኃላፊ እና መረጃ መሃንዲስ ባለሙያው እንድሁም አንድ የሻንበል መሪ የተካተቱ መሆናቸው ታውቋል::
የመብረቅ ክፍለ ጦርን ክንድ መቋቋም ያቃተው ጠላት እየተፍረከረከ ሲሆን በየጊዜው እየከዳ ወደ ወገን እየመጣ ነው::
የፋኖን የማድረግ አቅም መጠናከርን እና ውስጣዊ አንድነትን ተከትሎ የጠላት ኃይል ተስፋ በመቁረጡ የተነሱ በየዕለቱ እየከዳ መሆኑ ይታወቃል:: አሁንም ከጠላት ጋር ሆናችሁ የአማራ ህዝብን እየወጋችሁ ያላችሁ የመከላከያ፣ አድማ ብተና፣ ፓሊስ እና ሚሊሻ አባላት ዛሬ ነገ ሳትሉ ወደ ወገናችሁ ትቀላቀሉ ዘንድ የምናስታውሳችሁ የትኛውም ኃይል ህዝብን አሸንፎ እንደማያውቅ በማረጋገጥ ጭምር ነው:: ስለዚህ ከተሸናፊው አገዛዝ ጎን ቆማችሁ አላስፈላጊ ዋጋ ከምትከፍሉ ከወድሁ ወደ ወገን እንድትቀላቀሉ የምንላችሁ ህይወታችሁን ማትረፍ ለምትፈልጉት ሁሉ ነው::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም
+4
♦️ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በጠላት ኃይል ላይ ጥቃት ፈጸመች።
ዛሬ 06/2018 ዓ.ም የአፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካል የሆነው ንስር በለሳ ክ/ጦር ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በምስራቅ በለሳ ዳንጎራ ከተባለው ቦታ ላይ ስርዓቱ ጥምር ኃይል ብሎ በሚጠራው ጡት ቆራጭ ቡድን ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
በጥቃቱ ቁጥሩ በእውን የማይታወቅ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ከመደረጉም በላይ አስከሬኑንና ቁስለኛውን ትቶም እንዲፈረጥጥ ተደርጓል።
ብልጽግና ቀጣይ የግንቦት ስርዓታዊ ምርጫን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ተገዶ በፋኖ ጠንካራ ክንድ ተመትቶ የለቀቃቸውን ከተሞች መልሶ ለመቆጣጠር በመላው አማራ አካባቢዎች ያለ የሌለ ኃይሉን አሟጦ በአየር ኃይልና በድሮን በመታገዝ ውጊያዎችን እያደረገ መሆኑ የሚተወቅ ነው።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ
የካቲት 06/2018 ዓ.ም
የአገዛዙን ሻለቃ መሪ በመደምሰስ ብሬን ተማረከ‼️
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆነችው ይታየሁ ብርጌድ አባላት በትናንትናው እለት ከዳባት ወደ ገደብየ ሲንቀሳቀስ በነበረን የአገዛዙ ሀይል ዳራ ላይ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል ።
የይታየሁ ብርጌድ መሪ አርበኛ አስንቆ መኳንት በመራው አፕሬሽን የአገዛዙን ሻለቃ መሪን ጨምሮ 15 የጠላት ሀይል ሲደመሰስ ከ12 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ ቁስል አስተናግደው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።
የአርበኛ አስንቆ መኳንት ወታደራዊ ጥበብና እውቀት በታየበት አውደ ውጊያ ይታየሁ ብርጌድ 1 ብሬን ፣ 5 ክላሽንኮቭ ፣ 10 ቦንብ እንዲሁም በርካታ ተተኳሾች ከአስታጥቄው ብርሃኑ ጁላ ገቢ አድርጋለች ።
አገዛዙ ከገደብየና ዳባት ከተሞች ሀይል ሰባስቦ መልሶ ለማጥቃት ቢሞክርም የራስ አሞራው ሶስተኛ ኮር ሸጋው ውበት ብርጌድ እንዲሁም ሌሎች የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አባላት መከላከል ተችሏል።
አንድነት ሀይልም መዳህኒትም ነው !!!!
©አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
መጋቢት 6/2018 ዓ/ም
