2 703
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-77 أيام
+4330 أيام
أرشيف المشاركات
Parent-School Communication Book Guidelines:
Dear Parents and Guardians,
This Communication Book serves as a vital bridge between home and school to support your child’s academic progress and personal development. To ensure effective collaboration, please review the following guidelines:
1. 👉 Parents/guardians are required to check this communication book every evening.
2. 👉Please sign the designated space daily to confirm that you have reviewed all teacher notes, announcements, and completed homework.
3. 👉 Official notices, letters, and circular slips attached to this book must remain intact and should not be removed.
4. 👉Homework is assigned daily to reinforce classroom learning. Families are encouraged to guide and support children; however, the work must be completed by the student.
5. 👉 Ensure that homework is completed neatly and thoroughly before signing.
Pay close attention to the continuous improvement of your child's handwriting and presentation.
6. 👉 Maintaining close contact with teachers and the school administration is essential. We welcome your feedback, questions, and suggestions written directly in this book.
7. 👉 Your active participation and engagement are the strongest foundations for your child’s educational success.
Thank you for your partnership and dedicated support!
Best regards,
School Administration
የወላጅና ትምህርት ቤት መገናኛ ደብተር መመሪያዎች:-
ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች፤ ይህ የመገናኛ ደብተር በትምህርት ቤቱ እና በቤት መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የልጅዎን የትምህርት እድገትና ስነ-ምግባር ለመከታተል የሚረዳ ዋና መሣሪያ ነው። ይህ ትብብር ውጤታማ እንዲሆን የሚከተሉትን መመሪያዎች እንድትተገብሩ በአክብሮት እንጠይቃለን፦
👉1. የቀን ተቀን ክትትል እና ፊርማ: ወላጆች/አሳዳጊዎች ይህንን መገናኛ ደብተር በየቀኑ በጥንቃቄ የማየት ኃላፊነት አለባቸው።
👉2. የተጻፉ መልእክቶችን፣ ማስታወቂያዎችን እና የተሰሩ የቤት ሥራዎችን መመልከትዎን ለማረጋገጥ በየቀኑ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ይፈርሙ።
👉3. ከደብተሩ ጋር ተያይዘው የሚላኩ ይፋዊ ደብዳቤዎች እና ማሳሰቢያዎች ከደብተሩ ላይ መገንጠል የለባቸውም።
👉4. የቤት ሥራዎች የተማሩትን ለማጠናከር በየቀኑ የሚሰጡ በመሆናቸው ከፍተኛ ትኩረት ይፈልጋሉ። ወላጆች ለልጃቸው አስፈላጊውን እገዛ እና መመሪያ መስጠት ያለባቸው ሲሆን፣ ሥራው ግን በራሱ በልጁ መሰራቱን ማረጋገጥ አለባቸው።
👉5. የቤት ሥራው በትክክል እና በጥራት መሰራቱን ካረጋገጡ በኋላ ይፈርሙ። በተጨማሪም የልጅዎ የእጅ ጽሕፈት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን አጥብቀው ይከታተሉ።
👉6. ከክፍል መምህራን እና ከተቋሙ ጋር በቅርበት መነጋገር ለተማሪው ስኬት ወሳኝ ነው። አስተያየትዎን፣ ጥያቄዎን ወይም ሀሳብዎን በዚህ ደብተር ላይ በመጻፍ ከመምህራን ጋር እንዲገናኙ እናበረታታለን።
👉7. የልጅዎን ስኬት ለማረጋገጥ እጅግ አስተማማኙ መንገድ የእርስዎ ንቁ ወላጅነት እና አዎንታዊ ተሳትፎ ነው።
ለስራችን ስኬት ለምናደርገው የጋራ ጥረት አስቀድመን እናመሰግናለን!
ከሰላምታ ጋር!
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር
ውድ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች፤
ዛሬ ከጀማሪ (PRE KG) እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎቻችን የትምህርት ቤት እና የወላጅ መገናኛ ደብተር (School-Parent Communication Book) የሰጠን መሆኑን እንገልጻለን።
ወላጆች ደብተሩን በተመለከተ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በመተግበር ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን፡
1. አስፈላጊ መረጃዎችን የመሙላት እና የመለበድ ስራ፡
በደብተሩ የመጀመሪያ ገጽ ላይ አስፈላጊውን መረጃ (የተማሪውን ሙሉ ስም፣ ክፍል፣ ንዑስ ክፍል እና የወላጅ ስልክ ቁጥር) በመሙላት ደብተሩ እንዳይበላሽ በፕላስቲክ (በፕላስተር) እንድትለብዱት እንጠይቃለን።
2. የቀን ተቀን ክትትል እና ፊርማ፡ ልጅዎ በየቀኑ የሚሰጡትን የቤት ስራዎች በደብተሩ ላይ ጽፎ/ፋ መምጣቱን/ቷን በመከታተል፣ የቤት ስራውን መስራቱን/ቷን አረጋግጠው በየቀኑ በፊርማዎ ያረጋግጡ።
3. ደብተሩን በየቀኑ መላክ፡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ ሁልጊዜ ይህንን መገናኛ ደብተር ይዘው መምጣታቸውን እባክዎ ያረጋግጡ። ደብተሩ ከተረሳ ደውለን ለማስመጣት የምንገደድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡ ለቀሪዎቹ ክፍሎች መገናኛ ደብተሩ በነገው ዕለት የሚሰጥ ይሆናል።
የልጅዎን ትምህርታዊ እድገት ለማፋጠን ለምናደርገው የጋራ ጥረት ስለምታደርጉልን ቀጣይነት ያለው ትብብር አስቀድመን እናመሰግናለን።
ከአክብሮት ጋር!
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር
Dear Esteemed Parents and Guardians,
Today, we celebrated the 19th National Flag Day under the theme: “Our Flag for National Consensus and Unity.”
Our students, teachers, and staff gathered to honor this special day with a colorful and meaningful program. During the event, the school’s administrative staff presented engaging sessions highlighting the history of our flag, the symbolism of its colors, and its significance as an symbol of unity and togetherness።
We extend our heartfelt gratitude for your continuous support as we work together to strengthen our children's moral values and national pride through these meaningful events.
Happy 19th National Flag Day!
Warm regards,
The School Administration
ውድ ወላጆች/ ህጋዊ አሳዳጊዎች፤
ዛሬ በትምህርት ቤታችን 19ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በተማሪዎቻችን፣ መምህራኖቻችን እና በመላው የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ ተከብሮ ውሏል።
በዕለቱም በት/ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች ስለ ሰንደቅ ዓላማችን ታሪካዊ ፣ ስለቀለማቱ ትርጉም ፣ እንዲሁም የሕብረትና የአንድነታችን ምልክትነቱን የሚገልፁ ዝግጅቶች ቀርቧል።
የልጆቻችን መልካም ስነ-ምግባር እና አገራዊ ፍቅር በእንዲህ አይነት ውብ አጋጣሚዎች እየጎለበተ እንዲሄድ ለምናደርገው ጉዞ ስለምታደርጉልን ያልተቋረጠ ድጋፍ እያመሰገንን፤ እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሳችሁ እንላለን።
ከአክብሮት ጋር!
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር
ውድ ወላጆች፦
ነገ ጥቅምት 02 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የብሔራዊ ሰንደቅ አላማ ቀን ለ19ኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ በሙሉ ቀን የትምህርት መርሃ ግብር ይከበራል።
በመሆኑም በተለይ የኬጂ ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲመጡ ከተቻለ ትንሿን ሰንደቅ አላማ ፤ የማይቻል ከሆነ ደግሞ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ወይም ቀይ ቀለማት ያላቸውን ፊኛዎች ይዘው እንዲመጡ በታላቅ አክብሮት ማሳሰብ እንወዳለን።
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር።
ለቱሉዲምቱ ፣ ቂሊንጦ እና አካባቢው ትንሿ ባስ ተጠቃሚ ወላጆች በሙሉ።
ውድ ወላጆች ከትላንት ጀምሮ የተፈጠረው የባሱ ቴክኒካል ችግር ሙሉ በሙሉ የተስተካከለ መሆኑን እያሳወቅን በእነዚህ ሁለት ቀናት በእናንተ በወላጆች እና በተማሪዎቻችን ላይ ስለተፈጠረው እንግልት ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን።
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር
ለቱሉዲምቱ ፣ ቂሊንጦ እና አካባቢው ትንሿ ባስ ተጠቃሚ ወላጆች በሙሉ።
ውድ ወላጆች ከትላንት ጀምሮ የተፈጠረው የባሱ ቴክኒካል ችግር ሙሉ በሙሉ እስከአሁን ድረስ ያልተፈታ በመሆኑ ስለተፈጠረው መጉላላት ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በዛሬው ዕለትም ልጆቻችሁን አማራጭ የትራንስፖርት መንገዶችን በመጠቀም ወደ ትምህርት ቤት እንድታመጧቸው ወይም እንድትልኳቸው በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር
ማክሰኞ/መስከረም 26 ቀን/2019ዓ.ም
ውድ ወላጆች የጥቅምት ወር የሰርቪስ ክፍያ መክፈያ ጊዜ ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 5፣ 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን በአክብሮት እያሳወቅን ክፍያውን ከፈፀሙ በኋላ የባንኩን ደረሰኝ ወደ ሂሳብ ክፍል በመላክ ክፍያውን እንዲያወራርዱ ማሳሰብ እንወዳለን። ክፍያውም የሚፈፀመው መውደድ አበራ ሳህሌ በሚል ስም
- በኦሮሚያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር
1366406700001 ወይም
- በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000481876609 መሆኑን በአክብሮት ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
እናመሰግናለን፡፡
የት/ቤቱ አስተዳደር፡፡
በትምህርት ስኬታማ ለመሆን ጠንክሮ ማጥናት ብቻ በቂ አይደለም - በብልሃት ማጥናት ነው።
ጥረትን ወደ ውጤት የሚቀይሩ ውጤታማ የአጠናን ስልቶቹ የሚከተሉት ናቸው:-
1. ስታጠኑ ግልጽ የሆነ ዓላማ ይኑራችሁ
_ የምታጠኑትን መጽሐፍ ወይም ደብተር እንዲሁ አትግለጡት- መጀመሪያ ለምን እንደምታጠኑ እወቁ።
_ እራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፡- በዚህ የጥናት ጊዜዬ ምን መረዳት ወይም ማሳካት እፈልጋለሁ?
_ በዓላማ የሚያጠና ተማሪ በትኩረት ያነባል፣ የተሻለ ያስታውሳል፣ ጊዜውን አያባክንም።
ምሳሌ፡- “ሳይንስ ወይም ባዮሎጂ አጠናለሁ” ከማለት ይልቅ “የሰው ልጅ ልብ እንዴት እንደሚሰራ ••• እረዳለሁ” በሉ።
2. ተግባራዊ የንባብ ስልትን ተጠቀሙ፣ እንዲሁ ለማንበብ አትሞክሩ
- ማንበብ ብቻውን በቂ አይደለም። አእምሮ በንቃት ሲሳተፍ አንድን ነገር በተሻለ ሁኔታ መረዳት ትችላላችሁ።
ለምሳሌ ይህንን ሞክሩ፦
_ ያነበባችሁትን ነገር በራሳችሁ አገላለጽ ወይም ቃላት ከልሱት።
- ፅንሰ-ሀሳቡን ለጓደኞቻችሁ አስረዱ።
- በምታጠኑበት ጊዜ ለራሳችሁ ጥያቄዎችን ጠይቁ።
👉 አንድን ፅንሰ-ሀሳብ በቀላሉ ማስረዳት ከቻላችሁ፣ በትክክል ተረድታችሁታል ማለት ነው።
3. ጊዜያችሁን በጥበብ አስተዳድሩ
- ጊዜ ትልቁ ሀብት ነው። ስኬታማ ተማሪዎች ተነሳሽነትን አይጠብቁም - የራሳቸውን የጥናት መርሃ ግብር አዘጋጅተው በዚያ ይመራሉ።
- ጊዜያችሁን በጥበብ ለመጠቀም የሚከተሉትን ቴክኒኮች/ዘዴዎች ተጠቀሙ፦
- አእምሮአችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ ከ25–50 ደቂቃዎች ያህል በትኩረት አጥኑ።
- በመካከል አጭር እረፍት ውሰዱ።
- ከባድ ለሆኑ ትምህርቶች ቅድሚያ ስጡ
👉 አስተውሉ: በየቀኑ የሚደረጉ ትናንሽ ነገር ግን ወጥ የሆኑ ጥረቶች በመጨረሻ ሰአት ላይ የሚኖር መጨናነቅን ይበልጣሉ።
4. አስቀድማችሁ በማቀድ በተደራጀ ሁኔታ አጥኑ
👉ግልጽ የሆነ እቅድ ጭንቀትን ይቀንሳል፤ በራስ መተማመንንም ይጨምራል።
👉 ማስታወሻ ደብተር ወይም እቅድ ማውጫ ተጠቀሙ።
👉 ትላልቅ የጥናት ተግባራትን ወደ ትናንሽ ደረጃዎች ከፋፍሏቸው።
👉 ዕለታዊ እና ሳምንታዊ የጥናት ግቦችን አዘጋጁ።
👉 ጊዜያችሁን ስታቅዱ፣ የወደፊት ሕይወታችሁን ትቆጣጠራላችሁ።
5. አዘውትራችሁ ከልሱ
- መርሳት ተፈጥሯዊ ነው—ነገር ግን ክለሳ መርሳትን ይፋለመዋል።
- በጥናት ወቅት የምታዘጋጇቸውን ማስታወሻዎቻችሁን ምንጊዜም በ24 ሰዓታት ውስጥ ከልሱ።
- ከዚህ በፊት የተጠኑ የተለያዩ ርዕሶችን በየሳምንቱ እንደገና ለማየት ሞክሩ።
- ያለፉ ጥያቄዎችን በመስራት ተለማመዱ
👉አስተውሉ: አንድን ነገር መደጋገም ችሎታን ይገነባል።
6. ማንበብ ብቻ ሳይሆን ለልምምድ ትኩረት ስጡ
- በተለይ እንደ ሂሳብ፣ ፊዚክስ ወይም ኬሚስትሪ ላሉ ትምህርቶች ልምምድ ሁሉም ነገር ነው።
- ኘሮብሌሞችን ለመፍታት ጥረት አድርጉ Solve Problems
-ማስታወሻዎችን (notes) ሳትመለከቱ እራሳችሁን ፈትሹ
👉 ከስህተቶቻችሁ ተማሩ
-ስህተቶች ውድቀቶች አይደሉም—ምርጥ አስተማሪዎች ናቸው።
7. ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግዱ
አካባቢያችሁ ስኬታችሁን ይቀርፃል።
- ስልካችሁን ከአጠገባችሁ አርቁ ወይም ድምፁን አጥፉት።
- ጸጥ ያለ የጥናት ቦታ ምረጡ።
- በአንዴ ብዙ ነገሮችን ከማከናወን ተቆጠቡ።
- ባለንበት ሃሳብን በሚከፋፍል ዓለም ውስጥ #ትኩረት ማድረግ ሃይልን የሚያጎናፅፍ ልማድ ነው።
8. ሰውነታችሁን እና እምሮዎአችሁን ተንከባከቡ
👉የደከመ አእምሮ ውጤታማ በሆነ መንገድ መማር አይችልም።
- በቂ እንቅልፍ አግኙ
- ጤናማ ምግብ ተመገቡ
- በየጊዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ
👉 ጠንካራ ሰውነት ጠንካራ አእምሮን ይፈጥራል።
9. በየጊዜው አቅማችሁን ማሻሻል እንደምትችሉ እምነት ይኑራችሁ
- ብዙ ተማሪዎች የሚወድቁት ከሌሎች ያነሰ የማሰብ ችሎታ ስላላቸው ሳይሆን በራሳቸው እምነት ስለሌላቸው ነው።
አስታውሱ፡-
👉ብልህነት (የማሰብ/የመማር አቅም) በጥረት ያድጋል።
- እያንዳንዱ ስኬታማ የሆነ ባለሙያ በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር።
- ያለፈው ውጤታችሁ የወደፊቱን አይገልጽም።
👉 ለራሳችሁ እንዲህ በሉ፡- “ማንኛውንም ትምህርት መማር እችላለሁ። አሻሽላለሁ።”
ከየካ ት/ጽ/ቤት ገጽ የተወሰደ
ዉድ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ነገ መስከረም 18 ቀን ፣ 2019 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት የሚቀጥል መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
እናመሰግናለን!
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር
