ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

Dn Abel Kassahun Mekuria

Dn Abel Kassahun Mekuria

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው። ይወዳጁን ለፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL ለyoutube https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_ ለInstagram https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Dn Abel Kassahun Mekuria

تُعد قناة Dn Abel Kassahun Mekuria (@dnabel) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 18 562 مشتركاً، محتلاً المرتبة 4 306 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 1 899 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 18 562 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 10 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 51، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 0، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 43.10‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 11.25‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 7 999 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 2 088 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 195.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው። ይወዳጁን ለፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL ለyoutube https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_ ለInstagram https://www.instagram.com/abelkassahunm?ig...”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 11 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

18 562
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
+5130 أيام

جاري تحميل البيانات...

سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
أكتوبر '26
أكتوبر '26
+26
في 1 قنوات
سبتمبر '26
+125
في 5 قنوات
Get PRO
أغسطس '26
+65
في 7 قنوات
Get PRO
يوليو '26
+91
في 8 قنوات
Get PRO
يونيو '26
+124
في 10 قنوات
Get PRO
مايو '26
+107
في 5 قنوات
Get PRO
أبريل '26
+360
في 12 قنوات
Get PRO
مارس '26
+727
في 12 قنوات
Get PRO
فبراير '26
+1 402
في 13 قنوات
Get PRO
يناير '26
+179
في 6 قنوات
Get PRO
ديسمبر '25
+247
في 9 قنوات
Get PRO
نوفمبر '25
+235
في 9 قنوات
Get PRO
أكتوبر '25
+332
في 9 قنوات
Get PRO
سبتمبر '25
+107
في 4 قنوات
Get PRO
أغسطس '25
+236
في 6 قنوات
Get PRO
يوليو '25
+88
في 7 قنوات
Get PRO
يونيو '25
+45
في 2 قنوات
Get PRO
مايو '25
+108
في 2 قنوات
Get PRO
أبريل '25
+576
في 12 قنوات
Get PRO
مارس '25
+1 014
في 6 قنوات
Get PRO
فبراير '25
+1 098
في 5 قنوات
Get PRO
يناير '25
+803
في 6 قنوات
Get PRO
ديسمبر '24
+308
في 6 قنوات
Get PRO
نوفمبر '24
+79
في 3 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+108
في 1 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+194
في 3 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+319
في 7 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+129
في 2 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+137
في 4 قنوات
Get PRO
مايو '24
+255
في 3 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+254
في 6 قنوات
Get PRO
مارس '24
+306
في 2 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+122
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '24
+169
في 3 قنوات
Get PRO
ديسمبر '23
+234
في 5 قنوات
Get PRO
نوفمبر '23
+216
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '23
+215
في 5 قنوات
Get PRO
سبتمبر '23
+158
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '23
+94
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '23
+212
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '23
+175
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '23
+477
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '23
+189
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '23
+260
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '23
+180
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '23
+248
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '22
+697
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '22
+469
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '22
+188
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '22
+199
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '22
+118
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '22
+306
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '22
+341
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '22
+256
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '22
+245
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '22
+422
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '22
+179
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '22
+315
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '21
+165
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '21
+206
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '21
+225
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '21
+375
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '21
+683
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '21
+373
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '21
+441
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '21
+284
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '21
+988
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '21
+81
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '21
+101
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '21
+96
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '20
+3 144
في 0 قنوات
التاريخ
نمو المشتركين
الإشارات
القنوات
09 أكتوبر0
08 أكتوبر+5
07 أكتوبر0
06 أكتوبر0
05 أكتوبر+8
04 أكتوبر+2
03 أكتوبر+3
02 أكتوبر+1
01 أكتوبر+7
منشورات القناة
“ከኃጥአን የኀዘንን ሸክም የሚያቀለው ደስታ ከአንቺ ተወለደ” “ዘያቀልል እምኃጥአን ፆረ ኀዘን እስመ እምኔኪ ፍስሐ ተወልደ” መልካም የማኅሌተ ጽጌ ቁመት!!!

2
እስኪ የርእሰ ማዕምራን መሪጌታ ብርሃኑ ውድነህን ውድ መዝሙር ልጋብዛችሁ። እጅግ በሚመስጥ ግጥም እና በሚያራራ ዜማ የተከሸነ ነው። ስሙት እና ውቀሱኝ! https://youtu.be/ufcU-6jLDxU?si=P881REKjOEGWM5ZP
2 430
3
እመቤታችን ታዛችን፣ መደገፊያ የሃይማኖት በትራችን ከመውደቅ ትሰውረን። ከወደቅንም ፈጥና ታንሣን፤ አትተወን!!!
እመቤታችን ታዛችን፣ መደገፊያ የሃይማኖት በትራችን ከመውደቅ ትሰውረን። ከወደቅንም ፈጥና ታንሣን፤ አትተወን!!!
2 730
4
እግዚአብሔር የሚፈራ ሰው ምን ያስፈራዋል?! አምላካችን “እግዚአብሔር ማን ነው?” ብለው የተገዳደሩት ትዕቢተኞቹ እነ ፈርዖንን ያስጨነቀው በምድር ላይ በጣም ትንሽ በሆኑ እና በሚናቁ እንደ ዝንብ እና እንቁራሪት ባሉ ነፍሳት ነው። በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ እነ ዳንኤል ግን ለተራቡ አናብስት ቢሰጡ፣ ሦስቱ ወጣቶች ደግሞ ወደሚንቀለቀል እሳት ቢጣሉም ልባቸው ለደቂቃ እንኳ አልደነገጠም። እግዚአብሔርን የሚደፋፈሩ ሰዎች በጥቂት ነገር ሲፈሩ ሲጨነቁ ይታያሉ። እርሱን የሚፈሩ ግን በምድር ሌላ ምንም የሚያስፈራቸው ነገር የለም። “አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም” መዝ 23:4 ዲያቆን አቤል ካሣሁን መስከረም 26 - 2019 ዓ. ም. (የትኛው ድርሳኑ ላይ እንዳነበብሁት አሁን ከተዘነጋኝ የሂፖው ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ የተገኘ ምክር)
3 891
5
+++ በዚህ ንጉሥ ታምናለህ? +++ በሐዲስ ኪዳን ከተጻፉ እና ስለ እምነት ሲነሣ በጣም ከሚያስደንቁኝ ታሪኮች መካከል አንዱ የሰብአ ሰገል ታሪክ ነው። ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው ወደ ቤተልሔም ዋሻ የመጡት ሰዎች የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት ነበሩ። የንግሥናን ምንነት እና ክብር ሲወራ ሰምተው ወይም ከመጻሕፍት አንብበው ሳይሆን በመሆን ያውቁታል። በብዙ ሠራዊት ታጅበው ከያሉበት የወጡትም “የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ” ፍለጋ ነበር። ይሁን እንጂ ንጉሡን ያገኙት ግን በጦር አለቆች ተከቦ፣ ባማረ እልፍኝ ውስጥ ቅንጡ አልጋ ላይ ተኝቶ፣ ውድ በሆነ የተልባ እግር ጨርቅ ተሸፍኖ አልነበረም። ምስኪኗ ድንግል ማርያም ታቅፋው፣ ደካማው ሽማግሌ ዮሴፍ ከፊቱ ቆሞ፣ እንስሳት ከበውት፣ ባረጀ ጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ነው ያዩት። ታዲያ ይህን በመመልከታቸው ንጉሥነቱን አልተጠራጠሩም። ለምን? ብለውም የምርምር ጥያቄም አላቀረቡም። በዝምታ ውስጥ ያለ ጠንካራ እምነታቸውን እንደ ያዙ ወድቀው ለጌትነቱ ሰገዱለት። እጅ መንሻም አቀረቡለት። ልዑሉን አምላክ በትሕትናው ወራት አለመጠራጠር እንዴት ያለ እምነት ነው? እነዚህ የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት ለእኔ ከጥበብ ሰውነታቸው በላይ የእምነት ሰውነታቸው ይበልጥብኛል። እነሆ እግዚአብሔር ስለ እኛ ድኅነት ሲል ራሱን ባዶ ያደረገ ሰው በመሆን አንድ ጊዜ ዝቅ ካደረገ በኋላ እንግዲህስ ሁለተኛ ተዋርዶ የለበትም። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔርን ልዕልና እና ትሕትና የምታየው በአንተ ሕይወት ውስጥ ነው። ከፍፍ ሲያደርግህ ልዕልናውን፣ በመናቅ እና በመረሳት ውስጥ እንድታልፍ ሲያደርግህ ደግሞ ትሑት አምላክ መሆኑን ትረዳለህ። ነገር ግን አንተ በየትኛው ሁኔታ ብታየው ነው ንጉሡን የምታምንበት? ሁልጊዜ ተአምር ሲያደርግ፣ ከእሳት ነጥቆ ሲያወጣህ እና በከፍታው ላይ ሲያቆምህ ብቻ ነው ወይስ በሕመም እና በደዌ፣ በብዙ ውርደት እና መናቅ፣ በበረት ውስጥ እንደ ማደር እና ብጫቂ እንደ መልበስ ባዶ ሲያደርግህም ጭምር እንደ ሰብአ ሰገል በዝምታ ውስጥ ታምነዋለህ? ወድቀህስ ትሰግድለታለህ? ዲያቆን አቤል ካሣሁን መስከረም 24 - 2019 ዓ. ም. ቻይና፣ ጓንዡ
6 152
6
لا يوجد نص...
4 513
7
"በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አሁንም ልጅሽን እለዋለሁ... ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ አቤቱ ሆይ፤ የውጭ ተክል አታድርገኝ... የመጻሕፍት መጀመሪያ የ
"በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አሁንም ልጅሽን እለዋለሁ... ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ አቤቱ ሆይ፤ የውጭ ተክል አታድርገኝ... የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፣ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በእናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፣ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ። ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል። የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው፤ ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከእኔም አርቀው" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የውጭው ተክል አርዮስን ለማውገዝ ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት ለተሰበሰቡበት "የብዙኃን ማርያም" በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን! ዲያቆን አቤል ካሳሁን https://t.me/Dnabel
7 270
8
እንግዳ_ዲያቆን_አቤል_ካሳሁን_ሰአዳ_ጌታቸው_1.mp3
6 529
9
የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ከፋና ብሮድ ካስቲንግ ሬድዮ ጋር ያደረግነውን አጭር ጭውውት ጋብዣለሁ!
6 694
10
“መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር ያድኃነነ እምጸር” - “መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው፤ ከጠላትም ያድነናል” ቅዱስ ያሬድ እንኳን አደረሳችሁ!
7 996
11
لا يوجد نص...
10 603
12
"አሁንም አሁንም ወደቅሁ ብሎ የሚያዝን (ተስፋ የሚቆርጥ) አይኑር። ንስሐ የሞተን (በኃጢአት) እንኳን ከመቃብር ታነሣለችና” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
10 081
13
“ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል” ዕን 3:19
10 186
14
የጌታውን እናት የሰላምታ ድምጽ ሰምቶ በማኅጸን በደስታ የዘለለውን (የሰገደውን) ጽንስ፣ በንጉሡ ፊት በክፉት የደነሰችው ልጅ አንገቱን አስቆረጠችው። ጽንሱ ስለ ሕይወት መምጣት በጠባቡ አዳራሽ በማኅጸ
የጌታውን እናት የሰላምታ ድምጽ ሰምቶ በማኅጸን በደስታ የዘለለውን (የሰገደውን) ጽንስ፣ በንጉሡ ፊት በክፉት የደነሰችው ልጅ አንገቱን አስቆረጠችው። ጽንሱ ስለ ሕይወት መምጣት በጠባቡ አዳራሽ በማኅጸን ሲያመሰግን፣ የሄሮድያዳ ልጅ ግን የነቢዩን ሕይወት ስለ ማስጠፋት በሰፊው የንጉሡ አዳራሽ ዘፈነች። አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ልጆች በሄሮድያዳ ምክር የማይሄዱበት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተማሩ ሆነው የሚያድጉበት በጎ ዘመን ያድርግልን!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን https://t.me/Dnabel https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
12 840
15
+++ የአዲስ ዓመት ስለት +++ በኖኅ ዘመን የነበሩት ሰዎች አመጸኞች ሆኑ። የእግዚአብሔርን የምሕረት ጥሪ እምቢ ብለው መንገዳቸውን በፊታቸው አበላሹ። ምድሪቱንም በግፋቸው ሞሏት። ስለዚህም እግዚአብሔር ከትውልዱ ጻድቅ የነበረው ኖኅና ቤተሰቡን አስቀርቶ ሌሎቹን ከምድር ጋር ያጠፋቸው ዘንድ የጥፋት ውኃን አዘነመ። የታላላቅ ቀላያት ምንጮች ሁሉ ተነደሉ። የሰማይ መስኮቶችም ከፈቱ። ምድር በአምላክ የቁጣ ውኃ ተጥለቀለቀች። በመርከቢቱ ከነበሩት በቀር ምድር አንዲት ነፍስ አልቀረላትም። እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ ቁጣ በኋላ በመርከቡ የነበሩትን ኖኅንና እንስሳት አራዊቱን አሰበ። በምድርም ላይ ነፋስን አሳለፈ። የቀላያቱን ምንጮች የሰማዩንም መስኮቶች ደፈነ። ዝናሙንም ከሰማይ ከለከለ። ሞልቶ የነበረውም ውኃ ቀስ በቀስ እየጎደለ መጣ። በመጽሐፈ ኩፋሌ እንደ ተቀመጠው በውኃ ተጥለቅልቃ የነበረችው ምድር ግልጥ ሆና የታየችው በመጀመሪያው ወር መባቻ ላይ ነበር።(ኩፋ 7፥1) ባለ ዘመኖቹ እኛ ልክ በኖኅ ጊዜ እንደ ነበሩት የቀድሞ ሰዎች ክፋታችን ተካክሏል። መንገዳችንን በእግዚአብሔር ፊት አበላሽተናል። ምድርን በግፋችን ሞልተናታል። ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ያወረደው የጥፋት ውኃ ለእኛም ይገባን ነበር። እኛ ግን እርሱ እስኪቀጣንም አልጠበቅንም። እርስ በእርሳችን እየተጋደልን ምድራችንን በጥፋት ደም አጥለቀለቅናት። ወንድም ወንድሙን በጥይት ነደለ፣ በስለትም ሰውነቱን ከፈተ። የቁጣው ደም ከሰው እየመነጨ ምድርን ሸፈነ። ታዲያ በዚህች ጎስቋላ ምድራችን ላይ የፈሰሰውን ደም የሚያደርቅ የይቅርታ ነፋስ መቼ ይነፍሳል? እንደ ውኃ ያጥለቀለቀንስ ደም መቼ ይጎድላል? የምንሰማው መጨካከንስ እያደር እያደር የሚቀለው መቼ ነው? አሁን እኮ የመጀመሪያው ወር (መስከረም) መባቻ ነው። ምድራችን የሸፈናት ጥላቻ እና መገዳደል ተገፍፎላት ዳግመኛ ግልጥ ሆና አናያትም? የእኔ የአዲሱ ዓመት ስለቴ ይህ ነው። የእናንተስ? ዲያቆን አቤል ካሳሁን ጷጉሜን 5፣ 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ
15 912
16
“እግዚአብሔርን በመውደድ፣ በመንፈሳዊ ንቃት እና በንስሐ ራስህን ካላዘጋጀህበት፤ በትንሣኤ እና ከሞት በኋላ ባለ ዘላለማዊ ሕይወት ማመንህ ምን ጥቅም አለው?” አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
8 434
17
ሰይጣን መንፈሳዊ ሕይወትን ለመኖር ወስነህ ስትጀምር በእነዚህ ሁለት ሐሳቦች ይዋጋሃል። 1. አንተ ለዚህ ሕይወት እንደማትሆን እና መቼም እንደማትለወጥ ሹክ ይልሃል። ይህን የሚያደርገው ተስፋ ቆርጠህ የያዝከውን ሩጫ እንድታቆም ነው። የሚገርመው ግን መለወጥ ባትጀምር ኖሮ ሰይጣን “አልተለወጥህም” አይልህም። 2. ገና ከመጀመርህ የደረስህ እና ለመፈጸም ጥቂት የቀረህ አስመስሎ ያሳይሃል። ብዙ ርቀህ እንደ ሄድህ አስበህ ልክ እንደ ጥንቸሏ ተዘናግተህ እንድትተኛ እና የጽድቅ ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው ትዕቢት እስረኛ እንድትሆን ያደርግሃል። አሁንም ሰይጣን “ደርሰሃል” እያለ ሲክብህ ገና እግርህን ለማንሣት የምትጣጣር እንደ ሆንህ አቅምህን በደንብ ያውቀዋል። ጀማሪ ስትሆን ሰይጣን “አትችልም” ብሎ ተስፋ በማስቆረጥ ወይም “ደርሰሃል” እያለ ያለ ልክ በማመስገን ወጥመዱ ውስጥ ሊጥልህ ይሞክራል። “በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና” 2ኛ ቆሮ 2:11 ዲያቆን አቤል ካሳሁን abelmekuria2@gmail.com
10 620
18
ዝምታ ራሳችንን የምናይበት ጥሩ መጽሔት(መስታወት) ነው። አብዛኛውን ሰዓት በወሬ ተጠምዶ የሚውል ሰው ራሱን የሚመለከትበት እድል አይኖረውም። በሌሎች ኃጢአት ሲፈርድ፣ ሲተችና ሲያማ ስለሚውል የራሱን ስህተትና ውድቀት ለማወቅ ይቸገራል። ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ሲያወራ የሚውል ሰው የሚያሳዝነው ዝም አለማለቱ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅም ነገር የማይናገር መሆኑም ጭምር ነው። ነገር ግን ማር ይስሐቅ እንደሚለው "አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ብዙ ማውራት ባቆመ ጊዜ ወደ ራሱ ይመለሳል። በእግዚአብሔርም ፊት ምግባሩን ማቅናት ይጀምራል" የሥጋ አንደበታችንን መቆጣጠርና ዝም ማስባል ስንችል የነፍስ ጆሮአችን ንቁህ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ነፍሳችን ሳይሰለች ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚያንኳኳውን የመልካሙን እረኛ ድምጽ ትሰማለች። ደጇንም ከፍታ ታስገባዋለች። ከእርሱም ጋር ለእራት ትሰየማለች።(ራእይ 3፥20) በእውነት ይህ እንደ ምን ያለ መታደል ነው? ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር "የዝምተኛ ሰው ጆሮ የእግዚአብሔርን ድንቆች ትሰማለች" ያለው ለዚህ ይሆን?! ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelzebahiran@gmail.com
9 311
19
https://youtu.be/ECS9qUjWWyk?si=sH1QwxBfi5Y-txEM
7 996
20
በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በግብጽ ስለ ተፈጸመ አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ። በላዕላይ ግብጽ ይኖር የነበረ አንድ ምስጉን ካህን በጊዜው የከተማው ከንቲባ ወደ ሆነው ባለሥልጣን ቢሮ ሄዶ ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ለከንቲባው ጥያቄ ያቀርብለታል። ይሁን እንጂ ከንቲባው ግን በንቀት ያን የእግዚአብሔር ካህን እያመናጨቀ በጥፊ መትቶ ከቢሮው ያስወጣዋል። በዚህ ድርጊት እጅግ ልቡ ያዘነውም ካህን እንባውን እያፈሰሰ ለአገልግሎት ወደሚጠበቅበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ የጸሎት ሥርዓቱን አስጀመረ። ካህኑ በቤተ ክርስቲያን ሆኖ ሲጸልይ ሳለ ያ ከንቲባ በመንገድ ሲሄድ ድንገት ዙሪያው ጨለመበት፣ በፈረስ የተቀመጠ አንድ ሰውም ከመንገዱ አስቁሞ "ለምን ካህኑን እንደዚያ አዋርደህ ሰደብህ?" ሲል ጠየቀው። ከንቲባውም ገና መልስ መስጠት ሳይጀምር ያ ፈረሰኛ ፊቱን በጥፊ ጸፋው። ከምቱ ጥንካሬም የተነሣ አንድ ዓይኑ ጠፋ። ይህ እንደ ሆነም ወዲያው ጨለማው ተገፈፈ። ያ ፈረሰኛ ማን ነው? ካህኑ ሄዶ እንባውን ካፈሰሰለት ከሰማዕቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጭ ማን ሊሆን ይችላል። ዲያቆን አቤል ካሳሁን abelmekuria2@gmail.com አዲስ አበባ
10 031