Arsho Medical Laboratories | አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
الذهاب إلى القناة على Telegram
6 146
المشتركون
+1624 ساعات
+607 أيام
+25030 أيام
أرشيف المشاركات
What does "Occult" mean?
In medicine, it simply means hidden.
FOBT (Fecal Occult Blood Test) is a highly sensitive lab test that detects microscopic blood in stool completely invisible to the naked eye.
⚠️ When is it recommended?
Your doctor may order an FOBT if you have:
Persistent abdominal pain/cramping
Unexplained weight loss or chronic fatigue
Sudden bowel habit changes (diarrhea/constipation)
Unexplained anemia (low iron)
🔬 What do results mean?
✅ Positive Result: Bleeding in the digestive tract. Common causes include hemorrhoids, ulcers, polyps, or IBD.
⚠️ False Positive: Can occur if you eat red meat, raw vegetables (broccoli/turnips), or take NSAIDs within 3 days of the test.
Don't wait for loud symptoms. Catch hidden warning signs early.
Arsho Medical Laboratories
Trusted by generation!
📞 Call us at 612
🌐 Website: www.arsholab.com
"ኦከልት" ምን ማለት ነው?
በህክምናው አለም "ኦከልት" ማለት የተደበቀ ወይም በዓይን በቀላሉ የማይታይ ማለት ነው።
Fecal Occult Blood Test በዓይን ሊታይ የማይችል፣ በሰገራ ውስጥ የተደበቀ ጥቃቅን ደምን ለመለየት የሚያገለግል የላብራቶሪ ምርመራ ነው።
⚠️ ምርመራው መቼ ይታዘዛል?
* የማይጠፋ የሆድ ህመም ወይም ቁርጠት
* ምክንያቱ ያልታወቀ የክብደት መቀነስ ወይም ከፍተኛ የድካም ስሜት
* ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት
* ምክንያቱ ያልታወቀ የደም ማነስ ሲያጋጥም
ይታዘዛል
🔬 የምርመራው ውጤት ምን ያሳያል?
✅ ፖዘቲቭ ከሆነ፦በምግብ መፈጨት ሥርዓትዎ ውስጥ የደም መፍሰስ መኖሩን ያሳያል። የተለመዱት መንስኤዎች ኪንታሮት (Hemorrhoids)፣ የጨጓራ ወይም አንጀት ቁስለት (Ulcers)፣ ፖሊፕ (Polyps) ወይም የአንጀት መቆጣት (IBD) ሊሆኑ ይችላሉ።
⚠️ False Positive፦ አንዳንድ ጊዜ በትክክል ደም ሳይኖር፣ ከምርመራው 3 ቀን በፊት ጥሬ ሥጋ፣ አትክልቶችን (እንደ ብሮኮሊ ወይም ቀይ ስር) በመመገብዎ ወይም የህመም ማስታገሻዎችን በመውሰድዎ ምክንያት ውጤቱ በስህተት ፖዘቲቭ ሊመጣ ይችላል።
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የ ታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድህረ-ገጽ፡ www.arsholab.com
⏳ Your future self is watching you right now. What choices are you making for them?
We plan our careers, our vacations, and our finances down to the last detail. But how often do we proactively plan our health?
The truth is, a vibrant and healthy future isn’t a matter of luck, it’s an investment you make today. Major health issues don't always give a warning sign, but a routine health checkup does. It gives you a clear picture of your body's current state so you can prevent tomorrow's problems before they start.
Whether it’s managing stress, sleeping better, staying active, or eating right, it all starts with knowing where you stand.
Your health can't wait for a "better time." Take control of your tomorrow, today.
Book your General Health checkup with Arsho Medical Laboratories.
Arsho Medical Laboratories
Trusted by generation!
📞 Call us at 612
🌐 Website: www.arsholab.com
⏳ የወደፊት ሕይወትዎ የአሁኑ ውሳኔዎ ውጤት ነው። ዛሬ ለእራስዎ ምን ዓይነት ምርጫ እያደረጉ ነው?
የሙያ ጉዟችንን፣ የእረፍት ጊዜያችንን እና የፋይናንስ ሁኔታችንን በዝርዝር እናቅዳለን፤ ነገር ግን ለጤናችን የምንሰጠው ቅድሚያ ትኩረት ምን ያህል ነው?
እውነታው ግን፣ አስተማማኝ እና ሙሉ ጤንነት በአጋጣሚ የሚገኝ ሳይሆን ዛሬ በጤናዎ ላይ የሚያደርጉት መዋዕለ ንዋይ (investment) ነው። አብዛኛዎቹ የጤና እክሎች አስቀድመው ምንም ዓይነት ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ፤ የዘወትር የጤና ምርመራ ግን ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመለየት ያስችላል። ይህም ሊገጥሙ የሚችሉ የጤና እክሎችን ገና ሳይጀምሩ ቀድመው ለመከላከል የሚያስችልዎትን ትክክለኛ የሰውነትዎን ወቅታዊ ቁመና ያሳየዎታል።
ውጥረትን መቆጣጠር፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ ሁሉም ነገሮች የሚጀምሩት አሁን ያሉበትን የጤና ደረጃ በትክክል በመረዳት ነው።
ጤናዎ "ምቹ ጊዜ" እስኪመጣ ድረስ የሚዘገይ ጉዳይ አይደለም። የነገ ጤንነትዎን ዛሬውኑ ያረጋግጡ።
የ አጠቃላይ የጤና ምርመራዎን (General Health Checkup) በአርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪዎች ያስይዙ።
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የ ታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድህረ-ገጽ፡ www.arsholab.com
🧪 BEFORE YOU COME TO THE LAB... READ THIS! 👀
Here is how to prepare for common laboratory tests:
🔹 Fasting Blood Sugar (FBS): Strict fasting no food or drinks except plain water for 8–12 hours. Drinking water is encouraged to stay hydrated.
🔹 Lipid Profile( Total Cholesterol,LDL Cholesterol,HDL,Cholesterol,Triglycerides): Requires 9–12 hours of fasting. Always follow the specific timeline provided by your physician or the laboratory.
🔹 Cortisol: Timing is critical. Samples are usually collected in the early morning typically around 8:00 AM when levels peak.
🔹 Oral Glucose Tolerance Test (OGTT): Requires initial fasting. During the multi-hour testing period, you must remain at rest avoid eating, drinking, smoking, or physical exertion.
🔹 Prolactin: Best collected 2 to 3 hours after waking up. Ensure you are fully relaxed, as stress and physical exercise can artificially elevate results.
🔹 PSA (Prostate-Specific Antigen): Avoid ejaculation for 24–48 hours prior to the blood draw, as this can temporarily raise antigen levels.
🔹 Urine Culture: Collect a "clean-catch, midstream" sample using the designated protocol to avoid external contamination.
🔹 Stool Occult Blood Test: Certain medications and dietary choices like red meat can cause false positives.
💡 Important: Always inform the laboratory clinicians about any medications, supplements, vitamins, or recent illnesses before your sample is collected.
Arsho Medical Laboratories
Trusted by generation!
📞 Call us at 612
🌐 Website: www.arsholab.com
የላብራቶሪ ምርመራዎች ለማድረግ ከመምጣታችን በፊት እንዴት ተዘጋጅተን እንምጣ?፦
🔹በባዶ ሆድ የሚሰጥ የስኳር ምርመራ ፦ ከንጹሕ ውሃ በስተቀር ከ8-12 ሰዓታት ምንም ዓይነት ምግብ ወይም መጠጥ አይፈቀድም።
🔹 የስብ መጠን ምርመራ (Total Cholesterol,LDL Cholesterol,HDL,Cholesterol,Triglycerides)፦ ከ9 እስከ 12 ሰዓታት ምግብ አለመመገብ ይጠይቃል።
🔹 ኮርቲሶል ፦ የምርመራ ሰዓቱ በጣም ወሳኝ ነው። የሆርሞኑ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጨምርበት ጊዜ ማለትም ማለዳ ላይ ብዙውን ጊዜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ ናሙናው ይሰበሰባል።
🔹 Oral Glucose Tolerance Test (OGTT)፦ ለብዙ ሰዓታት በሚወስደው የምርመራ ወቅት ሙሉ በሙሉ ማረፍ አለብዎት ከመብላት፣ ከመጠጣት፣ ከማጨስ ወይም ከአካላዊ እንቅስቃሴ መቆጠብ ያስፈልጋል።
🔹 ፕሮላክቲን ከእንቅልፍዎ ከነቁ ከ2 እስከ 3 ሰዓታት በኋላ ቢመረመር ይመረጣል። ውጥረት እና አካላዊ እንቅስቃሴ ውጤቱን ያለአግባብ ከፍ ሊያደርጉት ይችላሉ።
🔹 ፒ.ኤስ.ኤ ፦ ከደም ምርመራው በፊት ለ24–48 ሰዓታት ያህል የዘር ፈሳሽ ከማፍሰስ ይቆጠቡ፤ ምክንያቱም ይህ የውጤቱን መጠን ሊጨምር ስለሚችል።
🔹 የሽንት culture ምርመራ፦
መጀመሪያ ላይ የሚፈሰው ሽንት በብልት አካባቢ ባሉ ተፈጥሯዊ ባክቴሪያዎች ሊበከል ስለሚችል፣ የመጀመሪያውን ጥቂት ሽንት ወደ መጸዳጃ ቤት ማፍሰስ ያስፈልጋል። ከዚያም በመሃል የሚመጣውን ሽንት በንጹሑ የናሙና ዕቃ ውስጥ መጨመር።
🔹 Stool Occult Blood Test፦ አንዳንድ መድኃኒቶች እና እንደ ቀይ ሥጋ ያሉ የምግብ ምርጫዎች የተሳሳተ አዎንታዊ ውጤት ሊያሳዩ ስለሚችሉ ናሙና ከመስጠቶ በፊት ጤና ባለሞያ ያማክሩ።
💡 ናሙናዎ ከመወሰዱ በፊት ማንኛውንም እየወሰዱ ያሉትን መድኃኒቶች፣ ቪታሚኖችን ወይም በቅርብ ጊዜ ያጋጠመዎት ሕመም ካለ ለላብራቶሪ ባለሙያዎች ያሳውቁ።
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የ ታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድህረ-ገጽ፡ www.arsholab.com
የላብራቶሪ ምርመራዎች ለማድረግ ከመምጣታችን በፊት እንዴት ተዘጋጅተን እንምጣ?፦
🔹በባዶ ሆድ የሚሰጥ የስኳር ምርመራ ፦ ከንጹሕ ውሃ በስተቀር ከ8-12 ሰዓታት ምንም ዓይነት ምግብ ወይም መጠጥ አይፈቀድም።
🔹 የስብ መጠን ምርመራ (Total Cholesterol,LDL Cholesterol,HDL,Cholesterol,Triglycerides)፦ ከ9 እስከ 12 ሰዓታት ምግብ አለመመገብ ይጠይቃል።
🔹 ኮርቲሶል ፦ የምርመራ ሰዓቱ በጣም ወሳኝ ነው። የሆርሞኑ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጨምርበት ጊዜ ማለትም ማለዳ ላይ ብዙውን ጊዜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ ናሙናው ይሰበሰባል።
🔹 Oral Glucose Tolerance Test (OGTT)፦ ለብዙ ሰዓታት በሚወስደው የምርመራ ወቅት ሙሉ በሙሉ ማረፍ አለብዎት ከመብላት፣ ከመጠጣት፣ ከማጨስ ወይም ከአካላዊ እንቅስቃሴ መቆጠብ ያስፈልጋል።
🔹 ፕሮላክቲን ከእንቅልፍዎ ከነቁ ከ2 እስከ 3 ሰዓታት በኋላ ቢመረመር ይመረጣል። ውጥረት እና አካላዊ እንቅስቃሴ ውጤቱን ያለአግባብ ከፍ ሊያደርጉት ይችላሉ።
🔹 ፒ.ኤስ.ኤ ፦ ከደም ምርመራው በፊት ለ24–48 ሰዓታት ያህል የዘር ፈሳሽ ከማፍሰስ ይቆጠቡ፤ ምክንያቱም ይህ የውጤቱን መጠን ሊጨምር ስለሚችል።
🔹 የሽንት culture ምርመራ፦
መጀመሪያ ላይ የሚፈሰው ሽንት በብልት አካባቢ ባሉ ተፈጥሯዊ ባክቴሪያዎች ሊበከል ስለሚችል፣ የመጀመሪያውን ጥቂት ሽንት ወደ መጸዳጃ ቤት ማፍሰስ ያስፈልጋል። ከዚያም በመሃል የሚመጣውን ሽንት በንጹሑ የናሙና ዕቃ ውስጥ መጨመር።
🔹 Stool Occult Blood Test፦ አንዳንድ መድኃኒቶች እና እንደ ቀይ ሥጋ ያሉ የምግብ ምርጫዎች የተሳሳተ አዎንታዊ ውጤት ሊያሳዩ ስለሚችሉ ናሙና ከመስጠቶ በፊት ጤና ባለሞያ ያማክሩ።
💡 ናሙናዎ ከመወሰዱ በፊት ማንኛውንም እየወሰዱ ያሉትን መድኃኒቶች፣ ቪታሚኖችን ወይም በቅርብ ጊዜ ያጋጠመዎት ሕመም ካለ ለላብራቶሪ ባለሙያዎች ያሳውቁ።
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የ ታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድህረ-ገጽ፡ www.arsholab.com
🦠 Hepatitis C: The Silent Liver Killer
Imagine a virus living in your body for 20 years with zero symptoms. That is Hepatitis C (HCV). By the time you feel sick, it may have already caused cirrhosis or liver cancer.
The good news? It is curable if caught early.
🚨 How It Spreads
HCV spreads strictly through blood-to-blood contact:
* Sharing needles or syringes.
* Unsafe medical/dental procedures or unsterilized equipment.
* Unscreened blood transfusion.
Early Stage symptoms
Often invisible, but can appear 1–3 months after exposure
Fatigue, Jaundice, Nausea & Appetite Loss,Abdominal Pain, Dark Urine & Clay-Colored Stools
🔸 Chronic Symptoms
Appear years later only after liver damage (cirrhosis) sets in:
Easy Bleeding & Bruising, Fluid Buildup ,Unexplained Weight Loss, Severe Itchy Skin,Confusion & Drowsiness.
🧪 The Diagnosis
1️⃣ HCV Antibody Test (Screening): Checks if you have ever been exposed. (Takes up to 12 weeks after exposure to show up).
2️⃣ HCV RNA Test (PCR/Confirmatory):
Checks if the virus is active right now (Detects the virus within 2 weeks. Positive = current infection).
If you’ve had a risk exposure, don't wait for symptoms.
Get tested, get cured.
Arsho Medical Laboratories
Trusted by generation!
📞 Call us at 612
🌐 Website: www.arsholab.com
🦠 ሄፓታይተስ ሲ፦ ድምፅ አልባው የጉበት ገዳይ
አንድ ቫይረስ በሰውነትዎ ውስጥ ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ ለብዙ ዓመታት ያህል እየኖረ እንደሆነ ያስቡት። ሄፓታይተስ ሲ እንዲህ ዓይነት ቫይረስ ነው። የበሽታው ስሜት መታየት በሚጀምርበት ጊዜ፣ ቫይረሱ የጉበት ጠባሳ ወይም የጉበት ካንሰር አስከትሎ ሊሆን ይችላል።
ጥሩው ነገር በሽታው በጊዜ ከተደረሰበት መዳን የሚችል መሆኑ ነው።
🚨 እንዴት ይሰራጫል?
የሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ የሚሰራጨው በደም ንክኪ ነው፦
* ስለታማ ነገሮችን በጋራ መጠቀም።
* ደህንነቱ ባልተጠበቀ የሕክምና ሂደት ወይም ያልተጸዱ መሣሪያዎች መጠቀም።
* ምርመራ ያልተደረገለት ደም በደም ልገሣ መውሰድ።
የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶች
እነዚህ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ በግልጽ አይታዩም። ነገር ግን ለቫይረሱ ከተጋለጡ ከ1 እስከ 3 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊከሰቱ ይችላሉ፡
ከፍተኛ የድካም ስሜት
የዓይን ወይም የቆዳ ቢጫ መሆን
የማቅለሽለሽ ስሜት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ
የሆድ ህመም
የሽንት ቀለም መጥቆር እና የሰገራ ቀለም መለወጥ/ነጣ ማለት
የከፋ ደረጃ ምልክቶች
እነዚህ ምልክቶች የሚታዩት ከብዙ ዓመታት በኋላ የጉበት መጎዳት ወይም ጠባሳ ከተከሰተ በኋላ ብቻ ነው፡
በቀላሉ መድማት እና መቁሰል/ማበጥ
በሆድ ወይም በእግር አካባቢ ማበጥ
ያለ ምንም ምክንያት የክብደት መቀነስ
ከፍተኛ የቆዳ ማሳከክ
የማስተዋል መቀነስ፣ ግራ መጋባት
🧪 ምርመራው
1️⃣ HCV Antibody Test - ለቫይረሱ መጋለጥዎን ወይም አለመጋለጥዎን ያረጋግጣል። (ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ከገባ በኋላ በምርመራ ለመታየት እስከ 12 ሳምንታት ሊወስድ ይችላል።
2️⃣ የሄፓታይተስ ሲ አር ኤን ኤ ምርመራ ቫይረሱ በአሁኑ ጊዜ በሰውነትዎ ውስጥ መኖሩን ያረጋግጣል። (ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ከገባ በ2 ሳምንታት ውስጥ ማወቅ ይችላል። ውጤቱ ፖዘቲቭ ከሆነ በአሁኑ ወቅት በበሽታው መያዝዎን ያሳያል
💡 ማሳሰቢያ፦ ለበሽታው ሊያጋልጥ የሚችል ሁኔታ አጋጥሞዎት ከሆነ፣ ምልክቶች እስኪታይቦት ድረስ አይጠብቁ።
ይመርመሩ፣ ይዳኑ!
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የ ታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድህረ-ገጽ፡ www.arsholab.com
🔍 "calcium oxalate crystals" in Your Urine Report?
Here’s What It Means
If your routine urinalysis flags Calcium Oxalate Crystals, it means calcium has bound with a compound called oxalate. Under the microscope, they look exactly like tiny envelopes! ✉️
⚠️ Why Do They Form?
Dehydration 💧 Concentrated urine allows crystals to stick together.
Diet 🥬 — High intake of oxalate-rich foods (spinach, beets, nuts, chocolate).
Supplements 🍊 — Excessive Vitamin C can break down into oxalate.
💡 Why It Matters
Finding a few is completely normal and harmless. However, a consistently high amount is a warning sign; if left unchecked, these tiny crystals can clump together to form painful kidney stones (which are most commonly made of calcium oxalate).
🛡️ Quick Prevention Tips:
Hydrate Constantly: Drink plenty of water to flush your system naturally.
Smart Pairing: Eat calcium-rich foods with oxalate-heavy meals so they bind in your stomach rather than your kidneys.
Arsho Medical Laboratories
Trusted by generation!
📞 Call us at 612
🌐 Website: www.arsholab.com
🔍 በሽንት ምርመራ ውጤቶት ላይ calcium oxalate crystals አለ ሲባል ምን ማለት ነው?
በሽንት ምርመራ ውጤትዎ ላይ Calcium Oxalate Crystals የሚል ስያሜ አይተው ያውቃሉ? እነዚህ ክሪስታሎች በአጉሊ መነጽር ሲታዩ ጥቃቅን የፖስታ ቅርፅ አላቸው! ✉️
በምን ምክንያቶች ይፈጠራሉ?
በቂ ውሀ ባለመጠጣት💧 — በቂ ውሃ አለመጠጣት ሽንት እንዲወፍርና ክሪስታሎቹ እርስ በርስ እንዲጣበቁ ያደርጋል።
የአመጋገብ ዘይቤ 🥬 — እንደ ቆስጣ፣ ቀይ ስር፣ ለውዝ እና ቸኮሌት ያሉ ኦክዛሌት የበዛባቸውን ምግቦች ማዘውተር።
የቫይታሚን ሲ መብዛት 🍊— የቫይታሚን ሲ ሰፕሊመንቶችን ካስፈላጊ በላይ መውሰድ።
በሽንት ውስጥ ጥቂት የክሪስታል ቅንጣቶች መገኘታቸው የተለመደና ጉዳት የሌለው ቢሆንም፣ መጠናቸው ከበዛ ግን አስቀድሞ የሚሰጥ የማስጠንቀቂያ ምልክት ነው። እነዚህ ጥቃቅን ክሪስታሎች ከተከማቹና ከተጣበቁ ለከፍተኛ ህመም ለሚዳርገው የኩላሊት ጠጠር መፈጠር ዋነኛ መንስኤ ይሆናሉ::
🛡️ መከላከያ ዘዴ
በቂ ውሃ መጠጣት: ሽንትዎ ፈዘዝ ያለ ቢጫ እስኪሆን ድረስ በቂ ውሃ በመጠጣት ክሪስታሎቹን በሽንት መልክ በቀላሉ ማስወገድ።
ኦክሳሌት የበዛባቸውን ምግቦች በሚመገቡበት ጊዜ ከካልሲየም (ለምሳሌ ከወተት ተዋጽኦዎች) ጋር አብሮ መውሰድ። ይህም ክሪስታሉ ወደ ኩላሊት ሳይደርስ በሆድ ውስጥ እንዲደባለቅና በሰገራ መልክ እንዲወገድ ይረዳል።
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የ ታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድህረ-ገጽ፡ www.arsholab.com
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Wishing all followers of the Islamic faith a peaceful 1447th Eid al-Adha (Arafa) celebration!
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የታመነ!
Arsho Medical Laboratories
Trusted by Generations!
📞 Call us at 612
🌐 Website: www.arsholab.com
Some things happen with age… But some things happen because we ignore the signs.”
As men grow older, the body changes quietly.
The late-night bathroom visits.
The weaker urine flow.
That uncomfortable feeling that lingers.
The easiest habit to form is saying: “Ah, it’s probably just normal aging.”
And maybe sometimes it is. But not always.
Many prostate-related conditions begin silently,with small signs most men learn to live with instead of investigate. Weeks turn into months. Months turn into years. And what could have been detected early becomes harder, more painful, and more expensive to manage later. ⚠️
🩸 That’s why a PSA test matters.
It is a simple, quick blood test that gives you answers before symptoms become serious. Because not every health issue starts with pain. Some start with silence.
🔬 At Arsho Medical Laboratories, we believe early testing gives you more than results,it gives you control and peace of mind. Real strength isn't ignoring the problem. Real strength is checking before it’s too late. 🤍
👨⚕️ Growing older is natural. Ignoring the warning signs shouldn’t be.
📞 Call 612 to schedule your test today. 🌐 Arsho Medical Laboratories | Trusted by generations!
“አንዳንድ ነገሮች ከእድሜ ጋር ይመጣሉ… አንዳንድ ነገሮች ግን ምልክቶችን ችላ ስለምንል ይከሰታሉ።”
ወንዶች እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ፣ ሰውነታቸው በዝምታ መለወጥ ይጀምራል።
•ያ በለሊት ደጋግሞ ወደ መጸዳጃ ቤት መመላለስ…
•የሽንት ፍሰት መዳከም…
•ከሽንት በኋላ የሚሰማው ያ ያልተመቸ ስሜት…
ብዙ ጊዜ ወንዶች የሚከተለውን ልማድ ያዘወትራሉ፦ “አይ… ከእድሜ ጋር የመጣ ተፈጥሯዊ ነገር ይሆናል!”
ምናልባት አንዳንድ ጊዜ እውነት ሊሆን ይችላል፤ ሁልጊዜ ግን አይደለም።
ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ከፕሮስቴት ጋር የተያያዙ የጤና እክሎች የሚጀምሩት በዝምታ ነውብዙ ወንዶች ምርመራ ከማድረግ ይልቅ አብረውት ለመኖር በሚለምዷቸው ጥቃቅን ምልክቶች። ሳምንታት ወደ ወራት፣ ወራት ደግሞ ወደ አመታት ይቀየራሉ። በመጀመሪያ ደረጃ ላይ በቀላሉ መታወቅና መከላከል ፤ ይቻል የነበረው ነገር… በኋላ ላይ ለመታከም እጅግ ከባድ፣ አስጨናቂ እና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ይሆናል። ⚠️
🩸 የ PSA (የፕሮስቴት) ደም ምርመራ ለምን አስፈለገ?
•ይህ ምርመራ ምልክቶቹ ሳይባባሱ እና ሳይጸኑ በፊት፣ የፕሮስቴት እጢ ተጨማሪ ክትትል ያስፈልገው እንደሆነ ለማወቅ የሚረዳ ቀላል እና ፈጣን የደም ምርመራ ነው። እያንዳንዱ የጤና ችግር የሚጀምረው በህመም አይደለም፤ አንዳንዶቹ በዝምታ ይጀምራሉ።
🔬 በ አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ፣ ቀድሞ መመርመር ከውጤት በላይ፤ የአእምሮ እረፍትንና ሙሉ ቁጥጥርን እንደሚሰጥ እናምናለን። እውነተኛ ጥንካሬ ችግርን ችላ ማለት አይደለም፤ እውነተኛ ጥንካሬ ነገሮች ሳይረፍዱ አስቀድሞ መፈተሽ ነው። 🤍
👨⚕️ መሸምገግ ተፈጥሯዊ ነው፤ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ችላ ማለት ግን መሆን የለበትም።
📞 በ 612 ደውለው የክትትል ቀጠሮዎን ዛሬውኑ ያስይዙ። 🌐 አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ | በትውልድ የታመነ !
What is your body's "Secret Password"? 🤫
Imagine your body has a strict Security Guard.
If you put the wrong blood type into your body, the guard thinks it is an enemy invader and attacks it! This makes the blood turn into thick glue, which is very dangerous. 💥
🆔 Your 2-Part ID Code
To keep you safe, your blood has a special 2-part password:
1. Your Group: Are you A, B, AB, or O?
2. Your Rh Tag: Are you Positive (+) or Negative (-)?
If you ever need blood in an emergency, doctors must know your exact code to save your life.
🔬 Stop Guessing. Know Your Type!
Finding your code takes just a few minutes and a single drop of blood.
Get your Blood Group & Rh Test at our lab today. It is fast, easy, and accurate! 👇
Arsho Medical Laboratories
Trusted by generations!
📞 Call us at 612
🩸 የሰውነትዎ "ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል" ምንድነው? 🤫
ሰውነትዎ ውስጥ ጥብቅ የሆነ "የሰላም አስከባሪ ዘበኛ" እንዳለ ያስቡ።
ከሰውነትዎ ጋር የማይስማማ የተሳሳተ የደም አይነት ወደ ውስጥዎ ሲገባ፣ ዘበኛው እንደ ጠላት ቆጥሮ ማጥቃት ይጀምራል! ይህ ደግሞ ደምዎ እንዲረጋና እንዲጠባበቅ ስለሚያደርገው በጣም አደገኛ ነው።
🆔 የደምዎ ባለ 2-ክፍል መለያ ኮድ
ሰውነትዎን ከአደጋ ለመጠበቅ፣ ደምዎ ልዩ የሆነ ባለ ሁለት ክፍል የይለፍ ቃል አለው፦
1. የደምዎ ምድብ፦ A፣ B፣ AB፣ ወይስ O?
2. የአር ኤች ፋክተር፦ ፖዘቲቭ (+) ወይስ ኔጋቲቭ (-)?
በድንገተኛ ሁኔታ ደም ቢያስፈልግዎት፣ ዶክተሮች ህይወትዎን ለማዳን የእርስዎን ትክክለኛ የደም አይነት ማወቅ አለባቸው።
🔬 መገመትን ያቁሙ። የደምዎን አይነት ይወቁ!
የደምዎን ሚስጥራዊ ኮድ ለማወቅ ጥቂት ደቂቃዎችና አንዲት ጠብታ ደም ብቻ በቂ ነው።
ዛሬውኑ ወደ ላቦራቶሪያችን በመምጣት የደም ምድብ እና የአር ኤች (Blood Group & Rh) ምርመራዎን ያድርጉ። ፈጣን፣ ቀላል እና አስተማማኝ ነው! 👇
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድረ-ገጽ: www.arsholab.com
One Test Tells a Clue. Related Tests Reveal the Truth. 🔍🩸
When you come to the lab for a specific check-up, have you ever considered adding these tests together? It’s the difference between finding a hint and finding the solution.
If you are coming for: Fasting Blood Sugar (FBS)
* Consider adding: HbA1c
* The Benefit: FBS shows your sugar levels right now. HbA1c shows your average over the last 90 days. Why look at a single moment when you can see the whole trend?
If you are coming for: CBC (Complete Blood Count)
* Consider adding: Ferritin
* The Benefit: A CBC can look normal even if your iron reserves are nearly empty. Ferritin identifies the root cause of fatigue before it turns into anemia.
If you are coming for: Urinalysis
* Consider adding: Urine Culture
* The Benefit: A urinalysis confirms there is an infection; a Culture identifies the specific bacteria. This allows for precise treatment instead of trial and error.
If you are coming for: Lipid Profile (Cholesterol)
* Consider adding: CRP (High-Sensitivity)
* The Benefit: High cholesterol is a risk factor, but CRP reveals active inflammation in your arteries. Together, they provide a much clearer view of your heart health.
If you are coming for: Kidney Function (Creatinine)
* Consider adding: Urinalysis (Protein/Albumin)
* The Benefit: Blood tests tell us how well kidneys filter, but urine tests catch early signs of stress before blood levels even change.
If you are coming for: Routine Stool Exam
* Consider adding: H. pylori or FOBT
* The Benefit: A standard exam looks for parasites, but adding H. pylori or an Occult Blood test (FOBT) investigates the hidden causes of stomach pain or silent bleeding.
Don’t just get tested. Get the answers you actually need.
Arsho Medical Laboratories
Trusted by generation!
📞 Call us at 612
🌐 Website: www.arsholab.com
አንድ ምርመራ ፍንጭ ይሰጣል፤ ተያያዥ ምርመራዎች እውነታውን ያሳያሉ! 🔍🩸
ለተወሰነ የጤና ምርመራ ወደ ላቦራቶሪ ሲመጡ እነዚህን ተያያዥ ምርመራዎች በአንድ ላይ ስለማድረግ አስበው ያውቃሉ?
ለስኳር ምርመራ (FBS) ሲመጡ፦
ቢጨምሩ የሚመከረው፦ HbA1c
* ጥቅሙ፦ የደም ስኳር (FBS) በዚያች ቅጽበት ያለውን መጠን ብቻ ያሳያል። HbA1c ደግሞ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ የነበረውን አማካይ መጠን ይነግረናል። የአንድ ቀን ሁኔታን ብቻ ከመመልከት ይልቅ የሦስት ወር ጉዞዎን ማወቁ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።
CBC ለማሰራት ሲመጡ፦
ቢጨምሩ የሚመከረው፦ Ferritin
* ጥቅሙ፦ CBC ውጤቶ መደበኛ ቢመስልም እንኳን በሰውነትዎ ውስጥ ያለው iron ክምችት ሊያልቅ ይችላል። ፌሪቲን (Ferritin) ለድካምዎ ትክክለኛውን ምክንያት የደም ማነስ ደረጃ ላይ ሳይደርሱ አስቀድሞ ለመለየት ይረዳል።
ለሽንት ምርመራ (Urinalysis) ሲመጡ፦
* ቢጨምሩ የሚመከረው፦ Urine Culture
* ጥቅሙ፦ መደበኛው የሽንት ምርመራ ኢንፌክሽን መኖሩን ብቻ ያረጋግጣል፤ የሽንት Culture ደግሞ የኢንፌክሽኑን መንስኤ የሆነውን ባክቴሪያ በስም ይለያል። ይህ ደግሞ በግምት ሳይሆን በትክክለኛ መድኃኒት እንዲታከሙ ይረዳል።
ለኮሌስትሮል ምርመራ (Lipid Profile) ሲመጡ፦
* ቢጨምሩ የሚመከረው፦ CRP
* ጥቅሙ፦ ከፍተኛ ኮሌስትሮል አንዱ የጤና ስጋት ሲሆን CRP ደግሞ በደም ስርዎ ውስጥ ያለውን ድብቅ inflammation ያሳያል። ሁለቱ በአንድ ላይ ስለ ልብዎ ጤንነት ግልጽ ምስል ይሰጣሉ።
ለኩላሊት ምርመራ (Creatinine) ሲመጡ፦
* ቢጨምሩ የሚመከረው፦ Urinalysis (Protein/Albumin)
* ጥቅሙ፦ የደም ምርመራው ኩላሊትዎ እንዴት እያጣራ እንደሆነ ይነግረናል፤ የሽንት ምርመራው ደግሞ በደም ውስጥ ለውጥ ሳይታይ በፊት ኩላሊትዎ ላይ የሚታይ ምልክትን አስቀድሞ ለማወቅ ይረዳል።
ለሰገራ ምርመራ (Routine Stool Exam) ሲመጡ፦
* ቢጨምሩ የሚመከረው፦ H. pylori ወይም FOBT(fecal occult blood test)
* ጥቅሙ፦ መደበኛው ምርመራ ጥገኛ ትላትሎችን ይለያል፤ ነገር ግን የH. pylori ወይም FOBT ምርመራዎችን መጨመር ለጨጓራ ህመም ወይም አንጀት አካባቢ ላለ ደም መፍሰስ ዋና መንስኤ የሆኑትን ምክንያቶች ይፈትሻል።
አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ
በትውልድ የ ታመነ!
📞 በ 612 ይደውሉልን
🌐 ድህረ-ገጽ፡ www.arsholab.com
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
