ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

إظهار المزيد
2 792
المشتركون
+124 ساعات
+87 أيام
+2030 أيام
أرشيف المشاركات
የአገልግሎት ዜና መስከረም 11/2019 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤታችን የበጎ አድራጎት ክፍል ከበጎ አድራጊ ምዕመናን እና ከአባላት ከሚያገኘው ድጋፍ በእየወሩ በቅዱስ ሚካኤል ስም ለነዳያን የቃለ እግዚአብ
+9
የአገልግሎት ዜና መስከረም 11/2019 ዓ.ም የሰንበት ት/ቤታችን የበጎ አድራጎት ክፍል ከበጎ አድራጊ ምዕመናን እና ከአባላት ከሚያገኘው ድጋፍ በእየወሩ በቅዱስ ሚካኤል ስም ለነዳያን የቃለ እግዚአብሔር እና የዝክር መርሐግብር ያከናውናል። የመስከረም ወርን በትላንትናው ዕለት በጥሩ ሁኔታ ያከናወነ ሲሆን፤ የዕለቱን ትምህርት በወጣት ካሳሁን እሸቱ ተሰጥቷል። በተያያዘ መረጃ አቅም ለሌላቸው አባላትና ለአካባቢ ምዕመናን ልጆች የቀለም ትምህርት መማሪያ ግብአቶችን የክፍሉ ተጠሪ አቶ ተሾመ እንዳለ እና የሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ ወጣት አበራ መላኩ በተገኙበት ስጦታውን ሰጥተዋል። አገልግሎቱን ለመደገፍና ለማገዝ በስልክ ቁጥር 0911091598/0909887744 በገንዘብ ለሚደግፉ ፦ 1000779793258 (ዳዊት አበበ እና ተሾመ እንዳለ) "ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።" መዝ 41፥1 ድጋፍ ላደረጋችሁልን ሁሉ አምላከ ነዳያን የነፍስ ዋጋ ያድርግላችሁ! ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

"...#ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ። እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር #እግዚአብሔርን_የሚያመልክና_የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።..."
"...#ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ። እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር #እግዚአብሔርን_የሚያመልክና_የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።..." በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

መስከረም 10/2019 ዓ.ም የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በክረምት ወቅት ለሁለት ወራት ሲማሩ የነበሩ ሕጻናት፤ ማዕከላውያን እና ወጣቶችን ትላንት መስከረም
+9
መስከረም 10/2019 ዓ.ም የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በክረምት ወቅት ለሁለት ወራት ሲማሩ የነበሩ ሕጻናት፤ ማዕከላውያን እና ወጣቶችን ትላንት መስከረም 9/2019 ዓ.ም እና ዛሬ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በዕለተ ሰንበት በምዕመናን ፊት የምርቃት መርሐግብር ተካሂዷል። በተለይ ለማዕከላውያን እና ወጣት ተማሪዎች ሕይወት ተኮር የሆኑ ትምህርቶችን በማሰናዳት ከ 10 በላይ መምህራንን በማሳተፍ ያስተማረች ሲሆን፤ ለመምህራኑና ለተማሪዎች በደብራችን አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ጸሐይ ቆሞስ አባ ብርሃነ ሥላሴ አስፋው የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። በዕለቱም ክቡር አስተዳዳሪያችን የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ከዚህም በላይ እንዲስፋፋ እና በመላው ዓለም ተደራሽ እንዲሆን ዘመኑን በዋጀ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ጠቅሰው፤ ለዚህ አገልግሎት መጠናከር የሚዲያ ግብዓቶችን በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ በመላው ዓለም ለሚገኙ ክርስቲያኖች የድጋፍ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

በሐዋርያት መንገድ እንድንመላለስ ፍኖተ ብርሃን አለች ከዚህ መቅደስ በሰንበት ት/ቤታችን ሕጻናት ክፍል ተማሪ በሆነው በሕጻን ዲ/ን ዮናስ ብርሃነ የቀረበ ቅኔ! ባለ ቅኔው፦ ዲ/ን ታዴዎስ ደምሴ ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የሰንበት ት/ቤታችን አገልጋይ የሆናችሁት ወንድማችን ነብዩ ኤልያስ እና እሕታችን ቅድስት ኩምሳ ዛሬ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በቅዱስ ቁርባን ስርዓተ ጋብቻችሁን ለመፈጸም ስላበቃችሁ እንኳን ደስ አ
+2
የሰንበት ት/ቤታችን አገልጋይ የሆናችሁት ወንድማችን ነብዩ ኤልያስ እና እሕታችን ቅድስት ኩምሳ ዛሬ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በቅዱስ ቁርባን ስርዓተ ጋብቻችሁን ለመፈጸም ስላበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን! ቀሪ ዘመናችሁ የፍሬ የበረከት ያድርግላችሁ! ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

#ጼዴንያ_ማርያም ከሀገረ ደማስቆ በጼዴንያ ክፍል በመሪና ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች። አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኮስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ መሽቶበት ከቤቷ በእንግድነት አድሮ ጧት ሊሄድ ሲነሳ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱን አውቃ የእመቤቴን ስዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ አለችው። ገንዘቡንስ ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ ብሏት ሄደ። ቅዱሳት መካናትን እጅ ነስቶ ስዕሉን ዘንግቶ ሳይገዛ ሲመለስ፤ "ለምንት ረሳዕከ ዘትብለከ ዛቲ ብእሲት" አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያች ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ የሚል ድምጽ ሰማ። ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን ሲሄድ አንበሳ መጣበት። ፈርቶ ሲጨነቅ ከስዕሉ ድምጽ ተሰምቶ አንበሳው ደንግጦ ሸሸ። ሁለተኛ፤ ሁለት ሽፍቶች አግኝተውት ሲፈራ እንደቀደመው ዓይነት ድምጽ ከስዕሉ ተሰማ። ምን መጣብን ብለው ሸሽተዋል። እሱም ይህን አይቶ #መድኃኒቴን_አሳልፌ_አልሰጥም ብሎ ወደ ሀገሩ ይዞ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ። ጽኑ ማዕበል ተነሥቶ መርከቡን እየገፋ ደማስቆ ዳርቻ አደረሳቸው። ሌላ መጠጊያ የለውምና ልብሱን ቀይሮ ድምፁን ለውጦ ከቤቷ ገብቶ አደረ። ሲነጋ ወጥቶ ሊሄድ ከበራፉ ሲደርስ ደጃፏ ጠፍቶት "ወወዓለ እንዘ ያርመስምስ" ይላል ከቅጽሩ ሲታገል ዋለ። ማርታ አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬን ደግሞ በዚህ አድርህ ነገ ትሄዳለህ አለችው፤ አደረ። በሁለተኛውም ዕለት እንዲሁ ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን አባቴ እንዲህ ስትሆን ዛሬ ሦስተኛ ቀን ነው፤ የሆንከው ምንድር ነው ? አለችው። መድኃኒቴን አሳልፌ አልሰጥም ብዬ እንጂ ስዕል ግዛልኝ ያልሽን መነኮስ ነኝ ብሎ አውጥቶ ሰጣት። ደስ አላት። ተቀብላ በክብር አስቀመጠችው። በመዓልትም በሌሊትም መብራት ታበራለታለች። ይህችም ስዕል ወንጌላዊው ሉቃስ የሳላት ናት። "ወይእቲ ስዕል ትመስል ልብስተ ሥጋ ወያንጸፈጽፍ ሐፍ እምኔሃ" ይላል፤ ሥጋ የለበሰች ከፊቷም ወዝ የሚያንጸፋጸፍ ትመስል ነበረ። አባ ቴዎድሮስም ስዕሏን እያገለገለ ከእሷ ጋር ኑሯል። ከዚህ በኋላ ብዙ ተአምራት አድርጋለች፤ ሕሙም ፈውሳለች፤ ዕውር አብርታለች። በዘመኑ የነበረ ሊቀ ጳጳስ ዜናዋን ሰምቶ አመጣታለሁ ቢል የማይሆንለት ሆነ፤ ከዚያው ስዕል ቤት ሠርቶላት ካህናት መድቦላት ስዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበትን ዕለት መስከረም 10 ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠርቶላት ተመልሷል። #ከእመቤታችን_ወላዲተ_አምላክ_ረድኤትና_በረከት_ያሳትፈን! ምንጭ ፦ መጽሐፈ ስንክሳር፣ ተአምረ ማርያም፣ መዝገበ ታሪክ ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረው
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የሐዘን መግለጫ የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆኑት የእህታችን ማኅሌት ያሬድ እና የወንድማችን ቅዱስ ያሬድ አያት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ መስከረም 8/2019 ዓ.ም በቅዱስ ዮሴፍ ቤ/ክ ከቀኑ 9:00 ሰዔት የሚፈጸም በመሆኑ በቀብሩ ላይ መገኘት የምትችሉ ተገኝተን እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው 43 ቀበሌ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የእናታችንን ነፍስ  ይማርልን ። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

መስከረም 8 "...ሙሴ... ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ:: ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና..." ዕብ. 11:24 በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅ
መስከረም 8 "...ሙሴ... ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ:: ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና..." ዕብ. 11:24 በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከትና ረድኤት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"...ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅ
"...ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።" ሉቃ 1፥41-45 በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የአገልግሎት መረጃ ባሳለፍነው 2 ወራት በሥራ አስፈጻሚ የትምህርትና ስልጠና ክፍል ዋና ተጠሪ የነበረው ወንድማችን ዲ/ን አብርሃም ታደሰ በስራ ጫና ምክንያት በክፍሉ ዋና አስፈጻሚነት መቀጠል ስላልቻለ በእርሱ ቦታ የሰው ሀብት አስተዳደር አስፈጻሚ የነበረውን መ/ር ፍቃዱ ኪሮስን ወደ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ዋና አስፈጻሚነት የተመደበ ሲሆን፤ የሰው ሀብት አስተዳደርን ወንድማችን ዲ/ን ዮናታን አርአያ በአስፈጻሚነት የሚመራው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። የሥራ አመራር ጽ/ቤት!

"...ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?..." ትንቢተ ኢሳይያስ 5፥4 በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅ
"...ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?..." ትንቢተ ኢሳይያስ 5፥4 በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልክተን፥
"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤" ዕብራውያን 12፥1 በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የሐዘን መግለጫ የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ኪሩቤል እንደሻው አያት አርፈው ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ተፈጽሟል። በሰንበት ት/ቤታችን ስም ለመላው ቤተሰብ መጽናናትን እየተመኘን፤ የአባታችንን ነፍስ በቅዱሳን እቅፍ ያሳርፍልን እንላለን። የመኖሪያ አድራሻቸው 43 ቀበሌ አካባቢ ነው። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc