የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
تُعد قناة የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 386 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 113 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 343 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 386 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 25 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 531، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 20، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 28.42%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً N/A% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 085 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 0 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 26 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
14 386
المشتركون
+2024 ساعات
+1147 أيام
+53130 أيام
أرشيف المشاركات
መጻጉዕ
"ጌታ ኢየሱስም ተነሣና ተሸክመህ ሂድ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸከሞ ሄደ።" ዮሐ 5:8-9
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
የበረከት ጾም ይሁንልን። መልካም ዕለተ ሰንበት! ሰናይ ሌሊት!
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
ምኲራብ
"እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።" ነህ 10፡39
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት!
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
ምኲራብ
"ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።" 1ጢሞ 3፡15
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት!
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
ምኲራብ
"ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና።" ኢሳ 56፡7
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት!
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
ምኲራብ
"አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ። አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።" 2ዜና 7፡14 - 15
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት! የበረከት ጾም ይሁንልን!
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
ምኲራብ
"ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች!" ማቴ 21፡13
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት! መልካም ዕለተ ሰንበት! የበረከት ጾም ይሁንልን!
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ያስተማራቸውን ተተኪ መምህራን አስመረቀ።
መጋቢት 16/07/2016 ዓ.ም (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ያስተማራቸውን ተተኪ መምህራን ባሳለፍነው ሳምንት ዕለተ ቅዳሜ 14/07/2016 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መሰብሰቢያ አዳራሽ አስመርቋል። በምረቃው መርሐ ግብር ተተኪ መምህራኑን ለአንድ ወር ያህል በአዳር መርሐ ግብር ሲያስተምራቸው እንደቆየ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩም የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነ ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማዕከል ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ተጠሪ ዲ/ን እሸቱ "ቤተ ክርስቲያናችን ከሚያስፈልጋት አገልግሎት አንዱ ሐዋርያዊ አገልግሎት ነውና ሐዋርያዊ ተልዕኮአችሁን ለመፈፀም ያብቃቹ" በማለት ለተመራቂዎቹ የምስጋና እና አደራ መልዕክት አስተላልፈዋልቃለ ፤ ቃለ እግዚአብሔርን ገላ 2:19 "ቀኝ እጃቸውን ሰጡን" በሚል ሐዋርያዊ ቃል መነሻ አድርገው ዲ/ን እዮአብ ግዛው አካፍለዋል፤ የበገና ዝማሬም ቀርቧል። በመጨረሻም ለተተኪ መምህራኑ የማኅተብ ስጦታ ተሰጥቶቸው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
@eotc-gssu
👉 Facebook
@EOTC.GSSU
👉 Telegram
@SSUGlobal
👉 Tiktok
@eotc_gssu
በመቀጠልም በሥርዓተ ትምህርቱ አተገባበር ዙርያ ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በሥልጠናው የማጠቃለያ ጉባኤውን በመታደም መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ መጋቤ ጥበብ ቀሲስ ወርቁ ተክሌ "የተናጠል ጉዞ የብቻ ሩጫ ዋጋ ቢያስከፍለንም ዛሬን በአንድነት ከሠራን የቤተክርስቲያንን ልዕልና ማስጠበቅ ይቻለናል። ለዚህም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ሰፊ ድርሻ አላቸውና አንድነታችንን አናጠናክር !" ሲሉ በተያያዘም "ሀገረ ስብከቱ በብዙ ፈተና ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም ማደራጃ መምሪያው ልዩ ትኩረት በማድረግ ለአንድነቱ መጠናከር ፣ ለሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራና ለመጽሐፍ ዝግጅቱ በበጀትና በተያያዥ ጉዳዮች ድጋፋችሁ እንዳይለይ" ብለዋል።
ስለ ሥልጠናው አሰጣጥና ዓላማ ሀሳባቸውን የሰጡት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የትምህርት ክፍል ሓላፊ መጋቢ ሃይማኖት ቀሲስ ይታገሱ ደሴ "ይህን መሰል ሥልጠናዎች መዘጋጀቱ ሀገረ ስብከቶች የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መዋቅርን በማጠናከርና ሥርዓተ ትምህርቱን በመተግበር የጠነከሩ እንዲሆኑ ማስቻል ነው" በማለት ከመምሪያው አስፈላጊውን እገዛ እናደርጋለን ሲሉ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።
በመጨረሻም ሰልጣኞች ባገኙት ግንዛቤ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን እንዲሁም ለአንድነቱ መጠናከርና ለሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ በየአጥቢያ በሚመለሱ ጊዜ በትኩረት የሚሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
@eotc-gssu
👉 Facebook
@EOTC.GSSU
👉 Telegram
@SSUGlobal
👉 Tiktok
@eotc_gssu
"የተናጥል ጉዞ ፣ የብቻ ሩጫ ዋጋ ቢያስከፍለንም ዛሬን በአንድነት ከሠራን የቤተክርስቲያንን ልዕልና ማስጠበቅ ይቻለናል።"
መጋቢት 16/07/2016 (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ክፍል አዘጋጅነት በመንበረ ጵጵስናው ስር ለሚገኙ ከ 8 ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራንና የሥራ አመራር አባላት በሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ ዙርያ የግንዛቤ መስጫ የሥልጠና መርሐ ግብር ተከናወነ።
ከመጋቢት 14-15 2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በቆየው በዚህ ሥልጠና መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ክፍል ሐላፊ መጋቤ ሃይማንት ቀሲስ ወርቅ አፈራው ስዩም "ምንም እንኳ ሀገረ ስብከቱ የሥርዓተ ትምህርቱን ትግበራ እስከዛሬ ያልጀመረ ቢሆንም ከዚህ በኋላ የወረዳውን አንድነት በማጠናከር ለመጀመር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና አስፈላጊ በመሆኑ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ መልካም ፈቃድና መመርያ ሰጭነት ከጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ጋር በመነጋገር ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል" ብለዋል።
በዚህ የሥልጠና መርሐ ግብር በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ምንነትና አስፈላጊነት ፣ የትግበራ አካሄድ ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መዋቅራዊ አካሄድ ፣ የትምህርት አሰጣጥና መሪነትን በተመለከተ ሰፊ ሥልጠናዎች በመንበረ ፖትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የትምህርት ክፍል ሓላፊ በሆኑት በመጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ይታገሱ ደሴና በሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የሥርዓተ ትምህርት የፕሮጀክት አስተባባሪ በሆኑት በዲ.ን ሚኪያስ ግዛቸው ተሰጥቷል።
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
