ar
Feedback
አባወራ abawera

አባወራ abawera

الذهاب إلى القناة على Telegram

አባወራ፦አባትነት፣ ባልነት፣ ወንድነት፣ ራስነት +251-9-11-67-46-87 https://youtube.com/@abawera826

إظهار المزيد
1 501
المشتركون
+324 ساعات
-27 أيام
-530 أيام
أرشيف المشاركات
መልክን በማጠልሸት እውነት አትጠይምም! =========================== ሰው የሚናገረውን ከኖረ መልኩም፣ ግብሩም፣ አቋሙም፣ እንቅስቃሴውም መልዕክቱን የሚያጠናክሩ የስሙ ምስክሮች ናቸው!
መልክን በማጠልሸት እውነት አትጠይምም! =========================== ሰው የሚናገረውን ከኖረ መልኩም፣ ግብሩም፣ አቋሙም፣ እንቅስቃሴውም መልዕክቱን የሚያጠናክሩ የስሙ ምስክሮች ናቸው! ኾኖም ግን እውነተኛ "መልክን" ኾን ብሎ ማበላሸት፣ የሚተላለፈውን እውነት በግልጽ ለማስጠላት ለመቅበርም የሚደረግ ሙከራ ነው! አንብቡት👇👇👇 https://abawera.substack.com/publish/post/203547610?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

ወግ አጥባቂነትን ወደ ሥነ-ልቦናዊ ጃንደርባነትና ግብረሰዶማዊነት የሚቀይረው የፒተርሰን ረቂቅ ክህደት ፫ (የቀጠለ) =================================== ይህ የፒተርሰን ውድቀት ም
ወግ አጥባቂነትን ወደ ሥነ-ልቦናዊ ጃንደርባነትና ግብረሰዶማዊነት የሚቀይረው የፒተርሰን ረቂቅ ክህደት ፫ (የቀጠለ) =================================== ይህ የፒተርሰን ውድቀት ምዕራባዊውን ፍልስፍና ለሚኮርጁ የሀገር ውስጥ ተርጓሚዎችና ወጣቶች ትልቅ የታሪክ ማስተማሪያና የማንቂያ ደወል ነው! ምንም ዓይነት ወግ ከማይጠብቅ ፌሚኒዝምና ሊበራሊዝምን ጠልነት ሰበብ ገንዘብና ዝና ብቻ አሳዶ የጠላት መሣሪያ ከመኾን ተጠበቁ!”👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/529?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

ወግ አጥባቂነትን ወደ ሥነ-ልቦናዊ ጃንደርባነትና ግብረሰዶማዊነት የሚቀይረው የፒተርሰን ረቂቅ ክህደት ፪ (የቀጠለ) ================================= ፒተርሰን በምቾት ወንበር ላይ
+1
ወግ አጥባቂነትን ወደ ሥነ-ልቦናዊ ጃንደርባነትና ግብረሰዶማዊነት የሚቀይረው የፒተርሰን ረቂቅ ክህደት ፪ (የቀጠለ) ================================= ፒተርሰን በምቾት ወንበር ላይ፣ በሊቅነት ፍልስፍና ላይ ኾኖ የፈቀደው "ዐዲሱ መደበኛነት" The new normal በተግባር መሬት ላይ ትውልድን ለጥፊዎች አሳልፎ የሚሰጥ፣ ማኅበረሰብ የሚያቃውስ የታሪክ ትልቁ ጥልቁም ስብራት ነው!👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/f86?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

ወግ አጥባቂነትን ወደ ሥነ-ልቦናዊ ጃንደርባነትና ግብረሰዶማዊነት የሚቀይረው የፒተርሰን ረቂቅ ክህደት ================================== ልጆቿን አባት የነፈገች እናት፣ አልጫና ም
ወግ አጥባቂነትን ወደ ሥነ-ልቦናዊ ጃንደርባነትና ግብረሰዶማዊነት የሚቀይረው የፒተርሰን ረቂቅ ክህደት ================================== ልጆቿን አባት የነፈገች እናት፣ አልጫና ምስኪን አባት፣ ተፈጥሮአዊ አባወራዊ ወንድነትን የኮነነ ማኅበረሰብ እኔ የምነግራችሁን የራሳችንን ወግ አይቀበልም! ፒተርሰንን ያደንቃል ለልጆቹም ይመግባል! መጨረሻውስ? ራሳችሁንና ልጆቻችሁን ጠብቁ!👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/802?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

የአባወራው መንገድ ከሚሞትላት ኾኖም ግን ከምትገለው ዓለም ይለያል =================================== በወደቀችው ዓለምና በጽዮን መንገድ መካከል ያለው የነፍስ ትግል ነው። ዛሬ
የአባወራው መንገድ ከሚሞትላት ኾኖም ግን ከምትገለው ዓለም ይለያል =================================== በወደቀችው ዓለምና በጽዮን መንገድ መካከል ያለው የነፍስ ትግል ነው። ዛሬ ላይ ክርስቲያናዊው ማኅበረሰብ፣ ቤተሰብ የቆመበት ምድር በከፍተኛ የሞራልና የመንፈስ ውዥንብር እየተናወጠ፣ እየተናጠም ይገኛል! 👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/70f?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

የአባወራ ውድቀት፦ በገንዘብ ያበጠ ከስብዕና ግን ያፈነገጠ ትውልድ ያፈራል ================================= ሕዝብና ሀገርን በጠንካራ ስብዕና ሳይኾን በባዶ ቁስ፣ ገንዘብና GDP
የአባወራ ውድቀት፦ በገንዘብ ያበጠ ከስብዕና ግን ያፈነገጠ ትውልድ ያፈራል ================================= ሕዝብና ሀገርን በጠንካራ ስብዕና ሳይኾን በባዶ ቁስ፣ ገንዘብና GDP ብቻ መለካት፣ የትውልዱን መከላከያ ጋሻ እርሱም የአባወራነቱን ልዕልና ጥሎ፣ ሀገሪቷን ለባዕድ ባህል አሳልፎ የሚሰጣት የስልብ ጃንደርቦች መናኃርያ ያደርጋታል። 👇👇👇   https://open.substack.com/pub/abawera/p/053?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

ጽድቅ የአቅመቢሶች ራት ሳይኾን የጀግኖች ቁርስ ነው ================================= እውነተኛ ጻድቅ የድርጊት ተቀባይ (Passive) አይደለም፤ እርሱ አድራጊ (Active) ነው
ጽድቅ የአቅመቢሶች ራት ሳይኾን የጀግኖች ቁርስ ነው ================================= እውነተኛ ጻድቅ የድርጊት ተቀባይ (Passive) አይደለም፤ እርሱ አድራጊ (Active) ነው። መልካሙን፣ ልኩን፣ ተገቢውንና ውቡን ኾን ብሎ ያስባል፣ ያቅዳል፣ ይቆርጣል፣ ይጨክናል፣ ያወራረዳል፤ እስከ መጨረሻውም ሰማዕት ኾኖ ይፈጽማል። ጃንደርባ ትውልድ ግን ባርያ ነው!👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/cc9?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

Repost from N/a
በመረጃ አራምባና ቆቦ ጽንስ አስወራጁ አዋላጅ ኾኖ ቀርቦ

photo content

አባቶቻችሁን የመሰላችሁ አባወራዎች እንድትኾኑ አይፈለግም! ============================== አባቶቻችሁን የመሰላችሁ አባወራዎች እንድትኾኑ አይፈለግም! ምክንያቱም እናንተ አባወራ ስትሆ
አባቶቻችሁን የመሰላችሁ አባወራዎች እንድትኾኑ አይፈለግም! ============================== አባቶቻችሁን የመሰላችሁ አባወራዎች እንድትኾኑ አይፈለግም! ምክንያቱም እናንተ አባወራ ስትሆኑ ቤታችሁ ይከበራል፣ ማኅበረሰባችሁ አይደፈርም፣ ታሪካችሁም አይከሽፍም። እነሱ የሚፈልጉት እንከፍ ምስኪንነታችሁን እያቆለጳለሳችሁ እንድትሰለቡ ነው፤ እኛ ግን የአባቶቻችን እውነተኛ ልጆች ሆነን ግርማችንን እንመልሳለን!👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/d3f?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

ድኩላ ድረውለት አንበሳ ኹን ይሉታል ልቤ ሞኙ አምኖ ለካ ሰልበውታል ========================================= ጁንጋውያኑ “አኒማህን አዳምጣት፣ በውስጥህ ያለውን ሴትነት አቅፈ
ድኩላ ድረውለት አንበሳ ኹን ይሉታል ልቤ ሞኙ አምኖ ለካ ሰልበውታል ========================================= ጁንጋውያኑ “አኒማህን አዳምጣት፣ በውስጥህ ያለውን ሴትነት አቅፈህ ያዛት” እያሉ የሚያቀርቡት ምክር፣ በተግባር ወንዱን ለአኒማው እጅ እንዲሰጥ፣ “በአኒማው ፍቅር እንዲያዝ” እና የገዛ ስሜቱ ምርኮኛ እንዲኾን፣ በዚያም ለባርነት የሚዳርግ መንፈሳዊና የሥነ-ልቦና ስልበት ነው። https://open.substack.com/pub/abawera/p/c17?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

ፒተርሰናዊ ጃንደርባ ትውልድ አባወራነት እሴቱ ይምታታበታል =================================== ይህ ፍልስፍና ወንዱን ከተፈጥሮአዊ ልዕልናውና ከአባቶቹ እሴት ነጥሎ፣ ኃላፊነትን ያ
ፒተርሰናዊ ጃንደርባ ትውልድ አባወራነት እሴቱ ይምታታበታል =================================== ይህ ፍልስፍና ወንዱን ከተፈጥሮአዊ ልዕልናውና ከአባቶቹ እሴት ነጥሎ፣ ኃላፊነትን ያለ ሥልጣን ጭኖ የጃንደርባነትን መንገድ ጠርጎለታል።ይህ ለስላሳ ግን ደግሞ ሸፍጠኛ የሥነ-ልቦና ዘር በሀገራችንም በቅጂዎቹ አማካኝነት ይዘራል። እኛ ግን ክብሩን ጠብቆ የሚያስጠብቀውን ቆራጡንና ቆፍጣናውን ወንድነት በተግባር እናሳየዋለን! https://open.substack.com/pub/abawera/p/dea?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

ፒትርሰናዊ ጃንደርባ ትውልድ፦ወግ አጥባቂዎቹ ተጽናንተው የመከኑበት ======================================== ፒተርሰን ሰነፍና ምስኪን ወንዶችን ኃላፊነትን ያለ ሥልጣን እንዲሸከ
ፒትርሰናዊ ጃንደርባ ትውልድ፦ወግ አጥባቂዎቹ ተጽናንተው የመከኑበት ======================================== ፒተርሰን ሰነፍና ምስኪን ወንዶችን ኃላፊነትን ያለ ሥልጣን እንዲሸከሙ፣ ባልተገለጠበት ስብከቱ “በኃይላችሁ ላይ የሠለጠናችሁበት ኃያላን (Monster) ኹኑ” ቢላቸውም ቅሉ ክብሩን ጠብቆ የማያስጠብቅ፣ ዘሩን ሰጥቶ የማያስወልድ፣ አቃለሁ ሲል የታጀረ፣ ዐይኑ እያየ እየጠፋ የመከነ ጃንደርባ ትውልድ አፍርቷል! https://open.substack.com/pub/abawera/p/ab8?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

በካርል ዩንግ ‘አኒማ’ የUN Women ዓላማ፦ ወንድነትን በጥበብ መስለብ ================================= በጎ አሳቢ መስሎ የቀረበው የUN Women የለውጥ ስትራቴጂ፣ የወንድን
በካርል ዩንግ ‘አኒማ’ የUN Women ዓላማ፦ ወንድነትን በጥበብ መስለብ ================================= በጎ አሳቢ መስሎ የቀረበው የUN Women የለውጥ ስትራቴጂ፣ የወንድን ተፈጥሯዊ የመሪነትና ጠባቂነት ሚና ንዶ ወንድነትን በጥበብ የመስለብ ሥልታዊ መዋቅር መኾኑን፤ ነባሩን፣ ባህላዊውን እና ሃይማኖታዊውን አባወራነት በማዳከም ማኅበረሰቡን ተገዢ ለማድረግ የዘረጋውን "የጁንግያን" መረብ ፈትሸነዋል።👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/un-women?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

በመረጃ አራምባና ቆቦ ጽንስ አስወራጁ አዋላጅ ኾኖ ቀርቦ የሐሰተኛ ትርክት አደገኛነት የእርሱ ሰለባ የኾነው ትውልድ ጥፋቱን ወዶ፣ ፈቅዶ፣ አጽድቆ ተመክቶበትም የሚፈጽመው መኾኑና፤ ከዚያም ከጥፋቱ ወደ
በመረጃ አራምባና ቆቦ ጽንስ አስወራጁ አዋላጅ ኾኖ ቀርቦ የሐሰተኛ ትርክት አደገኛነት የእርሱ ሰለባ የኾነው ትውልድ ጥፋቱን ወዶ፣ ፈቅዶ፣ አጽድቆ ተመክቶበትም የሚፈጽመው መኾኑና፤ ከዚያም ከጥፋቱ ወደ ሕይወት የሚያወጣውን ማንም በጠላትነት የሚፈርጅበት የጥፋት ቁልቁለት መኾኑ ነው። (Demoralization and Subversion ስለሚሉ ተከታታይና ተመጋጋቢ ጽንሰ ሃሳቦች አጥና)

በዜና አራምባና ቆቦ፦ ጽንስ አስወራጁ አዋላጅ ኾኖ ቀርቦ ቃላትን አሳምሮ መርዝን በትውልዱ ውስጥ መርጨት የዚህ ዘመን ትልቁ የልቦና ውጊያ ኾኗል። ዛሬ በመረጃ ዉካታ በዘመናዊነት ስብከት ውስጥ ትናንት
+1
በዜና አራምባና ቆቦ፦ ጽንስ አስወራጁ አዋላጅ ኾኖ ቀርቦ ቃላትን አሳምሮ መርዝን በትውልዱ ውስጥ መርጨት የዚህ ዘመን ትልቁ የልቦና ውጊያ ኾኗል። ዛሬ በመረጃ ዉካታ በዘመናዊነት ስብከት ውስጥ ትናንት የትውልድ መቋረጥን ዓላማው አድርጎ የተነሳው ፅንስ አስወራጅ፣ ዛሬ የነፃነትና የእናቶች ጤና ጠባቂ «አዋላጅ» መስሎ በአደባባይ ቆሟል! . . .. ይህንን ነገ አቀርብላችኋለሁ ነገር ግን በገጼ ውስጥ የምታገኟቸው ጥናቶች የአንድ የራሴ ጥረቶች ናቸውና። ለማወጣባቸው የኢንተርኔትና ሌሎችም ተያያዥ ወጪዎች እገዛችሁ ትውልድን ለማትረፍ ለምናነቃቸውና ለምናሠለጥናቸው አባወራዎች ትልቅ ግብዓት ይኾነኛል። በቴሌ ብር ለምታደርጉት የትኛውንም መጠን እገዛ አመሰግናለሁ!

ጾታዊ ምንፍቅና በጁንግያን ፍልስፍና፡-የጆርዳን ፒተርሰንም ትንተና ====================================== የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ማንነትን በሥነ-ልቦና ሳይንስ ውዥንብር ለመሸርሸ
+1
ጾታዊ ምንፍቅና በጁንግያን ፍልስፍና፡-የጆርዳን ፒተርሰንም ትንተና ====================================== የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ማንነትን በሥነ-ልቦና ሳይንስ ውዥንብር ለመሸርሸር የሚደረገው ስልታዊ ሙከራ፣ የቤተሰብን መዋቅር እና የአባወራውን መሪነት በመናድ ትውልድን ወደ ጥፋቱ እየገፋው ይገኛል። በጁንግያን ፍልስፍና፥ በጆርዳን ፒተርሰን የሚሰበከው "የውስጥ ሚዛን" ትምህርት፣ በተግባር ጾታዊ ምንፍቅና ነው! https://open.substack.com/pub/abawera/p/4d9?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true

እንዳያይል እንዳይበዛ፣ እየተሰለበ ሄደ ዳግም እንዳይነሳ ================================= ወንዱ ሲነቃ፣ ቤተክርስቲያንም ማኅበረሰብም ይታነጻሉ፤ ቤተሰብ ይጸናልና ሀገርም ትገነባለ
እንዳያይል እንዳይበዛ፣ እየተሰለበ ሄደ ዳግም እንዳይነሳ ================================= ወንዱ ሲነቃ፣ ቤተክርስቲያንም ማኅበረሰብም ይታነጻሉ፤ ቤተሰብ ይጸናልና ሀገርም ትገነባለች፣ ትጠበቃለች። ጠላትና ሆዳደሩ ምሁር ይህንን ያውቃልና ወንዱን እንከፍ ምስኪን የሚኾንበትን ዘርፈ ብዙ መንገድ ይዘረጋለታል። በዚያም ማየልና መብዛቱ ቀርቶ ቀና የሚልበት ወኔው ይኮላሻል! 👇👇👇 https://open.substack.com/pub/abawera/p/7f3?r=5gza3&utm_campaign=post&utm_medium=web&showWelcomeOnShare=true