cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

ይኼ ገጽ የአመቱ ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው። " ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15 # ያጋሩ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 232
المشتركون
+324 ساعات
+147 أيام
+4330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🙏✞ ስንክሳር  ሐምሌ  9 ✞🙏 https://t.me/Sinksar በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ እንኩዋን ለጻድቅ #አባ ኅልያን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ 🌿✞ አባ ኅልያን ገዳማዊ ✞🌿 ጻድቁ ተወልዶ ያደገው ዐይነ ፀሐይ በምትባል የቀድሞ የግብፅ ክፍለ ሃገር ሲሆን ወላጆቹ ዲስጣና ካልሞና ይባላሉ:: እነርሱ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩና ገና በልጅነት ይህንኑ አጥብቀው አስተምረውታል:: ቅዱሱ ኅልያን ጾምን: ጸሎትን ብቻ ያይደለ በሥጋዊ ሙያውም የተመሰገነ አንጥረኛ ነበር:: በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው:: በተለይ ወርቅና ብር እየሠራ ይተዳደር: ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ሳለ አንድ ቀን ፈተና መጣበት:: አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የጀሮ ጌጥ (ጉትቻ) እንዲሠራላት ትጠይቀውና እርሱም ከወርቅ ይሠራላታል:: የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች:: እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው:: ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ:: ከፊቷ ላይ አማትቦ: ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ:: ሙሉ ሌሊት ሲያዝን አደረ:: ሊነጋጋ ሲል በልቡ ወሰነ:: ይሕችን ዓለም ሊተዋትም ቆረጠ:: በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ሃብቱ: ንብረቱ: ቤቱ: መሬቱ: ወርቁ: ብሩ አላሳሳውም:: ነዳያንን ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አካፈላቸው:: የተረፈችው የለበሳት ልብስ ብቻ ነበረችና ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ:: ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና 3 ቅዱሳን ስውራንን ሰደደለት:: ሦስቱም የብርሃን አክሊል ደፍተው: የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሰው: የብርሃን ዘንግ ይዘው ተገለጡለት:: እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ ውሃ ከሚፈስባት: ደኗ ለዐይን ደስ ከምታሰኝ ዱር አደረሱት:: አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም:: 3ቱ ቅዱሳን ከቦታዋ እንደ ገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት:: ሰግዶ ቀና ሲል ግን 3ቱም በአካባቢው አልነበሩም:: ተሠውረዋልና:: #አባ_ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ:: ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት: በስግደትም አጠነከረ:: ቅዱሱ የሚመገበው: የሚለብሰውም ቅጠል ነበር:: በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል አልነበረም:: ምክንያቱም ያቺ ዘንግ ሲመሽ ግሩም የሆነ ብርሃን ታወጣ ነበርና ነው:: መንገድ መሔድ በፈለገ ጊዜም ትመራው: ጐዳናውንም ታሳጥርለት ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ:: አጋንንት በተለያየ መንገድ ፈተኑት:: ግን አልቻሉትም:: አቅም ሲያጥራቸው ወደ ከተማ ሔደው: በሰው አርአያ ሽፍቶችን አናግረው ሊያስገድሉት ሞከሩ:: ነገር ግን ከፊት ለፊት እያዩት ሽፍቶቹ ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም:: እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ መንገዱን ያረዝምባቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ሽፍቶቹ በድካምና በውሃ ጥም ሊያልቁ ሆነ:: ጻድቁ ምንም እርሱን ለመግደል ቢመጡም አዘነላቸው:: ባሕሩን ያለ ታንኩዋ እየረገጠ ደረሰላቸው:: ከዱር ፍሬ አብልቶ: ንጹሕ ውሃም አጠጥቶ ሸኛቸው:: እድሜው እየገፋ ሲሔድ አንድ ቀን እነዛ በፊት የተሠወሩ 3 ቅዱሳን እንደ ገና ተገለጡለት:: በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ:: 3ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀበሩት:: ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀመጡትና እንደ ገና ተሠወሩ:: =>የቅዱሳን አምላክ ለእኛም የአባቶችን ረድኤት ይላክልን:: ከጻድቁም በረከትን ይክፈለን:: =>ሐምሌ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ ኅልያን ገዳማዊ 2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር) 3.ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት 4.ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ (በንስሃ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች) =>ወርሐዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) 3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) => "ጌታ ኢየሱስም "አትግደል: አታመንዝር: አትስረቅ: በሐሰት አትመስክር: አባትህንና እናትህን አክብር: ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ" አለው:: ጐበዙም "ይህንማ ሁሉ ከሕጻንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ:: ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?" አለው:: ጌታ ኢየሱስም "ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሒድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ:: መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ:: መጥተህም ተከተለኝ" አለው:: " (ማቴ. 19:18) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> ❖•°ೋ•❖ °   ❖•°ೋ•❖ ° 👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇 https://t.me/Sinksar https://t.me/Sinksar https://t.me/Sinksar
إظهار الكل...
ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

ይኼ ገጽ የአመቱ ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው። " ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15 # ያጋሩ

🙏✞ ስንክሳር  ሐምሌ  9 ✞🙏 https://t.me/Sinksar በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ እንኩዋን ለጻድቅ #አባ ኅልያን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ 🌿✞ አባ ኅልያን ገዳማዊ ✞🌿 ጻድቁ ተወልዶ ያደገው ዐይነ ፀሐይ በምትባል የቀድሞ የግብፅ ክፍለ ሃገር ሲሆን ወላጆቹ ዲስጣና ካልሞና ይባላሉ:: እነርሱ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩና ገና በልጅነት ይህንኑ አጥብቀው አስተምረውታል:: ቅዱሱ ኅልያን ጾምን: ጸሎትን ብቻ ያይደለ በሥጋዊ ሙያውም የተመሰገነ አንጥረኛ ነበር:: በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው:: በተለይ ወርቅና ብር እየሠራ ይተዳደር: ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ሳለ አንድ ቀን ፈተና መጣበት:: አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የጀሮ ጌጥ (ጉትቻ) እንዲሠራላት ትጠይቀውና እርሱም ከወርቅ ይሠራላታል:: የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች:: እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው:: ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ:: ከፊቷ ላይ አማትቦ: ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ:: ሙሉ ሌሊት ሲያዝን አደረ:: ሊነጋጋ ሲል በልቡ ወሰነ:: ይሕችን ዓለም ሊተዋትም ቆረጠ:: በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ሃብቱ: ንብረቱ: ቤቱ: መሬቱ: ወርቁ: ብሩ አላሳሳውም:: ነዳያንን ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አካፈላቸው:: የተረፈችው የለበሳት ልብስ ብቻ ነበረችና ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ:: ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና 3 ቅዱሳን ስውራንን ሰደደለት:: ሦስቱም የብርሃን አክሊል ደፍተው: የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሰው: የብርሃን ዘንግ ይዘው ተገለጡለት:: እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ ውሃ ከሚፈስባት: ደኗ ለዐይን ደስ ከምታሰኝ ዱር አደረሱት:: አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም:: 3ቱ ቅዱሳን ከቦታዋ እንደ ገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት:: ሰግዶ ቀና ሲል ግን 3ቱም በአካባቢው አልነበሩም:: ተሠውረዋልና:: #አባ_ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ:: ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት: በስግደትም አጠነከረ:: ቅዱሱ የሚመገበው: የሚለብሰውም ቅጠል ነበር:: በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል አልነበረም:: ምክንያቱም ያቺ ዘንግ ሲመሽ ግሩም የሆነ ብርሃን ታወጣ ነበርና ነው:: መንገድ መሔድ በፈለገ ጊዜም ትመራው: ጐዳናውንም ታሳጥርለት ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ:: አጋንንት በተለያየ መንገድ ፈተኑት:: ግን አልቻሉትም:: አቅም ሲያጥራቸው ወደ ከተማ ሔደው: በሰው አርአያ ሽፍቶችን አናግረው ሊያስገድሉት ሞከሩ:: ነገር ግን ከፊት ለፊት እያዩት ሽፍቶቹ ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም:: እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ መንገዱን ያረዝምባቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ሽፍቶቹ በድካምና በውሃ ጥም ሊያልቁ ሆነ:: ጻድቁ ምንም እርሱን ለመግደል ቢመጡም አዘነላቸው:: ባሕሩን ያለ ታንኩዋ እየረገጠ ደረሰላቸው:: ከዱር ፍሬ አብልቶ: ንጹሕ ውሃም አጠጥቶ ሸኛቸው:: እድሜው እየገፋ ሲሔድ አንድ ቀን እነዛ በፊት የተሠወሩ 3 ቅዱሳን እንደ ገና ተገለጡለት:: በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ:: 3ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀበሩት:: ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀመጡትና እንደ ገና ተሠወሩ:: =>የቅዱሳን አምላክ ለእኛም የአባቶችን ረድኤት ይላክልን:: ከጻድቁም በረከትን ይክፈለን:: =>ሐምሌ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ ኅልያን ገዳማዊ 2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት (ዘሐምስቱ አሕጉር) 3.ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት 4.ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ (በንስሃ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች) =>ወርሐዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) 3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) => "ጌታ ኢየሱስም "አትግደል: አታመንዝር: አትስረቅ: በሐሰት አትመስክር: አባትህንና እናትህን አክብር: ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ" አለው:: ጐበዙም "ይህንማ ሁሉ ከሕጻንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ:: ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?" አለው:: ጌታ ኢየሱስም "ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሒድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ:: መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ:: መጥተህም ተከተለኝ" አለው:: " (ማቴ. 19:18)    🙏🕊🕊🕊🙏 🌹🌹< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >🌹                    👇👇👇 (ይህ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ይቀላቀሉን)     🕊 https://t.me/Sinksar 🕊      🕊 https://t.me/Sinksar 🕊      🕊 https://t.me/Sinksar 🕊 
إظهار الكل...
ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

ይኼ ገጽ የአመቱ ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው። " ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15 # ያጋሩ

🙏 1
🌿† ስንክሳር ሐምሌ 8 †🌿 እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃን ወከዋክብተ ገዳም አቡነ ኪሮስ: አባ ብሶይ እና አባ ሚሳኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 🔔†††  አቡነ ኪሮስ ጻድቅ  †††🔔 የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው:: በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል:: አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው:: ተወልደው ባደጉባት ሃገር #ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል:: ወንድማቸው (ታላቁ #ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው: አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ ( #ገዳመ_አስቄጥስ) መጡ:: እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም:: ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ:: "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ #ቅዱስ_ዳዊት:: አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው:: አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ #አቡነ_በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል:: ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ:: "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል:: ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል:: አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ:: ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው: ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን: ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ #እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር:: ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ:: #ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም:: †  የበርሃው ኮከብ አባ ብሶይ  † ታላቁ አባ ብሶይ (ቢሾይ):- ¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ¤በመላእክት መሪነት የመነኑ ¤የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ባልንጀራ ¤የአባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር የነበሩ ¤በአጭር ጊዜ የብዙዎች አባት የሆኑ ሰው ናቸው:: ††† እንቅልፍን የማያውቁ ¤በ40 ቀን ብቻ እህል የሚቀምሱ ¤የጌታችንን እግር በየቀኑ እያጠቡ የሚመገቡ ¤ፈጣሪያቸውን በጀርባቸው ያዘሉ (ነዳይ መስሎ አግኝተውት) ¤በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተጉ ¤በርካታ ጻድቃንን የወለዱ ታላቅ የፍቅር ሰው ናቸው:: በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሰርተው:  ቤተ_ክርሰቲያንን በንጽሕናቸው አስደስተው: ሐምሌ 8 ቀን ዐርፈዋል:: ግብፅ ውስጥ የሚገኘው ገዳማቸው ዛሬም ቤተ አበው: ተአምራት የማይለዩትና ተወዳጅ ነው:: ቦታው #መካነ_ሱባዔ_ወመንክራት ነውና:: 🕊†  አባ ሚሳኤል ነዳይ †🕊 መቼም ያ ዘመን (4ኛውና 5ኛው ክ/ዘመን) እጅግ የተባረከ ነው:: ቅዱሳኑ በብዛት የባለጸጐችና የነገሥታት ልጆች ናቸው:: አባ ሚሳኤልም የኬልቄዶን ንጉሥ ልጅ ሳሉ መንነው በበርሃ ለ65 ዓመታት ተጋድለዋል:: በመጨረሻ ግን በደዌ ምክንያት ወደቁ:: ለ5 ዓመታት መነኮሳቱ ሲጠይቁዋቸው ቆይተው ሰለቹ:: ከዛም ለ15 ዓመታት ላበታቸው በግንባራቸው እየተቀዳ: ያለ ምንም ምግብ እያቃሰቱ በበዓታቸው ወድቀው ኑረዋል:: ቸሩ አምላክ ግን 4ቱን ሊቃነ መላእክት ( #ሚካኤል: #ገብርኤል: #ሩፋኤልና #ሳቁኤልን) አዞላቸው ሲጠብቁዋቸው ኑረዋል:: በዚህች ቀንም #አቡነ_ኪሮስ መጥተው አጽናንተው: ጌታችንንም ጠርተው እንዲያርፉ አድርገዋል:: መላእክት እያጠኑና እየዘመሩ ጻድቁ ቀብረዋቸዋል:: በመቃብራቸውም ላይ ፈውስ የሆነ ጸበል ፈልቁዋል:: እግዚአብሔር የእኛን ያይደለ የጻድቃኑን ቅድስና አስቦ ይራራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ሐምሌ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ኪሮስ ጻድቅ (አረጋዊና ገዳማዊ) 2.አባ ብሶይ ጻድቅ (ኮከበ ገዳም) 3.አባ ሚሳኤል ነዳይ (ጻድቅ) 4.አባ ቢማ ሰማዕት 5.አባ በላኒ ሰማዕት 6.ቅዱሳን አቤሮንና አቶም (ሰማዕታት) ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 4.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) "በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው:: የኃጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሠቢያ ለበረከት ነው::" (ምሳ. 10:7) "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" (መዝ. 36:28-31)               🙏🕊🕊🕊🙏 🌹🌹< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >🌹                    👇👇👇 (ይህ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ይቀላቀሉን)     🕊 https://t.me/Sinksar 🕊      🕊 https://t.me/Sinksar 🕊      🕊 https://t.me/Sinksar 🕊 
إظهار الكل...
ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

ይኼ ገጽ የአመቱ ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው። " ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15 # ያጋሩ

🙏 4👍 2
#የሥላሴን_መንበር የሥላሴ መንበር ቅዱሳን ከበውት ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት ድንግልን ከመሃል ሚካኤልን ከፊት አእላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍርሃት እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ይህን ልዩ ተአምር ሊያዩ የታደሉ በፅድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ #አዝ====== የቅዱሳን ሕብረት የቅዱሳን ሀገር ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር ፅድቅና ርህራሄ የተሞላሰማይ እግዚአብሔር ያድለን በትንሳኤ እንድናይ(፪)     #አዝ====== የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ይህን ልዩ ተአምር ሊያዩ የታደሉ በፅድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ               🙏🕊🕊🕊🙏 🌹🌹< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >🌹                    👇👇👇 (ይህ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ይቀላቀሉን)     🕊 https://t.me/Sinksar 🕊      🕊 https://t.me/Sinksar 🕊      🕊 https://t.me/Sinksar 🕊 
إظهار الكل...
ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

ይኼ ገጽ የአመቱ ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው። " ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15 # ያጋሩ

🙏 8👍 1
🙏 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.