Assaye Derbie
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Assaye Derbie
تُعد قناة Assaye Derbie (@asayede) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 346 مشتركاً، محتلاً المرتبة 2 649 في فئة المدوّنات والمرتبة 2 354 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 346 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 24 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -112، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -7، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 39.43%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 12.21% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 5 656 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 752 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 25 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة المدوّنات.
14 346
المشتركون
-724 ساعات
-387 أيام
-11230 أيام
أرشيف المشاركات
14 343
"ሕዝባችን ጦርነት ሰልችቶታል" በማለቱ የተነሳ በእነ ናትናኤል መኮነንና ሙክታሮቢች ትዕዛዝ ወደ እስር ቤት የተወረወረ ወንድማችንን ፍቱት።
14 343
ከእነ ቀለጠ የበሰበሰ መንጋጋ አብንን መንግጎ ማውጣት የኔ፣ ያንተ፣ ያንቺ ግዴታ ነው። የአምሳ ሚሊዮን ሕዝብ ድርጅት አምስት በማይሞሉ ኅሊና ቢሶች ሊዳከም የቻለው በእነሱ ብርታት ሳይሆን በእኛ ድከመት ነው።
14 343
ተደራዳሪ ቡድኑ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ይጨቃጨቃል።
ጠሚው ከስንዴ ማሳ መሀከል ቁሞ "ህውሓት እራሱ የጻፈውን ሕገ መንግሥት ካከበረ የክልሉ አስተዳዳሪ ሁኖ ይቀጥላል" የሚል ውሳኔ ያስተላልፋል። 😆
14 343
አማራን አንድ የሚያደርጉ፣ አማራነትን ከፍ የሚያደርጉ መሪዎች እንፈልጋለን። አማራን የሚበትን አስተሳሰብ ይዘው በአመራርነት የተቀመጡ ኃይሎችም መልቀቅ አለባቸው።
በብሄር ከፋፍለው ሲያባሉን የነበሩት ሰዎች፣ ዛሬ ደግሞ በጎጥ እየከፋፈሉን ነው። የተማረው የአማራ ሀይልም ጥቅምንና የግል ክብርን ማዕከል ከማድረግ መቆጠብ አለበት።
ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ
14 343
ስለ ስኳድ ከተናገርኩት‼️
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬▬
#ጋዜጠኛ:- ስኳድ የሚባለው ማን ነው? ዋነኛ ዓላማውስ ምንድን ነው?
#የኔ_መልስ፦ ስኳድ የሚባለው ስብስብ ከአራቱም የአማራ ዞኖች የተውጣጡ አጋሰሶችን የያዘ አጥፊና ቀጣፊ ቡድን ሲሆን ዓላማው ደግሞ እንደሚከተለው ነው‼️
➔የሕዝብ ክንድ የሆኑ ጀግኖች ላይ ግድያዎችን ማቀነባበር፤
➔የአማራ ድምጽ የሆነ ሐቀኛ ልጆችን በትሕነግ ተላላኪነት እየፈረጁ ማሳሰር፤
➔የአማራን ሕዝብ አንድነት የሚበጣጥሱና የሚያፈራርሱ ሤራዎችን ማዋቀር፤
➔እንደ ወነግ ሕብረት እና ራዴፓ ካሉ አማራ ጠል አደረጃጀቶች ጋር በጋራ በመስራት ከትልቁ ክልል ውስጥ ትናንሽ ክልሎችን መፍጠር፤
➔በቁጥጥር ስር የሚውሉና የሚገደሉ የአማራ ልጆችን መለየት፤
➔የአማራን ሕዝብ ፋታ የሚያሳጡ አጀንዳዎችን ማሰራጨት፤
➔ታላቁን ሕዝብ ከፖለቲካ ውጭ አድርጎ ለቁማርተኛ ኃይሎች አሳልፎ መስጠት፤
➔በአማራ ክልል ውስጥ የሚፈጠሩ አደረጃጀቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባት የተደራጁበትን ዓላማ ማኮላሸት፤
.
.
(ስለ መፍትሔው ከአፍታ በኋላ እመለስበታለሁ)
14 343
በትናንቱ የክርክር መድረክ ላይ የአቶ ልደቱ አንደበት የአንቺን እውነት፣ እውቀት እና የንግግር ክህሎት ማሸነፍ አልተቻለውም።
እናም....
ሆዳም ፖለቲከኛ በመቀፍቀፍ የሚታወቀው የአማራ ሕዝብ አንቺን መሰል ልባም ሴት በማፍራቱ ሊጽናና ይገባዋል።
14 343
የእነ ቀለጠ መግለጫ
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬
➔የአማራ ሕዝብ በጦርነት ላይ እንጂ በድርድር ላይ መሳተፍ እንደሌለበት የገለጸ፤
➔ተዳራዳሪዎችን በአሸባሪ ድርጅት አጋርነት ፈርጆ ትሕ-ኦነግን ትርፋማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያደረገ፤
➔በአማራ ሕዝብ ላይ ያቀደው ክሕደት እና ሸፍጥ ተደራሽ እንዳይሆን እንግሊዘኛ ቋንቋን የተጠቀመ፤
➔ኢሕአዴግ ሕገ-መንግሥቱን ሲያረቅ የፈጸመውን አማራን የማግለል ተግባር በብልጽግና ዘመን ይደገም ዘንድ መንገድ የጠረገ፤
➔መግለጫውን የጻፈው ቡድን ከትሕ-ኦነግ ኃይሎች ባልተናነሰ መልኩ ጸረ አማራ መሆኑን ይፋ ያወጣ፤
➔ቡድኑ ከተሳካለት ወልቃይትን እና ራያን ብቻ ሳይሆን የአማራ ክልልን ሽጦ ኪሱን እና ከርሱን ከመሙላት የማይመለስ መሆኑን ያመላከተ፤
Share
14 343
በሆዱ የወደቀው ስኳድ ውድቅ ያደረጋቸው አእምሮዎች!
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬▬
የአማራ ሕዝብ አንደበት እና ክንድ የሆኑ ጀግኖችን ሲያስለቅም የከረመውና በሆዱ የወደቀው "ስኳድ" ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአማራ ማሕበር በአሜሪካ (ትሪፕል A) ያቀረባቸውን ተደራዳሪዎች "የትሕነግ አጋሮች" ብሎ ካጥላላቸው በኋላ ከፌደራል መንግሥት ውጭ ሌላ ተደራዳሪም ሆነ የአማራ ሕዝብ ወኪል ማየት እንደማይፈልግ ገልጿል።
እናም...
ለወገናቸው የሚታገሉ ጀግኖችን ሲያሳፍስ እንዲሁም ጠቃሚ አደረጃጀቶችን ሲያፈራርስ መክረሙ አንሶ ተደራዳሪ ሆነው ለመቅረብ የደፈሩ ልባሞችን የአሸባሪ አጋር አድርጎ ማንቋሸሽ የጀመረው ይህ የከሸፈ ቡድን በቀጣይ ጊዜያት "ከገዢው ፓርቲ ውጭ ሕዝባችንን ወክሎ ለምርጫ የሚቀርብ ሌላ ተፎካካሪ ፓርቲ አያስፈልግም" የሚል የአቋም መግለጫ ይዞ መምጣቱ አይቀርም።
14 343
ሃይ ጓዶች!
እንዴት ሰነበታችሁ?
በተወካይ ሲተዳደር የነበረውን የፌስቡክ ገጻችንን ተረክበናል። በቅርቡም በቀድሞ አቋማችን እና ጽናታችን የምንከሰት ይሆናል።
በተረፈ በእስር በቆየሁባቸው ሰላሳ ምናምን ቀናት የእኔና የቤተሰቦቼ አለኝታ ሆናችሁ የተገኛችሁ ወዳጆቼን አመሠግናለሁ። የፍትሕ ድምጽ ለሆናችሁኝ ወገኖችም ከወገቤ ጎንበስ ብዬ ምስጋናየን አቀርባለሁ።
አሳዬ ደርቤ‼️
14 343
መጪው አዲስ ዓመት
🌻የተፈናቀሉ ወገኖች በፍጥነት ወደ ጎጇቸው የሚመለሱበትና ከስጋት ጸድተው የሚኖሩበት…
🌻ያለጥፋታቸው የታሰሩ ዜጎች ነጻነታቸውን የሚጎናጸፉበት…
🌻እረፍት አልባ የሆነው የወገን ጦር አሸባሪ ኃይሎችን አጽድቶ የአገርን ሕልውና የሚያስከብርበት….
🌻በግፍ የተጨፈጨፉ ንጹሐን ፍትሕ የሚያገኙበትና የእልቂት ዜና የማንሰማበት…
🌻ሥልጣን ላይ ያለው ኃይል ከተረኝነት እና ቁማርተኝነት አባዜ ተላቅቆ ክልሎችን በእኩል ዐይን የሚመለከትበት…
🌻በመንግሥትና በጠላት ወጥመድ ውስጥ ገብቶ ሲዋትት የከረመው የአማራ ሕዝብ በልጆቹ እገዛ ከቅርቃሩ ወጥቶ እራሱን የሚያስከብርበትና ወገኑን የሚያከብርበት…
🌻በመስመር ትግል ውስጥ ተቸንክረው የኖሩ ወገኖች ወደ አገራዊ እሳቤ ተሸጋግረው ያለ ባንክ እና ያለ መብራት ሳይሆን ያለ ህው-*ት የሚኖሩበት…. እንዲሆን እመኛለሁ፡፡
የትኛውም የአዲስ ዓመት ምኞት ግን ያለ እኛ ጥረት እና ድርጊት ሊሰምር ስለማይችል ከላይ የዘረዘርኳቸው ምኞቶች ይሰምሩ ዘንዳ እንደ አንድ ዜጋ የሚጠበቅብኝን ለማድረግ ለእራሴ ቃል ገብቻለሁ፡፡
አሳዬ ደርቤ
መልካም አዲስ ዓመት!
14 343
"ከመንግሥት ጎን ካልሆንክ የጠላት ወገን ነህ"
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬▬
➔አገር ውስጥ ተቀምጠው፣ ከትሕ-ኦነግ ታጣቂዎች ጎን ተሰልፈው፣ የአገር ጠባቂ የሆነውን መከላከያ ሠራዊት የአንድ ብሔርና የአንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አገልጋይ አድርገው፣ የጌታቸው ረዳ የፕሮፖጋንዳ ክንፍ ሆነው.... ከመንግሥት ባለፈ አገር ለማፍረስ የሚተጉ እልፍ አእላፍ የኦነግ አክቲቪስቶችን ከዩቲዩብ ቻናላቸውና ከፌስቡክ ገጻቸው ጋር ላሳይህ እችላለሁ፡፡
ሆኖም ግን አገር አጣብቂኝ ውስጥ በወደቀችበት ጊዜ ከጠላት ጎን ተሰልፈው በአገር ላይ ዘመቻ ከከፈቱት ከእኒህ አክቲቪስቶች ጫጫታ ይልቅ የመዓዛ መሐመድ ዝምታ እንደ ትልቅ ወንጀል ተቆጠሮ ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ወህኒ ስትወረወር ታያለህ፡፡
➔የወሎ ወገናቸውን ከወራሪ ጥቃት ሊታደጉ ከጎጃምና ከጎንደር ምድር የመጡ ፋኖዎችን ሥም በማጠልሸት ወሎን ከወገኑ ነጥለው ለወራሪ ለማስረከብ የሚባትሉ........ አንዱን ጀብደኛ ሌላውን ጥቅመኛ በሚያደርጉ ፕሮፖጋንዳዎች የወሎ አማራ ፋኖን በመንደር የሚከፋፍሉ..... በሕብረት ሥም ልዩነት የሚዘራ ቡድን አዋቅረው ተፋቅሮ የኖረውን የወሎን ሕዝብ በሃይማኖትና በማንነት የሚሸነሽኑ..... በወራሪዎች ፈንታ ከምዕራብ ወሎ እና ከሰሜን ወሎ የዘመቱ ፋኖዎችን በሐሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያብጠለጥሉ.... ጸረ-አማራ አክቲቪስቶችን እኩይ ተግባር በማስረጃ አስደግፈህ ብታቀርብ የሚሰማህ የመንግሥት አካል የለም፡፡
በሌላ መልኩ ግን የወገናቸው ልሳን ሆነው የሕዝብን አንድነት እና የመኖር መብት ለማስጠበቅ በአቅማቸው ልክ የሚተጉ ወገኖች የሆነ ስህተት የተገኘባቸው ቀን ከላይ የተጠቀሱት እኩይ ኃይሎች የፌስቡክ ዘመቻ እና ዛቻ ይከፍቱባቸዋል፡፡ በዚያች ቅጽበትም ሥልጣን ላይ ያለው ኃይል ሰለባውን ከእስር ቤት ወርውሮ በጸረ አማራነት የተደራጀ የትኛውም ኃይል ጠቁሞ የሚያሳስር እንጂ ተጠቁሞ የሚታሰር አለመሆኑን ያስረዳኻል፡፡
እናም እላለኹኝ…
ከአሸባሪዎች ጋር የሚደረግን ትግል እንደ መልካም እድል ተጠቅሞ ‹‹ከመንግሥት ጎን ያልቆመ ሁሉ የጠላት ወገን ነው›› በሚል መናኛ አቋም የአማራ ድምጾችን የማክሰም እንቅስቃሴ ይቁም!!
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
