ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

የመልካ ጎራ ት/ቤት መረጃ መስጫ ገፅ(የተማሪ እና የወላጅ)

የመልካ ጎራ ት/ቤት መረጃ መስጫ ገፅ(የተማሪ እና የወላጅ)

الذهاب إلى القناة على Telegram

When Education Goes Right Nothing Can Go Wrong!

إظهار المزيد
812
المشتركون
-624 ساعات
-67 أيام
-1430 أيام
أرشيف المشاركات
ለተማሪዎች ውጤታማ የአጠናን ዘዴዎች! #የጊዜ አያያዝ እና እቅድ ማውጣት 1. የጊዜ ሰሌዳ መዘርጋት - ለእያንዳንዱ ትምህርት ዓይነት የተወሰነ የጥናት ጊዜ መመደብ 2. ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የትምህርት አይነቶችን መለየት 3. እቅድ ማውጣት - መነበብ ያለባቸውን ትምህርቶች በመለየት ዕቅድ ማውጣት #የጥናት አካባቢ 1. ምቹ የጥናት ቦታ መለየት 2. ንጹህ አየር ያለበት ቦታ መምረጥ 3. ጸጥታ የሰፈነበት ቦታ - ከረብሻ ነፃ የሆነ ቦታ መምረጥ 4· ከስልክ እና ሌሎች ትኩረት ከሚሰርቁ ነገሮች መራቅ #የማስታወስ ዘዴዎች 1. ቅድመ-ንባብ - አንድን ምዕራፍ ከማጥናቱ በፊት ጠቃሚ ይዘቶችን መለየት 2. መደጋገም - የተማርነውንና ያጠናነውን ወሳኝ ይዘት እንዳይረሳ በተደጋጋሚ መከለስ 3. ጎላ አድርጎ ማጉላት - ዋና ዋና ነጥቦችን በቀለም ማጉላት 4. የጎን ማስታወሻዎች - በደብተር ዳር አጫጭር ማስታወሻዎችን መጻፍ 5. ማጠቃለያ - ካነበብክ በኋላ በራስህ ሀሳብ በአእምሮ ማጠቃለል 6. ቁልፍ ቃላትን መለየት - አስፈላጊ ቃላትን እና ሀረጎችን መጠቀም 7. ቃላት አሳጥሮ መጠቀም - ለማስታወስ አጫጭር ስሞችን መጠቀም 8. ማስተማር - ከሌሎች ጋር መማማር ትምህርቱን ለማጠናከር ይረዳል 9. የማስታወሻ ቦታ ዘዴ - ነገሮችን በቀላሉ ለመያዝ ከቦታዎች ጋር ማዛመድ 10. ተረት መፍጠር - በቀላሉ ለማስታወስ መረጃዎችን በተረት መልክ መያዝ #ንባብ እና ጽሑፍ 1. ቅድመ-ንባብ - አንድን ምዕራፍ ከማጥናቱ በፊት ወሳኙን ይዘት መለየት 2. ያለፉ ፈተናዎችን መለማመድ - የቀድሞ ፈተናዎችን በመስራት ልምምድ ማድረግ 3. ጎላ አድርጎ መፃፍ - ዋና ዋና ነጥቦችን በቀለም በጉልህ መፃፍ 4. ማጠቃለያ መጻፍ - ካነበብክ በኋላ በራስህ ሀሳብና ቃል ማጠቃለል #የቡድን ጥናት 1. የጥናት ቡድን መመስረት - ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን መወያየትና መጠያየቅ 2. የጥያቄ እና መልስ ክፍለ ጊዜ - እርስ በርስ መጠያየቅ 3. የቡድን አብሮ መስራት - አብሮ በመስራት መማማር 4. መምህራንን መጠየቅ - ያልተረዳህን ነገር መጠየቅ 5. የፈተና መረጃዎችን መለዋወጥ - ከሌሎች ተማሪዎች ጋር መረጃ መለዋወጥ #ፈተና ለመፈተን ዝግጅት 1. አስቀድሞ መጀመር - በፈተና ቀን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ 2. ዘና ማለት - በፈተና ወቅት መረጋጋት እና ጥያቄዎችን በጥንቃቄ ማንበብ 3. ጭንቀትን ማስወገድና ዘና ማለት #ጤና እና ደህንነት 1. በቂ እንቅልፍ መተኛት 3. የአካል እንቅስቃሴ - በየቀኑ ትንሽ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ 4. ውሃ መጠጣት - በቂ ውሃ መጠጣት ለአዕምሮ ትኩረት ይረዳል 5. አጭር ዕረፍት - በማጥናት መካከል አጭር ዕረፍት ማድረግ

Repost from N/a
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ነገ ሰኞ ይከበራል፡፡
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ነገ ሰኞ ይከበራል፡፡

የሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ። ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህ/ ተ/ም/ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል። በዚህም መሰረት፦ 1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 3. አቶ አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር 4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር 5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር 6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር 7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር 8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር 9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር 10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር 11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር 12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር 13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር 14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር 15. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር 16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር 17. አቶ ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር 18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር 19. አቶ ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር 20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር 22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር 23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻እንኳን ለ2019 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ።🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ያሸጋገረን ፈጣሪ ሀዘናችንን ወደ ደስታ ይለውጥልን! ድከማችንን ወደ ውጤት ይቀይርልን! 💪ጭንቀታችንን ይይልን 💪ችግራችንን ይሙላልን 💪የምንፈልገው ይሳካልን 💪ደስታ በደስታ ያጎናፅፈን 💪ይሄው ስለቴ ሰመረ ለማለት ያብቃን። ከመምህር ታዬ❤️ 🏵️🏵️🏵️🏵️መልካም አዲስ ዓመት🏵️🏵️🏵️🏵️

telebirr 2,000 ብር እየሰጠ ነው 😳 እኔ አሁን ተቀብዬዋለሁ፣ አንተም ደርሶህ እንደሆነ ተመልከት እዚህ ጠቅ አድርግ 👇 https://uiee.jghxa.xyz/cHWI/?p=t&gver=1

telebirr 2,000 ብር እየሰጠ ነው 😳 እኔ አሁን ተቀብዬዋለሁ፣ አንተም ደርሶህ እንደሆነ ተመልከት እዚህ ጠቅ አድርግ 👇 https://uiee.jghxa.xyz/cHWI/?p=t&gver=1

ጎበዝ ተማሪ የመሆን ዋና ዋና አበይት ነጥቦች ጎበዝ እና ውጤታማ ተማሪ መሆን ድንገት የሚመጣ አጋጣሚ ሳይሆን፣ የትክክለኛ ልማዶች፣ የጽናት እና የጥሩ ስልት ውጤት ነው። ​በጥናት እና በተግባር የተረጋገጡ ጎበዝ ተማሪ የመሆን ዋና ዋና ሚስጥሮች የሚከተሉት ናቸው። ​1. የማጠናት ስልትን ማሻሻል (Smart Study strategy) ​በሰንጠረዥ ማናት (Time Blocking): ዋና ዋና የሚባሉትን አበይት ነጥቦች እጥር ምጥን ባለ መልኩ ለይቶ ማውጣት በየቀኑ ለጥናት የሚሆን የተወሰነ ሰዓት መመደብ፤ በጥናት መካከልም አጭር የዕረፍት ጊዜ መውሰድ(ለምሳሌ፦ 25 ደቂቃ አጥንቶ ለ5 ደቂቃ) ማረፍ። ​ንቁ ተሳትፎ (Active Recall): ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። ያነበብነውን መጽሐፍ ዘግተን "ምን ተረዳሁ?" ብለን ራሳችንን መጠየቅ፣ ወይም ማስታወሻ ሳናይ ራስን መፈትን። ​ለሌላ ሰው ማስረዳት (Feynman Technique): ያጠናነውን ርዕስ ለጓደኛችን ወይም ለራሳችን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳትም ሆነ ለመረዳት መሞክር። ጽንሰ-ሐሳቡን ምን ያህል ጠልቀን መረዳታችንን ለማወቅ የተሻለው መንገድ ይህ ነው። ​2. ክፍል ውስጥ ንቁ መሆን ​ከፊት መቀመጥና ማስታወሻ መያዝ: ባብዛኛው የምንረዳው ክፍል ውስጥ እንደመሆኑ መጠን አስተማሪው የሚናገረውን/የሚያስረዳውን  በአጭር በአጭሩ መያዝ። ​ጥያቄ መጠየቅ: ያልገባንን ነገር ወዲያውኑ አስተማሪያችንን ወይም ጓደኞቻችንን ጠይቀን መረዳትና የሚጠየቁ ጥያቄዎችን አለማከማቸት። ​3. ጊዜን በአግባቡ መያዝ (Time Management) ​ዛሬ የሚሰራውን ለነገ አለማስተላለፍ: የቤት ሥራዎችን፣አሳይመንቶችንና እና ፕሮጀክቶችን በተሰጠው ቀን መጀመርና ሰርቶ ማጠናቀቅ ከፈተና በፊት የሚፈጠርን ጭንቀት ይቀርፋል። ​ቅደም ተከተል ማውጣት: አስቸጋሪ ወይም ትኩረት የሚሹ ትምህርቶችን አእምሯችን ሳይደክም ጠዋት ወይም በጥናታችን መጀመሪያ ላይ ማጠናቀቅ። ቤተ መፅሀፍ ገብተን የምናነብበትን ጊዜ፣ የተለያዩ ትምህርቶችን መለማመጃ/መዘጋጃ ጥያቄዎችን የምንሰራበትን ጊዜ መመጠን ይኖርብናል። ​4. የአኗኗር ዘይቤ እና የአእምሮ ዝግጅት ​በቂ እንቅልፍ ማግኘት: አእምሮ ያጠናውን ነገር መዝግቦ የሚይዘው እና የሚያድሰው በእንቅልፍ ወቅት ነው (በቀን ከ7–8 ሰዓት እንቅልፍ አስፈላጊ ነው)። ​ጤናማ ምግብ እና እንቅስቃሴ: የተመጣጠነ ምግብ መመገብና አካላዊ ጤንነት ለንቁ አእምሮ መሰረት ናቸው። ​አዎንታዊ አስተሳሰብ (Growth Mindset): "አልችልም" ከማለት ይልቅ "በደንብ ካጠናሁና ከተለማመድኩ እችላለሁ" የሚል እምነት ሊኖረን ይገባል። በአጠቃላይ ጎበዝ ተማሪ ማለት በቀን 24 ሰዓት የሚያጠና ሳይሆን፣የሚያጠናበትን ሰዓት በአግባቡና በትኩረት የሚጠቀም ነው።

Never !!! ወላጆች ልጆቻችሁን . . . 1. በፍጹም ከሌላ ልጅ ጋር (ከእህት ወንድሞቻቸውም ጭምር) በማነጻጸር አትናገሯቸው - ወደ ፊት የሰዎች የተቀባይት ማረጋገጫ (approval) እንደፈለጉ
Never !!! ወላጆች ልጆቻችሁን . . . 1.  በፍጹም ከሌላ ልጅ ጋር (ከእህት ወንድሞቻቸውም ጭምር) በማነጻጸር አትናገሯቸው - ወደ ፊት የሰዎች የተቀባይት ማረጋገጫ (approval) እንደፈለጉ የመኖር ሕይወት ውስጥ ይገባሉ፡፡ 2.  በፍጹም ደካማ ጎናቸውን በማጉላት አትጨቅጭቋቸው - ወደ ፊት ስህተት ይገኝብኝና ሰዎች ይፈርዱብኛል ወደሚል ሕይወት ውስጥ ይገባሉ፡፡ 3.  በፍጹም ስሜታቸውን ሲገልጹ አታፍኗቸው - ወደ ፊት ሁሉን ነገር በውስጣቸው በመሸከም የመጎዳት ሕይወት ውስጥ ይገባሉ፡፡ 4.  በፍጹም አንዳንድ ተግባራቸውን የመከልከልና የመፍቀድ የሚጋጭ መልእክት አታስላፉላቸው - ወደ ፊት ሕግ ተላልፈው እንኳን ሊታለፉና ዝም ሊባሉ ወደማሰብ ሕይወት ውስጥ ይገባሉ፡፡ 5.  በፍጹም ስህተት እንዳይሰሩ በማለት ከላይ ከላዩ አትቆጣጠሯቸው - ወደ ፊት ስህተትን በመፍራት በፍጹም የማይንቀሳቀስ ሕይወት ውስጥ ይገባሉ፡፡ 6.  በፍጹም ጥሩ ሲሰሩ “እወድሃለው”፣ ሲሳሳቱ ደግሞ “አልወድህም” አትበሏቸው - ወደ ፊት ሰዎች እንዳይጠሏቸው ካመኑበት የሕይወት መስመር የመውጣት ሕይወት ውስጥ ይገባሉ፡፡

Repost from N/a
[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]
👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል። 👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። 👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ። 👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው። 👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው። 👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ። 👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ተማሪ እንዳይመለከቱ እንዳይኮርጁ  መቆጣጠር አለባቸው። 👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል። 👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። 👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 30 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም። 👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ

የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች፣ ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ
+1
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች፣ ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡ ➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ ⓫ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ ⓬ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም። ⓭ በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን።