ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

FMC Sport ፋና ስፖርት

FMC Sport ፋና ስፖርት

الذهاب إلى القناة على Telegram

This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel. @Fanatelevision @afanoromofana @tigrignafana For more updates please visit https://fanamc.com/amharic/

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام FMC Sport ፋና ስፖርት

تُعد قناة FMC Sport ፋና ስፖርት (@fmcsport) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 36 606 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 872 في فئة الرياضة والمرتبة 1 000 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 36 606 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 18 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 18، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -7، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: موثّقة (مؤكدة رسمياً من تيليجرام)
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 11.44‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 4.48‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 187 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 640 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 3.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel. @Fanatelevision @afanoromofana @tigrignafana For more updates please visit https://fanamc.com/amharic/”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 19 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الرياضة.

36 606
المشتركون
-724 ساعات
-937 أيام
+1830 أيام
أرشيف المشاركات
አንቷን ሴሜንዮ ለ8 ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቼስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች አንቷን ሴሜንዮ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አረጋግጧል፡
አንቷን ሴሜንዮ ለ8 ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቼስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች አንቷን ሴሜንዮ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አረጋግጧል፡፡ ተጨዋቹ ጉዳት ያጋጠመው በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ኢፕስዊች ታውንን 3 ለ 2 ባሸነፈበት ጨዋታ መሆኑ ተገልጿል። በዚህም ሴሜንዮ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለስምንት ሳምንታት ከሜዳ የሚርቅ ይሆናል፡፡

የካፍ ባለሙያዎች ቡድን በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉብኝት አደረገ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር (ካፍ) ባለሙያዎች ቡድን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ
+3
የካፍ ባለሙያዎች ቡድን በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉብኝት አደረገ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር (ካፍ) ባለሙያዎች ቡድን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉብኝት አድርጓል፡፡ ስታዲየሙ ውድድሩን ለማስተናገድ ከተመረጡት እጩ ስታዲየሞች አንዷ ሲሆን፤ ቡድኑ ከስታዲየሙ በተጨማሪ ከተማዋ ያላትን አጠቃላይ የማስተናገድ አቅም እንደሚገመግም ተመላክቷል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ዳዊት ሀዬሶ (ዶ/ር)፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሲቲ ያለመሸነፍ ጉዞ ኤክስትራ ታይም ስፖርት በፋና ፖድካስት ከደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን #ስፖርት_ፖድካስት #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanapodcast #fana
የሲቲ ያለመሸነፍ ጉዞ ኤክስትራ ታይም ስፖርት በፋና ፖድካስት ከደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን #ስፖርት_ፖድካስት #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanapodcast #fanadigitalmedia #fanamediacorporation #PoodkaastiiFaanaa #fanadigitalmedia فانا_عربي_بودكاست

አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔ
አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ያሬድ ቶሌራ እና መስዑድ መሐመድ ደግሞ በረዳት አሰልጣኝነት እንደሚሰሩ የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በ23 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር ህዳር ወር ላይ ሞሮኮን ይገጥማል።

አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔ
+2
አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ያሬድ ቶሌራ እና መስዑድ መሐመድ ደግሞ በረዳት አሰልጣኝነት እንደሚሰሩ የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በ23 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር ህዳር ወር ላይ ሞሮኮን ይገጥማል።

ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን 1 ለ 1
+2
ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ መድንን ግብ አልፍሬድ ኩሪንዚዛ አስቆጥሯል፡፡ የሀዋሳ ከተማን የአቻነት ግብ ደግሞ ጌታነህ ከበደ (በፍጹም ቅጣት ምት) ከመረብ አሳርፏል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ አደረገ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ኢፕ
+2
ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ አደረገ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ኢፕስዊች ታውንን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ (2) እና ፊል ፎደን አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ከተከታዩ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ አድርጓል፡፡ ማንቼስተር ሲቲ በሊጉ እስካሁን ያደረጋቸውን ሁሉንም 7 ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ሊቨርፑል ብሬንትፎርድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ቪክቶር ሙኖዝ እና አሌክሳንደር አይዛክ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ፉልሃም ሃል ሲቲን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል፡፡ አስቀድሞ በተደረገ የሊጉ ጨዋታ ቼልሲ ኤቨርተንን ፔድሮ ኔቶ ባስቆጠራቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡ የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ ይገናኛሉ፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 አሸንፏል
+3
ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች በፍቃዱ አለማየሁ እና ኦካይ ጁል አስቆጥረዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ አማኑኤል ኤርቦ ከመረብ አሳርፈፏል፡፡

ቼልሲ ኤቨርተንን አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ቀን 8 ሰዓት 30
+2
ቼልሲ ኤቨርተንን አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የቼልሲን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ፔድሮ ኔቶ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከኢፕስዊች ታውን፣ ብሬንትፎርድ ከሊቨርፑል እንዲሁም ፉልሃም ከሀል ሲቲ ይገናኛሉ፡፡ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ኒውካስል ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ የሚገናኙ ይሆናል፡፡

የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ባሕር ዳር ገባ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ባሕር ዳር ከተማ ገብቷል። የወ
+2
የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ባሕር ዳር ገባ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ባሕር ዳር ከተማ ገብቷል። የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ከቡድኑ ጋር ተገኝተዋል። ቡድኑ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ፤ በክልሉና በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በቆይታው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ዝግጅት ይገመግማል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና - ተጠባቂው ጨዋታ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
+3
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና - ተጠባቂው ጨዋታ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህም ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ይገናኛሉ፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ አቻ ተለያዩ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ ያለምን
+2
ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ አቻ ተለያዩ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ጨዋታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡ በሃላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ መደረግ የጀመረው የሀላባ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቅቋል፡፡ የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከሸገር ከተማ ይገናኛሉ፡፡

የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ የሚገመግመው የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በዛሬው ዕለት ጉብኝቱን ይጀምራል አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)የኢትዮጵያን የአፍሪካ
የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ የሚገመግመው የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በዛሬው ዕለት ጉብኝቱን ይጀምራል አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ የሚገመግመው የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በዛሬው ዕለት ጉብኝቱን ይጀምራል፡፡ በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት የአደይ አበባ እና አቃቂ ስታዲየሞችን እንደሚጎበኝ ተመላክቷል፡፡ በነገው ዕለት ደግሞ የባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን፣ እሁድ ድሬደዋ እና ሃዋሳ ስታዲየሞችን እንዲሁም ሰኞ የጅማ ስታዲየም የሚጎበኝ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ የሚገመግመው የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ከመንግሥት እንዲሁም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ጋር በትናንትናው ዕለት መወያየቱ ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄና ዝግጅት ለመገምገም የተሰየመው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ መግባቱ አይዘነጋም፡፡

ሲቲ ከሻምፒየንስ ሊግ ሽንፈት መልስ ኤክስትራ ታይም ስፖርት በፋና ፖድካስት ከደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን #ስፖርት_ፖድካስት #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanapodc
ሲቲ ከሻምፒየንስ ሊግ ሽንፈት መልስ ኤክስትራ ታይም ስፖርት በፋና ፖድካስት ከደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን #ስፖርት_ፖድካስት #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanapodcast #fanadigitalmedia #fanamediacorporation #PoodkaastiiFaanaa #fanadigitalmedia فانا_عربي_بودكاست

የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ የሚገመግም ቡድን አዲስ አበባ ገባ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄና ዝግጅ
+2
የኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ የሚገመግም ቡድን አዲስ አበባ ገባ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄና ዝግጅት ለመገምገም የተሰየመው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል። የቡድኑ አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) እንዲሁም የሚኒስቴሩና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገዋላቸዋል።

ፒኤስጂ ማንቼስተር ሲቲን አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር ፒኤስጂ ማንቼስተር ሲቲን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ምሽት
+4
ፒኤስጂ ማንቼስተር ሲቲን አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር ፒኤስጂ ማንቼስተር ሲቲን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ዱዌ፣ ዴምቤሌ፣ ቪቲንሀ እና አክሎቼ አስቆጥረዋል፡፡ ማንቼስተር ሲቲን ከሽንፈት ያልታደጉ ሁለት ግቦችን ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ ከመረብ አሳርፏል፡፡ በሌላ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ሮማን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ፣ ኢስፒ፣ ኤንድሪክ እና አርዳ ጉለር አስቆጥረዋል፡፡

ሊቨርፑል ላስክን 6 ለ 3 አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር ሊቨርፑል ላስክን 6 ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በጨዋታው ለ
+2
ሊቨርፑል ላስክን 6 ለ 3 አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር ሊቨርፑል ላስክን 6 ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በጨዋታው ለሊቨርፑል ብራድሊ ባርኮላ ሃትሪክ ሲሰራ ቀሪዎቹን ግቦች አራሆ፣ ፍሪምፖንግ እና ኩማስ አስቆጥረዋል፡፡ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታው ሲቀጥል ምሽት 4 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከፒኤስጂ እንዲሁም ሮማ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ቦዶ ግሊምት ከቦርሲያ ዶርትሙንድ፣ ሪያል ቤቲስ ከፖርቶ፣ አስቶንቪላ ከፌነርባቼ፣ ሻካታር ዶኔስክ ከአቴንስ እንዲሁም ስሎቫን ብራቲስላቫ ከስቱትጋርት ሌሎች ምሽት 4 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔ
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዩጋንዳ አቻው ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ግብ ዘሚካኤል ምንያህል ሲያስቆጥር፤ አርኖልድ ካዬምባ በ78ኛው ደቂቃ የዩጋንዳን የአቻነት ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከምድብ ሁለት 2ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

ማንቼስተር ሲቲ ከፒኤስጂ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት 9 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ማንቼ
ማንቼስተር ሲቲ ከፒኤስጂ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት 9 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ከፒኤስጂ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ እስካሁን ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ ድል ያደረገው ማንቼስተር ሲቲ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግም ያለመሸነፍ ጉዞውን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ ይገባል፡፡ ማንቼስተር ሲቲ በመጀመሪያ ዙር የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ፖርቹጋል አቅንቶ በሃንድ ሁለት ግቦችን ፖርቶን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ተጋጣሚው የወቅቱ የሻምፒየንስ ሊጉ አሸናፊ ፒኤስጂ በበኩሉ በመጀመሪያ ዙር የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ስሎቫን ብራቲስላቫን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡ ሁለቱ ቡድች እርስበርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ሦስቱን ሲያሸንፍ ፒኤስጂ በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡ https://web.facebook.com/share/p/1BdPw9KfiC/

አርሰናል ሲያሸንፍ፤ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ በአትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 0
+1
አርሰናል ሲያሸንፍ፤ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ በአትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ የስፔኑን ክለብ የማሸነፊያ ግቦች ባሪዮስ እና ሉክማን ሲያስቆጥሩ፤ ሌኒ ዮሮ ከማንቼስተር ዩናይትድ በኩል 74ኛው ደቂቃ ላይ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡ በሌላ የምሽቱ ጨዋታ አርሰናል የፈረንሳዩን ክለብ ሊል በኤሚሬትስ አስተናግዶ 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ መድፈኞቹ በመድረኩ ሁለተኛ ድላቸውን ሲያሳኩ፤ የማሸነፊያዎቹን ግቦች ቲምበር፣ ኤዜ እና ሳካ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡