📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚
الذهاب إلى القناة على Telegram
↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya
إظهار المزيد3 819
المشتركون
-524 ساعات
+1617 أيام
+15530 أيام
أرشيف المشاركات
الشيخ محمد بن زمران الهاجري ، وكلمات من ذهب عن دعاة الشر والفتنة ..
Repost from ጅብሪል ሱልጣን & ሙሀመድ ሰልማን
የቢድዓ ክፋት ከዚህም በላይ ነው :-
=========================
🌴قال التابعي الإمام أبو إدريس الخولاني:
لأَن أَرى فِي المسجِدِ نَارًا لا أَستَطِيعُ إِطفَاءَهَا أَحبُّ إِلَيَّ من أَن أَرَى فيه بِدعَةً لَا أَستَطِيعُ تَغيِيرَهَا .
ኢማም አቡ ኢድሪስ አል_ኸውላኒይ የተባሉት ታቢዕይ እንዲህ ይላሉ :-
መቀየር የማልችለው የሆነን ቢደዓ በመስጂድ ውስጥ ከሚመለከት ማጥፋት የማልችለው የሆነ እሳት መስጂድ ውስጥ ሲቀጣጠል ማየቱ ለኔ ይሻለኛል ።
كتاب السنة للمروزي (٩٩)📚
የቢድዓ አስከፊነቱ ከባድ ነው ምክንያቱም ቢደዓ ከእስልምና የሆነን ክፍል ነው የሚቀንሰው የቢድዓ መጨረሻው እስልምናን ማጥፋት ነው ምክንያቱም ቢደዓ ማለት የሌለን ነገር መጨመር ነው ይህ ዲናችን ደግሞ መጨመሪያ ትርፍ ቦታ ዬለውም ሙሉ የሆነ ዲን ነው ሙሉ በሆነ ነገር ደግሞ አዲስን ነገር ለመጨመር የግድ ካለው የሆነውን አንዱን ቦታ ማስለቀ ይፈልጋል ። ቢደዓዎች እየተጨማመሩ ከዲን የሆነው እየተቀነሰ በሄደ ቁጥር ደግሞ ዲን የሆነው እንዳለ ይጠፋና ዲን ያልሆነው መጤ የዲኑን ቦታ ይተካል ከዛ እስልምና ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል ። ሰይጣንም ዘንድ ለዚህ ነው ከወንጀል ይልቅ ቢደዓ የተወደደው ።
ከዚህ ለዲኑ ከመቆርቆር አኳያ ነው የሱና ሊቃውንቶች በተለያየ መልኩ ቢደዓን አጠንክረው የሚጠሉት አንዴ በጀርህና ተዕዲል ሌላ ግዜ በማስጠንቀቅ ቀን ተሌት የሚለፉት ። የቢደዓ ጠብታ ጠብ ባለች ቁጥር የሱና ኡለማዎች ባላየ ቢያልፏት ሌሎች ደግሞ የታላላቅ ኡለማዎችን ቁርዓን ሃዲስን የተደገፈ ፍርድ የሱ ኢጅቲሃድ ነው ብለው ባልሰማ ቢዘሏት እስልምና እስካሁን ባልዘለቀልን ነበር ። አላህ ዲኑን እጠብቀዋለሁ ብሏል ከሚጠብቅበት መንገድ አንዱ የጀርህና የተዕዲል ኡለማዎችን በየ ክፍለዘመኑ በመፍጠር ነው ። በየክፍለ ዘመኑ እስልምናን በጥልቀት አጥንተው ፍርድ የሚሰጡ ሊቃውንቶችን አላህ ፈጥሮልናል ኮሃላ የመጡ የነሱ ተከታዮችም ከቁርዓን ከሃዲስ የተደገፈ ፍርዳቸውን የግል አመለካከት ነው ብለው አልጣሉትም ተቀብለውታል እንጂ
የቢደዓ ቀልድ ፣ ትንሽና ጥሩ ዬለውም ትንሽ ትንሾች ተደራርበው ትልቅ ይሆናሉና ። ለዚህም ነው ትንሽም የቢደዓ ሽታ ያለው ነገር ሲከሰት ዛሬ ነጌ ሳይሉ የሚያስጠነቅቀት ።
ቢደዓ የሚሰራ አካል ሁሌም ትክክል ነኝ ብሎ ነው የሚያስበው በዚህ ተግባሩ ወደ አላህ እቃረባለሁ ብሎ ነው የሚየስበር እውነታው ግን አላህ ያለዘዘውን ነገር መስራት ከአላህ እንደሚያርቅ አላወቀም ። ይህ የቢደዓ ትልቁ አደጋው ነው ለዚህም ነው አላህ በቀርዓኑ እንዲህ ያለው :-
أَفَمَن زُيِّنَ لَهُ سُوءُ عَمَلِهِ فَرَآهُ حَسَنًا
መጥፎ ሥራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?)
ቢደዓ ነው የሚሰራው በእሱ እምነት ግን ዒባዳ እየሰራሁ ነው ብሎ ያምናል ። በርግጥ የታወቀን ወንጀል የሚሰራ ሰው ግን ይህን አያስብም ለምሳሌ አንድ ሰው ዘፈን ቢሰማ 100 % ወንጀል እየሰራ መሆኑን ያውቃል ( ከአንዳንድ ኢኽዋኖች ውጪ እንደነ ዩሰፍ አልቀርዳዊ አይነቶቹ ዘፈንም ስለሚፈቅዱ ነው እንዲሁም አንዳንድ አለዋቂዎች አላህ የሚል ቃል ያለበት ነገር ዘፈን አይደለም ብለው ከሚያስቡት ውጪ በርግጥ ) በተቃራኒው ዘመናዊ ሙዚቃ መሳይ ነሺዳ ተብዬዎችን የሚሰማ ሰው ግን በፍፁም ወንጀል እየሰራሁ ነው ብሎ አያስብም ። ወደ አላህ ለመቶበትም አያቅድም ። ዘፈን የሚሰማው ግን አንድ ቀን እቶብታለሁ እያለ ያቅዳል ።
ምክንያቱም :-
الَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا
እነዚያ እነሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ሕይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው፡፡
ሁሌም ወደ አላህ እየተቃረብኩኝ ነው ብሎ ነው የሚያስበው ።
አቡ ሙስዐብ
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Abumuseab
⚽️ "በኳስ ላይ ያለው ዕብደት የጋራ ሆኗል"
~ከሰልሰቢል መስጂድ ሙሐደራ የተወሰደ
📻 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር
♻️https://t.me/furiselsebla
♻️https://t.me/furiselsebla
📖صحيح مسلم للإمام مسلم بن الحجاج
👈الفن:الحديث
👈كتاب القدر - 02
📖رقم الحديث ٢٦٤٨-٢٦٥٦
🎙በተከበሩ ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም ሀፊዘሁላህ
👉👉ዘወትር ቅዳሜና ዕሁድ ጠዋት ከ1፡00-2፡30 እንዲሁም ከሰዓት ከዓሱር ሰላት በኃላ በቀጥታ ይተላለፋል
👉ቦታ ፉሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ
"نورها الله تعالى بمنه وكرمه بنور التوحيد والسنة "
ማስታወሻ
ይህ የደርስ ቅጂ ዛሬ እሁድ ሻዕባን 01-1445 ሂጅሪያ (የካቲት 03-2016 ) ከዓሱር ሰላት በኃላ በአቡበክር አስ'ሲዲቅ መስጂድ (ፉሪ) የተሰጠ ደርስ ነው ።
ትምህርቱን ለመከታተል ፡
https://t.me/abuhuzeyfashaikhmohammedzeyn
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam
🌴ኸንሳ ቢንት ዓምር (ረ.ዐ)🌴
➾ክፍል አንድ ❶
ከሙዛር ጎሳ የወጣችው ኸንሳ ሁለት ወንድሞች ነበሯት፡ ከአንደኛው ጋር በሁለቱም ወላጆቿ የምትገናኝ ሲሆን ከሌላው ጋር ግን አንድ ወላጅን ትጋራ ነበር፡፡ ከጎሳው አባላት ወጣቶች መካከል እነዚህ ሁለት ወንድሞች የተለየ ስፍራ እንደነበራቸውም ይነገራል፡፡
የጎሳው መሪ የነበሩት አባቷም በልጆቻቸው በእጅጉ ነበር የሚደሰቱት፡፡ ኸንሳ ሁለቱን ወንድሞቿን ከልቧ ነበር የምትወዳቸው፡፡ ኸንሳ (ረ.ዐ) አጅግ ሚዛናዊ የሆነ ሰብእናን የተላበሰች ከመሆኗም በላይ ጥልቅ የሆነ እውቀት ባለቤትም ነበረች፡፡ በዚህ ሰብእናዋ የተነሳ ታዲያ አባቷም ሆኑ ሁለቱ ወንድሞቿ ለኸንሳ የላቀ ክብር ነበራቸው፡፡ በነፃነት የምታስብ፤ ጀግና እና የብዙ ተሰጥኦዎች ባለቤት ነበረች፡፡ ከቅድመ ኢስላም ዘመን አንስቶ እስካሁን ድረስ የምትወሳበት የስነ-ጽሁፍ በተለይም የኪነ ጥበብ ክህሎቷ ነው። የእምነት ጥንካሬዋ ደግሞ በኢስላም ታሪክ ውስጥ የጎላ ስፍራን የቸራት እና ለአያሌ ሴት ሙስሊሞች ብርታት የሚሆነው ሌላው መለያዋ ነው፡፡
ሀዋዙን የተባለ ጎሳ መሪ የነበረው ጁረይጅ ቢን አሱማ ኸንሳን ለማግባት ጠይቆ ነበረ፡፡ ይህ እጅግ ባለፀጋ የነበረው ሰው በእድሜው የገፋ እና ከኸንሳ ጋር ተፈጥሯዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም አቻዋ ሆኖ ባለመገኘቱ ኸንሳ የራሷ ጎሳ አባል የሆነውንና ረዋሃህ ቢን አብዱል አዚዝ የተባለውን ወጣት አገባች፡፡
ኸንሳ (ረ.ዐ) ከዚህ ትዳሯ አብደላህ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ወለደች፡፡ ያም ሆኖ ይህ ትዳሯ ብዙም አልቆየም፡፡ ባሏ አብዱል እዚዝ ገና በወጣትነት እድሜው ሞተ፡፡
የአብዱል አዚዝን ሞት ተከትሎም ኸንሳ አብዱል ዒዛ የተባለ ሌላ ሰው አገባች፡፡ ሁለተኛው ባሏ ከሚገባው በላይ አበካኝ ከመሆኑም በተጨማሪ የቁማር፤ የወይን ጠጅ እና ከልክ ያለፈ የምግብ ፍቅር ነበረበት፡፡ በዚህም የተነሳ ያለውን ኃብት በሙሉ ጨረሰ፡፡ እናም በቤቱ ውስጥ የከፋ ችግር ገባ፡፡ በዚህም የተነሳ ኸንሳ ሳክሃር ወደተባለው ወንድሟ ዘንድ ሄደች። ወንድሟም ካለው ኃብት ግማሹን ለእህቱ አበረከተላት፡፡
ያም ሆኖ ግን አሁንም በድጋሚ የኸንሳ (ረ.ዐ) ቤት ድህነት አጠለለበት። ኸንሳም ለሁለተኛ ጊዜ ወንድሟ ዘንድ አመራች፡፡ ለእሀቱ ትልቅ ክብርና ፍቅር ያለው ሳሃር ኽንሳን አላሳፈራትም። ካለው ንብረት በማሰባባሰብ በድጋሚ ለእህቱ አበረክተላት። እንዲያም ሆኖ የኽንሳ ንብረት አሁንም የወንድሟ ሚስት አነስ ያለ ነገር እንዲሰጣት ባሏን መከረችው የሰሃርን ሚስት ይህንን ሀሳብ ያቀረበችው እህቱ የምታገኘውን ንብረት ሁሉ ከልክ በላይ አባካኝ የሆነው ባሏ ከማጥፋት ወደኋላ አይልም ከሚል ስጋት ነበር ያም ሆኖ ግን ሳክሃር ለእህቱ የሚያሳየውን ለጋስነት በዚያው በማሟላት በቅድመ ኢስላም ዘመን የለጋስነት አብነት ሆነ፡፡
ኸንሳ (ረ.ዐ) ለድህነት ሲዳርጋት የኖረው ሁለተኛው ባሏ ሲሞት ሚርድ አስ ቢን አሊ አሚር አሰላም የተባለ ስውን አገባች፡፡ የራሷ ጎሳ አባል ከሆነው ከዚህ ሶስተኛ ባሏ ሶስት ልጆችን አፈራች፡፡ ልጆቿ ዘይድ! ሙአዊያ እና ኡመር ይባሉ ነበር የመጨረሻ ክፍል ይቀጥላል........
ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ የሳሀቢያት ሴቶችን ታሪክ ያንብቡ ➴➴➴➴
https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk
https://t.me/+ZKXkcQYiRdcyMDFk
Repost from .
👆
ከላይኛው የቀጠለ
የአላህ ባሮች ሆይ ላዩቅኒዑኒ ላየልዚሙኒ የሚል አዲስ ፍልስፍና ሳይመጣ በፊት ዲኑ ይሄ ነው።
ዲን ሲመጣልህ ላዩቅኒዑኒ ላየልዚሙኒ ልትል ትችላለህ
እንዲሁም ዲኑ ይሄ ነው ስለዚህ በዚህ ስራ ስትባል ኢልዛም አደረጉኝ ልትል ትችላለህ!! አንተ ያላወከው ነገር ኢልዛም ገብቶህ ሳይሆን ሳታውቀው "የኩፍር ድሞክራሲ" አይት አስተሳሰብ ገብተህ ነው።
➻ የቢድዓ ባለቤቶችን ማስጠጋት የአላህን እርግማን ያመጣል።
عن علي رضي الله عنه قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم
" من أحدث حدثا؛ أو آوى محدثا؛ فعليه لعنة الله والملائكة والناس أجمعين "
الحديث متفق عليه
አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸው ከዓልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ በተወራ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ {{"አንድን ፈጠራ ( በዲን ላይ ) የፈጠረ ወይም የፈጠረን ያስጠጋን የአላህ ፣ የመላኢካዎችና የሰዎችም እርግማን በሱ ላይ ይሁን"።}}
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ከመልእክተኛው በላይ የፍልስፍና ሰዎችን ስሌት የምትከተል ከሆነ ይሄ ነው ግልጽ ጥመት። ግንዛቤ የለህ ሆኖ እንጅ ኢልዛም ያደረገህ ሸሪዓው ነው። ሌሎችም ደጋግ ቀደምቶችም እንደ ፍልስፍና ባለቤቶች የአስተያየታቸውንና የጥረታቸውን ጭማቂ ሳይሆን ይሄው ቀጥታ ከአላህ የመጣ ትእዛዝ ከመልእክተኛው (ዓለሂሶላቱ ወሰላም) የመጣውን ነው ያስተላለፉልን። ሀዲስ አይደለም። በድፍኑ ሊሳሳቱ ይችላሉ የሚሉ ወስዋሶች የሚያቀርብ የልብ በሽተኛ ነው።
➻ የቢድዓ ባለቤቶችን መስማት መድኃኒት ለሌለው በሽታ መጋለጥ ነው።
قال ابن مسعود رضي الله عنه: «لا تمكن صاحب هوى من أذنيك فيقذف فيهما داء لا شفاء له».
{ذم الكلام للهروي ٢٦٧
አላህ መልካም ሥቸውን ይውደድላቸው ሁለት እግሮቹ ከእሁድ ተራራ ይበልጥ ሚዛን ያላቸው ታላቁ ሰሀብይ አብደላህ ኢብኑ መሰዑድ እንዲህ በለዋል፦
{{ከስሜት ባለቤት ንግግር ሁለት ጆሮችህን ጠብቃቸው፣ በነርሱ (በሁለት ጆሮችህ ውስጥ) መድኃኒት የሌለው በሽታ ያስገባባሀልና}}
(ዘሙል ከላም ሊል ሀረውይ)
➻የቢድዓ ባለቤቶችን ማቀማመጥ ልብን ያሳምማል።
· وقال ابن عباس رضي الله عنه: لا تُجالِس أهل الأهواء؛ فإنَّ مجالستهم ممرضة للقلوب؛
{رواه أبو بكر الآجُرِّي في "الشريعة" }
አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ታላቁ የቁርአን ተንታኝና የነብያችን የአጎት ልጅ አብደላህ ኢብኑ አባስ እንዲህ ይላሉ፦
{{የቢድዓ ባለቤቶች አትቀማምጥ እነሱን ማቀማመጥ ልብን ያሳምማል}}
(አቡ በክር አል አጁሪ ሸሪዓ ላይ አውርቶታል)
➻የፈለገ አላህን ፈሪ ዛሂድም ቢመስሉ
قال الإمام البربهاري رحمه الله تعالى: وإذا رأيت الرجل مجتهدا في العبادة متقشفا محترقا بالعبادة صاحب هوى فلا تجالسه ولا تقعد معه ولا تسمع كلامه ولا تمشي معه في طريق، فإني لا آمن أن تستحلي طريقته فتهلك معه"
[شرح السنة:١٢٤]
አላህ ይዘንለላቸውና ታላቁ የቀደምት ሊቅ ኢማሙ አል በርበሀርይ እንዲህ ይላሉ፦
{{በዒባዳው ላይ ታጋይና በጣም የናጠ፣ ለጋሽም ዛሂድም የሆነን (ግን) የሥሜቱ ተከታይ (የቢድዓ) ሰው ካየህ ከሱ ጋር አትቀማመጥ፣ ንግግሩን አትስማ፣ በመንገድም ከሱ ጋር አትሂድ፣ (ምክንያቱም) ያለበትን የጥመት መንገድ #አቅልለህ ታየውና ከሱ ጋር ትጠፋለህ ብየ እፈራልሃለሁ}} (ሸርሁ ሱና 123)
➻የፈለገ ተውሒድና ሱናን የሚያንፀባርቁ ቢሆኑ
وقال مفضل بن مهلهل: لو كان صاحب البدعة إذا جلست إليه يحدثك ببدعته حذرته وفررت منه، ولكنه يحدثك بأحاديث السنّة في بدو مجلسه ثم يدخل عليك بدعته فلعلها تلزم قلبك فمتى تخرج من قلبك. 📚 [الإبانة (2/ 444)
ሙፈዶል ብን ሙሐልሐል- ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግሯል :-
"ከቢድዓ ባለቤት ዘንድ ከተቀመጥክ ፣ በቅድሚያ ቢድዓውን ቢነግርህ ኖሮ ትጠነቀቀው ነበር ፣ ከርሱም ትርቅ ነበር።
ነገር ግን በቅድሚያ የሱና ሐዲሶችን ነው የሚነግርህ። ከዚያም ቢድዓውን ያስገባልሀል። ልብህም ትይዛታለች። ከዚያ በኋላ ከልብህ መቸ ነው የምትወጣው?"
📚 አል-ኢባና (2/ 444)]
➻ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ስሚቀማመጥ ስለተደመረ
وقال الإمام البربهاري: وإذا رأيت الرجل يجلس مع أهل الأهواء فاحذره واعرفه فإن جلس معه بعد ما علم فاتقه فإنه صاحب هوى .
አላህ ይዘንላቸውና ኢማሙ አልበርበሀርይ እንዲህ ይላሉ፦
አንድ ሠው የሰሜት/የቢድዓ ባለቤቶች ጋር ሲቀመጥ ካየኸው ራቀው! በዚህ ዙሪያ ነገሮችን አሰረዳውና ካወቀ በኀላ አሁንም ከቢድዓ ባለቤት ጋ ከተቀመጠ እሱ ራሱ የቢድዓ ባለቤት ነውና ተጠንቀቀው (ሸርሁ ሱና)
وقال أبو داود السجستاني: قلت لأبي عبد الله أحمد بن حنبل: أرى رجلاً من أهل البيت مع رجل من أهل البدع، أترك كلامه؟قال: لا، أو تُعْلِمه أن الذي رأيته معه صاحب بدعة، فإن ترك كلامه وإلا فألحقه به، (1) [طبقات الحنابلة (1/ 160)]
አቡዳውድ አሲጅስታኒ ለኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሀምበል
አንድ የአህለል በይት (የሱናን ሰው) ከቢድዓ ሰው ጋር አየዋለሁና ንግግሩን ልተው (አላናግረው ወይ ) ብሎ ጠየቃቸው
እሳቸውም እንደሱማ አይደለም መጀመሪያ ያ ከርሱ ጋር ያየኸው የቢድዓ ሰው እንደሆነ ንገረው (ከነገርከው በኀላ) ከተመለሰ (ተመለሰ) ካልተመለሰ ግን ከርሱ ጋር አስጠጋው456)]
➻ ሱናን ሚሞግት የሚደባበቀው ይሄ ደግሞ የከፋ ነው።
قال ابن عون: الذي يجالس أهل البدع أشد علينا من أهل البدع. [الإبانة (2/ 273)]
ኢብኑ አውን እንዲህ ይላሉ፦
ያ የቢድዓ ባለቤትን የሚያቀማምጥ፣ በኛ ላይ ከቢድዓ ባለቤቱ ይበልጥ የከፋ ነው
➻ቢደባበቅም ሸሪዓው ያስቀመጠበት መለያ አለው። በጎደኞቹ ይለያል
وقال الأوزاعي: من ستر علينا بدعته لم تَخْفَ علينا أُلفته " [الإبانة (2/ 479]
ኢማሙል አውዛዒይ እንዲህ ይላሉ፦ ቢድዓውን የደበቀብን ሰው በተላመዳቸው ሰዎች እንለየዋል
وقال محمد بن عبيد الغلابي:" يتكاتم أهل الأهواء كل شيء إلا التآلف والصحبة" [الإبانة (2/ 479]
ኡበይዲ አል ጉላብይ እንዲህ ይላል፦ የቢድዓ ባለቤት ሁሉን ነገር ይደብቃል የተላመደውንና ጎደኛውን ሲቀር (ማንነቱ በጎደኛው ይታወቃል)
➻በሌላ በምን ይለያል ሱና ሰዎችን ሲዋጋ
قال أبو حاتمٍ الرازيُّ: «علامة أهل البدع الوقيعةُ في أهل الأثر، ». [عقيدة السلف (١٠٥)]
«አላህ ይዘንላቸው አቡ ሀቲም አራዚይ እንዲህ ብለዋል፦ «የቢድዓ ባለቤቶች ምልክት የሱና ሰዎችን (መወረፍ) ማጠልሸት ነው።» (ዐቂደቱ አሰለፍ 105)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abdurhman_oumer
📌የኢብኑ ሙነወር የተቀየረው አቋም
የሞጣን ቃጠሎ በተመለከት ኢኽዋኖችን የኮነነበት ንግግር
1,ሲሰበስቡ አናምናቸውም (ኢኽዋኖችን ማለቱ ነው)
2,ሪፖርት ሲያደረጉ አናምናቸውም
3,ሲያከፋፍሉ አናምናቸውም
✏️የአሁኑ አቋሙን በተመለከተ የራሱን ፁሁፍ እንደሚከተለው አሰፍረዋለሁ
▶️▶️▶️▶️▶️▶️▶️▶️▶️▶️▶️
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ትግራይ ላይ ያደረጉት መልካም ስራ ይበል የሚያሰኝ ነው። ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ። አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል
እነ ኢብኑ ሙነወር አቋም ቀይረዋል ስንል በመረጃ ነው!!
https://t.me/abdu_somed
https://t.me/abdu_somed
Repost from قناة دروس فضيلة الشيخ محمد زين بن آدم الحبشي - Sheikh MuhammedZain Adam - ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም
አሁን ቀጥታ ስርጭት
ክፍል - 40
سنن النسائي
7 - كتاب الأذان
(٩) المؤذنان للمسجد الواحد
رقم الحديث ٦٣٦
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam?livestream
🌍የቡሉጉል መራም ሚን አዲለቲል አህካም ማብራሪያ - ክፍል 285
👉ሐዲስ ቁጥር 1508-
🎙🎙🎙አቅራቢ
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም ሀፊዘሁላህ
🌍بلوغ المرام من أدلة الأحكام -285
📝تأليف: الحافظ بن حجر العسقلاني رحمه الله تعالى
🎙لفضيلة الشيخ محمد زين بن الشيخ آدم حفظه الله ورعاه
📖كتاب الجامع
باب الترهيب من مساوي الأخلاق
👈رقم الحديث (١٥٠٨-)
👉ዛሬ ሰኞ ሻዕባን 02-1445 (የካቲት 04-2016) የተሰጠ ደርስ ነው ።
።
👉👉ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከሱብሒ ሰላት በኃላ በቀጥታ ይተላለፋል
👉ቦታ ፉሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ
"نورها الله تعالى بمنه وكرمه بنور التوحيد والسنة "
https://t.me/abuhuzeyfashaikhmohammedzeyn
Or
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam
👉አዲስ _ረድ ቁ:01_A የኸድር ከሚሴ የግንዛቤ ድክመትን ማጋለጥ
⏩ሰሞኑን ይህ ሚስኪን ግለሰብ በታላቁ አሊም ሸይኽ አብዱል ሀሚድ አለተሚ ላይ የዘባረቀበት ንግግር ምን እንደሆነ? (ከድምጽ ማስረጃ ጋር)
↕️የሸይኹ ንግግር የተገጫጨ ነው ብሎ ያነሳው ድምጽ እውን እሱ እንዳለው ነውን?
↘️እጅግ የሚገርመው የግለሰቡ የማስተዋልና የግንዛቤ ችግሩ ምን ያክል የዘቀጠ እንደሆነ?(ከድምጽ ማስረጃ ጋር)
🔄ማን ይሆን የኡለማዎችን ንግግር በትር (በመቁረጥና) በተበላሸ አረዳዱ የሚታወቀው? (ከድምጽ ማስረጃ ጋር)
🔀ከዚህ በፊት ለተምይኡ በሽታ በፊት የጠቀሳቸውን ኡለማዎች ሸይኽ ረቢእና ሸይኽ ኡበይድ በኢልዛም ጉዳይ ምን ይላሉ?(ከድምጻቸው ማስረጃ ጋር)
↘️ሶስቱ የኢልዛም አይነቶች↙️
👉የሰለፍዮች አልዛም ምን አይነት ነው?
👉የሙመይአዎች ኢልዛም ምን አይነት ነው?
👉የሀዳድዮች ኢልዛም ምን አይነት ነው?
⤴️እነሱ የሚጠቅሷቸው የሱና ኡለማዎቻችን የትኛውን ኢልዛም ነው የተቃወሙት?
⏯የሸይኽ አብደል ሀሚድን ንግግር የተገጫጨ መስሎህ ከምትዋልል መጀመሪያ ንግግራቸውን ና ከላይ የተጠቀሱትን የኢልዛም አይነቶች ለይተህ አጥናቸው!!
🎙በኡስታዝ ሙባረክ ኢብራሒም አቡል ቡኻሪ (ሀፊዘሁላህ)
👇👇👇
t.me/mubarekabulbukhary
t.me/mubarekabulbukhary
t.me/mubarekabulbukharyRepost from Abu Imran Muhammed Mekonn
ለሰለፍዮች በሙሉ
🏝🏝🏝🏝🏝
➧
የካቲት 9 እና 10 2016 E.C በእነሞር ወረዳ ጉንችሬ ክ/ከተማ ካዕብ መስጂድ ላይ የሀገረችን ሰለፍይ መሻኢኾች የሚሳተፉበት ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶላችኋል።
➻ በዚህ ፕሮግራም ላይ ከሚሳተፉት መሻኢኾች ውስጥ፦
1— ሸይኽ ሐሰን ገላው (ባሕር ዳር)
2— ሸይኽ ዐ/ሐሚድ ያሲን ( ለተሚ )
3— ሸይኽ ዐ/ከሪም አሕመድ (አምቡዬ)
4— ሸይኽ አቡ ዘር አቡ ጠልሓ (ኮምቦልቻ)
5— ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (ኮምቦልቻ)
6— ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት (ሓራ)
7— ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ባሕር ዳር)
8 — ሸይኽ ጣሃ ኸድር (ሸገር )
9— ሸይኽ ሙባረክ ሑሰይን (አል ወልቂጤ)
10— ሸይኽ ዐ/ናስር አማን (ጉንችሬ ከዕብ መስጂድ)
11— ሸይኽ አሕመድ አወል (ወረታ)
12 — ሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ (ኦን ላይን )
🪑🪑🪑 ከኡስታዞች
1— ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን
2— ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ ( አቡ ሐመውያ) ኦንላየን
3— ኡስታዝ ሙሐመድ ኪርማኒ
4— ኡስታዝ ዐ/ቃድር ሐሰን ኡቡ ዐ/ራሕማን
5 – ኡስታዝ ሲራጅ (ወራቤ)
6 – ኡስታዝ ሰይፈዲን (ወላኢታ)
7 – ኡስታዝ ሙሐመድ አሚን ( ሸዋሮበት)
8— ኡስታዝ ኑረዲን አቡ ዚክራ ( መርሳ)
9— ኡስታዝ ዐ/ራሕማን (መርሳ)
10— ኡስታዝ ሙሐመድ ( አል ወልቂጤ )
11— ኡስታዝ ሙባረክ (ኡቡል ቡኻርይ)
12— ኡስታዝ ዐብዱ ሰመድ (አቡል ፊርደውስ)
13— ኡስታዝ ኑር አዲስ (ቡታጀራ)
14 ኡስታዝ ሱልጣን አቡ ኑዐይም
https://t.me/AbuImranAselefy/7943👉አዲስ _ረድ ቁ:01_A የኸድር ከሚሴ የግንዛቤ ድክመትን ማጋለጥ
⏩ሰሞኑን ይህ ሚስኪን ግለሰብ በታላቁ አሊም ሸይኽ አብዱል ሀሚድ አለተሚ ላይ የዘባረቀበት ንግግር ምን እንደሆነ? (ከድምጽ ማስረጃ ጋር)
↕️የሸይኹ ንግግር የተገጫጨ ነው ብሎ ያነሳው ድምጽ እውን እሱ እንዳለው ነውን?
↘️እጅግ የሚገርመው የግለሰቡ የማስተዋልና የግንዛቤ ችግሩ ምን ያክል የዘቀጠ እንደሆነ?(ከድምጽ ማስረጃ ጋር)
🔄ማን ይሆን የኡለማዎችን ንግግር በትር (በመቁረጥና) በተበላሸ አረዳዱ የሚታወቀው? (ከድምጽ ማስረጃ ጋር)
🔀ከዚህ በፊት ለተምይኡ በሽታ በፊት የጠቀሳቸውን ኡለማዎች ሸይኽ ረቢእና ሸይኽ ኡበይድ በኢልዛም ጉዳይ ምን ይላሉ?(ከድምጻቸው ማስረጃ ጋር)
↘️ሶስቱ የኢልዛም አይነቶች↙️
👉የሰለፍዮች አልዛም ምን አይነት ነው?
👉የሙመይአዎች ኢልዛም ምን አይነት ነው?
👉የሀዳድዮች ኢልዛም ምን አይነት ነው?
⤴️እነሱ የሚጠቅሷቸው የሱና ኡለማዎቻችን የትኛውን ኢልዛም ነው የተቃወሙት?
⏯የሸይኽ አብደል ሀሚድን ንግግር የተገጫጨ መስሎህ ከምትዋልል መጀመሪያ ንግግራቸውን ና ከላይ የተጠቀሱትን የኢልዛም አይነቶች ለይተህ አጥናቸው!!
🎙በኡስታዝ ሙባረክ ኢብራሒም አቡል ቡኻሪ (ሀፊዘሁላህ)
👇👇👇
t.me/mubarekabulbukhary
t.me/mubarekabulbukhary
t.me/mubarekabulbukharyRepost from ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
የዲን አጭበርባሪዎቹ የኢልያስ አህመድና የሙነወር ልጅ በሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ላይ የቀጠፉት ቅጥፈት ሲጋለጥ!!
—————
የቅጥፈት ማሽነሪዎቹ ኢልያስና የሙነወር ልጅ ህዝበ ሙስሊሙን ሐቅና ባጢልን በማደበላለቅ ማምታታታቸውንና ማጭበርበራቸውን እንደቀጠሉበት ነው። ይህ ተግባር አምላካችን አላህ አይሁዶችን እንዲህ በማለት የወቀሰበት አደገኛ ተግባር ነው:-
وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
«እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡» አል-በቀረህ 42
እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ኢኽዋኖች የዲን ነጋዴዎች እንደሆኑ አብዘሃኛው ሰው ነቅቶ ነበር፣ አሁን ግን ከኢኽዋኖች በላይ በኢኽዋኖች ምትክ የዲን ነጋዴ ሆነው ብቅ ያሉት ቆሻሻ የሆኑት ሙመይዓዎች ናቸው!!። ማህበረሰቡ በተለይ (የሱንናው ጀመዓ) በኢኽዋኑል ሙስሊሚን በፍጥነት ከነቃው በላይ በሱንና ካንሰር በሆኑት ሙመይዓዎች ሊነቃ ይገባል!!። ለዛሬ ወደተነሳሁበት ነጥብ ልመለስና የአላህ ፈቃድ ከሆነ ሰፋ ባለ መልኩ እመለሳለሁ። እንደሚታወቀው የቢድዐህ ባለ ቤቶች ብዥታ እንጂ ማስረጃ የላቸውም!!። በሰሞኑ የዲን አጭበርባሪዎቹ ኢልያስ አህመድና የሙነወር ልጅ በተካነው ውሸትን የማቀነባበር ፅሁፋቸው የቢድዐህ ባለ ቤቶችን ተንኮል በማጋለጥ ወደር የሌላቸው በሆኑት ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ላይ "የጀርህና ተዕዲል ነጥብ የኢጅቲሃድ ነጥብ ነው" ብለው እንደተናገሩ አስመስለው ሀሳባቸውን በመቆራረጥ የቀጠፉት ቅጥፈት ላይ ሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) ያጋለጡበትን ፅሁፋቸውን ወደ አማርኛ መልሼ ለሐቅ ፈላጊ አንባቢያን እንዲቀል ላቀርብላችሁ ወደድኩ።
ከዛ በፊት ግን የዲን አጭበርባሪዎቹ ኢልያስ አህመድና የሙነወር ልጅ ለማጭበርበር እንዲረዳቸው የተጠቀሙትን የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህን (ረሂመሁላህ) ንግግር እንደሚከተለው ለማስቀመጥ ወደድኩ…
وكلام يحيى بن معين والبخاري ومسلم وأبي حاتم وأبي زرعة والنسائي وأبي أحمد بن عدي و الدارقطني وأمثالهم في الرجال وصحيح الحديث وضعيفه هو مثل كلام مالك والثوري والأوزاعي والشافعي وأمثالهم في الأحكام ومعرفة الحلال من الحرام
የሙነወር ልጅ ለተምይዕ አካሄዱ በሚመቸው መልኩ እንደሚከተለው ተርጉሞታል:- "የሕያ ብኒ መዒን፣ ቡኻሪይ፣ ሙስሊም፣ አቢ ሓቲም፣ አቢ ዙር0፣ ነሳኢይ፣ አቢ አሕመድ ብኒ ዐዲይ፣ ዳረቁጥኒይ እና መሰሎቻቸው በዘገባ ሰዎች ላይ እና በሶሒሕና ዶዒፍ ሐዲሥ ብይን ላይ የሚናገሩት ንግግር ልክ ማሊክ፣ ሠውሪይ፣ አውዛዒይ፣ ሻፊዒይና መሰሎቻቸው በፊቅህ ህግጋትና የሐላልና ሐራም እውቀት ላይ እንደሚናገሩት ንግግር ነው።"
መቼም ጃሂል ድፍረት ተስጥቶታልና ቀጠል አደርጎ እንዲህ አለ:- "ስለዚህ! ልክ በፊቅህ ርእስ ላይ የአንድን ኢማም ንግግር በጭፍን መውሰድ እንደማይገባው በሐዲሥ ብይን ላይ፣ በአስተላላፊዎች ትችትና ሙገሳ ላይ የአንድን ኢማም ንግግር በደፈናው መውሰድም ግዴታ አይሆንም። ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም። ይልቁንም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ናቸው ረሒመሁላህ።” ውሸታም!!
ሸይኽ ሑሰይን (ሀፊዘሁላህ) ይህን የማጭበርበር ተግባራቸውን ሲያጋልጡ እንዲህ አሉ:-
“ይህ ኢልያስ አህመድና ኢብኑ ሙነወር የተምይዑን መንገዳቸውን ለማጠናከር ብለው ወደ ኢብኑ ተይሚየህ በማስጠጋት የጠቀሱት ንግግር፣ እርሱም ሸይኹ'ል ኢስላም "ተብዲዕ ወይም ጀርህና ተዕዲል ከኢጅቲሃድ ነጥብ ነው ብለው እንደሚያምኑ" አድርገው ማቅረባቸው በሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ላይ ግልፅ የሆነ ቅጥፈት ነው!!። ኢብኑ ተይሚየህ የተናገሩት ንግግር ከአላህ ውጭ ባለ አካል እርዳታ መጠየቅ እንደሚፈቀድ አድርጎ ደካማና ቅጥፈት የሆኑ ሀዲሶችን የጠቀሰውን በክሪ የሚባለውን ሱፊይ ሙብተዲዕ ለማስገደድ ነው። "የጀርህና ተዕዲል ባለ ቤቶች ይህ ሀዲስ ውዳቄ (ቅጥፈት) በመሆኑ ብይን መስጠታቸውን ግልፅ በማድረግ የሰጡትን ብይን መቀበል ደግሞ ግዴታ እንደሆነ ግልፅ እያደረጉ ነው። ምክንያቱም የጀርህና ተዕዲል ሰዎች በዚህ ዘርፍ የተካኑ የእውቀት ሰዎች ስለሆኑ፣ ልክ የፊቅህ ሰዎች በሀላልና በሀራም በህግጋትና በፊቅሂ ነጥቦች ልዩ ተሰጥዖ እንዳላቸው እነዚህም የጀርህና ተዕዲል ሰዎች የልዩ ተሰጥዖ ባለ ቤቶች ናቸውና ልንቀበላቸው ግድ ይለናል።" ነው ያሉት። በድጋሚ ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) በበክሪ ምላሽ በሰጡበት ኪታብ በራሱ ላይ እንዲህ ይላሉ:- “…ነገር ግን አላህ አበጣሪ በሆኑ የጀርህና ተዕዲል ባለ ቤቶች ሰበብ ሐቅና ባጢልን ለይቷል።” [አር-ረድ ዐለል በክሪ 170]
ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) በድጋሚ ገፅ 171 ላይ እንዲህ አሉ:- “በዒልም አልጀርህ ወትተዕዲል ላይ ያለው እውቀት ለባለቤቶቹ የሚደመጡ (የሚቀበሏቸው) እውቀት ነው። ምክንያቱም ልክ ህግጋት ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ሊቃውንቶች ልዩ እውቀት እንዳላቸው እነዚህ የጀርህና ተዕዲል ሊቃውንቶችም የተለያዩ መንገዶችና የሚለዩበት ልዩ የሆነ እውቀት አላቸውና።” የሸይኹል ኢስላም (ረሂመሁላህ) ንግግር እዚህ ላይ አበቃ።
ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) ሱፊይ የሆነው በክሪ ላይ የተቀጠፉ የሆኑ ሀዲሶችን ማስረጃ አድርጎ በመጠቀሙ ምላሽ እየሰጡት እያለ እንዴት በተብዲዕ (በጀርህና ተዕዲል) ዙሪያ ኺላፍ አለ ብለው ይናገራሉ?፣ ይልቁንም ኢብኑ ተይሚየህ የጀርህና ተዕዲል መሪዎች ብይን የሰጡበትን ሀዲስ መቀበል ግዴታ መሆኑን ነው ግልፅ ያደረጉት። ምክንያቱም በዘርፉ ላይ የልዩ ተሰጥዖና እውቀት ባለ ቤት ስለሆኑ። እናንተ ሙመይዖች ሆይ! አዕምሯችሁ የት ነው ያለው?!፣ በእርግጥም ከሰለፎች “ሙብተዲዕ አዕምሮ የለውም” ያለ አካል እውነት ተናገረ።
እኔ በሙመይዐህ ሸይኾች በኢልያስ አህመድና በሙነወር ልጅ በከደር ከሚሴ አልገረምም፣ ይልቅ የምገረመው ንግግራቸውን በሚቀበሉና ሙመይዕ ከሆነው ዐሊይ አልሀለቢ ዌብሳይት እንደማስረጃ አድርገው የሚያቀርቧቸውን ብዥታቸውን በሚቀበል ሰው ነው የምገረመው።
ታጋይ የሆኑ የዲን ተማሪዎች የታሉ???!! ለምንድነው እነዚያ ሙመይዓዎች እንደ ምንጭ አደርገው የሚጠቀሟቸውን ቦታዎች የማታጠኑዋቸው? ምክንያቱም ማምታቻቸውንና ውሸታቸውን እንድታውቁባቸው።
በአላህ ፈቃድ የሙመይዓ መንሀጅ ጀርህና ተዕዲልን በተመለከተ የሀዲስን ማስረጃነት ከአዕምሮ ከተጋጨ ውድቅ ከሚያደርጉ ጭፍራዎች ጋር እንደሚገናኝ እናጋልጣለን።” የዶ/ር ድንቅ ምላሽ እዚህ ላይ አበቃ። ከዐረቢኛ ወደ አማርኛ ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
ዶ/ር ሸይኽ ሑሰይን አስ-ሲልጢ አላህ በሰጣቸው እውቀት የሙመይዓን መርዝ በማክሸፍ ረገድ ለተወጡትና እየተወጡት ላለው ትልቅ ሀላፊነት አላህ በሐቅ ላይ በማፅናት በአዱኒያም በአኼራም አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸው!!
ለማንኛውም ኢልያስ አህመድና የሙነወር ልጅ ያለ ፊልዳችሁ ገብታችሁ በጀርህና ተዕዲል ነጥብ ላይ ለስሜታችሁ የምትገጥም ነገር ካገኘን ብላችሁ ስትኳትኑ በርእሱ ላይ ጭልጥ ያላችሁ መሀይምነታችሁን የማታውቁ ድርብ መሀይሞች መሆናችሁን ነው አደባባይ እያወጣችሁት ያላችሁት!!።
አላህ ከመገለባበጥና ከዲን አጭበርባሪነት ይጠብቀን!!
የፅሁፉ መግቢያ:- ✍🏻ኢብን ሽፋ
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
Repost from قناة دروس فضيلة الشيخ محمد زين بن آدم الحبشي - Sheikh MuhammedZain Adam - ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም
🔴 አሁን ቀጥታ ስርጭት
📚ሸርሑ ኢብኒ ዐቂል
ዐላ አልፊየቲ ብኒ ማሊክ -ክፍል 187-
النسب
🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም
የላይቩ ሊንክ
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam?livestream
Repost from « ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም፡፡
ምርጥ ጅልባብ ጥራት. ያለው. ጅልባብ
»ለምትፈልጉ አድራሻ
0530606479
https://t.me/umufewzan_asslefiya/1333
https://t.me/umufewzan_asslefiya/1333
