cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

E-LMIS - ብቁ

ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
58 445
المشتركون
+6824 ساعات
+4197 أيام
+1 05530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
🌏✨በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት E-LMIS የተመዘገቡ ሰራተኞች ቁጥር አንድ ሚሊየን ደርስዋል!! በብዙ የሥራ እድሎች፣ የሥልጠና፣ የውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት እና በሲስተሙ ውስጥ በተካተቱ ከሃያ ሁለት በላይ አገልግሎቶች የተገነባው በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ስር የለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት E-LMIS ድህረገጽ ላይ አንድ ሚሊየን ሰራተኛ ተመዝግቧል። በዚህ ሥርዓት የተመዘገቡ ሰራተኞች በቀጣይ አመታት የሚመጡ የሥራ እድሎችን፣ሥልጠናና ድጋፎች ተጠቃሚ በመሆን በሥራቸው ሥኬታማ በገቢያቸውም የተሻሉ መሆን የሚችሉበትን እድል ይጠቀማሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሥራ መረጃ ሥርዓት ለማዘመን እና የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ እንዲሁም የገቢ ደረጃን ለማሳደግ በምንገነባው የዲጂታል ሥርዓት ሥራችንን ተመልክታችሁ አብራችሁን ወደ ለውጡ መርከብ ለተሳፈራችሁ አንድ ሚሊየን ተመዝጋቢዎች ምስጋናችንን እናቀርባለን። በቀጣይም በጣም ባጠረ ግዜ ቀጣይ እቅዶቻችንን እያሳካን የጨባጭ ሥኬቶችን እንደምናሳይ አንጠራጠርም። በዚህ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ያልተመዘገባችሁ ዛሬውኑ በመመዝገብ የእድሉን መጠቀም ትችላላችሁ! ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ! የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት! ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et 👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836 📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/ 💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1 📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/
إظهار الكل...
👍 137 25😁 24👏 13🤷‍♂ 8🥰 5🔥 3🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
🌍🌟በምርትዎ ወይም አገልግልዎትዎ የሚተማመኑ ከሆነ ለትርፋማነትዎ ወደ E-LMIS ይምጡ አምራቾች ወይም አገልግሎት ሰጪዎች በምርታቸው ወይም አገልግሎታቸው የሚተማመኑ ከሆነ ወደ ብዙሃኑ ማህበረሰብ ተደራሽ ለመሆን እና ትርፋማነትን ለማረጋገጥ ትክክለኛውን ቦታ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል ለዚህም በስራና ክህሎት ሚኒስትር የለማው የኢትዮጲያ ስራ ገበያ መረጃ ስርዓት በሉሲ ገበያ ፕላትፎርም ድርጅትዎን ማስተዋወቅ እና ተደራሽነትዎን ማስፋት የሚችሉበትን እድል አቅርብዎልዎታል ጥራት ያላቸው ምርቶች እና አገልግሎቶችን ማግኘት ማን ይጠላል ሸማቹም ሆነ አገልግሎት ፈላጊው ወደ ሉሲ ገበያ ያምራል እርስዎም አለኝ የሚሉትን ይዘው ይቅረቡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት! ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ! ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et 👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836 📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/ 💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1 📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/ 🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q
إظهار الكل...
👍 38 2😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
✨🌏ብዙ ሥራዎችን በአንድ ድህረ-ገጽ!! ሥራ አጥነትን ለመቀነስ ብሎም ዜጎች ባላቸው ችሎታና አቅም መጠን መስራት ወይም ያላቸውን ሸጠው ማግኘት የሚችሉበትን እድል ማመቻቸት የእለት ተእለት ሥራችን ነው። በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ከሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ ያሉ ብዙ የሥራ አማራጮችን በአንድ ድህረገጽ የዜጎችን ሥራ ለመፈለግ ያለውን ድካምና መጉላላት ለማስቀረት አሰባስቦ በስልክ አልያም በኮምፒውተር በመጠቀም ከቤታችን ሆነን መስራት የምንችልበትን ማራጭ አቅርቦልናል። በE-LMIS- ብቁ ድህረገጽ ተመዝግበው የህይወትዎን ቀና መንገድ ይጀምሩ! የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት! ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ! ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et 👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836 📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/ 💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1 📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/ 🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q
إظهار الكل...
👍 135 37😁 16🤷‍♂ 10😢 9🔥 6😎 4🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
"ህጋዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት እያለ ህገወጥ መንገድን የሚመርጥ አይኖርም!" ክብርት ሙፈሪያት ካሚል
إظهار الكل...
👍 42 6😭 3🤷‍♂ 2🔥 2🤔 2😁 1🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌏✨ ሥራ ለመፈለግ ብዙ መድከም ቀረ! "ሥራ ፍለጋ ተንከራተንም አልሞላልንም" የሚል ልምድና እውቀት ያለው ሰው ማየት በጣም ከባድ ነው። አሁን ሥራ ለመፈለግ መንከራተት፣ አግኝቶም በአነስተኛ ገቢ ማማረር የሚቀርበትን የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ማወቅ የግድ ይልዎታል። ብዙ ሥራዎች በአንድ ድህረ-ገፅ ከሃገር ውስጥም ከሃገር ውጭም ተሰባስበው የሚገኙበት የደህንነት፣ የመብት እና የክብርዎ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የማይገባበት ሰፊ ስርዓት አለ። ይህም በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት E-LMIS- ብቁ ሲሆን በዚህ ሥርዓት ስር ከሃያ ሁለት በላይ አገልግሎቶች አሉ ከነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ National Job Portal አንዱ ሲሆን በሃገር ውስጥ እና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሥራዎችን በአንድ ላይ አሠባስብዎ ለእርስዎ እንደ ክህሎት እና እውቀትዎ ሠርተው ገቢዎን ማሳደግ የሚችሉበትን እድል አመቻችቶ የያዘ ነው። በዚህ ህይወት ቀያሪ የገበያ መረጃ ሥርዓት ይመዝገቡ የሥኬት መንገድዎን ያረጋግጡ! ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ  :https://lmis.gov.et 👍 ፌስቡክ  : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836 📸 ኢንስትግራም፡  https://www.instagram.com/bequ.elmis/ 💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1 📢 ሊንክደን   : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/ 🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q
إظهار الكل...
👍 220😭 54 37😁 24🤔 15 14🤷‍♂ 12🔥 12💊 11👏 8👀 5
Photo unavailableShow in Telegram
"የሥራ ዕድልን ከዳቦ በላይ በሚል ተልዕኮ የሚፈጠሩ የሥራ እድሎች ከእለት ጉርስ አልፈው ሃብት ማካበቻ እንዲሆኑ ድጋፍ እናደርጋለን!" ክብርት ሙፈሪያት ካሚል
إظهار الكل...
356👍 181😁 71 52🥰 17🤔 15🕊 15👏 12👻 11🤷‍♂ 9🙉 9
Photo unavailableShow in Telegram
ለ270 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል ተፈጠረ ***** (ኢ ፕ ድ) የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት እየተሠራ ባለው ተግባር እስከ መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ270 ሺህ ለሚሆኑት ዜጎች በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አለቃ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት እየተሠሩ ባሉት ሥራዎች በበጀት ዓመቱ እስከ መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስም ለ270 ሺህ ዜጎች በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። በ2016 በጀት ዓመት በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የሥራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፤ እየተሠራ ካለው ሥራም አንዱ ዜጎችን በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት ሄደው መብታቸው ተጠብቆላቸው ሥራ ሠርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህም እስካሁን ድረስ ለ270 ሺህ ለሚሆኑት ዜጎች በውጭ ሀገራት..... ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124313 ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼️
إظهار الكل...
👍 443 111😁 74🤷‍♂ 64🤔 31👻 21❤‍🔥 18🌚 16🏆 16💊 11🤯 9
Photo unavailableShow in Telegram
🌏✨ለሥራ ወደ ውጪ ሃገር መሄድ ቀላልና ከስጋት የፀዳ እንደሆነ አውቀዋል? ከዚህ ቀደም በውጪ ሃገራት ለሥራ መሰማራት፣ በሰላም ሰርቶ መለወጥ፣ በደህና ለሃገር መብቃት የእድል ጉዳይ ነበር። አሁን ግን ታሪክ ተቀይሮ የትኛውም ዜጋ ከሃገር ውጪ ደህንነቱ፣ ክብሩ እና መብቱ ተጠብቆ ሰርቶ መለወጥ የሚችልበት መንገድ ቀርቦለታል። ይህም በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት E-LMIS- ብቁ ከሃገር ውስጥ እስከ መዳረሻ ሃገሮች በተዘረጋው ኔትዎርክ አንድም ዜጋ የመብት ጥሰት ሳይፈፀምበት በአግባቡ ተከፍሎት ከአሰሪው ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዳለው ተረጋግጦ ሰርቶ ተለውጦ ለቤተሰብና ሃገር መትረፍ የሚችልበትን ዕድል ለሠሪው ዜጋ አቅርቧል። የእርስዎ ድርሻ ተመዝግቦ የባዮሜትሪክስ መረጃ ሰጥቶ እድሉን መጠቀም ነው። ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ :https://lmis.gov.et 👍 ፌስቡክ : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836 📸 ኢንስትግራም፡ https://www.instagram.com/bequ.elmis/ 💼 ቴሌግራም ፡ https://t.me/bequelmis1 📢 ሊንክደን : https://www.linkedin.com/company/86463026/admin/feed/posts/ 🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7 ብቁ ሰራተኛ:ብቁ ቀጣሪ:ብቁ ውሳኔ ሰጪ የሥራ ባለቤት እርሶ ኖት!
إظهار الكل...
👍 90 9🤨 7🕊 6💊 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ተስፋን ማየት የሚናፍቁ ወጣቶች ላሉበት ሃገር ቀልጣፋና ትጉህ አገልጋይ ከሆን ዓላማችንን ማሳካት አይከብደንም!" ክብርት ሙፈሪያት ካሚል
إظهار الكل...
104👍 36😁 15👏 8🕊 6
"ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ277 ሺህ ዜጎች የውጭ አገር የስራ ስምሪት እድል ተፈጥሯል-የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር ****** (ኢ ፕ ድ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ277 ሺህ ዜጎች የውጭ አገር የስራ ስምሪት እድል መፈጠሩን የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት አስተባባሪ ብርሃኑ አለቃ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ዜጎች ደህንነታቸው፣ መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ በውጭ አገራት የስራ እድል እንዲያገኙ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ለዚህ ደግሞ መንግስት ከተለያዩ አገራት ጋር ስምምነት መፈራረሙን ተናግረው፤ ለአብነትም ከሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ጆርዳን እና ሊባኖስ ጋር ሕጋዊ የሥራ ሥምሪት ሥምምነት መፈረሙን ጠቅሰዋል፡፡ የስራ ስምሪት መረጃዎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ እየተመሩ መሆኑንም ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የሥራ ገበያን ዲጂታል በሆነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል አንድ የዳታቤዝ ማዕከል ተገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡ መንግስት ከመዳረሻ አገራት ጋር ያደረገው የሁለትዮሽ ስምምነቶች የዜጎችን ደኅንነትና መብት ከማስጠበቅ ባሻገር መልካም የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረጉንም አንስተዋል፡፡ በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ለ277 ሺህ ዜጎች የውጭ አገር የስራ ስምሪት እድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡ ህጋዊ የስራ ስምሪቱ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመምራት የተከናወኑ ስራዎች ህገ-ወጥ ደላሎችን በመከላከል ረገድ ማሻሻል እንዲመጣ ማድረጉንም ነው የገለጹት፡፡ በዚህም በቴክኖሎጂ በመታገዝ በህገወጥ መንገድ ዜጎችን የሚያዘዋውሩ ደላሎችን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
إظهار الكل...
👍 313 82🤔 54😁 39🔥 11🥰 10🤯 7🤷 3