ar
Feedback
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

الذهاب إلى القناة على Telegram

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ይህ ቻናል የተከፈተው በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ የሚሰጡ ትምህርቶች፣መልዕክቶች የሚሰራጭበት ቻናል ነው በዚህ ቻናል ማንኛውንም ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ቻናሉ በመጋበዝ ተጠቃሚ ያድርጉ የመጋበዣ ሊንክ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/sumuslim_jemaa

إظهار المزيد
1 162
المشتركون
-124 ساعات
+17 أيام
-1830 أيام
أرشيف المشاركات
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ​ውድ እና የተከበራችሁ የጀመዐችን አባላት፣ ወንድም እና እህቶቻችን በሙሉ 👋 ​ከነገ ጀምሮ ብሔራዊ የExit Exam ለምትቀመጡ የ2018 ዓ.ል ተመራቂ ሙስሊም እህት እና ወንድሞቻችን በሙሉ፡ አላህ መልካም ዕድልና ስኬት! ይወፍቃቹህ ። ይርዳችሁ! 🤲

Repost from Tikvah-University
የ2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መርሐግብር (Exit Exam Schedule) የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። @tikvahuniversity

📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ! ✅ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እ
📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ! ✅ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ጥሪውን ያቀርባል። 📚 የፕሮግራሙ ልዩ እንግዳ፦ ታላቁ የ-የመን ሙሓዲስ ፈደይለቱ ሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ (ሀፊዘሁላህ) —(በየመን የሚገኘውና በርካታ ተማሪዎችን ያፈራው የታዋቂው የመዕበር መርከዝ አስተማሪ) ◈እንድሁም ትልቁ አባታችን ፈደይለቱ ሸይኽ ሙሳ አል-ቀጧን (ሀፊዘሁላህ) ይገኛሉ። 🎙️ በፕሮግራሙ ላይ የሚታደሙ መሻይኾች እና ኡስታዞች፦ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን   ከደሴ ▪️ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ         ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ    ከደሴ ▪️ ሸይኽ ይማም ሰዒድ        ከደሴ ▪️ ሸይኽ አሕመድ አወቀ       ከደሴ ▪️ ሸይኽ በድሩ ዩሱፍ           ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን     ከቢስቲማ ▪️ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ        ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን       ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሐሰን አሊ ቃዲ          ከደሴ ▪️ ሸይኽ ሁሰይን አቡ ሶላሑዲን ከደሴ ▪️ ሸይኽ አወል አህመድ          ከከሚሴ ▪️ሸይኽ ዒሳ አደም                 ከደሴ 🔸 ዶክተር /ኡ ሁሴን አሊ         ከከላላ 🔸 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር       ከአ.አበባ 🔸 ዶክተር/ኡ ሰዒድ ሙሳ         ከአ.አበባ 🔸 ኡስታዝ ኸድር አሕመድ     ከከሚሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሒዛም          ከአዳማ 🔸 ኡስታዝ  ዐብደሽኩር          ከአሶሳ 🔸ኡስታዝ ዐብዱሰላም ሐሰን   ከአዳማ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን   ከሀርቡ 🔸 ኡስታዝ አወል አሕመድ መነዮ  ከመረሳ 🔸 ኡስታዝ አቡ አዩብ      ከኮቦልቻ 🔸 ኡስታዝ ሙርሰል        ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሻኪር      ከኮንቦልቻ 🔸 ኡስታዝ አቡ ረያን        ከመርሳ 🔸ኡስታዝ መሀመድ አያሌው ከወልዲያ 🔸ኡስታዝ አቡ ዓብዱ ረዛቅ ጅረሳ ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ    ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ ዐብዱልመሊክ ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሐሳን        ከኮቦልቻ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሃኒፋ         ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን ኑርየ ጊቤ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሉቅማን 🔸 ኡስታዝ መ/ሲራጁ       ከኬሚሴ 🔸 ኡስታዝ ዐሊይ ሰይድ     ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አንሷር መሀመድ ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ         ከደሴ 🔸ኡስታዝ ጀውሀር  ክፍሌ    ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ዐብዲረሕማን ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡል መዓሊ      ከመርሳ 🔸 ኡስታዝ አቡ ሹራ            ከደሴ 🔸 ኡስታዝ አቡ ማሂ            ከኮንቦልቻ 🔸 ወንድም አቡ ሂበቲላህ       ከደሴ 👥 የአንሷር መስጅድ ኢማምና ጀመዓዎቹ ባጠቃላይ... 👤እንዲሁም ሌሎች ከተለያየ ሀገር  በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው መሻይኾችና ኡስታዞችም በቦታው ይገኛሉ! 📆 የፕሮግራሙ ቀናት፦ የመጀመሪያ ቀን፦ ሰኔ 6/2018 (ከፊታችን ቅዳሜ ጧት 3:00) ጀምሮ ለ 4 ተከታታይ ቀናት ይቆያል። 🏘 ማሳሰቢያ፦ ለታዳሚዎች በቂ የምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል።—የሌሊት ብርድ ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ መልካም ነው።— 🤩በእነዚህ የቴሌ ግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ ይመዝገቡ፦ 📝ኡስታዝ አቡ ሻኪራ አህመድኑር @Abuhureirehonline    0923467646 📝 ኡስታዝ አቡ ዐዩብ   092 588 7118 @Attewhid11 📝 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን @Abu_Hibetillah_Al_aseriy 0942819970 💙የቦታው አቅጣጫ ካስቸገራችሁ በነዚህ የእንግዳ ተቀባይ ወንድሞች ስልክ ቁጥሮች ላይ ይደውሉ፡ 📞 ወንድም አንዋር 0916582567 📞 ወንድም አቡ አማር 0913803997 📞 ወንድም ሰኢድ 0935568513

[አዲስ ደርስ ክፍል 02] የኪታብ ስም፦ ሉምዐቱል ኢዕቲቃድ የኢብኑ ቁዳማ ረሒመሁሏህ የሸርሑ አዘጋጅ፦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁሏህ የደርሱ አቅራቢ 🎙Hussein Ali Seid ፒዲኤፉን ለማግኘት👇 t.me/husseinali210/2396 ደርሱ የሚተላለፍበት ሊንክ👇 t.me/HawassaUniversityAlumniSunaJamaa

[አዲስ ደርስ ክፍል 01] የኪታብ ስም፦ ሉምዐቱል ኢዕቲቃድ የኢብኑ ቁዳማ ረሒመሁሏህ የሸርሑ አዘጋጅ፦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁሏህ የደርሱ አቅራቢ 🎙Hussien Ali Seid ፒዲኤፉን ለማግኘት👇 t.me/husseinali210/2396 ደርሱ የሚተላለፍበት ሊንክ👇 t.me/HawassaUniversityAlumniSunaJamaa

        ......             🌹🌹🌹🌹🌹🌹                          ትዳር ሁሉ እሚፈልጋት  ማረጋጊያ ነፍስ በጣም እምታምር ያላት የደስ ደስ ትዳር እምትባል አለች ትልቅ እቃ ፈሪ አይገባባትም  ነውጅ   የነቃ ነገር ግን ትውልዱ ያሁኑ ዘመን ፊትናን   ያራግባል ትቶ ትዳርን አወይ ጊዜ ክፉ    ምነው ተበላሸ ወንዱም ትዳር ሲሉት በሩቁ እየሸሸ ሴቷም ሲጠይቋት መስፈርቷ መኪና እስኪ ተመልከቱ  ይሔንን   ብልግና መንሀጁን እንጅ አትበይ ገንዘብ ይመጣል ከአላህ ከሪም ነው እረብ ሱረቱል እሩም ላይ  አላህ ሲናግረን ቶሎ እንድንዘወጅ  ሲያበረታታን ወጀአለ በይነኩም መወደተን ወራህማ እያለ ጌታችን ሰቶን  ትልቅ ኒዕማ ገንዘብ አትመልከች እስትኮኝ እማማ ሰለፍያ ማለት መስፈርቱ ቀላል ነው ለሠው ልጅ ትልቁ ዋናው ሙሀባ ነው መዳኒት ነው ሸባብ ትዳርን መወፈቅ ከትልቁ ወንጀል ዚናን ለመጠንቀቅ ከቻት  ጋ አትጃጃል ግባ ወደ ተግባር አንተ ሸባብ ሁላ ግባ  ወደ  ትዳር ቶሎ አግባና ዉለድ አንችም እንደዛው እርጅናም ይመጣል ሞትም ቅርብ ነው ነፍስ እወቅ እባክህ ...ተው አንተ ወጣት በጣም ይቀርሀል .......ገና ነህ ንቃት እባክህ ኢላሒ ................  አንተ ዘውጀን በዚህ ፊትና ዘመን............ አንተ ጠብቀን ወንዱንም ሴቱንም ...........ነፍስ አሳውቀን አሚን .........

ምንም በዱኒያ ጉዳይ ባተሌ ብትሆኑ ከእዉቀት ማድ አትራቁ ​የሁሉም ደረሳ አላማ የግድ አሊም መሆን አይደለም፤ ይልቁንም እውቀትን በመፈለግህ የሚፈለገው ዋናው ዓላማ የሚከተሉትን እንድታሳካ ነው፡- ​① ከራስህ ላይ አላዋቂነትን እንድታነሳ፣ ② አላህን ትክክለኛ በሆኑ አምልኮዎች (ኢባዳዎች) እንድታመልክ፣ ③ እንዲሁም አቂዳህ (እምነትህ) የቀና ሆኖ አላህ ዘንድ በንፁህ ልብ እንድትቀርብ ነዉ። ​የላቀዉ ጌታችን እንዲህ ይላል፦ ​﴿وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَ * يَوْمَ لَا يَنْفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ * إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ﴾ [الشعراء: 87-89]. ​«በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፤ ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡ ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡» ​💡 ንፁህ ልብ ማለት፡- ከጥርጣሬዎች (ሹብሃት) የጠራ እና በስሜት ፍላጎቶች (ሸህዋት) ላይ ከመዘውተርና ከመውደድ የዳነ ነው። ​🌐 https://t.me/durusuabihizam

🎉 بَارَكَ اللَّهُ لَكُمَا وَبَارَكَ عَلَيْكُمَا وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْرٍ --------------------------------------------
🎉 بَارَكَ اللَّهُ لَكُمَا وَبَارَكَ عَلَيْكُمَا وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْرٍ ---------------------------------------------------------------------- የ2016 ተመራቂዎች የላጤነትን ሕይወትን በማጠናቀቅ ወደ ተከበረው የትዳር ዓለም የሚያደርጉትን ጉዞ ቀጥለውበታል። ዛሬም ከእነዚሁ መካከል አንዱ የሆነው ወንድማችን ሰኢድ አህመድ ይህንን የተቀደሰ መንገድ ተቀላቅሏል። በHealth Informatics የ2016 ዓ.ል ተመራቂ የሆነው፤ በጀማዓችን  ንቁ የሆነ ተሳትፎ እና ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረግ አርኣያ የነበረው ወንድማችን ሰኢድ፣ በአሏህ መልካም ፈቃድ በሀላል መንገድ ዛሬ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጀምሯል። ይህ የደስታ ጉዞ ይበልጥ ድምቀት ያገኘው፣ ከጀማዓችን የ3ኛ ዓመት የአረብኛ ቋንቋና የማኔጅመንት ተማሪ ከሆነችው ከእህታችን አሚናት አያል ጋር ኒካሃቸውን በመፈጸማቸው ነው። አላህ የመሰረቱትን ትዳር የፍቅር፣ የደስታ፣ ያማረና የተሳካ እንዲያደርግላቸው፤ ሕይወታቸውንም በበረካ እንዲሞላው ዱዓችን ነው። ሁላችንም ለወንድማችን ሰኢድ እና ለእህታችን አሚናት “መብሩክ” እያልን ልባዊ መልካም ምኞታችንን እንግለጽላቸው። ⚠️ ለግቢ ሰፈር ወጣቶች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት ነቃ በል እንጂ! "የራሳቸውን ባች ትተው ተመርቀው ከወጡ በኋላ፣ ደግሞ መጥተው የኛን ጨረሱብን!" የምትሉ ተፎካካሪዎችና የጊቢ ጓዶች... እንግዲህ   በፍጥነት ካልቀደማችሁ፣ የ2016 ባቾች ገበያውን ሙሉ በሙሉ በሞኖፖል ሊቆጣጠሩት እንደሚችሉ ፍንጮች እያሳዩ ነውና ቀጣዩን መስመር ለማስከበር 'ነቃ' ማለቱ ለእናንተም ይመረጣል! እንጂ....  ይሄ ጀምአ በዚህ አያያዙ ከቀጠለ ባዶህን መቅረትህ ነው!  ህዕ...!

💐የጁመዓ ቀን ሱናዎች💐 ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️💎 ‏سنن يوم الجمعة ➊ 💎الغسل ➋💎 الطيب ➌ 💎السواك ➍💎 لبس الجميل ➎💎 قراءة سورة الكهف ➏💎 التبكير لصلاة الجمعة ➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➊ 🌺መታጠብ ➋ 🌺ሽቶ መቀባት ➌🌺 ሲዋክ መጠቀም ➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን ➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ ➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ   🌺በሰለዋት በዚክርያውለን ﷺ 🌹 .................🌹 ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹  ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹 በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!                

💐 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 💐 ውድ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቤተሠብም ጋር ግቢም ውስጥ ያላቹህ በሙሉ ........ 🌙🌟عيد مبارك 🌴🌴🌴تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 🌴🌴🌴كل عام وأنتم بخير🌙🌟 ኢድ ሙባረክ ✋               🌺 🥀 ᴇɪᴅ 𝑀𝑢𝑏𝑎𝑟𝑒𝑘🌹

⚠️ ጥንቃቄ! የቴሌግራም አካውንትዎን ከጠለፋ (Hack) ይጠብቁ! ውድ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች፣ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ሊንኮች (Links) አማካኝነት የሰዎችን የቴሌግራም አካውንት የመጥለፍ ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል። አካውንትዎን ለመጠበቅ እነዚህን ነጥቦች በጥብቅ ይተግበሩ፦ 🚫 ያልታወቁ ሊንኮችን አይክፈቱ፦ በማያውቋቸው ወይም አጠራጣሪ በሆኑ ሰዎች የሚላኩልዎትን ሊንኮች በፍጹም አይክፈቱ። 🔐 ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) ያስተካክሉ፦ ወደ Setting > Privacy and Security > Two-Step Verification በመሄድ የይለፍ ቃል ያስገቡ። ይህ አካውንትዎ ቢሰረቅ እንኳ እንዳይከፈት ይረዳል። 🔗 ሊንክ ሲከፍቱ ይጠንቀቁ፦ "ሽልማት አግኝተሃል"፣ "የቴሌግራም አካውንትህ ሊዘጋ ነው" ወይም ሌሎች አሳሳች መልእክቶችን በመላክ ሊንክ እንዲጫኑ የሚያደርጉ የማጭበርበሪያ ስልቶችን ይለዩ። 👤 ኮድ ለማንም አያጋሩ፦ ከቴሌግራም የሚመጣን ማንኛውንም የደህንነት ኮድ (Login Code) ለሌላ ሰው በፍጹም አያካፍሉ። በጥንቃቄ ይስሩ፤ መረጃዎን ይጠብቁ! ይህንን መልእክት ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የሌሎችን አካውንትም ከጥቃት ይታደጉ። #SecurityAlert #TelegramTips #StaySafe #CyberSecurity #ኢትዮጵያ

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ 👉ያጀማዓ  4 ቲቸርት ብቻ ስለቀረን መውሰድ የምትፈልጉ አናግሩን።እንዳትቀደሙ!!!

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ 👉ያጀማዓ  ቲቸርቱን ካፌ መልበስ ስለማይቻል  ለብሳቹህ እንዳትሄዱ!እንዳትቀሙ .....!!!!!

​🌟 ልዩ የመለያያ፣ የዳዕዋና የአዝናኝ ፕሮግራም ጥሪ 🌟 ​ክቡራትና ክቡራን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች፤ ​አልሀምዱሊላህ! በታላቁ አላህ ፍቃድና እገዛ የዚህን ሴሚስተር ፈተናዎች በሰላም
​🌟 ልዩ የመለያያ፣ የዳዕዋና የአዝናኝ ፕሮግራም ጥሪ 🌟ክቡራትና ክቡራን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች፤ ​አልሀምዱሊላህ! በታላቁ አላህ ፍቃድና እገዛ የዚህን ሴሚስተር ፈተናዎች በሰላም አጠናቀን ወደየቤተሰቦቻችን ልንመለስ ዋዜማ ላይ እንገኛለን። ​ባሳለፍናቸው የትምህርት ቀናት ውስጥ የነበረንን ትስስርና ወንድማማችነት ይበልጥ የምናጠናክርበት፣ ልባችንን በምክር የምናድስበትና አብረን የምንዝናናበትን ልዩና የመጨረሻ የነሲሀና የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅተናል። ​ይምጡና የዩኒቨርሲቲ ቆይታችንን ባማረ ትውስታ እንቋጨው! ​📌 የፕሮግራሙ ይዘቶች፦ 👉​አጠር ያለ ዳዕዋ (ነሲሀ)፦ ከግቢ ስንወጣ ምን ይዘን መውጣት እንዳለብን እና በረፍት ጊዜያችን ምን ማድረግ እንዳለብንየሚጠቁም መካሪ መልእክት(ሁሉም ቋንቋ )። 👉​አዝናኝ የጥያቄና መልስ ውድድር፦ አእምሮን የሚያነቁና ሽልማት የሚያስገኙ ጥያቄዎች። 👉​ማራኪ ግጥሞች፦ በወንድሞች የሚቀርቡ ምርጥ ግጥሞች ። ​ሌሎች በርካታ አስደሳችና ፕሮግራሞች! ​⏰ የፕሮግራሙ ቀን እና ሰዓትቀን፦ መጪው አርብ (የጁሙአ ዕለት) ​ሰዓት፦ ከመግሪብ ሰላት በኋላ
​🎯 ማሳሰቢያ፦ ፕሮግራሙ ልክ ከመግሪብ ሰላት በኋላ ወዲያውኑ የሚጀምር በመሆኑ ሁላችሁም በሰዓቱ እንድትገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ኑ አብረን እንማር፣ አብረን እንዝናና! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ SUMU ጀመዓዎች ነገ ለሚጀምረው የፋይናል ፈተና (Final Exam) አላህ (ሱ.ወ) ለሁላችንም ሰፊ መረጋጋትንና ማስተዋልን እንዲሰጠን እመኛለሁ። እስካሁን ባለው ጊዜ ሁላችንም የቻልነውን ያህል ለፍተናል፣ ደክመናል፣ አጥንተናል። አሁን የቀረን ሰበቡን አድርሰን በአላህ ላይ መወከል (Tawakkul) ብቻ ነው። አሏህ ጭንቀታችንን አውርዶ ቀልባችንን እንዲያረጋጋውና ፈተናውን ገር እንዲያደርግልን ዱአ እናድርግ ። ዛሬ ማታ ራሳችንን ሳናስጨንቅ በሰዓቱ ተኝተን እረፍት እንውሰድ። ኢንሻአላህ ሁላችንም ይሄንን ሴሚስተር በታላቅ ስኬትና በመልካም ውጤት እንደምናጠናቅቀው ሙሉ ተስፋ አለኝ። 🤲 አላህ ለሁላችንም ስኬቱን ይወፍቀን! ያጠናነውን እናስታውስ ዘንድ ዱዓ እናድርግ ! መልካም የፈተና ጊዜ ይሁንልን!💯✨ አላህ ፈተናውን ያግራልን፣ መልካም እድል ለሁላችንም!

አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት!.pdf6.94 MB

🌙✨ የዙልሒጃ መጀመሪያ አሥር ቀናት ✨🌙 ﴿ وَالْفَجْرِ ۝ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴾ "በጎህ እምላለሁ፤ በዐሥሩም ሌሊቶች እምላለሁ።" 📖 Quran — ሱረቱል ፈጅር 89:1-2 ብዙ ዑ
+1
🌙✨ የዙልሒጃ መጀመሪያ አሥር ቀናት ✨🌙 ﴿ وَالْفَجْرِ ۝ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴾ "በጎህ እምላለሁ፤ በዐሥሩም ሌሊቶች እምላለሁ።" 📖 Quran — ሱረቱል ፈጅር 89:1-2 ብዙ ዑለሞች በዚህ አንቀፅ ውስጥ “ዐሥሩ ሌሊቶች” የተባሉት የዙልሒጃ መጀመሪያ 10 ቀናት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ዑለሞችም፦ “አላህ سبحانه وتعالى በአንድ ነገር ሲምል፣ ይህ የዚያን ነገር ታላቅነትና ክብር ያሳያል” ብለዋል። ┈┈┈┈┈┈ 🌙 ┈┈┈┈┈┈ ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «مَا العَمَلُ فِي أَيَّامِ العَشْرِ أَفْضَلَ مِنَ العَمَلِ فِي هَذِهِ» قَالُوا: وَلاَ الجِهَادُ؟ قَالَ: «وَلاَ الجِهَادُ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ يُخَاطِرُ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ، فَلَمْ يَرْجِعْ بِشَيْءٍ» “በእነዚህ በዙልሒጃ መጀመሪያ ዐሥር ቀናት ውስጥ እንደሚደረግ መልካም ሥራ፣ በማንኛውም ሌላ ቀናት የሚደረግ መልካም ሥራ አላህ ዘንድ የበለጠ ተወዳጅ የሆነበት ቀን የለም።” ሰሐባዎችም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን ከእነዚህ ቀናት ሥራ አይበልጥም?” ብለው ጠየቁ። ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦ “አዎ፣ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን አይበልጠውም። ነገር ግን በነፍሱም በገንዘቡም ወጥቶ በዚያው ሸሂድ ሆኖ ከነዚህ ነገሮቹ ምንም ሳይመለስ የቀረ ሰው ሥራ ሲቀር።” 📚 Sahih al-Bukhari 969 ┈┈┈┈┈┈ ✨ ┈┈┈┈┈┈ 🌙 ምናልባት ነገ ወይም ከነገ ወዲያ እነዚህ ውድና የተባረኩ ቀናት ሊገቡ ይችላሉ… ስለዚህ ለዒባዳ እንዘጋጅ። ▫️ ቁርኣን ▫️ ሶላት ▫️ ዚክር ▫️ ዱዓ ▫️ ሶም ▫️ ሰደቃ አላህ ያበርታን!!

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ የጀማዓው ቲሸርት ስለመጣ ከዒሻ ሰላት በኋላ ታችኛው መስጂድ እየመጣቹህ መውሰድ ትችላላችሁ ።