ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

الذهاب إلى القناة على Telegram

Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

إظهار المزيد
9 923
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+387 أيام
+13730 أيام
أرشيف المشاركات
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች 19ኛውን የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ EED (ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም) "ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታች" በሚል መሪ
+9
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች 19ኛውን የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ EED (ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም) "ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታች" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን 19ኛውን የሠንደቅ ዓላማ ቀንን የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች አክብረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ ቀኑን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ሰንደቅ ዓላማችን የህዝቦች ነፃነት፣ የሉዓላዊነት፣ የታሪካዊ ገድልና የጋራ ማንነት ሕያው ምልክት ነው ብለዋል፡፡ ጀግኞች አባቶችና እናቶች በከፈሉት መስዋትነት ሀገራችን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ እንድትቆይና ሰንደቅ ዓላማዋ ከፍ ብሉ እንዲውለበለብ መደረጉን አስገንዝበዋል፡፡ የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር የወደፊት ብልጽግናችንን በጽኑ መሰረት ላይ ለመትከል ብሔራዊ መግባባትን ለማጠናከርና የጋራ ሀገራችንን በሰላምና በልማት ከፍ ለማድረግ ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል፡፡ በተለይም እንደ ተቋም በኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፉ ላይ የሚሰራውን ስራ ከፍ በማድረግ የዘርፉን የኢኮኖሚ ድርሻ ማሳደግ እንዲቻል ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት!›› ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‎ ‎“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” ‎ ‎ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው። ሠንደቅ ዓላማችንም የጋራ ታሪካችንን፣ ሉዓላዊነታችንና በልዩነቶቻችን መካከል በጋራ የመቆም አቅማችንን የሚያስታውስ የብሔራዊ አንድነታችን ምልክት ነው። ‎ ‎በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆማቸው፣ በታላቅ ገድላቸው የዓለምን ትኩረት መሳብ ችለዋል። አባቶቻችን በፈተናዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ይህ በጋራ የመቆም ጥሪ መቼም ቢሆን ተቋርጦ አያውቅም፤ እያንዳንዱም ትውልድ ለዚህ ጥሪ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። ‎ ‎መደመር ሁላችንንም አንድ ቀላል ጥያቄ ይጠይቀናል፤ እኛ የሀገራችንን እጣ ፈንታ ከዳር ቆመን የምንታዘብ ተመልካቾች ነን? ወይንስ “ይህች ሀገሬ ናት፤ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም ያሳስበኛል” ማለት የምንችል ባለቤቶች? ‎ ‎ቋንቋዎቻችን፣ ሃይማኖቶቻችን እና ማንነቶቻችን ለዘመናት በጋራ በምናልፍበት ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ አብረው ተሰናስለው የተሸመኑ የአንድ ሸማ ክሮች ናቸው። ለሀገር መቆም ከትንንሽ የድፍረት እርምጃዎች ይጀምራል፤ ከራስ አልፎ ሰፊ ርዕይ ይዞ መሥራትንም ይጠይቃል። ያለፉት ትውልዶች ሀገሪቱን እንድንረከብ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ዛሬ በጋራ የምናጸናትን ሀገር ነው ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው። ‎ ‎ስለሆነም ዛሬ ራስዎን ይጠይቁ፤ ለሀገርዎ አንድነትና ብልጽግና ምን አበረክታለሁ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የተቋማት አመራሮች ሾመዋል፦ #PMOEthiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የተቋማት አመራሮች ሾመዋል፦ #PMOEthiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦ #PMOEthiopia #የመደመርመንግሥት
+2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦ #PMOEthiopia #የመደመርመንግሥት

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአመራር ስራ ርክክብ ተካሄደ ፡፡ ========================== EED መስከረም 29/2019 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቀድሞ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና
+3
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአመራር ስራ ርክክብ ተካሄደ ፡፡ ========================== EED መስከረም 29/2019 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቀድሞ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና አዲሱ ሚኒስትር ዶ/ር ፍሰሐ ይታገሱ የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል። በስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቀድሞው ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ ተቋሙን በበላይነት በመሩባቸው ያለፉት ዓመታት ከፈታኝ ወቅቶች ጋር ተጋፍጠው በቡድን ጥንካሬ የተሻሉ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። አዲሱ ሚኒስትር ዶ/ር ፍሰሐ ይታገሱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽንን ሲመሩና በኢንዱስትሪ ካውንስል ውስጥ ሲሰሩ የቆዩ፣ ዘርፉን በቅርበት የሚያውቁ እና ለቦታው ብቁ አመራር መሆናቸውን በመግለጽ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተውላቸዋል። አክለውም በቀጣይም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ስትራቴጂዎችን፣ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄን እና ሌሎች የተመረጡ ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። አዲሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በበኩላቸው ዶ/ር ፍሰሐ ይታገሱ፣ ከአቶ መላኩ ጋር ላለፉት ዓመታት በታላቅ ወንድምነትና በአማካሪነት አብረው ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል። የተጀመሩ አገራዊ እና ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን በዱላ ቅብብል መርህ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ተደጋግፈውና ተባብረው ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም ሁለቱም አመራሮች የስራ ርክክብ ሰነድ አካሂደዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት!›› ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

ኢትዮጵያን የሚመስል ስብጥር ያለውና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ያቀፈ የመደመር መንግሥት ካቢኔ 1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒ
ኢትዮጵያን የሚመስል ስብጥር ያለውና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ያቀፈ የመደመር መንግሥት ካቢኔ 1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 3. አቶ አዲሱ አረጋ፦ የግብርና ሚኒስትር 4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፦ የገንዘብ ሚኒስትር 5. መሐመድ እድሪስ ፦ የመከላከያ ሚኒስትር 6. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፦ የትምህርት ሚኒስትር 7. ሀና አርያስላሴ ፦ የፍትህ ሚኒስትር 8. ያስሚን ወሃብረቢ፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር 9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፦ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር 10. ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፦ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር 11. ዶክተር መቅደስ ዳባ፦ የጤና ሚኒስትር 12. አቶ አወሉ አብዲ፦ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር 13. ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ፦ የገቢዎች ሚኒስትር 14. አቶ በረከት ፍሰሃጽዮን፦ የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር 15. ሰላማዊት ካሳ፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር 16. ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ፦ የማዕድን ሚኒስትር 17. አቶ ሳዳት ነሻ፦ የሎጅስቲክስ ሚኒስትር 18. ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ፦ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር 19. አቶ ሙሳ አደም፦ የሰላም ሚኒስትር 20. ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 21. ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን፦ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር 22. ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር)፦ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር 23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር)፦ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር

እንኳን ለ7ኛው ሀገራዊ አዲስ የመንግሥት ምሥረታ በሰላም አደረሳችሁ! የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሕዝብን ድምፅ በማግኘት በስኬት ከተካሄደው አዲስ የመንግሥት ምሥረታ ጋር ተያይዞ ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላልፋል! ተቋማችን አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በበቂ የፋይናንስ፣ የማምረቻ ማዕከላት፣ የግብዓት፣ የቴክኖሎጂ፣ የክህሎትና የገበያ ትስስር አቅማቸው ጎልብቶ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገሩ፣ ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና የተኪና የወጪ ምርት አቅማቸውን እንዲገነቡ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፤ በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርምን መነሻ በማድረግ ዘርፉን ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። በተለይም የዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጠውን የአምራች ኢንዱስትሪ አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን በስኬት አጠናቀን ወደ ትግበራ ምዕራፍ ተሸጋግረናል። በተጨማሪም የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሼቲቭን ወደ ትግበራ በማስገባት የአካባቢን ፀጋ ወደ ምርት የመቀየርና ሰፊ የሥራ ዕድል የመፍጠር ሥራ የተሠራ ሲሆን፣ በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄም አምራቾቻችን ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና ሰፊ የገበያ ዕድል የሚያገኙበት መድረክ ተፈጥሯል። በአዲሱ የመንግሥት ምሥረታና በያዝነው አዲስ የበጀት ዓመትም የተጀመረውን የሪፎርም ትግበራ አጠናክረን በመቀጠል፣ የኢንተርፕራይዞቻችንን የምርት ጥራትና ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ሁለንተናዊ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እንሰራለን። የሀገራችንን የኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመቀነስና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የሚደረገውን የሀገር ውስጥ ምርት የመተካትና የወጪ ምርት ድጋፍም አጠናክረን እንቀጥላለን። ለእቅዶቻችን ስኬትና ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ እድገት ለምትተጉ የተቋማችን ሠራተኞችና አመራሮች፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ከጎናችን ለሆናችሁ ባለድርሻ አካላትና የልማት አጋሮቻችን በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ በአዲሱ የመንግሥት ምሥረታ የተጣለብንን ሀገራዊ ኃላፊነት በሙሉ አቅማችን በመወጣት የሀገራችንን የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለማጠናከር ያለንን ዝግጁነት እናረጋግጣለን። ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት!›› የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት

https://www.youtube.com/watch?v=1DBnJENB1Lo #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

የኢንዱስትሪ ማኔጅመንት ========//////======== የኢንዱስትሪ ማኔጅመንት ማለት የሰው ሀይልን፣ ማሽነሪዎችን፣ ቁሳቁሶችን፣ ገንዘብን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እርስ በርስ በማቀናጀት ውጤታማ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና ትርፋማ የሆነ የምርት ወይም የአገልግሎት ሂደት መፍጠር የሚያስችል የትምህርት እና የስራ መስክ ነው። ይህን ዘርፍ ከባህላዊ አስተዳደር ለየት የሚያደርገው ሳይንሳዊ ዘዴዎችን፣ የሂደት ትንተናዎችን እና የሂሳብ ቀመሮችን በመጠቀም በምርት እና በአሰራር ሂደት ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ነው። ለዚህም ዘርፍ ውጤታማነት መሠረት የሆኑ አምስት ዐበይት ምሰሶዎች አሉ፦ የመጀመሪያው የምርት እና የኦፕሬሽን እቅድ ነው፤ ይኸውም ሀብቶች በምን መልኩ፣ በምን ያህል መጠን እና መቼ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለባቸው አስቀድሞ ማቀድን ያካትታል። ሁለተኛው የጥራት ቁጥጥር ምርቶች ወይም አገልግሎቶች የደንበኞችን ፍላጎትና አለም አቀፍ ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ማረጋገጥ እና ስህተቶችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ላይ ያተኩራል። ሦስተኛው የአቅርቦት ሰንሰለት ማኔጅመንት ሲሆን፣ ጥሬ እቃ ከየት እንደሚገዛ፣ እንዴት እንደሚጓጓዝ፣ በፋብሪካው ውስጥ እንዴት እንደሚሰራ እና የተጠናቀቀው ምርት ለደንበኛው እንዴት እንደሚደርስ ማስተባበርን ያቀላጥፋል። አራተኛው የ Ergonomics እና የስራ ቦታ ደህንነት ሰራተኞች በምቾት እና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሰሩ የስራ አካባቢውን በማስተካከል አካላዊ ድካምን እና ጉዳትን ይቀንሳል። አምስተኛው ደግሞ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሲሆን አዳዲስ ማሽኖችን መትከል፣ ፋብሪካዎችን ማስፋፋት ወይም አዳዲስ ምርቶችን ማስተዋወቅ የመሳሰሉ ስራዎችን በሰዓቱ፣ በበጀት እና በጥራት ማጠናቀቅን ያረጋግጣል። የኢንዱስትሪ ማኔጅመንት ዋና አላማና ግብ ወጪን መቀነስን፣ ጥራትን መጠበቅን እና ሰዓቱን አክብሮ ማድረስን የተሰኙ እጅግ ወሳኝ የሆኑ የንግድ እውነቶችን ማመጣጠን ነው። በአጠቃላይ «ጥሩ የኢንዱስትሪ ማኔጅመንት ማለት በትንሽ ግብአት ከፍተኛውን ጥራት ያለው ውጤት ማግኘት ማለት ነው።» ምንጭ: https://www.facebook.com/share/1HxNtgmRdu/ ​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል EED መስከረም 25/2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይካሄዳል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 4
+1
የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል EED መስከረም 25/2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይካሄዳል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተሳትፈው በስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል። ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ ነው በስኬት የተከናወነው። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን ይደነግጋል። የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረትም ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምስረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል። ​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

https://youtu.be/1bcA10rgHd0   #የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል 20) - #ቢ ኤም ኤፍ የባህል እና ዘመናዊ ልብስ ዲዛይን ማምረቻ (ማርስ ዲዛይን) ===========///////==============   በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ የሚገኘው ቢ ኤም ኤፍ የባህል እና ዘመናዊ ልብስ ዲዛይን ማምረቻ (ማርስ ዲዛይን) አምራች ኢንተርፕራይዝ በሀገር ባህልና ዘመናዊ አልባሳት ምርቱ በዘርፉ አዲስ ተስፋና አርአያነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡   ​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!   ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡   https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ደንብ መፅደቅ በአገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል! ========================== EED መስከረም 18/2019 ዓ.ም የፌዴራል ሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ ያጸደቀው የፌዴራል የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ደንብ በሀገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች የገበያ ተወዳዳሪነትና ዕድገት ላይ የተደቀኑ ዋና ዋና የታክስ ማነቆዎችን የሚቀርፍ ውሳኔ ነው። ቀደም ሲል አምራች ኢንተርፕራይዞች ለምርት ሂደት የሚጠቀሙባቸው የተወሰኑ ግብአቶችና አቅርቦቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የታክስ ጫና የምርት ወጪን በመጨመር ከሀገር ውስጥና ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ጋር በሚደረግ የገበያ ውድድር ላይ ተጽዕኖ ሲፈጥር የቆየ ሲሆን፣ አዲሱ ማሻሻያ ደንብ እነዚህን አቅርቦቶች ከታክስ ነፃ ማድረጉ የተሻለ የገበያ ዕድል ይፈጥራል። የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ማሻሻያ ደንብ የአገር ውስጥ አምራቾቻችን የነበረባቸውን የግብአት ታክስ ጫና በማቃለል በዝቅተኛ ወጪና በጥራት እንዲያመርቱ መንገድ ይከፍታል። ይህም 'ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት' የሚለውን አገራዊ የኢንዱስትሪ ንቅናቄ ግብ ለማሳካትና አምራች ዘርፉን የበለጠ ተወዳዳሪ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።" የማሻሻያ ደንቡ ዋና ዋና አዎንታዊ ፋይዳዎች፦ የምርት ወጪን መቀነስ፦ በኢንዱስትሪ ግብአቶች ላይ ተጥለው የነበሩ የታክስ ጫናዎች በመነሳታቸው ምክንያት የአገር ውስጥ አምራቾች የምርት ወጪያቸው ይቀንሳል። የገበያ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፦ ወጪ በመቀነሱ ምክንያት አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች የመተካት አቅማቸውን ያጎለብታሉ። የታክስ ስርዓት ግልጽነትና ፍትሃዊነት፦ የደንቡ መሻሻል ቀደም ሲል የተርን ኦቨር ታክስ (TOT) ሲከፍሉ የነበሩ አገልግሎት ሰጪዎች  የታክስ ድርብርብነትን (Tax Cascading) በማስቀረት ፍትሃዊ የንግድ ውድድር እንዲኖር ያስችላል። የሸማቾችን የመግዛት አቅም መጠበቅ፦ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እና የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ለማጠናከር ያግዛል። #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነት ላይ ጫናን ያሳደረ የታክስ ደንብ ተሻሻለ =============//////================= EED መስከረም 18/2019 ዓ.ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት
+1
በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነት ላይ ጫናን ያሳደረ የታክስ ደንብ ተሻሻለ =============//////================= EED መስከረም 18/2019 ዓ.ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያ ደንብ ላይ ተወያይቷል፡፡ ቀደም ሲል የሙያ አገልግሎት እና ሌሎች አቅርቦቶችን እየሰጡ የተርን ኦቨር ታክስ ይሰበስቡ የነበሩ ግብር ከፋዮች የተርን ኦቨር ታክስ የተሻረ በመሆኑ እነዚህ ግብር ከፋዮች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝግበው ታክሱን እንዲሰበስቡ ለማድረግ፣ በአንዳንድ አቅርቦቶች ላይ የተጣለው ታክስ ለህብረተሰቡ በሚቀርቡ መሰረታዊ አቅርቦቶች እና በአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነት ላይ ጫናን ያሳደረ በመሆኑ አቅርቦቶቹን ከታክሱ ነፃ ለማድረግ እንዲያስችል ማሻሻያ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ ምክር ቤቱ በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይም ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

https://www.youtube.com/watch?v=uN1ykTtii_E #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት! ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡ https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment