cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Minber TV

#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ! #ሚንበር_ቲቪን ለማግኘት 📡 በኢትዮሳት ይከታተሉ:– 👇 ፍሪኩዌንሲ:- 11545 ሲምቦልሬት:- 30000 ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል ★★★★★

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
39 857
المشتركون
-1524 ساعات
+117 أيام
+29130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ፈተና የቀን ለውጥ እንዲደረግበት ተጠየቀ ዕለተ ጁመዓ ግንቦት 23 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 23 – 1445 | ሚንበር ቲቪ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ፈተና የቀን ለውጥ እንዲደረግበት የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡ ምክር ቤቱ ከዒድ አል አድሓ በዓል ማግሥት የሚሰጠው ፈተና በተማሪዎች ውጤት ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጧል፡፡ የክልሉ እስልምና ጉዳዮ ከፍተኛ ምክር ቤት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ግንቦት 21/2016 በጻፈው ደብዳቤ፣ ፈተናው ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚከበረው የዒድ አል አድሓ በዓል እለት እንደሚሰጥ በመጥቀስ፣ የቀን ለውጥ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ የፈተናው ቀን ከበዓሉ ጋር በአንድነት መሰጠቱን በሕገ መንግስሥቱ የተቀመጠውን የሃይማኖትን እኩልነት የሚጥስ ነው ብሎታል፡፡ ምክር ቤቱ በተጨማሪም የበዓል ዋዜማ እና ማግሥት ላይ የሚደረግ ፈተና በተማሪዎች ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረውም ነው የገለጸው፡፡ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ክፍተኛ ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ዞኖች ትምህርት መምሪያዎች፣ ወረዳ እና ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች የፕሮግራም ለውጥ ያድርጉ ብሏል፡፡ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ስምንተኛ ክፍል ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረውን ክልል አቀፍ ፈተና ለስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች መስጠት የጀመረው ከባለፈው ዓመት አንስቶ ነበር፡፡ በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8222 ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
إظهار الكل...
👏 11👍 4 2
በሀገራዊ ምክክር የተወካዮች ልየታ ወቅት ከተሳትፎ ውጪ መደረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለጸ ዕለተ ጁመዓ ግንቦት 23 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 23 – 1445 | ሚንበር ቲቪ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ በሀገራዊ ምክክር የተወካዮች ልየታ ወቅት ተሳታፊ አለመደረጉን የገለጸው ለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ረቡዕ ግንቦት 21/2016 በጻፈው ደብዳቤ፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሠራሩን ካላሻሻለ ዕውቅና አልሰጥም ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የመጣው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሦስተኛ ያለውን የምክክር ምዕራፍ ከጀመረ በኋላ ነው፡፡ ኮሚሽኑ በዐድዋ መታሠቢያ ሙዝየም ባስጀመረውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የምክክር መድረክ በቀጣይ በክልሎች የሚካሄድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በአንጻሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮ ከፍተኛ ምክር ቤት፣ ለሀገራዊ ምክክር በሚደረገዉ ሒደት የመጀመሪያ ዙር የምክክር ጉባዔ የሚሳተፉ ሰዎች ተለይተው ወደ ሥራ እንደገቡ በማስታወስ፣ በተሳታፊ ልየታ ወቅት ተሳትፎ እንዳላደረገ ጠቅሷል፡፡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሒደት የክልሉን ሙስሊም በተገቢው መልኩ አሳታፊ እንዲያደርግ ጥሪ የቀረበበት የምክር ቤቱ ደብዳቤ፣ ይህን እንዲያቀርብ የጠየቀው ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነው፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “አሠራሩን የማያሻሽል ከሆነ” በቀጣይ “ምንም ዐይነት ትብብር” እንደማያደርግና ዕውቅና እንደሚነፍገው አስታውቋል፡፡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ቅሬታ ሲቀርብበት እንደነበር ይታወቃል፡፡ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ግንቦት 12/2016 ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ለአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር እና ለክልሉ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ፣ የሀገራዊ ምክክር የተሳታፊ ልየታ አሠራር ሳይሻሻል ባለበት የሚቀጥል ከሆነ ለምክክሩ ዕውቅና እንደማይሰጥ አስጠንቅቆ ነበር፡፡ በምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጀውሐር ሙሐመድ በተጻፈው ደብዳቤ፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሉ ባካሄደው ጉባዔ ላይ ያሳተፈው “የኔ የሚለውን ብቻ” እንደሆነ ተጠቁሟል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልል እስልምና ጉዳዮች ከቀረበበት ቅሬታ በፊት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ አካሔዱ ላይ ተቃውሞ ሲያቀርብበት ነበር፡፡ ምክር ቤቱ ይህንኑ ተቃውሞውን ለዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መሥፍን አርዓያ በጻፈው ደብዳቤ ገልጧል፡፡ ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ለቀረበበት ተቃውሞ እስካሁን ድረስ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት በእስላማዊ ጉዳዮች አተኩረው ከሚሠሩ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና አንቂዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ እስካሁን ድረስ በነበረው በዚህ የልየታ ሒደት የሙስሊሞች ውክልና ከ2 በመቶ ያነሰ መሆኑን የሰበሰበውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል፡፡ (ሚንበር ቲቪ) በድረ ገጽ ተጨማሪ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8216 ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
إظهار الكل...

👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
በሀገራዊ ምክክር የተወካዮች ልየታ ወቅት ከተሳትፎ ውጪ መደረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለጸ
إظهار الكل...
😱 4👍 1
ኅብረተሰቡ ከመጭበርበር የወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አሳሰበ ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 22 – 1445 | ሚንበር ቲቪ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ኅብረተሰቡ ከመጭበርበር የወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ ማሳሰቢያ ሰጠ። አገልግሎቱ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 22/2016 ባወጣው መግለጫ አንዳንድ ግለሰቦች እና የወንጀል ድርጊት ፈፃሚዎች የተለያየ ገጽታ ያላቸው ወንጀሎችን በመፈጸም በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ለማግኘት እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል። የወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም ገንዘብ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች እንደሁኔታው አዋጭነት ሁሉንም የማጭበርበሪያ ስልቶች ይጠቀማሉ ያለው አገልግሎቱ፣ የወንጀል ድርጊታቸውም በሕግ አስከባሪ አካላት በቀላሉ እንዳይደረስበት ራሳቸውን መደበቅ ወይም ከሕግ ዕይታ ለማራቅና ለመሰወር ጥረት እንደሚያደርጉም አመልክቷል። የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አጭበርባሪ ናቸው ባላቸው ግለሰቦች በቅርቡ እየተስተዋለ ያለው የወንጀል ድርጊት አፈጻጸም፣ በተለያዩ ሀገራት ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ ዜጎችን በመቅረብ በሕገ ወጥ መንገድ የውጭ ሀገራት ገንዘብ መሰባሰብ የሕገ ወጥ ሐዋላ የወንጀል ድርጊት ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን ጠቁሟል። አገልግሎቱ እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም የኦንላይን እና ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም “የትርፍ ጊዜ ሥራ”፣ “አማራጭና አዋጭ ሥራ” እንዲሁም “ኢንቨስትመንት በሚል ማደናገሪያ ስልቶች በመጠቀም ግለሰቦችን በኦንላይን በመቅረብና ግንኙነት በመፍጠር ወደ ማጭበርበሪያ ሰንሰለት ውስጥ በማስገባት ገንዘብ በተለያየ አግባብ ወስደው ሲሰወሩ መቆየታቸውንም አስታውሷል። ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፦ https://minbertv.com/?p=8213 ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
إظهار الكل...
👍 9 5
Photo unavailableShow in Telegram
ኅብረተሰቡ ከመጭበርበር የወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አሳሰበ
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
00:55
Video unavailableShow in Telegram
በሽታ አምጪ ቫይረሶችን ይዞ የተገኘው የልገሳ ደም! ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል። 🔗 https://youtu.be/s--trwgiTbY 🔗 #እንግሊዝ #የደም_ባንክ #ደም_ልገሳ #ዳር_እስከ_ዳር #መወዳ_መዝናኛ ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 22 - 1445 ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
إظهار الكل...
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኤንዶኔዢያ በርካታ ሙስሊም ዜጎች ካሏቸው የአለም ሐገራት መሓል ናት ። በሀይማኖታዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ አንቱ የሚሰኙ ጎበዞችም አፍርታለች ። ዛሬ በምናወሳው ስብዕና በኩል በቤተሰብ የተወራረሰውን አንቱታም ተርከናል ። ዛሬ ምሽት ከ02፡00 ጀምሮ ይጠብቁን! #ክብር_ይወራረሳል #እነሆ_ኸበር ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 22 - 1445 ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
إظهار الكل...
👍 11
00:55
Video unavailableShow in Telegram
ወደ እስልምና ስትመጣ የምትወደው እየሱስን አጣሀው? ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል። 🔗 https://youtu.be/7ovpHi1J2SU 🔗 #እየሱስ #ዒሳ #ሂዳያ #የኔ_መንገድ ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 22 - 1445 ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
إظهار الكل...
👍 15🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
ባሳለፍናቸው ሁለት ሳምንታት ስለ ሥራ ሲያወጉን የቆዩት ሸይኻችን በሥራ የዳበረ ጉልበት በአስተሳሰብ የዳበረ አእምሮ፣ ከጥገኝነት የተላቀቀ ግለሰብ ስኬተ ብዙ እንደሆነ የተለያዩ ሐዲሶችን እና ቂሳዎችን እያነሱ እራሳችንን እንድንፈትሽ አድርገውናል። ዛሬ ሸይኻችን “እንደ ግለሰብ ምን አይነት ማንነት መላበስ እንዳለብን” ያብራራሉ። በመምሰል እና በማስመሰል መሀከል ያለውን ልዩነት እያነሱ እኛም ካለፉት ሕዝቦች ብዙ መማር እንዳለብን የሚያሳዩ ታላላቅ ስብዕናዎችን እና ቂሳዎችን እያስረዱን ከኛ ጋር ያመሻሉ። ተወዳጁ ኡስታዝ በድር ሁሴን በቢስሚከ ነህያ ዝግጅቱ "ተፈኩርን"ን እየቃኘና፤በዋናነት በአላህ (ሱ.ወ) ችሮታ ስለ ተሰጠን እና አከባቢያችን ላይ ስላለው ኒዕማ ማስተንተን ያለውን ደርጃ እና ይበልጥ ወደ አላህ (ሱ.ወ) እንደሚያቃርበን እየዳሰሰ አብሮን ይቆያል። ምሽት ከ 2፡30 ጀምሮ ይጠብቁን!! #ኸሚስ_ምሽት #ለይሉ_ጁምዓ_ነው!! #ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!! ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 22 - 1445 ★ ★ ★ Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
إظهار الكل...
👍 11