cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የስነልቦና ምክሮች

ጠቃሚ ለሂወት ወሳኝ የሆኑ ነገሮች የሚለቀቁበት ቻናል

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 224
المشتركون
-324 ساعات
+37 أيام
+2330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

አንድ ሰው አንዲት የከሳች በቅሎ ነበረችው።አወጣና ሸጣት።ከዓመታት በኋላ ገበያ ሲወጣ አንድ ሰው እጅግ ያማረች የኮርቻ በቅሎ ይዞ ተመለከተ።ሰውዬው ጠጋ ብሎ "ጌታው ይህችን የመሰለች በቅሎ ከየት ትገኛለች እባክዎ ? እኔም ለመግዛት እፈልግ ነበር" አላቸው።ሰውዬውም "እኔም በአጋጣሚ ከሰው ነው የገዛኋት።ስትገዛ ከስታ ልትሞት ደርሳ ነበር።የሸጠልኝ ሰው እንደነገረኝ ባለቤቷ ለበቅሎ ግድ አልነበረውም።እኔ የበቅሎ ጠባይ ስለማውቅ ነው ከሰውዬው የገዛኋት።በአንድ አመት ውስጥ በደንብ ስይዛት ጊዜ እንዲህ ያማረች በቅሎ ሆነች" አሉት።"መቼ ነበር የገዙት ?"አላቸው "የዛሬ አራት ዓመት ከዚሁ መንደር ገዝቷት ሲሔድ ነው ለምኜ የገዛሁት" አሉት።እራሱን እየነቀነቀ ተመለሰ ። በቅሎዋ የእርሱ ነበረች።የሰውዬውን ያህል ግን የበቅሎዋን ዋጋ አላወቀውም ነበር።ተፈላጊዋን ምርጥ በቅሎ ይፈልጋል።እኛም ያሉንን ምርጥ ነገሮች እየሸጥን የሌሉንን ምርጥ ነገሮችን እንፈልግ ይሆናል። በእጃችን ያለው ነገር የእኛ ነው።በእጃችን የሌለው ግን ገና የእኛ አይደለም።የእኛ የሆነው የእኛ ካልሆነው ነገር ይበልጣል።ምክንያቱም የእኛ በሆነው ነገር መጠቀም እንችላለን የእኛ ባልሆነው ነገር ግን ልንጠቀም አንችልም።የእኛ በሆነው ነገር ልናዝ እንችላለን የእኛ ባልሆነው ነገር ግን ልናዝ አንችልም።የእኛ የሆነው ነገር ማግኘታችንን እርግጠኛ ሆነናል።የእኛ ያልሆነውን ማግኘት ግን እርግጠኛ መሆን አንችልም፤የእኛ በሆነው ነገር ልንወስንበት እንችላለን፤የእኛ ባልሆነው ነገር ግን ልንወስን አንችልም።የእኛ የሆነውንነገር ለሌላው መስጠት እንችላለን የእኛ ያልሆነውን ግን መስጠት አንችልም።ካለን ነገር ላይ ቆመን የሌለንን ማየት እንችላለን፤ከሌለን ነገር ላይ ቆመን ግን ያለንን ነገር ማየት አንችልም። አንዳንድ ጊዜ የምናማርረው ችግር ስለደረሰብን ብቻ ሳይሆን ያለንን ስለማናውቀው ጭምር ነው።ችግር በራሱ ችግር አይደለም።ችግር ችግር የሚሆነው መፍትሔ መስጠት ለማይችል ሰው ብቻ ነው።መፍትሔ መስጠት ለለመደ ችግር ትምህርት ቤት ነው።ችግር የፍች፣የመለያየት፣የጠብ፣የኩርፊያ፣የክስ፣የመለቀቂያ መንገድ የሚሆነው ለዐቅመ ቢስ ሰው ነው።ለብርቱ ሰው ግን ሞት የትንሳኤ መቅድም ነው ። የሌለንን ነገር ብቻ ካሰብን ያለንንም እናጣለን።ያለንን ነገር ካሰብን ግን የሌለንንም እናገኛለን።እስኪ ያለንን እንወቀው፣እናክብረው፣አሟጠን በሚገባ እንጠቀምበት፣እንኑርበት እናጊጥበት።ከዚያ ሌላውን ያጣነውን ለመያዝ እንፈልግ።ባለን የማንረካ ከሆን ግን ሩጫችን የተሻለ ነገር ፍለጋ ሳይሆን ሌላ ነገር ፍለጋ ድካም ብቻ ይሆናል።ባለው ያለረካ ቢሰጠውም አይረካ፣ባለው ያልተደሰተ ቢጨመርለትም አይደሰት፣ባለው ያላመሰገነ ቢጨመርለትም አያመሰግንም፣ባለው መጠቀም ያልቻለ ቢጨመርለትም መጠቀም አይችልም፣ያለውን ባግባቡ ያልያዘ ቢጨመርለትም መያዝ አይችልም።
إظهار الكل...
👍 4 2
👉🏿በሕይወት ዘመንህ!፦ 👉🏿ስኬትህን በራስህ ሚዛን መዝነው፤ በሰው ሚዛን ከመዘንከው ሚዛን አይደፋልህምና። 👉🏿ደስታህን በራስህ መስፈሪያ ስፈረው፤ በሰው ሚዛን ስትሰፍረው አይሞላልህምና። 👉🏿ውድቀትህን በራስህ አይን እየው፤ በሰው አይን ከተመለከትከው ጉድጓዱ ይበልጥ ይርቅሃልና። 👉የራስህን ህይወት በሌላ ሰው እይታ ከተመለከትከው ፈጽሞ እርካታ አይኖርህም:: 👉ህይወትሀን ከሰው ጋር እያነጻጸርክ የምትኖር ከሆነ እርካታ የሌለው ኑሮ እየኖርክ ነው፤ ✍ምክንያቱም በንጽጽር ህይወት ውስጥ  ሁሌም የሚበልጥህ አታጣምና።
إظهار الكل...
4👍 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
MOVIE SUGGESTION ውሸት በጣም ጠቃሚም፣ አስፈላጊም ነገር ነው። እውነት ሁሌ አይነገርም ሙድ፣ አገባብ፣ መቼት ተጠብቆ ነው። እውነት ሁሌ ሲነገር ይሰለቻል፣ ይቸካል፣ ይረክሳል። እውነት የክት ነው። አንዳንዴ እውነት መናገር ስሜት ሊጎዳ ይችላል። ያኔ እንዋሻለን። ውሸት ባይኖር በድብርት እንሞት ነበር። የፊልሙ ርእስ The Invention of Lying ይሰኛል። ሰዎች መዋሸት የማይችሉበት አለም ነው። ዋና ገፀባህሪው ማርክ ይባላል። ከአንዲት ውብ ኮረዳ ጋር የፍቅር ቀጠሮ አለው። ታዲያ ልጅት እንዲህ ትለዋለች፦ "መልክህ ብዙ አያምርም። በዚያ ላይ ሃብታም አይደለህም። የሁለታችን ነገር የሚሆን አይደለም" ቆይ! ላስብበት የለ! ሌላ ሰው አለኝ የለ! እውነቱን ቁርጥ፣ ፍርጥ አድርጎ መናገር። እና ይሄ አለም አያስቀይምም?! ለማንኛውም ጥናት እንደሚለው እያንዳንዱ ሰው በቀን 4 ግዜ ይዋሻል። በአመት 1460።
إظهار الكل...
👍 3😁 1
በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና እዚያው ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ። ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመሩ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን አዘነች፡፡ ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች። በሂደት በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡ በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡ የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር  በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡ አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ።  ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡ በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡ በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው! ልክ እንደ አህያዋ (የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው) ሁሉ እኛም በየጊዜው የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀምን በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልገናል። ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው! ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ እንጓዝ!! እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተጠቀምክበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!
إظهار الكل...
👍 7 1🥰 1
በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና እዚያው ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ። ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመሩ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን አዘነች፡፡ ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች። በሂደት በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡ በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡ የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡ አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡ በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡ በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው! ልክ እንደ አህያዋ (የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው) ሁሉ እኛም በየጊዜው የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀምን በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልገናል። ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው! ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ እንጓዝ!! እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተጠቀምክበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!
إظهار الكل...
Visit TikTok to discover videos!

Watch, follow, and discover more trending content.

ወዳጄ ሆይ.... ንጉስ ሰለሞን ‹‹ልጄ ሆይ...... ከሕዝብ ጋር አትሂድ!›› የሚልህ ከህዝብህ ተለይተህ ጥፋ ለማለት ሳይሆን ለሕዝብህ የሚሆን መፍትሄ ታበጅ ዘንድ ከመንጋው ተለይተህ አስብ እያለህ ነው፡፡ ከህዝብ ጋር ሙሉ ጊዜህን የምታጠፋ ከሆነ የምታስብበት ጊዜ አይኖርህም፡፡ ህዝብ በተፈጥሮው በወል ነው የሚያስበው፡፡ አይመረምርም፣ አይፈትንም፣ የተቀበለውን መስጠት እንጂ አዲስ የሕይወት መንገድ አይቀርፅም፡፡ ህዝብን የምትከተል ከሆነ ለራስህም፣ ለሐገርህም አትሆንም፡፡ ማሰላሰያ፣ ማገናዘቢያ፣ ራስህንም ዓለሙንም ማንበቢያ ጊዜ ከሌለህ ራስህን ዘንግተህ ያንተ ባልሆነው የሌሎች ዓለም ስደተኛ ነው የምትሆነው፡፡ መንጋው ያንጋጋሃል! ወዳጄ ሆይ.. ወዳጅነት መልካም ነው፤ ዝምድና አይከፋም፣ አብሮአደግነት ደግ ነገር ነው፤ ባልንጀርነት ደስ ይላል፡፡ ነገር ግን የማሰቢያህን ጊዜ የሚሻማ ማንኛውም የማህበራዊ ግንኙነት ሁሉ ዘለቄታዊ ጥቅም አይሰጥህም፡፡ ሰዎች በዘልማድ ባሰመሩት የአኗኗር መስመር ብቻ መሄድ የሚያስገኘው አንዳች ነገር የለም፡፡ የብዙዎቻችን ሕይወት አሰልቺ እየሆነ የመጣው በድግግሞሽ ህይወት ውስጥ ስለምንመላለስ ነው፡፡ ኑሯችን አዙሪት የሆነው በሰጡን ርዕዮት ዓለም፣ ባቀበሉን የአኗኗር ዘይቤ ስለምንጓዝ ነው፡፡ የራሳችን መንገድ የሌለን የማሰቢያ ጊዜ ስላጣን ነው፡፡ የተወጠርንበትና የተጠመድንበት ነገር ሁሉ የሚያለማን ሳይሆን የሚያጠፋን ነው፡፡ በራሳችን መንገድ ካላሰብን የትም አንደርስም፡፡ እንዲሁ የኋሊት እንምዘገዘጋለን፡፡ ህዝብነት አያተርፍም፤ መንጋነት በራስህ እንዳትተማመን ያደርግሃል፡፡ ለህዝብ መቆም እንጂ ከህዝብ ጋር መሄድ የተለየ ውጤት አያስገኝም፡፡ ለህዝብህ ጠብ የሚል መፍትሄ አምጠህ የምትወልደው ከመንጋው ተነጥለህ ማሰብ ስትችል ብቻ ነው፡፡ መነጠልህ እስመጨረሻው የሚለይህ ሳይሆን ህዝብህን መልሶ እንዲጠቅም የሚያደርግ ነው፡፡ ወዳጄ ሆይ.... ምርጫዎችህን ለመምረጥ፣ የሕይወት መንገድህን ለመቀየስ፣ መነሻህን አሳምረህ ፍጻሜህን ለማስዋብ አንተ አንተን ሆነህ መገኘት አለብህ፡፡ ለራስህ የማታውቅ ከሆነ ሌሎች ባወቁትና በቀረፁት መንገድ ትከተላለህ እንጂ ራስህን አትመራም፡፡ ስታስብ፣ ስትመረምር፣ ስታሰላስል፣ ስታስተውል፣ አዲስ ሃሳብ ስትፈጥር ግን ችግሮችህን ትቀርፋለህ፣ መሰናክሎችህን ትሻገራለህ፣ ስልጣኔን ታመጣለህ፡፡ ራስህን ከሌሎች ባርነት ነፃ ታወጣለህ፡፡ አልያ ግን በመንጋው ተጠልፈህ በራስህ መንገድ ትመላለስ ዘንድ እንዳትችል አቅም ታጣለህ፡፡ ተከታይነት በራስህ ፀንተህ ለመቆም ሃይል እንዳይኖርህ ያደርግሃል፡፡ ተጎታች እንጂ መሪ አትሆንም፤ ጠባቂ እንጂ ሰጪ ትሆን ዘንድ አትችልም፡፡ የሰው ዓለም መፃተኛ እንጂ የራስህ ዓለም ሰሪ ለመሆን አይቻልህም፡፡ በተኮረጀ ሕይወት ዘመንንህን ትጨርሳለህ፡፡ እስኪ ሃሳብ ስጡበት👆              
إظهار الكل...
👍 5 1🥰 1
የቀጠለ ወዳጄ ሆይ.... ንጉስ ሰለሞን ‹‹ልጄ ሆይ...... ከሕዝብ ጋር አትሂድ!›› የሚልህ ከህዝብህ ተለይተህ ጥፋ ለማለት ሳይሆን ለሕዝብህ የሚሆን መፍትሄ ታበጅ ዘንድ ከመንጋው ተለይተህ አስብ እያለህ ነው፡፡ ከህዝብ ጋር ሙሉ ጊዜህን የምታጠፋ ከሆነ የምታስብበት ጊዜ አይኖርህም፡፡ ህዝብ በተፈጥሮው በወል ነው የሚያስበው፡፡ አይመረምርም፣ አይፈትንም፣ የተቀበለውን መስጠት እንጂ አዲስ የሕይወት መንገድ አይቀርፅም፡፡ ህዝብን የምትከተል ከሆነ ለራስህም፣ ለሐገርህም አትሆንም፡፡ ማሰላሰያ፣ ማገናዘቢያ፣ ራስህንም ዓለሙንም ማንበቢያ ጊዜ ከሌለህ ራስህን ዘንግተህ ያንተ ባልሆነው የሌሎች ዓለም ስደተኛ ነው የምትሆነው፡፡ መንጋው ያንጋጋሃል! ወዳጄ ሆይ.. ወዳጅነት መልካም ነው፤ ዝምድና አይከፋም፣ አብሮአደግነት ደግ ነገር ነው፤ ባልንጀርነት ደስ ይላል፡፡ ነገር ግን የማሰቢያህን ጊዜ የሚሻማ ማንኛውም የማህበራዊ ግንኙነት ሁሉ ዘለቄታዊ ጥቅም አይሰጥህም፡፡ ሰዎች በዘልማድ ባሰመሩት የአኗኗር መስመር ብቻ መሄድ የሚያስገኘው አንዳች ነገር የለም፡፡ የብዙዎቻችን ሕይወት አሰልቺ እየሆነ የመጣው በድግግሞሽ ህይወት ውስጥ ስለምንመላለስ ነው፡፡ ኑሯችን አዙሪት የሆነው በሰጡን ርዕዮት ዓለም፣ ባቀበሉን የአኗኗር ዘይቤ ስለምንጓዝ ነው፡፡ የራሳችን መንገድ የሌለን የማሰቢያ ጊዜ ስላጣን ነው፡፡ የተወጠርንበትና የተጠመድንበት ነገር ሁሉ የሚያለማን ሳይሆን የሚያጠፋን ነው፡፡ በራሳችን መንገድ ካላሰብን የትም አንደርስም፡፡ እንዲሁ የኋሊት እንምዘገዘጋለን፡፡ ህዝብነት አያተርፍም፤ መንጋነት በራስህ እንዳትተማመን ያደርግሃል፡፡ ለህዝብ መቆም እንጂ ከህዝብ ጋር መሄድ የተለየ ውጤት አያስገኝም፡፡ ለህዝብህ ጠብ የሚል መፍትሄ አምጠህ የምትወልደው ከመንጋው ተነጥለህ ማሰብ ስትችል ብቻ ነው፡፡ መነጠልህ እስመጨረሻው የሚለይህ ሳይሆን ህዝብህን መልሶ እንዲጠቅም የሚያደርግ ነው፡፡ ወዳጄ ሆይ.... ምርጫዎችህን ለመምረጥ፣ የሕይወት መንገድህን ለመቀየስ፣ መነሻህን አሳምረህ ፍጻሜህን ለማስዋብ አንተ አንተን ሆነህ መገኘት አለብህ፡፡ ለራስህ የማታውቅ ከሆነ ሌሎች ባወቁትና በቀረፁት መንገድ ትከተላለህ እንጂ ራስህን አትመራም፡፡ ስታስብ፣ ስትመረምር፣ ስታሰላስል፣ ስታስተውል፣ አዲስ ሃሳብ ስትፈጥር ግን ችግሮችህን ትቀርፋለህ፣ መሰናክሎችህን ትሻገራለህ፣ ስልጣኔን ታመጣለህ፡፡ ራስህን ከሌሎች ባርነት ነፃ ታወጣለህ፡፡ አልያ ግን በመንጋው ተጠልፈህ በራስህ መንገድ ትመላለስ ዘንድ እንዳትችል አቅም ታጣለህ፡፡ ተከታይነት በራስህ ፀንተህ ለመቆም ሃይል እንዳይኖርህ ያደርግሃል፡፡ ተጎታች እንጂ መሪ አትሆንም፤ ጠባቂ እንጂ ሰጪ ትሆን ዘንድ አትችልም፡፡ የሰው ዓለም መፃተኛ እንጂ የራስህ ዓለም ሰሪ ለመሆን አይቻልህም፡፡ በተኮረጀ ሕይወት ዘመንንህን ትጨርሳለህ፡፡ እስኪ ሃሳብ ስጡበት👆              
إظهار الكل...
የትኩረት ለውጥ! ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት . . . 1.  ያልሆናችሁት ላይ ሳይሆን የሆናችሁት ላይ አተኩሩ፡፡ ያልሆናችሁት ላይ ስታተኩሩ የሆናችሁትን እውነተኛ ማንነት መኖር ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት እንዳገኛችሁት ሰው ሁኔታ ያልሆናችሁትን ማንነት እየለዋወጡ መኖር ነው፡፡ 2.  የሌላችሁ ላይ ሳይሆን ያላችሁ ላይ አተኩሩ፡፡ የሌላችሁ ነገር ላይ ስታተኩሩ ያላችሁን ነገር በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት ከሌላችሁ ነገር በመነሳት በዝቅተኝነት ስሜት የመመታት ሁኔታ ነው፡፡ 3.  የማታውቁት ላይ ሳይሆን የምታውቁት ላይ አተኩሩ፡፡ የማታውቁት ላይ ስታተኩሩ የምታውቁትን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት እውቀታችሁን ተጠቅማችሁ ከማደግ ይልቅ ስለማታውቁት ነገር በማሰብ ጊዜን መፍጀት ነው፡፡ ወሳኙና ጨዋታውን የሚለውጠው ነገር ትኩረታችሁ ነው፡፡ የሆናችሁት፣ ያላችሁና የምታውቁት ነገር ላይ ስታተኩሩና ቀና ብላችሁ በድፍረት ስትኖሩ፣ ያልሆናችሁት፣ የሌላችሁና የማታውቁት ነገር ላይ የመስራትና የማደግም እድላችሁ የሰፋ ነው፡፡ Dr እዮብ ማሞ
إظهار الكل...
👍 8
4